av12c | Unsorted

Telegram-канал av12c - Arada education office

6896

Subscribe to a channel

Arada education office

የሰዓት ማስተካከያ መደረጉን ማሳወቅን ይመለከታል። ለሰኞ ጥዋት 3፡00 የተጠራው ስብሰባ ወደ ከሰዓት 7:30 የተቀየረ በመሆኑ የተጠራችሁ በሰዓቱ ተገኙ።

Читать полностью…

Arada education office

አስቸኳይ መልዕክት

በአራዳና ቂርቆስ ክ/ከተማ ስር ለምትገኙ ርዕሰመምህራን በሙሉ

ግንቦት 2/ 2016ዓ.ም ላይ የመምህራንና የትምህርት አመራር የፅሁፍ ፈተና መስጠታችን ይታወቃል።

የፅሁፍ ፈተና ውጤት የደረሰ በመሆኑ መጥታችሁ እንድትወስዱ  የት/ቤት ር/መ/ር በድንቅ ስራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት በመገኘት ከመምህራን ሙያ ብቃት ባለሙያዎች በስማቸው በፖስታ የታሸገውን የተፈታኞች ውጤት በቁጥራቸው ልክ በመረከብ በቀን 11/02/2017ዓ.ም ለተፈታኞች እንደታሸገ እንድትወስዱ እያሳሰብን

1. ውጤታችሁ ላይ ቅሬታ የሚኖራችሁ መምህራንና የትምህርት አመራር በተያያዘው የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም በመሙላት እንድታቀርቡ

2. ተፈትነው ስም ዝርዝራቸው ያልተገኙ ካሉ ለማመሳከር እንዲመች ር /መ/ራን ወደ ተቋማችን ስትመጡ በት/ቤታችሁ ምዘናውን የወሰዱ አካላት መረጃን በማጥራት ይዛችሁ እንድትገኙ (ከስራ ክፍሉ ከተያዘው ጋር ለማመሳከር )

3. ውጤታችሁ በመረከብ ከ62.5 በላይ ያመጣችሁ ተፈታኞች የማህደረ ተግባር ፈተና ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ስለሚሰጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታካሂዱ እናሳስባለን።

ስልክ ሲደወል ስልካቸው ያልሰራ ር /መ/ራን ስለአጋጠመን መረጃው እንዲደርስ ይህን መልዕክት ያያችሁ አካላት መረጃውን  ለር/መ/ራን አካፍሉ


የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት

አራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Читать полностью…

Arada education office

ለመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን
የሂሳብ እና እንግሊዘኛ የትምህርት ዓይነቶች በተመለከተ ከጥቅምት 4 ጀምሮ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች ወደ ተቋማችሁ የሚመጡ በመሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉላቸው እንጠይቃለን።

Читать полностью…

Arada education office

ሂሳብና እንግሊዝኛ በት/ት ዘመኑ የት/ት ማህረሰቡ የርብርብ መአከል ሆኖ በትኩረት ይሰራበታል ይህ ማለት የሌላ ሳብጀክት መምህራኖች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ የCPD ፍላጎት ለይተው ያቅዳሉ ይተገብራሉ ምክንያቱም እንደስሙ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ስራ ስለሆነ።

Читать полностью…

Arada education office

ለመንግስት ት/ቤቶች የኦን ላይን ተማሪን መረጃን ለማጥራት የክፍል ድልድል ለመሰራት የመምህራን መረጃ ለማሰገባት ነገ 30/1/17  ከሰአት 8:00 ላይ ሰልጠና ሰለምንሰጥ 1ኛ.ምዝገባውን ሲከታተል የነበረ 1 ር/መምህር 2ኛ.ምዝገባውን ሲከታተል የነበረ 1 የict ባለሙያ ወይም  ተወካይ እንድትገኙ እያሳሰብን መቅረት የማይቻል መሆኑን እንገልጻለን ት/ጽ/ቤት
ቦታ ት/ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ

Читать полностью…

Arada education office

በአፄ ፋሲል ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት
በመምህራን የዲሲፒሊን መመሪያዎች ፤ የትምህርት ፈተና አስተዳደር የጋራ መመሪያ ዙሪያ፣ የሒሳብ እና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት ለማሻሻል በተዘጋጀ እስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በዛሬው ቀን ከመምህራን ጋር ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ። በውይይቱ ላይም ከመምህራን ለተነሱት ጥያቄዎች በት/ቤቱ አመራሮች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
Guyyaa 14/1/2017 mana barumsaa sadarkaa tokkoffaan duraa sadarkaa 1ffaa fi giddu galeessaa Atsee Faasil  keessatti qajeelfama naamusa barsiisotaa, qajeelfama waloo bulchiinsa qormaata barnootaa fi karoora tarsiimoo fooyya’iinsa qabxii gosa barnootaa herregaa fi Afaan Ingiliffaa irratti barsiisota waliin mariin taasifameera.maree kana irratti gaaffilee barsiisotaan gaafatameen deebiin hoggantootan itti kennameera.

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም ት/ቤት ር/መምህራን
የወላጆች ውይይት ሪፖርት እስከ አሁን ድረስ የላከው የኒውኤራ ት/ቤት ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ሪፖርቱን እንድትልኩ ደግሜን እናሳስባለን፡፡

Читать полностью…

Arada education office

መደበኛ የትምህርት በሬዲዮ መርሀ ግብር የፊታችን ሰኞ መስከረም 13 ዓ.ም ይጀምራል ።

Читать полностью…

Arada education office

English and Maths Strategy Plan for 2017.pot

Читать полностью…

Arada education office

Document from Desalegn Debele

Читать полностью…

Arada education office

ውድና የተከበራችሁ ር/መ/ራን የ2017 ዓ ም የተማሪዎች የምገባ ሜኑ ነው ስለዚህ በዚህ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ክትትላችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል።

Читать полностью…

Arada education office

ነገ ቅዳሜ በ04/01/2017 ዓም ጠዋተ 2:30 አራዳ ክ/ከተማ አደራሽ:_
#የክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊዎች
# ሁሉም 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ሱፐርቫይዘሮች
# የክ/ከተማ የስረዓተ ት/ት አስተባባሪዎችና ሁለቱ የስረዓተ ት/ት ቡድን መሪዎች
# የወረዳ ስረዓተ ትምህርት ቡድን መሪዎች በ2017 ትምህርት ዘመን ስትራቴጂ ላይ ዉይይት ስለሚካሄድ በሰዓቱ እንድትገኙ።
መልካም ቀን!

Читать полностью…

Arada education office

የ2ኛ ደረጃ ር/መምህራንና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች የክፍለ ከተማውን እንደ መነሻ በመውሰድ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ በማዘጋጀት ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 25/11/2016 ዓ.ም
የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
በቀን 26/11/2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ
1. የ2ኛ እና የመ/ደረጃ ት/ቤት ዋና ር/መምህር የመንግስት
2. የ2ኛ እና የመ/ደረጃ የመማር ማስተማር ም/ር/መምህር
3. የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች
4. የወረዳ ስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች
በከተማ ደረጃ በተደረገው ድጋፍና ክትትል ዙሪያ የጋራ ሲለምደረግ ሰዓት አክብራችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
ማርፈድና መቅረት የተከለከለ ነው።
ማሳሰቢያ፡- የ2ኛ ደረጃ የወከላችሁትን ሰው መላክ አለባችሁ።

Читать полностью…

Arada education office

ውድ ለክፍለ ከተማችን የፅ/ቤት ሀላፊዋች፣    4ቱ ርእሰመምህራን፣ አጠቃላይ  የክ/ከተማና የወረዳ ባለሙያዋች እና አጠቃላይ የክ/ከተማና የወረዳ ሱፐርቨዘሮች በሙሉ ሰኞ ጠዋት 2:00 ስአት አድዋ መታሰቢያ ሙዝየም አዳራሽ ስአት አክብራችሁ  እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
በቀን 11/2/2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም እና የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ በጋራ ግምገማ ይደረጋል። በዚህም መሰረት
1ኛ. የመንግስት ት/ቤት ሁሉም ዋና ር/መምህራን
2ኛ. የ2ኛ ደረጃ ሁሉም ሱፐርቫይዘሮች
3ኛ. የመ/ደረጃ ክላስተር አስተባባሪዎች
ሰኞ 3፡00 ት/ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ እንድትገኙ እናሳስባለን። መቅረትና ማርፈድ በፍፁም የተከለከለ ነው። በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ የማትገኙ አመራሮች ጽ/ቤቱ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂ የማንሆን መሆኑን እየገለፅን ም/ር/መምህራን የሒሳብና እንግሊዘኛ ቀን በዕለተ ሰኞ ተግባራዊ መሆኑን እንድከታተሉ አድርጉ። ሶስት ሰዓት የሚጀመርበት መሆኑን አውቃችሁ በሰዓት ተገኙ።

Читать полностью…

Arada education office

የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የሂሳብ እና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት ለማሻሻል ስትራቴጂ በመንደፍ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ትግበራውን ለመከታተል የሱፐርቪዥን ቡድን በማዋቀር የትምህርት ተቋማት ክትትል መደረጉ ይታወቃል።በመሆኑም በቀን  08/02/2017 ዓ.ምከቀኑ 7፡00 ሰዓት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ በቢሮ ኃላፊ የሚመራ ውይይት ስለሚከናወን
1ኛ. የመንግስት 1ኛ መካከለኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዋና ርዕሳነ መምህራን ፤ 2ኛ.የክፍለከተማ እና ወረዳ ሱፐርቫይዘር አስተባባሪዎች
3ኛ. ድጋፍና የክትትል ስራ ላይ የተሳተፋችሁ በተባለው ቀን እንዲትገኙ እናሳስባለን፡፡
መቅረትና ማርፈድ አይቻልም።
ሰዓት ይከበር
ት/ጽ/ቤት

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤት ር/መምህራን ጥቅምት 4 የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመሆኑ ዕለቱን አስመልክቶ በተለያዩ ፕሮግራሞች እንድታከብሩ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች የሂሳብና የእንግሊዘኛ ትምህርትን ማሻሻል ከመምህሩ እስከ አመራሩ ጭምር አንዱ የተሙማ ዕቅድ ሆኖ እንዲሰራበት ከወዲሁ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ለወረዳ ት/ጽ/ቤቶችና ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራን በቢጋሩ መሰረት በተባለው ቀን በሀርድና በሶፍት ኮፒየ 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንድትልኩ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

የወላጆች ውይይት ሪፖርት የላኩት ኒውኤራ እና ወ/ሮ ቀለመወርቅ አመራሮች ለፈጣን መረጃችሁ እናመሰግናለን። ውይይት ያደረጋችሁ ት/ቤቶች ሪፖርቱን በሀርድና በሶፍት ኮፒ ጠይቀን እየላካችሁ አይደለም። ለመጨረሻ ጊዜ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 11/01/2017 ዓ.ም
ለሁሉም ር/መምህራን በሙሉ
በዛሬው ቀን የወላጆች ውይይት ያደረጋችሁት በውይይት የተሳተፉ ወላጆች ብዛት፣ በውይይት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች፣ መድረኩ የተመራበት አግባብና ውይይቱ ድምዳሜ ሪፖርት በሀርድና በሶፍት ኮፒ ለሰኞ ለክፍለ ከተማ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

Document from Desalegn Debele

Читать полностью…

Arada education office

Document from Desalegn Debele

Читать полностью…

Arada education office

Document from Desalegn Debele

Читать полностью…

Arada education office

ቀን 03/01/2017 ዓ.ም
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት "የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራትና ለሀገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ጉባኤውን አካሄደ።

በፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና  ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ ጌታሁን እንደተናገሩት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በእውቀትና በክህሎት እንዲዳብሩ በማድረግ ለሀገራቸው አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ዓላማቸው መሆኑን ገልጸው የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻልና በሀገራቸው የብልጽግና ጉዞ ላይ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ በማድረጉ በኩል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘሁ በበኩላቸው በ2016 በጀት ዓመት በመማር ማስተማሩ ላይ በተሰራው ውጤታማ ስራ የተማሪዎች ውጤት  ላይ መሻሻል የታየበት እንደነበር ገልጸው  ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና  ጉዞ እውን እንዲሆን ተማሪዎች በእውቀትና በአመለካከት የዳበሩ እንዲሆኑ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ጉባኤው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የውጤት ትንተና እና የ2017 ዕቅድ ላይ  ውይይት የተደረገበት ሲሆን በ2016 በጀት ዓመት ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ት/ቤቶች ፣ ወረዳዎች ፣ተማሪዎችና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።።

Читать полностью…

Arada education office

ጳጉሜ 4/41

## በአራዳ ክፍለ ከተማ 31ኛው የትምህርት ጉባኤ ጥሪ፣ ##

*የጉባኤው ቀን መስከረም 03/17 (ዐርብ)

* ቦታ ፣ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 11ኛ ፎቅ አዳራሽ

* ሰአት 2:30

* በጉባኤው ላይ የሚታደሙ

1. የወረዳዎች ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች

1. የመንግስት ት/ቤት ዋና ርእሰ መምህራን

2. የግል ት/ቤት ዋና ርእሰ መምህራን

3. የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሁሉም ቡድን መሪዎች

4. የወረዳ ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች በሙሉ

5. የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሱፐር- ቫይዘሮች
6. የወተመህ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚዎች

7. የመምህራን ማህበር ስራ አስፈጻሚዎች

8. ተሸላሚ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው (31)

* አጀንዳ 1. የ2016 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት
2. የ2017 እቅድ
3. የውጤት ትንተና
4. እውቅና እና ሽልማት

Читать полностью…

Arada education office

በዚህ ቅፅ መሰረት የ3ኛ ዙር የትምህርት ለትውልድ ችግሮች በቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ በመለየት እስከ ረቡዕ እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን።

Читать полностью…

Arada education office

1. በ ቅድሚያ login ካደረጉ በኋላ በ ግራ በኩል ከተዘረዘሩት አማራጮች መካከል "Student" የሚለውን ይምረጡ።
2. ከ Student  page ላይ Approve የተደርጉ ተማሪውች ዝርዝር ይመጣል።
3. ከ ዝርዝር ውስጥ የሚስተካከለዉን ተማሪ ይምረጡ እና "View" ሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ ከዛም "Edit" የሚልዉን ይጫኑ፡፡
4. የተማሪው መረጃ ካስተካከሉ በኋላ "Update" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።

Читать полностью…

Arada education office

ቦሌ ክ/ከተማ የተባለው ወደ አራዳ ክ/ከተማ ተቀይሯል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel