aybclub | Unsorted

Telegram-канал aybclub - AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

-

ቃልህ(ሕግህ) ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው። መዝሙረ ዳዊት 119:105

Subscribe to a channel

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Geta hoy ibakihn yetemarkutn besiralay mawal indchl Zend betsegah irdagn

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Tebarekulign, kezih club bizu ngr temirebetalew!! Keep it up

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እርሱ ትልቅ ነው!
============================

📖“የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል።”

  — ኢዮብ 9፥10


ምድራችን ታላላቅ ነገርን በሰሩ ሰዎች ተሞልታ ይሆናል። ከታላቅነታቸው የተነሳ ወደር የማይገኝላቸውን ሰዎች ዓለማችን አስተናግዳለች። ነገር ግን ይህ ታላቅነታቸው ከአፈር በታች እንዳይሆኑ አላደረጋቸውም። ሞት በርትቶባቸውና አይሎባቸው ጠፍተዋል። የሰው ምድራዊ ታላቅነት መጨረሻው ይሄ ነው።


ኢዮብ ስለ እግዚአብሔር ታላቅነት ሲናገር በዚህ ክፍል ውስጥ ከተፃፈው እናነባለን። “ተራሮችን ይነቅላል፤ አያውቁትም፤ በቍጣውም ይገለብጣቸዋል። ምድርን ከስፍራው ያናውጣታል፥ ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ። ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ያትማል። ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል። ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደርያዎች ሠርቶአል።” (ኢዮ 9፥5-9)


የእግዚአብሔር ትልቅነት ወደር አልባ ነው። ትንሽ በሆነው አዕምሯችን ታላቅነቱን በሙላት ልንረዳውም ሆነ ልናስታውለው ከቶ አይቻለንም። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ስልጣን ያለው ኃያል አምላክ ነው። ተፈጥሮ እንኳን የሚታዘዝለት ድንቅ ጌታ ነው። ታዲያ ይህ ታላቅ አምላክ ዝቅ በማለት ፈለገን። ከተበተንበት ስፍራ ሰበሰበን። ፀጋውን አስታጥቆ አበረታን። ቅርባችንም ሆኖ ወዳጅ ሆነን። ይህንን እውነት ስናስታውል ታዲያ በሚደርሱብን በትናንሽ ነገሮች ልንለካው አንነሳም። እንዲህም በማለት እናውጃለን፦ “የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል።” (ቁ 10)


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ምንም ነገር ሊይዝህም ሆነ ሊገዳደርህ የማይችል ታላቅ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። ይህንን ታላቅነትን በመረዳት ደግሞ “የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል” ብዬ እንድመሰክር አቅም ሁነኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

"እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል" ዮሐንስ 16፡7-8።

ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን በምድር ትቶ ሊያርግ ሲል መንፈስ ቅዱስን እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው። በዚያም መሰረት በመንፈስ ቅዱስ ሞላቸው።

መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ስለሚኖረው ሚና ክርስቶስ ምንድነው ያለው? መንፈስ ቅዱስን ከማን ነው የምንቀበለው? በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ውስጥ የሚኖር ሰው ምን ምልክቶች ይታዩበታል? 

በዚህ ሳምንት በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ እያሰብን እንቆያለን። ሐሳብና ጥያቄያችሁን አጋሩን። እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/xhys_991TEk?si=V5pg3iCwttD09twU

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Amen yegeta beteseboch

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

“ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥
ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።”
  — ዮሐንስ 19፥30


📖 በዮሐንስ 19 ላይ የተመሠረተ ልዩ የሆነ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ውይይት 👇👇

https://youtu.be/fMCZhW0cKZ0?si=XwFxsv3VQAtowYw3

📌 እናንተም ተባረኩበት ሌሎችም እንዲባረኩበት ሼር & ሰብስክራይብ ያድርጉ።


መልካም ቀን 🎁

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔርን በራሳቸው መንገድ ለማምለክ ሞክረው ተቀባይነትን ያጡና የተቀጡ ባለታሪኮች ትንሽ የሚባሉ አይደሉም።

ለምሳሌ የአቤልና የቃየንን መስዋዕት መመልከት እንችላለን።

"ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤ አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም" ዘፍጥረት 4:3-5።

የአቤል አምልኮ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሰረት ስለነበር ተቀባይነትን አገኘ። አቤል ግን ተተወ። የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድም እንግዳ እሳት በመቅደሱ ውስጥ ለመጠቀም በመሞከራቸው በእሳት ተቃጥለው ጠፉ (ዘሌ 10:1-2)።

አምልኮ በጊዜ፣ በቦታና በሁኔታ አይገደብም። የምናመልክበት መንገድ ወይም ቀመር ግን በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው። እኛ በፈለግነው መንገድ ልናመልከው አንችልም።

"አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው" ኢሳይያስ 55:8-9።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ለእስራኤላውያን ታቦቱን የያዘው መቅደሱ የነበረበት እየሩሳሌም ልዩ ትርጉም ነበረው። እነርሱ በመቅደሱ ተገኝተው ወይም ከአገራቸው ሲርቁ ወደ እየሩሳሌም ዞረው ይጸልያሉ፤ በሰማርያ የሚገኙት ደግሞ በተራራ ይሰግዱ ነበር።

ስለዚህ ሳምራዊቷ ሴት አይሁድ በእየሩሳሌም እኛ ደግሞ በተራራ እናመልካለን ምን አገናኘን አለችው። ክርስቶስም መልሶ እንዲህ አላት፥

"ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል" ዮሐንስ 4:23-24።

በአዲስ ኪዳን አምልኮ በቦታ እንደማይገደብ ክርስቶስ ተናገረ። ለማምለክ እየሩሳሌም መሔድ የግድ እንደማይሆን ሆኖም ሰው ሁሉ በመንፈስና በእውነት ባለበት ቦታ ሆኖ የሚያመልክበት ስርዓት ቅርብ እንደሆነ ነገራት። 

ብቸኛው እግዚአብሔርን የማምለኪያው ትክክለኛ መንገድ በመንፈስና በእውነት ማምለክ ነው!

በመንፈስ ማምለክ
"እግዚአብሔር መንፈስ ነው" የምናመልከውም በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ከልባችን በሚመነጭ ውስጣዊ ፍላጎት ነው። መንፈስ የሆነውን አምላክ (በዓይናችን አሁን የማናየውን) በተፈጥሯዊ ስጋችን ማምለክ አንችልም።

በመጀመሪያ ከመንፈሳዊ ጉዳይ ጋር ጠላት የሆነው ማንነታችን በመንፈስ ሊቀየር ይገባል። ይህንን የመለወጥ ስራ ልብ ውስጥ የሚሰራው መንፈስ ቅዱስ ነው። “ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” ዮሐንስ 3፥5።

ልባዊ አምልኮ በመንፈስ ቅዱስ ድጋሚ መወለድን ይጠይቃል። ባልተለወጠ ተፈጥሮ የምናቀርበው አምልኮ ከወግና ከስርዓት አይዘልም።

በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይገረዙ ነበር። በአዲስ ኪዳን ይህ አካላዊ መገረዝ በልብ መገረዝ ተተክቷል። “እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና” ፊልጵስዩስ 3፥3።

ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል” ዮሐንስ 16፥13። መንፈስ ቅዱስ በልብ ውስጥ ሲሰራ ለእውነት ፍላጎታችንን ያነሳሳል። ወደ እውነትም ይመራናል።

በእውነት ማምለክ

አምልኮ እምነትን እምነትም እውቀትን ይጠይቃል። "እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው" ሮሜ 10:17።

አምልኮ የእምነት ውጤት ነው። ወይም እምነት የሚገለጽበት አንዱ መንገድ በአምልኮ ነው። እምነት ደግሞ ጭፍን አይደለም፤ በቃሉ በቅሎ በቃሉ የሚያድግ መልካም ፍሬ ነው። አውቀነው እንድናመልከው እግዚአብሔር እውነትን በቃሉ አማካኝነት ገልጾልናል።

ቃሉን መሰረት ባላደረገ በጠቅላላ እውቀትና በድንግዝግዝ እምነት የሚፈጸም አምልኮ የመርሃ-ግብር ክንውን ነው።   

ቃሉ የሚነግረንን እውነት በየዋህ እምነት ስንቀበለው ሕይወታችንን ይቀድሳል፤ አዲስ ልምምድም ያስተምረናል። "በእውነትህ ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው" ዮሐ 17:17። መቀደስ በቃሉ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ቅዱስ ኃይሉ የሚለቀቅበት መንገድ ነው።

ከሰው ልጅ ውድቀት በፊት ተፈጥሮ የሰዎች ትምህርት ቤት ነበር። ከኃጢያት በኋላ ግን ከተፈጥሮ በላይ ቃሉ አስተማሪያችን ሆኖ ተሰቶናል።

የአዲሱ ስርዓት ዋነኛ መገለጫ ልባችን የቃሉ ማደሪያ፤ በዚያም የእግዚአብሔር መኖሪያ መሆኑ ነው።

“ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል” ኤርምያስ 31፥33።

ቃሉ ልባችንን ሲይዝ እግዚአብሔር አምላካችን እኛም ሕዝቦቹ እንሆናለን። በተለይ ቃሉን የማወቅ እድሉ ላለን ከፈጣሪያችን ጋር ያለን የአምልኮ ግንኙነት እውን የሚሆነው በዚህ መልኩ ነው።

በአጠቃላይ እውነተኛ አምልኮ በቦታና በጊዜ ሳይገደብ ልብን በሚያድሰው በበመንፈስ ቅዱስ ምሪት በቃሉ የተገለጸልንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ልባዊ በሆነ መታዘዝ የሚፈጸም ነው።

ጥያቄና ሐሳባችሁን ልታጋሩን ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

"ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል" ዮሐንስ 4:23-24።

በክርስትናው ዓለም 'አምልኮ' በተለያየ መንገድ ሲፈጸም እናያለን። ሰዎች የመሰላቸውን ሲከተሉና በአምልኮ ስም ወጣ ያሉ ተግባራትን ሲፈጽሙ ይስተዋላል።

ክርስቶስ እንደተናገረው አምልኮ ቀመር አለው! እግዚአብሔርን እኛ በፈለግነው መንገድ ልናመልከው አንችልም።

ለሳምራዊቷ ሴት ሲመልስላት "የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል" አላት። ስለዚህ እግዚአብሔርን የምናመልክበት ብቸኛው መንገድ በእውነት እና በመንፈስ ነው። ለመሆኑ በእውነትና በመንፈስ ማምለክ ምን ማለት ነው?

በዚህ ሳምንት ይህን ጉዳይ ለመዳሰስ እንሞክራለን። ሐሳብና ጥያቄያችሁን አጋሩን። እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ግሩምና ለወቅቱ አስፈላጊ የሆነ ሐሳብ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እግዚአብሔር ውስብስብ የኑሮ ዘይቤን አላቀደልንም። ለኑሯችን እግዚአብሔር የሰጠን ረቂቅ ሆኖ የተፈጠረውን ተፈጥሮን ነው። ሆኖም ፈጣኑ ስልጣኔ ሕይወትን የሚያቀልል ቢሆንም ተፈጥሮ ላይ ያለንን ጥገኝነት በመቀነስ ውድ በሆነ ዋጋ በሚገኙ ሰው ሰራሽ ግኝቶች ላይ ጥገኛ አድርጎናል።

ከዚህም የተነሳ ዘመናዊው ሕይወት የሚጠይቀውን ለማሟላት በየቀኑ መጣራችን መንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ጫና የሚያሳድር መሆኑ አልቀረም።

በተለይ እንደ ኢንተርኔት ያሉ ለኑሯችን ጠቃሚ የሆኑ መልካም ግኝቶች አጠቃቀማችን ጤነኛ ካልሆነ ክርስትናችንን እንድንሰዋ የሚያደርግ ነው።

መረዳት ያለብን የክርስትና አኗኗር በጊዜ ብዛትና በዘመናዊነት አይቀያየርም። አዳዲስ ግኝቶች ክርስትናን አያሻሽሉትም። መልካም ግኝቶች ኑሯችንን እንዲያሻሽሉ እየተጠቀምንባቸው የክርስትናን መርህ ግን እንድንጥስ እንዳያደርጉን መጠንቀቅ ይኖርብናል።

ዘመናዊ ሕይወት ክርስትናን ከተካብን ቃሉ እንዲህ ይመክረናል፦

በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ” ኤርምያስ 6፥16።

የሚከተሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆች በዘመናዊነት እንዳንወሰድ ይረዱናል፦

"በመጠን ኑሩ"፦ ምናልባት ምንም የለኝም ይህ መርህ ለእኔ አይሆንም እንል ይሆናል። ሆኖም በሌለን ነገር በሐሳባችን አለመጠመድንም ይጨምራል። ክርስቶስ በሉቃስ 12:15 እንዳለው "የሰው ይህወቱ በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ ከመጎምዠትም ሁሉ ተጠበቁ።" በክርስቶስ ገለጻ መሰረት ገንዘብን በመጎምዠት የሚኖር ሰው ሀብት ቢያገኝ ይሰናከልበታል። ስለዚህ በሁሉም ነገር መሻትን መግዛት ለክርስትና እድገትና ስኬት የግድ አስፈላጊ የሆነ የመንፈስ ፍሬ ነው (ገላ 5:22)። በዚህ የዘመናዊነት ሕይወት የሚያስፈልገንን በመጠኑ መጠቀምን የሚጎዳንን ደግሞ ሙሉ ለሙሉ መተው ይጠበቅብናል። ቀለል ያለ አመስጋኝ ሕይወትን በመለማመድ ከተጽዕኖ መራቅ እንችላለን።

በየቀኑ መኖር፦ “ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል” በማቴዎስ 6:34። ብዙ ጊዜ የምንንቸገረው አዕምሯችን ከኑሯችን እየቀደመብን ነው። ዛሬ ላይ ሆነን የነገውን በምናብና በሐሳብ ለመኖር መሞከር ዛሬ ይዞልን የመጣውን መልካም ዕድል ያሳጣናል። በተመሳሳይ ዛሬ ላይ ቆመን በትላንት መብሰልሰል የዛሬን መልካምነት እንዳናገኝ ያደርግብናል። ስለዚህ ማድረግ የምንችለውን እያደረግን በየቀኑ መኖር ይኖርብናል። ለነገ ማሰብ መልካም ቢሆንም ዛሬ ላይ ሆነን በምናብ ነገን መኖር ፍሬያማ አያደርገንም። ነገን የተሻለ ማድረግ የምንችለው ዛሬን እንደሚገባው በመኖር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በመጨነቅ ብቻ ሳይሆን በመጓጓት ጭምር ነገን እንዳናሰላስል ይነግረናል፥ “ቀን የሚያመጣውን ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ” ምሳሌ 27፥1።

የእለት እንጀራ፡ “በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለለቀመ አልተረፈውም ጥቂትም ለለቀመ አልጐደለበትም፤ ሁሉ እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ለቀመ” ዘጸአት 16፥18። እግዚአብሔር መናው በየእለቱ እንዲወርድ ያደረገው በምክንያቶች ነው።  አንዱ ምክንያት በየእለቱ አምላካቸው ላይ ጥገኛ መሆናቸውን ለማስተማርና ለማለማመድ ነው። ይህ ባለን ነገር ለምንመካና በሌለን ነገር ለምናዝን ትምህርት ነው። ፈቅዶ እግዚአብሔር ካኖረንና ጥረት ካደረግን ለቀኑ የሚያስፈልገንን አያጎድልብንም። ሁላችንም "ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል እንጂ" የሚለውን ብናውቅም በአብዛኛው ለመኖር የምንሞክረው ግን በአካላዊ ምግብ ብቻ ነው። የሕይወትን እንጀራ ማጣት መንፈሳዊ ሞትን ያስከትላል። ስለዚህ ሕያው ሆኖ ለመኖር በየዕለቱ መንፈሳዊ መና የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ያስፈልገናል።

መምረጥ መቻል፦ ዓለም የምታቀርበው ሁሉ ለክርስቲያኖች መልካም አይደለም። “ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም” 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥12። ለክርስትና ጉዟችን የሚረዳንን እና የሚያስፈልገንን ብቻ በመምረጥ ብልጥ ልንሆን ይገባል። በተለይ ፋሽንን ችላ ማለት አግባብ ከሌለው ዓለማዊ መወዳጀት ይታደገናል።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ መልካም ቀን!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Selam kidusan indet nachu andi tyake alegn, malet korstos bemimetabet gize ye aizab ita fanta mndnew?

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እንዚህ ሰዉ ሰሪሽ ነገሮች በአሁኑ ባለንበት ዓለም በጣም ወሰኝንና አሰፈላጊ ነቸው :: ነገር ግን እኛን ሊቆጣጠር አይገባም:: ሁሉም ነገር በጊዜውና በወቅቱ መሆን አለበት :: የአሁኑ ወቅት ወቅታዊ መሆን ያለበት የእግ/ር ቃል ወቅታዊነት ነው መሆን ያለበት::

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል” በማቴዎስ 6:34

ሰላም እንደምን ቆያችሁ ወንድሞችና እህቶች፤

በዚህ ሳምንት የእግዚአብሔር ቃል በየቀኑ እንዴት መኖር እንዳለብን የሚነግረንን እንመለከታለን።

በምንኖርበት ዘመናዊው ዓለም ኑሮን የሚያቀሉ በርካታ መልካም ግኝቶች ቢኖሩም በአንጻሩ ደግሞ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድሩ የተለማመድናቸው አኗኗር አሉ። ከዚያ አንጻር ትንሽ ነገር ጎደል ሲል ቅር ይለናል አንዳንዴም ይጨንቀናል።

ለምሳሌ በተለይ ከሰሃራ በታች ለምንኖር ሰዎች መብራት ሲጠፋ፣ ስልካችን ሲዘጋ፣ የምንጠብቀውን ነገር ሳናገኝ ስንቀር፣ ከኪሳችን ወይም ከአካውንታችን ገንዘባችን እየቀነሰ ሲሔድ፣ ኢንተርኔት ሲዘጋ …… ክርስትናችን እንዴት ነው?

እነዚህ ነገሮች መልካምና አስፈላጊዎች ናቸው። ነገር ግን ከጥቂት ትውልዶች በፊት ያልነበሩት የሰው ግኝቶች ስሜቶቻችንን የሚቆጣጠሩ አንዳንዴም የክርስትናን ድንበራችንን የሚጥሱ እየሆኑብን ነው።

በዘመናዊው ኑሮ ለመኖር የሚያስፈልጉን ቁሳቁሶችና አገልግሎቶች እጅግ ከመበርከታቸውም በላይ ሰውን ወደ አላስፈላጊ ፉክክር ውስጥ በመክተት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥሩ ሆነዋል። 

በአጠቃላይ ጥገኝነታችን በቀጥታ ተፈጥሮ ላይ መሆኑ ቀርቶ ሰው ሰራሽ ነገሮች ላይ ሆኗል። ታዲያ የክርስቲያን ሕይወት በዚህ ምድር ምን መምሰል አለበት?

ሐሳቦቻችሁን አጋሩን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ዕለታዊ የሕይወት ስንቅ ኦንላይን ሚኒስትሪ በነሐሴ 27፣ 2021 እ.ኢ.አ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ያሉትን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የጥሞናን (devotional) ይዘት በመከተል አጫጭር የሆኑ መንፈሳዊ ፁሁፎችን ማዘጋጀት ዓላማው አድርጎ የተነሳ ኦንላይን ሚኒስትሪ ነው። በዚህ አገልግሎት ውስጥ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናቶች ምሽት ምሽት የተለያየ አይነት ይዘት ያላቸው መልዕክቶች ይቀርቡበታል።


እስካሁን እግዚአብሔር አምላክ አቤኔዘራችን ሆኖ ረድቶናል። ቃሉንም ያለማጓደል በመላክ ከዘፍጥረት "ሀ" ብለን የጀመርነው ጥናት አሁን ላይ መፅሐፈ ኢዮብ ላይ ደርሷል። ታምነን የተነሳነው ታማኙን አምላክ ነውና ወደፊትም ያዘልቀናል። ጣፋጭ በሆነው ሕያው ቃሉም ውስጣችንን ያረሰርስልናል።


ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ (link) በመጫን ወደዚህ የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ ዘንድ በፍቅር እናድማችኃለን። ባራኪው ራሱ እግዚአብሔር ነውና ለሌሎች ወዳጆቻችሁም በማጋራት ቤተሰብ አድርጓቸው።


Invitation Link: /channel/Eletawi_Yehiwot_Sinik


ተባረኩ!

ዕለታዊ የሕይወት ስንቅ ኦንላይን ሚኒስትሪ

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

"፤ ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።
"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4: 16)
እንደቃሉ መኖር እንዲንችል ፈጣሪ ይርዳን። አሜን

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አሜ...................ን

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እንደምን ቆያችሁ ወዳጆች፤ የኃጢያት አጀማመርን በሰማይና በኤደን ተመልክተናል። በዚህ ጽሑፍ ስለኃጢያት መስፋፋትና ውጤቶቹ በአጭሩ እናያለን።

የዚህ መልዕክት ዓላማ የነፍስ ካንሰር የሆነውን የኃጢያትን መስፋፋትና አስከፊ ውጤቶቹን አስተውለን ስር ሳይሰድና ሳይረፍድብን የምንመለስበትን መንገድ መጠቆም ነው።

ያልተነገረለት ወረርሽኝ

"ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው" 1ዮሐ 3:4።

ኃጢያት ማለት ትዕዛዝን መተላለፍ ነው።
የሰው ዘር አንዴ ከሳተ በኋላ በራሱ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ የማይችል በመሆኑ ኩነኔ ውስጥ ወድቋል። ስለዚህ ኃጢያት በዓይነትም በብዛትም እጅግ ተስፋፍቷል።

ሰው ሆኖ በአባቱ ኃይል ድል ካደረገው ከአዳኛችን ከክርስቶስ በቀር ይህ ወረርሽኝ ያልደረሰበት ሰው በምድር ላይ የለም!

ከኃጢያት መስፋፋትና ከክፉ ውጤቶቹ የሚከተሉትን እንማራለን፦

1. ኃጢያት ተፈጥሯዊ ስጦታን ያሳጣል፦ በአዳም መውደቅ የሰው ዘር ሁለት ተፈጥሯዊ ስጦታዎችን አጥቷል። እነዚህም የእግዚአብሔር ክብር መጓደል እና ምድርን የማስተዳደር ኃላፊነትን ማጣት ናቸው። የክብሩ መጓደል ወይም መጥፋት በአሉታዊ የአካልና የባሕሪይ ለውጦች ይስተዋላል። አካል ለሕመም፣ ለድካም፣ ለእርጅናና ለሞት ተገዥ ሲሆን ባሕሪይ ደግሞ ለቁጣ፣ ለንዴት፣ ቅናት፣ ብስጭት፣ ንጭንጭ፣ አለመረጋጋት፣ ስጋት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ ጥላቻ ተጋላጭ ሆኗል። የእግዚአብሔርን ክብር ማጣትን ተከትሎ ሰው የምድር ገዥ የመሆኑ ኃላፊነት በሰይጣን ተነጥቋል። "የአምላክ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፥ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ። እግዚአብሔርም ሰይጣንን፡ ከወዴት መጣህ? አለው። ሰይጣንም፡ ምድርን ሁሉ ዞርሁአት፥ በእርስዋም ተመላለስሁ ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ" ኢዮብ 1:6-7። ሰይጣን የምድር ተወካይ ሆኖ በጉባዔው ይቀርብ እንደነበር ቃሉ ይነግረናል። በክርስቶስ የደህንነት ስራ ግዛቱ ሙሉ ለሙሉ እስኪመለስ ድረስ የማስተዳደር አደራውን ጠላት ተረክቧል። ለእኛም ዛሬ የእግዚአብሔር በረከቶች በመታዘዝ ላይ የተመሰረቱ ናቸው (ዘዳ 28:1-14)። ሮቤል የአባቱን ምንጣፍ በማርከሱ ብኩርናውን እንዳጣ ሁሉ (1ዜና 5:1) ምናልባትም ዛሬም ኃጢያትና ውጤቱ በየዕለቱ ዋጋ እያስከፈለን ይሆናል። አለመታዘዝ ሕይወትን ከማስከፈል ባለፈ ተፈጥሯዊ ስጦታዎቻችንን የሚያመክንና ዕድሎችን የሚዘጋ ጋሬጣ ነው።

2. ኃጢያት በቀላሉ ይስፋፋል፦ “… እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ” ዕብ 12፥1-2። ኃጢያት ቶሎ የሚከብ ነው። በትንሹ መውደቅ የጀመረ ሰው በዚያው አይቆይም፤ በንስሃ ካልተመለሰ ቁልቁል መውረዱ አይቀርም። አንዲት የክፋት እርምጃ ቁልቁል ታወርዳለች በኃጢያት ደረጃ! ለዚህ መፍትሔው በኃጢያት ውስጥ ላለመኖር ወስኖ በጌታችን ፀጋ መታገል ነው። ሳንናዘዝ የምናልፋት አንዲት ኃጢያት አታልፈንም፤ ወደሚቀጥለው ከዚያም ወደሌላው ትመራናለች። በዚህ መልኩ ወረርሽኙ ስር ይሰዳል። በተቻለ መጠን ሩቅ ሳንሔድና በኃጢያት የሚመጣን ጊዜያዊ ጥቅም ሳንለማመድ መለስ ማለት ከኃጢያት ኃይል ለመውጣት የምናደርገውን ውጊያ ቀለል ያደርገዋል። “ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል” ምሳሌ 28፥13።

3. በማር የተሸፈነ መርዝ፦ አለመታዘዝና ውጤቶቹ ይህን ያህል ጎጂ ቢሆኑም ጊዜያዊ ጥቅሞቹ እንደ መልካም እንዲታይ አድርገውታል። በኃጢያት የሚገኝ ጊዜያዊና ስጋዊ ጥቅም በሰብአዊ አመክንዮ መሰረት ተቀባይነት ማግኘቱ የኃጢያት አስከፊነት እንዲሸፈንና እንደ ጽድቅ እንዲታይ እያደረገው ይገኛል።  ይህ የሚሆነው ኃጢያት ለሰዎች ተፈጥሯዊና አጓጊ ስለሆነ ነው። በድጋሜ ወደ ኋላ መለስ ብለን አንድ ምሳሌ እንመልከት። "የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ" ዘፍ 3:7። የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ለኃጢያት የተዘጋ ጽድቅን ብቻ የሚያውቅ ዓይኖች ነበሯቸው። አለመታዘዝ ግን ለመንፈሳዊ ዕይታ የሚቸገር የኃጢያት ዓይኖችን ከፈተ። እኛም የወረስነው ለኃጢያት የተከፈቱ ዓይኖችና ወደ ክፉ ያዘነበለ ልብን ነው። ዓይኖቻችንንና ስሜቶቻችንን ማመን የሌለብን ለዚህ ነው! አዳምና ሔዋን ራቁታቸውን እንደሆኑ ባወቁ ጊዜ ተሸማቀው ተደበቁ። ራቁትነት የሚያሸማቅቅ የኃጢያት ውጤት ነው። ዛሬ ግን ራቁትነት ፋሽን፣ የሚያሸልም ውበትና ክብር ሆኗል። ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሰው ኃጢያትን ሲላመድ የደረሰበት የዝቅታ ደረጃ ነው። እግዚአብሔር ግን ወደ ቀድሞ አባቶቻችን ሊመልሰን ይፈልጋል። “የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል” ሚልክያስ 4፥6። ይህ በኃጢያት እጅግ እየተራራቀ የመጣውን የእኛን ትውልድ ወደ ነብያቱና ወደ ሐዋርያቱ በጽድቅ ለማቀራረብ የተገባ ቃል ኪዳን ነው። “እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ” ኤር 31፥18።

4. መለኮታዊው አጥር፦ ኃጢያት ማለት ከመለኮታዊው አጥር ከሆኑት ትዕዛዛቱ ውጪ መኖር ነው። ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳችን አመጽ ይለዋል። ሕጉ መልካሙንና ክፉውን የምንለይበት የግብረገብ መለኪያ በመሆኑ እግዚአብሔር አጥርን የሚያጥርብን እኛን ከውድቀትና ተከትሎት ከሚመጣው መዘዙ ለመጠበቅ ነው። “እነሆ መንገድሽን በእሾህ እዘጋለሁ፥ መንገድዋንም እንዳታገኝ ቅጥርን እቀጥርባታለሁ” ሆሴዕ 2፥8። ይህ ኃጢያት ወዳድ የሆነውን ስጋችንን የሚጨቁን መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያለመልም የከበረ ቃል ኪዳን ነው። ሙሉ ለሙሉ ፈቃዳችንን ስንሰጠው እግዚአብሔር የኃጢያትን መንገድ ይዘጋልናል፤ የጽድቁንም መንገድ ያስተምረናል።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ! መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Good morning, have yоu seen thіs рhоtо?! check https://efiop-tg.live/jdUBrd34

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል
============================

📖“የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል አልኋቸው።”

— ነሀምያ 4፥20


የአንድ ሀገር ልዕልና ባላት የጦር ኃይል ይወሰናል። በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ ሀገር መንግስታት የመሪነት ቦታውን ለመውሰድና ራሳቸውን በከፍታ ላይ ለማስቀመጥ፣ ከፍ ሲልም መላ ዓለምን ለመቆጣጠር የጦር ኃይላቸውን በከፍተኛ ደረጃ ያጠናክራሉ። ረብጣ ገንዘቦችንም ለዚህ ዓላማ ያፈሳሉ። አሁን ላይ ብዙ ሀገሮች በቴክኖሎጂ የረቀቁ የጦር መሳሪያዎችን በመታጠቅ ዳር ድንበራቸውን ከወራሪ ኃይል በተጠንቀቅ ይጠብቃሉ።


በነህምያ መሪነት የሚሰራው ሥራ ያሰጋቸው ጎረቤት ሀገሮች፣ ሥራውን ለማስቆም የተቻላቸውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው በተነሱ ጊዜ ነበር ነህምያ እንዲህ ያለው፦ “የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል አልኋቸው።” (ነህ 4፥20) የኢየሩሳሌም ሰዎች ጠላቶቻቸውን የሚከላከሉት፣ ገፍተው ሲመጡም ድል የሚነሱት በእጃቸው ባለው ሰይፍ ሳይሆን በእግዚአብሔር እርዳታ ነበር። እግዚአብሔር ተዋጊያቸው በመሆን ከጠላቶቻቸው እንደሚያሳርፋቸል ነህምያ ሲናገር እንመለከታለን።


ምን አልባት አሁን ላይ የጠላት ፍላፃ እጅግ በዝቶብን ለመዛል እየዳዳን ያለንበት ሁኔታ ላይ ልንሆን እንችላለን። ይህንን የሰይጣን ጡጫ ማሸነፍ የምንችለው በራሳችን አቅም አይደለም። በስጋችን ኃይል ብቻ ጠላትን ድል ልንነሳው ከቶ አይቻለንም። ልጆቹ በእንደዚህ አይነት ሕይወት ውስጥ ሲያልፉ አምላካችን ብቻችንን አይተወንም። ይልቁን ዘውትር ቅርባችን ሆኖ ስለ እኔና እናንተ ይዋጋልናል። ሰይጣንንም ድል በመንሳት የአሸናፊነትን ካባ ይደርብልናል።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ዘውትር ስለ እኔ ስለምትዋጋ አከብርሃለሁ። በአንተ ላይ እምነቴን እንዳፀና ደግሞ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/etdHmWdc_Rw?si=X0Ob8QQfLuZfmLzr

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

መፈለግ፣ ማድረግ፣ ማስተማር
============================

📖“ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።”

          — ዕዝራ 7፥10


“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” (ማቴ 28፥19-20) በማለት ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የከበረን ዕድል ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። ይህ ተልዕኮ በዛን ዘመን ለነበሩ ለደቀ መዛሙርቱ ብቻ የተሰጠ አልነበረም። ክርስትና የዱላ ክብብሎሽ እንደ መሆኑ ዛሬ ላይ ይህ ኃላፊነት ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ተሰጥቷል። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የእርሱ ተከታዮች የሆኑት ደቀ መዛሙርቱን ለሶስት ዓመት ከመንፈቅ ካስተማራቸው፣ የእውነትን ዝናር ካስታጠቃቸውና እምነታቸውን በተግባር ከተፈተነ በኃላ ሌሎችን ይደርሱ ዘንድ መመሪያን ሲሰጣቸው እንመለከታለን።


በንጉስ አርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ዕዝራ የሚባል ታላቅ ፀሐፊ ነበር። ይህ ሰው የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ስለነበረች በንጉሱ ዘንድ ሞገስን አገኘ። የዕዝራን ምዕራፍ ሰባት መፅሐፍ ስናነብ ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እንመለከታለን። ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሁ በዋዛና ጊዜ ለማሳለፍ ሳይሆን የመጣው ለቁም ነገር እንደነበር እንመለከታለን። “ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።” (ዕዝ 7፥10) የዕዝራ የሕይወት ልምምድ አስደናቂ ነበር። መንፈሳዊ ሕይወቱን የገራበት መንገድ ለብዙዎቻችን ትልቅ ትምሕርትን ይሰጠናል። ዕዝራ የእግዚአብሔርን ቃል ተግቶ በማጥናት፣ በቃሉ በመኖርና ያወቀውን እውነት ለሌሎች ለማስተማር ይተጋ ነበር።


ቃሉን ከልብ ማጥናት፣ በዛ ቃል ላይ መኖር፣ ያንን የሕይወት ቃል ለሌሎች ማስተማር ትክክለኛው የደቀ መዝሙርነት መርህ ነው። ብዙዎቻችን ለእግዚአብሔር ቃል የጠለቀ እውቀትና መሰጠት ሳይኖር ለሌሎች ለማስተማር እንሞክራለን። ይህ ልምምድ እጅግ የበዙ ክስረቶችን እንድናስተናግድ ያደርገናል። አገልግሎታችን ፍሬ የማይኖረው፣ ብዙዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ማፍለስ ያቃተን ትክክለኛውን የደቀ መዝሙርነት መርህ ባለመከተላችን ነው።


ቃሉን ለሌሎች ከማስተማራችን በፊት ራሳችን መሰራትና መኖር ያሻናል። ስለዚህ የአገልግሎት ሕይወታችንን መለስ ብለን እንቃኝ። የጎደለና የተበላሸ ነገር ካለ ከቃሉ አንፃር ለማስተካከል ፈቃደኛ ልብ ይኑረን። እንደዚህ ስናደርግ በአገልግሎታችን እጅግ የከበረን ውጤት በፀጋው ማምጣት እንችላለን።


ስናጠቃልል፣ በክርስቶስ እየሱስ የተሰጠንን ታላቅ ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ እነዚህን ቅደም ተከተል እንተግብር፦

1. የእግዚአብሔርን ቃል በፍፁም ልብ መፈለግ
2. በእግዚአብሔር ቃል መኖር
3. የእግዚአብሔርን ቃል ለሌሎች ማስተማር

ሕይወታችን በእንደዚህ አይነት መርህ ሲያልፍና ሲገራ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሚከብርበትን አገልግሎት ማቅረብ እንችላለን።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ሌሎችን ወደ አንተ እንዳመጣና ደቀ መዛሙርት እንዳደርግ የከበረን ዕድል ስለ ሰጠኸኝ አከብርሃለሁ። ይህንን ተልዕኮ ደግሞ ከፍፃሜ እንዳደርስ ቃልህን በማጥናት፣ እንደ ቃልህ በመኖርና ቃልህን ለሌሎች በማስተማር ዘመኔን እጨርስ ዘንድ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

በእዉነት እና በመንፈስ ማለት አስረዱኝ ?

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እንዲህ አይነት የምህረት አምላክ ስላለን ክብር ለእርሱ ይሁን።🙏🙏

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው
===============================

📖“ወደ እርሱም ጸለየ፤ እርሱም ተለመነው፥ ጸሎቱንም ሰማው፥ ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው ምናሴም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ አወቀ።”

           — 2 ዜና 33፥13


አሁን ላይ ይሁዳን በንጉስነት የሚያስተዳድረው ምናሴ ነው። ይህ ሰው በለጋነት ዕድሜው ወደዚህ ንግስና በመምጣት አያሌ አመታትን ገዛ። በእነዚህ ረጅም የንግስና ጊዜያት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን በማድረግ ከነበረበት ከፍታ እታች ወረደ። “በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አሳለፈ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፥ አስማትም አደረገ፥ መተተኛም ነበረ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።” (2 ዜና 33፥6)


ምንም እንኳን እግዚአብሔር አምላክ ከስህተት መንገዳቸው እንዲመለሱ ለምናሴና ለይሁዳዊያን ቢናገርም እነርሱ ግን ሊሰሙት አልወደዱም ነበር። በዚህም ምክንያት አሦራዊያን ወደ ባቢሎን ምድር አፈለሷቸው። ታዲያ በዚህን ወቅት ንጉስ ምናሴ ራሱን እጅግ በማዋረድና የእግዚአብሔርን ምሕረት በመናፈቅ የአምላኩን ፊት ፈለገ። “ወደ እርሱም ጸለየ፤ እርሱም ተለመነው፥ ጸሎቱንም ሰማው፥ ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው ምናሴም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ አወቀ።” (ቁ 13)


ዛሬ ላይ ከእግዚአብሔር እጅግ ርቀን እንደሄድን በማሰብ መመለሻው ጠፍቶን እዛው እየዳከርን ያለን ወገኖች እንኖራለን። የህሊና ወቀሳ አላስቆም፣ አላስቀምጥ ብሎን እየወቀረን ያለንም አንጠፋም። ንጉስ ምናሴ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ በሚያልፍበት ጊዜ የአምላኩን ፊት በመፈለግ ወደ እርሱ ቀረበ። ምሕረትንም አገኘ።


ወዳጆቼ፣ ራሳችንን በፊት በሰራናቸው ጥፋቶቻችን አስረን አናስቀምጥ። ከልብ በሆነ ንሰሀ ራሳችንን እፊቱ እናፍስስ። ስህተቶቻችንን አሽቀንጥረን ለመጣል አሁኑኑ ውሳኔን እናድርግ። እርሱም ይለመነናል። ወደ ቀደመውም ክብራችን ይመልሰናል።


ይህንን ስናስተውል ታዲያ እንዲህ በማለት እናውጃለን፦ “ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።” (መዝ 66፥20)


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ጸሎቴን ስላልከለከልከኝ፣ ምሕረትህን ከእኔ ስላላራቅህ አመሰግንሃለሁ። በድዬሃለሁና በምሕረትህ ጎብኘኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እንዴት ቆያችሁ ወንድሞችና እህቶች፤

በዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ አሉታዊ ተጽዕኖ ውስጥ እንዴት ክርስትናን መኖር ይኖርብናል የሚል ጉዳይ ለውይይት አንስተን ነበር።

በማንበብና በሐሳብ የተሳተፋችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ! ጉዳዩ ሰፊ ቢሆንም ጥቂት ሐሳቦችን እንመልከት።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Darkness cannot drive out darkness; only light can do that. Hate cannot drive out hate; only love can do that.
~ Martin Luther King Jr.

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Keerru maganikera illana

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አሜን God bless you!!!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፍረዱ
============================

📖“እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ እንዲሁ እግዚአብሔርን በመፍራት በቅንነትም በፍጹምም ልብ አድርጉ።”

— 2 ዜና 19፥9


እውነተኛ ፍርድ በጠፋበት አስቀያሚ ዘመን ላይ እንገኛለን። የብዙ ሰዎች ሕይወት ቅን የሆነን ብይን በማጣት ጎስቁሏል። የሕይወት መውጫቸው የሆነው ልባቸው እንዳይጠገን ሆኖ ፍርክስክሱ ወጥቷል። ፍርድ የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉሙ ጥቅም ከሆነ ሰነባብቷል። እውነት ተክዳ ሀሰት ደግሞ በፍርድ ወንበር ላይ በክብር ተሽሞንሙና ተቀምጣለች። ንፁህ የሆነው ሕሊና ለሆዳቸው ባደሩ ፈራጆች ረክሷል።


ንጉስ ኢዮሣፍጥ በሚመራት ሀገር ላይ ፍትህ ይሰፍን ዘንድ ዳኞችን ሲሾም እንመለከታለን። “በምድር ላይ በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆች አኖረ።” (2 ዜና 19፥5) ቀጠል አድርጎም እንዲህ የሚልን መመሪያ ሰጣቸው፦ “ፈራጆቹንም፦ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ እርሱም በፍርድ ነገር ከእናንተ ጋር ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ።” (ቁ 6)


ፍርድ የእግዚአብሔር መሆኑን ንጉስ ኢዮሣፍጥ ጠንቅቆ በማወቅ ይህንን መመሪያ ሰጣቸው። መፅሐፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ እንደሆነ በጉልህ ይናገራል። “ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።” (መዝ 50፥6) ዛሬ ላይ ፍርድን የምንሰጠው እኛው ራሳችን እንደሆንን በማሰብ የተዛባን ብይን እንሰጣለን። በዚህም የእሳት ፍምን እላያችን ላይ እናነዳለን። ይህ ጥፋትን የሚያስከትል፣ ራሳችንንም ሰይጣን የዘረጋው ወጥመድ ውስጥ የሚከትት ድርጊት ነው። ለዚህም ነው ንጉስ ኢዮሣፍጥ ዳኞችን (ፈራጆችን) ከሾመ በኃላ አካሄዳቸውን ያስተካክሉ ዘንድ ምክሩን የለገሳቸው። “እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ እንዲሁ እግዚአብሔርን በመፍራት በቅንነትም በፍጹምም ልብ አድርጉ።” (ቁ 9) እያንዳንዷ የምናሳልፋት ውሳኔ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በታማኝነትና ንፁህ በሆነ ልብ ሊሆን እንደሚገባ ልብ ይሏል።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ እውነተኛ ፍርድ በጠፋበት በዚህ ክፉ ዘመን ቅን ፈራጅ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። ይህ ባህሪይ ደግሞ በሕይወቴ ይገለጥ ዘንድ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel