የፈተና መረጃ ለ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች
✅ የ6ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉አካ/ሳይንስ እና
👉ሞራል ሲሆኑ ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፍል ብቻ(5ኛ ክፍልን አይጨምርም)
✅ 8ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉ሶሻል ሳይንስ
👉አጠ/ሳይንስ
👉የዜግነት ት/ት እና ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል ብቻ(7ኛ ክፍልን አይጨምርም)
✅12ኛ ክፍል በተመለከተ
👉በ2016 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው:: እነሱም :-
ሀ/የተፈጥሮ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ባዮሎጅ
✍️ፊዚክስ
✍️ኬሚስትሪ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት
ለ/የማህበራዊ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ታሪክ
✍️ኢኮኖሚክስ
✍️ጅኦግራፊ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት
የፈተና ዝግጅትም:-
1. የኢኮኖሚክስ ፈተና ከ12ኛ ክፍል ብቻ
2. ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ -11ኛ በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል::
3. ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት በነበረው አሠራር መሠረት ይቀጥላል::
👉የሚከተሉትን ምክሮች በመተግበር የማስታወስ ችሎታችንና የትኩረት አቅማችንን ማዳበር እንችላለን :-
✅ 1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች.
👉ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።
👉ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል።
👉ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።
✅ 2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት
👉ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።
👉ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።ጠዋት ጥናት የምንጀምርበትና የምናበቃበት ሰዓት ከፈተናው በፊት ባሉት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ተመሳሳይ ለማድረግ መሞከርም ውጤታማ ያደርጋል።
3. ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ
በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ነው ወይስ የተግባር? ወይስ ቃለመጠይቅ ነው የሚለውን መለየት ወሳኝ ነው።
👉ሁሉም ዓይነት ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተለያየ አይነት አቀራረብ አላቸው። በምሳሌ አስደግፎ ማብራሪያ መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ላይ በትኩረት መዘጋጀት።
ምናልባት ፈተናው ምርጫ አልያም አጭር መልስ የሚፈልግ ዓይነት ከሆነ ቀለል ያለና አጠቃላይ መረጃዎችን ለመያዝ መሞከር።
✅ 4. እቅድ ማዘጋጀት
👉ምናልባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ለማስያዝና እቅድ ለማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዳለባችሁና መቼ ማጥናት እንዳለባችሁ እቅዳችሁ ይነግራችኋል። ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክል እንደተጓዛችሁ ለመመዝገብና ለመከታተል ይረዳል።
👉የትኞቹን ማስታወሻ ደብተሮች መቼ መመልከት እንዳለባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት ለተጨማሪ ማብራሪያ እንደምትጠቀሙ እንዲሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መለማመድ እንዳለባችሁ በእቅድ ውስጥ ማስገባት ውጤታማ ያደርጋል።እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ለእረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዳለብን ነው።
✅5. ከፋፍሎ ማጥናት
👉የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
👉ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ።
✅ 6. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ
👉የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
👉ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው ።የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል።
✅ 7. መምህር መሆን
👉ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።
✅8. ከተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ራቅ በሉ
👉ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
👉ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።ብትችሉ ስልካችሁን አጠገባችሁ እንኳን አታድርጉት።
✅9. ሙዚቃ መቀነስና በጸጥታ ማንበብ
👉በጸጥታ ውስጥ ሆነው ጥናታቸውን የሚያከናወኑ ተማሪዎች ሙዚቃ እየሰሙ ከሚያጠኑት ጋር ሲወዳደሩ በእጅጉ የተሻለ የማስታወስና የትኩረት አቅም እንዳለቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
✅10. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ
👉ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል።
👉ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል።
👉አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።
✅11. እንቅልፍ
👉ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
አራዳ ወረዳ 5 ኒዉኤራ ክላስተር ማዕከል በቀን 10/07/2016ዓ.ም በቅድመ 1ኛ ደረጃ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በቀዳማይ ልጅነት ዘመን በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴ ላይ በክላስተሩ ስር የሚገኙ የመንግስትና የግል ቅድመ 1ኛ ት /ቤቶች አፍሪካ አንድነት ቁጥር 2 ት/ቤት በመገኘት በሁለቱም ስርዓተ ትምህርት የልምድ ልዉዉጥ አድርገዋል።
Читать полностью…በዚህ ደብዳቤ መሰረት በየትምህርትቤቱ የተቀመጡት ትራንኪንጎች ያለምንም ሞዴል ያልቡና ለመውሰድም ሞዴል የማያስፈልጋቸው መሆኑን አውቃችሁ በድልድሉ መሰረት ያለምንም ውጣ ውረድ በዓግባቡ እንዲሰራጭ ለትምህርትቤቶቹ እንድታሳውቁ ........ስርጭቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን ጎንለጎን ብሁሉም ትምህርትቤት ኦፕቲማይዜሽን ትግበራ ስለሚጀመር ክትትሉን እንድትጀምሩ
Читать полностью…በዛሬው እለት በአጼ ፋሲል ት/ት ቤት ከ3ኛ እስከ 8ኛ ክፋል ለሚማሩ ተማሪወች በሒሳብ ት/ት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የአብቲቲውድ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተሰጥቷል።
Читать полностью…ቀን 12/06/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶችና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች
የግማሽ ዓመት የምዘና ፕሮግራም
ረቡዕ 13/06/2016 ዓ.ም ከጥዋት 2፡30 ጀምሮ
የ2ኛ ደረጃ እና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች ሲሆን
ሐሙስ በ 14/06/2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ የምትመዘኑበት ቀን በመሆኑ በተባለው የፕሮግራም መሰረት መዛኞችን በሰዓቱ እንድትጠብቁ እናሳስባለን።
መረጃ የለኝም ማለት አይቻልም።
#Grade12NationalExam
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞ ምዝገባ በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል።
የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ምን አሉ ?
- የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት የመመዝገቢያ መስፈርቱን ማሟላት አለባቸው። በተቀመጠው የጊዜ ገድብ ውስጥም መምዝገብ አለባቸው።
- ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / አማካኝነት ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም
ይሆናል።
- በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው ብለዋል ፦
✍️1ኛ. ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ አለባቸው። ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ።
✍️2ኛ. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል አለባቸው።
✍️3ኛ. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ አለባቸው።
✍️4ኛ. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት ይሆናል።
✍️5ኛ. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወርዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች ይሆናል።
✅መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።
ቀን 05/06/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች እና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች በሙሉ
የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ምዘና ከየካቲት 11 ጀምሮ ምዘና የምካሄድ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲታደርጉ እናሳስባለን።
ቀን 04/06/2016
በአራዳ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎችን ጥሩ አቀባበል በማድረግ በትምህርት ቤቶች ትምህርት በዛሬዉ እለት መሰጠት ተጀምሯል።
የትምህርት መረጃና ኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን
የ2016 ዓ.ም አጠቃላይ የትምህርት መረጃዎችን በአግባቡ ለመያዝ የሚያስችልና በትምህርት መዋቅሩ ያለውን የተማሪ ፣ የመምህር ፣ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ የምገባ ግብአቶች ፣ የመጋቢ እናቶችና ሌሎች በትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶችን አጠቃላይ መረጃ ወደ ዳታ ቤዝ ለማስገባት ለወረዳና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መረጃ ባለሙያዎች በቅጹ አሞላል ፣አሰባሰብ ዙርያ ስልጠና ተሰጥቷል።
29/5/2016ዓ.ም
አስቸኳይ ማስታወቅያ
የ2016 ዓ.ም የመጀመርያ ግማሽ አመት የመምህራንን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የስኮር ካርድ አፈፃፀም ምዘና ውጤት እንዲሁም የወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊዎች በፅ/ቤታችሁ ያሉትን የቡድን መሪ እና ባለሙያውችን ስኮር ካርድ የምዘና ውጤት እስከ ሰኞ(8/6/2016ዓ.ም) ከቀኑ 6:00 ድረስ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
የከተማ ግብርና በመስከረም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
(ቀን መጋቢት 13/2016 ዓ.ም) በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በዳግማዊ ምንሊክ 2ኛ ደረጃ ሱፐርቪዥን ክላስተር ማዕከል ስር የሚገኘው መስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ቀን 19/06/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን
በዛሬ ቀን በ8፡00 ሰዓት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ በተባለው ሰዓት የፋይናንስ ቡድን መሪዎችን ይዛችሁ የት/ቤቱ ዋና ር/መምህራን በስብሰባ ላይ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ማርፈድና መቅረት አይቻልም፡፡
ቦታ ት/ጽ/ቤት
በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በዛሬው እለት በቀን 7/6/2016 የሁለተኛ መንፈቅ አመት የትምህርት አጀማመርን በተመለከተ ከርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በአጀማመር ወቅት የተስተዋሉ ክፍተቶች በመገምገም የጋራ መግባባት በመድረስ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
Читать полностью…የ2016ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጤት ትንተና እስክ 30/05/2016ዓ.ም ገቢ እንዲደረገ ቀደም ሲል በደብዳቤ ተገልጻ ነበር ፤ ነገር ግን እስካሁን ከወረዳ 7 ÷ቤተልሔም ÷ ነጃሺ ÷ናዝሬት እና ቅ /ስላሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በስተቀር የውጤት ትንተናው እስከ ዛሬ ስላልደረሰን እንድትልኩ እናሳስባለን
Читать полностью…ቀን 30/05/2016 ዓ.ም
የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 4/2016 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን።
አራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
29/05/16
የአራዳ ክፍለ ከተማ ስርዓተ-ትምህርት ትግበራ እና ክትትል ቡድን የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሰርትፊኬት ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ አስፈጻሚች ስልጠና ተሰጠ
በጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የከተማ ግብርና እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከመተከሉ በፊት ያለ ገጽታ እና ለጓሮ አትክልት ለመትከል መሬቱ ሲዘጋጅ
Читать полностью…