የሰብሰባ ጥሪ ለመንግስት ዋና ርእሰ መምህራን የተማሪዎችን on line ምዝገባን በሚመለከት ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ስለሚሰጥ አራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ነገ 4/4/17 ከሰአት 8 ሰአት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን:: መረጃና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ቡድን
Читать полностью…ለሁሉም ወረዳ ት/ጽ/ቤቶችና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ በእንግሊዘኛን ሂሳብ ስትራቴጂ ዙሪያ ድጋፍን ክትትል የሚደረግ በመሆኑ የሚመጡ ባለ፣ያዎችን እንድታስተናግዱ እናሳስባለን፡፡
መልካም ቀን፡፡
ለውድ ርዕሳነ መምህራን !
ስላማችሁ ይብዛ!
ዛሬ አርብ ከሰዓትና ነገ ቅዳሜ ይዘነው የነበረው የሪፎርምና የሌሰን ስተዲ ስልጠና በአሰልጣኝ አለመመቸት ምክንያት ለቀጣይ ሣምንት ያዞርነው መሆኑን በትህትና እንገልፃለን ።
ቀን 24/03/2017 ዓ.ም
የስብሰባ ጥሪ
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ዋና ር/መምህራን፣ የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች ዛሬ 8፡00 ሰዓት ላይ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
በውይይት ላይ ስትገኙ፡-ድጋፍና ክትትል ከተደረገ በኃላ በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት፣ በሪፎርም በክፍተት ተለይተው የተስተካከሉ እና በተጨማሪ የተሰሩ ስራዎችን መረጃ በሪፖርት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- መቅረት፣ ማርፈድ፣ መወከል የማይቻል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ቦታ ትምህርት ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ
ቀን 23/03/2017ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን
ከ24/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የእውቅና ምዘና በባለሙያዎች የሚካሄድ በመሆኑ መዛኞች ስመጡ አስፈላጊውን መረጃ እንድታሳዩ እናሳውቃለን።
ቀን 19/03/2017 ዓ.ም
ማሳሰቢያ፡-
የስብሰባ ጥሪ የቀን ለውጥ መደረጉን ማሳወቅን ይመለከታል፡፡
ተሳታፊዎች
1ኛ. ሁሉም የመንግስት ዋና ር/መምህራን
2ኛ. የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች
3ኛ. የ2ኛ ደረጃ እና የመ/ደረጃ ክላስተር ሱፐርቫይዘር አስተባባሪዎች
ቅዳሜ በ21/03/2017 ዓ.ም ጥዋት 2፡30 ተጠሪቶ የነበረው ወደ አርብ 20/03/2017 ዓ.ም 7፡00 ሰዓት አራዳ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ የተቀየረ በመሆኑ ተሳታፊዎች በተባለው ሰዓት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ሰዓት ይከበር!!!
ቀን 17/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ
የተቋም የውስጥ የእውቅና ፈቃድ ምዘና መደረጉ ይታወቃል፡፡ በምዘናው መሰረት በእያንዳንዱ በስታንዳርድ የተቀመጠ መስፈርት የታዩ ክፍተቶች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ (17/03/2017 ዓ.ም - 21/03/2017 ዓ.ም) ድረስ ግብዓት የማሟላት ስራ የሚሰራበት ሳምንት በመሆኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተግባሩን እንድትመሩና የተጓደሉ ጉዳዮችን በማሟላት የተቋማችሁን ደረጃ እንድታሻሽሉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ የተጓደሉ ስለመሟላቱ በክትትል የሚናረጋግጥ መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡
ሰላም የተከበራችሁ ርመምህራን በ2016 ዓ.ም በሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ዙሪያ ጥናትና ምርምር የሠሩ መምህራንን ስምና የጥናቱን ርዕስ እንድትልኩልን ይሁን
Читать полностью…ቀን 06/03/2017 ዓ.ም
የስልጠና ጥሪ
1. ሁሉም የመንግስት የት/ቤት መሻሻል ም/ር/መምህራን
2. የተመረጡ የሲፕ ኮሚቴ 2ቱ መምህራን
3. የኬጅ አስተባባሪዎች
4. የወረዳ ቡድን መሪዎችና የሲፕ ባለሙያዎች
ቅዳሜ 2፡30 ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ተገኙ።
ሰዓት ይከበር
እንዴት አረፈዳችሁ!
