aybclub | Unsorted

Telegram-канал aybclub - AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

-

ቃልህ(ሕግህ) ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው። መዝሙረ ዳዊት 119:105

Subscribe to a channel

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ይህ ትንቢታዊ የጊዜ ሠሌዳ የትምህርቱ አጋዥ እንዲሆን የተዘጋጀ ሲሆን በትንቢተ ዳንኤልና በራዕይ የተጻፈውን የ1,260 ቀን ወይም የ42 ወር ወይም የዘመን፣ የዘመናት እና የዘመን እኩሌታ ትንቢታዊ የጊዜ ቀመር በቀላሉ ለመረዳት እንዲያስችል የተዘጋጀ ነው።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/xwzm1Sqbe1w

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/tirYwZzgHw8?si=IviAZFi8o-gDxX51

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል !

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

የዳዊት መጽሐፍ ማብራርያና፣ታርክ pdf እንድትልኩልኝ በጌታ ስም እለምናለሁ

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

🌍 .... ክርስቲያኖች በሰይፍ ስለት ወደቁ፣ ከነሕይወታቸው ተቃጠሉ፤ ለአናብስት ተጣሉ፤ ተሰደዱ፣ የምድር መከራና ሥቃይ ሁሉ ደረሰባቸው፡፡ የክርስቲያኖች ሰማዕት መሆን ወንጌልን እንዳላስቆመው ዲያቢሎስ ሲያውቅ ስልቱን ወደ ሰጥቶ መቀበል ቀየረ፡፡
📌 ይህ የሠይጣን ስልት ምንድር ነበር ?

https://youtu.be/u7R_hxpLJMw

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

በሆፕ ቲቪ ላይ የተነገረው 2ኛው የሰንበት ትምህርት የጥናት መምሪያ ይህ ነው።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ስምህን የሚያውቁ
============================

📖“ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።”

— መዝሙር 9፥10


አንድ በዕድሜ ለጋ የሆነ ልጅ ቅርቡ ወደ ሆነ ሱቅ ጎራ በማለት የሱቁን ባለቤት ስልክ ያስደውለው ዘንድ ይጠይቀዋል። ሰውዬውም እሺታውን በመስጠት ስልኩን ያቀብለዋል። ይህም ልጅ የስልኩን እጄታ በአንድ እጁ በመያዝ፣ በሌላኛው እጁ ደግሞ ቁጥሮችን በመፃፍ መደወል ይጀምራል። ከዛም "ሄሎ!" የሚል ድምፅ ይሰማል። እርሱም "ጤና ይስጥልኝ የእኔ እመቤት፣ አከሌ እባላለሁና በጊቢዎት ያለውን የአትክልት ስፍራ ላፀዳልዎት፣ አትክልቶችንም ልንከባከብልዎት እፈልጋለሁ" ይላቸዋል። ሴቲዬዋም፣ "ይቅርታ የእኔ ልጅ እኔ አሁን ላይ አትክልተኛ አለኝ። ስለዚህ ሌላ አትክልተኛ አልፈልግም" ይሉታል። ልጁም "እኔ በጣም ጎበዝ አትክልተኛ ስለሆንኩ እኔን ይቅጠሩኝ" አላቸው። ሴቲዬዋም በፊት ካሉት ጋር ተመሳሳይ ምላሽ ይሰጡታል። ታዲያ ይህ ነገር ያልበገረው ልጅ እንዲህ የሚልን ግብዣ ያቀርብላቸዋል፦ "ግድ የለዎትም አሁን ላለው አትክልተኛ ይከፍሉት ከነበረው ክፍያ በግማሽ እሰራለሁ" አላቸው። እሳቸውም "አሁን ያለው አትክልተኛ በጣም ጎበዝ ስለሆነ ከስራው ላሰናብተው አልችልም" አሉት። ልጁም አመስግኖ ስልኩ ተዘጋ።


