av12c | Unsorted

Telegram-канал av12c - Arada education office

6896

Subscribe to a channel

Arada education office

ቀን 02/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ዋና ር/መምህራን በሙሉ
ማክሰኞ 7፡30 ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

Photo from Desalegn Debele

Читать полностью…

Arada education office

Photo from Desalegn Debele

Читать полностью…

Arada education office

አስቸኳይ መልዕክት

እንዴት ዋላችሁ

ትላንት በነበረን የተመዛኞች ኦረንቴሽን እና  ጥቅምት 09/2017 በዚህ ቴሌግራም ቻናል ባሳወቅነው መሰረት ከነገ ቅዳሜ 23_24/02/2017 ጀምሮ የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና የሚጀመር ስለሆነ

ከኮተቤ ዮኒቨርሲቲ ፕሮግራም ጋር በማጣጣም ቅዳሜና እሁድ የነበረው ስልጠና አራዳ ክ/ከተማ ቅዳሜ እሁድ ቂርቆስ በሚል ስለተሻሻለ በተቀራኒው ስልጠና የምትገቡት መምህራን አራዳ እሁድ ዳግማዊ ምኒልክ ቂርቆስ ደግሞ ምስራቅ ጎህ የተመደባችሁ ለመመዘን ስለሆነ

ስልጠና የማትገቡት ተመዛኞች ነገ ከ2:30  ጀምሮ ምዘና ስለሚጀምር በየክ/ከተማችሁ በተመደባችሁት መሰረት በት/ቤቱ በመገኘት የተመደባችሁበትን ክፍል በማየት ምዘናውን እንድታከናውኑ እየገለፅን

ትላንት የገለፅንላችሁ ያለፉ ተመዛኞች ቁጥራችሁ ውስን የሆነበት የትምህርት አይነት ወደ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስለተመደባችሁ ስም ዝርዝራችሁን እስክንለቅ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን


ር/መምህራን ተመዛኝ መምህራንና ትምህርት አመራሮች በት/ቤታችሁም በማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ አሳውቁ
በተጨማሪም ሁሉም ተመዛኝ የዚህ ቴሌግራም ቻናል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሊንኩን ሼር አድርጓቸው

/channel/licencingAradakirkos

እናመሰግናለን

ማሳሰቢያ:- የፕሮግራም ለውጥና አዲስ መረጃዎችን ስለምንለቅ ቴሌግራሙን ተከታተሉ

የመመዘኛ ጣቢያ አድራሻ

ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ኪሎ
ከአራዳ ክ/ከተማ የምትመጡ ተመዛኞች


ምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካሳንቺስ ቶታል   ፊት ለፊት
ከቂርቆስ ክ/ከተማ የምትመጡ ተመዛኞች

Читать полностью…

Arada education office

ብሐራዊ ቤተ መንግስት
ትምህርት ብልጭታ
መሃል ግንፊሌ
አፍሪካ ቁጥር 1
ገነት አፀደ ህፃናት
ኢትዮጵያ እድገት
ደግማዊ ሚኒልክ መሰናዶ
አበበችጎበና
ቤተሊሂም
ቅለም ወርቅ
መስከረም 2ኛ ደረጃ

Читать полностью…

Arada education office

ቀን፡21/02/2017
ማስታወቂያ
ለሁሉም የ12ኛ ክፍል አስፈታኝ ት/ቤቶች እና በግል ለተፈተናችሁ ተፈታኞች በሙሉ
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናችሁ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና በግል ለተፈተናችሁ ተፈታኞች የውጤት ካርድ ስለመጣ እስከ ከ 22/02/2017 ድረስ ብቻ አንድትወስዱ ፡፡ ትምህርት ቤ/ቶች የትምህርት ቤቱ ር/መምህራን ወይም በደብዳቤ የተወከለ ሰው መጥቶ እንዲወስድ እናሳስባለን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 20/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት የመ/ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራንና ለሁሉም የግል ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ
በቀን 21/02/2017 ዓ.ም ቀኑ 8 ሰዓት ላይ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ በመሆኑ ትምህርት ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ላይ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

አስቸኳይ መልዕክት

በአራዳና ቂርቆስ ክ/ከተማ ስር ለምትገኙ ርዕሰመምህራን እና መምህራን በሙሉ

ግንቦት 2/ 2016ዓ.ም ላይ የመምህራንና የትምህርት አመራር የሙያ ብቃት የፅሁፍ ምዘና መስጠታችን ይታወቃል።

በተሰጠው የፅሁፍ ምዘና ውጤት መሰረት 62.5 እና በላይ ያመጡ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና ለማካሄድ ለተመዛኞች ኦሬንቴሽን ስለሚሰጥ ሐሙስ ማለትም በ21/2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የት/ቤት ር/መምህራን መልዕክቱን እንድታደርሷቸው እያልን ጥሪውን በት/ቤቱ የማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ በሰአቱ እንዲገኙ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት

አራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Читать полностью…

Arada education office

በድጋሚ
ለአራዳ ክ/ከተማ የመንግስት ት/ቤቶች በሙሉ
የሙያ ፍቃድ ፖርት ፎሊዮ መዛኝ መምህራን የሙያ ፍቃድ ያለቸውን ዲግሪና ማስተርስ ያለቸው እንድመዘገቡ ማሳወቃችን ይታወቃል። በመሆኑም የተፈለገው የሰው ሀይል ያልተሟላ ስለሆነ
ጂኦግራፊ 2 ፣ አማርኛ 4፣እንግሊዘኛ 8፣ ስቴቲክስ 1፣ አርት 1፣ አ/ሳይንስ 1፣ ISS 1 ሙዚቃ አፋን ኦሮሞ 1፣ ቋንቋ ለአማርኛ 1፣ አፋን ኦሮሞ enviromental Science ፣ 1፣ ነገ እስከ 6:00 መምህራን ልማት መጥተው እንዲመዘገቡ በድጋሚ በማስታወቂያ እንድታሳውቁልን እንጠይቃለን ።

Читать полностью…

Arada education office

👍አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ:-
👍የስብሰባ ቀን ዓርብ 15/2/2017ዓ.ም
👍ሰዓትን=7:30
👍ቦታ =ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት
👍ተሳታፊዎች=ሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህራን

Читать полностью…

Arada education office

በቦሌ ክ/"ከተማ ተጠርቶ የነበረው የሰው ሀይል ቡድን መሪዎች ስብሰባ ስለቀረ ር/መምህራን በእናንተ በኩል ጥሪው መሠረዙ ይነገራቸው።

Читать полностью…

Arada education office

የሰዓት ማስተካከያ መደረጉን ማሳወቅን ይመለከታል። ለሰኞ ጥዋት 3፡00 የተጠራው ስብሰባ ወደ ከሰዓት 7:30 የተቀየረ በመሆኑ የተጠራችሁ በሰዓቱ ተገኙ።

Читать полностью…

Arada education office

አስቸኳይ መልዕክት

በአራዳና ቂርቆስ ክ/ከተማ ስር ለምትገኙ ርዕሰመምህራን በሙሉ

ግንቦት 2/ 2016ዓ.ም ላይ የመምህራንና የትምህርት አመራር የፅሁፍ ፈተና መስጠታችን ይታወቃል።

የፅሁፍ ፈተና ውጤት የደረሰ በመሆኑ መጥታችሁ እንድትወስዱ  የት/ቤት ር/መ/ር በድንቅ ስራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት በመገኘት ከመምህራን ሙያ ብቃት ባለሙያዎች በስማቸው በፖስታ የታሸገውን የተፈታኞች ውጤት በቁጥራቸው ልክ በመረከብ በቀን 11/02/2017ዓ.ም ለተፈታኞች እንደታሸገ እንድትወስዱ እያሳሰብን

1. ውጤታችሁ ላይ ቅሬታ የሚኖራችሁ መምህራንና የትምህርት አመራር በተያያዘው የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም በመሙላት እንድታቀርቡ

2. ተፈትነው ስም ዝርዝራቸው ያልተገኙ ካሉ ለማመሳከር እንዲመች ር /መ/ራን ወደ ተቋማችን ስትመጡ በት/ቤታችሁ ምዘናውን የወሰዱ አካላት መረጃን በማጥራት ይዛችሁ እንድትገኙ (ከስራ ክፍሉ ከተያዘው ጋር ለማመሳከር )

3. ውጤታችሁ በመረከብ ከ62.5 በላይ ያመጣችሁ ተፈታኞች የማህደረ ተግባር ፈተና ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ስለሚሰጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታካሂዱ እናሳስባለን።

ስልክ ሲደወል ስልካቸው ያልሰራ ር /መ/ራን ስለአጋጠመን መረጃው እንዲደርስ ይህን መልዕክት ያያችሁ አካላት መረጃውን  ለር/መ/ራን አካፍሉ


የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት

አራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Читать полностью…

Arada education office

ለመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን
የሂሳብ እና እንግሊዘኛ የትምህርት ዓይነቶች በተመለከተ ከጥቅምት 4 ጀምሮ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች ወደ ተቋማችሁ የሚመጡ በመሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉላቸው እንጠይቃለን።

Читать полностью…

Arada education office

ሂሳብና እንግሊዝኛ በት/ት ዘመኑ የት/ት ማህረሰቡ የርብርብ መአከል ሆኖ በትኩረት ይሰራበታል ይህ ማለት የሌላ ሳብጀክት መምህራኖች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ የCPD ፍላጎት ለይተው ያቅዳሉ ይተገብራሉ ምክንያቱም እንደስሙ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ስራ ስለሆነ።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 02/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግት ት/ቤቶችና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች በሙሉ፡-
የሪፎርም አተገባበር ዙሪያ ክትትልና ድጋፍ ለማድረገ ከረቡዕ ጀምሮ ከከተማ ባለሙያዎች የሚመጡ በመሆኑ ቅድመ ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
መልካም ቀን

Читать полностью…

Arada education office

29/02/17

በ28/02/17 የስልጠና ጥሪ እንዲተላለፍ የለጠፍነው ማስታወቂያ ላይ የቦታ ለውጥ የተደረገ መሆኑ ተነግሮናል። በዚህ መሠረት የስልጠናው ቦታ ከንቲባ ጽ/ቤት በሚገኘው አዳራሽ ሆኗል። ስለዚህ በስልጠናው ላይ የሚሳተፈውን አንድ መምህር እና አንድ ተማሪ በተቀየረው ቦታ መሆኑን አሳውቃችሁ በሰአቱ እንድትገኙ።
ማሳሰቢያ፣ ተማሪዎች ዩኒፎርም መልበስ አለባቸው
መምህራን መታወቂያቸውን መያዝ አለባቸው
በስልጠናው ላይ የሚሳተፉት ማን ማን እንደሚሆኑ ደብዳቤ መያዝ አለባቸው

Читать полностью…

Arada education office

ማሳሰቢያ፡-
በክፍለ ከተማችን ስር ለሚትገኙ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘናው የአራዳ በሙሉ ዳግማዊ ሚኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን የምዘና ቀናት ቅዳሜና እሁድ (ከ23-24/02/2017 ዓ.ም) መሆኑን አውቃችሁ በተባለው ት/ቤት በመገኘት እንድትመዘኑ እናሳስባለን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 22/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ፡-
በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መፅሐፍት እየተሰራጨ በመሆኑ ሰው በመላክ መፅሐፍት ዛሬውኑ እንድትወስዱ እያሳሰብን ከዛሬ በስተቀር መፅሐፍት የማንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

ሰላም ወንድምና እህቶች
በየትምህርት ቤታችሁ የጥቅምት ወር ደሞዝን በአዲሱ ስኬል መሰረት ሰርታችሁ እንድትልኩ ለሰው ሃይል ባለሙያዎች በፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሓይል ጽ/ቤት በኩል እስከ ጥቅምት 2/2017 እንዲላክ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ምላሽ ያልሰጣችሁ በመሆኑ ደሞዝ ለመስራት አስቸግሯል፡፡ ስለሆነም ርእሳነ መምህራን የየራሳችሁ ት/ቤት በትክክል መሰራቱን አረጋግጣችሁ እስከ ዛሬ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም አስከ ቀኑ 5፡00 ተጠናቆ ለክፍለከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ ገቢ እንድታደርጉ እያሳወቅን የማይልክ ትምርት ቤት ለሚፈጠረው ችግር ሃላፊነቱን በራሱ የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