የፊታችን ቅዳሜ ጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት ዋና ር/መምህራን በአዳዋ ሙዚየም እንዲገኙ ጥሪ ይተላለፍ።
አጀንዳው:- የቀዳማይ ልጅነት
መቅረትና ማርፈድ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
ለሁሉም ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊዎች!
ለሁሉም የሁለተኛ አንደኛና ቅድመአንደኛ ትምህርት ቤት ርእሳነ መምህራን!
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ነገ ሃሙስ ህዳር 5/2017 ዓ.ም በሁሉም የወረዳ ጽ/ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ በሱፐርቪዥን ምልከታ በከተማው በተዋቀረ ቡድን ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት ጀምሮ ይከናወናል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ጽ/ቤት ሃላፊና ርእሰ መምህር ለዚህ ጉዳይ የተለየ ትኩረት በመስጠት የስትራቴጂውን አተገባበር በንቃትና በበቂ ዝግጅት ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ያለበትን ደረጃ እንዲያሳይ እያሳወቅን ለዚህ ስትራቴጂ አተገባበርና ሱፐርቪዥን ላይ መዘናጋት ማሳየት ከፍተኛ ተጠያቂነት ያለበት ጭምር በመሆኑ በበቂ ጥንቃቄና ዝግጅት እንዲከናወን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ደሳለኝ ደበሌ
የአራዳ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ
አስቸኳይ መረጃ፡-
ለመንግስትና ለግል ት/ቤቶች ከላይ የላክነው ፎርም መሰረት በተቋማችሁ ያሉ የሰው ሀይል መረጃ ቶሎ ሞልታችሁ ላኩልን፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ የወጣ ማስታወቂያ
በመምህራንና የትምህርት አመራር ሙያ ብቃት የፅሁፍ ምዘና 62.5 እና በላይ ላመጡ ተመዛኞች የነበረው የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና የተጠናቀቀ ቢሆንም
በተለያየ ምክንያት ምዘናውን ያልወሰዱ ተመዛኞች ጥያቄ እና ምክንያት መነሻ በማድረግ ለመጨረሻ ጊዜ ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው ፕሮግራም ቅዳሜ 28/03/2017 ዓ.ም ከ2:30 -11:00 ድረስ ብቻ የክዋኔ ማህደረ ተግባር (ፖርትፎሊዮ) ምዘና ስለሚሰጥ አራት ኪሎ ድንቅ ስራ ህንፃ በሚገኘው ቢሯችን 8ኛ ፎቅ አዳራሽ መረጃችሁን ይዛችሁ በመገኘት የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና እንድትመዘኑ በጥብቅ እናሳስባለን።
የት/ቤት ር/መ/ራን ማስታወቂያ ለመምህራን በሚታይ ቦታ በመለጠፍ መረጃው እንዲደርሳቸውና በእለቱ መጥተው እንዲመዘኑ ይደረግ።
የአራዳ ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት
የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት
ማሳሰቢያ ፡- ለመዛኞች የመመዘኛ ቼክሊስቱን የትምህርት ቤት ር/መምህራን ፕሪንት አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን። ቼክሊስቱ የእውቅና ፈቃድ ምዘና መስፈርት መሆኑን እንገልፃለን።
Читать полностью…አስቸኳይ
ቀደም ተብሎ ሲከናወን የነበረውን መምህራን online በመመዝገብ ወደ ሲስተም የማስገባት ስራ እሰከ መጪው ሀሙስ እንዲጠናቀቅ መግባባት ላይ ስለተደረሰ በት/ት ቤት ያሉ መምህራን ልማት ም/ል ርእሳነ መምህራኖች በየቀኑ የተመዘገቡ መምህራንን እስከ
6:00 ሪፖርት ለክፍለ ከተማ የተደረሰበትን በጾታ ተለይቶ እንዲቀርብ ይደረግ እኛ ደግሞ እሰከ 8:00 በየቀኑ የክ/ከተማዉን መረጃ እየጠመርን ለቢሮ የምንልክ ስለሆነ ከትላንት እስከ ዛሬ በአለዉ የላከ ባለመኖሩ መረጃዉን ጠምረን መላክ አልቻለንም ስለሆነም የደረሳችሁበትን መረጃ ቶሎ ላኩልን ። አንድም መምህር ሳይመዘገብ እንዳይቀር ጉዳዩን በልዩ ትኩረት አስተባብሩ። ስለ ትብብራችሁ እናመሰግናለን፡፡
ቀን 19/03/2017 ዓ.ም
የስብሰባ ጥሪ
ተሳታፊዎች
1ኛ. ሁሉም የመንግስት ዋና ር/መምህራን
2ኛ. የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች
3ኛ. የ2ኛ ደረጃ እና የመ/ደረጃ ክላስተር ሱፐርቫይዘር አስተባባሪዎች
ቅዳሜ በ21/03/2017 ዓ.ም ጥዋት 2፡30 በ2ኛ ዙር በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች በተደረገ ድጋፍና ክትትል የጋራ የሚደረግ ሲሆን ተሳታፊዎች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ አዳራሽ በተባለው ሰዓት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ሰዓት ይከበር!!!
ማሳሰቢያ፡-
የእውቅና ምዘና ግብረ መልስ ያልላካችሁ ት/ቤቶች በአስቸኳይ ግብረ መልሱን እንድትልኩ እያሳሰብን ቅዳሜ በክፍለ ከተማ ደረጃ ግብረ መልሱ የጋራ ስለምደረግ ፈጥናችሁ ላኩ፡፡ ግብረ መልሱን ስትልኩ በሀርድና በሶፍት ኮፒ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ቀን 10/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም ት/ቤት ር/መምህራን
የእውቅና ፈቃድ የውስት ምዘና እያካሄዳችሁ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም በምዘናው መሰረት ኮሚቴዎች ግብረ መልስ ሰርተው ለ12/3/2017 ዓ.ም ለክፍለ ከተማ ገቢ እንድያደርጉ በእናንተ በኩል መልዕክት እንድታስተላልፉ በጥብቅ እናሳስባለን።
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ዛሬ የእውቅና ፈቃድ ምዘና ስለሚካሄድ ቅዳሜ ስልጠና የወሰዱ የሲፕ ኮሚቴዎች የውስጥ ምዘና እንድያካሂዱና መረጃ እንድታደርሱን እናሳስባለን።
Читать полностью…እንዴት አደራችሁ!
በትምህርት ቤቶች ዘውትር ዓርብ የጽዳት ዘመቻ ባህል እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል።
ስለሆነም የብልጽግና ፓርቲ የተመሰረተበት 5ኛ ዓመት በተለያዩ ኩነቶች የሚከበር ሲሆን የዚህ አካል የሆነው የጽዳት ዘመቻ ከወትሮ በላቀ ንቅናቄ ነገ ዓርብ ጠዋት በሁሉም ት/ቤቶች ቅጥር ግቢ እና ውጪ የጽዳት ዘመቻ የሚካሄድ ስለሆነ አመራሩ ለተግባሩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ የጽዳት ዘመቻ እንዲካሄድና የጽዳት ዘመቻዎቹ በኮሚኒኬሽን እንዲታጀብ በማድረግ አፈጻጸሙን ሪፓርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን።
በዕለቱ የሚተላለፉ መልዕክቶች
1. ቆሻሻ በማቃጠል አካባቢያችንን አንበክልም
2. ትርክታችን ጽዱ መሆናችን
3. ውስጣችን ከጥላቻ አካባቢያችንን ከቆሻሻ እናጽዳ
መልካም ቀን
ለሁሉም የመንግስት የመ/ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራን
ቅዳሜ ስልጠና ላይ የሚሳተፉ
1ኛ. የት/ቤት መሻሻል ም/ር/መምህር
2ኛ. ከሲፕ ኮሚቴ አባላት ውስጥ 2 መምህር
3ኛ. የቅድመ አንደኛ ደረጃ አስተባባሪ 1 ሰው ስም ዝርዝራቸውን ዛሬ ሀሙስ እስከ 6 ሰዓት ላኩልን።
ማሳሰቢያ፡- ቅድመ አንደኛ ላላቸው ብቻ ነው አስተባባሪ ስም የሚላከው።
ቀን 04/03/2017ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች እና ወረዳዎች ሐሙስ (05/03/2017) የሕሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ዙሪያ ድጋፍና ክትትል የሚደረግ በመሆኑ ከቢሮ ተልከው የሚመጡ ባለሙያዎችን ተቀብላችሁ እንድታስተናግዱ እናሳስባለን።
ከርፎርም ክትትል ጋር ተደራራቢ የሆነባችሁ ት/ቤቶች ሁለቱን አጣጥማችሁ እንድታስተናግዱ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።