አስቸኳይ ማስታወቅያ
ለሁሉም የመንግስት የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህራን የበጀት defence እንድታደርጉ።
👍ቀን=30/09/2016ዓ.ም
👍 ሰዓት=4:00
👍ቦታ=አራዳ ክፍለ ከተማ 8ኛ ፎቅ
👍መገኘት ያለበት=ዋና ርዕሰ መምህር እና ፍይናንስ ቡድን መሪ
የወረዳ ት/ጽ/ቤቶችና ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከላይ የተላከውን ቢጋር መሰረት የ2016 ዓ.ም የዓመቱን ሪፖርት እስከ ሰኔ 10/2016 ዓ.ም እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
Читать полностью…ቀን 23/09/2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አራዳ ቅርንጫፍ የታክስ ክበባት የአሸናፊዎች አሸናፊ በተደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር ከኒውኤራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ፅዮን ብርሃኑ 1ኛ በመውጣት ተሸላሚ መሆን ችላለች።
ለመንግስት የትምህርት ተቋማት በሙሉ
ከነገ ጀምሮ የሁለተኛ ዙር የእውቅና ፈቃድ ምዘና ስለሚከናወን በተቋማችሁ በተሰጣችሁ ግብረመልስ መሰረት ከወዲሁ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን።
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/+U94HRfix7u8CjEb-
የአራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና እውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት
አራት ኪሎ ድንቅ ስራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡
(ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም) ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠው የፈተና መርሃ ግብር የሚከተለው መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የገለጸ ሲሆን ተፈታኞችና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስባል፡፡
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!!
በአራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ቡድን ወራዊ የስራ ግምገማ ከት/ቤት ር/መምህራንና ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ጋር ውይይት አድርጓል።
Читать полностью…ሀሙስ ግንቦት 1/ 2016 ዕ.ም የምዘና ቀን
ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ሃሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ እንዲሁም በምዘናው ወቅትም ተመዛኞች ስልክም ሆነ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዘው ፈተና ክፍል መግባት እንደማይችሉ ፣ ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣ ተመዛኞች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ፈታኞች 1፡30 ላይ ይገኛሉ።
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የባለስልጣን መስራቤቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ቀን 21/08/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሙሉ
የ2016 ዓ.ም የሙያ ፈቃድ ተመዛኝ መምህራን፣ ር/መምራን እና ሱፐርቫይዘሮች ባለፈው ሳምንት ስለ ፈተና አሰጣጥ ሂደት ኦሬንቴሽን መሰጠቱ ይታወቃል። በመሆኑም በኦሬንቴሽን ላይ ያልተገኛችሁት መ/ራን ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ረቡዕ በ23/2016 ዓ.ም ጥዋት 2:30 ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ እንድገኙ ር/መምህራን መልዕክት እንድታስተላልፉ እና እንድታስተባብሩ እናሳስባለን።
ቀን 18/08/2016 ዓ.ም
በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2016 ዓመት የሳይንስና ቴክኖሎጂ አዉደ-ርዕይ "በፈጠራ ስራ የዳበረ ትውልድ ለሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የሳይንስና የሂሳብ የፈጠራ ስራዎች በተማሪዎችና በመምህራን የተሰሩ በዳ/ሚኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በዛሬዉ እለት ለእይታ ክፍት ተደረገ ። በዕለቱም የክብር እንግዳ የነበሩት አቶ ወንድሙ ዑመር የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ መልዕክት ያስተላለፊ ሲሆን በመልዕክታቸውም
ማስታወቂያ
ለሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ነገ ሀሙስ በ17/08/2016 ዓ.ም ርእሰ መምህራን ብቻ ፍላሽ በመያዝ የ6ኛ እና የ8ኛ 2ኛ ሰሚስተር ሞዴል ጥያቄ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት መጣችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን ፡፡
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል አስፈታኝ ት/ቤቶች በሙሉ፡
1. የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ኦን ላይን ምዝገባ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ ያልተመዘገቡበትን ምክንያት በመጥቀስ በደብዳቤ እንድታሳውቁ፣
2. ከተመዘገቡት ውስጥ ፎቶ ያልገባ ፣ ስም ስህተት እዲት የሚያስፈልግ ካለ በደብዳቤ እንዲታሳውቁ;
3. የአካል ጉዳት ያለባቸው የተመዘገቡ (6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች) ካሉ ዝርዝራቸውን በሸኚ ደብዳቤ አያይዛችሁ እንድትልኩ። በአይን የማይታይ ጉዳት ከሆነ የህክምና ማስረጃ መያያዝ አለበት፣
4. ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ሀሳቦች 03/08/2016 ሐሙስ እስከ 6 ሰአት እንዲደርሰን ፤
ያላከ ት/ቤት ኃላፊነቱን ት/ቤቱ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን
ነገ 24/2016 ኔትዎርክ ሰርቬይ የሚሰራላቸው ትምህርትቤቶች
1, ጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና
2, በላይ ዘለቀ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስሆን ት/ቤቶች አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን ። አራዳ ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት የት/ት መረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ።
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች በሙሉ
የአራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ የዕውቅናና ምዘና ባለስልጣን ያደረገውን የሱፐርቪዥን ግብረ መልስ ሰው በመላክ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰኞ ጥዋት እንድትወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን ።
በዛሬው ውይይት ላይ ያልተገኙ ት/ቤቶች
1ኛ. ራስ አበበ አረጋይ
2ኛ. አ.አንድነት ቁ.2
3ኛ. አበበች ጎበና በመሆኑም ሰው በመላክ አስቼኳይ መረጃ እንድትወስዱ እናሳስባለን።
አስቸኳይ ማስታወቅያ
ለሁሉም የመንግስት የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህራን በቀን 30/09/2016ዓ.ም የበጀት defence ስላለ 8ኛ ፎቅ ፍይናንስፅ/ቤት እንዲገኙ እና በጀታቸውን ተወያይተው እንዲተማመኑ ።
እንኳን ደስ አለን አላችሁ !!!በ9ኛው ከተማ አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መስከረም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ፋልካን አካዳሚን በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
Читать полностью…ቀን 06/09/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሙሉ ከ07/09/2016 ዓ.ም እስከ 08/09/2016 ዓ.ም ድረስ ከከተማ የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮች በየተቋማችሁ ለክትትልና ድጋፍ ስለምመጡ በአግባቡ እንድታስተናግዷቸው በአክብሮት እናሳውቃለን።
አራዳ ትምህርት ጽ/ቤት
መልካም አዳር
####ARAADAA####
Waajjira barnootaa kutaa magaalaa araadaatti Hooggantoota sirna barnootaa Afaan Oromoo bakka bu'an waliin gamaggamni hojii ji'a Eeblaa taasifameera.
Erga Riifoormiin hooggansa barnootaa taasifamee sirna barnoota Afaan Oromoo yeroo hunda ji'a ji'aan walarganii bakka tokkotti Akka kutaa magaalaatti hojiilee jojjetaman gamaggamaa adeemuun barmaata gaarii ta'ee itti fufaa jira.
Kutaama sagantaa kana kan ta'e gaafa guyyaa 2/9/2016ALI tti bakka :
#Qindeessiitootni kutaa magaalaa
# Hoggantootni waajjira barnootaa aanoolees
#.A/A/S/B/A/Oromoo
# Suupparvaayizaroota kutaa magaalaa
# Suupparvaayizaroota wiirtuulee
# Ogeessota sirna barnootaa kutaa magaalaa jiranitti hojiiwwan ji'a Eeblaa keessa hojjetaman gabaasni Raawwii isaa mana barnootaa irraa kaasee hanga kutaa magaalaatti dhiyaachuun gamaggamni bal'aan irratti taasifameera.
####saganticha irratti yaadoolee gurguddoo irratti marii gad _fageenyaan taasifame keessaa muraasni:-
✓Haala baruu Fi barsiisuu nagaqabeessa ta'e uumuu irratti qidoominaan hojjetamuu akka qabu.
✓Qiisa'insa waayitii barnootaa irratti araarama tokko malee hojjetamuu akka qabu
✓Madaallii walitti fufaa ilaalchise
###Barattootaa kutaa 6,8 Fi 12 irratti gamanumaan qormaataaf haala isaan qophaa'uu danda'an irratti hojjetamuu akka qabu.
Keessattuu :_
✓Gaaffilee workshiitii garaagaraa barattootaaf hojjetamuu akka qabu.
✓Qormaanni bara darbee illee barattootaaf hojjechuun shaakkalchisuu Akka qaban.
✓Barattoota xiinsamuun qormaataaf qopheessuu Akka qabu
∆ Uwwisa barnoota sadarkaa maalii irra Akka jiru gosa barnootaa tokko tokkoon adda baasuun sadarkaa inni irra jiru beekuun furmaata arifataa ta'e kennamuu Akka qabu.
Waltajjicha irratti kaka'umsi hooggantootni riifoormiin gara hoggansaatti dhufan humna qabanii Fi beekumsa qaban fayyadamii hojii baruu Fi barsiisuu deemsisuuf kutannoo isaan qaban gabaasa ji'a kana isaan dhiyeessan irraa hubachuun danda'ameera.
Haa ta'u malee ammas hoggantootni baay'inaan xiqqoo ta'an miira eeggattummaa keessaa kan hin baay'ee Fi kallattii hojii isaaniif keennamu irratti laafina kan qabaniifii ofjijjiiruufis kutannoo kan hin agarsiifne mullaachaa jiraachuu isaanii waltajjii kanarraa hubachuun danda'ameera.
✓ Hanqinaaleen muraasni mula'atan immoo yeroo itti anutti hordoffii Fi deeggarsa addaa qaamoolee kanaaf taasisuun yeroo itti aanutti Akka isaan jijjiirama addaa agarsiisan irratti hojjetamuu akka qabu irrattis akkaatama waltajjicha irraa yaadni kennameen kan cimsinee Akka addatti deeggarru ta'a
Hojiin barnootaa hojiiwwan kan irraa kan adda taasisu hojii qidoominaan hojjetamu ta'uu isaati..kana hubannoo keessa galchuun gara fuulduraattis harka wal qabannee qindoomuudhaan sirni barnoota Afaan Oromoo daran dagaagee Akka mul'atu irratti hojjechuu Akka qabnu sagalee tokkoon dhuma waltajjichaa irratti walii galuun qabxiilee xiyyeeffannoo armaan olii katabaman irrattis gara fuulduraattis Akka galteetti fudhachuun irratti hojjechuu Akka qabnu irratti adde Dammaquu Garramoo qindeessituun barnootaa kutaa magaalaa araadaa kallatti ka'uun sagantichi xummuramera.
ለሁሉም ር/መምህራን
የነገ ተፈታኝ መምህራን ስም ዝርዝር ማስታወቂያ ቦርድ ላይ እንድትለጥፉ እያሳወቅን ከዚህ በፊት ለመመዘን ስማቸው ያልተላለፈ በነገው ዕለት መመዘን የማይችሉ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
የመፈተኛ ቦታ ዳግማዊ ምኒልክ አንደኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ
ሰዓት ሁሉም 1:30
ለፈተና ስመጡ:-
1. ሞባይ መያዝ የተከለከለ ነው
2. የታደሰ መታወቂያ መያዝ አለባችሁ
3. ምንም ዓይነት ወረቀት መያዝ የተከለከለ ነው
4. ማንኛው ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመሩ ከ30 ደቂቃ በኋላ መግባት አይቻልም
4. የፈተና ስነ ስርዓት ማክበርና ለፍተሻ መተባበር
ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሙሉ
የ2016 ዓ.ም ተመዛኝ መምህራን ድልድል ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በፊት ለመመዘን ስማቸው ተላልፎ በድልድሉ ላይ የተዘለሉ ካለ ፈጥናችሁ እንድታሳውቅን እናሳስባለን፡፡
የፈተና ቀን ግንቦት 1/2016 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሂሳብና ሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ-ርዕይና ውድድር ተካሄደ።
(ቀን ሚያዚያ 18/ 2016 ዓ.ም) "በፈጠራ ስራ የዳበረ ትውልድ ለሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል በከተማ ክፍለ ከተማው አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው የሂሳብና የሳይንስ የፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ እና ውድድር ላይ በተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ለእይታ ቀርበዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም እንደተናገሩት እየተካሄደ ያለው የሂሳብና ሳይንስ የፈጠራ ስራዎች ውድድር ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልፀው የመርሃ-ግብሩ መዘጋጀት በተማሪዎች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር የምርምር የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ክህሎታቸው የበለጠ እንዲያድግ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቀፀላ በበኩላቸው በሳይንስና ሂሳብ የፈጠራ ስራዎች ለሃገር እድገትና ብልፅግና መሰረት ናቸው ብለው ተማሪዎች ለሚሰሩት የፈጠራ ስራ ጽ/ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በውዝዋዜና በፈጠራ ስራው ተወዳድረው አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎችና መምህራን የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር መከናወኑን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጵ/ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት በለፉት ዘጠኝ ወራት የተሰሩ ስራዎችን ዕቅድ አፈፃፀም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማለትም የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቨይዘሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ማካሄድ ጀምሯል።በዕለቱም የተሰሩ ስራዎች ከተመረጡ በትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና ክላስተር ማዕከል ሪፓርት ከቀረበ በኃላ የክፍለ ከተማውን የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ።
ለሁሉም የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲሁም ለመንግስት 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መረጃዉን በቅፁ መሰረት በአስቸካይ ሞልታችሁ ዛሬ እስከ 10፡00 እንድትልኩልን።
Читать полностью…ብሄረ ኢትዮጵያ ት/ቤት ዛሬ 21/07/2016 ስለ ተማሪዎችን ውጤት እና ስነ-ምግባር በተመለከተ ከ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች ጋር ውይይት አደረገ። የተማሪን ውጤትም ገመገመ።
Читать полностью…በቀን 19/07/2016 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የትምህር ጉባኤ ተካሄደ። በመድረኩም በክፕአይ ምዘና እና የአገልግሎት አሰጣጥ ምዘና ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የመጀመሪያ ደረጃ ፣2ኛ ደረጃ እና ወረዳ ት/ጽ/ቤቶች የዋንጫ እና የሰርተፊኬት እውቅና ተሰጥቷል።
Читать полностью…ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ርዕሳነ መምህራን በሙሉ ነገ ጥዋት 2፡30 ላይ የመማር ማስተማር ም/ርዕሳነ መምህራን ላኩልን ባልነው መሰረት ት/ጽ/ቤት 7ኛ ላይ እንድትልኳቸው በድጋሚ እናሳስባለን።
ማሳሳቢያ ሁለት ርዕሰ መምህር ባለበት ት/ቤት ም/ር/ መምህር ይመጣሉ።
ሰዓት ይከበር።
ጥሪው ለ20/07/2016 ዓ.ም ነው።