ይህንን ሁሉ የስልክ ልውውጥ ሲሰማ የነበረው ባለ ሱቅ ልጄ ለስራ ያለህን ፍቅር አደንቃለሁ። እኔ የአትክልት ስፍራ ስላለኝ እኔ ጋር መስራት ትችላለህ አለው። ልጁም ይቅርታ ጌታዬ እኔ እንኳን ስራ አለኝ። አልችልም አለው። ቅድም በስልክ ስሜን ቀይሬ ሳወራቸው የነበሩት ሴትዮ አሰሪዬ ናቸው። እንደው ስራዬን ወደውታል ወይስ አልወደዱትም የሚለውን ነገር ላጣራ ፈልጌ ነው አላቸው። ይህ ልጅ በስራው ታታሪ ስለነበር በአሰሪዋ ዘንድ መልካም ስም ነበረው።


ስም ማንነትን የመግለጥ አቅም አለው። ሰዎች የእኛን ድርጊት በማየት ስምን ይሰጡናል። በስራችን ጎበዞችና ጠንካሮች ከሆንን ስማችን ከዚህ የተለየ አይሆንም። በተቃራኒው ደግሞ ስንፍና ቤቱን እላያችን ላይ ከሰራብን መጠሪያችን ከስንፍና ጋር የተያያዘ መሆኑ አይቀሬ ነው።


የእግዚአብሔር ስም ከስሞች ሁሉ በላይ ነው። ለእርሱ የተገቡት ስሞች ባህሪውን አጉልተው ይናገራሉ። ኤልሻዳይ የሚለውን ስሙን ስንጠራ ሁሉን ቻይ መሆኑን እናውጃለን። ኤልሻሎም ስንል ሰላሙን እንመሰክራለን። ኤልሮኢ የሚለውን ስሙን ስንጠራ ዘውትር የሚያየንን እንዳየነው እንናገራለን። አቤኔዘር ስንል እርዳታው ትውስ ይለናል። እነዚህን የእግዚአብሔር ስሞች ለአብነት ያክል አነሳን እንጂ ባህሪውን የሚገልፁ ስሞች በመፅሐፍ ቅድሳችን ውስጥ በብዛት ይገኛሉ። ታዲያ ይህንን የእግዚአብሔር ስም ስናውቀው እምነታችንን በእርሱ ላይ እናፀናለን። መሻታችን እርሱ ብቻ ይሆናል። እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦ “ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።” (መዝ 9፥10)


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ስምህ ከስሞች ሁሉ በላይ ስለሆነ አከብርሃለሁ። ከአንደበቴ ስምህ አይለይ ስል እፀልያለሁ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/LOy4q9lKf64?si=sPEQUoynx-Nupntt

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

May God richly bless you for making this inspirational documentary available...it's also motivating to see the older generation passing the buttons...

Deuteronomy 32.7: "Remember the days of old; consider the years of many generations; ask your father, and he will show you, your elders, and they will tell you."

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/7JPVTMljbmU?si=aBrTefmZorI-N7Eo

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/xYzsbVpdilI?si=uYIYbg9df8F3oQUc

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ስለ ወዳጆቹ በጸለየ ጊዜ
============================

📖“ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔርም ምርኮውን መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ቀድሞ በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው።”

            — ኢዮብ 42፥10


የኢዮብ ወዳጆች ከማፅናናት ይልቅ በቁስሉ ላይ እንጨት በመስደድ ውጋት ሆኑበት። እግዚአብሔርንም ያስከበሩ በመምሰል ቃላቶችን ወደ ኢዮብ ወረወሩ። ነገር ግን ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም። “... እግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን፦ እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል። አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፤ ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ፤ እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና። ቴማናዊውም ኤልፋዝ ሹሐዊውም በልዳዶስ ናዕማታዊውም ሶፋር ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም የኢዮብን ፊት ተቀበለ።” (ኢዮ 42፥7-9)


ኢዮብ በህይወቱ ከባድ ጊዜያት እንኳን ለሌሎች መትረፊያ በረከት ሆነ። ወዳጆቹን በአምላኩ ፊት ይዞ በመቅረብ አስማራቸው። “ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔርም ምርኮውን መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ቀድሞ በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው።” (ቁ 10)


ይህ የኢዮብ ድርጊት የፀሎት ህይወታችንን እንድንፈትሽ ዕድሉን ይሰጠናል። ፀሎታችን በራሳችን አጥር ውስጥ ብቻ የተወሰነ እንዳይሆን ያሳስበናል። የወዳጆቻችን ነገር ግድ ብሎን ስለ እነርሱም በፀሎት እፊቱ ልንቀርብ ያሻናል። ኢዮብ ይህንን ካደረገ በኃላ ነበር በረከት ቤቱን የሞላው። ምን አልባት እስካሁን ድረስ በረከቶቻችንን ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልተቀበልነው ራስ ተኮር የሆነ የፀሎት ልምምድ ስለምንከተል ይሆናል።


🛐 ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ፀሎት ሰሚ አባት ስለሆንክ አከብርሃለሁ። የፀሎት ህይወቴ በአንተ የተቃኘ ይሆን ዘንድ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም
======================================

📖“እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።”

          — ኢዮብ 36፥26


“እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።” (ኢዮ 36፥26) የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በደንብ ያስተዋልኩት አባቴ በጠና ታሞ በነበረ ወቅት ነበር። ይህ ነገር ለምን በአባቴ ላይ ሆነ በማለት ያነባሁባቸው ቀናቶች ነበሩ። እንደ ቤተሰብ የምንይዘውና የምንጨብጠው ነገር በማጣት በዛልንባቸው ጊዜያት ይህንን ሕያው ቃል እግዚአብሔር በልቤ ላይ አስቀመጠ።


አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ላይ እየሆኑ ባሉ ነገሮች እግዚአብሔርን ልንለካው እንነሳለን። ከባድ በተባሉ ሁኔዎች ውስጥ ራሳችንን ስናገኘው "ይህ እንዴት በእኔ ላይ ደረሰ?" በማለት የማያባራ ጥያቄን በእግዚአብሔር ላይ እናነሳለን። በዚህም አናበቃም፤ ትንሽ በሆነው አዕምሯችን ታላቅ የሆነውን እግዚአብሔር ልንመረምር እንዳዳለን።


እግዚአብሔርን የህይወቴ ጌታ አድርጌ ከሾምኩት በኃላ የእኔ ነገር ከእኔ በላይ እርሱን ያስጨንቀዋል። ዓይኖቹ ለአፍታ እንኳን ከእኔ ላይ አይነሱም። ነገሮች መስመር ቢስቱ፣ ሁኔታዎች ግልብጥብጣቸው ቢወጣ፣ ችግሮች ከየስፍራው ተጠራርተው ቢመጡ እግዚአብሔር በማደሪያው አለ። ለዘመናት የገነባሁት ነገር ቢናድ፣ ጤናዬ ቢታወክ፣ ባላሰብኩት ነገር ብጎበኝ እግዚአብሔር በማደሪያው አለ። እርሱ ሁሉን የሚመረምር በማንም ግን የማይመረመር ታላቅ አምላክ ነው።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ህይወቴ በአንተ እጅ ስላለ አከብርሃለሁ። ከነገሮች ሁሉ በላይ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ። በምንም አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ብሆን አንተን መታመንን አስተምረኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Ameeeeeen .....tebareku...

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ሰላም እንዴት ናችሁ.....  ጸጋ ና ህግ  የሚል soft copy ያላችሁ ለኩልኝ

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ይህ የጥናት መምሪያ ትምህርቱን በቀላሉ ለመማርም ይሁን ለማስተማር እንዲረዳ የተዘጋጀ ነው

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

እነዚህ...፣ ክፍል አራት
============================

📖“ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።”

— መዝሙር 15፥4


በከበረው በእግዚአብሔር ድንኳን ውስጥ ማደሪያውን ማድረግ የሚወድድ ሰው ሊኖሩት ስለሚገቡት ባህሪያትና ሊያደርጋቸው ስለሚያስፈልጉ ምግባሮች እያጠናን እንገኛለን። በዛሬው ጥናታችን “ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።” (መዝ 15፥4) የሚለውን እንመለከታለን።


አንደኛ፣ ነውረኛ በፊቱ የተናቀ

ከነውረኞች ጋር በአንድ አይነት ህብረት ልንቀመጥ አይገባም። "ስላንተ እንድነግርህ ከፈለክ ጓደኛህን ንገረኝ" እንደሚባለው በዙሪያችን ያሉት ሰዎች በእኛ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ ያደርጋሉ። ስለዚህ ዙሪያችን ዞር ዞር በማለት እንቃኝ። ከነውረኞችም እንቆጠብ።


ሁለተኛ፣ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር

የክርስቶስ ፍቅር ሲገባን የፍቅር ሰዎች እንሆናለን። ፍቅር እንዲሁ በስሜት ብቻ የሚቀር ሳይሆን በተግባር የሚገለፅ ነው። ተግባር የሌለው ፍቅር በእውነተኛ ፍቅር ሚዛን ላይ ሲለካ ትርጉም አልባ ነው የሚሆነው። ታዲያ እኛም ፍቅራችንን በተግባር ልንገልጥ ያስፈልጋል። ይህንን ልናደርግበት ከምንችለው ነገር አንዱ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ወገኖች በማክበር ነው።


ሶስተኛ፣ ባልንጀራውን የማይከዳ

ሁለት ሰዎችን የሚያስተሳስረው ፍቅር መሆኑ እሙን ነው። ታዲያ ሕይወት ሁልጊዜ በተስተካከለ መንገድ አይሄድምና አንዳንድ ጊዜ መንገጫገጮች ይፈጠራሉ። አንዳችን ለሌሎች ወዳጆቻችንን ዋጋ መክፈል የሚያስፈልግበት ወቅት ሊመጣ ይችላል። ይህ ጊዜ ሲመጣ ታዲያ ከሁኔታው ገሸሽ ማለት ሳይሆን የሚገባን ችግሩን አብሮ መጋፈጥ ይጠበቅብናል። የክህደት በትርን አንስቶ ሌላኛውን ሰው አውላላ ሜዳ ላይ ጥሎ መሄድ የአንድ የክርስቲያን ባህሪይ አይደለም።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ “ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም” ሰው አድርገኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

📌 ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ከ8:30 ጀምሮ
በአቃቂ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ለትምህርቱ እንዲረዳ የተዘጋጀው ይህ አንድ ገፅ የጥናት መምሪያ ትምህርቱን ለመከታተልም ሆነ ለማስጠናት የሚጠቅም ነው።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

አመሰግናለሁ
============================

📖“የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።”

— መዝሙር 13፥6


እስኪ ዞር ብለን የመጣንባቸውን መንገዶች እንመልከት። እንደ ተራራ ገዝፈው እፊታችን ቆመው አላሳልፍ ያሉንን ነገሮች ደረማምሰን ማለፍ የሆነን በማን ነው? በሰው ዘንድ ተስፋ አስቆራጭ በሆኑት ነገሮቻችን ላይ ተስፋን የዘራው እግዚአብሔር አይደለምን? እኛ ራሱ በራሳችን ተስፋ ስንቆርጥ በሁለት እግራችን እንድንቆም አቅምን የሰጠን ከእርሱ ውጪ ማን አለ? የእግዚአብሔር ረዳታትነት አላገኘኝም የሚል ሰው ለቁጥር ይገኝ ይሆን?


ዳዊት በነገሮቹ ሁሉ ላይ ቀኝ እጅ ሆኖ ያበረታውን አምላክ ከቶ አልዘነጋውም። "ረዳቴ" በማለት የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። አንደበቱም ዝማሬን አፈለቀ። “የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።” (መዝ 13፥6)


ዛሬም ይህ አምላክ ከእኛ ጋር ነው። አባቶቻችንን የረዳው ያ ኃያል ክንዱ አሁንም እንደበረታ ነው። ይህ አምላክ ደርሶ ባይረዳንና ባያግዘን ኖሮ መታሰቢያም ባልነበረን ነበር። እስኪ መለስ ብለን ከእግዚአብሔር የተቀበልናቸውን በረከቶቻችንን እንቁጠር። አሁን ላይ ሕይወታችን እንደቀደመው አይደለም። ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል፤ ተለውጠውማል። ክብሩን ሁሉ የሰማይ አምላክ ይውሰድ! ይህንን የእርሱን እርዳታ ስናስተውል ታዲያ እንዲህ በማለት እንናገራለን፦ “የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።”


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ረዳቴ ስለሆንክ እባርክሃለሁ። ለስምህም ቅኔን እቀኛለሁ። አባት ሆይ፣ ባንተ ላይ ደግሞ ማረፍን አስተምረኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

🪐 በሰማይ የጀመረው ታላቁ ተጋድሎ ወደ ምድር ወረደ
🌍 በአዳምና ሔዋን መበደል ሰይጣን የምድር ገዢ ሆነ (ዘፍጥረት 3)
🌒 እግዙአብሔር በዘፍ 3፡15 ተጋድሎው በምድር እንዴት እንደሚቀጥል ተናገረ።
📌 ከዚያስ ?

https://www.youtube.com/watch?v=6XtODg-OA3I

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/ZlgUtT41l4Q?si=2FWJjH2mKjGVtvDM

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

በልቤ ደስታን ጨመርህ
============================

📖“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”

            — መዝሙር 4፥7


በዩኒቨርስቲዎችና በኮሌጆች ተቋማት የምርቃት ጊዜ ሲደርስ መፅሔት ማሰራት የተለመደ ነው። ታዲያ ተመራቂ ተማሪው ለመፅሔት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ከገንዘብ ማዋጣት ጀምሮ በመፅሔቱ ላይ የሚታተመውን ፎቶ ሟሟላት ይጠበቅበታል። መፅሔቱ ሙሉ እንዲሆን እነዚህን ነገሮች ብቻ ማቅረብ በቂ አይደለም። የተወሰኑ ቃላቶችን በፁሁፍ የምናሰፍርበት ትንሽዬ ቦታ በዛ ስፍራ ይዘጋጃል። ብዙዎች ያንን ቦታ ፈጣሪያቸውን ለማመስገን፣ የረዷቸውን ሰዎች ለማጉላት ይጠቀሙበታል። አስታውሳለሁ እኔም ይህንን ስፍራ እንዲህ የሚሉትን ቃላቶች እንዳሰፈርኩበት፦ “በልቤ ደስታን ጨመርህ፤” (መዝ 4፥7)


የእውነተኛ ደስታና ፍሰሃ ባለቤት እግዚአብሔር ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ የሚገኙ የሚመስሉን ደስታዎች ዛሬ ታይቶ ነገ እንደሚጠፋ ጤዛ ነው። ምን አልባት ደስታን ከሰዎች ማግኘት የምንችል ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን እነዛን ሰዎች ካጠገባችን ስናጣቸው ደስታውም አብሮ ይጠፋል። የደስታ ልካችን ደግሞ ገንዘብ፣ ስልጣን፣ ዕውቀት ወዘተ ቁሳዊ ነገር ከሆነ እነዚህ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸውና መክሰማቸው አይቀሬ ነው። ታዲያ በዚህን ጊዜ ከበፊቱ ይልቅ የልብ ስብራት ይገጥመናል።