አስቸኳይ የስልጠና ፕሮግራም ማሻሻያ መልክት
==============================
አማርኛና አፋን ኦሮሞን እንደ 2ኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን ስልጠና ለሁለት ቀን (23-24/02/2017) ያልነው ወደ 1 ቀን ስለተቀየረ ክ/ከተሞች ከዚህ ቀጥሎ በወጣላችሁ ፕሮግራም መሠረት ሰልጣኞችን ትልኩልናላችሁ
ቅዳሜ:- አዲስ ከተማ ፣አራዳ ፣ኮልፌ ፣የካ እና ጉለሌ
እሁድ:- ልደታ፣ ቦሌ፣ አቃቂ፣ ን/ስልክ፣ ለሚኩራ፣ ቂርቆስ፣ መነንና ገላድ አዳሪ
የቦታ ለውጥ የለም እዛው ኮተቤ የት/ት ዩኒቨርሲቲ ነው

Читать полностью…

Arada education office

በአራዳ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የሚከናወነውን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተመለከቱ የምዝገባ ቅድመ ሁኔታዎች
1. የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መላው ትምህርት ቤቶች ከ5 አመት በላይ ያሉ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችን፣ የምገባ ማዕከላት ሰራተኞችን የመመዝገብ ዘመቻ ላይ ያተኮረ ነው፤
2. የምዝገባው ሂደት ስልክ ቁጥር አስፈላጊ በመሆኑ ስልክ የሌላቸው ልጆች በወላጆች ወይም በአሳዳጊዎች ስልክ እንዲመዘገቡ ይደረግ፤
3. እድሜያቸው ከ 5- 16 የሆኑ ተመዝጋቢዎች የፍቃድ መስጫ ቅጽ በወላጅ ወይም በአሳዳጊ መሞላት ስላለበት ከምዝገባው አንድ ቀን አስቀድሞ የምዝገባ ቅጹን ለወላጆች በመላክ ተሞልቶ ወደ ትምህርት ቤት ይላክ፤ (መምህራን እና ርዕሰ መምህራን የልደት ምዝገባ ወረቀቱ የልጆቹ ስለመሆኑ እንዲሁም የፍቃድ መስጫ ቅጹ በወላጆች በትክክል ስለመሞላቱ በማረጋገጥ ይኖርባቸዋል)፤
4. ከ5 እስከ 16 ዓመት የሆኑ ተመዝጋቢዎች የወላጅ ወይም የአሳዳጊ መታወቂያ ኮፒ ይዘው መገኘት አለባቸው፤
5. እድሜያቸው ከ16 በላይ የሆኑ ወጣቶች ለመመዝገብ የሚያስፈልገውን የፍቃድ መስጫ ቅጽ እራሳችው በመሙላት መመዝገብ ይችላሉ፤
6. ወላጆች አስቀድመው ከተመዘገቡ የፋይዳ ቁጥራቸውን በፍቃድ መስጫ ቅጹ ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል፤
7. በክረምት ዘመቻ የልደት ምዝገባ መከናወኑ ይታወሳል፤ የልደት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው በሙሉ ምስክር ወረቀቱን በማምጣት እንዲመዘገቡ መረጃው ይውረድ፤ የልደት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሌላቸው ብቻ በትምህርት ቤት መታወቂያ ይመዝገቡ፤
8. የዘገየ የፋይዳ መለያ ቁጥር ማረጋገጫ ወደ ስልካቸው በአጭር የስልክ መልዕክት (SMS) ለማስላክ እባክዎን id.et/help ወይንም 9779 ይጠቀሙ፤
9. .የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት ክፍያ የለውም፣ ዲጂታል መታወቂያ ማለት ባለ 12 አሀዝ ልዩ ቁጥር በመሆኑ ካርድ ማሳተም ግዴታ አይደለም፤

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 20/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት እና የግል ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ
በ2016 ዓ.ም የሙያ ብቃት ምዘና ተመዝነው 62.5 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ መምህራን ሐሙስ ማለትም በ21/2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በማህደረ ተግባር ዙሪያ ኦሬንቴሽን ስለምሰጣቸው የት/ቤት ር/መምህራን መልዕክቱን እንድታደርሷቸው እያልን ጥሪውን በማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ መምህራን እንድገኙ አድርጉዋቸው።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 18/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች በሙሉ
አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ ትምህርት እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መ/ራን ስም ዝርዝር እስከ 8፡ 00 ሰዓት ድረስ ለስርዓተ ትምህርት ቡድን እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡
መልካም የስራ ቀን!!!

Читать полностью…

Arada education office

ለአራዳ ክ/ከተማ የመንግስት ት/ቤቶች የሙያ ፍቃድ ፖርት ፎሊዮ መዛኝ መምህራን የሙያ ፍቃድ ያለቸውን ዲግሪና ማስተርስ ያለቸው ነገ እስከ 6:00 መምህራን ልማት መጥተው እንዲመዘገቡ በማስታወቂያ አሳውቁልን አሰቸኳይ ነው።

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስት ተ/ቤት ር/መምህራን
ነገ ጥዋት 2፡30 የት/ቤት የሰው ሀይል ቡድን መሪዎች ቦሌ ክፍለ ከተማ ስብሰባ ላይ እንድገኙ በእናንተ በኩል ጥሪው እንድደርሳቸው አድርጉ፡፡
መልካም ቀን!

Читать полностью…

Arada education office

የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
በቀን 11/2/2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም እና የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ በጋራ ግምገማ ይደረጋል። በዚህም መሰረት
1ኛ. የመንግስት ት/ቤት ሁሉም ዋና ር/መምህራን
2ኛ. የ2ኛ ደረጃ ሁሉም ሱፐርቫይዘሮች
3ኛ. የመ/ደረጃ ክላስተር አስተባባሪዎች
ሰኞ 3፡00 ት/ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ እንድትገኙ እናሳስባለን። መቅረትና ማርፈድ በፍፁም የተከለከለ ነው። በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ የማትገኙ አመራሮች ጽ/ቤቱ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂ የማንሆን መሆኑን እየገለፅን ም/ር/መምህራን የሒሳብና እንግሊዘኛ ቀን በዕለተ ሰኞ ተግባራዊ መሆኑን እንድከታተሉ አድርጉ። ሶስት ሰዓት የሚጀመርበት መሆኑን አውቃችሁ በሰዓት ተገኙ።

Читать полностью…

Arada education office

የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የሂሳብ እና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት ለማሻሻል ስትራቴጂ በመንደፍ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ትግበራውን ለመከታተል የሱፐርቪዥን ቡድን በማዋቀር የትምህርት ተቋማት ክትትል መደረጉ ይታወቃል።በመሆኑም በቀን  08/02/2017 ዓ.ምከቀኑ 7፡00 ሰዓት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ በቢሮ ኃላፊ የሚመራ ውይይት ስለሚከናወን
1ኛ. የመንግስት 1ኛ መካከለኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዋና ርዕሳነ መምህራን ፤ 2ኛ.የክፍለከተማ እና ወረዳ ሱፐርቫይዘር አስተባባሪዎች
3ኛ. ድጋፍና የክትትል ስራ ላይ የተሳተፋችሁ በተባለው ቀን እንዲትገኙ እናሳስባለን፡፡
መቅረትና ማርፈድ አይቻልም።
ሰዓት ይከበር
ት/ጽ/ቤት

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤት ር/መምህራን ጥቅምት 4 የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመሆኑ ዕለቱን አስመልክቶ በተለያዩ ፕሮግራሞች እንድታከብሩ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች የሂሳብና የእንግሊዘኛ ትምህርትን ማሻሻል ከመምህሩ እስከ አመራሩ ጭምር አንዱ የተሙማ ዕቅድ ሆኖ እንዲሰራበት ከወዲሁ እናሳስባለን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel