av12c | Unsorted

Telegram-канал av12c - Arada education office

6896

Subscribe to a channel

Arada education office

የሰኞና ማክሰኞ የመምህራንና ሰራተኞች መድረክ በምንም ሁኔታ ሠው መቅረት የለበትም። ሲሪየስ ነው። የአዳራሽ ዝግጅት ድኮር የተጠበቀ ይሁን አንድም መ/ር እና ሰራተኛ እንዳይቀር። በዚህ መድረክ ያልተገኘ ምክንያቱ ተለይቶ ርምጃ ይወሰዳል። ሰው ተንጠባጥቦ እንዳይቀር። ይህ የሆነበትን ት/ቤት ተጠያቂነት ይኖረዋል። በየደረጃው ያላችሁ ሱፐርቫይዘሮች ለዚህ መድረክ ስኬትአወንታዊ አሥተዋፅኦ አድርጉ። የተግባሩ ሥኬትና ውድቀት በእናንተም ይለካል። መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ።
ሀብታሙ ደረሰ አራዳ ት/ርት ፅ/ቤት ሃላፊ!!

Читать полностью…

Arada education office

22/05/16
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የመንግስት የ2ኛ ደረጃ እና የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የርእሰ-መምህራን ውድድር እና ምደባ ማጠቃለያ 8ቱ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች በተገኙበት ለ84 ርእሰ-መምህራን ገለጻ እና ማብራረያ ተሰጠ፡፡

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 06/05/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሙሉ
የመኪና ግዥ በብድር በመግዛት የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ የተመቻቸ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ የተዘጋጀ ደብዳቤ ሰው በመላክ ከትምህርት ጽ/ቤት እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

የናዝሬት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች 100% ውጤታማ ሁነው እንደሚያልፋ እቅዳቸውን በሚማሩበት ክፍል አስቀምጠው ሲፈተኑ ማየት አስደማሚ ነበር።

Читать полностью…

Arada education office

በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በዛሬው ቀን ለ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሁለቱም ስርዓተ ትምህርት በመንግስትና በግል ት/ቤቶች ሞዴል ፈተና ተሰጥቷል።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 30/04/2016 ዓ.ም ለመንግስት አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ የመጽሃፍት መጠመሪያ ቅጽ መሰረትበመሙላት እና በመጠመር ከከተማ ለድጋፍ እና ክትትል ለሚመጡ ባለሙያዎች እንድትጧቸዉ ስንል እናሳስባለን ፡፡

Читать полностью…

Arada education office

የስልጠና ቀን ፡- እሁድ 05/5/2016
ሰኣት ፡- ጥዋት 2፡30
የስልጠና ቦታ ፡- ትምህርት ቢሮ ካፌ በሚገኘው አዳራሽ
1. በክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመንግስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሬዲዮ ትምህርት ተወካይ /ተጠሪ መምህር ብዛት ከየትምህርት ቤቱ 1

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 30/04/2016 ዓ.ም
ከዛሬ ጀምሮ ከትምህርት ቢሮ ለድጋፍና ክትትል የምመጡ በመሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንዲታደርጉ እንጠይቃለን።

Читать полностью…

Arada education office

የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች እና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እስከ አሁን ድረስ የ6 ወር ሪፖርት ያላስገባችሁ ዛሬ ማለትም 26/04/2016 ዓ.ም ብቻ እስከ 5፡30 ብቻ ገቢ እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 24/04/2016 ዓ.ም
የትምህርት ለትውልድ ሁለተኛ ዙር ችግር ልየታ ለይተው የላኩ 4 ት/ቤቶች ናቸው፡፡ ስለሆነም ቀሪ ት/ቤቶች ምንም የምለይ ችግር የሌላቸው መሆኑን ለሚመለከተው ልናሳውቅ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

የሁለተኛ ዙር የትምህርት ለትውልድ ችግር ልየታ ቅፅ ሲሆን በዚህ ቅፅ መሰረት የቅድመ አንደኛ፣የአንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ለየብቻ ችግሮቹን በመለየት እስከ ማክሰኞ 23/4/2016 ዓ.ም በሀርድና በሶፍት ኮፒ እንዲትልኩ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ኢንስቲትዩቱ ከጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር በመተባበር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ክበብ አቋቋመ፡፡

ክበቡ ታዳጊዎች ስለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ያላቸውን እውቀት በማዳበር በዘርፉ የሚስተዋለውን የባለሞያ እጥረት በመቅረፍ ተተኪዎችን ለማፍራት ያለመ ነው፡፡

በክበቡ ምሥረታ መርሓ ግብር ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ባስተላለፉት መልዕክት በቴክኖሎጂው ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የታዳጊ ክበብ አባላት ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚደርሱበት ዕድል በኢንስቲትዩቱ በመመቻቸቱ ታዳጊዎች የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን በርትተው መስራት እንዳለባቸው አመላክተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ታዳጊዎችን በዘርፉ የሚያሰለጥንበት የክረምት የሥልጠና መርሓ ግብር እንዳለው አውስተዋል፡፡ በመሆኑም ክበቡ ውጤታማ ተማሪዎችን እንዲያፈራ ተቋሙ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርግ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ በላይ ፀጋዬ በበኩላቸው የክበቡ መቋቋም የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ ለክበቡ ዕውን መሆን ኢንስቲትዩቱ ለነበረው ጉልህ ሚና ርዕሰ መምህሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ለክበቡ ምሥረታ ግምታዊ ዋጋቸው መቶ ሺህ ብር የሆኑ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ኢንስቲትዩቱ አበርክቷል፡፡

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 18/04/2016 ዓ.ም
ለግል ት/ቤቶች በሙሉ
የሰላም ክበብ አባላት ስም ዝርዝር እንድትልኩ ከዚህ በፊት መጠየቃችን ይታወቃል። ይሁን እንጂ የክበብ አባላትን መረጃ እስከ አሁን ድረስ ያልላካችሁት እስከ ነገ 5፡00 እንዲትልኩ እያሳሰብን የመንግስት ት/ቤቶችም በተመሳሳይ መረጃ ያልላካችሁ እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 15/04/2016 ዓ.ም
ነገ ማለትም በ16/04/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ውይይት ላይ የምትገኙ የመንግስት ት/ቤት ብቻ
1. የ2ኛ ደረጃ ዋና እና የመማር ማስተማር ም/ር/መምህራን
2. የ2ኛ ደረጃ ሁሉም ሱፐርቫይዘሮች
በሰዓት ተገኙ

Читать полностью…

Arada education office

በዚህ ቅፅ መሰረት ከዚህ በፊት መረጃ ያልላካችሁ በአስቸኳይ እንዲትልኩ እናሳስባለን

Читать полностью…

Arada education office

የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ደረሰ እንደ ተናገሩት "በመልሶ ማደራጀቱ አልፋችሁ ይህንን ትልቅ ሀላፊነት መቀበላችሁ ሊያኮራችሁ ይገባል፣ እንዲሁም በትምህርቱ ስራ ህብረተሰቡን ማገልገል ፀጋ እና ክብር ስለሆነ በአዲስ መንፈስ ውጤታማ ስራ በመስራት ለሀገራችን የተሻለ ለውጥ በማምጣት አሻራችውን እንዲያኖሩ፣ ታሪክ እንዲሰሩ አሳስበው በቀጣይ ትኩረት ሰጥተው ስለሚሰሯቸው ጉዳዮች አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Читать полностью…

Arada education office

አርብ የከተራ እለት መንገዶች ሥለሚዘጋጉና ተማሪዎችና ሠራተኞች ላይ እንግልት ሥለሚፈጥር በሁሉም የመንግሥትና የግል ት/ቤቶች ትምህርት አይኖርም።

Читать полностью…

Arada education office

አፋን ኦሮሞ የማንበብና የመጻፍ ክህሎት ፈተና ነገ 04/05/2016 ጠዋት 3:00 በዳግማዊ ሚንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይካሄዳል ሁሉም ተፈታኞች መረጃው እንዲደርሳቸው ይደረግ።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 01/05/2016 ዓም
የሞዴል ፈተና ዜና
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
በዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሞዴል ፈተና መሰጠት ተጀመረ።
ለተፈታኝ ተማሪዎች፣ ለፈታኝ መምህራንና አስተባበሪዎች  በተሰጠው ገለፃ መሰረት ሁሉም እንደየዘርፉ የሚገባውን ሚና ተወጥቷል። በመሆኑም የጠዋት ፈረቃ ደስ በሚል መልኩ ፈተናው ተካሂዷል: እየተካሄደ ይገኛል። በርቱ እንበርታ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 01/05/2016 ዓ.ም
ለሁሉም ት/ቤቶች በሙሉ የሞዴል ፈተና ፕሮግራም በወጣላችሁ መሰረት ብቻ ፈተናው መስጠት እንዳለባችሁ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

bzih checklist msrt moltwe ylaku

Читать полностью…

Arada education office

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ በሬዲዮ ትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡
ስለሆነም ተሳታፊዎችና ብዛት
1. የክፍለ ከተማ የመረጃና አይ ሲ ቲ ቡድን መሪ/ተወካይ ብዛት 1
2. በክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመንግስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ምክትል ርዕሰ መምህር ብዛት 1
3. በክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመንግስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሬዲዮ ትምህርት ተወካይ /ተጠሪ መምህር ብዛት 1


የስልጠና ቀን ፡- ቅዳሜ 04/5/2016
ሰኣት ፡- ጥዋት 2፡30
የስልጣና ቦታ ፡- ትምህርት ቢሮ ካፌ በሚገኘው አዳራሽ
ከቡድን መሪ/ተወካይ ፡- 1. የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወር የሬዲዮ ትምህርት አተገባበር ሪፖርት
2. በክፍለ ከተማ ስር ባሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሬዲዮ ትምህርት ተወካይ
መምህር ስምና አድራሻ በደብዳቤ እና በሶፍት ኮፒ ይዞ መቅረብ
ይኖርበታል ፡፡
ከርዕሰ መምህር የሚጠበቅ ፡- 1. የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወር የሬዲዮ ትምህርት አተገባበር ሪፖርት
2. የትምህርት ቤቱን የሬዲዮ ትምህርት ተወካይ መምህር ስምና አድራሻ
በደብዳቤ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
1. የክፍለ ከተማ የመረጃና አይ .ሲ .ቲ ቡድን መሪ/ተወካይ …………………………. ብዛት 1
2. በክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመንግስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ምክትል ርዕሰ መምህር ብዛት…………………….. 1

Читать полностью…

Arada education office

26/04/16
የትምህርት ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በሰሩት ጥናትና ምርምር በተሰጠው ጽብረቃ ላይ የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙትን ትምህርት ቤቶች ርእሰ-መምህራን እና የመማር ማስተማር ምክትል ርእሰ-መምህራን ጋር "በምዘና ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶች" እና "ያለው ችግር ምን ይመስላል?" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የጋራ የማድረግ ውይይት ተደርጓል፡፡
1. ምዘናን አንዱ የመማር ክፍል ወይም አካል አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ፣
2. አንድ ፈተና ምን ሊኖረው እንደሚገባ ወይም ምን ሊይዝ እንደሚገባ፣
3. የምናዘጋጀወው ፈተና "ኮምፒተንሲ" አለው ወይ ?
4. ቀረብ ብለን የፈተናን ስራ መምራት እንደሚጠበቅብን፣
5. የተጠየቂነት ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ፣
6. በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጁ ፈተናዎች ተለይተው እና ተገምግመው በፈተና ባንክ የማስቀመጥ ስራ ቢጠናከር፣
7. በዚህ ዙሪያ በክፍለ ከተማ፣ በትምህርት ቤት እና በወረዳ ደረጃ ጥናትና ምርምር ተሰርቶ ከመምህራን ጋር ውይይት እንዲደረግ፣
8. መምህራን ከዚህ በፊት በፈተና አዘገጃጀት እና አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ቢወስዱም ማደስ ስለሚገባ አጭር ስልጠና እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ቢቻል፣
9. በሰሚስተሩ የተቀመጡ ምእራፎች መሸፈናቸውና አለመሸፈናቸው ቢረጋገጥ፣ እና ፈተናው ሁሉንም ምእራፎች ስለመሸፈኑ (ስለመያዙ) ማረጋገጥ ቢቻል፣
10. ውጤት ትንተና ላይ የቁጥር መረጃዎችን ከመላክ ባሻገር ስለመጣው ወይም ስለተመዘገበው ስለውጤቱ ማብራሪያ ቢዘጋጅ እና ተተንትኖ ቢገመገም፣ የጋራ ቢደረግ፣
11. ስለፈተና ዝግጅት እና ውጤት አያያዝ የሚረዳ ወጥ የሆነ ስራ ለመስራት እንዲቻል እየተዘጋጀ ነው የተባለው ማንዋል (መመሪያ) ፈጥኖ እንዲደርሰን ቢደረግ፣

በሚሉ ተጨማሪ በርካታ ሀሳቦች ላይ መግባባት ላይ በመድረስ እና ሁላችንም ተረባርበን ከሰራን ለውጥ እንደሚመጣ በመተማመን ውይይታችን ተጠናቋል፡፡

Читать полностью…

Arada education office

አስቸኳይ ስብሰባ(25/04/2016)
በቀን 26/04/2016ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ትምህርት ፅ/ቤት መገኘት ያለባችሁ
1. ሁሉም የመንግስት ት/ቤት ዋ/ር/መ/ራን
2. ሁሉም የመንግስት ት/ቤት የመማር ማስተማር ም/ር/መ/ራን።
ስትመጡ ፍላሽ ይዛችሁ እንድትገኚ ከስብሰባ በኋላ የ6:8&12 የሞዴል ፈተና ትወስዳላችሁ።
ማርፈድ  እና መቅረት አይቻልም።
መድረኩን የሚመሩት የፅ/ቤት ሃላፊ እና አስተባባሪዎች

Читать полностью…

Arada education office

በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በሁለቱም ስርዓተ ትምህርት የጥያቄና መልስ ውድድር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

Читать полностью…

Arada education office

በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ወራዊ የፅዳት ዘመቻ በዛሬው ቀን ተከናውኗል።

Читать полностью…

Arada education office

በአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የስኩል ኔት መሰረተ ልማቶችን በአዲስ መልክ ለማስጀመር በዳ/ሚኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ቤቴልሄም፣መስከረም፣ጥቁር አንበሳ፣ወ/ሮ ቀለም ወርቅ፣በቀዳማዊ ሚኒልክ(በሳይንስ ሸርድ) 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲሁም በአፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመስክ ምልከታ (sight survey) ተካሂዷል።
የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
1.ዳታ ሴንተር ክፍል ዉስጥ የሚገኙ የኢ.ኮ.ቴ መሰረተ ልማቶችን ማለትም IPTV system፣VDI server፣Ups battery፣fiber cable ያሉበትን ሁኔታ ልየታ ስራ ተሰርቷል፣
2.በICT ላብራቶሪ እና በመማሪያ ክፍል ዉስጥ የሚገኙ አክሰስ ስዊቾችን የሚሰሩ እና የማይሰሩ እንዲሁም 2ict lab ክፍሎች optimazation የሚደረጉ እና ጥገና የሚያስፈልጋቸዉን የመለየት ስራ ተሰርቷል፣
3.በት/ቤቱ የሚገኙ AP wifi የሚሰሩ እና የማይሰሩ የመለየት እንዲሁም አዲስ wifi የሚያስፈልጋቸዉን ቦታዎች የመለየት ስራ ተሰርቷል፣
4.CCTV camera installation የሚደረግባቸዉን ቦታዎች የመለየት ስራ ተሰርቷል።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 17/04/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች በሙሉ
ቀይ አፈር የምትፈልጉ ካላችሁ ፍላጎታችሁን እስከ 6፡20 ድረስ ብቻ በቴሌግራም መልዕክት በመላክ እንዲታሳውቁን እናሳስባለን፡፡
ትምህርት ጽ/ቤት

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 15/04/2016 ዓ.ም
ነገ ማለትም በ16/04/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ውይይት ላይ የምትገኙ
1. የ2ኛ ዋና እና የመማር ማስተማር ም/ር/መምህራን
2. የ2ኛ ደረጃ ሁሉም ሱፐርቫይዘሮች
በሰዓት ተገኙ
የተጠሩት የመንግስት ት/ቤት ብቻ ነው

Читать полностью…

Arada education office

አስቸኳይ መረጃ
ለግል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ት/ሚኒስቴር መጽሃፍን ለማስራጨት የህንን ቅጽ በአሰቸኳይ እንዲሰበሰብ ጠይቋል በቅጹ መሰረት መረጃ ሞልታችሁ ላኩልን
አራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት

Читать полностью…
Subscribe to a channel