╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩ ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል። Contact. @atronosebot please dont touch the leave button.😔😳😳
💰💵 በቤቲንግ መበላት ሰልችቷችኋል❓
እንግዲያውስ ይሄን ቻናል ተቀላቅላችሁ ትርፋማ ሁኑ ✅ ማየት ማመን ነው 🏆
የማይታሰብ ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሁሉ አንዲት አንሶላ ወይም ሽርጥ ለብሶ በረንዳ ላይ ይተኛል፡፡ ደግነቱ ሌባ የሚባል ነገር አልፎ አልፎ ካልሆን በስተቀር እምብዛም አይሰማም፡፡ የተኛ ሰው መተናኮልም ስላልተለመደ ውጪ መተኛት የሚያስፈራ ነገር አይደለም፡፡ ቤቶቹ በፊልም ላይ ያየኋቸውን የድሮ የአረብ ከተማ ቤቶችን ይመስላሉ፡፡ ነዋሪዎቹ አፋሮች ሲሆኑ የሚወደዱ ደግ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ዛሬ ተጣልተው ነገ አፉ (ይቅር) ይባባላሉ፡፡ በአፋር ጊሌ (ጎራዴ መሰል መሳሪያ)
ወይም ጠመንጃ ይዞ መሄድ ባህል ነው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ዘመዱን የገደለበትን ለመበቀል አሊያም ለጦርነት ወቅት ካልሆነ በስተቀር አፋር እነዚህን መሳሪያዎች ለተራ ጠብ አይጠቀምባቸውም። እዛ በነበርኩበት ወቅት ከማስተማር በተጨማሪ ቀሪውን ጊዜዬን የእነሱን ባህል በማጥናት ላይ ማሳለፍን ተያያዝኩት፡፡ ስለ ባህላቸውና አኗኗራቸው እየፃፍኩ በብዕር ስሜ ለጋዜጦች አስተላልፋለሁ፡፡ በትርፍ ጊዜም ተማሪዎችን እየጠራሁ አስተምራለሁ፡፡ ከዚህ የተረፈች የማታ ጊዜ ከተገኘችም እጠጣባታለሁ፡፡ መሸታ ቤቶች ያሉበት አካባቢ ቀይ መብራት እየተባለ ይጠራል፡፡ እንደእኔ ከተማ ተወልዶ ላደገና ብዙ ቀይ መብራት ቤቶችን ላየ ሰው እነዚህን ቤቶች ቀይ መብራት ብሎ ለመጥራት ህሊናውን መፈታተኑ የማይቀር ነው፡፡ ሁሉም ቤቶች ማለት ይቻላል ግድግዳቸውና ጣሪያቸው ከአፈር ክዳን የተሰራ ነው፡፡ ጣሪያው ሙቀት እንዲያስቀር በማለት በትላልቅ ወራጅ ግንድ ከተረበረበ በኋላ ሳር ይለብሳል፡፡ በዚያ ሳር ላይ አፈር ይደረግበታል፡፡ ወጉ እንዳይቀር እንደነገሩ ቀያይ መብራቶች ስለሚደረጉበት ከሌላ አካባቢ ከሄዱ ከውብ ሴት አስተናጋጆች ጋር ተዳምሮ ቤቱ በግድ የመሸታ ቤት ይሆናል፡፡ ሞቅ ሲልና ከእነዛ የገንዘብና የፍቅር ቅልቅል ከሆኑ ሴቶች ጋር መጫወትና መዳራት ሲጀመር እውነተኛው የቀይ መብራት መሸታ ቤትም ይሆናል፡፡ እዚህ ያሉት ሴተኛ አዳሪዎች ከሌሎች ክልሎች የመጡ ሲሆን የሚገርመው ነገር ደግሞ መጀመሪያ ገንዘብ አይተው ይጠጉና ብዙም ሳይቆዩ ፍቅር የሚይዛቸው መሆኑ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ከአንዷ ጋር አንድ ሁለቴ ካደርክ በሶስተኛው ጊዜ ገንዘብ ባይኖርህም ተከትላህ ትመጣለች፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ስትል ቡና ቤት እንደምትስራ ትረሳውና ፍቅር ይዟት አንተን አንተን ስትከተልና የዋህነቷን ስታይ አንተም ቀስ በቀስ ፍቅር ይይዝህና አግብተሀት ታርፋለህ፡፡ ታዲያ በዚህ መልኩ ብዙ ተምሯል የተባለ ባለስልጣን በዚህ መልክ እያገባ እዛው ስለሚቀር "እነ አጅሪት እጣናቸውን እያጫጫሱ አንዱን ኮርማ ጠለፉት" እየተባለ ይወራል፡፡ ሴቶቹም ቢሆኑ እጣኑ ይህንን ያደርጋል ብለው ስለሚያስቡ ቀን ቀን በእረፍት ሰዓታቸው ጫት እየቃሙና እጣን እያጨሱ የሚወዱትን ሰው እንዲያመጡላቸው አባድርን ይለምናሉ፡፡ ታዲያ ከእኔ ጋር በእነዚህ ቤቶች ዘወትር እየተገኙ የሚያጣጡኝ መንግስት እርሻ ልማት ውስጥ የሚሰሩ ጓደኞችም አሉኝ፡፡ እነሱ እንደእኔ ተስፋ በመቁረጥ ሳይሆን ለመዝናናት ሲሉ ይጠጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ መዝናናታቸው ገደብ ስለሌለው እና ከዛሬ ውጪ ነገ የሚባል ጊዜ አለ ብለው ስለማያስቡ ከእኔ ምንም የሚለያቸው ነገር አልነበረም፡፡ ለእነሱ ቀንም ሕይወትም ማለት ዛሬ ናት፡፡ ነገ ወይም ተነገወዲያ የሚባል ቀንም እንዳለ ቢያውቁም ከዛሬ ምንም ልዩነት አለው ብለው ግን አያስቡም፡፡ ከእነሱ ውስጥ
ነገም ያው እንደዛሬ የደስታ ቀን እንጂ ከዛሬ የተለየ የችግር ቀን ይመጣል ብሎ የሚያስብ ስለሌለ ያገኘውን ዛሬውኑ በልቶና ጠጥቶ ማጥፋት እንጂ ለክፉ ቀን ማስቀመጥ የሚባል ነገር አይታወቅም፡፡ የሚኖሩበት ቤት የሚያምርና ሁሉም ነገር የተሟላለት በመሆኑ ምንም የሚያስጨንቃቸው ነገር የለም፡፡ ነገ ከዚህ ሲወጡ ቤት እንደሚያስፈልጋቸው የቤት እቃ ማሟላት እንዳለባቸው አንዳቸውም አስበውበት አያውቁም፡፡ ሁሉም እንደዝንጀሮዋ "ከእጀ በጉንጩ' ናቸው፡፡ እነዚህ ጓደኞቼ እንደእኔ በሴት ፍቅር የተጎዱ አይሁኑ እንጂ ከእኒ ምንም ልዩነት ስላልነበራቸው ብቸኝነት እንዳይሰማኝ ስላደረጉ ወድጃቸዋለሁ። ተሳክቶልኛል ባልልም ከእነሱ ጋር በመዋልና በዚህ መልኩ ጊዜዬን በማላለፈ አልማዝን ለመርሳት ሞከርኩ፡፡ ሳልወድ በግድ በፈጠርኩት የስራ ፍቅር የተነሳ ካሉት አስተማሪዎች ተመርጬ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቱ ዳይሬክተር ለመሆን ቻልኩ፡፡ ከሁለት ዓመት አገልግሎት በኋላ አዲስ መሥሪያ ቤት ተቀጥሬ አዲስ አበባ ገባሁ:: "८ ॥ ४३८" (Reach the Unreached) P९+१००३१८९ ९৯৮১ ድርጅት ውስጥ በእርሻ ኤክስፐርትነት ተቀጠርኩ፡፡ መ/ቤቱ ጥሩ ደሞዝ ቢከፈለኝም ከምግብና ከመጠጥ አልፎ የማስቀምጠው ምንም ገንዘብ አልነበረኝም፡፡ እዚህም ቢሆን ሳልጠጣ ገብቼ አላውቅም፡፡ ዝም ብሎ መኖር እንጂ ሕይወቴን ለማሻሻል በሚል የማቅደው አንድም ነገር አልነበረም:: ሌላው ቀርቶ አልማዝን ላለማየት የሚል የማይረባ ምክንያት ፈጥሬ ያቋረጥኩትን ትምህርት እንኳን አለማያ ሄጄ ለመቀጠል አልፈለኩም፡፡ በዚህ መልኩ በእኔና በአልማዝ መካከል የነበረው ግንኙነት ላይቀጥል ሆኖ ተበጠሰ። ያቺ ስለእኔ ያላትን ፍቅር ዲያሪዋ ላይ ስትዘረዝር እምባዬ እንዲፈስ ያደረገችው ሴት፣ በጥላቻ የደም እምባ እንዳለቅስ ማድረጓን ሳስብ ደግሞ በጥላቻ እንጂ በፍቅር እንዳላነሳት ጣርኩ፡፡ ግን የዚያን ከፍቅር ወደ ጥላቻ የተሸጋገረ ታሪክ እውነተኛ ገፅታ ማወቅ ነበረብኝና ዲያሪውን ማንበቤን ተያያዝኩት፡፡
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
ላልወለድሻት ልጅ የሚለውን ንግግር ስሰማ ግራ ተጋባሁ፡፡ በቅሎ ደግሞ እንደማትወልድ አውቃለሁ፡፡ ነገሩ ግራ ገባኝ፣ እናቴ እኔን ካልወለደችኝ እንዴት ልታገኘኝ ቻለች? ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ፡፡ ቀናትና ወራት አለፉ፡፡ ቀስ በቀስ ስለሁኔታው ለማወቅ መጣር ጀመርኩ፡፡ በአንድ አጋጣሚ አንድ ቀን ከአንድ የሰፈር ልጅ ጋር ተዋውቀን እንዳቅማችን ቀልዱንም ቁም ነገሩንም መጫወት ጀመርን፡፡ ከቀን ብዛት ያንን ለኔ ድብቅ የነበረውን፣ ነገር ግን አገር ያወቀውንና ፀሐይ የሞቀውን ሚስጢር ነገረኝ። ከዚያ በኋላ እነዚያ ወላጆቼ የሚመስሉኝ ሰዎች አሳዳጊዎቼ መሆናቸውን እንዳወቅሁ እያንዳንዷን ድርጊታቸውን መከታተል ጀመርኩ፡፡ እንደልጃቸው ስለሚያዩኝ ግን ከእነሱ በኩል ለእኔ የነበራቸውን ፍቅር ቀንሶ አያውቅም፡፡ እኔ ግን ከእነሱ ውጪ ወላጆች እንዳሉኝ በማወቄ እነዚያን የማላውቃቸውን ወላጆቼን የማግኘት ጉጉቴ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጣ፡፡ አሳዳጊዎቼ ወላጆቼ አለመሆናቸውን ልወቅ እንጂ ስለወላጆቼ ማንነት የሚያውቅ ሰው ግን አልነበረም፡፡ አሳዳጊዎቼ የማን ልጅ እንደሆንኩ ያውቁ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ቢኖረኝም ይህንን መጠየቅ ማለት ደግሞ የእነሱን ምስጢር ማወቅና ልጃቸው አለመሆኔን በግልጽ መረዳቴን የማርዳት ያህል በመሆኑ ሊደርስባቸው የሚችለውን ሐዘን በማሰብ መጠየቁን እተወዋለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ጊዜን ጊዜ እየተካው ቢሄድም ወላጆቼን የማወቅን ጉጉት የሚተካ ምንም ነገር ሊገኝ አልቻለም፡፡ ውስጤ የተደበቀውን ቤተሰቦቼን የማወቅ ምኞቴ እየደበዘዘ ከመሄድ ይልቅ ውስጥ ውስጤን _ እየሸረሸረኝ በሰውነቴ መክሳት፣ በትምህርቴ መድከምና በመሳሰሉት ይገለፅ ጀመር፡፡ ወላጆቼ በግልጽ ያልተረዱት ጭንቀት እንዳለብኝ ቢያውቁም የሚያስጨንቀኝን ነገር ለመረዳት ግን አልቻሉም፡፡ በተለይ እናቴ፤ "አልምዬ ምን ሆነሽብኛል? ሰውነትሽም እየከሳ ነው፣ ያምሻል እንዴ? ንገሪኝ እንጂ የእኔ ቆንጆ" እያለች ብትወተውተኝም መልሴ ግን "ምንም አልሆንኩም" የሚል ብቻ ነበር፡፡ እያደግሁ ስሄድ ግን ስሜቴንና ፍላጎቴን ደብቄ ላኖረው ከማልችልበት ደረጃ ላይ በመድረሴ አንድ ቀን ቤት ውስጥ ተስብስበን ቡና እየጠጣን ሳለ ፈራ ተባ እያልኩ፤ “አባዬ፣ እማዬ፣ አንድ ነገር ብጠይቃችሁ አትቀየሙኝም?" በማለት ያላሰቡትን ጥያቄ ጠየቅኋቸው፡፡ ሁለቱም የምጠይቃቸው ተራ ጥያቄ ይሆናል ብለው ስለገመቱ ሳይሆን አይቀርም፤ “እንዴ አልሚና፤ ለምን እንቀየምሻለን? የፈለግሽውንና ደስ ያለሸን ጠይቂን" አሉኝ፡፡ እኔ ግን እንደሚቀየሙኝ እርግጠኛ ስለነበርኩ እንደማይቀየሙኝ እንዲምሉልኝ ጠየቅኋቸው:: ገና ባላወቁት ነገር መማል አዳጋች ቢሆንባቸውም አንድ ተራ ጥፋት ያጠፋሁ አድርገው በማሰብ አሊያም
የፈለኩትን ባጠፋ እኔን የሚቀየም አንጀት እንደሌላቸው በመረዳት ሳይሆን አይቀርም ሁለቱም ማሉልኝ። እኔም ከማሉልኝማ በእርግጠኝነት አይቀየሙኝም ብዬ በመገመት በፍፁም ያልጠበቁትንና የማይገምቱትን ነበር ዘርግፌ አወጣሁት፡፡ "ወላጆቼ እነማን ናቸው?" አልኳቸው፡፡ ባልጠበቁት ሁኔታ ከፉኛ ደንግጠው እርስ በርስ ተያዩ፡፡ አሳዳጊዎቼ መልስ መስጠት ትተው እምባቸውን ማዝራት ተያያዙት፡፡ ፊታቸው በአንድ ጊዜ የሐዘን ማቅ ለበሰ። እኔም ባየሁት ነገር ደነገጥሁ፡፡ ይህንን በመጠየቄ እንደማሳዝናቸው ባውቅም እንዲህ ይሆናል ብዬ ግን አልገመትኩም ነበር፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል ትካዜና ፀጥታ ሰፈነ። ሁለቱም እምባ በሚያጎርፍ ዓይኖቻቸው ትኩር ብለው አዩኝ:: አስተያየታቸው ምን ጊዜም ቢሆን አይረሳኝም፡፡ እናቴ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች "አልምዬ የእኔ ቆንጆ! እረ ለመሆኑ ወላጆችሽ እንዳልሆንን የነገረሽ ማነው? ስትለኝ የሰማሁት ወሬ የተሳሳተ መስለኝና እንደዚያም እንዲሆንልኝ ፀለይኩ፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያስጨንቀኝን እንቆቅልሽ እስከመጨረሻው አፍኘ ማቆየት አለመቻሌን በመጥቀስ ይቅርታ እንዲያደርጉልኝ ነገር ግን ጥያቄዬን እንዲመልሱልኝ ለመንኳቸው፡፡ ግን ምን ያደርጋል! ምንም የማይፈይደው ጥያቄዬ የአሳዳጊዎችን ስሜት አቁስሎ ከማለፉ ውጪ ለእኔ ያስገኘው አንድም ፋይዳ አልነበረም.. እኔን እንደወላጅ ብቻ ሳይሆን እንደዓይናቸው ብሌን ሲጠብቁኝ የነበሩትን የአሳዳጊዎቼን ቅስም ሰብሬ የሐዘን ማቅ ከማልበስ ውጪ ለጥያቄዩ እንደጠበኩት የሚያረካ መልስ አላገኘሁም:: በመጨረሻም ወላጆችን እንደማያውቁና ተጥዬ አግኝተው እንዳሳደጉኝ ብቻ ነበር የነገሩኝ፡፡ የእናተ ንግግር ግን ሁሌም አይረሳኝም:: በአሳታወስኩት ቁጥርም የበደለኝነትና የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማኛል፡፡ እናቴም በደከመ ድምፅና ተስፋ በቆረጠ መንፈስ፣ "አልሙ የእኔ ቆንጆ! እኛ ልጅ ወልዶ ለማሳደግ ያልታደልን፤ ሕይወታችንና ፍቅራችን በአንቺ መገኘት የታደሰ፣ የምንጓጓለትን የወላጅነት ወግ ያጎናፀፍሽን ልጃችን ነሽ፡፡ ሁሉም ነገር ለክፋት የተደረገ አይደለምና አትቀየሚን፡፡ እርግጥ ወላጆችሽን አናውቃቸውም፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር የተደበቀው አንቺ ለእኛ፣ እኛ ለአንቺ ያለንን የወላጅነት ፍቅር እንዳያፋልሰው ነበር፡፡ ምን ያደርጋል ነገሩ ሁሉ የውሸት ካብ ነበርና ፈረሰ፡፡ ምስጢራችን ምስጢርነቱ ለእኛ እንጂ አገር ካወቀውና ፀሐይ ከሞቀው ቆይቷል ማለት ነው፡፡ የነበረንን ቤታችንን ሽጠን፣ ስፈር ቀይረን፣ ውሸቱን እውነት
ለማስመሰል ብንሞክርም ለዓመታት የገነባነው የውሸት ካብ የተገነባው በአሸዋ ላይ ስለነበር ከስሩ ተቦርቡሮ መፍረሱ አልቀረም፡፡ እኛ የአንቺ ወላጆች እንዳልሆንን ቀድሞውንም ቢሆን እናውቃለን፡፡ አንቺም ከእኛ የተወለድሽ የአብራካችን ክፋይ ልጃችን አለመሆንሽን እወቂው፡፡ ምን ይደረግ እንዲህ ያለ ምስጢር ተደብቆ አይቀር! አልሚ የእኔ ቆንጆ! የእኛን አባትነትና እናትነት፣ የአንቺን የእኛ ልጅ መሆን ግን የሚፍቅ አንዳችም ነገር ይኖራል ብለን አንገምትም፡፡ ይህንን ማድረግ የሚችል ሁኔታ ከተፈጠረ ግን የእኛም መኖር ከንቱ መሆኑን እወቂው" ያለችኝ ምንጊዜም አይረሳኝም ፡፡ ይህ ደግሞ ከማንም ሰው በላይ ለእኔ ያላቸው ፍቅር ከዋንኞቹ እናትና አባት ፍቅር በላይ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ በተለይ በእነርሱ በኩል የተስፋ መቁረጥ ዓይነት ስሜት ቢኖርም እነሱ ለእኔ እኔ ለእነሱ ያለን ፍቅር ግን አልተለወጠም፡፡ መልስ ማግኘቴ በአንድ በኩል እረፍት የሰጠኝ ቢሆንም በሌላ በኩል የሚያረካ መልስ ላላገኘሁበት ጥያቄ የወላጆቼን ቅስም መስበሬ ወላጆቼን ከማወቅ ፍላጎት ጋር ተደምሮ እንቅልፍ ነሣኝና ደስታዬንም አበነነው፡፡ ከዛ በኋላ ማንነቴን ባሰብኩ ቁጥር ትካዜ ላይ እወድቃለሁ፡፡ ያን ለት ከሁሉም በላይ የገረመኝ ነገር ቢኖር ግን እናቴ ይህንን ሁሉ ነገር ስትናገር አባቴ ዝም ብሎ ከማልቀስ ውጪ አንድም ቃል አለመተንፈሱ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ እያደር ለትምህርት ያለኝ ፍቅር ቀስ በቀስ በመጨመሩ ሁሉንም ነገር እያስረሳኝ መጣ :: አብዛኛውን ጊዜዬን በዚሁ ላይ ስለማሳልፍ የጭንቀቱ ጊዚያት ትውስታ ሙሉ በሙሉ በንኖ ባይጠፋም ቢያንስ መደብዘዝ ጀመረ፡፡ የተዳፈነው የወላጆቼን ማንነት የማወቅ ፍላጎቴ ከውስጤ ባይወጣም ወላጆቼ ልጃቸው አለመሆኔ እንዳይሰማቸው ለማድረግ ግን መጣር ጀመርኩ። አስራ ሁለተኛ ክፍል ስጨርስ በማትሪክ ጥሩ ውጤት በማምጣቴ ትምህርት ቤቱ ባዘጋጀው የሽልማት ስነ ሥርዓት ላይ ቤተሰቦቼ እንዲገኙ ተጋበዙ፡፡ በወቅቱ የነበረው የአባቴ ሁኔታ የሚረሳ አልነበረም፡፡ ተሸልሜ ስመጣ ከዓይኖቹ ላይ የሳቅና የደስታ ስሜት ሳይሆን እምባ ይፈሰው ስለነበር ደነገጥሁ፡፡ "ለምንድነው የምታለቅሰው? ዛሬ እኮ የምንደሰትበት እንጂ የምናዝንበት ቀን አይደለም" አልኩት፡፡
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
================
..ፎጣዋን አገልድማ ስትወጣ እሱ ደግሞ ለመግባት እርቃን ሰውነቱን በፓንት ብቻ ሆኖ ወደእሷ አቅጣጫ ሲመጣ አየችው…ዞር ብላ መንገዱን ለቀቀችለት …ቀጥታ ወደውስጥ ገባና የሻወሩን በራፍ ዘጋው…
ባለቤቷን እንዲህ እርቃኑን ስታየው ሁሌ እንደአዲስ እንደገረማት ነው፡፡ሰለብሪቲ አክተር ወይም ታዋቂ ሞዴል እኮ ነው የሚመስለው፡፡እዚህ አካባቢ እንደዚህ ቢሆን የሚባል ቅር የሚያሰኝ የአካል ክፍል የለውም‹‹ሆሆ..ለናሙና የተፈጠረ እኮ ነው የሚመስለው››አለችና ሰውነቷን አደራርቃ በምሽቱ ሶስቱን የእድሜ ልክ አድናቂዎቾና አፍቃሪዎቾ ወንዶችን ያስደምማል ያለችውን አለባበስ ለበሰች፡፡ፀጉሯን አስተካከለች፡፡የተወሰነ ሜካፕ ተጠቀመችና ሽቶ እላዮ ላይ ነስንሳ ወደሳሎን ወጣች፡፡
አለማየሁ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሙሉ ሱፍ ለብሶ ዝንጥ ብሎ ሳሎን ቁጭ ብሎ እስኪወጡ እየጠበቃቸው ነበር፡፡
እንዳየችው ‹‹እንዴ ኩማንደር….አምባሳደር መስለሀል፡፡›› አለችው፡፡
‹‹የወደፊት እጣ ፋንታዬ ምን አልባት አምባአሳደር ሊሆን ይችላል፡፡››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምነው አፍጥጠህ አየሀኝ…ልብሱ አልሄደብኝም እንዴ?››ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት፡፡
‹‹አረ የሚያስደነግጥ አለባበስ ነው … እንከን አይወጣለትም ..በጣም ያምራል፡፡››
‹‹ልብሱ ብቻ ነው ሚያምረው?››ስትል ልስልስ በሆነ ቅንዝራም ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹ስለአንቺ አላዛር ሲመጣ ይነግርሻል….ያንን አስተያየት የመስጠት መብት ለጊዜው የእሱ ነው፡፡››
ግንባሯን ቋጠረች‹‹ለጊዜው ስትል…?››
‹‹ይሄ ጥያቄ ይዝለለኝ፡፡››
‹‹በጣም ተቀይረሀል ..ድሮ እንደዚህ አልነበርክም››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ከእኔ ጋር ለምትነጋገረው ነገር ስትጠነቀቅ አይቼህ አላውቅም ..እንደመጣልህ በነፃነት ነበር የምናወራው፡፡ትዝ ይልሀል ..አንተ እኮ ጓደኛዬ ብቻ አልነበርክም….አንድ ቤት ውስጥ አብረኸኝ ያደክ ወንድሜ ነህ፡፡››
‹‹አዎ..በልጆቼን በሞት ሳጣና አያቴም በቃኝ ብላ ገዳም ጥላኝ ስትገባ ..አንተም ልጄ ነህ ..ከልጄ ጋር አሳድግሀለው ብላ የወሰደችኝ እናትሽ እቴቴ ነች፡፡በእውነት ለእሷ በሚገባው መጠን አልተንከባከብኳትም…፡፡››
‹‹ተው ተው..እቴቴንማ በጣም ነው የተንከባከብካት፡፡.በየጊዜው ብር እንደምትልክላት ማላውቅ ይመስልሀል፡፡እዚህ ከተቀየርክ በኃላ እንኳን እሷን ደጋግመህ አግኝተህ እኛን ግን ለማግኘት ፍቃደኛ አልነበርክም፡፡ካንተ ደግሞ ይልቅ ደግሞ የሚገርመኝ የእሷ ያንተ ተባባሪ ሆና መደበቅ፡፡ …እንደውም አንዳንዴ ከእቴቴ ጋር ስንጣላ እኮ…‹‹ከአንቺ ይልቅ የእኔን እናትነት የተረዳው አለማየሁ ነው…››እያለች ታበሳጨኛለች፡፡እና እሷ በአንተ ደስተኛ ነች…ትንሽ ቅር ሚላት በየጊዜው በአካል ሄደህ ስለማትጠይቃት ነው፡፡በዛ ከአንተ እኔ እሻላለሁ….፡፡››
‹‹ቢሆንልኝ…ለእሷ ምንም ነገር ባደርግ ይገባታል፡፡››
‹‹ለእኔስ…ለስድስት አመት የት እንዳለህ እንኳን ደውለህ አሳውቀሐኝ አታውቅም…አለማየሁ ደወሎ እንዲህ አለ…አለማየሁ ደውሎ በባንክ ይሄንን ላከ ሲባል እንጂ አንድ ቀን ሰሎሜ ሰላም ብሎሻል…?ሰሎሜ አለማየሁ ሰለአንቺ እንዲህ ያስባል ብሎ የነገረኝ ሰው የለም..ሁል ጊዜ አእመሮዬን እንደበላኝ ነው…‹‹ምን አድርጌዋለው…?መቼ ቀን ነው ያስከፋሁት …?.የቱ ጋር ነው የተቀየመኝ? ብዬ እንደተከዝኩ ነበር..እወነቱን ለመናገር በጣም ተቀይሜህ ነበር ..ባገኝህ እንደማላናግርህ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር..ግን በእንደዛ አይነት ሁኔታ ስንገናኝ…ምንም ማድረግ አልቻልኩም...ተቀይሜህ እንደነበረ ራሱ ከእስር ተፈትቼ ቤቴ ከገባው በኃላ ነው ያስታወስኩት፡፡››
‹‹ጥሩ ነው፣ ቂመኛ አይደለሽም ማለት ነው…አንቺን ያላገኘሁሽ ግን ላላገኝሽ ስላልፈለኩ ሳይሆን ተገድጄ ነው››
‹‹ተገድጄ ስትል?››
‹‹ማለቴ….››ንግግሩን እንዳንጠለጠለ አላዛር ከእነሱ በበለጠ.. ልክ እንደእለቱ ሙሽራ ዝንጥ ብሎ ወደእነሱ ሲመጣ ስለተመለከተ ለንግግር የተከፈተ አፉን መልሶ ዘጋ፡፡
‹‹በሉ…እንሂድና …ቀደም ብለን እዛው አካባቢ ደርሰን ብንጠብቀው ይሻለል፡፡››
አለማየሁ አላዛር መጥቶ ማውራት ከማይፈልገው ነገር ስለገላገለው በመደሰት ‹‹ጥሩ …እንሂድ››አለና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ርምጃውን ከአላዛር አስተካክሎ ወደውጭ መራመድ ጀመረ.፡፡ሰሎሜ ከኃላ ሁለቱንም በትኩረት እያየች ተከተለቻቸው፡፡ሁለቱም ፈርጣማና ወንዳወንድ የሚባሉ ናቸው፡፡ግን አላዛር ወደላይ የተሳበ መለሎ ነው፡፡
//
ከ30 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ የተጠበቀው ሁሴን ግዙፍ ሻንጣውን በጋሪ እየገፋ ከተርሚናሉ ሲወጣ ሶስቱም በእኩል አዩት…በደስታና በጩኸት እንዲያያቸው እጃቸውን አውለበለቡለት…ሁሴን ከዛሬ ስድስት አመት በፊት እደሚያውቁት አይነት ነው፡፡ እንዳዛው ውልምጭምጭ ቀጫጫ…ባለትልቅ ጭንቅላትና ሉጫ ፀጉር…የህፃን የመሰለ ፍልቅልቅ ፊት…ነጭ ከሩቅ አይን የሚስብ በረዶ መሳይ ጥርስ ……
ሶስቱም በየተራ እየተጠመጠሙበት ሰላምታ ከሰጡትና ይዘው የመጡትን የእንኳን በሰላም መጣህ ምኞታቸውን የሚገልፅ አበባ አስታቀፉት፡፡ከዛ በኃላ አለማየሁና አላዘር ሻንጣውን ተቀብለው ወደመኪናው ወሰዱና ከኋላ ጫኑለት፡፡…በአላዛር ሹፌርነት ሰሎሜ ገቢና ከእሱ ጎን ተቀምጣ አለማየሁና ሁሴን ከኋላ ሆነው ወደቤት ጉዞ ጀመሩ፡፡
ድንገት‹‹ይገርማል…?››አለ ሁሴን፡፡
አለማየሁ‹‹ምኑ ነው የገረመህ?ከተማዋ ልደቷን የምታከብር የቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ መሰለችህ አይደል…?››አለው፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹አሸብርቃና ተኳኩላ …በደማቅ መብራቷች ተንቆጥቁጣ ስታያት ገርሞህ እንደሆነ ብዬ ነዋ?››
‹‹..አዎ ያልከው ነገር በጣም አስገርሞኛል..ግን እኔ ለማውራት የፈለኩት ሶስታችሁን በአንድነት መጥታችሁ ትቀበሉኛላቹሁ የሚል ምንም አይነት ግምት ስላልነበረኝ በዛ መደነቄን ነው፡፡፡፡›
ልክ እንደሁሴን እሷም ሶስቱም የልጅነት እና የአፍላ ወጣትነት ጓደኞቾ እና አፍቃሪዎቾ ከበርካታ አመታት በኋላ እንዲህ አንድ ላይ ተሰብስበው አይናቸው እሷ ላይ ሲያቁለጨለጩ በመመለከቷ እየተገረመች‹‹ምን ማለት ነው? ሶስታችንም እኩል ጓደኞችህ አይደለንም እንዴ…?ለመሆኑ መጥቶ ይቀበለኛል ብለህ የገመትከው ማንን ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አሌክስን ነበር፡፡እናንተን በማግስቱ ባገኛችሁ ብዬ ነበር ያሰብኩት፡፡››
‹‹አንተ …ከእኛ ይልቅ አሌክስ ቁምነገረኛ የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው…?ነው ሰው ሀገር ከሄድክ በኃላ ፀባያችን ተምታታብህ››አለችው ሰሎሜ በመገረም፡፡
አለማየው በፈገግታ‹‹አንቺ …ሰው ሁሉ ስለእኔ ልክ እንደአንቺ የተሳሳተ ግምት ያለው ይመስልሻል እንዴ?››አላት፡፡
‹‹ተው ተው…ከመሀከላችንማ አንደኛው ቁምነገረኛና ኃላፊነትን የሚወስደው አላዛር ነው…አንተ እንደውም በዚህ ጉዳይ የመጨረሻው ሰው ነህ››አለው ሁሴን፡፡
‹‹አንተ ዲያስፖራ ለመሆኑ ዜግነትህን ቀይረሀል?››ሲል ጠየቀው፡፡
ያልጠበቀውን ጥያቄ ስለተጠየቀው ግራ ተጋባ‹‹አይ አልቀየርኩም…ግን ለምን ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ኢትዬጵያዊ ዲያስፖራ ከሆንክ የሚጮህልህ ኤምባሲ ስለሌለ ለዚህ ንግግርህ የሆነ ሰበብ ፈልጌ ከርቸሌ ልወረውርህ ነዋ….እንደድሮ አለማየሁ ብቻ አይደለሁም..ኩማንደር አለማየሁ ነኝ፡፡››
ሁሌ ቤቴንግ መበላት ከሰለቸህ ይሄን ቻናል ተቀላቀል ሁሌ ነው አሸናፊ እምትሆነው Ethiopia ውስጥ ይሄ ብቻ ነው እውነተኛ ቻናል ስለዚ ሳያመልጣህ አሁኑኑ ተቀላቀል
Читать полностью…ሁኔታ ተመልሶ እዚያ ግቢ ለመሄድ የሚያሳፍር በመሆኑ ምርጫዬ በደብዳቤ ብቻ መገናኘት ሆነ፡፡ የደብዳቤዎቹን መምጣት በናፍቆት የምጠብቅ መሆኑን የአሳኢይታው ፖስተኛ በደንብ ያውቃል፡፡ አልፎ አልፎ ከተማ ባገኘሁት ቁጥር ለወዳጅነት ያህል ቢራ ስለምጋብዘው ደብዳቤ ከመጣ ደውሎ ይነግረኛል፡፡ አንዳንዴ ከተማ ውስጥ ስንገናኝም እንዳልረሣኝ ለመግለፅ በሚመስል ሁኔታ "ደብዳቤ _ ስላልመጣ ነው ያልጠራሆት ይለኛል"፡፡ እንደነገረኝም ከሆነ ደብዳቤ በመቀበልና በመላክ በኩል በከተማው ውስጥ ተወዳዳሪ አልነበረኝም፡፡ ነገር ግን ሪከርዱን ይዤ መቆየት አልቻልኩም፡፡ ከእኔ የሚላከው ደብዳቤ ባይቀነስም የአልማዝ ደብዳቤዎች ግን ቀስ በቀስ እየቀነሱ መምጣት ጀመሩ፡፡ በሣምንት የሚደርሰኝ ደብዳቤ በየአሥራአምስት ቀን፣ ቀስ በቀስ ደግሞ በየወሩ እየሆነ መጣ፡፡ እየቆየም ሁለትና ሶስት ወራት እያሳለፈ መምጣት ጀመረ፡፡ ዘግይተው የሚመጡት ደብዳቤዎችም ከይቅርታ ይጀምሩና ጥናት እንደሚበዛባት፣ ደብዳቤዋም በዚህ ምክንያት መዘግየቱን አትተው ዶክተር አድማሱ እያደረገላት ያለውን ውለታ ጠቃቅሰው ይጠናቀቃሉ፡፡ ናፍቆትህ ሊገለኝ ነውና እወድሀለሁ የሚሉትም ቃላት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ ቀስ በቀስም ደብዛቸው እየጠፋ ሄደ፡፡ “ያንተው አፍቃሪ እህትህ" የሚለው ቃልም " እህትህ" በሚለው ነጠላ ቃል ተተካ፡፡
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
መስከረም 21 ቀን 1975 ዓ.ም "ጠዋት እንደተነሳን ተርሳችንን ለመብላት ተሰለፍን: ምግብ እኔ የጠበኩት በተለያዩት ጎድጓዳ ማቅረቢያው ጋ ስንደርስ ለእያንዳንዳችን የተለያዩ ጎድጎድ ያሉ ክፍተቶች ያሉት ሳህንና አንድ ኩባያ ተሰጠን። ቦታዎች ሁሉ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ተሞልተው እንደሚሰጡን ቢሆንም በሳህኑ ላይ አንድ ዳቦ ተደረገና በኩባያው ሻይ ብቻ ተቀዳልን:: እኔ የገበሬ ልጅ ስለሆንኩ እኛ ቤት ቁርስ የሚበላው ፍርፍር፣ እንቁላል በእንጀራ አሊያም እንጀራ በሸሮ ወጥ ስለነበር እንጀራ አይሰጡንም እንዴ?" ብዬ ኤልሳን ስለጠየቅኋት እየሳቀች! ቁርስ ላይ ዳቦ በእንቁላል፣ በማርማላታ አሊያም በዳቦ ቅቤ፣ ከወተት ወይ ከሻይ ጋር ይበላል እንጂ እንዴት እንጀራ ይበላል” ስትለኝ ደነግጥ ከው የኤልሳ ድምፅ፣ የአነስናና ክድምጽዋ ጋር እጆችዋን፤ ዓይኖችዋንና አንገቷን የምታን አለበት ገመንገድና አረማመድዋ ሳይቀር ከሁላችንም የተለየ መሆኑን ዕዳ ከኣ ባይና ልዩነት ጋር ተያይዞ የመm ስለመሰለኝ ይህ እሷ የምትወደውን ምግብ ባይጥመኝም መብላት ጀመር የመ ጠዋት ቁርስ ከበላን በኋላ ግቢውን ከኤልሳና ከሌሎቹ የመኖሪያ ክፍላችን ልጆች ጋር ሆነን እየተሄርን መጎብኘት ጀመርን። መጀመሪያ የነበኘነው የተለያዩ የዱር እንስሳት የሚገኙበትን አካባቢ ማለትም ዙ (200) እየተባለ የሚጠራውን ስፍራ ነበር፡፡ አንበሳ፣ ዝንጀሮ፣ ጅብና አዞን የመሳሰሉ እንስሳትን ጎበኘሁ፡፡ በተለይ አንበሳና አዞን በአካል ሣይ የመጀመሪያዬ ጊዜ በመሆኑ በጣም ደስ አለኝ፡፡ አካባቢው በጣም የሚያምር ውብ አካባቢ ሲሆን ያ ጀግና አንበሳ በብረት ፍርግርግ ውስጥ ተዘግቶበት ወዲህና ወዲያ ሲንቆራጠጥ፣ አዞ በገንዳ ውስጥ አፉን ከፍቶ ተኝቶ መመልከትና ዝንጀሮዎቹ በተለይ ሴት ሲያዩ የሚያስሙትን ጩኸትና ዝላይ ማየት በጣም የሚያስደስት ነበር፡፡ ቀጥለን የጎበኘነው የተለያዩ የዛፍ ዓይነቶች የሚገኙበትን አርቦራተም እየተባለ የሚጠራውን ስፍራ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ የሌለ የዛፍ ዓይነት የለም:: የዛፎቹ የአካባቢ መጠሪያ ስምና ሣይንሳዊ ስያሜያቸው ተፅፍ ተለጥፎባቸዋል፡፡ በዛፎቹ ውስጥ መንቀሳቀስ _ ሕይወትን በፍስሐ ይሞላል፡፡ ከዚያም ቀጥሎ የሄድነው ወደ ዓለማያ ሐይቅ ነው:: ዓለማያ ሐይቅ ዩንቨርስቲውን የሚያዋስን ሲሆን ስፋቱ አነስተኛ ነው:: ከዓሳ አጥማጆች ጀልባ ተከራይተን በሐይቁ ላይ ተዝናናን፡፡ በዚህም ጉብኝት በእኔና በኤልሳ መካከል የጎላ ልዩነት መኖሩን ተገነዘብኩ፡፡ ለእኔ ምንም የማይደንቀኝ ነገር እሷን በጣም ይደንቃታል፣ ያስደስታታልም፡፡ ዝንጀሮ፣ ዛፍ፣ ሐይቅ .. ባየን ቁጥር፤
"ኦ ማይ ጋድቃስ አይልምል እያለች ስትፍለቀለቅ እኔ ካየኋቸው ነገሮች ይልቅ በእሷ ደስታ ስገረም ዋልኩ:: ሌላው የገረመኝ ነገር የእርሻ ምርቻሮች ስንጎበኝ፣ ሁሉ የምትበላውን ጤፍና ስንዴ ሳይቀር “ይኸ ምንድነው? ይኸኛውስ?" እያለች ስትጠይቀኝ የምትቀናጣ መስሎኝ ልጠላት ቃጥቶኝ ነበር ::በኋላ ግን መኖሪያዋ ከተማ ውስጥ መሆኑ ትዝ አለኝና ጥያቄዋ ሁሉ ከልብ የመነጨ መሆኑን አወቅሁ:: ግቢው ሠፊ ከመሆኑ የተነሳ ሳናውቀው የምሳ ሰዓት ደርሶ ኖሮ ወደ ካፍቴሪያው በድጋሚ አመራን:: አሁን ደግሞ ምን ያቀርቡልን ይሆን? እያልኩ ሳስብ ቦታው ላይ ደረስንና በውሀ የተሞላ ኩባያና ያው ሳህን ተሰጠን:: ቢያንስ አሁን ምሳ ስለሆነ ያ ሳህን በተለያየ ምግብ ይሞላል ብዬ ጠብቁ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደጠበቅሁት ሳይሆን ሥጋ ውር ውር የሚልበት ቀጭን ቀይ ወጥ ከእንጀራ ጋር ተሰጠን:: በጣም የገረመኝ ነገር ቢኖር የሚሰጠን አንድ ዓይነት ወጥ ከሆነ ለምን ይህ ዓይነቱ ሳህን እንደተመረጠ ነበር:: በኋላ ግን በወሬ ወሬ እንደሰማሁት ግን ቀደም ሲል በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ዩንቨርስቲው አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ኦክላሆማ ከተባለ ዩንቨርስቲ ጋር በጣምራ ይሠራ ስለነበር ተማሪዎች የሚመገቡት ልክ እንደአሜሪካ ተማሪዎች ነበር አሉ:: በዛ ወቅት የሚገርመው ነገር፣ ተማሪዎች ወተት የሚቀርብላቸው በቧንቧ ሲሆን የሚለብሱትም ሱፍ ነበር ይባላል:: እኛ ዕድለ ቢሶቹ ታዲያ ዕድሜ ለደርግ! አሜሪካኖቹን አባሮ የድሮ ተማሪዎችን ለማስታወስና ስንበላ እንዳንደበር በማሰብ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ብቻ ወጥ ይደረግልንና በቀሪው ላይ እየበላን ገበጣ እንድንጫወትበት ሳይሆን አይቀርም ሳንወድ በግድ እንድንይዘው ተፈርዶብናል::'' ዲያሪው በዚህ መልክ ቀን በቀን አልማዝ ያሳለፈቻቸውን ሁኔታዎችንና ያጋጠሟትን ድርጊቶች ይተርካል፡፡ ለእኔ ደግሞ እነዚህ ታሪኮች ብዙም ጠቀሜታ ስለሌላቸውና የምፈልገውን መረጃ በፍጥነት እንዳላገኝ ስለሚያደርጉኝ እያንዳንዱን ገፅ ለመመልከት ትዕግስት አልነበረኝም፡፡ ስለዚህም በቀጥታ ያቺን የማልረሳትን የፍቅር መጀመሪያችንን ቀን ማለትም ስለ ጥር 2 ቀን 1976 የምትተርከውን ክፍል ፈልጌ ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡ "አማረ ሁልጊዜ መተዋወቅና ጓደኛ እንዲሆኑኝ ከምፈልጋቸው ወጣቶች አንዱ ነው፡፡ ረጋ ያለና የማይንቀለቀል፣ መልከ መልካም ባይሆንም የደስደስ ያለው ወጣት በመሆኑ ከጓደኝነትም አልፎ የመጀመሪያ የወንድ ጓደኛዬ እንዲሆንም ጭምር የምመኘው ነበር፡፡ ቁመናው ረዥምና በሥጋ የተሞላ ሲሆን ከደረቱ ሰፋ ያለ ሆኖ በስፖርት የዳበረ የሰውነት ቅርፅ አለው፡፡ ነገር ግን እጅግ ዓይነ አፋር ከመሆኑ የተነሳ ሰውን ቀና ብሎ ማየት እንኳን ስለሚፈራ ከሱ ጋር መተዋወቅ እንዲህ በቀላሉ የሚታሰብ አልነበረም፡፡ እንደ
እኔ በእርሻ ምህንድስና የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ቤተመጻሕፍት ውስጥ የሚቀመጥበት አካባቢ እኔ ከምቀመጥበት ወንበር ፊት ለፊት ስለሆነ ሳንተያይ የምንውልበት ቀን አለ ማለት ይከብዳል፡፡ ይሁን እንጂ ዓይነአፋር ከመሆኑ የተነሳ ድንገት እንኳን ቀና ሲል ዓይን ለዓይን ከተያየን ቶሎ ብሎ ደብተሩ ላይ ይደፋል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ቢሞት ቀና ብሎ እያየኝም። ብዙ ሰዎች ድምፄን እንደሚወዱት ስለሚነግሩኝ አሱን ሰምቶ እንኳን ቢያፈቅረኝ እያልኩ የቤተመጻሕፍቱን ፀጥታ እንኳን ማናጋቴ ሳይታወቀኝ ጮክ እያልኩ አወራ ነበር፡፡ በዚህም እኔና ኤልሳ ከቤተመጻሕፍቲ ሀላፊ ጋር በተደጋጋሚ ተጣልተናል፡፡ ለኤልሳቤጥ እንደምወደው ነግሬያት ስለነበር እንድንተዋወቅ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራት፡፡ ብዙ ጊዜም ላስተዋውቅሽ እያለች ትጨቀጭቀኝ ነበር። ለእኔ ግን የእሷ ማስተዋወቅ አልተዋጠልኝም እክንያቱም ምንም እንኳ ከአንድ አካባዜ ያለማንም ከእርሱ ጋር ምን ትውውቅ አልነበራትምና ነወስንና ከቤተመጻስ ያለማንም እርዳታ እንደምንም ብዬ አነጋግረዋለሁ ብዬ ኣወስንና ኣብ ሓጥጻሕፍት ሲወጣ እከተለዋለሁ ነገር ግን እሱ ዞር ብሎም ስለማያዮ ላዩ ስለሚከትራልገኝ ያዋርደኛል ብዬ በማገር ተወዋለሁ። አንዳንዴ ከኋላ ኋላዬ ስለሚከተለኝ ዛሬስ ላነጋግረው ብዬ ዞር ካልኩ ተጠማዞ ወደ መጣበት ይመለሳል፡፡ ዛሬ ግን ቀንቶኛል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተመጻሕፍት ውስጥ የሞት ሞቴን ከጠቀስኩት በኋላ ቀና ብሎ ሲያየኝ ፈገግ አልኩለት:: ከድንጋጤው የተነሳ ፊቱን ወደ ኋላ ሲያዞር ግን ደነገጥኩ፡፡ ግን ቆየት ብሎ ቀና ሲል አየኝና ዓይን ለዓይን ስንገጣጠም ፈገግ አለልኝ፡፡ ደስታዬ ጣራ ሊነካ ደረሰ፡፡ ውስጣዊ ስሜቴ አሁኑኑ ሄደሽ ተዋወቂው፣ አሁኑኑ አነጋግሪውም አለን፡፡ ግን ሰው ያየኛል ብዬ ፈራሁ፡፡ ቤተመጻሕፍት ሲዘጋ ቀደም ብለን ወጥተን ጠብቀን እንድናነጋግረው ከኤልሳ ጋር ተስማማን፡፡ ደግነቱ እኛም ስንወጣ እሱም ተከትሎን ወጣ፡፡ እንደተባባልነውም መንገድ ዘጋንበትና በሰበቡ ተዋወቅነው፡፡ ይህችም ቀን የፍቅራችን የመክፈቻ ዕለት ሆነች" ይላል
የሚገጥመውን ፉክክር በተገቢው ብቃት በአሸናፊነት ለመወጣት አስቦበትና ወስኖ ነበር..አሁን ግን ባልና ሚስቶቹ ባቀረቡለት ሀሳብ መሰረት ሁሴን ቀጥታ እንደመጣ እነሱ ቤት የሚያርፍና እዛው የሚሰነብት ከሆነ ከእሱ በተሻለ የሰሎሜን ልብ የማሸነፍ እድል ተመቻቸለት ማለት ነው፡፡አምስት ሺ ሜትር እሩጫ ለመወዳደር የወሰኑ ሮጮች…በድንገት ለአንደኛው የ1ሺ ሜትር አባንስ ተሰጥቶት በቃ ሩጡ እንደታባለ አይነት ስሜት ነው የተሰማው፡፡
እና እንደምንም ብሎ ሁሴን ከመጣ እና ባልና ሚስቶቹ ቤት ካረፈ በኃላ ቡዙም ሳይሰነብትና ስር ሳይሰድ በሁለት በሶስት ቀን የሆነ ሰበብ ፈልጎ ከእዛ ቤት አስወጥቶ ከተቻለ ሁኔታዎቹንና የየእለት እንቅስቃሴውን መቆጣጠር እንዲያመቸው ወደራሱ ቤት ካልሆነም ወደሆቴል የሚገባበትን ሁኔታ በሆነ ዘዴ ማመቻቸት እንዳለበት አስቦ ወሰነ፡፡
በተነጋገሩት መሰርት አላዛርም ሆነ አለማየሁ ከስራ ቀርተው ሁሴንን ለመቀበል በሚደረገው ዝግጅት ላይ ሰሎሜን ሲያግዟት ነው የዋሉት፡፡የሚገዙ ነገሮች በመግዛት ፤በግ ገዝቶ በማረድና በመከታተፍ..ቤት በማዘጋጀት..ሚጠጡ መጠጦችን ከግሮሰር በማምጣት እንዲሁ ሲባክኑ ዋሉ፡፡ሰሎሜም ከሰራተኛዋ ጋር የሚያስፈልገውን የምግብ አይነት በማዘጋጀት ስትለፋ ነው የዋለችው፡፡
አስራሁለት ሰዓት ሆኖ መሰራት ያለበት ስራ ሁሉ ካተጠናቀቀ በኃላ እራሳቸውን ወደማዘጋጀት ሄዱ፡፡
‹‹ቀኑን ሙሉ ስታፈጉኝ ስለዋላችሁ ሰውነቴ ሁሉ ላብ ላብ ብሏል …ቤቴ ሄጄ ሻወር ወስጄ ልምጣ…››
ሰሎሜ‹‹ምነው ሻወር የላቸውም አሉህ እንዴ?››ስትል መለሰችለት፡፡
‹‹አለ አውቃለሁ… ግን ልብስም መቀየር አለብኝ፡፡››
‹‹ምን ?የደንብ ልብስህን ለብሰህ ልትመጣ ነው?፡፡››
‹‹አረ…ጓደኛዬን እንኳን ደህና መጣህ ..ብዬ ልቀበል እንጂ ግዳጅ እኮ አይደለም ምሄደው….››
‹‹እንደዛ ከሆነ እዚሁ ሻወር ውሰድ….ሳይዛችን እንደሆነ አንድ ነው ያለበስኳቸው ሱፍ ልብሶች አሉ ..እንሱን ትጠቀማለህ››አለው አላዛር፡፡
‹‹እንዴ ባልና ሚስቶች ልትድሩኝ አስባችኃል እንዴ?››
‹‹ምን ይታወቃል…ባል ፍለጋ ብር በሻንጣ ጭና የምትመጣ ዲያስፖራ ሴትን ከኤርፖርት ስትወጣ ልታገኝ ትችላለህ…ከዛ እንደምታየው ድግሱ ተዘጋጅቷል …ጠለፍ አድርገህ ወደእዚሁ ማምጣት ብቻ ነው…፡፡››
አላዛር‹‹በቃ ና …ሻወር ቤቱን ላሳይህ ››ብሎት ይዞት ወደ እንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ሲሄድ ሰሎሜ ወደገዛ መኝታ ቤቷ ገባች፡፡ልብሷን አወላልቃ ቀጥታ ወደሻወር ቤት ነው የገባችው፡፡በጉጉት እና በመገረም ስትጠብቅ የነበረው ቀን መድረሱን ማመን አልቻለችም፡፡ከነፃንነቷ ጀምሮ እስከጉርምስናዋ ሲከተሏትና ሲንከባከቧት የነበሩ ሶስት ወንዶች በአንድ ቤት ተሰብስበው ከእንደገና በእሷ ዙሪያ ተቀምጠው አይን አይኖን በስስት እያዩ የሚቁለጨለጩበት ቀን ደርሷል…ያ ጣፋጭ ጊዜያቶች ተመልሰው ሊመጡላት ነው፡፡ ምንም ቢሆን ምንም እንደበፊቱ እንደማይሆን እና እሷም ነፃ ሆና ከሶስቱም ትከሻ ላይ በእኩልነት እንደማትንጠለጠል..እነሱም እንደበፊቱ ነፃሆነው እንደበፊቱ እንደማይሆኑ ታውቃለች..ቢሆንም አሁንም በፊት ከእነሱ ጋር ስትሆን እንደሚሰማት አይነት ተመሳሳይ ስሜት ነው እየተሰማት ያለው፡፡ደስ የሚል ስሜት፡፡ልቧን የሚያሞቅ ሴትነቷን የሚያጎላ …ምን ይፈጠር ይሆን ከሚል ጉጉት ጋር የተለወሰ…..፡፡
ሰውነቷን ታጥባ ከመጨረሷ በፊት የመኝታ ቤቱ በራፍ ሲከፈት ሰማች፡፡አላዛር እንደሆነ ታውቃለች፡፡ ፈጠን ብላ ከሰውነቷ ላይ ያለውን ሳሙና አስለቅቃ ሻወሩን ልትለቅለት መጣደፍ ጀመረች …
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
atronosem" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronosem
ስልኩ ተዘጋ፡፡ከአላዛር ጋር ስልክ እያወራ ሳይታወቀው ቤቱ በረንዳ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ከፍቶ መግባት አልቻለም፡፡ሁሉም ነገር ድንግርግር ነው ያለበት….‹‹እውነት እንዳወራሁት አላዛርን ማገዝና ከገባበት ችግር እንዲወጣ እፈልጋለሁ?›› መልሱ ቀላል ነው ፡፡ፈፅሞ አይፈልግም፤ምኞቱ እንዳይሳካለት ነው፡፡ግን ደግሞ እንደተናገረው እሱን የእውነት መቅረብ እና እንደልጅነታቸው ሚስጥሮቻችውን ሁሉ እንዲለዋወጡ ይፈልጋል፡፡የዛም ምክንያት የህክምናው ሂደት እንዴት እየሄደለት እደሆነ በየቀኑ ዝርዝር መረጃዎችን ማግኘት ስለሚፈልግ ነው… እንዴት ሆኖ ይሆን ?ብሎ ከመጨነቅ ይገላለግለዋል…ለዛ ነው ከእሱ ጋር ያለውን ቀረቤታ ወደ ድሮ መመለስ የሚፈልገው፡፡
በራፉን ከፍቶ ገባና የደንብ ልብሱን ቀይሮ በቢጃማ ሳሎን ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ በማለት ፊት ላፊት ያለውን ቴሊቪዥን ከፈተና ወደ ሀሳቡ ተመለሰ፡፡
‹‹ቆይ ግን ቪያግራ ለምን አይሞክርም….?መቼስ ስለዛ መድሀኒት መረጃ ሳይኖረው ቀርቶ አይደለም….እንኳን እሱ ችግር ያለበት እኔ እራሱ ሁለት ሶስት ጊዜ ከፋራማሲ ገዝቼ መጠቀሜን አስታውሳለው፡፡››ሲል አጉረመረመ፡፡
አለማየሁ እርግጥ ችግር ስላለበት ወይም አልቆም ብሎት አልነበረም ለመጠቀም የተነሳሳው፡፡አዲስ ሴት ሲተዋወቅ በተወሰነ መልኩ ያለመረጋጋትና በራስ የመተማመን ችግር ያለበት ሲመስለው ነበር የተጠቀመው፤እርግጥ ይሄ ስሜት ሁሌ የሚሰማው አይነት ስሜት አይደለም…ለሴቷ የተጋነነ ግምት ሲኖረውና ምን አልባት በፈለገችው ልክ አላረካት ይሆን …?የሚል ጥርጣሬ ስለሚያሳድርበት ነው የሚጠቀመው….እርግጥ ቪያግራ ብልትን ልክ እንደብረት የመገተር እና በወሲብ ወቅትም ለረጅም ጊዜ በሞቀ ስሜት ለመቆየት የሚያስችል ኃይል ሚያጎናፅፍ መድሀኒት ነው፡፡አንዳንዴም ሴቷ ሁለት ሶስቴ ደጋግማ እስክትረካ የመጠበቅ ችሎታን ያጎናፅፋል….ያው እንደሚታወቀው ሴቶች ለመርካት የሚወስድባቸው ጊዜ ከወንዱ አንፃር ረጀም ነው…ምክንያቱም ወንድ ልጅ በፍጥነት መጋል ሲችል ሴት ልጅ ግን በጣም ዝግ ብላ ነው ወደሪትሙ የምትገባው፡፡ በዛ ወቅት ደግሞ ወንዱ ጡዘት ላይ የሚደርስበት ጊዜ ስለሚሆን መተላለፍ ይፈጠራል….ቪያግራም ያንን መተላለፍ እንዳይፈጠር ያግዛል፡፡ግን አለማየው እንዳታዘበው የሆነ ደስ የማይል ነገር አለው….ትንሽ የሚያስጨንቅ የውጥረት አይነት ስሜት ….እና ደግሞ ከመጠን በላይ ውጥርጥር ስለሚል ያማል….እና ደግሞ የሴቷን ብልት እስከመላጥ ድረስ ሊያደርስ የሚችልበት አጋጣሚም ያስከትላል…እና በተከታታይ እሱን ተጠቅሞ ወሲብ ማድረግ በቀጣይ በሚኖር የራስ መተማመን ላይ ችግር ያስከትላል፡፡ልክ ሽጉጥ በጎኑ ሳይሽጥ ለተልዕኮ እንደተሰማራ ፖሊስ አይነት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡…ይሄ በግል ትዝብቱ ያካበተው ልምድ ነው፡፡ሲወራ እንደሰማው ከሆነ ደግሞ ልብ በሽታ ያለባቸውንና በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ይህንን መድሀኒት ሲጠቀሙ እራስን እስከመሳትና ከዛም አልፎ እስከህይወት እልፈት የሚያደርስ ችግር እንደሚያስከትል ነው፡፡
‹‹እና ግን እንደአላዛር አይነት ችግር ያለባቸው ሰዎች ግን ቢጠቀሙት የሚሻል ይመስለኛል››ሲል አሰበ.‹‹ግን ይሄንን እስከአሁን ሳያውቅ ወይ ሳይሞክር ይቀራል እንዴ?››ሲል እራሱን ሞገተ፡፡በመጨረሻም በሀሳብ ብዛት ሰውነቱ ዝሎ ወደመኝታ ቤቱ ገባና ጥቅልል ብሎ ተኛ፡፡ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰደው፡፡ቢሆንም ብዙም ሳይቆይ ሲያስባቸው የዋላቸው ሁሉም የድሮ ጓደኞቹ በህልሙ ተግተልትለው የመጡበት ..ሁሴን ፤ አላአዛርና እሱ አንድ ላይ ቆመው ይታዩታል …ሰሎሜ ነጭ ቪሎ ለብሳ ነጭ ክንፍ አብቅላ በአየር ላይ እየተንሳፈፈች ነው፡፡ሶስቱም ዙሪያዋን ከበው….በደስታ እየዘለሉ ይጨፍራሉ፡፡አንዳቸውን መርጣ እንድታቅፋቸው ከእሷ ጋር አብራ ይዛቸውን ወደላይ ደመናውን ገምሳ ሰማዩን ሰንጥቃ እንድትበር እየተማፀኗት ነው፡፡
‹‹ማነው ይበልጥ እኔን የሚያፈቅረኝ››በፈገግታ እንደደመቀች ወደታች አዘቅዝቃ እያየቸቻቸው ትጠይቃለች፡
‹‹እኔ ነኝ..እኔ ነኝ…አይደለም እኔ ነኝ…›› እያሉ ሁሉም ከሬሜላ እንደሚበተንለት ህፃን ልጅ እጃቸውን ወደ እሷ አንከርፍፈውና አይናቸውን አንጋጠውን እርስ በርስ እየተጎሻሸሙ ሲጮጮሁ ይታያል፡፡
‹‹ስርዓት ያዙ...እኔ አንድ ነኝ.. እንዴት ለሶስታችሁም ልሆን እችላለሁ?››በሳቅና ቁጣ መካከል ባለ ድምፀት በመገሰፅ ትጠይቃቸዋለች፡፡
‹‹ማሬ ታውቂያለሽ ከሁሉም በላይ እኔ ነኝ የማፈቅርሽ …ሁሉም ሲጎረምሱ አንቺን ጥለውሽ ሔደዋል..እኔ ግን ሁሌ አብሬሽ ነብርኩ….ደግሞ አትርሺ ተጋብተናል..ቃልሽን ሰጥተሸኛል››ሲል አላዛር ከሁለቱ የተሻለ የሆነበትን ምክንያት አስረዳ፡፡
‹‹ወዴ እሱ እንደሚለው አይደለም..እኔ ጥዬሽ አልሄድኩም …ለአንቺና ወደፊት ለምንወልዳቸው ልጆቻችን የተደላደለ ህይወት ስል ነው ወደ ስደት የሄድኩት፡፡አሁን ግን ሁሉንም ነገር አሳክቼ ወደአንቺ ተመልሼለሁ፡፡የተደላደለ የገነት አይነት ህይወት አኖርሻለው፡፡አንቺ ንግስቴ ነሽ……አይደለም አነዚህ ከንቱዎች አንቺ ራሱ እራስሽን እኔ በማፈቅርሽ መጠን አታፈቅሪውም››ይሄንን ንግግርግር በኩራትና በበላይነት መንፈስ ተቀጣጥሮ የተናገረው ሁሴን ነው፡፡
አለማየሁ ከእነሱ የተሻለ እንደሚያፈቅራት የሚስረዳበት ምንም ምክንያት ማስቀመጥ አልቻለምና..እሷ በአየር ላይ እየተንሳፈፈች የሆነ ነገር እንዲል እየጠበቀች እንደሆነ ገብቶታል....እሱ ደግሞ ሚናገረውን አጥቷል….፡፡
‹‹በቃ እናንተ እስክትስማሙ እኔ ልሂድ›› ብላ ወደ ላይ መነሳት ስትጀምር አላዛር ተንጠራርቶ አንደኛውን የቀሚሷን ጫፍ ይይዛል….ወዲያው ዞሮ ሁሴንን ሲያየው እሱም በተቃራኒው ያለውን የቀሚሷን ጫፍ በተመሳሳይ ይዟል …አለማየሁ
‹‹እንዴ እኔስ ለምን ይቅርብኝ?›› ብሎ እግሮቾን ሊይዝ ሲል እሷ ወደላይ ተንሸቅንጥራ መብረር ትጀምራለች..እነሱም ተንጠልጥለው በአየር ላይ ተንሳፈው ይታዩታል፡፡ ምርጫ አልነበረውምና በፍጥነት ወሰነ..‹‹ብቻዬን ምድር ላይ ከምቀር ››ብሎ በአንድ እጁ የሁሴንን እግር በሌላ እጁ የአላዛርን እግር ያዘ …ሰሎሜ ልክ እንደንስር ሰማይን ሰንጥቃ ወደላይ መክነፍ ጀመረች…‹‹ልቀቅን ልታስወድቀን ነው…እግራችንን ልቀቀ››እያሉ ሁለቱም ባልተያዘው አንድ እግራችው ትከሻውን በመደብደብ ወደ ምድር ሊያሽቀንጥሩት ይሞክራሉ፡፡እሱ ደግሞ እነሱን ከለቀቀ ወደታች ተፈጥፍጦ መሞት ብቻ ሳይሆን ከሰሎሜም ጋር ለዘላለሙ መለያየቱ እንደሆነ በማሳብ በተቻለው አቅም መታገሉን ቀጠለ…… .ጭንቀቱ ከፍተኛ ነበር…ድንገት ሲባንን አንሶላውና ብርድልብሱን ከላዩ ላይ አሽቀንጥሮ ወለሉ ላይ ጥሎ ራቁቱን ነበር፡፡.መላ ሰውነቱ በላብ ተዘፍቆል….‹‹በስመአብ››ሲል አማተበና ‹‹ እንኳንም ህልም ሆነ…..››ሲል እራሱን አፅናና…ከዛ በኃላ መልሶ ለመተኛት ድፍረቱን አላገኘም..እንዲሁ ሲገላበጥ ነጋና እንደወትሮ ተዘገጃጅቶ ወደመደበኛ ስራው ሄደ፡፡
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
atronosem" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronosem
🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ ‼️
ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇
‹‹አረ እንደዛ እንዳያስብ ንገሪው…እኔ ይሄንን እንደራሴ ሚስጥር ነው የምይዘው..ከማንም ሰው ጋር አንስቼ እንደማልወያይበት ለአንቺም ሆነ ለእሱ ቃል መግባት እፈልጋለው፡፡››
‹‹አመሰግናለሁ..ቅድም ስንገናኝ ይሄንን ውለታ ልጠይቅህ ነበር..ግን እንዴት እንደምነግርህ ቸግሮኝ ነው ዝም ብዬህ የወጣሁት፡፡››
‹‹አታስቢ አልኩሽ እኮ!!››
‹‹በድጋሚ አመሰግናለሁ
…በወቅቱ እዛ ፖሊስ ጣቢያ ስንገናኝ በችግሬ ታውሬ ስለነበር ነገሩን አስፍቼ አላየሁትም ነበር…፡፡››
‹‹ችግር የለም አልኩሽ እኮ››
‹‹እሺ..የፊታችን እሁድ ይመችሀል እንዴ?››
‹‹ይመቸኛል..ምነው…?እንገናኝ ልትይኝ ነው?››
‹‹አይ..አብረን ለምን እቴቴ ጋ ሄደን አናስገርማትም ልልህ ነው፡፡››
‹‹እርግጠኛ ነሽ ?››
‹‹በደንብ››
‹‹እሺ እንደፈለግሽው እናደርጋለን››
‹‹ጥሩ …በቃ እንደዋወላልን››
‹‹በይ እሺ… አሁን መልካም ህልም፡፡››
‹‹ቻው ላንተም እንደዛው››
ስልኩና አስቀመጠና አልጋው ላይ ወጥቶ ጥቅልል ብሎ ተኛ….ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰደው፡፡
ጥዋት አለማየሁ ወደስራ ለመሄድ እየተዘጋጀ ሳለ ነበር… የውጭ ስልክ በሞባይሉ ጠራ..ግራ በመጋባት አነሳውና‹‹ሄሎ..ማን ልበል?››ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹አለማየሁን ማናገር ፈልጌ ነበር››
‹‹አዎ አለማየሁ ነኝ…ማን ልበል?››
‹‹አሌክስ ሁሴን ነኝ››
‹‹ሁሴን ሁሴን››
‹‹የድሮ ጓደኛህ….የልጅነት ጓደኛህ…ሁሴን ጀማል….››
‹‹አንተ…ከየት ተከሰትክ…?ሰላም ነህ..?ቁጥሬን ከየት አገኘህ….››የጥያቄ ናዳ አግተለተለበት፡፡
‹‹ሰላም ነኝ…..እንደአጋጣሚ የሰሎሜ ስልክ ስለነበረኝ በቀደም ስደውልላት ከአንተ ጋር መገናኘት እንደጀመራችሁ ስትነግረኝ በጣም ተደስቼ ፤ስልክህን ጠየቅኳትና ሰጠችኝ፡፡››
‹‹በእውነት ስለደወልክልኝ ደስ ነው ያለኝ፡፡እስከወዲያኛው የተለያየንና የተረሳሳን መስሎኝ ነበር…፡፡››
‹‹እኔም እንደዛ ነበር የማስበው…አድራሻህን እንዳገኘሁ ለዛ ነው ወዲያው ሳልውል ሳላድር የደወልኩልህ፡፡››
‹‹በጣም ጥሩ አደረክ…ለመሆኑ ሰላም ነህ…?ስራ ..?››
‹‹ሁሉም ነገር ሰላም ነው…ሰሞኑን ልመጣ ነው›
‹‹የት እዚህ አድስ አበባ?››
‹‹አዎ …ከአስር ቀን በኃላ እመጣለሁ››
‹‹በእውነት ደስ ይላል..ለቫኬሽን ነው?››
‹‹ለቫኬስሽንም ና…ሁለተኛ ዲግሪዬን እየሰራሁ ስለሆነ ለሪሰርች ጭምር ነው…ቢያንስ ሶስት ወር ቆያለሁ››
‹‹በጣም ደስ ይላል ..በቃ….የምትመጣበትን ቀን እና ሰዓት አሳውቀኝ …እቀበልሀለው፡፡.››
‹‹በእውነት ይህንን መስማቴ ደስ ብሎኛል…..ለአላዛርም ስደውልለት ልክ እንደአንተ ነው ደስ ያለው…እሱም እቀብልሀለው ብሎኛል፡፡››
‹‹አዎ በጣም ደስ ይላል…የተበታተኑ የድሮ ጓደኛሞች መልሰው የሚሰባሰቡበት ጊዜ ደርሷል ማለት ነው፡፡››
‹‹አዎ እንደዛ ነው..በል ከዚህ በላይ አልያዝህ..በድጋሜ ደውዬ መምጫ ቀኔን አሳውቅሀለው..››
‹‹እሺ ቻው ሁሴን…››ስልኩን ዘጋ፡፡ፈጽሞ ያልጠበቀው ነገር ነው፡፡ድብልቅልቅ የሆነ የሚረብሽ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው፡፡ደስታም መረበሽም ….አሁንም ሶስቱም አንድ ላይ ተገናኝተው ሰሎሜን ከበው ሲቀመጡ ምን እንደሚሰማቸውና ምንስ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አልቻለም፡፡እርግጥ አሁን እንደድሮው አይደለም ሰሎሜ የአላዛር ህጋዊ ሚስት ሆናለች፡፡ግን ደግሞ በመሀከላቸው ያለው ሸለቆ ስምጥና እሩቅ ነው፡፡እና አላዛር ከበሽታው ማገገም ተስኖት ሁለቱ ከተፋቱ ሰሎሜን መልሶ ለማግኘት ሁለቱ ይፎካከራሉ ማለት ነው…አለማየሁና ሁሴን…..‹‹ምን አልባት እሱ እስካሁን ባለበት ሀገር አንዷን ወዶና አጭቶ ወይንም አግብቶ ሊሆን ይችላል… እንደዛ ከሆነ ግልግል ››ሲል አሰበና እራሱን እንደምንም ለማረጋጋት ጥረት ማድረግ ጀመረ፡፡
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
atronosem" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronosem
#ታላቁ_እልቂት
በዚያ ቀን፣ ልክ የዛሬ 89 ዓመት፣ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በተካሄደው ጭፍጨፋ አዲስ አበባና አካባቢዋ ውስጥ ብቻ ወደ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን፣ ዘንድሮ 89ኛ ዓመቱ ላይ ነው። የካቲት 1929 ዓ.ም.የሚያክል ለኢትዮጵያ የመከራና የጽልመት ወራት ኖሮ አያውቁም።በጣም የሚገርመው፣ በዚሁ በወርኃ የካቲት 1888 ዓመተ ምህረትም ከሰባ ሺህ በላይ ወገኖቻችንን መሥዋዕት አድርገናል። ግፈኛው የንጉሥ ኡምቤርቶ ጦር፣ በጄኔራል ባራቴሪ እየተመራ ሃይማኖት ሊቀለብስ፣ መሬት ሊቆርስ፣ ነፃነታችንን ሊገስ መጥቶ ማጭድና ጎራዴ፣ ጦርና ጋሻ የያዙትን በመድፍና በዘመኑ መሳሪያዎች ፈጃቸው።
ከአርባ አንድ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ለወረራ የመጣው በማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ የሚመራው የፋሺስትም ጦር፣ ከየካቲት 12 ቀን እስከ የካቲት 14 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ከሠላሳ ሺህ በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን ገደላቸው።
#የመታሰቢያ_ሐውልታቸው
ሀውልቱ የወራሪው የጣሊያን ወታደሮች በግፍ የጨፈጨፏቸውን 30ሺ ያህል ሰዎች ለመዘከር የቆመ ነው፡፡ ግራዚያኒ ሰራዊቱን እና መኳንንቱን ጠርቶ ፣ ህዝቡን ሰብስቦ የአሁኑ አዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ቀደም ሲል ገነተ ልዑል በሚል ይታወቅ በነበረው በአፄ ኃይለስላሴ ቤተ መንግስት ውስጥ የተለመደ የእብሪት ንግግሩን በማሰማት ላይ ነበር፡፡ ግራዚያኒን ለመግደል አመቺ ቦታ እና ጊዜ ሲጠባበቁ የነበሩት አብርሐም ደቦጭ እና ሞገስ አሰግዶም የያዙትን ቦምብ አከታትለው ወረወሩበት፤ ግራዚያኒም ቆሰለ፡፡ ከዚያች ቅፅበት በኋላ በማንኛውም ሁኔታ የተገኘ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በግፍ ተጨፈጨፈ፡፡ አዲሰ አበባም በንፁሀን የደም ጎርፍ ተጥለቀለቀች፡፡ በህፃናት ለቅሶ በእናቶች ዋይታ ተዋጠች፡፡ በወቅቱ የተፈጠረው ሁኔታም ኢትዮጵያውያን በድፍረት እና በወኔ ጠላትን እንዲፋለሙ ብርታት ሆናቸው፡፡ እነዚህን ያለርህራሄ የተጨፈጨፉ ንፁሀን ዜጎች ለማሰታወስም ዛሬ በየካቲት 12 ሆስፒታል ፣ በአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በቀድሞዉ በአንበሳ ግቢ መካከል 6ኪሎ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የሰማዕታቱ ሃውልት ቆሟል፡፡
በዚህ ሀውልት ቀረፃ ላይ ኢትዮጳያውያን ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል፡፡ ሀውልቱ 28 ሜትር ቁመት ያለው ሲሆን ባለ ሶስት ማዕዘንም ነው፡፡ ሀውልቱ የተሰራው በሁለት የዩጎዝላቪያ ዜግነት ያላቸው ባለሙያተኞች ሲሆን በሀውልቱ ላይ ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ወታደሮች በግፍ ሲገደሉ የሚያሳዩ ቅርፃ ቅርፆችም ይስተዋላሉ፡፡ ሀውልቱ ከቅርፃ ቅርፆቹ ባሻገር የተለያዩ ፅሁፎችም አሉት፡፡
ክብር #ለተሰውት #ሰማዕታት……..!!!
በሀገራችን ኢትዮጵያ የተከፈተ ምርጥ የ ስፖርት ቻናል ✔️
https://t.me/joinchat/AAAAAERNvsQgUA8gYjwX3Q
አባቴ ግን ቅዝዝ ባለ ዓይን እያየኝ፤ "አልሙ! ለምን አላለቅስ! የዛሬዋ ቀንማ ለእኔና ለእናትሽ የሐዘን ቀን ነች.፡፡ አሁን ዩንቨርስቲ ልትገቢ ነው፣ ከዛ ሥራ ትይዢያለሽ፣ ከዛ በኋላ ደግሞ ትዳር ትመሰርችያለሽ፡፡ እርግጥ ይኼ ትልቅ ደስታችን ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ ከእኛ ራቅሽ ማለት ነው፡፡ ቤታችንን የምታደምቀው ኩራዝ ከዛ
በኋላ ብርሃኗ ቢፈካም ለእኛ ግን አይደርሰንም፣ በመሃላችን የሚለያየን ግድግዳ አለና፡፡ ሕይወታችንን ያደሰችው የአልማዝ አለመኖር የድሮውን የብቸኝነትና የጨለማ ዘመን መልሶ የሚያመጣው ስለመሰለኝ ፈራሁ! እባክሽ አትቀየሚኝ " አለኝ። እርግጥ አባባ የፈራው ነገር አልቀረም፡፡ እነሆ ዩንቨርስቲ ገባሁ የአማረም ፍቅረኛ ሆንኩ፡፡ ዛሬ በእነሱ የወላጅ ፍቅር ፋንታ ይኸው እሱን ማምለክ ጀምሬአለሁ፡፡ ነገ ደግሞ እሱ ባለቤቴ ሲሆን ሁሉም ነገር እንደተፈራው ሆነ ማለት ነው :: ከዛ በኋላ ደግሞ ከእሱና ከእኔ ሌሎች ጣዖቶች ይፈጠራሉ፡፡ ይህም ማለት የአባትና እናቴን カチ ヘルパン የአማረንም ፍቅር የሚሻሙ ሌሎች ተረኞች በተራቸው ይመጣሉ እያልኩ አስብ ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል፤ ይህ ሁሉ ከምኞትነት አልፎ እውነት ሊሆን አልቻለም! ላይጨበጥ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡ ይኸው ዛሬ እንደፈራሁት አማረ ለእኔ ከነበረው ፍቅር የተነሳ ትምህርቱ ሊሳካለት ስላልቻለ ግቢውን ለቅቆ ለመውጣት ተገደደ፡፡ ያ ስፈራው የነበረው የብቸኝነትና የባዶነት ስሜት መልሶ ጥላውን አጠላብኝ፡፡ ይህች ቀንም በሕይወቴ የማልረሳት የሐዘን ቀን ሆና አለፈች። ከዚህች ቀን በኋላ ለብዙ ጊዜያት ያህል እንቅልፍ አልወስድሽ እያለኝ ተቸገርኩ፡፡ ሌላው የረበሸኝ ነገር ቢኖር በእነዚያ ከአማረ ጋር ተቃቅፈን ስንምነሸነሽባቸው በነበሩ መንገዶች ላይ ብቻዬን ስሄድና ስመጣ ያየ ተማሪ ሁሉ በለበጣ መልክ ከንፈሩን ሲመጥልኝ ነበር፡፡ በየዕለቱ ወገቤን አቅፎ በውብ ቃላት እያወራ ከጥናት በኋላ የሚያዝናናኝና በዓለም ላይ የእኔ ብቻ የምለው እሱ አጠገቤ እስካለ ድረስ ቀንና ሌሊት መፈራረቁን ቢያቆም እንኳን ቅር የማይለኝን ፍቅሬን ማጣቴ ሰላም አሳጣኝ፡፡ እጅግ የምወደውንና የማፈቅረውን ሰው ያጣሁባትን ይህችን ቀንም ያቺን በወሬ ሰምቼ በሐሳብ የምስላትን በልጅነቴ ሰው በራፍ ላይ ከተጣልኩባት ቀን ጋር አመሳሰልኳት፡፡ ያቺ ቀን ዋንኛዎቹን ወላጆቼን ያጣሁባት፣ ይህችኛዋ ደግሞ ውድ ፍቅረኛዬን ያጣሁባት ቀን ነበረችና፡፡" የማነበውን ነገር ማመን አቃተኝ፡፡ ውስጤ አልማዝን ቢቀየምም ይህንን ሣነብ ግን እምባዬ ዓይኔን ሞላው፡፡ በጉንጬም ላይ የሚወርደው እምባ ዲያሪው ላይ ተንጠባጠበ፡፡ የተዘበራረቀ ሀሳብም ጭንቅላቴን ሞላው፡፡ እንዲህ የምትወደኝ ከሆነ ታዲያ ለምን ጠላቺኝ? እኔስ ከሷ በላይ እወዳት አልነበረምን? እኮ ለምን ከዳችኝ? እያፈቀርኳትና እየወደድኳትስ ለምን ችላ አለችኝ? ለሚሉትና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ ባላገኝላቸውም ራሴን ግን ጠየቅሁ፡፡ ታዲያ ይህ ከሆነ ምን ሊያለያየን ቻለ? አዎ የጓደኛዬ የሰለሞን
መላኩ ደብዳቤ ትዝ አለኝ፡፡ ከሞላ ጎደል እንደማስታውሰው : እንዲህ የምትል ነበረች። "ውድ ጓደኛዬ አማረ፤ ለመሆኑ እንደምን ከርመሀል?፡፡ ጤንነትህስ እንዴት ነው? ምነው ደብዳቤ መፃፉን ተውከው? አንተ ደብዳቤ መፃፉን ብትተወውም እኔ መፃፍ ስለነበረብኝ ብዕሬን ለማንሳት ተገደድኩ፡፡ ምንም ቢሆን የሚወዱት ሰው ሲጠቃ ከራስ መጠቃት ስለማይተናነስ ዝም ብሎ ማለፍ አላስቻለኝም፡፡" ይላል የሰለሞን ደብዳቤ፡፡ መግቢያው በዚህ የጀመረው ትረካው እንዲህ ይቀጥላል፡፡ "አልማዝ አንተ ደብዳቤ በየጊዜው እንደምትፅፍላትና ገንዘብም እንደምትልክላት አጫውታኛለች፡፡ ግን ይህንን ሁሉ እየሰማሁና አላስፈላጊ ድርጊቶች ሁሉ ሲደረጉ እያየሁ፤ በአንተ በጥሩው ሰው ገንዘብ እና ከዚያም በላይ በአንተ ሕይወት ስትጫወት ማየቱ አላስችል ስላለኝ የግድ ለመፃፍ ተገደድኩ፡፡ አማረ ሁሉም ነገር እንደነበረ ይኖራል ብለህ አትጠብቅ፡፡ የሰው ባህሪ እንደዓለማችን ተፈጥሮ ይለዋወጣል፡፡ የተወለደ ያድጋል፣ ያረጃል፣ ብሎም ይሞታል፣ ፍቅርም እንዲሁ ነው፡፡ ያ ትላንትና እንደ ታሪክ የሚወራው የአንተና የአልማዝ ፍቅር ሞቶ በአልማዝና በአድማሱ ፍቅር ቢተካ የሚያስደነግጥ አይሁንብህ፡፡ እንዳረጀ ቆጥረህ አንተም በሌላ አዲስ ፍቅር ተካው፡፡ እርግጥ አንኳን ለአንተ፣ ለእኔም በመካከላችሁ የነበረውን ፍቅር ለሚያውቅ ሰው ያ ፍቅር እንዲሞት መፍረድ ከባድ ነው፡፡ ለብዙ ጊዜ ከህሊናዬም ጋር ልንገር አልንገር እያልኩ ታግያለሁ፡፡ ግን በደልን እያዩ ዝም ብሎ ማለፉ እኔም አብሬ እንደበደልኩህ ዓይነት ስሜት እንዲሰማኝ ስላደረገኝ አላስችል አለኝ፡፡ የትላንትናዋ የአንተ ፍቅረኛ የዶክተር አድማሱ እንጂ የአንተ እንዳልሆነች የትላንትና ፍቅራችሁን የሚያውቀው ተማሪም ሆነ አስተማሪ ሁሉ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ እባክህን ጊዜና ገንዘብህን ለማይረባ ነገር ማጥፋትህን ተወው፡፡ የቀድሞዋን አልማዝንም እርሳትና ስለሌላ አልማዝ አስብ ። በተረፈ ከዚህ በላይ ማውራት ላንተ የሚጠቅም ነገር ስለሌለው ብዙ ማውራት አልፈልግም፡፡ አንተም ሌላ አመቺ ነው ባልከው መንገድ ሁኔታውን ለማጣራት ሞክር፡፡ በሰላም ለመተያየት ያብቃን˚ የሚለው የውድ ጓደኛዬ መልዕክት ጣልቃ ገብቶ ትዝ አለኝ፡፡ ይህች ደብዳቤ ነበረች ለእኔና ለአልማዝ ፍቅር መሻከር የመጀመሪያ መንስኤ የሆነችው፡፡ እርግጥ ነው አልማዝ ለኔ ያላት ፍቅር ማለቁ ላይ ጥርጣሬ አልነበረኝም፡፡ ምክንያቱም ለምልክላት ደብዳቤዎች መልስ መንፈግ
ከጀመረች ቆይታለችና፡፡ እኔ በየጊዜው ደብዳቤ ብዕፍም ከእሷ በኩል መልስ በመቅረቱ ከነገ ዛሬ ትመልስ ይሆናል እያልኩ በመጠባበቅ ላይ እያለሁ ይህ ደብዳቤ ስለደረሰኝ የእኔና የአልማዝ ፍቅር ማክተሚያው መሆኑን በመረዳቴ እሷን ከማስታወስ ይልቅ እንድጠላት መጣጣሩን ተያያዝኩት፡፡ ግን እንዴት ይቻላል? የሚወዱትን ሰው በአንድ ጊዜ ከጭንቅላት ጎትቶ ማውጣት ቤት ጠርጎ ቆሻሻ እንደመድፋት ቀላል አልነበረም፡፡ በዚህ ላይ ያ ጨክኜ ሰባብሬ ላቃጥለው ያልቻልኩት ፎቶግራፏ ከራስጌዬ በላይ ጉብ ብሏል፡፡ ስለሞን እንደመከረኝ ሁኔታውን ለማጣራት ሌላ መንገድ መፈለግ ግን አልተዋጠልኝም፡፡ እኔ እዚያ ግቢ ውስጥ ያለኝ የማምነው ጓደኛዬ እሱ ነበርና፡፡ ነገር ግን እውነታውን ማወቅ ስለነበረብኝ የሰማሁትን ነገር ገልጬ እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን እንድትነግረኝ ለአልማዝ በቀጥታ ደብዳቤ ፃፍኩላት፡፡ አልማዝም ያለርህራሄ መራራውን ፅዋ እንድጎነጭ በደብዳቤ አሽጋ ላከችልኝ፡ በደብዳቤውም ውስጥ እሷን ከእንግዲህ ወዲህ በመጠበቅ ጊዜዬን እንዳላባክን፣ እሷ ግን የዲግሪ ትምህርቷን ለመቀጠል እንዳሰበችና እኔም ቢጤዬን እንድፈልግ የሚመክር ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ አልማዝን መርሳት ነበረብኝና እያንገፈገፈኝም ቢሆን መርሣትን መለማማድ _ ጀመርኩ፡፡ ለሴት ያለኝም ፍቅር ከአልማዝ ጋር አከተመ፡፡ ሁሉንም ነገር ትቼ ማስተማሩንና መጠጣቱን ተያያዝኩት: የመጠጥ ሱሴም ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጣ፡፡ ጥሩ እንቅልፍም መተኛት ካለብኝ የግዴታ መጠጣት ነበረብኝ፡፡ ለሌላ ሴት ዳግም ልቤን ላለመስጠትም የአልማዝን ፎቶ ከራስጌዬ አስቀመጥኩት ። ሁሌ እሷን ሳይ ለሴት ልጅ ያለኝ ጥላቻ ይጨምራል፡፡ በተለይ ፎቶው እየሳቀች የተነሳቸው በመሆኑ በጅልነቴ እና በቂልነቴ የምትስቅብኝ መስሎ ስለሚሰማኝ ዳግም ተመሳሳይ ስህተት ላለመሥራት ስል ከሴት እንድርቅ ረድቶኛል፡፡ አሳዒይታ ሞቃት ከተማ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሙቀቱ ከአርባ ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ይደርሳል፡፡ በተለይ በእንደዚያ ያለው ወቅት ቤት ውስጥ መተኛት
🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_7
ደብዳቤዎቹ በዘገዩና ይዘታቸው እየተለወጠ በመጣ ቁጥር ለእኔ ያላት ፍቅር አልቋል የሚል ግምት አደረብኝ። በተለይ ከዶክተር አድማሱ ጋር ያላት ግንኙነት እንደድሮው ቀጥሎ ከሆነ እኔን በእሱ ልትተካኝ ትችላለች የሚለው አስተሳሰብ ሁሌም ያስጨንቀኝ ነበር። ዶክተሩ ባለትዳር ስላልሆነ፣ አንድ ሴት ልጅና አንድ ወንድ ለብቻቸው ሲሆኑ "በመሐላቸው የማይጠፋው ሴይጣን' እንዳያሳስታቸው ሁል ጊዜ እፀልይ ነበር። አንዳንዴ ደግሞ አልማዝ ለኔ የነበራትን ፍቅር ሳስብ "ይህ ሊሆን አይችልም ብዬ እራሴን እየደለልኡ አዕናናለሁ፡፡ ትላንትና ለእኔና ለእሷ የወደፊት ሕይወት ከልቧ የምትጨነቀው ውድ ፍቅረኛዬ በአንድ ግዜ ትከዳኛለች ብሎ ማሰብ የሚከብድ ነበር፡፡ ግን እርግጥ አልማዝ ትወደኝ ነበር? አዎ ትወደኛለች እንጂ! ግን እኮ ፍቅሯ ቀንሶ ቢሆንስ? ይኸማ አይደረግም! ቢሆንም ሰው ነችና ልትሳሳት ትችላለች፣ እያልኩ መጨነቁ ግን አልቀረም፡፡ ለማንኛውም _ መልሱን ከዲያሪው ለማግኘት በማሰብ ስለዚሁ የሚያወራውን አውጥቼ ማንበብ ቀጠልኩ፡፡ መጋቢት 10 ቀን 1976 ዓ.ም "ለአማረ ያለኝ ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ ስለሱ ሳስብ የምውልበት ቀን ከማጠናበት ቀን ይበልጣል፡፡ በየቀኑ ማታ ማታ ከቤተመጻሕፍት መልስ ተቃቅፈን ግቢውን መዞር የማይቀር የዕለት ተዕለት ፕሮግራማችን ሆነ፡፡ የግቢው ሰው ሁሉ የሮሜዮና የጁልዬት ተምሳሌቶች እንደሆንን አድርጎ ያየናል፡፡ እኔ ደግሞ የእነሱ መጨረሻ ስለማያምረኝ እንዲህ ሲሉኝ ብዙም ደስ አይለኝም፡፡ በልጅነቴ ያጣሁትን የእውነተኛ እናትና አባት ፍቅር የሚተካ ፍቅር ያገኘሁም ስለመሰለኝ ጁልዬት ሮሜዮን ባጣችበት መልኩ ላጣው አልሻም፡፡ ዛሬ ከአማረ ጋር ለሽርሽር ወደ ድሬደዋ ሄድን፡፡ በተለይ በከዚራ ዛፎች ስር በምሽት የተንሸራሽርነውና ናይት ክለብ ውስጥ ቯልስ የደነስነው የሚረሳ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ያላሰብኩት ነገር ሆነ፡፡ እንደዛ የምወደውና የማፈቅረው ጓደኝዬ ባልጠበኩትና ባልገመትኩት መንገድ የገባልኝን ቃል ጥሶ በሰርጌ ዕለት አቀርብለታለሁ ያልኩትን ክብረንፅህናዬን ገሰሰው፡፡ ይህ ብቻ አልነበረም፤ እኔም በእሱ ላይ የነበረኝን እምነት ናደው፡፡ ያላሰብኩት ነገርም ባላሰብኩበት ወቅት በመፈፀሙ በእጅጉ አዘንኩ፡፡ ግን ካለእሱ ማንም ስለሌለኝና እሱ ለእኔ፣ እኔ ለእሱ ያለን ፍቅር ቢናድ ደግሞ ወደብቸኝነቱ ዓለምና ዳግም ወደ ሐዘን ባህር የምሰምጥ መሆኔን በመረዳቴ ቢከፋኝም እንዳልከፋኝ ሆኜ እንደምወደው ነገርኩት፡፡ እሱም በድርጊቱ እጅግ በጣም ተፀዕቶ ስለነበር በዚሁ ተፅናና፡፡ በድርጊቱ ብናደድም አምላክ ግን ለእሱ ያለኝን ፍቅር እንዳይቀንስብኝ ፀለይኩ፡፡''
ባነበብኩት ነገር ተገረምኩ፡፡ እንዲህ አዝናብኛለች ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ በወቅቱም ይቅርታዋ እና እወድሀለሁ ያለችኝ ከልቧ እንጂ በፍፁም ከአንገት በላይ የተደረገ ይቅርታ አልመሰለኝም ነበር፡፡ አልማዝ በእኔ ላይ ያደረገችው ሁሉ ሆን ብላ በቂም በቀል የፈጸመችው ሊሆን ይችላል ብዬም ገመትኩ፡፡ እውነቱንም ለማወቅ ዲያሪውን አለፍ አለፍ እያልኩ ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡ ሚያዚያ 25 ቀን 1977 ዓ.ም "አማረ አብዛኛውን ጊዜ ከማጥናት ይልቅ ከእኔ ጋር እየተዝናና ቀኑን በሙሉ ቢያሳልፍ ደስ ይለዋል፡፡ እኔ ደግሞ ከእሱ ጋር መሆኑን ባልጠላውም ለትምህርቴ የተወሰነ ጊዜ መስጠት እንዳለብኝ ግን ይሰማኝ ነበር፡፡ ሁሌም ከእሱ ከተለየሁ በኋላ ሀሳብ ባህር ውስጥ ሰጥሜ እንዳልቀር መደበቂያዬ የጥናት ደብተሬ ነበር፡፡ ይህም በትምህርቴ ጥሩ ውጤት እንዳመጣ ረድቶኛል፡፡ ቀስ በቀስ የሱ ውጤት እያሽቆለቀለ መምጣት ጀመረ፡፡ አማረ ከእኔ ጋር ከመተዋወቁ በፊት ጎበዝ ተማሪ የነበረ ሲሆን ለአሁኑ ውጤቱ ማሸቆልቆል ሆን ብዬ ያደረግሁት ባይሆንም እንኳ በተዘዋዋሪ ተጠያቂ መሆኔን እኔ ብቻ ሳልሆን ተማሪዎች ሁሉ ያውቃሉ።ይህም በእኔ ላይ ትልቅ ሃላፊነት እንደሚያርፍ እያመላከተኝ በመምጣቱ ይበልጥ ማጥናቴን ተያያዝኩት፡፡ ውጤቴም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጣ፡፡ ለዚህም የዶክተር አድማሱ አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዶክተር አድማሱ ታሪኬን ነግሬው ስለነበር እጅግ ያዝንልኝና ይንከባከበኝ ነበር፡፡ እቤቱ በትርፍ ጊዜው ብመጣ እንደሚረዳኝ ቃል ገብቶልኝ ስለነበር ከእኔም በዕድሜ የበሰለና ብዙ ነገር ያየ በመሆኑ በእሱ ላይ ካለኝ እምነት የተነሳ ብቻውን የሚኖር ቢሆንም ምንም ሳልፈራና ሳልጠራጠር በትርፍ ጊዜዬ ሁሉ እቤቱ እየሄድኩ ያስጠናኝ ነበር፡፡ አማረ ይህ ሁሉ ደስ ባይለውም የእኔን ታማኝነት መጠራጠር ስላልፈለገ ደፍሮ ሊያስቀረኝ አልከጀለም፡፡ እርግጥ ከዶ/ር አድማሱ ጋር ከተዋወቅሁ ጀምሮ ከአሳዳጊዎቼና ከአማረ ውጪ ዘመድ ለሌለኝ ምስኪን አንድ ተጨማሪ ዘመድ ማግኘት ስለመሰለኝ ቅርበቴ ይበልጥ እየጨመረ መጣ፡፡ ከዚህም በላይ ዶክተር አድማሱ እንደአስተማሪዬ ብቻ ሳይሆን እንደጓደኛ ያቀርበኝ ነበር፡፤ በዚህም አስጠኚ ብቻ ሳይሆን ሲከፋኝ የሚያበረታታኝ፣ ሣዝን የሚያፅናናኝ፣ ጨዋታውም አፍ የሚያስከፍት ጓደኛ ሆነልኝ። ይሁን እንጂ ከአማረ ጋር ያለኝን ግንኙነት አይወደውም ነበር፡፡ በእሱም የተነሳ ውጤቴ ሊያሽቆለቁል ስለሚችል እንድጠነቀቅ እየደጋገመ
ይመክረኛል። ቀስ በቀስ ግን ለአማረ ያለኝን ፍቅር ጥልቀት እያወቀ ሲመm ጣልቃ መግባቱን ተወ። ስለዚህ ጉዳይ ባነሳ ቁጥር ከፊቴ ላይ የሚያየው የመከፋት ስሜትም ያንን የማይጥም ምክሩን እንዲተው አደረገው::" ሰኔ 20 ቀን 1977 ዓ.ም "የዛሬው ቀን በሕይወቴ ውስጥ የማልረሳውና እናትና አባቴ እውነተኛ ወላጆቼ አለመሆናቸውን ከሰማሁበትና ተጥዬ አግኝተው እንደሚያሳድጉኝ እንጂ እውነተኛ ወላጆቼ እነማን እንደሆኑ እንደማያውቁ በነገሩኝ ዕለት ከነበረኝ ስሜት ጋር አመሳሰልኩት። የዛን ቀን ወላጆቼ እነማን እንደሆኑ፣ ከእነማንና የት እንደተወለድኩ፣ የምን ብሄር ተወላጅ እንደሆንኩ፣ እህት፣ ወንድም፤ አክስት፤ አጎት ባጠቃላይ ዘመዶች ይኑሩኝ አይኑሩኝ ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት በኖ የጠፋበት ቀን በመሆኑ፤ በሕይወቴ የማልረሳው የሀዘን ቀን ሆኖ አለፈ፡። አዎ! እውነተኛ የአብራካቸው ክፋይ አለመሆኔን የነገሩኝን ዕለት እጅግ አድርጌ እጠላታለሁ፡ አጋጣሚው እንዲህ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ከአንድ የሰፈር ልጅ ጋር ተጣላንና እኔ በዕድሜ ትንሽ በለጥ ስለምል እያሳደድኩ እደበድበው ጀመር። በመሃል እናትየው መስኮት አጠገብ ቆመው ያዩ ኖሮ እየሮጡ መጥተው ሕፃን ነች እንኳን ሳይሉ ባልወለደ አንጀታቸው ራሴን በተደጋጋሚ ኮረኮሙኝ፡፡ እኔም እያለቀስኩ ለእናቴ ተናገርኩ፡፡ እናቴም በአድራጎታቸው ተናዳ ወደ ሴትየዋ አስከትላኝ ሄደችና፤ "እንዴት ይቺን አንድ ፍሬ ልጅ ጭንቅላቷን በኩርኩም ይመቷታል? ልጅና ልጅ ዛሬ ቢጣላ ነገ ተመልሶ ይገናኛል፣ ነውር አይደለም እንዴ!" ትላቸዋለች፡፡ ሴትየዋ ሰው ዘርጣጭ ስለነበሩ፤ "ዝምበይ ይህችን የማደጎ ልጅሽን ቀጥተሸ ማሳደግ ነበረብሻ™ ይሏታል፡፡ በወቅቱ ማደጎ የሚለው ቃል ትርጉም አልገባኝም ነበር፡፡ እናቴ ግን በጣም ተናዳ፤ "ምነው ከአፎት የሚወጣውን ቃል ቢመርጡ.፣ ባለጌ!" ትላቸዋለች:: ሴትየዋም በንዴት፤ "ምነው አርፈሽ ብትቀመጪ፣ ንገሩኝ ባይ! ላልወለድሻት ልጅ ጠበቃ መኮኑ ነው? በቅሎ! " ይሏታል፡፡ እናቴ ሲሰርቅ እንደተያዘ ሰው ክው ብላ ደንግጣ ኩምሽሽ አለች፤ "እግዚአብሔር ይይልሽ!" ብላ ምልስ አለች፡፡
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ሁሉም ከእንቅልፋቸው ተነስተው ሳሎን በረንዳ ላይ ቁርስ ለመብላት ጠረጴዛ ከበው ተቀምጠዋል፡፡
ሰሎሜ ከሰራተኛዋ ጋር ተጋግዛ ቁርስ ለመስራት 11፡30 ላይ ነበር አልጋዋን ለቃ የተነሳቸው፡፡እርግጥ ማታ ሰባት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታዋ እንዳመራች ቀኑን ሙሉ ስትደክም ስለዋለች ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰዳት…ቢሆንም ከ3 ሰዓት በላይ መተኛት አልቻለችም፡፡አስር ሰዓት ላይ ሙሉ በሙሉ ነቅታ ግን ደግሞ እዛው አልጋዋ ላይ ጀርባውን ሰጥቷት ከተኛው ባሏ ጎን በጀርባዋ ተንጋላ በመተኛት…የባጥ የቆጡን ስታብሰለስል ነበር፡፡ አንድን አውጥታ ሌላውን ስታወርድ ከቆየች በኃላ 11፡30 ሲሆን ተነስታ ወደኪችን ገባች፡፡ሰራተኛዋ ቀድማት ተነስታ ቁርስ ለመስራት ሽንኩርት ስትከታትፍ ነበር ያገኘቻት፡፡ከዛ እየተጋገዙ ሰሩና የሚፈልጉትን ቁርስ አንድ ሰዓት ላይ ጥንቅቅ አድርገው ሰርተው ጨረሱ…፡፡ወንዶቹ ተነስተው እና ተጣጥበው ጠረጴዛው ዙሪያ አስኪቀርቡ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ …ሁለት ሰዓት ላይ የቁርስ ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፡፡
‹‹ምድረ ስራ ፈት….እኔ እንግዲህ የመንግስት ኃላፊነት ያለብኝ ሰው ነኝ ፣ወደስራ ልሔድ ነው፡፡››አለ አለማየሁ፡፡
‹‹ስማ ሀገሪቱ እያደገች ያለችው በመንግስት ሰራተኞች ብቃትና ትጋት አይደለም እኮ…››አላዛር ነው የመለሰለት፡፡
‹‹ታዲያ በማን ነው?››
‹‹በእኛ በግል ባለሃብቶች ትጋትና ልፋት ነው፡፡›› አላዛር መለሰ፡፡
‹‹ታዲያ ምን ይሁን እያልክ ነው?››
‹‹ስራ ያለብህ አንተ ብቻ አይደለህም..እኔም ስራ አለብኝ ለማለት ነው››
‹‹አውቃለሁ…አንተ ግን አረፋፍደህ ባሰኘህ ሰዓት መግባት ትችላልህ ብዬ ነው››
‹‹አይ …ማርፈድ የስፍና ምልክት ነው ይባል የለ..አብረን እንውጣ፣ቢሮህ አድርሼህ ወደስራ ገባለሁ፡፡››
‹‹እንዴ የእኔ ቢሮ ቄራ ያንተ ቢሮ አራትኪሎ ዙሪያ ጥምዝ እኮ ነው››
‹‹ችግር የለውም…››ብሎ ከመቀመጫው ተነሳ..አለማየሁም ተከትሎት ተነሳ፡፡
‹‹እና ጥላችሁን ልትሄዱ ነው?››ሁሴን ጠየቀ
‹‹ምንም ማድረግ አንችልም..ሁለት ሁለት ተካፈልን ማለት ነው…››
‹‹ምሳ ሰዓት ትመጣላችሁ እንዴ?››ሰሎሜ ሁቱም ላይ ተራ በታራ አይኖቾን እንከባለለች ጠየቀች፡፡
እኔ እየዞርኩ ሳይቶችን የማይበት ቀን ስለሆነ ምመጣ አይመስለኝም..ምን አልባት ኩማንደር››
‹‹አይ እኔም አልችልም…ዲያስፖራው እሷ ካስደበረችህ ግን ራይድ ታክሲ ተሳፍረህ ቢሮ ድረስ ከች በል››
‹‹አንተ ፣እንዴት እንዴት ነው የምታስበኝ …?እኔ የማስደብር ሰው ነኝ?››
‹‹አይ ነገሩን ነው ያልኩት››
አላዛር‹‹በሉ ሄደናል…ማታ ተያይዘን እንመጣለን››አለና ፊቱን አዙሮ መንገዱን ቀጠለ
‹‹እሺ ሞቅ ሞቅ አድርገን እንጠብቃችኃለን››አለች ሰሎሜ ፡፡
አላዛር እና ኩማንደሩ መኪና ውስጥ ገብተው የጊቢውን በራፍ ዘበኛው ከፍቶላቸው ወጥተው ሲሄዱ ሁለቱም በትኩረት እየተመለከቷቸው ነበር፡፡?
‹‹የማየው ነገር ሁሉ ህልም ህልም እየመሰለኝ ነው››አለ ሁሴን
‹‹ምኑ?››
‹‹የአራታችን ከአመታት በኃላ እንዲህ አንድ ላይ መሰባሰብ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…መቼም ይሆናል ብዬ አስቤው አላውቅም ነበር….በተለይ አንተ ወደሀገር ተመልሰህ ትመጣልህ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር››
ትኩር ብሎ እያያት‹‹ለምን?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ወደዚህ እንድትመጣ የሚያደርግ ምክንያት የለህማ››
‹‹ተሳስተሻል…አንቺ እስካለሽ ምክንያት አለኝ ማለት ነው››
ያሰበችውን መልስ ከአንደበቱ አውጥቶ እንዳይነግራት በመፍራትና ደግሞም በተመሳሳይ ጊዜ የሚለውን ለመስማት መጓጓት በሚታይበት ግራ በተጋባ ስሜት ‹‹አንቺ ስትል…ሶስታችንንም ለማለት ነው አይደል…?የልጅነት ጓደኞችህን?››
‹‹አዎ ..የአንቺ ግን በተለየ ነው…ሶስታችንም እናፈቅርሽ እንደነበር ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹ይሄ ነገር እውነት ነው እንዴ…?በቀደም አሌክስ እንደዚህ ሲለኝ ሙሉ በሙሉ አላመንኩትም ነበር…ዛሬ አንተ ደገምከው››
‹አይ እወነቱን ነው..ህፃን ሆነን ጀምሮ የሶስታችንም የወደፊት ምኞታንና እቅዳችን አንቺን ማግባት ነበር..››
‹‹የህፃንነት ምኞታችሁ ነዋ..ስትጎረምሱ ግን ተዋችሁት..እንደዛ ነው አይደል?››
‹‹አይ ተሳስተሻል..ስንጎረምስ እንደውም የበለጠ እያፈቀርንሽ..የበለጠ እየተራብንሽ ነው የሄድነው…፡፡››
የምትመልሰው መልስ ስለጠፋት ዝም አለች…..
‹‹ምነው ሶስታችንም እንደምናፈቅርሽ ስላወቅሽ ደበረሽ….?ማለት ከዳተኛ ጓደኞች መስለን ታየንሽ?››
‹‹አይ ..ማንኛዋም ሴት እኮ በመፈቀሯ አይደብራትም..እንደውም ኩራትና ደስታ ነው የሚሰማት…ግን ያልተዋጠልኝ የምትሉትን ያህል የምታፈቅሩኝ ከሆነ ለምን ጥላችሁኝ ተበታተናችሁ…አብሮኝ አስከመጨረሻው ከጎኔ የነበረው አላዛር ነው…እናም አፈቅርሻለው ቢለኝ የማምነው እሱን ነው፡፡››ስትል በእውነት የምታምንበትን ነገር ነገረችው፡፡
‹‹እዛ ላይ ትክክል ነሽ…የአሌክስን አላውቅም …እኔ ግን ያው እንደምታውቂው ከዩኒቨርሲቲ ልመረቅ ጥቂት ወራት ሲቀረኝ አንድ የቀረችኝ ብቸኛ ዘመድ እናቴ ሞተች..ያ በጣም ነበር ያበሳጨኝ..እና በዛ ስሜት ላይ እያለው ነበር እስኮላሩን ያገኘሁት…ያ ለእኔ ታላቅ እድል ነበር..አሻፈረኝ ብዬ የማልገፋው እድል..ምክንያቱም ምንም የሚረዳኝ ሌላ ይቅር የኮፒ ሳንቲም የሚሰጠኝ ዘመድ አልነበረኝም፡፡ለትምህርቴ ያለኝን ፍቅር ደግሞ የምታውቂው ነው…እና እድሉን ሳገኝ በደስታ ነበር የተቀበልኩት..ያንን ስቀበል አንቺን ያሳጣኛል የሚል ምንም አይነት ጥርጣሬ አልነበረኝም…መጀመሪያውኑ እኔ ከሁለቱ ጓደኞቼ በትምህርት የተሻልኩ በመሆኑ እኔን እንደምትመርጪ በእርግጠኝነት አምን ነበር..የውጭ እድል ሳገኝ ደግሞ በራስ መተማመኔ የበለጠ ጨመሮ ነበር፡፡››
‹‹ይገርማል ..ወንዶች ስትባሉ ሁላችሁም ጅሎች ናችሁ ማለት ነው?እንዴት እንደዛ ልታስብ ቻልክ… ?ከሄድክ በኃላ እኮ ለረጅም ጊዜ ግንኙነት አልነበረንም..ተመልሰህ እንደምትመጣ እንኳን አላውቅም ነበር…እንደው እንደምታፈቅረኝ አውቄ ላንተ ፍላጎት ቢኖረኝ እንኳን እንዴት ልጠብቅህ እችላለሁ?፡፡
‹‹ነይ እስኪ የሆነ ነገር ላሳይሽ?››ብሎ ከተቀመጠበት ..ተነሳ፡፡
‹‹ምንድነው?››ግራ በመጋባት ጠየቀችው፡፡
‹‹ዝም ብለሽ ተከተይኝ›› አለና እጇን ይዞ እየጎተተ ወዳረፈበት መኝታ ክፍል ወሰዳት…‹‹በገዛ ቤትሽ ልጋብዝሽ ተቀመጭ››አላት፡፡
አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡
ግድግዳውን ተጠግተው ከተቀመጡ ሁለት ሻንጣዎች ወደአንደኛው ሄደና ዚፑን ከፈተው…አንድ አነስተኛ መጠን ያለው ላፕቶፕ አወጣና ወደእሷ ቀረበ ከጎና ተቀመጠና ላፕቶፑን ከፈተው…. ከዛ ኤሜል ከፈተና
‹‹አየሽ ይሄን ኤሜል››
ወደእሱ ጠጋ ብላ አየችው
salome2013@gmail.com ይላል
ግራ በመጋባት በትኩረት አየችው፡፡
‹‹ምንድነው ..?አልገባኝም››
‹‹ወደ እንግሊዝ ከሄዱክ ከተረጋጋው በኃላ ደውዬ ላገኝሽ ሞክሬ ነበር..ስልክሽ ግን አይሰራም..አላዛርን ስጠይቀው..ስልኳ ጠፍቶባታል ..አዲስ ቁጥር ደግሞ ገና አላወጣችም አለኝ፡፡ከዛ ኢሜልሽን እንዲልክልኝ የጠየቅኩት…እና ይሄንን ኤሜል ላከልኝ››
‹‹ግን እኮ ይሄ የእኔ ኢሜል አይደለም››
‹‹ይቅርታ ኩማንደር….ይቅር ይበሉኝ፡፡››አለና ተሳሳቁ፡፡ እንዲህ እየተጫወቱ እነአላዛር መኖረሪያ ቤት ደርሰው መኪናዋን ወደውስጥ አስገብተው አቁመው ተከታትለው ወደቤት ገቡ፡፡ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሆኖ ነበር..፡፡ሳሎን እንደደረሱ ሁሴን ሁለተኛ መገርም ነው የጠበቀው፡፡ቤቱ በዲኮሬሽንን በባለቀለም መብራቶች አሸብርቋል፡፡..መግቢያ ላይ የተቀመጠው ግዙፍ ጠረጴዛ በምግብ ሰህኖችና በመጠጥ ተሞልቷል፡፡ ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ወንድማችን ሁሴን እንኳን ወደ ሀገርህ በሰላም ተመለስክ›› የሚል ባነር ተለጥፎ ሲያይ እንባው አመለጠው…፡፡
ወደሀገር ቤት ተመልሶ ለመምጣት ስንት ለሊትና ቀን ከራሱ ጋር እንደታገለ እሱና ፈጣሪ ናቸው የሚያውቁት፡፡በህይወት የተረፈ ዘመድ የለኝም..ጓደኞቼም ተበታትነዋል፣ የማፈቀርት ሴት የምወደውን ጓደኛዬን አግብታለች..አሁን ብሄድ በብቸኝነት ህመም ራሴን ከማሰቃየት ውጭ ምን ማተርፈው ነገር አለ››በሚል ከራሱ ጋር ሲሟገት ሰንብቶ የራሱ ጉዳይ በሚል ነበር የመጣው፡፡ይሄው በመጀመሪያ ቀን ያልጠበቀው ገራሚና ደማቅ አቀባበል ነው.. የገጠመው፡፡በዛ ላይ ሶስት እድሜ ልኩን የሚያውቃቸው የሚወዳችው ጓደኞቹ ጠቅላላ በአንድ ላይ ተሰብስበው፡፡‹‹እንኳንም መጣሁና እንደዚህ የሚያከብሩኝና የሚወዱኝ ጓደኞች አሁንም እንዳሉኝ አወቅኩ››ሲል በውስጡ አሰበ፡፡ጎትተው ወስደው እንዲያርፍ ሶፋው ላይ አስቀመጡት..፡፡ አለማየሁ ከጎኑ ተቀመጠ.. ፡፡በዘበኛው አማካይነት ሻንጣው እየተጎተተ የተዘጋጀለት የእንግዳ ክፍል ገባለት፡፡
ከዛ የእራት መብላትና ከመጠጡም የየምርጫቸውን በመውሰድ መጎንጨት ጀመሩ፡፡..የልጅነታቸውና እና ወጣትነታቸውን ገጠመኞች ተራ በተራ እያስታወሱና እየተረኩ መሳሳቅና መጮጮኸህ ቀጠሉ…እስከለሊቱ ሰባት ሰዓት ስለእንቅልፍ ያነሳ ሰው አልነበረም..፡፡በእውነት ዝግጅቱን አስመልክቶ ሁሴን ብቻ ሳይሆን ራሳቸው ያዘጋጁት እንደዚህ ይዋጣልናል ብለው አልገመቱም ነበር፡፡ለሁሉም በጣም አስደሳች እና ፈንጠዝያ ውስጥ የከተታቸው ነበር፡፡
በመሀል አለማየሁ በተቀመጠበት ተንጠራራና ‹‹ሰዎች ሰባት ሰዓት ሆነ..አሁን እንግዳውን ለእናንተ አስረክቤ ልሂድ››የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡
‹‹እንዴ ወዴት ነው የምትሄደው?››ድንገት ነው ሰሎሜ የጠየቀችው፡፡
‹‹ወደቤቴ ነዋ››
‹‹ማለቴ… በዚህ ለሊት ሰባት ሰዓት ሆኗል እኮ››
‹‹ፖሊስ እኮ ነኝ..በዛ ላይ ሽጉጥ ታጥቄለሁ››ሲል በልበ ሙሉነት መለሰ፡፡
ዝም ብሎ ንግግራቸውን ሲያዳምጥ የነበረው አላዛር..‹‹ሠውዬ ፖሊስ መሆንህን እናውቃለን..ግን በዚህ ውድቅት ለሊት የምትሄድበት ምንም ምክንያት የለም…ለአንተም ክፍል ተዘጋጅቷልሀል፡፡››
‹‹ግን እኮ!!!››
አላዛር ይበልጥ ኮስተር አለ‹‹በቃ ይሄ ውሳኔ ነው፡፡እንቅልፋችሁ ከመጣ ተነሱ… ክፍላችሁን ላሳያችሁ…እረፉና ጫወታችንን ነገ ካቆምንበት አንቀጥላለን፡››በማለት ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡
‹‹ጥሩ በቃ… እኔም ባርፍ ደስ ይለኛል ››ብሎ ሁሴን በአላዛር ሀሳብ ተስማምቶ ተነሳ..አለማየሁም ተከትሎት ተነሳ፡፡ባልና ሚስቶቹ ከፊት ቀድመው እየመሩ ወደእንግዳ ክፍል ወሰዷቸው…፡፡
‹‹ሁሴን እቃህ እዚህኛው ክፍል ነው የገባው…ስለዚህ ያንተ ክፍል ይሄ ነው ማለት ነው..ኮማንደር ደግሞ ይሄው ቀጥሎ ያለው ክፍል፡፡የምትፈልጉት ነገር ካለ መጥሪያውን ተጫኑት.. ሰራተኛዋ መጥታ ትሰጣችኃለች….ሚጠጣ ነገር በየክፍላችሁ ባለው ፍሪጅ ውስጥ አለ፡፡በሉ ደህና እደሩ››
‹‹እናንተም ደህና እደሩ››በጋራ መለሱላቸው፡፡
ባልና ሚስቶቹ ፊታቸውን አዙረው ወደቀዘቀዘ መኝታ ክፍላቸው በቆዘመ ስሜት ሄዱ፡
ሁሴንና አለማየሁ ጎን ለጎን ባለ ክፍላቸው በራፍ ላይ ቆመዋል፡፡
‹‹አይገርም?››አለው ሁሴን፡፡
‹‹ምኑ…?››በቁዘማ ላይ ያለው አለማየሁ በደመነፍስ ጠየቀ፡፡
‹‹እንደዚህ አራታችንም አንድ ቤት እንሰበሰባለን ብለህ አስበህ ታውቃለህ?››
‹‹በፍፅም››
‹‹ግን ስሜቱ ደስ ይላል አይደል..?ማለቴ ምንም አንኳን ከመሀከላችን እድለኛ የሆነው አላዛር ቢያገባትም…አሁንም ከእሷ ዙሪያ ማንዣበብ ልዩ ስሜት አለው..ማለቴ ለእኔ እንደዛ ነው የሚሰማኝ፡፡››
‹‹ትክክል ነህ ፡፡እኔም ተመሳሳይ ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡ደስ የሚል ስሜት አለው…ግን ደግሞ ደስ የሚል ብቻም አይደለም..የሚያምና ሚለበልብም ስሜት አለው…በል ብዙ ብዙ ነገር የምናወራበት ብዙ ጊዜ አለን …ቀኑ ለአንተ በጣም አድካሚ እንደነበረ እገምታለው …ግባና ተኛ››
‹‹እሺ ደህና እደር ኩማንድር››
‹‹ደህና እደር፡፡ሁለቱም ወደየክፍላቸው ገቡና በራፋቸውን ዘጉ..፡፡ቀጥታ ልብሳቸውን አወላልቀው የተዘጋጀላቸውን ቢጃማ በመልበስ አልጋቸው ላይ ወጥተው ተዘረሩ…፡፡
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
atronosem" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronosem
🎬ምን አይነት ፊልም መመልከት ይፈልጋሉ?😱😱😱😱😱😱😱😱😱👇👇👇
▶️የቱርክ ፊልም JOIN 👈 ይንኩ
▶️የአሜሪካ ፊልም JOIN 👈 ይንኩ
▶️ የህንድ ፊልም JOIN 👈 ይንኩ
▶️የቻይና ፊልም JOIN 👈 ይንኩ
▶️የአማርኛ ፊልም JOIN 👈 ይንኩ
▶️ተከታታይ ፊልሞች JOIN 👈 ይንኩ
▶️ አኒሜሽን ፊልሞች JOIN 👈 ይንኩ
▶️አክሽን ፊልሞች JOIN 👈 ይንኩ
▶️የጫካ ፊልሞች JOIN 👈 ይንኩ
▶️የፍቅር ፊልሞች JOIN 👈 ይንኩ
▶️የsex ፊልሞች JOIN 👈 ይንኩ
✅ እንደ ምርጫው መርጦ ይቀላቀሉ ✅
JOIN
ይቀላቀሉ ይቀላቀሉ
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል በአዲሱ የውድድር ዘመን ለረጅም ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዡን የሚመራው ቡድን ማነው ?
Читать полностью…ዲያሪው፡፡ የማውቃቸው ታሪኮች በሷ አንደበት እንደቀረቡልኝና አጠገቤ ቁጭ ብላ የምታወራኝ ያህል ሆኖ ተሰማኝ፡፡ የማነበው የእሷን የእጅ ጽሑፍ እንጂ የምሰማው ያንን ጣፋጭ ድምጽዋን አልነበረም፡፡ ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስታውሰው ግን ጣፋጭነቱም ቢሆን ከንቱ ነበር። በጣም የገረመኝ ጉዳይ ግን እርግጥ እንዲህ የምትወደኝ ከሆነ እንዴት ወደ መጨረሻው አካባቢ ያ ሁሉ ፍቅሯ በአንድ ጊዜ ሊበን ቻለ? የሚለው ነበር፡፡ አዎ! ዛሬም ቢሆን ያ መራራ ታሪክ ትዝ ይለኛል፡፡ እንዲህ እወደዋለሁ እያለች እኔን ለማግኘት ምን ያህል እንደደከመች የምታወራውና
ያቺን ቀን የፍቅር ሕይወታችን የመክፈቻ ዕለት ያለችው ጉብል፣ ዛሬ ግን ያቺ ቀን የእኔ የመከራ ሕይወት የመክፈቻ ዕለት መሆኗን ብታውቅ ምን ይሰማት ይሆን? እኔ በእሷ ፍቅር የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥናት እንኳን ማጥናት ከማልችልበት ደረጃ ላይ ደረስኩ፡፡ የፈተና ውጤቴም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሽቆለቆለ፡፡ ምንም እንኳ እሷም ብዙ ግዜዋን ከእኔ ጋር በፍቅር የምታሳልፍና እንደኔ በፍቅር ተይዛለች ብዬ ብገምትም፣ እንደ እኔ ግን አልነበረችም፡፡ ክፍል ውስጥ የተማረችውን ነገር የማስታወስ ችሎታዋ ከፍተኛ በመሆኑ ውጤቷ በፍፁም አላሽቆለቆለም፡፡ እንዲያውም ትምህርት ቤት ውስጥ ጥሩ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች አንዷ ነበረች፡፡ በዚህ ችሎታዋና ለትምህርት ካላት ፍቅር የተነሳ አድናቂዎቿ ከነበሩት ውስጥ አንዱ የሜካኒክስ ሌክቸረር የነበረው ዶ/ር አድማሱ ብሩክ አንዱ ነበር። ዶ/ሩ በትምህርት ቤቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉ የተከበሩ ምሁራን አንዱ ሲሆን መልከ መልካምም ነው፡፡ እሷ በተለይ እሱ በሚያስተምረው ትምህርት የተለየ ስጦታ ስለነበራት የምታመጣው ውጤትም በትምህርት ቤቱ ውስጥ ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡ ዶ/ር አድማሱም ወደፊት እሱን ልትተካ የምትችል እሷ እንደሆነች በመንገር በትምህርቷም እንድትበረታ ሁሌ ይመክራታል፡፡ የሚከብዳት ነገር ካለም እቤት ጭምር እየወሰደ በትርፍ ጊዜው ያስጠናታል፡፡ ይሁን እንጂ ከእኔ ጋር ያላት ግንኙነት በግቢው ተማሪዎች ሆነ አስተማሪዎች ዘንድ ሁሉ የሚታወቅ ስለነበር ይህንኑ በልኩ እንድታደርገውም ይመክራት ነበር። "ለፍቅር ጊዜ አለው፣ እንደተማሪ መጀመሪያ ቅድሚያ መስጠት ያለብሽ ለትምህርትሽ ነው" እያለ በተደጋጋሚ እንደሚመክራትም ትነግረኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለእኔና ለእሷ፤ በተለይ ደግሞ ለእኔ፣ ከፍቅር በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ስላልነበር በእኛ በኩል ምክሩ ብዙም ተቀባይነት አልነበረውም፡፡ አልማዝ ፍቅርና ትምህርትን ጎን ለጎን ማካሄድ ብትችልም እኔ ግን አልሆነልኝም፡፡ ጓደኞቼ እንደ ዶ/ር አድማሱ ሁሉ ፍቅሩን በልኩ እንዳደርገውና መጀመሪያ ለትምህርቱ ትኩረት እንድሰጥ ቢመክሩኝም በፍፁም የሚቻለኝ አልሆነም፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የውጤቴ ማሽቆልቀል ቢያስደነግጠኝም ማጥናት ግን በፍፁም አልቻልኩም፤ ደብተሮቼ በሙሉ በእሷ ምስል የተሞሉ ናቸውና፡፡ ደብተሬን በከፈትሁ ቁጥር በየትኛውም _ ገፅ ላይ የማየው የአልማዝን ፊት፣ የማጠናው የአልማዝን ፍቅር እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ቀስ በቀስ ውጤቴ እያዘቀዘቀ መጥቶ ከዩንቨርስቲ መባረር ደረጃ ላይ መድረሴን እርግጠኛ እየሆንኩ መጣሁ፡፡ ግን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ያለኝ አማራጭ
የሴሚስተሩን መጨረሻ በኀዘን መጠበት ብቻ ሆነ። የምበረረው ወደ አራተኛ ዓመት መሽጋገር የሚገባኝ ወቅት ላይ ቢሆን, ከመባረሩ በላይ እኔን ያስጨነቀኝ ጋን ከአልማዝ ጋር ሳንተያይ የምናሳል ጦባብትን በመት ነበር፡፡ ጸርግት እሷ ከተመረቀች በኋላ እንደምንጋባ ታደግ ላግባባ አር ስለነበር ከነዚያ በኋላ ያለውን ቀሪ ሕይወቱን ከእሷ ጋር እንደማላልፍ እርግጠኛ ነበርኩ ቢያንስ ዲግሪ ይዤ መውጣት ባልችል እንኳን እሷን አግኝቼ ስለምወጣና ትምህርቱንም ቢሆን ቀስ ብዬ ስረጋጋ መልሰ ናበለ (readmission) በመmp አጠናቅቀዋለሁ እያልኩ ስለማስብ በዚሁ እፅናና ነበር፡፡ የእኔ መባረር ቁርጥ እየሆነ ሲመጣ አልማዝ የራሷን የጥናት ጊዜ ማራዘም ጀመረች። አብዛኛውን ጊዜዋን የያስተላልፈውም ዶ/ር አድማሱ ቤት ሆነ እኔም ሁኔታዋ ሁሉ አላምርህ እያለኝ መጣ:: በተለይ ዶክተሩ እኔን መንገድ ላይ ሲያየኝ ሰላምታ ለመስጠት እንኳን ከመጠየፉም በላይ አልፎ ተርፎ ስለእኔ ስንፍና እየነገረ፤ በቅድሚያ ብትችል ከእኔ ጋር የምታሳልፈውን ጊዜ እንድትቀንስ ከዚያም ጨራሽ ግን ን እንድትተው እንደሚመክራት ትነግረኝ ስለነበር ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የምትሞክር መሰለኝ፡ ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር አድማሱ በቁመቱ፣ በውፍረቱ፤ በፀጉር አበጣጠርና በተይምነቱ ከእኔ ጋር እንደሚመሳሰል እየደጋገመች ትነግረኝ ነበር፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እሷ እኔን በአካላቴ ቅርጽና ሁኔታ ከወደደችኝ፤ እርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ከተመሳሰለ እሱንም ልትወደው ትችላለች ብዬ ስለፈራሁ አዘውትራ ወደ እሱ ቤት መሄዷን አልወደድኩትም ነበር፡፡ እንደፈራሁትም ከእሱ ቤት መዋሉ እየተዘወተረ _ ሲመጣ _ ስለእኔ የነበረው መጥፎ አመለካካት የተለወጠ ይመስል ከእሱ አንደበት ስለእኔ ምንም መጥፎ ነገር እንደማይወራ ትነግረኝና በመጨረሻም ስለ እሱ ጥሩነት፣ ርህሩህነትና ምሁርነት ተገልጾ ወሬው ይዘጋ ጀመር፡፡ አንድ ቀን ከዚሁ ጋር ተያይዞ እያወራችኝ እያለ በንዴት፤ "አሁንስ አላበዛሽውም እንዴ! እኔን እኮ ትተሸ ውሎሽ ሁሉ ከእሱ ጋር ሆኗል" አልኳት፡፡ እሷ ግን ምንም የመናደድ ስሜት ሳይታይባት የምለውን ሁሉ በትዕግስት አድምጣ ስታበቃ ፈገግ እያለችም፤ እሷ የምትጥረው ለእኔና ለእርሷ ትዳር መሠረት ለመጣል እንደሆነና በተለይ ለተወሰነ ጊዜ የሁለታችንን መተዳደሪያ የእሷ ደሞዝ ብቻ ሊሆን ስለሚችል በርትታ ትልቅ ደረጃ ላይ ለመድረስ መጣር እንዳለባት ትነግረኝ ጀመር። በአባባሏ ባምንበትም ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን በእሷ ጥገኝነት ላይ መውደቄን ሳስብና ከዶ/ር አድማሱ ጋር ያላትን እየጠበቀ የመጣ ግንኙነት ሳስታውስ ጥሩ ስሜት ስለማይሰማኝ ነጭናጫና ተጣይ እየሆንኩ መጣሁ፡፡ በተገኛኘን ቁጥር ነገር ፈልጌ ሳልጣላት አልውልም ነበር፡፡ ነገር ግን ለአንድ ቀን ውሎ ያህል
እንኳ መጨከን ስለማልችል በማግስቱ ተመልሼ አሷው ሥር እገኛለሁ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ በተለይ በዚህ በአዲሱ ጠባዬ በጣም ትናደድ ስለነበር በነጋታው ስንገናኝ ምን እየሆንኩ እንደሆነ ትጠይቀኝ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን ለምዳው ይሁን ወይም በውጤቱ ተበሳጭቶ የሚያደርገው ነው ብላ ገምታ እንደሆን ባይገባኝም፣ ጠዋትም ሆነ ማታ ስንገናኝ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በሳቅና ደስታ ትቀበለኛለች፡፡ የማይደርስ የለምና ያ የፈራነው የመለያያችን ቀን ደረሰ፡፡ አልማዝ በማዕረግ ስታለፍ እኔ ግን በውርደት ከግቢው ተባረርኩ፡፡ የዩንቨርስቲ ሕይወቴ በአሳዛኝ ሁኔታ ተደመደመ። የሆነው ቢሆን ግን እኔን ከሁሉ በላይ ሰላም የነሳኝ ትምህርቴን መቀጠል አለመቻሌ ሳይሆን ከአልማዝ የመለየቴ ነገር ነበር፡፡ አልማዝ ለእኔ በጨለማ ውስጥ ሆና ብርሀን የምትለግሰኝ ደማቅ ሻማዬ ነበረች፡፡ እየቀለጠች ልትጠፋ ጭል ጭል ማለት ብትጀምርም አማራጭ ስላልነበረኝ በጨለማ ውስጥ ቢሆንም ጉዞዬን ተያያዝኩት፡፡ እኔ ከተባረርኩ በኋላ ከአልማዝ ጋር ያለኝ ግንኙነት በደብዳቤ ብቻ እየሆነ መጣ፡፡ ቤተሰቦቼ ጋ አዲስ አበባ ውስጥ እየኖርኩ ሥራ ማፈላለጉን ተያያዝኩት፡፡ እንደዕድልም ቀንቶኝ የአስተማሪነት ሥራ አግኝቼ ወደ አፋር አሳዒይታ ከተማ ሄድኩ፡፡ ከአሳኢይታ አለማያ ድረስ ያለው ርቀትም ያው ከአዲስ አበባ ዓለማያ እንደአለው ርቀት በመሆኑ እንደልብ ሄድ ብሎ ከአልማዝ ጋር ለመገናኘት አዳጋች ሆነብኝ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ከግቢው የወጣሁበት
🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_6
"እና ምንድነው? ምን ተፈጠረ?'' አለኝ፡፡ “አልማዝ መሞቷን እስካልነገርከኝ ድረስ ወደ ሚቀጥለው ገፅ ማለፍ አልችልም፤ ግዝት አለበት' አልኩት፡፡ እሱም እንደመሳቅ እያለ! "አቶ አማረ፤ እኔ ለጥያቄዎ በሙሉ መልስ የሚሆንዎትን ዲያሬ ሰጥቼዎታለሁ፡፡ ማንበብና አለማንበብ የእርስዎ የራስዎ ምርጫና ውሳኔ ነው" ብሎ ጥሎኝ ወጣ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች አመነታሁ፡፡ ፊርማውን ትኩር ብዬ አየሁት፤ በእርግጠኝነት የእሷ ፊርማ ነው፡፡ ነፍሴ ተጨነቀች፡ ትንሽ ቆየት ብዬ ግን ራሴን ማታለል ካልሆነ በስተቀር አልማዝ እንደሆነ ሞታለች የሚለውን የራሴን ያልተረጋገጠ ድምዳሜ ይዤ ንባቤን ቀጠልኩ፡፡ "ዓለማያ የደረስኩት ወደ አሥር ሰዓት ገደማ ነበር፡፡ ከጭናክሰን ይዞን የተነሳው አውቶቡስ ቀርፋፋ ስለነበርና ሐረርና ጅጅጋ ላይ ብዙ ስለቆምን ከሚጠበቀው በላይ ዘግይተናል፡፡ ጭናክሰን ተወልጄ ያደግሁባት፣ ከጅጅጋ ከተማ በግምት ሃያ አምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች፡፡ ወይናደጋ የአየር ጠባይ ያላት ሲሆን አብዛኛው ህዝቧ በግብርናና በንግድ ሥራ ይተዳደራል፡፡ የወታደር ካምፕ ያለባት በመሆኗ በተለይ የወታደሩ ቁጥር ብዙ ነው:: በከተማዋ ዙሪያ ከሁሉ በላይ ጫትና በቆሎ በብዛት ይመረታል፡፡ ከጭናክሰን ዓለማያ ድረስ ያለው ርቀት ወደ መቶ ሀምሳ ኪ.ሜ ይጠጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ ዓለማያ ከጭናክሰን ቅርብ ስለሆነ ቢያንስ አለፍ አለፍ እያልኩ ወላጆቼን ለመጠየቅ እችላለሁ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ትምህርት ቤት በተዘጋበት ወቅት አዲስ አበባ አጎቴ ጋ ለእረፍት በሄድኩበት ጊዜ ዓለማያን አልፌ የሄድኩ ቢሆንም ዩንቨርስቲው እዚያው አካባቢ ይሆናል ብዬ ስላልገመትኩ እንደዚህ ቅርብ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ እንዲህ ቅርብ መሆኑን ባውቅ ኖሮ ጠዋት ጉዞ ስጀምር ያፈሰስኩትን ያህል እምባ በሸኚዎቼ ፊት ባላፈሰስኩ ነበር፡፡ የጎረቤት ሰዎች ያደረጉልኝን አሸኛኘት ሳስታውሰው ለምን ያንን ያህል አዝነው በብዛት ሊሸኙኝ እንደወጡ ገርሞኛል፡፡ እኛ ወጣቶቹ እንኳን ላይፈረድብን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ ትልልቅ ሰዎች ግን አለማያንና ቅርበቱን ያውቁታልና ለምን እንደዚያ እንዳለቀሱ ሳስብ
መገረሜ አልቀረም፡፡ ህፃን አዋቂው ሁሉ ያለቅስ የነበረው እዚህ ቅርብ አካባቢ እንደምሄድ ሳይሆን በጣም ሩቅ አገር ወይም ወደ ጦር ሜዳ እንደሚሄድ ዘማት አድርጎኝ ነበር። እንደሚመስለኝ ሰፈር ውስጥ ይበን ተወዳጅ ልጅ ስለነበርኩና በሁሉም የምላላክ በመሆኔ አብዛኛው ሰው ይወደኝ ስለነበር ሊሆን ይችላል:: በሌላ በኩል ደግሞ ከተማዋ ትንሽ ስለሆነችና ሁሉም ሰው ቀረቤታ ይችላል በለለግዚያ ጋር ግጭት በተነሳ ከበር ታራ ወደ ጦር ሜዳ ስላለውናንዲህ መያለቀሱ መሸኘት የተለመደ ስላካባናና ሰው መለየቱን እንጂ ሲሄድ እንዲተለውን የመጨረሻ ውጤት ልዩነት ሳያገናዝብ በለመደው መልኩ አልቅሶም ሊሆን ይችላል በማለት አሰብኩ። ብዙ ጊዜ ከወላጆቹ ጋር Eና ሰርቻለሁ:: አብዛኛውን ጊዜ ልብስ ሲገዛልኝ እመጣ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባና ሐረር ቀጥሎ ያየሁት ትልቁ ከተማ ገሀል ነው። ከተማው ትላልቅ ፎቅ አይኑረው እንጂ ቆንጆ ከተማ ነው:: ሕዝቦቹም እንደጭናክሰን ሰዎች ኮ ና ግባቢዎች ናቸው፡፡ የአካባቢያችን ሕዝብ ዛሬ ያገኘውን ተካፍሎ መብላት እንጂ ለነገ ብዙም አይጨነቅም፡፡ የሰን ሰው ከዚህ የተለየ መሆኑን እናታው ንሬኛለች:: ሚስጢሩን በሆዱ ይይዛል? ያለውን ገንዘብ የሚያጠፋው ለብቻው ነው፣ በዚህ ላይ ለነገ እግዜር ያውቃል የሚለው አባባል እዚያ አይሰራም ብላኛለች፡፡ እንዲያውም ከዚሁ ጋር ተያይዘ አንድ የሚያስቅ ነገር ነግራኛለች፡፡ ሐረር ላይ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ አንድ ሱማሌ ወደ አዲሰ አበባ ይቀየርና ቀደም ሲል ሐረር ውስጥ የነበረና የሸዋ ተወላጅ ከሆነ ጓደኛው ቤት ሄዶ በእንግድነት ያርፋል፡፡ ያ ጓደኛው ሹፌር ስለነበር ከክፍለ ሀገር አራት ኩንታል ጤፍ በርካሽ ገዝቶ እንደመጣ ለዚሁ ሱማሌ ጓደኛው ይነግረዋል:: ይህንን የሰማው ሱማሌ በመደነቅ፧ "ታዲያ የፈለገ ቢረክስ ይህ ሁላ ጤፍ ምን ያደርግልሀል? ልትሸጠው ነው ?'' ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ባለቤቱም የእነሱን ባህል ያውቃልና በጓደኛው ጥያቄ ሳይገረም፤ "ለምን እሸጠዋለሁ? ክረምት እየገባ ስለሆነ በኋላ ጤፍ ሊወደድ ይችላል፡፡ አሁን ከገዛሁ ለዓመት ይበቃኛል" በማለት ይመልስለታል፡፡ ሱማሌውም አሁንም በመገረም ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ፤ "ያባው! አሊያ አንተ አላህ ሆንክ ወይስ ከአላህ ጋር ተማክረሀል? እንዴት አንድ ዓመት ሙሉ በሕይወት እንደምትኖር እርግጠኛ ሆንክ? አለው ብላ ያጫወተችን አይረሳኝም፣
ወደ ዓለማያ ስንሄድ ሌላዋ መንገድ ላይ ያየኋት ከተማ ሐረር ነች፡፡ ሐረር ነፍስ ካወቅሁ በኋላ ወደ አራት ጊዜ መጥቼባታለሁ። ወደዚህ ስመጣ ታዲያ ሁልጊዜ በመንገድ ላይ የማያቸው የባቢሌ የቆሙ ድንጋዮች ምንጊዜም ከሕሊናዬ አይጠፉም፡፡ የድንጋዮቹን ቅርፅና አቋቋም ያየ ሰው እውነት በተፈጥሮ የተገኘ ነው ብሎ ለመናገር ይከብደዋል። በጥሩ ጠራቢ ተጠርበው የተኮለኮሉ ሐውልቶችን ነው የሚመስሉት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አባቴ ሁል ጊዜ ባቢሌ ስንደርስ ኦቾሎኒ ሳይገዛልኝ አያልፍም:: እኔም ዛሬ አውቶብሱን ለቁርስ እንዳቆሙልን አንድ ኪሎ ኦቾሎኒ ገዝቼ እየበላሁ ሐረር ደረስኩ:: ሌላው ሐረርን ሳስብ የማልረሳው ቆንጆዎቹን የሀደሬ ሴቶችንና ሰፈራቸው ጀጎልን ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ እየተጓዝኩ ዓለማያ ደረስኩ፡፡ ግቢ እንደገባሁም በቀጥታ ወደ ሬጅስትራር ቢሮ ሄጄ ተመዝግቤ ከጨረስኩ በኋላ ቁልፍ ተቀብዬ ወደ መኖሪያ ክፍሌ አመራሁ፡፡ ከእኔ ጋር አምስት ሴቶች አንድ ላይ አንድ ክፍል ውስጥ የተመደብን ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ገና ሳያት ዓይኔ ያረፈባትና ለጓደኝነት የመረጥኳት ኤልሳቤጥ ነበረች፡፡ ኤልሳቤጥ የአዲስ አበባ ልጅ ስትሆን መልኳም ሆነ አለባበሷ እጅግ በጣም ማራኪ ነው፡፡ ከሌሎቹም ይልቅ ፈጥና የተግባባችው __ እኔን ስለነበር እርሷም እንደኔው ለጓደኝነት እንደመረጠችኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ከሰው ጋር ፈጥኖ መግባባት ላይ ችግር ያለብኝ ቢሆንም ኤልሳቤጥ ግን ተግባቢና ተጫዋች ስለነበረች ለመግባባት ጊዜ አልፈጀባትም፡፡ ልክ ብዙ ጊዜያትን አብረው እንዳሳለፉ ጓደኛሞች ማታም የቆጥ የባጡን ስናወራ አመሸተን ነው የተኛነው፡፡ እኔ በአንድ ቤት ውስጥ ከብዙ ሰዎች ጋር ስተኛ የመጀመሪያዬ በመሆኑ ልብሴን አውልቄ ለመተኛት ሁሉም እስኪተኙልኝ መጠበቅ ነበረብኝ:: ኤልሳቤጥ ግን እንዲህ ሁላችንም በተሰበሰብንበት አፏ ሥራውን ሳይፈታ ልብሷን አወላልቃና የሌሊት ልብሷን ለውጣ አልጋዋ ውስጥ ገባች:: እርግጥ ቀሚሷ፣ የጡት መያዢያዋና የሌሊት ልብሷ ሁሉ በውድ ገንዘብ እንደተገዛ የሚያስታውቅና የሚያምር ስለነበር እኛ እያለን ብታወልቀው እኛን ያስቀና እንደሆነ እንጂ እሷን የሚያሳፍር አልነበረም:: በዚህ ላይ የሰውነቷ ቅርፅና ጠቆር የገላዋ ቀለም እጅግ ውብ ነበር፡፡ እርግጥ እኛ አካባቢ የተለያዩ ልብሶች በኮንትሮባንድ ከሱማሊያ ስለሚገቡ እኔም ብሆን የለበስኩት ልብስ ለክፉ የሚሰጥ ባይሆንም እንደእሷ ግን በሰዎች መኻል ልብሴን ለማወላለቅ ድፍረቱን እንዲህ በቀላሉ ላገኘው የምችል አልነበርኩም፡፡''
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
================
አለማየሁ በቀጠሮው መሰረት ከአላዛርና አለማየሁ ጋር ከተገናኘ በኋላ ‹‹እሺ ባላና ሚስቶች ለምንድነው የፈለጋችሁኝ….?ለጥሩ ነገር እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡››ሲል የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ..አንተ ንገረው አንቺ ንገሪው እየተባባሉ የሚገባበዙ ይመስላል አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በሚቀጥለው ሳምንት ሁሴን እንደሚመጣ ታውቃለህ አይደል?››
ያልጠበቀውን ርዕስ ነው ያነሳበት‹‹ትክክለኛውን ቀን አላውቅም እንጂ እንደሚመጣ አዎ በቀደም ደውሎልኝ ነበር..››
‹‹ጥሩ እንግዲህ ..እናቱም አባቱም እንደሞቱ ታውቃለህ…..እዚህ ሌላ ዘመድ የለውም ..ከፋም ለማም የልጅነት ጓደኞቹና የቅርቡ ሰዎች እኛ ሶስታችን ነን››
በውስጡ ‹‹የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች›› የሚለውን ተረት እየተረተበት ‹‹አዎ ትክክል››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እና እንዴት እንቀበለው የሚለውን ለመነጋገር ነው፡፡››
‹‹በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ይሄ የድሮ ጓደኛችንን የመቀበል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እኛም መልሰን ለአመታት ተራርቀን ከቆየንበት ለመቀራረብና መልሰን ጓደኝነታችንን ለማደስ ያግዘናል….››አለ
…እንደዛ ሲል በውስጡ ያለው ከአላዛር ወይም ከሁሴን ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ድሮ ጓፈደኛነታችው የመመለስ ጉጉት ኖሮት አይደለም..ከዛ ይልቅ ስለሰሎሜ በውስጡ እያሰበ ነው፡፡
‹‹በጥሩ ሁኔታ ብንቀበለው ደስ ይለኛል…እኔ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ….ዝግጅቱን እኔ ቤት ማድረግ እንችላለን››አለ…
‹‹አይ ከአንተ ቤት የእኛ ቤት ይሻል ይመስለኛል….ማለት የወንደላጤን ቤት ማድመቅ ይከብዳል›› ሰሎሜ ነች ተናጋሪዋ፡
‹‹እሺ እንዳልሽ…እኔ ቤት ብንቀበለው በዛውም የራሱን ነገር እስከሚያመቻች አኔ ጋር መቆየት ይችላል ብዬ ነው፡፡››
‹‹እኛ ጋርስ ለመቆየት ምን ይከለክለዋል…?እቤታችን እንደሆነ እንኳን እሱንና አንተም ብትጨመር በቂ ክፍት ክፍሎች አሉን ….እንደምታውቀው እዛ አፓርታማ ቤት ውስጥ እኔና እሱ ብቻ ነን....ልጅ የለን ምን የለን››
በሰሎሜ ንግግር አላዛር ሽምቅቅ አለ..ሆነ ብላ አስባበት የተናገረችው እንደሆነ ያውቃል….ግን ዋጥ አድርጎ በትዕግስት ከማሳለፍ ውጭ ምርጫ እንደሌለው ያውቃል፣ያደረገውም እንደዛ ነው፡፡
አለማየሁ‹‹በቃ እሺ እጅ ሰጥቼለው››ሲል በሀሳባቸው ተስማማ፡፡
‹‹ጥሩ በቃ …እንደዛ ከሆነ በፊታችን እሁድ ቤት ናና ስለዝርዝሩ እንነጋገርበታለን››
‹‹ጥሩ..እንደውም በሰበቡ ቤታችሁን አያለሁ››
‹‹አዎ ››
ከዛ በኃላ ብዙም ያወሩት ነገረ የለም ፡፡ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡
‹‹አላዛር እና ሰሎሜ በአንድ መኪና ገብተው ወደቤታቸው እየተጓዙ ወሬ ጀመሩ‹‹ግን እርግጠኛ ነህ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ምኑን?››
‹‹ማለቴ የሁሴን እኛ ቤት ማረፍ….ነው ወይስ አንድ ሁለት ቀን እኛ ጋር ካደረ በኃላ ሌላ ማረፊያ ፈልግ ልንለወው ነው፡?››
‹‹ለምን …አንቺን ካልደበረሽ እቤታቸን ሰፊ ነው…ሁሴን የማናውቀው ሰው አይደለም ….ለሁለታችንም ቅርብ የሆነ ሰው ነው፡፡››
‹‹ገባኝ….በደንብ አስበህበታል ወይ ለማለት ነው…?.እኔማ ደስ ይለኛል..ግን እወቅ እንደነገረኝ ከሆነ እስከሶስት ወር ሊቆይ ይችላል፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ታውቂያለሽ የሆነ የእኛ የምንለው ሰው አብሮን እንዲኖር እንዴት እፈልግ እንደነበረ…እህቶቼም ሁለቱም ስላገቡ ወደቤታችን ላመጣቸው አልቻልኩም…የአንቺም እናት አሻፈረኝ ብላለች..እስኪ አሁን በጓደኛችን እንሞክረው፡፡››
‹‹እማዬ እኮ ከእናንተ ጋር አልኖርም አላለችም..እሷ ያለችው ልጅ ስትወልዱ እሱን ለማሳደግ መጣለሁ…አሁን ግን መጥቼ የእናንተ ሞግዚት መሆን አልፈልግም ነው ያለችው››።
‹‹እና በሞግዚት ኑሪ እንጂ ሞግዚት ሁኚን መች አልናት?››
‹‹ተወው አሁን… ለምን የማይሆን ጭቅጭቅ ውስጥ እንገባለን…ቁርጥ አድርጋ አቋሟን አሳውቃለች…መውለድ ስንችል ትመጣለች››
‹‹ይሁን እሺ… ለማንኛውም ስለሁሴን አትጨነቂ… ሁኔታዎች ካልተመቹት እኮ እራሱ አማራጭ ይፈልጋል፡፡››በማለት የተጣመመውን ርእስ እንደምንም ብሎ አቃናው፡፡
‹‹ጥሩ..ለእኛም ከብቸኝነት ጋር ከመታገል በተወሰነ መንገድ ይታደገናል…›› ስትል መለሰች፡፡
‹‹እኔም እሱን አስቤ ነው ››አላት..ግን ሁለቱም ስጋታቸው ሌላ እንደሆነ ግልፅ ነው…ሁሴን ልክ እንደአላዛር ሁሉ የሰሎሜ የልጅነት አፍቃሪዎ እንደሆነ ሁለቱም ያውቃሉ፡፡ለሁለቱም እኩል ጓደኛቸው ቢሆንም ለእሷ ግን በተለየ መልኩ አፍቃሪዋም ጭምር ነው…እና አሁን አንድ ቤት እሱን ጎትቶ ማምጣት ለዛውም አሁን ባልና ሚስቶቹ ባሉበት ሁኔታ ላይ አደጋ እንዳለውና የልታሰበ መዘዝ ሊያመጣ እንደሚችል…ለሁለቱም ግልፅ ነው….እና ሰሎሜ ደጋግማ ስለውሳኔው እርግጠኝነት እየጠየቀችው ያለው..ነገ አንድ ነገር ቢከሰት ኃላፊነቱን እንዲወስድ በማሰብ ነው፡፡
እሷ ያላወቀችው ግን የእሱን እቅድ ነው…እሱ ሁሴን ወደቤት እንዲመጣ ሲወስን መዘዙንም አስቦና አስልቶ ነው፡፡ምን አልባት የጀመረው የህክምና ጉዳይ ባይሳካለት ሊያደርግ የሚችለውን እቅድ አስቦና አስልቶ ጨርሷል..በቃ እራስ ወዳድ መሆን እንደሌለበት ገብቶታል…እየወደደም ቢሆን ከሰሎሜን ህይወት ሾልኳ መውጣት እንዳለበት ወስኗል.. ከህይወቱ ሲሸኛት ግን በተሰበረ ልብ ሆና ስነልቦናዋ ተጎድቶ መሆን እንደሌለበትም ነው የሚያምነው..ለእሱ መሆን ካልቻለች ከሁለት የልጅነት ጓደኞቾና ከልብ ከሚያፈቅሯት መቼም ቢሆን ሊጎዶት ለማይችሉት ለአንዱ ሊያስረክባት ነው ያሰበው….ለዛም ጥሪጊያ መንገድ ለመፍጠር ሁሴን በእንግድነት እሱ ቤት ማረፍ እንዳለበት ማድረግ እንዳለበት ተሰምቶታል፡፡፡ያንን ካደረገ ደግሞ አለማየሁም በተደጋጋሚ ወደእሱ ቤት ለመመላለስና ከሰሎሜ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ የመገናኘት እድል ይኖራዋል፣በሂደት ከሁለት አንዱ ከእሷ ጋር በተሻለ መቀራረብ ይፈጥሩና ልቧን ማግኘት ይችሉ ይሆናል….ከዛ አንዱ ያገኛታል ማለት ነው፡፡ከዛ እሱ ሀዘኑን ለብቻው ያዝናል..ማጣቱን በማስታመም ቀሪ የብቸኝነት ዘመኑን ይገፋል…….፡፡እግዚያብሄር ቀንቶት ከተፈወሰ ደግሞ በቃ ምን ይፈልጋል…እና አሁን እያደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ነው፡፡ይሄ ነው ሰሎሜን ያልገባት፡፡
ይሄ ጉዳይ ደግሞ ከሰሎሜ ይልቅ አለማየሁን ነው ፍፅም ግራ ያጋባው‹‹ሰውዬው ምን እየሰራ ነው?››የሚለው ሀሳብ በውስጡ መጉላላት የጀመረው ገና ከእነሱ እንደተለየ ነው፡፡እና ደግሞ አልተመቸውም….በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ወሳኝ ወቅት የሁሴን ወደሀገር ቤት ተመልሶ መምጣት ደስ አላሰኘውም ነበር፡፡፡በእሱ እምነት አላዛር ካልተሳካለት ቀጥታ ሰሎሜን የእሱ የማድረጉን ትግል በብቸኝነት ለመወጣት ነበር ዕቅዱም ምኞቱም..ሁሴን ደውሎ እንደሚመጣ ከነገረው በኋላ ግን ሌላ ተፋላሚ እየመጣበት እንደሆነ ነው ወዲያው የገባው…እንደውም መምጣቱ እራሱ ያጋጣሚ ነገር ሳይሆን ሆነ ብሎ የታሰበበት እንደሆነ ነው የሚጠረጥረው…ሰሎሜ አላዛርን ከማግባቷ በፊት ከእሱ ጋር ለረጅም ጊዜ እንደምትደዋወል ነግራዋለች..በእሷ እና በባሏ መካከል ያለውን ቦንብ ሚስጥር ለእሱ በተገናኙበት በመጀመሪያው ቀን ከነገረችው…ለረጅም ጊዜ ስትደዋወል ለነበረው ለዛውም ከባህር ማዶ ላለው ሁሴን ላትነግረው የምትችልበት ምክንያት ምንም እየታየው አይደለም…እንደጠረጠረው ነግራው ከሆነ ደግሞ በተለይ የሰሞኑን ግር ግር አብራርታለት ከሆነ የሆነ ምክንያት ፈጥሮ አጋጣሚውን ለመጠቀም እንደመጣ ነው የሚያምነው..እና ከእሱ ጋር
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
:
:
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
‹‹እሺ ቻው ሁሴን…››ስልኩን ዘጋ፡፡ፈጽሞ ያልጠበቀው ነገር ነው፡፡ድብልቅልቅ የሆነ የሚረብሽ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው፡፡ደስታም መረበሽም ….አሁንም ሶስቱም አንድ ላይ ተገናኝተው ሰሎሜን ከበው ሲቀመጡ ምን እንደሚሰማቸውና ምንስ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አልቻለም፡፡
እርግጥ አሁን እንደድሮው አይደለም ሰሎሜ የአላዛር ህጋዊ ሚስት ሆናለች፡፡ግን ደግሞ በመሀከላቸው ያለው ሸለቆ ስምጥና እሩቅ ነው፡፡እና አላዛር ከበሽታው ማገገም ተስኖት ሁለቱ ከተፋቱ ሰሎሜን መልሶ ለማግኘት ሁለቱ ይፎካከራሉ ማለት ነው…አለማየሁና ሁሴን…..‹‹ምን አልባት እሱ እስካሁን ባለበት ሀገር አንዷን ወዶና አጭቶ ወይንም አግብቶ ሊሆን ይችላል… እንደዛ ከሆነ ግልግል ››ሲል አሰበና እራሱን እንደምንም ለማረጋጋት ጥረት ማድረግ ጀመረ፡፡
የሁሴንን ድምፅ በስልክ ከሰማ በኃላ የአላዛርን የህክምና ውጤት ለማወቅ በጣም ነው የጓጓው…ደውሎ ሊጠይቀው አስበና ደግሞ ምን ብሎ እንደሚጠይቀው ስላልገባው ሀሳቡን ሰረዘ፡፡
…‹‹እራሱን ወይም ልቡን አሞት ቢሆን ኖሮ በቀላሉ ደውዬ የድሮ ጎደኛዬ ልብህን እንዴት ሆንክ ..?አሁን ምን ይሰማሀል…?ምርመራው ምን ውጤት አስገኘ….?ምናምን እያልኩ በዝርዝር እጠይቀው ነበር፡፡››ሲል ተነጫነጨ…ድንገት ብልጭ አለለትና ከተኛበት አልጋ ተነሳና ቁጭ አለ.. ስልኩን ከተቀመጠበት አነሳና ዳታ አበራ…..
ስንፈተ ወሲብ ብሎ ሰርች ሲያደርግ ብዛት ያላቸው መረጃዎች ተዘረገፉለት…የመጀመሪያውን ከፈተ፡፡
ስንፈተ ወሲብ ወይም የወንድ ብልት አለመቆም ችግር ለወንዶች አሳሳቢ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ይህ ችግር የወንዶችን በራስ መተማመን የሚቀንስና ፍርሃት የሚያሳድር ነው። ስንፈተ ወሲብ ማለት በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የወንድ ልጅ ብልት በደንብ መቆም አለመቻል ነው።
ንባቡን አቆመና ማሰብ ጀመረ..‹‹የእሱ ግን ያለመቆም ችግር ነው እንዴ..?ነው ወይስ ሙሉ በሙሉ ፍላጎት ማጣት…?.››መረጃው ስለሌለው ማሰቡን አቁሞ ንባቡን ቀጠለ፡፡
ስንፈተ ወሲብን ማከም የምንችልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።
• ስኳር የበዛባቸው ምግቦች የወሲብ መነሳሳትን ወይም የወሲብ ፍላጎትን ሊቀንሱ ስለሚችሉ ብዙ ስኳርንና ከፍተኛ ካርቦሀይድሬት ያላቸውን ምግቦች ማስወገድ።
• የኮሌስትሮል መጠናችን ጤነኛ በሚባለው ደረጃ መቆጣጠር።
• የደም ፍሰትን ለመጨመር ከፍተኛ አሚኖ አሲድ ያላችው ምግቦችን መጠቀም።
• በዚንክ የበለፀጉ ምግቦችን መጠቀም እንዲሁም የቴስቴስትሮን ሆርሞን እንዲመረት የሚረዱ ሰፕልመንቶችን መውሰድ።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች ቀለል ያለ የስንፈተ ወሲብ ችግር ላለባቸው ሰዎች እንደመፍትሄ የተቀመጠ ሲሆን ከዛ ከፍ ያለና አሳሳቢ የሆነ ስንፈተ ወሲብ ችግር ካለብዎ የሜዲካል ህክምና ማግኘት እንደ ኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክም ማግኘት ይገባል ይላል፡፡የኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክምና የታካሚው ብልት ውግት አድርጎ በመያዝ ዝቅተኛ ኢንተንሲቲ ባለው ግፊት ሞገድ ወደ 4000 ሾክ በወንዱ ብልት 4 ቦታ ላይ የብልት የደምስሮችን ለማነቃቃት ይሰጣል። በዚህ ህክምና ታካሚው በሳምንት ከ1-2 ጊዜ በተከታታይ ለ12 ሳምንት ህክምናውን መውሰድ አለበት።
የሚያነበው ነገር ሁሉ ምንም እየገባው አይደለም…ልክ ያንቀላፋ ያለን ልብ በኤልኬትሪክ ሾክ መንጭቆ እንደማስነሳት አይነት ህክምና ይሆን እንዴ..?ልክ እንደዛ በብልት ዙሪያ የኤሌክትሪክ ንዝረት በመልቀቅ ተመንጭቆ እንዲነሳና እንዲያቆም ማድረግ ይሆን እንዴ….?ተመንጭቆ ተነስቶ አልተኛም ቢልስ?››በራሱ ጥያቄ እራሱ ሳቀ፡፡
እግዚያብሄር ከዚህ አይነት በሽታ አንዲሰውረው በመፀለይ ስልኩን አጠፋና መልሶ ተኛ፡፡
በሶስተኛው ቀን ከስራ ወደቤት እየተመለሰ መንገድ ላይ እያለ አላዛር ደወለለት፡፡
‹‹ሄሎ አላዛር እንዴት ነህ?››
‹‹ምንም አልል ሰላም ነኝ››
ምን ሊነግረው እንደደወለለት ለማወቅ በከፍተኛ ጉጉት ‹‹አይ ጥሩ ነው…ምነው ፈለከኝ….?.››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ …ነገ ማታ እራት ብጋብዝህ ብዬ አሰብኩ››
‹‹ይቻላል….የትና በስንት ሰዓት እንደምንገኛኝ ንገረኝ..እገኛለሁ››
‹‹ጥሩ …ቴክስት አደርግልሀለው››
‹‹እሺ እጠብቃለሁ….ግን ሰላም ነው አይደል…?ማለቴ የተነጋገርነው ህክምና በተመለከተ አዲስ ነገር አለ?››በመከራና በጭንቀት ጥያቄውን አፈረጠው…
እስከነገ እንዴት ብሎ አምቆ ይያዘው…?‹‹የእራት ግብዣው ሙሉ በሙሉ ተፈወስኩ ብሎ የምስራች ሊለኝ ቢሆንስ?.››ሲል አሰበና ተጨነቀ፡፡ የእሱ የምስራች ማለት ለእሱ በተዘዋወሪ መርዶ ነው….
‹‹አሌክስ ያው በተነጋገርነው መሰረት ቀናቶች አሉኝ አይደል?››
‹‹አዎ ..20 ቀን አለህ…እንዲሁ ሂደቱ እንዴት እየሄደልህ ነው የሚለውን ለማወቅ ነው››
‹‹ለጊዜው ሁሉ ነገር በሂደት ላይ ስላለ መጨራሻውን በእርግጠኝነት አላውቅም ..ሀኪሞቹም የሚያውቁ አይመስለኝም››
‹‹ጥሩ ..በእኔ በኩል ላግዝህ የምትፈልገው ነገር ካለ ሁሉ ጊዜ አለሁልህ…አሁን መራራቃችንን ሳይሆን የልጅነት ቅርበታችንን አስበህ ምንም ነገር ልትጠይቀኝ ትችላለህ….ይሄ ነገር ተስተካክሎ ሁለት የልጅነት ጓደኞቼ ደስተኛ የሆነ ትዳራቸውን እንዲያስቀጥሉ እፈልጋለው…ሁለታችሁንም ስል ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አደርጋለሁ››አለው…ንግግሩ ለራሱ ጆሮ እንግዳ ስሜት ነው የፈጠረበት፡፡
‹‹በእውነት አሌክስ ይህንን መስማቴ ደስ ብሎኛል…በቀደም ቢሮህ ተገናኝተን በጉዳዩ ላይ ስንወያይ ንግግርህ ጨከን ያለ ነበር…ይቅርታ አድርግልኝና እንደውም…የሄ ልጅ የእኛን መለያየት ይፈልጋል እንዴ?ብዬ እንዳስብ ነበር ያደረከኝ..ያንን ስሜቴን ደግሞ በእለቱ ነግሬሀለው››ሲል እውነቱን አፍርጦ ነገረው፡፡
እንደዛ ሲለው ዛሬም መደንገጡ አልቀረም….ያን ያህል እስከሚያስታውቅበት እንደዘባረቀ አልተሰማውም ነበር…..ማስተባበሉን ቀጠለ‹‹እንዴ ምን ነካህ ?ለምንድነው እንድትለያዩ የምፈልገው?››
‹‹ያው ታውቃለህ አይደል…..?››
‹‹ምኑን ነው የማውቀው?››
‹‹ያው ልጅ ሆነን ጀምሮ ሶስታችንም ነበር የምናፈቅራት››
‹‹ልጅ ሆነን ነበራ ››
‹‹አሁን እንደውም በይበልጥ ውብና ማራኪ ሆናለች እኮ…እንደውም በበለጠ በፍቅር የምታማልለው አሁን ነው…ማለቴ ስሜቱን በራሴ አውቀዋለው..በየጊዜው ትንሽ ባደገችና እድሜ በጨመረች ቁጥር ውብና ማሪኪ እየሆነች እኔም አምርሬ እያፈቀርኳት ነው እየሄድኩ ያለሁት››
‹‹አላአዛር…አንተ እኮ እንደዛ ቢሰማህ ሚስትህ ስለሆነች ነው…..እኛን በተመለከተ የምታወራው ግን የልጅነትና ያለፈ ታሪክ ነው››
‹‹ለማንኛውም እንደዛ ስላሰብኩህ ይቅርታ…በእውነት ያንተን እገዛና ማበረታቻ በጣም ነው የሚያስፈልገኝ…በዚህ ጉዳይ ላይ ከአንተ በተሻለ የሚረዳኝና የሚያግዘኝ ሰው እደሌለ እኔም አምናለው››
‹‹አዎ እንደዛ ጥሩ ነው..በል አሁን ቻው …ነገ እንገናኛለን፡፡››
‹‹.ቻው እሺ ..አመሰግናለሁ፡፡››
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን
===================
ቀለል ያሉ ሌሎች ጫወታዎችን ሲጫወቱ አመሹና እቤቷ ድረስ ሸኝቷት በብዙ ነገር ተወስውሶ ወደቤት ተመልሶ ገባና የወንደላጤ ቤቱን ከፍቶ ባዶ ቤት ውስጥ ባዶ አልጋ ላይ ብቻውን ተኝቶ ማሰላሰል ጀመረ፡፡
ሰሎሜ ደጋግማ እንደጠየቀችው..ከተማውንም ሆነ ሁሉንም ጓደኞቹን ድንገት ጣጥሎ ፖሊስ ማሰልጠኛ የገባበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው..በቂና ጠንካራ ምክንያት ነበረው::
አለማየው የፈራረሰና ጣሪያው የዛገ ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ ከእናትና አባቱ እና ከታናሽ ወንድሙ እና የሴት አያቱ ጋር የድህነት ግን ደግሞ ጣፋጭ ሳቅና ደስታ የሞላበት ኑሮ ይኖር ነበር፡፡ነበር እንዲህ ህልም ሆኖ አይን ጨፍኖ ሲገልጡ እንደሚበን ማሰብ ይከብደል፡፡ያ ሞቀትና የደመቀ… በፍቅር ሀውልት የተገናባ የቤተሰብ ትስስር በአንድ ወር ውስጥ ነው ድርምስምሱ ወጥቶ የፈረሰው፡፡በወቅቱ እሱ የ13 አመት ወጣት እና የ7 ክፍል ተማሪ ነበር፡፡ድንገት አባትዬው ታመምኩ አለና አልጋ ያዘ፡፡በሶስተኛው ቀን ሰፈር ያለ ጤና ጣቢያ ወሰዱት ፡፡አንድ ቀን አድሮ እስከወዲያኛው አሸለበ፡፡ ያልተጠበቀ ስለነበረ ሁኔታው ጠቅላላ ለቤተሰቡ እንደመቅሰፍት ነበር ፡፡በተለይ ለእናቱ…፡፡አባትዬው በሞተ በማግስቱ ተቀበረ፡፡ከቀብር መልስ እናትዬው ወደ ድንኳን ውስጥ ገብታ በተነጠፈላት የሀዘንተኛ ፍራሽ ላይ ተቀምጣ ሊያስተዛዝኗት የመጣውን የሩቅም ሆነ የቅርብ እንግዶችን በመቀበል ፋንታ ወደቤት ገብታ ከባሏ ጋር ትተኛበት የነበረበት አልጋዋ ላይ ገብታ ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡.በሶስተኛው ቀን እስትንፋሷ በውስጧ አልነበረም…፡፡ጉድ ተባለ..፡፡ፍቅር እስከመቃብር….ማለት ይሄ ነው ተባለ…፡፡
የአለማየሁና የወንድሙ እጣ ፋንታ ግን በደካማና እድሜዋ በጋፋ ተጦሪ አያቱ እጅ ነበር የወደቀው፡፡፡ድሮም የድህነት መቀመቅ ላይ የነበረ ቤተሰብ ውሉ የጠፋበት ሆነ፡፡ ምርጫ አልነበረም፡፡አለማየሁና ታናሹ ለመለያየት ተገደዱ፡፡አያትዬው ጎንደር ለሚኖር ሌለኛው ልጃቸው..‹‹ቢያንስ አንደኛውን ልጅ ውሰድልኝ ››ብለው ተማፀኑት..አጎትዬው ታናሹ ይሻለኛል ብለው መረጡና እሱን ወሰዱት፡፡አለማየሁና አያትዬው ቀሩ..፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግድግዳ ሚጋሩት ቀጥሎ ካለው የቀበሌ ቤት የሚኖሩት ሰሎሜና እናትዬው ከጎናቸው ነበሩ፡፡በማፅናናቱም ካላቸው ላይ ቆረስ እያደረጉ በማጉረሱም አልተለዬቸውም ነበር፡፡ከዛ አያትዬው ሁለመናው ጭልምልም ሲልባቸው.የሰሎሜ እናት እቴቴን ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው‹‹ …እኔ በቃኝ፡፡ ለራሴ ማልሆን ሰው የልጅ ልጄን ጠቅመዋለው ብዬ እዚህ አልቀመጥም…፡፡ጭራሽ ሸክም ነው የምሆንበት፡፡አንቺ ለእናቱ ጎደኛዋ ነበርሽ…አለማየሁንም ልክ ከሰሎሜ እኩል አንቺም አሳድገሽዋል ፡፡..ልጅሽ ነው…፡፡አሁንም አንቺው ነሽ ምታጎርሺን.. ስለዚህ እኔ የልጅ ልጄን ላንቺ ጥዬ ወደ ገዳም መሄዴ ነው…ባይሆን እዛ ሄጄ ፀልይልሻለሁ››በማለት አለማየሁን ለሰሎሜ እናት ጥለውት ጠቅልለው ገዳም ገቡ፡፡አለማየሁ ብቻውን ቀረ …፡፡
ከዛ ሁሉ ከሞላ ቤተሰብ አመት ባልሞላ ጊዜ ቀስ በቀስ እየበነኑ ጥለውት በመሄዳ ባዶውን አስቀሩት፡፡ በቃ ባዶውን…፡፡ግን ሰሎሜና እናትዬው ከመጠን በላይ እንዲሰበርና አልፈቀዱለትም፡፡ለሰሎሜም እህት ለእሳቸውም ሁለተኛ ልጅ ሆነ ፡፡በመሀከል የሚያዋስናቸውን ግድግዳ ቀደው የውስጥ ለውስጥ በር አበጁለትና አንደኛውን በር ዘጉት፡፡ሁለት የተለያ ክፍል የነበረው ቤት ሁለት ክፍል ያለው አንድ ቤት ሆነ፡፡
እሱ ከትምህርት ቤት በተረፈው ጊዜ ሰፈር ውስጥ እየተሯሯጠና እየተላላከ በሚያገኘው ብር እራሱን መደጎም ቀጠለ፡፡የሰሎሜ እናት በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የመዝገብ ቤት ሰራተኛ ስለሆኑና ቆሚ ደሞዝ ስላላቸው..ምንም እንኳን የተትረፈረፈ ኑሮ ባይኖራቸውም ለሁለቱ ልጆችና ለእራሳቸው ለለት ጉርስ የሚቸግራቸው አይነት ሰው እልነበሩም…አለማየሁን ከልጃቸው እኩል ለማኖር የእለት ጉርስንና የአመት ልብሱን ለመሸፈን ቸግሯቸው አያውቅም፡፡በዛ ላይ አለማየሁን ከልጅነት ጀምሮ ሚወዱትና ከእናትዬው ጋር ካላቸው ቅርበት የተነሳ ብቸኛ ልጃቸውን ክርስትና የነሳቸው የእሱ እናት ስለሆነች ልጄ ወንድም ይሆናታል በሚል አመለካከት ከልባቸው ነበር የተቀበሉት፡፡በዛ ላይ ከዚህ በፊት ልጃቸው በህይወትና በሞት መካከል ሆና ሆሲፒታል በገባች ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እሷን ለማትረፍ ያደረጉትን ታሪካዊ ድርጊት መቼም አይረሱትም…እናም ደግሞ ለሌላ ለማንም ሰው የማይነግሩት ተጨማሪ ዋና ምክንያትም ነበራቸው፡፡
.ከዛ ቀስ በቀን ከሰሎሜ ጋር ያለውን ግንኙነት እያላላ ከእናትዬውን ግን በወጉና በስርኣቱ በስልክ እየጠየቀ ስልጠናውን ጨርሶ በምክትል መቶ ሀለቅነት ተመረቀ..ከዛ አዲስ አበባ አካባቢ የመመደብ እድል ቢኖረውም በራሱ ምርጫ ድሬደዋ እንዲመድቡት አድርጎ እርቆ ሄደ፡፡ይሄንን ታሪክ ሰሎሜ ሆነች ሌሎች ጓደኞቹ አያውቁም..አይደለም በዛ ጊዜ ዛሬም እንዲህ ነበር ብሎ ሊነግራትና ሊያብራራላት አይችልም….ከባድ ነው፡፡በሀሳብ ሰውነቱ ስለዛለ ለመተኛት ወደ መኝታ ቤቱ ሄዶ …ድንገት ሳያስበው የአላዛር ምስል በአእምሮ ተሰነቀረ፡፡
‹‹አሁን አላዛር ህክምናው ባይሳካለትስ…?ሰሎሜ ወደፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዛ እንድትሄድ መክራታለው ወይስ ምን አደርጋለው….? ፍርድ ቤቱ እንዲፋቱ ከወሰነስ በኋላ ከእሷ ጋር ያለኝ ግንኙነት እንዴት ነው የሚሆነው…?አሁን ሳይቸግረኝ ሳፈቅራት እንደኖርኩና አሁንም እንደማፈቅራት ነገሬታለሁ…እና በቀጣይ ፡፡ ርቃታለሁ ወይስ የበለጠ ከእሷ ጋር ያለኝን ጓደኝነት አጠናክራለሁ….?እና ከዛስ…አሁን ተራው የእኔ ነው አግቢኝ እላታለሁ? ወይስ ?››..እራሱን አመመው፡፡
ስለምንም ነገር ማሰብ አቁሞ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ለመተኛት በመፈለግ የለበሰውን ልብስ አውልቆ ቢጃማ እየቀያየረ ሳለ ስልኩ ድምጽ አሰማ..አነሳውና አየው… መልዕክት ነው፡፡ሰሎሜ ነች የላከችው፡፡
‹‹አሌክሶ ..በሰላም እቤት ገባህ..?››ይላል፡፡
‹‹አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለና መልስ ፅፎ ላከላት‹‹አዎ….ቢራ ቢሮዋ ሰላም ገብቼለሁ?››
ከልጅቷ ጀምሮ በጣም ቀጭን እና በንፋስ ግፊት በአየር ላይ ተንሳፋ የምትበር ስለምትመስል ቢራቢሮ የሚል ቅፅል ስም አላት…ብዙውን ጊዜ እሱ በዚህ ስም ነው የሚጠራት፡፡
‹‹ጥሩ…ደስ የሚል ምሽት ነበር ያሳለፍነው…አመሰግናለሁ››
‹‹እኔም የልጅነት ጊዜዬን ወደኋላ ተመልሼ እንዳስታውስ ስላደረግሺኝ ደስ ቢለኝም የተዳፈነ የልጅነት ፍቅሬን ስለቀሰቀሺብኝ ችግር ላይ ነኝ፡፡››ብሎ ፃፍላና ላከላት፡፡
‹‹አንተ ባለትዳር እኮ ነኝ…ለምን ታሽኮረምመኛለህ?››
‹‹ይቅርታ ምን ላድረግ..?እንደምታውቂው ፍቅር ይሉኝታ ቢስ ስሜት ነው፤ለማንኛውም አላዛርን ሰላም በይልኝ››
‹‹አይ …እራስ ደውለህ ሰላም በለው፤.ሌላ ነገር እንዲያስብ አልፈልግም…በመጀመሪያ ጉዳዩን ስለነገርኩህ እራሱ በጣም ቅር ብሎታል?፡፡››
‹‹አይ ታዲያ ምን ማድረግ ትችይ ነበር..?እስከመቼ ለብቻሽ በጉዳዩ መሰቃየት ትችያለሽ?››
‹‹አየህ አንተ ከልጅነቱ ጀምሮ የምታውቀው ጓደኛው ነህ.. ሁለታችሁም በጋራ የምታውቋቸው በርካታ ሰዎች አሉ ....ይሄንን ጉዳይ አንተ አወቅከው ማለት ሌሎች እሱንና አንተን የሚያውቁ ሰዎችም የማወቅ እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው. .ይሄ ደግሞ ስነልቦናውን ይበልጥ ይጎዳል…..በዛ ላይ እንደምታውቀው የእናንተ የወንዶች ኢጎ ከፍተኛ ነው፡፡››