ዳዊት የእውነተኛ ደስታ ምንጭ እግዚአብሔር እንደሆነ የተረዳ ሰው ነበር። ይህ ስጦታም ከእርሱ ዘንድ ብቻ እንደሚገኝ ስላስተዋለ እንዲህ በማለት ተናገረ፦ “በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።” (መዝ 4፥7) ወዳጆቼ፣ ደስታን ፍለጋ ወደ ተለያዩ ስፍራዎች አንኳትን። ዓለም አለኝ ወደ ምትለው ደስታ በመሮጥ አንባክን። ውስጥን በእውነተኛ ሀሴት ሊሞላ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ በመገንዘብ ወደ እርሱ እንቅረብ። እርሱም ደስታችን ይሆናል።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ የእውነተኛ ደስታ ምንጭ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። በዚህ ፍሰሃ ትባርከኝ ዘንድ ደግሞ እፊትህ በፀሎት እቀርባለሁ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/GbhTCtP4dH8?t=2

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

መጠጊያዬ ነህ
============================

📖“አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።”

             — መዝሙር 3፥3


ዳዊት ይህንን መዝሙር ሲቀኝ በመከራ ውስጥ ሆኖ እንደ ነበር እንዲህ ተብሎ ከተፃፈው መረዳት እንችላለን። “አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው። ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።” (መዝ 3፥1-2) ነገሩን ደግሞ ይበልጥ ከባድና አሳዛኝ የሚያደርገው ለዚህ መከራ ምንጩ የአብራኩ ክፋይ የሆነው አቤሴሎም መሆኑ ነው። በዚህ ጭንቅ ሰዓት ነበር ዳዊት አምላኩን "መጠጊያዬ ነህ" በማለት የጠራው። “አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።” (ቁ 3)


ሕይወት ሁልጊዜ በአንድ አይነት መስመር የሚሄድ አይደለም። በከፍታና በዝቅታ ማለፍ የግድ የሚሆንበት ጊዜ ይኖራል። ጠላት የመከራ በትሩን በመዘርጋት ሊደቁሰን አጋጣሚዎችን ይጠብቃል። አንዳንድ ጊዜ መከራዎች ከሚጠበቁበት ስፍራ ሲመጡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ካላሰብነው ስፍራ ከተፍ ይላሉ።


ዳዊት ይህ የመከራ ማዕበል የተነሳበት ከጠላቶቹ ሳይሆን መከታዬ ብሎ ከሚያስበው ከገዛ ልጁ ነበር። እኛም ዛሬ ምን አልባት በችግር ጊዜ ራሴን ባገኘው መፍትሔ ይሆነኛል ባልነው የቅርብ ሰው ጉድጓድ ተምሶልን ይሆናል። አንስጋ! በመከራ ጊዜ ረዳት፣ በጭንቅ ጊዜ መጠጊያ የሚሆን አምላክ በሰማይ አለ። ከእርሱ እቅፍ ውስጥ ማንም ፈልቅቆ ሊያወጣን አይችልም። እርሱ ማለት የምቾት ቀጠናችንና ዋስትናችን ነው። ታዲያ ይህ አምላክ መጠጊያንችን ብቻ አይደለም። በተጨማሪም ክብራችን ነው።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ መጠጊያዬና ክብሬ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። በተለያዩ ስንክ ሳሮች ሳልፍ አንተን መጠጊያዬ እንዳደርግ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/3jFxbE4gWdI?si=sRYNhLsHiTWYFCaX

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

https://youtu.be/5AA_3QWehd0?si=KRZppaEfoewtTVN6

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ሰላም እንዴት ናችሁ ዘመናት ምኞት PDF ያላችሁ ላኩልኝ ።

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

ሰላም ወገኖች እንደምን ቆያችሁ፤ ከዚህ በፊት የጀመርነውን ለኃጢያት የተሰጠውን መፍትሔ ቀጥለን እናያለን። በዚህ ክፍል የክርስቶስ ምድራዊ ተልዕኮ አጀማመርን እንመልከት።

“ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ” ማቴዎስ 3፥16። የክርስቶስ ጥምቀት ከሰማይ በተሰማው የአባቱ ማረጋገጫና መንፈስ ቅዱስን በመቀበል የመሲህ ተልዕኮውን እንዲጀምር ያደረገው ታላቅ ክስተት ነበር።

ከጥምቀቱ በኋላ የክርስቶስ ሕይወት የተመራው ወደ ፈተና ነበር። "ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ" ማቴ 4:1-2።

የነጠረ ሕይወት ይኖረው ዘንድ ክርስቶስ በምድረበዳ እንዲፈተን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር። ክርስቶስ ስጋን በመላበሱ ከነበረበት ዕለታዊ የስጋ ፈተና በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የሚፈተንበትን ጊዜ ተጋፈጠ።

"ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው። ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው። ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፦ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው" ማቴ 4:3-11።

አዳኛችን በአንዲት ኃጢያት ቢወድቅ የሰው ዘር የመዳን ተስፋ ሙሉ ለሙሉ እንደሚከሽፍ የሚያውቀው ጠላት በደካማ ጎኑ የተጠና ፈተናን አመጣበት። ክርስቶስ ተጋፍጦ ካሸነፋቸው ፈተናዎች የሚከተሉትን እንማራለን።

1. አምኖና ወስኖ በጥምቀት ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ ነፍስ ላይ ጠላት ወዲያውኑ ፈተናውን ያበዛል። ክርስቶስ ከጥምቀት በኋላ ወዲያው ከባድ ፈተና እንደገጠመው እንዲሁ ተከታዮቹም ይኸው ክፉ ጠላት ለሚያመጣቸው ፈተናዎች የተጋለጡ ናቸው። ሆኖም ከአቅም በላይ እንድንፈተን የማይፈቅደው አምላካችን ብቻችንን አይተወንም። ታማኝነታችንንና ቁርጠኛነታችንን አይቶ ውጤቱን ይቆጣጠርልናል። በፈተና ውስጥም አንጥሮ ያወጣናል።

2. ክርስቶስ የተፈተነው የመጀመሪያ ፈተና ከሁሉም በላይ ከባድ ነበር። አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሳይበላ ሳይጠጣ ለቆየው ክርስቶስ ምግብ እጅግ አስፈላጊ በሆነበት ሁኔታ መለኮታዊነቱን ተጠቅሞ ለራሱ ተዓምር እንዲያደርግ ግፊት ቀረበበት። ክርስቶስ ይህንን ፈተና በድል መወጣቱ ለሰብዓዊ ዘር በሙሉ ታላቅ የምስራች ነው። ምክንያቱም ክርስቶስ ዲያቢሎስን ተጋፍጦ ያሸነፈው አዳምና ሔዋን በዚሁ ጠላት ተፈትነው በወደቁበት በምግብ ፍላጎት (appetite) ጉዳይ ነው። አዳም ፍሬውን በልቶ ከሳተ በኋላ የሰው ዘር በዚህ ጉዳይ በቀላሉ የሚሸነፍ ደካማ ሆኗል። ለምሳሌ ኤሳው ብኩርናውን በምግብ ለወጠ፣ የሰዶማውያን አንዱ ኃጢያት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የምግብ ፍላጎት ነበር (ሕዝ 16:49)፣ እስራኤላውያን የግብጽን ስጋ ናፍቀው አለቀሱ ከበሉም በኋላ ብዙዎች ሞቱ (ዘሁ 11)። የክርስቶስ ድል የስጋ ስሜትን ባለማመንና የምግብ አምሮትን በመቆጣጠር በአመጋገብ ዙሪያ መሻትን መግዛት የሚያስችለን ዋስትናችን ነው።

3. "የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ" የሚለው ተደጋጋሚ የዲያቢሎስ አነጋገር ክርስቶስ በክርክርና በእልህ ተነሳስቶ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለማሳየት ድንጋዩን ዳቦ እንዲያደርግ ወይም ራሱን እንዲወረውር ለማድረግ የተጠቀመበት ስልት ነበር። ክርስቶስ ግን ቢፈተንም በአባቱ ላይ ጥርጣሬ አልነበረውም፤ ለዲያቢሎስም የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ ማረጋገጫ መስጠት አላስፈለገውም። መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ እንደሚነግረን እያወቀ የሚጠይቅና የሚከራከር ሰው ምላሽ አይገባውም፤ ምላሻችን ከእንደዚህ አይነት ሰው መሸሽ መሆን አለበት (1ጢሞ 6:3-5)። ምክንያቱም የዚህ ዓይነት ምልልስ እኛን ለማጥመድና ስሜታዊ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታችንን ለማዳከም የሚደረግ የጠላት ፈተና ነው እንጂ እውነትን ለማወቅ የሚደረግ ጥረት አይደለም። ስለዚህ "እንደነዚህ ካሉት ራቅ!"

4. ጠላት የእግዚአብሔርን ቃል ያውቃል፤ ሆኖም ዕውቀቱን የሚጠቀምበት ሰዎችን ለማሳት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ባልሆነ ይዘትና ቦታ እየጠቀሱ ትርጉሙን እያጣመሙ ለራሳቸው ፍላጎት እንዲገጥም በማድረግና ሌሎችን በማሳት የሚሰማሩ የዚሁ ጠላት መሳሪያዎች ናቸው። ቃሉ መቀደሻና መዳኛ ነው እንጂ ማሳቻና መጥፊያ አይደለም። ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር ቃል ሊገልጽልን የሚገባው እግዚአብሔር እራሱና አገልጋዮቹ ናቸው! “ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም” ኢሳ 8፥20። ቃሉን በማዛባት ብዙዎችን አስቷል። በክርስትና ስም ያሉ ነገር ግን ቃሉ ከሚለው ውጪ ሰው ሰራሽ ስርዓትን የሚከተሉ ሰዎች ክርስቶስ የገጠመውን ዓይነት ፈተና ተፈትነው ባለማወቅ፣ ባለማስተዋል ወይም በቸልተኝነት የተረቱ ናቸው። የተበረዘ ወንጌል ከጥፋት የማያድን የተመረዘ ወንጌል ነው! የተመረዘውን ቃል መለየት የምንችለው እውነተኛውን አስተምሮ ስናውቅ ብቻ ነው።

5. ከሶስተኛው ፈተና እንደምንረዳው ሰይጣን ዓለማዊ ቁሶችንና ክብርን መስጠት ይችላል! በጥንቆላና ሟርት በአጭር ጊዜ ኃብት ላይ ኃብት የሚያካብቱ በርካታ ሰዎች መኖራቸው የዚህ ማሳያ ነው። ሰይጣን ኃብትና ዝናን በመስጠት አሁንም ብዙዎችን ያስታል። ቃሉ እንደሚነግረን "ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነው" 1ጢሞ 6:10። ገንዘብ ከመገልገያነት ባለፈ በሕይወት ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ሲሰጠው መጨረሻው እኛን ዲያቢሎስ ጋር ማድረስ ነው። ገንዘብና አምሮቱ እንዳይሰለጥንብን መጠንቀቅ ይኖርብናል። “የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ” ሉቃስ 12፥15።

6. የሰይጣንን የማሳቻ መንገዶች በአራት ልንከፍላቸው እንችላለን። ማታለል/መሸወድ (ሔዋን እውነት መስሏት እንድትበላ እንዳደረጋት)፣ ማባበል/ማጓጓት (ስህተት መሆኑን እያወቀ ከሚስቱ ጋር መሞትን እንደመረጠው እንደ አዳም)፣ አዕምሮን ማስጨነቅ (ክስና ተስፋ ማስቆረጥ)፣ አካላዊ ጉዳት (ማጎሳቆል እንደ እዮብ) ናቸው። “እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል” ማቴ 10፥22። ሁሉንም ተጋፍጦ ሁሉንም ድል ያደረገልን አዳኝ አለን። ስለዚህ በፈተናችን ሊረዳን ይችላል። “እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና” ዕብ 2፥18።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!

Читать полностью…

AY Bible Club( የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር)

Amen+++... እግዚአብሔር ይርዳን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel