ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶችና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች በሙሉ
ለ2017 ዓ.ም የመ/አስተዳደር፣ የኪራይ ስባሳቢነትና አዋኪ ጉዳዮች ዕቅድ እንደ ተቋማችሁ ተጨባጭ ሁኔታ በመለየት እስከ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም በተላከው ቅፅ መሰረት በሀርድና በሶፍት ኮፒ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡
Hubachiisa akeekkachisaa.
Manneen barnootaa sadarkaa tokkoffaa Fi sadarkaa lammaffaa tokko tokko keessatti yeroo galmeen eegalamee jiruu fii hojiiwwan gurguddoon haala galmeen waliin walqabatee hojjetamuu qabuutti suppervaayizaroonni muraasni Fi hoggantootni sirna barnoota Afaan Oromoo bakka buutanii jirtan eeyyama waggaa jechuun ba'aa jirachuun keessan mirkaneeffachuu dandeenyee jirra.kun immoo kaayyoo Fi karoora baay'ina barattoota sirna barnoota Afaan Oromoo dabaluuf hojjetamaa jiru faallaa waan ta'eef kanarraa of qusachuun gara hojii galmee barattootaa milkeessuutti humna qabdanii Fi tooftaa mataa keessaniin Akka irratti hirmaattan cimsinee isin beeksifna! Kana alatti kan ergama mataa isaa hin baaneef itti gaafatamummaa dhufuuf itti gafatamuummaa isaa kan fudhatu abbaama kallattii kana cabse ta'uu isaa irra deddeebinee isin beeksifna.
Olmaa gaarii.
Milkaa'ina galmee bara 2017 hunda keenyaaf haa ta'u!
ቀን 21/10/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ
የሰኔ ወር ደመወዝ ለፋይናንስ ገቢ ያላደረጋችሁ ዛሬ በአስቸኳይ ገቢ እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።
ስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
• የስብሰባ ቀን=ማክሰኞ 11/10/2016ዓ.ም
• ቦታ=ት/ት ፅ/ቤት 7ኛ ፎቅ
• ሰዓት=8:00
• መገኘት ያለበት የመንግስት እና የግል ዋና ርዕሰ መምህር እና የወረዳዎች ት/ት ፅ/ቤት ሃላፊዎች
• መድረኩን የሚመራ =አቶ ደሳለኝ ደበሌ የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ
ማሳሰብያ:- ተደራራቢ ስራዎች እንዳሉ ቢታወቅም አጀንዳዎቹ አስቸኳይ በመሆናቸው በመሆኑ በሰዓቱ እንገናኝ።
. ጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው የሚመጡ አዲስ የተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል
. መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለተማሪዎች ስለ ት/ቤቱ ህገደንብና ተያያዥ ጉዳይ ላይ ገለጻ ይሰጣል
. መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት ይጀምራል
. መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ይጀምራል
. ህዳር 16-18 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል
. ከጥር 7-9 ቀን 2017 ዓ.ም ለ6ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል
. ከጥር 19-23 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል
. ከጥር 26-29 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን ፈተና የሚያርሙበት እና ውጤት ማጠናቀሪያ ሳምንት
. ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል
. የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ይጀምራል
. ሚያዚያ 6-8 ቀን 2017 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል
. ግንቦት 19-22 ቀን 2017 ለ6ኛ፣ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል
. ከሰኔ 3-4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ይሰጣል
. ከሰኔ 9-11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይሰጣል
. ከሰኔ 16-20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል
. ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል
. ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የውጤት መግለጫ ካርድ በመስጠት የዓመቱ ትምህርት ይጠናቀቃል
ማሳሰቢያ፡-
1. በ1ኛ ወሰነ ትምህርት 103 የትምህርት ቀናት ሲኖሩ በ2ኛ ወሰነ ትምህርት 101 ቀናት በጠቅላላው በዓመቱ 204 የትምህርት ቀናት አሉ፡፡
2. ትምህርት ቢሮ የትምህርት ካላንደሩና ካላሻሻለ በስተቀር ማንኛውም ትምህርት ቤት ከካላንደሩ ውጪ የትምህርትን ስራ ማከናወን የተከለከለ ነው፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: addisababaeducationbureau9728" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- aaeducationbureau" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ /channel/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶችና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች በሙሉ
ለ2017 ዓ.ም የመ/አስተዳደር፣ የኪራይ ስባሳቢነትና አዋኪ ጉዳዮች ዕቅድ እንደ ተቋማችሁ ተጨባጭ ሁኔታ በመለየት እስከ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም በተላከው ቅፅ መሰረት በሀርድና በሶፍት ኮፒ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡
እንደምን ዋላችሁ ውድ የወረዳ ት/ፅ/ቤት ሀላፊዎች ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች
👉👉👉በ8/10/2016 ዓ.ም የ2016 ዓ.ም የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት የክረምት ንቅናቄ ስራዎችን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ 11ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 የሚጀመር ትልቅ መድረክ ያዘጋጀ በመሆኑ በመድረኩ ላይ የሚገኙ አካላት
1.የወረዳው ት/ት/ፅ/ቤት ሀላፊ
2.የወረዳ የጎልማሶች መሰረታዊ ት/ት ባለሙያ በሁለቱም ስርዓተ ት/ት
3.በየወረዳችሁ ያሉ የጎልማሳ ት/ት አመቻቾችና አስተባባሪዎች ሲሆኑ ማርፈድና መቅረት የማይቻል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ🙏
የስብሰባ ጥሪ በተመለከተ፡-
ቦታ፤አራዳ ክ/ከተማ ትልቁ አዳራሽ
ቀን፡ 7/10/2016ዓ.ም
ሰዓት፡ ከጥዋቱ 2፡00
በስብሰባው መገኘት ያለባቸው ፡- የቅድመ አንደኛ፤የመጀመርያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ የግል ት/ቤቶች ባለቤቶች
ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊዎች መድረኩን ትምህርት ቢሮ ስለሚመራው ማንም እንዳየቀር በየወረዳችሁ በመተማመን ጥሪ እንድታደርጉ እና በውይይት ቀን ቀድማችሁ በመገኘት የማስተባበር እና አቴንዳንስ የመያዝ ስራ እንድትሰሩ፡፡
አስቸኳይ ማስታወቅያ
ለሁሉም የመንግስት የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህራን የበጀት defence እንድታደርጉ።
👍ቀን=30/09/2016ዓ.ም
👍 ሰዓት=4:00
👍ቦታ=አራዳ ክፍለ ከተማ 8ኛ ፎቅ
👍መገኘት ያለበት=ዋና ርዕሰ መምህር እና ፍይናንስ ቡድን መሪ
የወረዳ ት/ጽ/ቤቶችና ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከላይ የተላከውን ቢጋር መሰረት የ2016 ዓ.ም የዓመቱን ሪፖርት እስከ ሰኔ 10/2016 ዓ.ም እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
Читать полностью…ቀን 23/09/2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አራዳ ቅርንጫፍ የታክስ ክበባት የአሸናፊዎች አሸናፊ በተደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር ከኒውኤራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ፅዮን ብርሃኑ 1ኛ በመውጣት ተሸላሚ መሆን ችላለች።
የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
(ሀምሌ 5/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አድርገዋል።
በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።
የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ ተግባር ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው በቀጣይ ጥቂት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ አስታውቀዋል።
ይህን ፎርማት ከዚህ በፊት መላካችን ይታወሳል። ይሁን እንጂ በቅፁ መሰረት ዕቅዱ ታቅዶ ያልተላከ በመሆኑ በድጋሚ ቅፁን የላክን ስለሆነ መረጃውን እስከ ሐምሌ 5 እንድትልኩ። የመ/አስተዳደር ችግር፣ የሌብነትና ብልሹ አሰራር ችግር እንዲሁም የአዋኪ ጉዳዮች ችግር የለብንም የምትሉ ት/ቤቶችና ወረዳዎች አሳውቁን። መልስ ካልሰጣችሁ ችግሩ የለም ማለት ነው።
Читать полностью…ለመንግስት ት/ቤት ርእስ መምህራን የ2017 የተማሪ ምዝገባን በተማለከተ ተጨማሪ ግንዘቤ ለመፍጠር ዛሬ 8 ሰአት(1/11/2016) ክፍለ ከተማ ትምህት ጽ/ቤት እንድትገኙ እየጠየቅን ጥያቄ የሌለዉ በትምህርት ቢሮ website https://aaceb.sims.addislearning.edu.et/ በመግባት ትምህርት ቤታችሁን በመምረጥ ምዝገባዉን መጀመር ትችላላችሁ username and pasward በቴሌ sms 8465 ተልኳል አረጋግጡ
Читать полностью…የ መንግስት ትምህርት ቤቶች ይመለከታል የonline ምዝገባን በሚመለከት በተሰጣችሁ ስልጠና መሰረት ዝግጅት ስለማድረጋችሁ አሳውቁን ያጋጠማችሁ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጠይቁ
Читать полностью…ለ1ኛ እና 2ኛ የመንግስት ርእሰ መምህራን በ25 /10/16 ትምህርት ቢሮ 12ኛ ፎቅ የኦላይን ምዝገባን በሚመለከት ስልጠና ስለሚሰጥ 2:30 መገኘት ያለባቸው 1.ዋና ርእሰ መምህር 1 2.የአይሲቲ ባለሙያ 2 3.የሪከርድ ባለሙያ 1
Читать полностью…ከ 12ኛ ክፍል ኦንላይን ፈተና ጋር በተያያዘ በኦፕትማይዜሽን ፕሮጀክት የሚሳተፉ አካላት ትምህርት ቤቶችን ለፈተና ብቁ እንዲያረጉ አስገዳጅ ተልዕኮ ተሰቷቸዋል በመሆኑም በሁሉም የመንግስት ትምህርትቤቶች በዋናነት :-
አክሰስ ስዊች
ዳታሴንተር
ICT ላብ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች በማንኛውም ሰዓት እና ቀን ክፍት እንዲደረግ ቢቻል ቁልፎች ርእሳነ መምህራን ጋር ቢቀመጥ እያሳወቅን ይህ ሳሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ትምህርትቤቱ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን
ማሳሰቢያ :- ትምህርትቤቶች መረጃ በወቅቱ አይደርሰንም የሚል ቅሬታ እያቀረቡ ስለሆነ መረጃ ሲተላለፍ ማስረጃዎችን እየያዝን
ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ጣቢያ ሀላፊዎች
ሰኞ 5:00 ሰዓት ላይ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ላይ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ እያሳሰብን በዛው ለ6ኛ ክፍል ፈተና ዶክመንቶች እንድትወስድ እናሳስባለን ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/
(ሰኔ 7 /2016 ዓ.ም) በ2017 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ወጥነት ያለው የትምህርት አተገባበር በማስፈለጉ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡
. ከሰኔ 24 እስከ 30/2016 ዓ.ም ድረስ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ እና የመጽሐፍት ስርጭት
. ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ ይደረጋል
. ከነሃሴ 21-30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የ7ተኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል
ቅድመ መደበኛ ላላችሁ የግል ት/ቤቶች በአዲስ አበባ ት/ቢሮ ቀዳማይ ልጅነት ዳይሬክቶሬት በቀን 10/10/2016 ዓ.ም ለዋና ር /መምህራን ስልጠና ስለሚሰጥ በጧቱ 2:00 ሰዓት ወንድራድ ት/ቤት ኮተቤ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
Читать полностью…በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በ2016 ዓ.ም ከሰኔ 4/2016 እስከ ሰኔ 05 በ10 ክላስተር ማዕከላት ሲሰጥ የቆየው የ8ኛ ክፍል ፈተና በሰላም ተጠናቋል።
Читать полностью…የአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸዉን ገልጿል።
(ሰኔ 3/2016 ዓ.ም) የአራዳ ክ/ከተማ ት/ት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ደበሌ በክ/ከተማ ውስጥ በሚገኙ 51 የግልና የመንግስት ት/ቤቶች ለ1952 ወንድ እና ለ2456 ሴት በድምሩ ለ4408 የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ይህንንም ለማስፈጸም የሚያስችሉ የፈተና ቁሳቁስ፣ የመፈተኛ ቦታ ዝግጅት፣ የፈታኝና ክትትል የሚያደርጉ አካላትን የመመደብና አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታ እንዲኖር መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ተፈታኝ ተማሪዎች በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ መደረጉን የገለጹት ሀላፊው ፈተናው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አንዱ በመሆኑ ተማሪዎች ካላስፈላጊና ከተከለከሉ ተግባራት ተቆጥበው ፈተናቸውን በአግባቡ እንዲፈተኑ አሳስበዋል፡፡
በፈተና ስርአቱ ላይ አስተማሪዎች፣ ተማሪዎች፣የወላጅ ኮሚቴዎችና መምህራን ኮሚቴዎች የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች አጠቃላይ አመራሩ የጸጥታና ባለድርሻ አካላት በጋራ ትብብር ፈተናው በጥሩ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አቶ ደሳለኝ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
አስቸኳይ ማስታወቅያ
ለሁሉም የመንግስት የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህራን በቀን 30/09/2016ዓ.ም የበጀት defence ስላለ 8ኛ ፎቅ ፍይናንስፅ/ቤት እንዲገኙ እና በጀታቸውን ተወያይተው እንዲተማመኑ ።
እንኳን ደስ አለን አላችሁ !!!በ9ኛው ከተማ አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መስከረም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ፋልካን አካዳሚን በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
Читать полностью…