aybclub | Unsorted

Telegram-канал aybclub - AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

-

ቃልህ(ሕግህ) ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው። መዝሙረ ዳዊት 119:105

Subscribe to a channel

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Amen God bless you!!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ሰላም እንዴት ናችሁ..... ጸጋ ና ህግ የሚል soft copy ያላችሁ ለኩልኝ

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Tebarek.... Amen++++

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ጥበብ፣ ዋጋው ላቅ ያለ!
============================

📖“ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም። የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ይበልጣል።”

            — ኢዮብ 28፥18


አንድ ንጉስ ህልም ያልምና የህልሙን ፍቺ ይነግሩት ዘንድ በማሰብ ጠቢባንን ከተለያየ ስፍራ ያስጠራል። ህልሙን በትክክል ለፈታለት ሰው ዳጎስ ያለ ሽልማትም እንደሚሰጥ በአዋጅ ያስነግራል። ይህንንም ጥሪ በመስማት ታዲያ ጠቢባን ከያሉበት ስፍራ ተሰበሰቡ። ጠቢባን ተብለው ከመጡት ውስጥ ተራቸውን ጠብቀው ወደ ንጉሱ መግባት ይጀምራሉ። ነገር ግን ለንጉሱ የህልሙን ትክክለኛ ፍቺ ከተናገሩ በኃላ ሽልማት ሳይሆን የጠበቃቸው ሞት ነበር።


ንጉሱ አየሁት ያለው ህልም ይህ ነበር፦ "የምሳሳላቸው ጥርሶቼ በሙሉ ሲረግፉ አየሁ።" ታዲያ መጀመሪያ የገቡት ጠቢባን ህልሙን እንዲህ በማለት ነበር የፈቱት፦ "ንጉስ ሆይ የህልሙ ፍቺ ይህ ነው። አንተ በመጀመሪያ ትሞታለህ። ከዛ በኃላ ደግሞ እጅግ የምትወዳቸው ልጆችህና ባለቤትህ ይሞታሉ።" ነገር ግን አንዱ እነዚህን ነገሮች ካስተዋለ በኃላ እንዲህ በማለት ለንጉሱ የህልሙን ፍቺ ነገረው፦ "የልጆችህንና የሚስትህን ሞት አታይም።" ንጉሱ ፍቺውን ከሰማ በኃላ ታዲያ ይህን ሰው በመሸለም አሰናበተው።


ሁሉም የተናገሩት ነገር ተመሳሳይ ቢሆንም በመጨረሻ ላይ የህልሙን ፍቺ የተናገረው ሰው ግን የጥበብን ቃል ከአንደበቱ አወጣ። ይህንም በማድረጉ ምክንያት ሕይወቱን ከማትረፉ ባሻገር ከንጉሱ ዘንድ ሽልማት ተበረከተለት።


ይህ ታሪክ ጥበብን አጥብቀን እንድንሻ ይነግረናል። የጥበብ ቃል መፍለቂያ ስፍራዎች እንድንሆን ይጋብዘናል። ኢዮብ የጥበብን ዋጋ ከዕንቁ አስበልጦ በመናገር ጥበብ ምን ያክል አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ተናገረ። “ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም። የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ይበልጣል።” (ኢዮ 28፥18) ጠቢቡ ሰለሞንም ተመሳሳይነት ያለውን ሀሳብ ሲያፀና እንመለከታለን። “ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ትበልጣለችና፤ የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።” (ምሳ 8፥11)


የዚህ ሁሉ ጥበብ ባለቤት ደግሞ እግዚአብሔር ነው። ይህ አምላክ ታዲያ ጥበብን ከማስተዋል ጋር ደርቦ ለመስጠት ሁሌም ናፍቆቱ ነው። “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።” (ምሳ 1፥7) ተብሎ እንደ ተፃፈ እግዚአብሔርን ከፍቅር የተነሳ በመፍራት የጥበብ ባለቤቶች እንሆን ዘንድ ናፍቆቴ ነው።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ የጥበብ ሁሉ ባለቤት አንተ ስለሆንክ እባርክሃለሁ። ሕይወቴን በትክክለኛው መንገድ መምራት እንድችል ዋጋው ከቀይ ዕንቁ ይልቅ በሚበልጠው ጥበብ ባርከኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ነገ ሠንበት ከሠዐት ከ8:45 ጀምሮ
እንዳያመልጣችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/24AHZHosqpI?si=JEt42R9JG1b63AK-

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እንደ ወርቅ እወጣለሁ
============================

📖“የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።”

           — ኢዮብ 23፥10


በትምህርት ስርዓት ውስጥ ፈተና አንዱ አካል ነው። የእውቀት አባት የሆነው መምህር የተማሪዎቹን አዕምሮ ለመገንባት ሳይታክት ያስተምራል። ይህ መምህር ተማሪዎቹን በሚያስተምርበት ጊዜ የቾኩ ብናኝ አያስበረግገውም። ረጅም ሰዓት ቆሞ የሚያሳልፈውን ጊዜ እንደ ጉዳት አይቆጥረውም። እውቀቱን ለማደርጀትና ጣዕም ያለውን ትምህርት ለተማሪዎቹ ለመስጠት ካለው ፍላጎት የተነሳ የተለያዩ ማጣቀሻ መፅሐፍትን ያገላብጣል። ድንገት በክፍሉ ውስጥ አንድ ተማሪ ከቀረ የእርሱ ነገር ግድ ይለዋል። ታዲያ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት ለተማሪዎቹ የሚከፍለው መምህር ፈተናን ያዘጋጃል። ይህ መምህር ለተማሪዎቹ ካለው መልካም ቅናት የተነሳ ይፈትናቸዋል። ጠልቷቸው ነው? በፍፁም! ተማሪዎቹ ከነበሩበት የክፍል ደረጃ ከፍ እንዲሉ ስለሚፈልግ በዚህ ውስጥ እንዲያልፉ ያደርጋቸዋል።


ተመሳሳይነት ያለውና የማያድግ ሕይወት መኖር ካለ መኖር ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ለውጥ የሌለውና ፈቀቅ የማይል ማንነት መጨረሻው ያማረ አይሆንም። ኢዮብን የያዘው መርከብ በከፍተኛ ማዕበል ቢመታም ኢዮብ አልሰጠመም። በዝቅታ ውስጥ ከፍ ማለት እንዳለ የኢዮብ ሕይወት ምስክር ነው። ለዚህ እኮ ነው ኢዮብ እንዲህ በማለት ሲናገር የምናደምጠው፦ “የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።” (ኢዮ 23፥10)


የነጠረን ወርቅ መሆን የማይፈልግ ያለ አይመስለኝም። እንግዲያውስ አላሳድግ ብለው አንቀው የያዙን አጉል ልምምዶች በእሳት ውስጥ ያልፉ ዘንድ እንፍቀድ። ከዚያ በኃላማ አንፀባራቂ ወርቆች እንሆናለን። ሕይወታችን ክርስቶስን የሚያሳይ ሕያው ምስክር ይሆናል። ስለዚህ ከፍ ሊያደርገን በተለያየ ምክንያት ፈተና ወደ ሕይወታችን ሲመጣ እንዲህ ማለትን እንለማመድ፦ “የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።” (ኢዮ 23፥10)


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ አንተ በክፉ ማንንም ስለማትፈትን አከብርሃለሁ። አላስፈላጊ ልምምዶችን ከሕይወቴ በማስወገድ እንደ ወርቅ አንፃኝ ስል እፊትህ እቀርባለሁ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አሜን ጌታ ይባርክህ ወንድማችን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አሜን የኛምእይወት እንደዛ ይመስክር።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ብልጭ አይልም
============================

📖“የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም።”

— ኢዮብ 18፥5


ነፋሻማ አየር ባለበት ጊዜ እሳት ማቀጣጠል ትንሽ ከበድ ይላል። ከክብሪቱ የምናገኛት ትንሽዬ የእሳት ፍንጣቂ ከለላን ካላገኘች ንፋሱ መጥቶ ወዲያው ሊያጠፋት ይችላል። ይህንን ሁሉ ነገር አልፋ ያቺ ትንሽዬ የብርሃን ፍንጣቂ አንዴ ከእንጨቱ ጋር ከተያያዘች ግን ልትጠፋ አትችልም። መላ ስፍራውን በብርሃንና በሙቀት ትሞላዋለች።


ብርሃን የማይታይበት ሕይወት ከውስጣዊ ሰላም ጋር የተፋታ ነው። እንደዚህ አይነት ማንነት በውስጡ ጨለማ ስለሞላ በዙሪያው ላሉ ሰዎች ብርሃንን ሊሰጥ አይችልም። ሹሐዊው በልዳዶስ ይህንን ሀሳብ እንዲህ በማለት ያፀናዋል፦ “የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም።” (ኢዮ 18፥5)


የዓለም ብርሃን የሆነውን ጌታችንን በሕይወታችን ላይ ስንሾም ጨለማ በእኛ ዘንድ ስፍራ አይኖረውም። መታወቂያችን ይቀየራል። የብርሃን ልጆች እንባላለን። እንደቀደመው ዘመን መኖር አይቻለንም። የጨለማን ስራ አሽቀንጥረን በመጣል የብርሃን ብልጭታ መፍለቂያ ማዕከል እንሆናለን። ታዲያ ይህ ሲሆን ሕይወታችን በመንፈስ ቅዱስ እሳት ይቀጣጠላል።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ብርሃኔ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። ሕይወቴን ደግሞ የብርሃን ብልጭታ መፍለቂያ ስፍራ አድርገው። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ” ዘፍጥረት 3፥15።

ሰላም ወንድሞችና እህቶች እንደምን ቆያችሁ፡ ከዚህ በፊት በተከታታይ የኃጢያትን አጀማመር፣ መስፋፋትና ውጤቱን ተመልክተናል። ከዚህ በመቀጠል ለዚህ ክፉ ወረርሽኝ ከሰማይ የተሰጠውን ምላሽ እናያለን።

የሰው ዘር በኃጢያት ከወደቀ በኋላ እግዚአብሔር ለኃጢያቱ አልተወውም። ሰውን ለዘላለም ከሚያጠፋው ኃጢያት የሚያድንበትን መንገድ እግዚአብሔር አዘጋጀ። እርሱም ልጁ እየሱስ ክርስቶስ ነው።

በፍጥረት የእግዚአብሔር የነበረው የሰው ዘር በኃጢያት ምክንያት የዲያቢሎስ ሆነ። “ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና” 1ኛ ዮሐንስ 3፥8። ሰዎችን ከእግዚአብሔር ለይቶ ከዲያቢሎስ ጋር የሚያስማማው አንድ ጉዳይ ነው እርሱም ኃጢያት ነው።

ስለዚህ አዳምና የሰው ዘር ባጠቃላይ ከሰይጣን ጋር በኃጢያት አንድ ሆነ። ይህንን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰው ዘር ከሰይጣን ኃይል የሚላቀቅበትን ታላቅ ቃል ኪዳን በኤደን ገባ።

"በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ።" እግዚአብሔር በሰይጣንና በሰዎች መካከል ጠላትነትን በልጁ አማካኝነት አኖረ። የእግዚአብሔር ጠላትነት ከአመጽ ጋር ነው። በጽድቅና በኃጢያት መካከል፣ በመልካምና በክፉ መካከል፣ በብርሃንና በጨለማ እንዲሁም በእውነትና በሐሰት መካከል ጠላትነትን አድርጓል።

ይህም እውን የሆነው ዘር ተብሎ በተጠቀሰው በክርስቶስ አማካኝነት ነው። ሰዎችን ከዲያቢሎስ መንጋጋ ለማስጣል ክርስቶስ በመሃል ገባ። “ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል” ኢሳይያስ 53፥12። በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ የሚያምን ሰው የጽድቅ ምርኮኛ ሆኖ የሰማይ ቤተሰብ አባል ይሆናል።

እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ፍጻሜ የሚሆንበትን የመሲሁን መምጫ የትውልድ መስመር ለየ። ይህንን ማድረግ ያስፈለገው በተለይ ክፋት በምድር ላይ በመስፋፋቱና ከውሃ ጥፋት በኋላ እንደገና የጀመረው የሰው ዘር መልሶ ጥፋት ውስጥ በመዘፈቁ ነበር።

"እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ" ዘፍጥረት 121-3።

እግዚአብሔር  ስለ መሲሁ መምጣትና ስለደህንነት በድጋሜ ቃል ገባ። አብርሃምን ለመሲሁ መምጫ የትውልድ መስመር ከለየ በኋላ "የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ" አለው።

ይህም ማለት የትኛውም ሕዝብ ለአብርሃም የተነገረውን አምኖ የሚቀበል ከሆነ እንደሚባረክና የቃል ኪዳኑ ወራሽ እንደሚሆን፤ የአብርሃምን ዘር የሚዋጋ ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔርን እንደሚዋጋ የሚያመለክት ነው።

በዚህ መሰረት በጊዜው የተመረጠ ሕዝብ የነበረው በእስራኤላውያን ላይ ይደርስ የነበረውን ውጊያ ሰይጣን የመሲሁን መምጫ የሆነውን የትውልድ መስመር ለማጥፋት እየሞከረ ስለነበር እግዚአብሔር በጦርነት ሲመክትላቸው ነበር።

ከላይ ከተመለከትናቸው ሐሳቦች ቢያንስ ሁለት ትምህርቶችን እናገኛለን፦

1. ክፉን የመጥላት ቃል ኪዳን፦ በሰይጣንና በሰዎች መካከል የተደረገው ጠላትነት የደህንነታችን ዋና መርህ ነው። ይህንን ጠላትነት በየዕለቱ አምኖ የሚቀበል ሰው በየዕለቱ ኃጢያትን የመጥላትና ጽድቅን የመውደድ ኃይልን ከእግዚአብሔር ይቀበላል። ኃጢያትን ለሚወደው ተፈጥሯዊ ባሕሪያችን ይህ እጅግ ገጣሚ መድኃኒት ነው። እግዚአብሔር ቃል ገብቷልና ኃጢያትን መጥላት ይቻላል! ከኃጢያት ጋር የጠላትነት ግንኙነት እንዲኖረን የምንፈልግና ጥረት የምናደርግ ከሆነ እግዚአብሔር ይዋጋልናል።

2. የሚዋጋልን እግዚአብሔር፦ የሚጠራን እግዚአብሔር እራሱ ለእኛ ይዋጋልናል። አብርሃምን ነጥሎ ጠራው፣ ለዘሩ ጥበቃውን እንደሚያደርግ ቃል በገባለት መሰረትም ተዋጋለት። በምድረበዳ ሕዝቡን የመራው ጌታ በተለይ ታማኝነታቸውን ጠብቀው እስከቆዩ ድረስ ይዋጋላቸው ነበር። "እግዚአብሔር ስለናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ" ዘፀ 14:14። መጠራታችንና መለየታችን ተጠብቆ የሚኖረው የሚዋጋልን እግዚአብሔር ስላለን ነው።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል !
መልካም ሠንበት🎁

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/QqwLsFKnwg8?si=l-qG8to6e0bkk47r

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ያልተነገረለት ወረርሽኝ ክፍል 2

ባለፈው ሳምንት ስለ ኃጢያት የመስፋፋት ባሕሪይና ስለ ውጤቶቹ ተመልክተናል። በተለይም የሰው ዘር በኃጢያት ምክንያት የእግዚአብሔር ባሕሪይ የሆነውን ክብሩንና ምድርን የማስተዳደር ኃላፊነትን እንዳጣ፤ ዛሬም ዋጋ የሚያስከፍለን እንደሆነ አይተናል።

ዛሬ በቤተሰብና በማሕበረሰብ ደረጃ የደረሰውን ጉዳት ለማየት እንሞክራለን።

የዚህ ትምህርት ዓላማ ኃጢያት ያሳጣንን በረከቶችና ያመጣብንን ቀውሶች በተቻለ መጠን በመረዳት አለመታዘዝን የሚጠላና ጽድቅን የሚራብ ሕይወት እንዲኖረን የሚረዳ መልዕክት ማስተላለፍ ነው።

ኃጢያት የማህበረሰባችን ራስ ምታት!

ምድራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ማስተናገዷን ቀጥላለች። የምናመሰግንባቸውና የምንደሰትባቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ ሆነው የችግሮቹ ዋነኛ ተጠቂ የሆነው እኛ ሰዎች በምድር ላይ የምንኖረው ሕይወት የግድ መከራን በመጋፈጥ ሆኗል።

የምድር ችግር የሰዎች ችግር ውጤት ነው። የእያንዳንዱ ሰው አመጣጥ ከቤተሰብ ወይም ከወላጆች የሚመዘዝ በመሆኑ የቤተሰብ መንፈሳዊ ሁኔታ ለተቀባዩ ትውልድ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው።

ለብዙ ትምህርት መነሻ የሆኑንን የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን በድጋሜ በሌላ ጎን እንመልከት።

ቤተሰብን ያቋቋመውና ትዳርን የመሰረተው እግዚአብሔር እራሱ ነው። ትዳርን ያቋቋመበት መንገድ ዛሬ ከምናየው የተለየ ነው።

አዳም ሲፈጠር ሔዋን አልነበረችም። ስለዚህ አዳም ሕያው ሰው እንደሆነ አስቀድሞ የተመለከተው ፈጣሪውን እግዚአብሔርን ነው። ሌላ ማንንም አያውቅም። ሔዋን እንደተፈጠረች አዳም እንቅልፍ ላይ ነበርና ያየችው እግዚአብሔርን ነው። ይህ ትልቅ ትምህርት አለው። እግዚአብሔር አስቀድሞ በተናጠል ከእርሱ ጋር እንዲተዋወቁ ካደረገ በኋላ አንድ አደረጋቸው። ያጣመራቸው እርሱን በግል ካወቁት በኋላ ነበር። በመሐላቸው ያለው ፈጣሪያቸው ነበርና ፍጹም ሕብረትና ፍቅር ነበራቸው።

ፍሬውን ከበሉ በኋላ ክስና ጥርጣሬ በመሐላቸው ገባ። “አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” ዘፍ 3፥12። አዳም ሔዋንን አጣጣላት እግዚአብሔርንም ወነጀለ። ለተከሰተው ጥፋት ኃላፊነት የሚወስድ ጠፋ።

አዳምና ሔዋን የሳቱት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሳይወልዱ በመሆናቸው ከእነሱ የቀጠለው የሰው ዘር በሙሉ በኃጢያት ጥላ ስር ወድቋል።

በማሕበረሰብ ተገልጠው የምናያቸው ኢሞራላዊ ድርጊቶችና አመለካከቶች እንዲሁም ወንጀሎች በቤተሰብ ደረጃ የሚስተዋሉ የመንፈሳዊነት አለመኖር ወይም መጓደል ነጸብራቅ ናቸው። ስለዚህ በሰፊው የሚስተዋለው የግብረገብ መበላሸት ምንጩ በአብዛኛው ከትውልድ ትውልድ እየተንከባለለ የመጣ የቤተሰብና የአስተዳደግ ችግር ነው።

ከነዚህ ቢያንስ የሚከተሉትን ነጥቦች እንማራለን፦

1. ቤተሰብ የእግዚአብሔር ተቋም ነው፦ ዛሬም ቤተሰብ የመመስረቻው ትክክለኛውና ብቸኛው መንገድ በእግዚአብሔር ዕቅድ መመራት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ "በመጨረሻ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን" እንደሚመጣ ይነግረናል። አስጨናቂ የሚሆነውም በትውልድ መበላሸት ምክንያት ነው። "ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ" 2ጢሞ 3:2-5። እነዚህ በተለይ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ላይ የሚስተዋሉ ናቸው፤ ምክንያቱም የአምልኮ መልክ እንዳላቸው ቃሉ ይነግረናል። እነዚህ መገለጫዎች በአጠቃላይ ማህበረሰብ ላይ የሚታዩ ሲሆኑ ሁሉም መጥፎ ባሕሪያት በአንድ ግለሰብ ላይ ይኖራሉ ማለት ላይሆን ይችላል። ቁጥር 6 እና 7 ላይ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርግ ነጥብ እናያለን። “ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።” በመጨረሻ ዘመን በአብዛኛው ትዳር የሚመሰረተው ከላይ የተዘረዘሩት ማሕበረሰብን የሚያስጨንቅ ባሕሪያት ባሏቸው ወንዶች እና ኃጢያት በተከመረባቸውና ሁልጊዜ እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ባልቻሉ ሴቶች መካከል ነው። ከመሰል ቤተሰቦች የሚወለዱ ልጆች በአመዛኙ የባሱ እንጂ የተሻሉ ይሆናሉ ተብሎ አይጠበቅም። እግዚአብሔር ከዚህ ሕይወት ይጠብቀን! አስቀድሞ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ከእርሱ ጋር ዘወትር መቆየት እንደተለመደው ተመስርቶ እንደማንኛውም ቤተሰብ ከሚኖር አኗኗር ያድነናል። “እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ… ኖህ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ" ዘፍ 6፥5፣8። ሙሉ ቤተሰቡን ይዞ በእግዚአብሔር ማዳን የተረፈው ኖህ ከሎጥ በተቃራኒ ለመልካም ማሕበረሰብ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል። ሰዎችን ከመከተል ይልቅ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ በግል፣ በቤተሰብና በማሕበረሰብ ውስጥ ልዩነትን ይፈጥራል።

2. ጻዲቅ ቤተሰብ የጠላት ስጋት ነው፦ ጠላት ቤተሰብ ላይ ትኩረት የሚያደርገው በምክንያት ነው። የክፋት ዕቅዱ በቀላሉ ተሳክቶ ይዛመታል። ይህንን የምንመክትበት ወይም ቢያንስ ተጽዕኖውን የምንቀንስበት መርህ በቃሉ ተገልጾልናል። ልጆች የወላጆቻቸውን ዝንባሌና የስራቸውን ውጤት ይወርሳሉ። መልካምም ሆነ ክፉ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ቤተሰባዊ በመሆኑ ለእኛ ለልጆቹ ባሕሪውንና የስራውን ውጤት ያወርሰናል። በተመሳሳይ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ከፈጣሪ ባገኙት እውነትና ብርሃን ያሳድጋሉ። ከኃጢያት በኋላ ይህ ስርዓት ጥቃት ቢደርስበትም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም። በድሃ ቤቱ ውስጥ ለ8 ዓመት በሚስኪን እናቱ የተማረው ሙሴ በተቀማጠለው ቤተ-መንግስት ውስጥ ባለ መስህብ አልተወሰደም። ንግስና ያላጓጓው “ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ” ዕብ 11፥24። “ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ” ዘፀ 2፥11። ዓለምን እየናቀ አምላኩን እያላቀ የሚኖር ልጅ በአጋጣሚ ሳይሆን በወላጆች የሚያንጽ ወጥ ባሕሪይ፣ በቤተሰባዊ አምልኮና ትጋት ሊገኝ የሚችል ነው። “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” ምሳሌ 22፥6።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ያልተነገረለት ወረርሽኝ ክፍል 2

ባለፈው ሳምንት ስለ ኃጢያት የመስፋፋት ባሕሪይና ስለ ውጤቶቹ ተመልክተናል። በተለይም የሰው ዘር በኃጢያት ምክንያት የእግዚአብሔር ባሕሪይ የሆነውን ክብሩንና ምድርን የማስተዳደር ኃላፊነትን እንዳጣ፤ ዛሬም ዋጋ የሚያስከፍለን እንደሆነ አይተናል።

ዛሬ በቤተሰብና በማሕበረሰብ ደረጃ የደረሰውን ጉዳት ለማየት እንሞክራለን።

የዚህ ትምህርት ዓላማ ኃጢያት ያሳጣንን በረከቶችና ያመጣብንን ቀውሶች በተቻለ መጠን በመረዳት አለመታዘዝን የሚጠላና ጽድቅን የሚራብ ሕይወት እንዲኖረን የሚረዳ መልዕክት ማስተላለፍ ነው።

ኃጢያት የማህበረሰባችን ራስ ምታት!

ምድራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ማስተናገዷን ቀጥላለች። የምናመሰግንባቸውና የምንደሰትባቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ ሆነው የችግሮቹ ዋነኛ ተጠቂ የሆነው እኛ ሰዎች በምድር ላይ የምንኖረው ሕይወት የግድ መከራን በመጋፈጥ ሆኗል።

የምድር ችግር የሰዎች ችግር ውጤት ነው። የእያንዳንዱ ሰው አመጣጥ ከቤተሰብ ወይም ከወላጆች የሚመዘዝ በመሆኑ የቤተሰብ መንፈሳዊ ሁኔታ ለተቀባዩ ትውልድ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው።

ለብዙ ትምህርት መነሻ የሆኑንን የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን በድጋሜ በሌላ ጎን እንመልከት።

ቤተሰብን ያቋቋመውና ትዳርን የመሰረተው እግዚአብሔር እራሱ ነው። ትዳርን ያቋቋመበት መንገድ ዛሬ ከምናየው የተለየ ነው።

አዳም ሲፈጠር ሔዋን አልነበረችም። ስለዚህ አዳም ሕያው ሰው እንደሆነ አስቀድሞ የተመለከተው ፈጣሪውን እግዚአብሔርን ነው። ሌላ ማንንም አያውቅም። ሔዋን እንደተፈጠረች አዳም እንቅልፍ ላይ ነበርና ያየችው እግዚአብሔርን ነው። ይህ ትልቅ ትምህርት አለው። እግዚአብሔር አስቀድሞ በተናጠል ከእርሱ ጋር እንዲተዋወቁ ካደረገ በኋላ አንድ አደረጋቸው። ያጣመራቸው እርሱን በግል ካወቁት በኋላ ነበር። በመሐላቸው ያለው ፈጣሪያቸው ነበርና ፍጹም ሕብረትና ፍቅር ነበራቸው።

ፍሬውን ከበሉ በኋላ ክስና ጥርጣሬ በመሐላቸው ገባ። “አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” ዘፍ 3፥12። አዳም ሔዋንን አጣጣላት እግዚአብሔርንም ወነጀለ። ለተከሰተው ጥፋት ኃላፊነት የሚወስድ ጠፋ።

አዳምና ሔዋን የሳቱት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሳይወልዱ በመሆናቸው ከእነሱ የቀጠለው የሰው ዘር በሙሉ በኃጢያት ጥላ ስር ወድቋል።

በማሕበረሰብ ተገልጠው የምናያቸው ኢሞራላዊ ድርጊቶችና አመለካከቶች እንዲሁም ወንጀሎች በቤተሰብ ደረጃ የሚስተዋሉ የመንፈሳዊነት አለመኖር ወይም መጓደል ነጸብራቅ ናቸው። ስለዚህ በሰፊው የሚስተዋለው የግብረገብ መበላሸት ምንጩ በአብዛኛው ከትውልድ ትውልድ እየተንከባለለ የመጣ የቤተሰብና የአስተዳደግ ችግር ነው።

ከነዚህ ቢያንስ የሚከተሉትን ነጥቦች እንማራለን፦

1. ቤተሰብ የእግዚአብሔር ተቋም ነው፦ ዛሬም ቤተሰብ የመመስረቻው ትክክለኛውና ብቸኛው መንገድ በእግዚአብሔር ዕቅድ መመራት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ "በመጨረሻ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን" እንደሚመጣ ይነግረናል። አስጨናቂ የሚሆነውም በትውልድ መበላሸት ምክንያት ነው። "ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ" 2ጢሞ 3:2-5። እነዚህ በተለይ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ላይ የሚስተዋሉ ናቸው፤ ምክንያቱም የአምልኮ መልክ እንዳላቸው ቃሉ ይነግረናል። እነዚህ መገለጫዎች በአጠቃላይ ማህበረሰብ ላይ የሚታዩ ሲሆኑ ሁሉም መጥፎ ባሕሪያት በአንድ ግለሰብ ላይ ይኖራሉ ማለት ላይሆን ይችላል። ቁጥር 6 እና 7 ላይ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርግ ነጥብ እናያለን። “ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።” በመጨረሻ ዘመን በአብዛኛው ትዳር የሚመሰረተው ከላይ የተዘረዘሩት ማሕበረሰብን የሚያስጨንቅ ባሕሪያት ባሏቸው ወንዶች እና ኃጢያት በተከመረባቸውና ሁልጊዜ እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ባልቻሉ ሴቶች መካከል ነው። ከመሰል ቤተሰቦች የሚወለዱ ልጆች በአመዛኙ የባሱ እንጂ የተሻሉ ይሆናሉ ተብሎ አይጠበቅም። እግዚአብሔር ከዚህ ሕይወት ይጠብቀን! አስቀድሞ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ከእርሱ ጋር ዘወትር መቆየት እንደተለመደው ተመስርቶ እንደማንኛውም ቤተሰብ ከሚኖር አኗኗር ያድነናል። “እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ… ኖህ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ" ዘፍ 6፥5፣8። ሙሉ ቤተሰቡን ይዞ በእግዚአብሔር ማዳን የተረፈው ኖህ ከሎጥ በተቃራኒ ለመልካም ማሕበረሰብ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል። ሰዎችን ከመከተል ይልቅ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ በግል፣ በቤተሰብና በማሕበረሰብ ውስጥ ልዩነትን ይፈጥራል።

2. ጻዲቅ ቤተሰብ የጠላት ስጋት ነው፦ ጠላት ቤተሰብ ላይ ትኩረት የሚያደርገው በምክንያት ነው። የክፋት ዕቅዱ በቀላሉ ተሳክቶ ይዛመታል። ይህንን የምንመክትበት ወይም ቢያንስ ተጽዕኖውን የምንቀንስበት መርህ በቃሉ ተገልጾልናል። ልጆች የወላጆቻቸውን ዝንባሌና የስራቸውን ውጤት ይወርሳሉ። መልካምም ሆነ ክፉ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ቤተሰባዊ በመሆኑ ለእኛ ለልጆቹ ባሕሪውንና የስራውን ውጤት ያወርሰናል። በተመሳሳይ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ከፈጣሪ ባገኙት እውነትና ብርሃን ያሳድጋሉ። ከኃጢያት በኋላ ይህ ስርዓት ጥቃት ቢደርስበትም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም። በድሃ ቤቱ ውስጥ ለ8 ዓመት በሚስኪን እናቱ የተማረው ሙሴ በተቀማጠለው ቤተ-መንግስት ውስጥ ባለ መስህብ አልተወሰደም። ንግስና ያላጓጓው “ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ” ዕብ 11፥24። “ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ” ዘፀ 2፥11። ዓለምን እየናቀ አምላኩን እያላቀ የሚኖር ልጅ በአጋጣሚ ሳይሆን በወላጆች የሚያንጽ ወጥ ባሕሪይ፣ በቤተሰባዊ አምልኮና ትጋት ሊገኝ የሚችል ነው። “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” ምሳሌ 22፥6።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እግዚአብሔር ክፉ አይሠራም
============================

📖“በእውነት እግዚአብሔር ክፉ አይሠራም፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ፍርድን ጠማማ አያደርግም።”

         — ኢዮብ 34፥12


አሁን ባለንበት ዘመን ክፋት በምድር ላይ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ተንሰራፍቷል። በሰዎች ጭንቅላት ላይ ተረማምዶ ማለፍ የጥበብ መለኪያ ቱንቢ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል። የሰው ልጅ በራስ ወዳድነት ሰንሰለት ራሱን ተብትቦ በማሰሩ የሌሎች ነገር ግድ አይለውም። ብቻ የእርሱ ጥቅም ይጠበቅለት እንጂ የክፋት ጥግ የተባለውን ነገር ከማድረግ ወደ ኃላ አይልም። ብዙ ግንኙነቶችና ሕብረቶች በአንዱ ወገን ክፋት በማየሉ ምክንያት ፈርሰዋል፤ ጠፍተውማል።


ምን አልባት እጅግ የቅርብ ያልናቸው ሰዎች የክፋትን ጥግ አሳይተውን ይሆናል። እኩይ የሆነውንም ሴራቸውን ሸርበው ሊያጠፉን ቆርጠው የተነሱበት ጊዜ ላይ ራሳችንን ዋና ተዋናይ ሆነን አግኝተነውም ሊሆን ይችላል። ደግሞም በማር የተለወሰ መርዛቸውን እፉታችን በማቅረብ ገበታን ያዘጋጁልን መስሎን ልባችን የተሰበረበት ጊዜ ትውስ ይለን ይሆናል።


እግዚአብሔር ግን ከዚህ ፍፁም ይለያል። “በእውነት እግዚአብሔር ክፉ አይሠራም፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ፍርድን ጠማማ አያደርግም።” (ኢዮ 34፥12) የእግዚአብሔር ወዳጅነት ወረት የማያውቀው፣ ጥቅምን የማይፈልግ ነው። እርሱ ያለ ምክንያት ወድዶን በምክንያት አይጠላንም። እርሱ ክፋት የማያውቀው መልካም ነው። “እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።” (ናሆ 1፥7) ተብሎ እንደ ተፃፈ።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ክፋት የማያውቅህ መልካም ስለሆንክ አከብርሃለሁ። ከአንተ ደግሞ የተቀበልኩትን መልካምነት ለሌሎች አካፍል ዘንድ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

”ኢየሱስም፣ “ገና ወደ አብ ስላላረግሁ፣ አትንኪኝ፤ ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፣ ‘ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ’ ብሏል ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።“
ዮሐንስ 20:17


📖 በዮሐንስ 20 ላይ የተመሠረተ ልዩ የሆነ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ውይይት 👇👇

https://youtu.be/_ZaDdU0bBtU?si=7PdtRArukbhuuXTE

📌 እናንተም ተባረኩበት ሌሎችም እንዲባረኩበት ሼር & ሰብስክራይብ ያድርጉ።


መልካም ቀን 🎁

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አሜን አሜን እግዚአብሔር ይባርክ።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Is this going to be live? At least can someone record and share? God bless you all.

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ልዩ ፕሮግራም
የዛሬ ሳምንት ሰንበት በፍልውሀ ቤተክርስቲያን
ሁላችሁም ታድማችኋል !

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Thanks God bless you
It is an amazing message

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አሜን እግዚአብሔር አምላክ ሆይ በህይወቴ አንተ ተገለጥ

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

“እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ” ማቴዎስ 1፥21።

ለረጅም ዓመታት ሲጠበቅ የነበረው ታላቁ ቃል ኪዳን ተፈጸመና መሲሁ ስጋን ለብሶ ወደ ምድር መጣ።

ዓለም ሳይፈጠር በፊት የተዘጋጀልን አዳኝ በመጀመሪያ ለአዳም ከዚያም ለአብርሃምና ለትውልዱ ተስፋ እንደተሰጣቸው፣ በኢሳያስና በዳንኤል እንደተተነበየው የምድር አገልግሎቱን ሊፈጽም ወደ ታች ዝቅ አለ።

በሰማይ አመጸኛውን ሉሲፈርን ተዋግቶ ያሸነፈው እራሱ ክርስቶስ ሰዎችን ከሰይጣን ግዛት ነጻ ለማውጣት የምድርን ፍልሚያ ጀመረ።

የሰዎችን የኃጢያትን ዕዳ ለመክፈል ክርስቶስ ሰው ሆኖ መምጣት ነበረበት። በሰማይ የተካሔደውን ሰልፍ ያሸነፈው በአምላክነቱ ነበር። ምድር ላይ ግን ሰው ሆኖና በአባቱ ኃይል ታምኖ ተገለጠ። ክርስቶስ መለኮታዊነቱን ተጠቅሞ ከነክብሩ ቢገለጥ ኖሮ ሰዎች በክብሩ ይጠፋሉ እንጂ ሰዎችን የሚያድን ስራውን መፈጸም አይችልም ነበር።

በእግዚአብሔር ወልድ ሰው መሆን ውስጥ ተረድተነው የማንጨርሰው ሚስጥር ያለ ቢሆንም በትንሹ የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት፦

1. በአካላዊው ሰው መለኮታዊ ባሕሪይ፡ ክርስቶስ ምድር ላይ የኖረው ሰው ሆኖ ነው። እንደማንኛችንም መጥፎ ዝንባሌና ፈተና የሚያጠቃውን ደካማ አካል ተላብሶ ኖረ። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለን “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው” ዕብ 4፥15። ኃጢያትን በተግባር ከማወቅ በቀር ሰው ሆኖ በቅድስና ኖሮ የሰውን ኃጢያት ተሸክሞ አገልግሎቱን ፈጽሟል። የክርስቶስ አካላዊው ማንነቱ ከእኛ እንደ አንዳችን ነበር። "በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም" ኢሳይያስ 53:2-3። ክርስቶስ እንደ አዳኝነቱ በምድር ላይ ተቀባይነትን አላገኘም። ሆኖም ባሕሪው መለኮታዊ ስለነበር በሰማይ ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነትን አግኝቷል። እኛ ደካማ ስጋን የለበስነው እግዚአብሔርን መምሰልን እንማር ዘንድ ስጋ ለብሶ እግዚአብሔርን በባሕሪው ገለጸልን። “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው” ዮሐንስ 1፥18። የክርስቶስ ኑሮ አባቱን መተረክ ነበር። ይህንን የምናምን ሁላችን አንድ ተልዕኮ አለን እሱም በጸጋው ኃይል የክርስቶስን ሕይወት የሚያስታውስ ኑሮን መኖር ነው።

2. ከኃጢያት አዳኙ ኢየሱስ፡ የክርስቶስ መከራ ለማየት ወደ ምድር መምጣት ዓላማ አንድ ነው እሱም ሰዎችን ከኃጢያታቸው ማዳን ነው። "እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ” ማቴዎስ 1፥21። በተከታታይ እንደተመለከትነው ኃጢያት በሰብአዊው ዘር ላይ ውድመትን አስከትሏል። የዚህ ወረርሽኝ ብቸኛው መድሃኒት ደግሞ ክርስቶስ ነው። ከክርስቶስ ውጪ ሆኖ ከኃጢያት ማምለጥ አይቻልም። ከአዳኙ ውጪ ያለ የሕይወት መስመር ሁሉ የጥፋት ጎዳና ነው። ሰፊው የክርስቲያኑ ዓለም የክርስቶስን ተልኮ ከምድራዊ ጥቅም ጋር በማያያዝ አሳስቶ ይተረጉመዋል። ክርስቶስ እስከ መስቀል ሞት ድረስ ራሱን ያዋረደው እኛን በምድራዊ ሕይወታችን ለማበልጸግ፣ በገንዘብም ሃብታምና ዝነኛ ሊያደርገን አይደለም። እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር በረከቶች ቢሆኑም ሰማይ የማያስገቡ ወደ ሰማይም የማይገቡ ምድራዊ መገልገያዎች ናቸው። የክርስቶስ ዓላማ አንድ ነው እርሱም የኃጢያትን ኃይል ማሸነፍ ነው። ከክርስቶስ ድካም ተጠቃሚዎች የምንሆነው በዓላማው ተባብረን በገዛ ራሱ ኃይልና መንገድ ኃጢያትን እየተዋጋን ስንኖር ነው። “እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም” 1ኛ ዮሐንስ 3፥5።

3. ራስን ዝቅ ማድረግ፡ ክርስቶስ እጅግ የተናቀና ዝቅ ያለን ሰው ያነሳ ዘንድ የመጨረሻን ቦታ ያዘ። ከሚስኪን ቤተሰብ ውስጥ በከብቶች በረት እንደ በግ ተወልዶ በአዋራማው የችግረኞች መንደር በሆነው በናዝሬት መንደር በድህነትና ቀለል ባለ ሕይወት አድጎ እንደ በግ ለሞት ተነዳ። ይህ እንከን አልባ ራስን የማዋረድ ሕይወቱ ለደሃው፣ ለተናቀው፣ ለተገፋው፣ ለሚስኪኑ፣ ለተጠላው፣ ለተገለለው፣ ለተራበው፣ ላዘነው፣ ለተጨነቀው፣ የብቸኝነት ስሜት ለሚያጠቃው፣ ለተጎሳቆለው፣ በበሽታ ለሚሰቃየው ታላቅ ተስፋ ነው። እርሱ በዚህ ውስጥ አልፏልና ይህን ሁሉ ስሜት ይረዳል፤ እንዴት መርዳት እንዳለበትም ያውቅበታል። “እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና” ዕብ 2፥18። ስለዚህ ከክርስቶስ በላይ ዝቅታና ጉስቁልና ውስጥ ያለፈ ወይም ስቃይ ላይ ያለ ሰው ስለሌለ ከአዳኙ አገልግሎት ውጪ ሊሆን የሚችል ችግረኛ ሰው የለም። ለሁሉም ለመድረስ እርሱ ብቻውን ሁሉንም ሆኖ አይቷል፤ በድካማችንም ይራራልናል። እኛም መዳንን የምንቀበለው በትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ ነው። ልንኮራበት የሚገባው አንድ ነው እርሱም ክርስቶስ ነው። “ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ” ገላትያ 6፥14።

4. ራስን ባዶ ማድረግ፡ አምላክ የሆነው ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመጣ ራሱን ባዶ አድርጎ ነበር። ይህም እራሱን እንደካደ የሚያስረዳ ነው። "እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ" ፊሊ 2:6-7። ክርስቶስ ከአባቱ ጋር በስልጣንና በመለኮት አንድ ቢሆንም ሰው ሆኖ ሲመጣ መታዘዝንና ጽድቅን ሊያስተምረን የራሱን መለኮታዊ መብት ትቶ ለአባቱ ተገዥ ሆነ። ይህም በመሆኑ ቅር አላለውም! በምርጫው መብቱን ተወ። ራሱን ባዶ በማድረጉም እግዚአብሔር በሰብአዊ ማንነቱ ውስጥ ከበረበት። “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ” ዮሐንስ 1፥14። ፀጋንና እውነትን የተሞላው ራሱን ባዶ አድርጎ አባቱ ላይ ጥገኛ ስለሆነ ነው። ዛሬ ብዙዎቻችን በመንፈሳዊ በረከት የማንሞላው ልባችን ባዶ ስላልሆነና ጽድቅን ስለማይራብ ነው። የሚሞላን ነገር ከንቱ ልማድ እንደሆነ አውቀን ባዶነታችንን ለእርሱ ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን የመንፈሳዊ በረከትን ለመቀበል ፍላጎት ማሳየትና ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/hahmhdvho_s?si=4r_gCdA0DguIEp8v

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Selami nachu wondimoche

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Selam lenante yibza wendmocha

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ጥቂትና መከራ የበዛበት
============================

📖“ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ መከራም ይሞላዋል።”

             — ኢዮብ 14፥1


ዘላለማዊ ሆነን እንኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ሀሳብ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ሞት የማያውቀው ሕይወትን ብቻ አልነበረም የሰጠን። ዘመናችን በሙሉ ፍፁም ሰላም የሞላበት ይሆን ዘንድ ፈጠረን። ነገር ግን የሰው ልጅ ይህንን በረከት በፈቃዱ በመግፋት ኃጢአትን የሙጥኝ አለ። ዘላለማዊነትን በጊዜያዊነት ለወጠ። ሕይወትን በሞት፣ የተስተካከለ የኑሮ ዘይቤን በመከራ ተካ። ይህ ሊታመን የማይችል ነገር ግን የሆነ እውነታ ነው።


ከዚህ በኃላ ሞትና መከራ አንዱ የሰው ልጅ መገለጫ ሆነ። ጥሮና ግሮ መብላት አይኑን አፍጥጦ መጣ። ምድር አሜኬላንና እሾህን ማብቀል ጀመረች። መላ ሰብአዊ ፍጡር የፀሃዩን ሀሩርና የብርዱን ቆፈን ተቋቁሞ ሕይወቱን መምራት ግዴታው ሆነበት።


ኢዮብ በብዙ መከራ ውስጥ በማለፍ ተስተካካይ አይገኝለትም። ሕይወቱን የኃሊት ሲመለከት ማግኘትና ማጣት፣ ደስታና ሀዘን የተፈራረቀበት ሆኖ አገኘው። ከዛም እንዲህ አለ፦ “ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ መከራም ይሞላዋል።” (ኢዮ.14፥1)


ወዳጆቼ፣ ወደድንም ጠላንም ዘመናችን ጥቂት ነው። ይህም ጥቂቱ ዕድሜያችን ብዙ ነገሮች ተራቸውን ጠብቀው ይፈራረቁበታል። ዛሬ ጌታችን በደጅ ቆሞ የልባችንን በሮች እንከፍትለት ዘንድ ያንኳኳል። "አሁን ወጣት ነኝ። ያሻኝን ነገር አድርኔ በዕድሜዬ አመሻሽ ላይ ወደ ጌታ እመጣለሁ" በማለት አንሳት። “፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (2ኛ ቆሮ 6፥2) ልጅነታችንን፣ ወጣትነታችንን፣ ጉልበታችንን፣ ጉብዝናችንን፣ ዕድሜያችንን ዛሬውኑ እንስጠው። እርሱም የክብሩ መጠቀሚያ ያደርገናል።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ የፍቅር ጥሪህ ዛሬም ስላልተለየኝ አከብርሃለሁ። ዕድሜዬን፣ ዘመኔን፣ ጉብዝናዬን ተጠቀምበት። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ከቀትር ይልቅ ሕይወትህ ይበራል
============================

📖“ከቀትር ይልቅ ሕይወትህ ይበራል፤ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል።”

  — ኢዮብ 11፥17


አንድ ወዳጄ እንዲህ ሲል አጫወተኝ። አብሮ አደግ ጓደኛው አንድ የምርምር ማዕከል ስራ በማግኘቱ ከነበረበት ከሀገረ ጣሊያን በመነሳት ብዙም እንኳን ወደ ማያውቀው ሀገር ያቀናል። ስራ ማግኘቱ ቢያስደስተውም ነገር ግን በዛ ያለውን የአየር ሁኔታ ሊወደው አልቻለም። ነጋ ጠባ ዝናብ ነው ሀገሩ። ሕይወቱ ከቤት ወደ ስራ፣ ከስራ ወደ ቤት ሆነበት። ድብርት እላዩ ላይ ቤቱን ሰራበት። የፀሀይ ብርሃን ናፈቀው። ከዛም ለችግሩ መፍትሔ ይሆናል በማለት የፀሃይ ብርሃንን ሊተካ ይችላል ብሎ በማሰብ ተለቅ ያለ መብራት ያስገባል። ከአንፓሉ የሚወጡት የብርሃን ፍንጣቂዎች የፀሃይ ብርሃንን በመጠኑም ቢሆን የተኩለት መሰለ።


የጨለማ ሕይወት ማንም ሊኖረው የማይፈልገው አይነት ሕይወት ነው። ፍክትና ድምቅ ያለን ሕይወት መኖር የሁላችንም መሻትና ናፍቆት ነው። በእውነት ምንም ነገር የማይጋርደውና ጥላ ሆኖ የማያስቀረው የሕይወት ዘይቤ መኖር ያጎጎል።


በእያንዳንዱ እርምጃዎቻችን እግዚአብሔርን ስናስቀድም ከጨለማ ስራ እየተፋታን እንሄዳለን። እርሱ የሕይወታችን ባለቤት እንዲሆን ስንፈቅድለት ብርሃንን ለመያዝ እንዘረጋለን። ጌታን የቤታችን ዋናና ራስ አድርገን ስንሾመው ከሕይወታችን ብርሃን ይፈነጥቃል። “ከቀትር ይልቅ ሕይወትህ ይበራል፤ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል።” (ኢዮ 11፥17) የተባለውም ቃል በሕይወታችን ተፈፃሚ ይሆናል።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ “ከቀትር ይልቅ ሕይወትህ ይበራል፤ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል” በማለት ስለ ተናገርከኝ የተስፋ ቃል አከብርሃለሁ። ሕይወቴን የብርሃን ፍንጣቂ መፍለቂያ ስፍራ አድርገው። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ጌታ እግዝአብሔር ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ውድ የኤ ዋይ የወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

👉 ከሰኞ እስከ እሮብ ባሉት ቀናት ውስጥ እየተለቀቁ ባሉት የጽሑፍ መልዕክቶች ጠቃሚ ትምህርቶችን እናገኛችሁና እየተባረካችሁ እንደሆነ እምነታችን ነው።

👉 በቀጣይም በቴሌግራም ቻናሉ በሳምንቱ በአንዱ ቀን ምሽት ላይ በቀጥታ ስርጭት
ውይይቶችን ለማድረግ አቅደናል። ይህ የሚሆነው በእናንተ በኩል የውይይት ጥቆማዎች ሲደርሱን ይሆናል።

በመሆኑም በተለይ እስካሁን ከተነሱት ትምህርቶች ውስጥ ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል የምትሉትን እንድታሳውቁን ጥሪ እናቀርባለን።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel