av12c | Unsorted

Telegram-канал av12c - Arada education office

6896

Subscribe to a channel

Arada education office

ለመንግስት የትምህርት ተቋማት በሙሉ

ከነገ ጀምሮ የሁለተኛ ዙር የእውቅና ፈቃድ ምዘና ስለሚከናወን በተቋማችሁ በተሰጣችሁ ግብረመልስ መሰረት ከወዲሁ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን።

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/+U94HRfix7u8CjEb-


የአራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና እውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት


አራት ኪሎ ድንቅ ስራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ

Читать полностью…

Arada education office

የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡

(ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም) ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠው የፈተና መርሃ ግብር የሚከተለው መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የገለጸ ሲሆን ተፈታኞችና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስባል፡፡

የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!!

Читать полностью…

Arada education office

በአራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ቡድን ወራዊ የስራ ግምገማ ከት/ቤት ር/መምህራንና ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ጋር ውይይት አድርጓል።

Читать полностью…

Arada education office

ሀሙስ ግንቦት 1/ 2016 ዕ.ም የምዘና ቀን
ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ሃሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ እንዲሁም በምዘናው ወቅትም ተመዛኞች ስልክም ሆነ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዘው ፈተና ክፍል መግባት እንደማይችሉ ፣ ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣ ተመዛኞች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ፈታኞች 1፡30 ላይ ይገኛሉ።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የባለስልጣን መስራቤቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 21/08/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሙሉ
የ2016 ዓ.ም የሙያ ፈቃድ ተመዛኝ መምህራን፣ ር/መምራን እና ሱፐርቫይዘሮች ባለፈው ሳምንት ስለ ፈተና አሰጣጥ ሂደት ኦሬንቴሽን መሰጠቱ ይታወቃል። በመሆኑም በኦሬንቴሽን ላይ ያልተገኛችሁት መ/ራን ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ረቡዕ በ23/2016 ዓ.ም ጥዋት 2:30 ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ እንድገኙ ር/መምህራን መልዕክት እንድታስተላልፉ እና እንድታስተባብሩ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 18/08/2016 ዓ.ም
በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2016 ዓመት  የሳይንስና ቴክኖሎጂ አዉደ-ርዕይ "በፈጠራ ስራ የዳበረ ትውልድ ለሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የሳይንስና የሂሳብ የፈጠራ ስራዎች በተማሪዎችና በመምህራን የተሰሩ በዳ/ሚኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በዛሬዉ እለት ለእይታ ክፍት ተደረገ ። በዕለቱም የክብር እንግዳ የነበሩት አቶ ወንድሙ ዑመር የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ መልዕክት ያስተላለፊ ሲሆን በመልዕክታቸውም

Читать полностью…

Arada education office

ማስታወቂያ
ለሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ነገ ሀሙስ በ17/08/2016 ዓ.ም ርእሰ መምህራን ብቻ ፍላሽ በመያዝ የ6ኛ እና የ8ኛ 2ኛ ሰሚስተር ሞዴል ጥያቄ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት መጣችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን ፡፡

Читать полностью…

Arada education office

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል አስፈታኝ ት/ቤቶች በሙሉ፡
1. የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ኦን ላይን ምዝገባ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ ያልተመዘገቡበትን ምክንያት በመጥቀስ በደብዳቤ እንድታሳውቁ፣
2. ከተመዘገቡት ውስጥ ፎቶ ያልገባ ፣ ስም ስህተት እዲት የሚያስፈልግ ካለ በደብዳቤ እንዲታሳውቁ;
3. የአካል ጉዳት ያለባቸው የተመዘገቡ (6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች) ካሉ ዝርዝራቸውን በሸኚ ደብዳቤ አያይዛችሁ እንድትልኩ። በአይን የማይታይ ጉዳት ከሆነ የህክምና ማስረጃ መያያዝ አለበት፣

4. ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ሀሳቦች 03/08/2016 ሐሙስ እስከ 6 ሰአት እንዲደርሰን ፤
ያላከ ት/ቤት ኃላፊነቱን ት/ቤቱ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን

Читать полностью…

Arada education office

ነገ 24/2016 ኔትዎርክ ሰርቬይ የሚሰራላቸው ትምህርትቤቶች
1, ጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና
2, በላይ ዘለቀ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስሆን ት/ቤቶች አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን ። አራዳ ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት የት/ት መረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ።

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች በሙሉ
የአራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ የዕውቅናና ምዘና ባለስልጣን ያደረገውን የሱፐርቪዥን ግብረ መልስ ሰው በመላክ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰኞ ጥዋት እንድትወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን ።

Читать полностью…

Arada education office

በዛሬው ውይይት ላይ ያልተገኙ ት/ቤቶች
1ኛ. ራስ አበበ አረጋይ
2ኛ. አ.አንድነት ቁ.2
3ኛ. አበበች ጎበና በመሆኑም ሰው በመላክ አስቼኳይ መረጃ እንድትወስዱ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

የፈተና መረጃ ለ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

✅ የ6ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉አካ/ሳይንስ  እና
👉ሞራል ሲሆኑ ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፍል ብቻ(5ኛ ክፍልን አይጨምርም)

8ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉ሶሻል ሳይንስ
👉አጠ/ሳይንስ
👉የዜግነት ት/ት እና ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል ብቻ(7ኛ ክፍልን አይጨምርም)

12ኛ ክፍል በተመለከተ
👉በ2016 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን  በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው::   እነሱም :-
ሀ/የተፈጥሮ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ባዮሎጅ
✍️ፊዚክስ
✍️ኬሚስትሪ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት

ለ/የማህበራዊ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ታሪክ
✍️ኢኮኖሚክስ
✍️ጅኦግራፊ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት


የፈተና ዝግጅትም:-
1. የኢኮኖሚክስ ፈተና ከ12ኛ ክፍል ብቻ
2. ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ -11ኛ በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል::
3. ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት በነበረው አሠራር መሠረት ይቀጥላል::

👉የሚከተሉትን  ምክሮች በመተግበር  የማስታወስ ችሎታችንና የትኩረት አቅማችንን ማዳበር እንችላለን :-

1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች.

👉ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።

👉ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል።

👉ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።

2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት

👉ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።

👉ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።ጠዋት ጥናት የምንጀምርበትና የምናበቃበት ሰዓት ከፈተናው በፊት ባሉት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ተመሳሳይ ለማድረግ መሞከርም ውጤታማ ያደርጋል።

3. ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ


በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ነው ወይስ የተግባር? ወይስ ቃለመጠይቅ ነው የሚለውን መለየት ወሳኝ ነው።

👉ሁሉም ዓይነት ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተለያየ አይነት አቀራረብ አላቸው። በምሳሌ አስደግፎ ማብራሪያ መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ላይ በትኩረት መዘጋጀት።
ምናልባት ፈተናው ምርጫ አልያም አጭር መልስ የሚፈልግ ዓይነት ከሆነ ቀለል ያለና አጠቃላይ መረጃዎችን ለመያዝ መሞከር።

✅ 4. እቅድ ማዘጋጀት

👉ምናልባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ለማስያዝና እቅድ ለማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዳለባችሁና መቼ ማጥናት እንዳለባችሁ እቅዳችሁ ይነግራችኋል። ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክል እንደተጓዛችሁ ለመመዝገብና ለመከታተል ይረዳል።

👉የትኞቹን ማስታወሻ ደብተሮች መቼ መመልከት እንዳለባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት ለተጨማሪ ማብራሪያ እንደምትጠቀሙ እንዲሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መለማመድ እንዳለባችሁ በእቅድ ውስጥ ማስገባት ውጤታማ ያደርጋል።እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ለእረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዳለብን ነው።

5. ከፋፍሎ ማጥናት

👉የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።

👉ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ።

✅ 6. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ

👉የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።

👉ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው  ።የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል።

7. መምህር መሆን

👉ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።

8. ከተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ራቅ በሉ

👉ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።

👉ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።ብትችሉ ስልካችሁን አጠገባችሁ እንኳን አታድርጉት።

9. ሙዚቃ መቀነስና በጸጥታ ማንበብ

👉በጸጥታ ውስጥ ሆነው ጥናታቸውን የሚያከናወኑ ተማሪዎች ሙዚቃ እየሰሙ ከሚያጠኑት ጋር ሲወዳደሩ በእጅጉ የተሻለ የማስታወስና የትኩረት አቅም እንዳለቸው ማረጋገጥ ተችሏል።

10. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ

👉ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል።

👉ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል።

👉አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።

11. እንቅልፍ

👉ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።

Читать полностью…

Arada education office

አራዳ ወረዳ 5 ኒዉኤራ ክላስተር ማዕከል በቀን 10/07/2016ዓ.ም በቅድመ 1ኛ ደረጃ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በቀዳማይ ልጅነት ዘመን በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴ ላይ በክላስተሩ ስር የሚገኙ የመንግስትና የግል ቅድመ 1ኛ ት /ቤቶች አፍሪካ አንድነት ቁጥር 2 ት/ቤት በመገኘት በሁለቱም ስርዓተ ትምህርት የልምድ ልዉዉጥ አድርገዋል።

Читать полностью…

Arada education office

በዚህ ደብዳቤ መሰረት በየትምህርትቤቱ የተቀመጡት ትራንኪንጎች ያለምንም ሞዴል ያልቡና ለመውሰድም ሞዴል የማያስፈልጋቸው መሆኑን አውቃችሁ በድልድሉ መሰረት ያለምንም ውጣ ውረድ በዓግባቡ እንዲሰራጭ ለትምህርትቤቶቹ እንድታሳውቁ ........ስርጭቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን ጎንለጎን ብሁሉም ትምህርትቤት ኦፕቲማይዜሽን ትግበራ ስለሚጀመር ክትትሉን እንድትጀምሩ

Читать полностью…

Arada education office

የሴቶች ቀን አከባበር በመስከረም ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት(29/06/2016ዓ.ም)

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 06/09/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሙሉ ከ07/09/2016 ዓ.ም እስከ 08/09/2016 ዓ.ም ድረስ ከከተማ የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮች በየተቋማችሁ ለክትትልና ድጋፍ ስለምመጡ በአግባቡ እንድታስተናግዷቸው በአክብሮት እናሳውቃለን።
አራዳ ትምህርት ጽ/ቤት
መልካም አዳር

Читать полностью…

Arada education office

####ARAADAA####
   Waajjira barnootaa kutaa magaalaa araadaatti  Hooggantoota sirna barnootaa Afaan Oromoo bakka bu'an waliin gamaggamni hojii ji'a Eeblaa taasifameera.
    Erga Riifoormiin hooggansa barnootaa taasifamee sirna barnoota Afaan Oromoo yeroo hunda ji'a ji'aan walarganii bakka tokkotti Akka kutaa magaalaatti hojiilee jojjetaman gamaggamaa adeemuun barmaata gaarii ta'ee itti fufaa jira.
     Kutaama sagantaa kana kan ta'e gaafa guyyaa 2/9/2016ALI tti bakka :
   #Qindeessiitootni kutaa magaalaa
# Hoggantootni waajjira barnootaa aanoolees
#.A/A/S/B/A/Oromoo
# Suupparvaayizaroota kutaa magaalaa
# Suupparvaayizaroota wiirtuulee
# Ogeessota sirna barnootaa kutaa magaalaa jiranitti hojiiwwan ji'a Eeblaa keessa hojjetaman gabaasni Raawwii isaa mana barnootaa irraa kaasee hanga kutaa magaalaatti dhiyaachuun gamaggamni bal'aan irratti taasifameera.
  ####saganticha irratti  yaadoolee gurguddoo irratti marii gad _fageenyaan taasifame keessaa muraasni:-
   ✓Haala baruu Fi barsiisuu nagaqabeessa ta'e uumuu irratti qidoominaan hojjetamuu akka qabu.
  ✓Qiisa'insa waayitii barnootaa irratti araarama tokko malee hojjetamuu akka qabu
  ✓Madaallii walitti fufaa ilaalchise
###Barattootaa kutaa 6,8 Fi 12 irratti gamanumaan qormaataaf haala isaan qophaa'uu danda'an irratti hojjetamuu akka qabu.
Keessattuu :_
✓Gaaffilee workshiitii garaagaraa barattootaaf hojjetamuu akka qabu.
✓Qormaanni bara darbee illee barattootaaf hojjechuun shaakkalchisuu Akka qaban.
✓Barattoota xiinsamuun qormaataaf qopheessuu Akka qabu
∆ Uwwisa barnoota sadarkaa maalii irra Akka jiru gosa barnootaa tokko tokkoon adda baasuun sadarkaa inni irra jiru beekuun furmaata arifataa ta'e kennamuu Akka qabu.
  Waltajjicha irratti kaka'umsi hooggantootni riifoormiin gara hoggansaatti dhufan  humna qabanii Fi beekumsa qaban fayyadamii hojii baruu Fi barsiisuu deemsisuuf kutannoo isaan qaban gabaasa ji'a kana isaan dhiyeessan irraa hubachuun danda'ameera.
Haa ta'u malee ammas hoggantootni baay'inaan xiqqoo ta'an miira eeggattummaa keessaa kan hin baay'ee Fi kallattii hojii isaaniif keennamu irratti laafina kan qabaniifii ofjijjiiruufis kutannoo kan hin agarsiifne mullaachaa jiraachuu isaanii waltajjii kanarraa hubachuun danda'ameera.
✓ Hanqinaaleen muraasni mula'atan immoo yeroo itti anutti hordoffii Fi deeggarsa addaa qaamoolee kanaaf taasisuun yeroo itti aanutti Akka isaan jijjiirama addaa agarsiisan irratti hojjetamuu akka qabu irrattis akkaatama waltajjicha irraa yaadni kennameen kan cimsinee Akka addatti deeggarru ta'a
  Hojiin barnootaa hojiiwwan kan irraa kan adda taasisu hojii qidoominaan hojjetamu ta'uu isaati..kana hubannoo keessa galchuun gara fuulduraattis harka wal qabannee qindoomuudhaan sirni barnoota Afaan Oromoo daran dagaagee Akka mul'atu irratti hojjechuu Akka qabnu sagalee tokkoon dhuma waltajjichaa irratti walii galuun qabxiilee xiyyeeffannoo armaan olii katabaman irrattis gara fuulduraattis Akka galteetti fudhachuun irratti hojjechuu Akka qabnu irratti adde Dammaquu Garramoo qindeessituun barnootaa kutaa magaalaa araadaa kallatti ka'uun sagantichi xummuramera.

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም ር/መምህራን
የነገ ተፈታኝ መምህራን ስም ዝርዝር ማስታወቂያ ቦርድ ላይ እንድትለጥፉ እያሳወቅን ከዚህ በፊት ለመመዘን ስማቸው ያልተላለፈ በነገው ዕለት መመዘን የማይችሉ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
የመፈተኛ ቦታ ዳግማዊ ምኒልክ አንደኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ
ሰዓት ሁሉም 1:30
ለፈተና ስመጡ:-
1. ሞባይ መያዝ የተከለከለ ነው
2. የታደሰ መታወቂያ መያዝ አለባችሁ
3. ምንም ዓይነት ወረቀት መያዝ የተከለከለ ነው
4. ማንኛው ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመሩ ከ30 ደቂቃ በኋላ መግባት አይቻልም
4. የፈተና ስነ ስርዓት ማክበርና ለፍተሻ መተባበር

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በሙሉ
የ2016 ዓ.ም ተመዛኝ መምህራን ድልድል ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በፊት ለመመዘን ስማቸው ተላልፎ በድልድሉ ላይ የተዘለሉ ካለ ፈጥናችሁ እንድታሳውቅን እናሳስባለን፡፡
የፈተና ቀን ግንቦት 1/2016 ዓ.ም

Читать полностью…

Arada education office

የ2016 ዓ.ም ተመዛኝ መምህራን ከዚህ በፊት ከተላኩት የቀሩ ካሉ ቶሎ እንድያሳውቁ የት/ቤት ር/መምህራን መረጃውን አድርሱን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሂሳብና ሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ-ርዕይና ውድድር ተካሄደ።

(ቀን ሚያዚያ 18/ 2016 ዓ.ም) "በፈጠራ ስራ የዳበረ ትውልድ ለሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል በከተማ ክፍለ ከተማው አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው የሂሳብና የሳይንስ የፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ እና ውድድር ላይ በተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ለእይታ ቀርበዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም እንደተናገሩት እየተካሄደ ያለው የሂሳብና ሳይንስ የፈጠራ ስራዎች ውድድር ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልፀው የመርሃ-ግብሩ መዘጋጀት በተማሪዎች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር የምርምር የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ክህሎታቸው የበለጠ እንዲያድግ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቀፀላ በበኩላቸው በሳይንስና ሂሳብ የፈጠራ ስራዎች ለሃገር እድገትና ብልፅግና መሰረት ናቸው ብለው ተማሪዎች ለሚሰሩት የፈጠራ ስራ ጽ/ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በውዝዋዜና በፈጠራ ስራው ተወዳድረው አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎችና መምህራን የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር መከናወኑን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

Читать полностью…

Arada education office

የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጵ/ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት በለፉት ዘጠኝ ወራት የተሰሩ ስራዎችን ዕቅድ አፈፃፀም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማለትም የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቨይዘሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ማካሄድ ጀምሯል።በዕለቱም የተሰሩ ስራዎች ከተመረጡ በትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና ክላስተር ማዕከል ሪፓርት ከቀረበ በኃላ የክፍለ ከተማውን የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ።

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲሁም ለመንግስት 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መረጃዉን በቅፁ መሰረት በአስቸካይ ሞልታችሁ ዛሬ እስከ 10፡00 እንድትልኩልን።

Читать полностью…

Arada education office

ብሄረ ኢትዮጵያ ት/ቤት ዛሬ 21/07/2016 ስለ ተማሪዎችን ውጤት እና ስነ-ምግባር በተመለከተ ከ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች ጋር ውይይት አደረገ። የተማሪን ውጤትም ገመገመ።

Читать полностью…

Arada education office

በቀን 19/07/2016 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የትምህር ጉባኤ ተካሄደ። በመድረኩም በክፕአይ ምዘና እና የአገልግሎት አሰጣጥ ምዘና ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የመጀመሪያ ደረጃ ፣2ኛ ደረጃ እና ወረዳ ት/ጽ/ቤቶች የዋንጫ እና የሰርተፊኬት እውቅና ተሰጥቷል።

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ርዕሳነ መምህራን በሙሉ ነገ ጥዋት 2፡30 ላይ የመማር ማስተማር ም/ርዕሳነ መምህራን ላኩልን ባልነው መሰረት ት/ጽ/ቤት 7ኛ ላይ እንድትልኳቸው በድጋሚ እናሳስባለን።
ማሳሳቢያ ሁለት ርዕሰ መምህር ባለበት ት/ቤት ም/ር/ መምህር ይመጣሉ።
ሰዓት ይከበር።
ጥሪው ለ20/07/2016 ዓ.ም ነው።

Читать полностью…

Arada education office

የከተማ ግብርና በመስከረም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

(ቀን መጋቢት 13/2016 ዓ.ም) በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በዳግማዊ ምንሊክ 2ኛ ደረጃ ሱፐርቪዥን ክላስተር ማዕከል ስር የሚገኘው መስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Читать полностью…

Arada education office

በአራዳ ክ/ከተማ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የስኩል-ኔት መሰረተ ልማትን ለማሻሻል optimization ስራ ሲሰራ

Читать полностью…

Arada education office

በእት/ትቅደም ት/ቤት የእነቶች ቀን ተከበረ።

Читать полностью…

Arada education office

የሴቶች ቀን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተከብሮ ውሏል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel