ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21
"እንዳይነጋ እንዳይመሽ ብልኃት ተገኝቶ፣
ጊዜውን መከልከል እንዳይቻል ከቶ፤
እንዲሁም ባ'ለም ላይ አለ ብዙ ነገር፣
በዚያም ቢሉት በዚህ፥ መኾኑ የማይቀር።"
(በክቡር ከበደ ሚካኤል)
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
/channel/azop78
/channel/azop78
ይህችን የጠፋች የኦስካር ትውልድ መጽሐፍ በተደጋጋሚ የጠየቃችኹኝ አንድ ኮፒ ተገኝታለች
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
እጅግ ተፈላጊዋ የሀመር መጽሔት ልዩ እትም እጃችን ላይ ነው።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
ለካስ ሰው መሆን እዳ ነው
ለካስ ሰውነት ባዳ ነው
እህል ውሃ ቢያደነድነው
ሲያጣ ሲነጣ በድን ነው፡፡
የኛስ ይሁን እንዳሻው ለእጥፍ ፈተና ከፈጠርከን
ለፍታችሁ ተፍታችሁ ኑ ካልከን
ለቀብር አፈር ከወጠንከን
ግን ፡- ግን ብላቴኖች ምን በደሉ
የማንን አደራ በልተው የማነን አማና አጎደሉ
እንብርታቸው ያላረረ
አጥንታቸው ያልከረረ
ሰማይ በቀል እንደቋጠረ
እጣቸውን እየመጠረ
መንገዳቸውን በእሾህ እያጠረ
እንደ ደራሽ ውሃ አግተልትሎ
በራብ አኮርማጅ ተልትሎ
ከእናት እቅፍ በግፍ ነጥቆ
ሲሰልፍብን ባጭር ታጥቆ
እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ!
አያ ሙሌ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
የሩሲያ ትርጉም መጻሕፍት
ሠላም ቤተሰቦች አንድ ወዳጄ በውስጥ መስመር "እባክህ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ የሩሲያ መጻሕፍት ርዕሳቸውን፣ ደራሲዎቹን፣ ተርጓሚዎቹን እና አታሚዎቹን መረጃው ብትልክልኝ?" ብሎ ጠየቀኝ።
የቃልም፣ የጽሑፍም መረጃዎች ሳሰባስብ ቆይቼ ለጊዜው ከዚህ በታች ያሉትን አግኝቻለሁና ወዳጆቼ የጎደለውን በማሟላትና የተረሱትን በማስታወስ ተባበሩኝ።
1. ሳይላክ የቀረ ደብዳቤ-ካሣ ገ/ሕይወት ፕሮግሬስ፣
2. ጸሐይቱን ለማየት በቃሁ-ኖዳር ዱምባድዜ-ካሣ ገ/ሕይወት ፕሮግሬስ፣
3. እናት-ማክሲም ጎርኪ ግዕዛን የማነ ፕሮግሬስ፣
4. ባለውሻዋ እመቤት-ግርማ ተፈራ እና ካሣ ገ/ሕይወት ፕሮግሬስ።
5. የአንድ ሰው ዕጣ-በሚኻኤል ሾኾሎቭ፣ አድማሱ ባድማ፣ የውጭ ቋንቋዎች አሳታሚ።
6. ልጅነት-ማክሲም ጎርኪ በካፋ ኃይለየሱስ ፕሮግሬስ፣
7. ከቤተሰብ ወደ ኅብረተሰብ-ማክሲም ጎርኪ በካፋ ኃይለየሱስ ፕሮግሬስ፣
8. ዩኒቨርሰቲዎቼ-ማክሲም ጎርኪ ካሣ ገ/ሕይወት ፕሮግሬስ፣
9. ደሃ ሰዎች*ብርሃናማ ሌሊቶች ፣ ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ፣ ካሣ ገ/ሕይወት ፕሮግሬስ፣
10. ወንጀልና ቅጣት፣ ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ፣ ካሣ ገ/ሕይወት እና ፋንቱ ሳህሌ፣ፕሮግሬስ፣
11.ታራስ ቡልባ፣ ኒኮላይ ጎጎል፣ ፍስሓ አጥላው ወ/ዮሐንስ ፕሮግሬስ፣
12. አና ካሬኒና፣ ሊዮ ቶልስቶይ፣ ቴዎድርስ ጸጋዬ።
13. ካፖርቱ-ኒኮላይ ጎጎል፣ መስፍን አለማየሁ።
14. የዘመናችን ሰው-ሚኻኤል ሌርሞንቶቭ፣ ደስታ ታደሰ፣ ፕሮግሬስ።
15.እኛና የእኛ ተራሮች-ስብስብ ሥራዎች፣ ካሣ ገ/ሕይወት ፕሮግሬስ፣
16. የካራማዞቭ ወንድማማቾች፣ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ፣ መክብብ አበበ።
17. እንደ ብረት ጠንካራ 1 እና 2፣ ኒኮላይ ኦስትሮቭስኪ፣ ሲሜን አዶልፎቪች።
18. የሩሲያ ሰዎች ጠባይ
19. አጎቴ ቫኒያ-አንቷን ቼኾቭ
20. የአሌክሳንደር ፑሽኪን ግጥሞች- አያልነህ ሙላቱ።
21. እንደሰው በምድር እንደ ዓሣ በባሕር፣ አሌክሣንደር ቤላየቭ፣በካፋ ኃይለየሱስ ፕሮግሬስ፣
22.የካፒቴኑ ሴት ልጅ፣ አሌክሣንደር ፑሽኪን፣ መለሰ ጥላሁን።
23. የነበረው እንዳልነበረ እና እናት መሬት- ቺንግዝ አይትማቶቭ።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
/channel/azop78
/channel/azop78
-ይኼንን ቃለ ምልልስ ሁሌም የማንበብ ስሜት አለኝ። ሳነበውም ልቤ ደስ በሚል ምኒልካዊ ሙቀት ሲዳሰስ ይሰማኛል።
ለሰንበታችኹ ይኾን ዘንድ እነኾ
#ጂጂ_እና_ዓድዋ
(የጂጂ የቀድሞ "ማኔጀርና" ጓደኛዋ እንዲሁም ቤዝ ጊታሪስት ቶማሥ ጎበና Thomas Gobena (Tommy T) ጋር ካደረግኩት ቆይታ )
እኔ፦ "ቶሚ፤ አድዋ ይገርመኛል። ሲሠራ ታስታውሳለህ??"
ቶማሥ፦ "ታስታውሳለህ?? እንዲያውም ይገርመኛል፤ ልንገርህ። ፕሮፌሠር ኃይሌ ገሪማ አድዋ የተሠኘውን ፊልማቸውን በአሜሪካ እንደነገ ሊያስመርቁ እንደዛሬ የኔን ባንድ ተከራዩ። Instrument ብቻ ነበር ልንጫወት የታሰበው። ከዚያ ፕሮፌሠር ሀይሌ መጡና "እስቲ፤ የፊልሙን ምርቃት የሚከፍት ዘፋኝም ፈልግ። ብቻ ሴት ኢትዮጵያዊት ትሁን" አሉኝ። እሺ ብዬ ማንን እንደምጋብዝ እያሰብኩ ቤቴ ሄድኩና ከጓደኞቼ ጋር ልምምድ ጀመርን። ማታ 2 ሰዓት ተኩል ገደማ ጂጂ ሁለት ሺፍት ሥራዋን ጨርሳ ወደ ቤቷ ልትሄድ ስትል ጎራ አለች። "አንቺ፤ ፕሮፌሠር ሀይሌ ዘፋኝ ይፈልጋሉ። ለምን አንቺ አትሠሪም?!" አልኳት። "መጣሁ!" ብላ እየሮጠች ወጣች። 4 ሠዓት ሲል መጣች። "አዲስ ሙዚቃ ሠርቻለሁ። እናጥናው።" አለች። "አንቺ ልጅ አብደሻል እንዴ?! አይሆንም!" አልኳት።
እኔ፦ ለምን???
ቶማሥ፦ እንዴ ፕሮፌሠር ሀይሌ እኮ ናቸው። በጣም ነው የምንፈራቸው። የማይሆን ሥራ ይዘን ገብተን አበላሽተን ቢገሉንስ?? ከዚያ "ዝምብለሽ "እማማ ኢትዮጵያ" የሚለውን ዝፈኝ እንጂ አይሆንም" አልኳት። ተስማማች። በማግስቱ ጠዋት መድረክ ላይ ወጥተን ልትዘፍን ስትል በምልክት "ፀጥ በሉ!" አለችን። በጣም ብዙ ህዝብ ነበር። ትላልቅ እንግዶች ከፊት ነበሩ። እኛ መጫወት አቆምን።
"ዓድዋ"ን ያለ ሙዚቃ በድምጿ ብቻ መዝፈን ጀመረች።
"የሠው ልጅ ክቡር..........." ስትል ክው አልኩ። ሰምተነው አናውቅም። በ 1 ሰዓት ተኩል የተደረሠ ዘፈን ነው።
ከዚያ ከሀይሌ ጋር የተቀመጡ ነጭ ምሁራን እንባቸውን ያወርዱታል። ቋንቋው አይገባቸውም። ጂጂ ራሷ ደንግጣ እየዘፈነች ወደኔ ዞራ "ምንድነው?!" የሚል አስተያየት አየችኝ። በምልክት "ቀጥይ!" አልኳት። ስትጨርስ ቤቱ በእግሩ ቆመ። ፕሮፌሠር መጡና "እቺን ጉደኛ መተዋወቅ እፈልጋለሁ" ብለው ተዋወቋት። ያልመጣ ሠው አልነበረም። ከነሱ መሀል የ 7 ግራሚ አሸናፊዋና የ Bob Marley ልጅ ሚስት Lauren Hill ነበረች። እሷም ከትላልቅ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሮች ጋር አገናኘቻት። ከአመታት በኋላ አልበም ሆኖ ወጣ። ይኼ ነው ታሪኩ።"
#ሠናይ ሰንበትን ተመኘሁላችሁ!
ጅጅን ስለምንወዳት !!! ከወይን ዘለላ ፔጅ ያገኘውት ነው
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
"ነፋሱን መክተል መሰጠት አንጂ መባክን አይሆንም። ደግሞም እራስህን እንጂ ነፋሱን አታሳድደውም! እራስህን እንጂ ነፋሱን
ልትለውጠው አትችልም።በእውነታው ሊያጠምቅህ! ለያላምድህ ያባብልሃል እንጂ ነፋስን ስታሳድደ ወይ ልትከተለው የማይሆን ነገር ነው።የምዕራብ ነፋስ ሲጠነሰስ ከባህር ልብ ከትልቁ እንደማዕበል ይጀምራል።ነፋሱ ንጹህ፣ፍጹም ፣ የማያድስ(nourisher) እና የሚገነድስ(dastroyer)፣የማምነው ረቂቀ ልሳን፣ እስትንፋስ፣አሻራ ነው.... ደግም የሆነ ጊዜ ከዚያ ወዲያ ነፋስን መከተል ወይ ማሳደድ አስፈላጊ የማይሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ነፋስ አወኩት የሞትልበት ገጽ፣ ያዝኩት የትለው አካል የለውምና።ይህ ሲገባክ ያኔ መማረክህ፣ ሁለመናህ ማስረከብ
{surrender)ይከተላል። ራስህን ካስረከብክ በኋላ ነፋሱን፣ሁለንተናን ትሆናለህ እንጂ ቀትረሰብህ አይቀጥልም።
ሆኖም ነፋስን መከተል እንዲሁ ቀላል አይምሰልህ። አንድ ቀን የሆነ ቀን የሆነ ቦታ አጥንቶችህ ወላልቀው አስኪገኘ ድረስ የነፋሱን አዙሪት ተከትለህ ወደ ተራሮች ጫፍ መውጣት ወይም ወደ ወንዞች ጥልቅ መውረድ ሊኖርበህ ይችላል። ነፋስን መታዘዝ ባህሪው እሱ ነው። እናም አንድ ቀን የሆነ ቀን እእንደ ሉባንጃ ጭስ አሊያም እንደ ብናኝ አመድ የትም አስኪበትንህ ፣ ከሁሉም ጋር አስኪቀይጥህ ለነፋሱ አፍኝ እና
መዳፍ መታዘዝን ትታዘዛለህ....
“መኖርን ለማስቀጠል ካሻህ መረሳት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡” (There are things that have to be forgotten if you want to go on living) እዚህም ላይ የማስታወስ ብቻ ሳይሆን የመርሳት ጥበብን መማር ሊጠበቅብን ነው ማለት ነው፡፡ የሥነ ልቦና ኮርስ 101 (መተዋወቂያ) የማስታወስ ብቃትን እንዴት ማዳበር እንደሚቻልና እራሱ የማስታወስ ባህርይ ምን እንደሚመስል የሚተነትን ምዕራፍ አለው፡፡ አእምሮ መረጃዎችን የሚደረድረውና ሲያስፈልግ የሚያቀርበው ነገሮችን ዘርፍ፣ ባህሪና አዝማሚያ እያለ በመደልደል ነው አሉ፡፡ መቅደስ አና ቅድስት የተባሉ ስሞችን በባህሪና በድምፅ ዘርፍ ስለሚመሳሰሉ አእምሯችን መመዝገብና ሲያስፈልግ ፋይሉን አውጥቶ ማቅረብ የሚቸገረው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ የነገሮችን አምታቺ ባህሪያት አራግፎ ለአእምሮ ማቅረብ ለማስታወስ አይነተኛ መፍትሄ ነው፡፡
ለምሳሌ ስልክ ቁጥሮችን በጥሬው ለመያዝ ከመሞከር፣ ከሁነቶች ጋር አዛምዶ ማጥናት ከተወለድንበት ቀን ጋር፣ ከአውቶቡስ ቁጥር ጋር ከፔሬዲክ ቴብል ንጥረ ነገሮች ቁጥር ጋር … የስልክ ቁጥሩን ማዳበል፡፡
ማስታወስ መቻል ለመርሳት ከመቻል በላይ ቀላል ነገር ይመስላል፡፡ ከባድ ጉዳት ያላቸውን መጥፎ ገጠመኞች መርሳት እንጂ የሚያስፈልገንን መዘንጋት አይደለም፡፡ ውጥንቅጡ የአእምሮ ጉዳይ ውስጥ ገብተን ጨዋታችንን ውጥንቅጥ ውስጥ ከማስገባታችን በፊት ወደ ታላላቆቹ ዝንጋዜ ነገር እናምራ፡፡ አንድ እንጥቀስ፡፡ አሜሪካዊው ተመራማሪ ቶማስ አልኤዲሰን፤
ኤዲሰን እረጅም ጊዜውን የሚያሳልፈው የምርምር ክፍል ውስጥ ነው፡፡ ግድ ካልሆነት አይወጣም፡፡ ማርጋሬት ካውሲን የፃፈችው የህይወት ታሪክ መፅሐፍ (The man who heighted )ውስጥ አንድ ጊዜ የረሳውን ነገር ትተርካለች፡-
ለሚሰራቸው ስራዎች የመንግስት ግብር ለመክፈል ወደ ከተማው ማዘጋጃ ቤት ሄዶ ነው አሉ፡፡ የግብር መክፈያ ጊዜው ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታልና ወረፋው ረጅም ነበር፡፡ ኤዲሰን ተሰለፈ፡፡ ቢሰለፍም የሚያውጠነጥነው ስለ ሳይንስ ምርምሩ ነውና ከቀልቡ አልነበረም፡፡ ወረፋው ደርሶት ግብር ተቀባዩ መስኮት ጋ ሲደርስ አንድ ጥያቄ ቀረበለት፡-
‹‹ሥም የሚል?››
‹‹የፈጣሪ ያለህ ዘንግቼዋለሁ፡፡ ኧረ ስሜን እረስቼዋለሁ›› አለ፡፡ አሰብ፡፡ አውጠነጠነ፡፡ ስሙ ጠፋው፡፡
‹‹ሥምም ከጠፋዎ ምንም ማድረግ አልችልም፤ ዘወር ይበሉ›› ብሎ ቀጣዩን ግብር ከፋይ ተካ፡፡
ኤዲሰን ግብር ሳይከፍል ዛሬን ካሳለፈ ለነገ ቅጣቱ ብዙ ብር ነውና ጨነቀው፡፡ ከግቢው በመውጣት ሰዎች እያስቆመ፤ ‹‹ታውቁኛላችሁ? ሥሜ ማው?›› እያለ መጠየቅ ጀመረ፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ አንድ የሚያውቀው ሰው አግኝቶ ስሙን ነገረው፡፡ እ-ፎ-ይ!!
ለመሆኑ እናንተ ሥሙ የጠፋው ሰው መንገድ ላይ ቢያጋጥማችሁ ምን ይሰማችኋል? ቂል፣ የአእምሮ ህመምተኛ? አጭበርባሪ?... ወይስ ምን? መጠርጠር ደግ ነው፤ እርሱ የአምፖልን መብራት ጨምሮ ከአንድ ሺህ በላይ ሳይንሳዊ በረከት ጀባ ያለን ቶማስ አልቫ ኤዲሰን ሊሆን ይችላልና፡፡
በፈረንጆች 2015 ላይ ፡ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ፡ የቅዳሜ እትሙ እንዳስነበበው
____
''ለሰባት ዓመታት፣ እንደ ተራ አገልጋይ በመሀከላችን ጠብ ርግፍ ብሎ አገለገለን - ርግት ያለ፣ ንቁ፣ ፈፅሞ ሰው የማያስቀይም፣ ትሁት፣ ባልተፈለገበት ቦታ ጥልቅ የማይል እና የገዳሙን ባልደረቦች የትኛዋንም ትዕዛዝ ለመፈፀም ወደ ኋላ የማይል ነበር፡፡ ሲሄድ በዓየር ላይ የሚንሳፈፍ ነው የሚመስለው፡፡ አንዲትም ቃል ከአፉ አትወጣም፡፡
ቃላት ሳይወጡት በአርምሞ ለመክረም ቃል ሳይገባ አልቀረም ብለን ደምድመናል፡፡ መጀመሪያ አካባቢ የተወሰንነው በሹፈት ልንጎነትለው ሞከረን፡፡ እሱ ግን ሹፈት እና ስላቃችንን ከምድር ባልሆነ ርጋታ አሳለፈው፤ ይህም አርምሞውን እንድናከብርለት አስገደደን፡፡
“በሚያባብል ርግት ያለ መንፈሱ ሐሴት ከሚያደርጉት ሰባቱ ባልደረቦች በተቃራኒ፣ ርጋታውና አርምሞው እረፍት ይነሳኝ፣ ያበሳጨኝ ጀመር፡፡ ልረብሸው ብዙ ጣርኩ፤ ጥረቴ ሁሉ ግን ከንቱ ሆነ፡፡
ሥሜ ብሎ የነገረን ሚርዳድ ነው፡፡ በሌላ ቢጠሩት አይሰማም፡፡ ይህን ብቻ ነው ስለእሱ የምናውቅ፡፡ ቢሆንም ግን … የመንፈሱ ግዝፈት በአንዳች ኃይሉ ለሁላችንም ይሰማል፡፡ ለዚህም ነው … እሱ ወደ ማደሪያው ካልገባ በቀር ምን ወሳኝ ጉዳይ ቢገጥመን አናወራም፡፡''
የመጽሐፉ ርዕስ:- መጽሐፈ ሚርዳድ
ተርጓሚ:- ግሩም ተበጀ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
/ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር፤/
ልጄ ሆይ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡
ልጄ ሆይ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ ሆነ ግን፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም፡
ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ፣ ሲያዝኑ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል፡፡
ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል?
የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡
ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን፤ የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡
ልጄ ሆይ፤ ሰው ምንም ብልህና አዋቂ ቢሆን በራሱ ሥራ ብቻ ራሱን ችሎ እንደማይኖር ዕወቅ:: ነገር ግን ሁሉም በየሥራው ጸንቶ እርስ በርሱ በሥራ ይፈላለጋል:: ስለዚህ ሰውን ሁሉ አክብረህ ኑር እንጂ ሰውን አትናቅ ሥራውንም አትንቀፍ::
ልጄ ሆይ: አካልህና ልብስህ ዘወትር ንጹህ ይሁን:: እጅህን ለሥራ: ዓይንህን ለማየት: ጆሮህን ለመስማት ፈጣኖች አድርግ:: አፍህን ግን በጠንካራ ልጓም ለጉመህ ያዝ:: አረጋገጥህ በዝግታ አነጋገርህ በለዘብታ ይሁን:: ያልነገሩህን አትስማ: ያልስጡህን አትቀበል: ያልጠየቁህን አትመልስ:: ሽቅርቅር አትሁን: ንብረትህ ተጠቅላላ ይሁን: ምግብና መጠጥህ በልክ ሆኖ ያው የጠዳና የጣፈጠ ይሁን::
ልጄ ሆይ ፈቃደ ሥላሴ፤ አሳብ አታብዛ፤ ወደ ፊትም ምን ነገር ይመጣ ይሆን ብለህ አትጨነቅ፤ ምንም አሳብና ጭንቀት ብታበዛ የሚሆን ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወደ ፊትም እሾማለሁ፤ እሸለማለሁ፤ ብለህ በአሳብህ ደስ አይበልህ፡፡ ለሰውም አትናገር፤ ምናልባት ከተናገርህ በኋላ ሳታገኘው የቀረህ እንደ ሆነ ታላቅ ኀፍረት ይሆንብሃልና፡፡ ወደ ፊት የሚያናድድ ሥራ አትሥራ፡፡ በገዛ እጅህ በሠራኸውና ባለፈው ሥራ አትናደድ፡፡ ልጄ ሆይ፤ ጌታ ለመሆን ትፈልግ እንደ ሆነ ጌትነት ማለት ያለ አሳብና ያለ ጭንቀት መኖር ነው፡፡ አሳብህም ሁሉ ከሞትህ በኋላ ወዲያኛው ዓለም ስለሚሆነው ስለ ነፍስህ ነገር ይሁን እንጂ በዚህ ዓለም በሥጋህ ስለሚሆነው ነገር እጅግ አትጨነቅ፡፡
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏🙏
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቍጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል። ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
#ከባዶላይ መዝገን
#የካህሊል አማልክት
እና
#ሰልስቱ ጣኦታት በሚሉ ሥራዎች የምናውቀው ያዕቆብ ብርሃኑ
#የመሻገር ሲቃ ከአውሎ ነፋስ ጋር መደነስ በሚል ታላቅ መጽሐፍ በቅርብ ቀን ልንቀበለው ዝግጅታችንን ጨርሰናል !!!!
ውድ አንባቢያን ዝግጁ !????
ሳምንት ቅዳሜ ጠብቁን !!!!
በቃ ራሳችሁን ሁኑ እንጂ ስለ ዓለም በትንሹም እንኳን ግድ አይስጣችሁ።ከዚያ በኋላ በልባችሁ ውስጥ አስደናቂ የመዝናናት እና ጥልቅ የሆነ የሰላም ስሜት ይሰማችኋል።
የዜን ሰዎች [ዋናው ፊታችሁ] ብለው የሚጠሩት ይህንኑ ነው። ውጥረቶች፣
ልታይ ልታይ ባይነት፣ ግብዝነት የሌለበት እንዲሁም እንዴት አይነት ባህሪይ ሊኖራችሁ እንደሚገባ የሚደነግጉ የስነ-ምግባር ደንብ ተብዬዎች የሌለበት
ዘና ያለ ሁኔታም ነው።
#ኦሾ
#ካህሊል_ጂብራን
ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ! በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ?
በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ? እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ? ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?
በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም።
ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት።
በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት። መሪዎች ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት።
አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት።
ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት።
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
/channel/azop78
/channel/azop78
ለልጆችዎ እጅግ አስፈላጊ የተረቶች ስብስብ መጽሐፍ በመደብራችን ይገኛል።
የተዎዳጁ የኤዞፕ ተረቶች
ምርጥ ምርጥ ተረቶችን አካቷል
ብዙዎች እጅ ገብቷል
ሁለተኛ እትም ልንገባ ትንሽ ኮፒዎች ብቻ ቀርተውና!!
ያልደራችሑ አንባቢያን ባሉበትም እንልክልዎታለን !!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
/channel/azop78
/channel/azop78
.......በአንድ ውብ ቀን የሃሳብ ጅረት አዕምሮዬን ሲወጥረው የከተማዋን ጠርዝ ይዤ ፍርስራሹ ብቻ በቀረ አንድ የተዘነጋ ቤት በራፍ አለፍኩ፡፡
በፍርስራሹ ውስጥ አንድ ውሻ በቆሻሻውና በአመዱ ላይ ተኝቶ አየሁ፡፡ ቆዳው ቆሳስሏል፣ የተጉዳ አካሉን ህመም ሰቅዞታል። የምትጠልቀውን ፀሃይ ደጋግመው የሚመለከቱት አይኖቹ ሃፍረት፣ ተስፋ መቁረጥና ስቃይ ይነበብባቸዋል፡፡
የእንስሶችን ቋንቋ ባውቅና ሃዘኔን ልገልፅለት ብችል ብዪ እየተመኘሁ በቀስታ ተጠጋሁት። ወደ እሱ መቅረቤ ግን አስፈራውና በተልፈሰፈሱ እግሮቹ ለመነሳት እንዲሞክር አደረገው፡፡ መልሶ እየወደቀ ቁጣና ልመና በተቀላቀለበት አስተያየት ዞሮ ተመለከተኝ፡፡ አስተያየቱ ከወንድ ንግግር የጠራ፣ ከሴት እንባ የቀደመ ነበር፡፡ እንዲህ ያለኝ
መሰለኝ:
«ሰውዬ ፣ በአንተ ጭካኔ እና ክፋት ሳቢያ ብዙ ስቃይ አይቻለሁ ...
«ጉዳት ከሚያደርስብኝ እግርህ ርቄ እዚህ ከትሜያለሁ፣ አፈርና አመድ ከሰው ልጅ ልብ ይልቅ ቅን ናቸውና፣ እነዚህ ፍርስራሾች ከሰው ነፍስ የላቀ ስቃይ የለባቸውምና፡፡ ሂድልኝ፣ ህግና ፍትህ ከሌለበት ዓለም የመጣህ አንተ ...
«የአዳምን ዘር በእምነት እና በክብር ያገለገልኩ የስቃይ ቋት ፍጥረት ነኝ፡፡ የሰውን ልጅ ጠዋትና ማታ በመጠበቅ ታማኝ ጓደኛው ነበርኩ፡፡ ከአጠገቤ ሲለይ አዝኛለሁ፣ ዳግመኛ ሲመለስ በደስታ ተቀብዬዋለሁ፡፡ ከሰሃኑ በሚረግፈው ፍርፋሪ ጠግቤያለሁ፣ ከጥርሶቹ በሚወድቀው አጥንት ተደስቻለሁ፡፡ ነገር ግን ዕድሜዩ ሲገፋና በታመምኩ ጊዜ ከቤቱ አባርሮ ለምህረት የለሾቹ የመንገድ ልጆች ወረወረኝ
«የአዳም ልጅ ሆይ፣ በእኔ እና ዕድሜ በተጫናቸው ዘመዶችህ መሀል አንድነት ይታየኛል። በአፍላ ዕድሜያቸው ለሃገራቸው ተዋግተው በኋላ ላይ አፈሯን የሚገፉ አሉ፡፡ አሁን ግን የህይወታቸው ክረምት ደርሶ እርባና የለሽ ተብለው ወደ ጎን ተገልለዋል ...
«በእኔ ዕድል እና ልጃገረጅ ሳለች የወጣት ወንዶችን ልብ በምታቀልጥ ሴት መሃልም አንድነት ይታየኛል፡ በኋላ ላይም እናት እንደመሆኗ ህይወቷን በሙሉ ለልጆቿ ትሰዋለች። አሁን ግን እድሜዋ ገፍቶ ተረስታለች፡ ተገፍታለች፡፡
እንዴት ጨካኝ ነህ! የአዳም ልጅ! እንዴት ጨካኝ ነህ!!»
ዲዳው እንስሳ ሊነግረኝ የፈለገውን ልቤ ተረዳችው፡፡
✍ካህሊል ጂብራን
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
/channel/azop78
/channel/azop78
" የዓለም መጥፊያዋ"
ደረሰ ይሉናል ዓለም ማለፊያዋ
ዋ ! የሰው ነገር ዋ !
ጊዜው መቼ ገና
መቼ ደረሰና ,
ሰው ነው በገዛ እጁ የራሱ መፍረሻ
ሌላ ነገር ሲሻ ,
አይበቃኝም ብሎ ሲሰስት ሲሻማ
የሌሎቹን ዓለም ሲናጠቅ ሲቀማ :
ይፈጥራል ጦርነት . . .
ይጠዛጠዛሉ ዓለማት ካለማት
ከኮከብ ጨረቃ ከጨረቃ መሬት
ያቶሚኩ ርችት . . . ይላካል ይመጣል
የክዋክብት መስመር ጉዞአቸው ይናጋል ::
ተጋጭቶ እየሄደ አንዱ ክበብ ካንዱ
ዓለሞች ሲወርዱ . . .
ዓለሞች ሲፈርሱ . . . ዓለሞች ሲናዱ ,
እልፊት የሚመጣው :
ወዮ !
ያን ጊዜ ነው ::
( ገብረ ክርስቶስ ደስታ )
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
ለወደመ እድል አለን !!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
Small Habits Make a Big Difference
When we watch people make small choices, like ordering a salad at lunch instead of a burger, the difference of a few hundred calories doesn’t seem to matter much. At the moment, that’s true. These small decisions don’t matter all that much. However, as days turn to weeks and weeks to months and months to years, those tiny repeatable choices compound. Consider another example, saving a little money right now won’t make you a millionaire tomorrow. But starting to save today makes it more likely you will become a millionaire in the future.
Atomic Habits
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
#ደግሜ_የምሥራች_ልበላችሁ
በደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ የተደረሰው መጽሐፍ ነገ በየ መጽሐፍት መደብሮች እንደሚበተን ስሰማ ኃሴት አደረግሁ...
ምክንያቱም ልጁን በቀደምት ሥራዎቹ ዓውቀዋለሁ... አንብቢያለኹ "ከባዶ ላይ መዝገን" የሞራል ኂስ ጥልቀቱ እንዳለ ሆኖ፣ ቋንቋ በዛ ልክ ሻፍዳ ከምትሽኮረመምላቸው ጥቂት ከያኒዎች አንዱ ያዕቆብ እንደሆነ እንዴት ልንክድ እንችላለን... ቃላቶቹ እርጥ ሳር እርጥ ሳር፣ አደይ አበባ አደይ አበባ ነው የሚሸቱት...
ይሄ ሰው ስለ ኪነት ስድስት ዓመታትን በጎዳና ዳር ቆፈን በሚያዥ የሌሊት ነፋስ እየተላሰ፣ በሀሩሯ በምትቆጋ ፀሐይ እየተርመጠመጠ፣ ወቅቶች ከነጸባያቸው ተፈራርቀውበታል... እና ከዚህ ሰው ነፍስ አንዳች የጥበብ ጩልቅታ ልናገኝ አንችልም ብላችሁ ታስባላችሁ...? እንደዛ ከአሰባችሁ እናንተ ጨርሶ ኪነት ዋጋዋን የምትሰፍርበት ቦታ፣ ድንኳኗን የምትዘረጋበት ዐጸድ አልተገለጠላችሁም ማለት ነው....
#ልብ ብላችሁ ስሙኝ፣ ለገና አራት ኪሎ ሥጋ ብቻችሁን በልታችሁ፣ ስድስት ኪሎ ሰገራ ከምትጸዳዱ፣ ግማሽ ኪሎ ብሎና፣ #"የመሻገር ሲቃ"ን ገዝታች ሁ ከወይናችሁ ጋር ተጎንጯት.... #ሌላም ልበላችሁ ከገና ቀጥሎ ጥምቀት አይደለ..? ለዛም በሎሚ ውርወራ ሔዋንህን አትፈልግ... እሱ ተለምዷል... የተለመደ ነገር ደሞ ይሰለቻል አይደል...? እና ምን ማድረግ አለብህ መሰለህ፣ ዓይንህ ለፈቀዳት ልጅ፣ የመሻገር ሲቃን ገዝተህ ስጣት፣ እርግጠኛ ነኝ፣ ልጅቱ ከሌሎች ይልቅ ለአንተ ትሻፍዳለች... እውነቴን ነው... ለአንተ ይጠቅማል ስላልኩ ነው እንጅ ይሄንን ሁሉ መጻፌ፣ በዓለም ላይ ከሚሰለቹኝ ነገሮች አንዱ fb ላይ መቸክቸክ ነው...ሐሳብ አጥቼ አይደለም መጻፍ ስለሚደክመኝ ነው.... እና ይሄ ሁሉ ድካም ለእናንተ ነውና ከነገ ጀምረህ ሽልንግህን እየቋጠርክ በአቅራቢያህ ወደሚገኝ መጽሐፍት መደብር ጎራ እያል የመሻገር ሲቃን እየመነዘርክ በየ ቤትህ...
በዛውም እጅግ መነበብ እያለባቸው ግን ያልተነበቡ መጽሐፎች መካከል ጥቂት ልመርቅህ፣ እግረ መንገድህን ቤየ ነው....
#ስለ_ትናንሽ_አለላዎች ( ዮናስ አ.)
#ሀገር_ያጣ_ሞት (ሔኖክ በቀለ ለማ)
#ትዝታዬን_ለአንቺ_ትዝታሽን_ለእኔ (እሱባለው አበራ ንጉሴ )
#መሐረቤን_ያያችሁ (ሙሉጌታ አለባቸው)
#የደመና_ሳቆች ( ደረጄ በላይ ነህ)
#የሚመጣው_አልፏል (ዳዊት ጸጋዬ)
#ቤተልሔም (በኃይሉ ሙሉጌታ)
#አሌፍ_ቤት ( ወንድሙ ገዳ)
#ፑታምፑልቶ
#እና የራሱ የደራሲው #ከባዶ_ላይ_መዝገን (ያዕቆብ ብርሃኑ) ከዚህ ውጭ ለሸክምም ስለሚከብድህ፣ የዛሬ ግብዣዬን ስትጨርስ፣ ጠይቀኝ እጠቁምኃለሁ... በእኔና በአንተ ዘመን፣ የገለባ ግብስብስ እየተባልን ብንታማም፣ አብጥርጥሮ ላየ ብዙ እሳት እሳት የላሱ ደራሲንም እያፈራን ነው
ኧረ ወዳጄ ደከመኝ
በል ቴሌግራሜን ጆይን አድርግ!!
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
መርሳት፤ አንዱ ጥበብ፣ ሌላው ጀሃነብ!
__
(Written by ዓለማየሁ ገላጋይ)
_
❨...ለመዳረስ ያሰብኩባትን ሃያት ሬጀንሲ ረስቼ በማለፍ ራሴን መገናኛ ሳገኝ አለቅጥ ስለተለጠጠው ዝንጉነቴ ተሸማቀቅሁኝ። ይኼ ጦማር ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞም እንደገለጠኝ....❩
____
ስለመርሳት ሳስብ ሁለት ሰዎች አስታውሳለሁ፤ አንዱ… በመርሳት የታወቀ፣ ወይም የመርሳት ተሰጥኦ ያለው አለበለዚያም የመርሳት ችግር ያለበት አንድ ልጅ አለ፡፡ ለመርሳት ፣ የሚያሳየው ፍጥነት ከዕለት ወደ ዕለት ጨምሮ ወደ መጨረሻ ገደማ እያወራም መዘንጋት ጀመረ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡-
አንድ የጎረቤት ሰው መጥቶ ‹‹ቹቹ፤ እናትህ አለች?›› ሲለው
‹‹የለችም›› ብሎ ይመልሳል
‹‹የት ሄደች?›› የሚል ጥያቄ ሲደገምለት እረስቶ
‹‹ማን?›› ብሎ መልሶ ይጠይቃል
‹‹እናትህ?›› ሲሉት
‹‹እራስህ እናትን›› ሲል ለፀብ ይጋበዛል፡፡
…ሌላኛውን የተዋወቅሁት ነፍሱን ይማርና በአያሻረው (አስማማው ኃይሉ) ወግ ነው፡፡ አሜሪካ ውስጥ ለሠላሳ አምስት አመታት የኖረ የኢህአሠ (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ሠራዊት) ታጋይ ነው፡፡ በመጨረሻ ዕድሜው ላይ ሁሉን በመርሳት የአእምሮ ህመም (Alzheimer) ተያዘ፡፡ ዘመድ፣ አዝማድ ብቻ ሳይሆን ቋንቋ ሁሉ ጠፋው የአፍ መፍቺያ ቋንቋ ተራ ቱማታ በሆነበት ወቅት አንድ ቃል ብቻ አልጠፋውም ነበር፤ ያም ቃል የትግል ሥሙ የነበረ ነው፡፡ ‹‹በትግል ስሙ ሲጠሩት ይዞራል›› ብሎ አያሻረው አለቀሰ፡-
በእርግጥም ያስለቅሳል፡፡ ያ የትግል ሥም ምን ትኩረት ቢሰጠው፣ እየትኛው የአንገሉ ጥግ ቢወሽቀው ትውስታን ሁሉ ከሚያጠፋው የአእምሮ ወረርሽኝ ተረፈ? ከበሽታው በላይ የትግል ሥሙ ተአምር አይሆንም? ከበሽታው ባሻገር በዓመታት መግፋት በራሱ ጊዜ ሊጠፋ አይገባውም ነበር?
….. ሰው እራሱ ተአምር ነው፡፡ ትኩረት የማይሠጠው በሰከንዶች ሽራፊ ከአእምሮው ሲያስወግድ፤ አክብዶ ያየውን ደግሞ እንደ መክሊት ላያተርፍበት አእምሮው ውስጥ ቀብሮት ይኖራል፡፡ ከማስታወስ ይልቅ መርሳት እንደ ጉድለት ስለሚታይ፣ የሰው ልጅ የመሳትን ምንጭ ለማግኘት ብዙ ዳክሯል፡፡ የሥነ ልቡና ምሁራን፤ ለምን እንረሳለን? ለተሰኘው አውራ ጥያቄ መንታ ምላሾችን ያቀርባሉ፡፡ አንዱ ሊታወስ የሚባው መረጃ፣ ከቦታው ሲጠፋ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መረጃው ቢኖርም አንቅቶ ለመጠቀም ሲያዳግት ነው ይለሉ፡፡ ነገርየው የቀበሌ መዝገብ ቤት መሰለ እንዴ? ‹‹ፋይልህ ጠፍቷል›› ለካ ተፈጥሯዊ ነው? ስንቀጥል….
….. ስለመርሳት ሳስብ ሌሎች ሁለት ሰዎች ትዝ ይሉኛል፡፡ አንዱ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ በርናንዶ ሾ ነው፡፡ በባቡር ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ እየተጓዘ ነው፡፡ ፊርማታ ላይ ትኬት ተቆጣጣሪው፤ ሾ ወዳለበት ፋርጎ ገብቶ፡-
‹‹ትኬት አውጡ፣ ትኬት›› ሲል ጮኸ፡፡
ሾ ከተመሰጠበት ተናጥቦ ትኬቱን መፈለግ ይጀምራል፡፡ የደረት ኪስ፣ የጎን ኪስ፣ የኋላ ኪስ፣ የውስጥ ኪስ፣ የቦርሳ ኪስ፣ የምስጢር ኪስ፣ የፓንት ኪስ…. ትኬት የለም፡፡ ተበሳጨ፡፡ የፈተሻቸውን ኪሶች መልሶ ፈተሸ፤ አጣው፡፡
ትኬት ተቆጣጣሪው ትኬቱን እንዳጣው ስለገባው፤
‹‹ሚስተር ሾ፣ እርስዎን የማያውቅ ሰው የለም፡፡ ቀስ ብለው ይፈልጉት፤ ካጡትም ግዴለም፤ እርስዎ ያጭበረብራሉ ተብሎ ስለማይታሰብ ይጥፋ!›› አለ፡፡
ሾ ቱግ ብሎ፤ ‹‹ትኬቱን ላንተ የምፈልገው መስሎሃል? ለእኔ ነው፤ የምሄድበት‘ኮ የተፃፈው ትኬቱ ላይ ነው›› ለካ መሄጃው ጠፍቶታል፡፡ ይሄ መርሳት የጭንቀትላት ጉድለት አይሆን እንዴ? የሾን የመርሳት ልክፍት በሁለተኛው በአይዛክ ኒውተን እናፅናው፡፡
የሒሳብ ሊቅ ሰር አይዛክ ኒውተን፤ በሥራ ከሚጠመድበት ክፍል ፊት ለፊት ጠረጴዛ ላይ የሚመገበው ይቀመጥለት ነበር፡፡ እንዳይረበሽ ነው፡፡ በሆነ ሰዓት ወጥቶ ይመገብና ተመልሶ ይገባል፡፡ አንድ ቀን ግን አንድ ወዳጁ በቀጠሮ መጥቶ ሲጠብቀው፣ የምግቡን ጥሪ መቋቋም ተሳነው፡፡ በዚህ ላይ ርቦታል፡፡ ቀርቦ መመገብ ጀመረ እስኪጨርስ ድረስ ኒውተን አልወጣም፡፡ በኋላ ብቅ ሲል ሰሃኑ ባዶ ነው፡፡ እንዲህ አለ፡-
‹‹አይ የኛ ፈላስፎች ነገር! እራት ያልበላሁ መስሎኝ ልበላ መውጣቴ ነበር፡፡ ለካ አቀላጥፌው ኖሯል፡፡ (How absent we philosophers are, I realy thought that I had not dined)
አለማስታወስ የበሽተኞች ወይም የደደቦች አለበለዚያም የልበ-ቢሶች ብቻ እንዳልሆነ በበርናርድ ሾ እና በኒውተን ያረጋገጥነው ጉዳይ ይመስላል፡፡ ታዲያ መርሳት ምንድነው? የማነው? ጉዳት አለው? ጉዳቱ እንዳለ ሆኖ ጥቅምስ? እያልን በጥያቄ መታጠር የሰው ልጅ ሁሉ ባህርይ ነው፡፡ የቼኩ ደራሲ ሚላን ኩንዴራ (Milan Kundera) መርሳት ላይ ያተኮረ አንድ ልቦለድ አለው፡፡ “The book of Laughter and Forgetting” የሚል፡፡ ገፀ-ባህሪዎቹ እንደ ደሴት የተከፋፈሉ ታሪኮችን የሚያስተዳድሩ (እንደ አዳም ረታ) ናቸው፡፡ የአንዱ አንባ ታሪክ ገዢ ሚርክ (Mirek) ማስታወስን የሥልጣንና የበላይነት ምንጭ አድርጎ የሚናገርበት ጥቅስ አለው፡፡ (The struggle of man against power is the struggle of memory against forgetting) ይላል፡፡ ትውስታውን የሚያነቃ የኃይል ባለቤት ከሆነ፣ የማያነቃው የደካማነት ድልድል ውስጥ ይገባል ማለት ነው? እንዲህ ከሆነ በዝንጋኤ ታሪክ የተጥለቀለቀ የህይወት ታሪክ ያላቸው ደራሲዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ የሂሳብ ሊቆች … እንዴት ማስደግደግ ቻሉ?
ጀርመናዊው ፈላስፋ ፍሬዲሪክ ኒች (Friedrich Nietzsche) በመርሳት ላይ የኩንዴራ ተቃራኒ አቋም ያለው ይመስላል፡፡ ነገሮችን ለመርሳት አለመቻል፤ ለመኖር አለመቻል ነው በሚል፡፡ ታሪክን (ታሪክ ማስታወስ አይደል?) የሚያብጠለጥል አንድ መፅሐፍ አዘጋጅቷል- “Disadvantage of History for life” የሚል እዚህ መፅሀፍ ውስጥ እንዲህ የሚል አባባል አለ፡-
“መርሳት ባይኖር መኖር ጨርሶ አዳጋች ይሆን በነበር” (without forgetting it is quite impossible to live at all)
ለሰው ልጅ የማስታወስ ጥበብ ብቻ ሳይሆን የመርሳት ክህሎትም ያስፈልገዋል ማለት ነው፡፡ ነገሮችን በመርሳት የሚቸገሩ እንዳሉ ሁሉ ለመርሳት ባለመቻልም የሚሰቃዩ ሞልተዋል፡፡ በቀላሉ የጦርነት፣ የግርግር የሽብር ሰለባ የሆኑ ግለሰቦችን ማሰብ ይበቃል፡፡ በቀይ ሽብር ዘመን ልጆቸውን ያጡ አንዲት እናት ታሪካቸውን ሰምቻለሁ፡፡ ልጃቸው ከተገደለ ከአርባ ዓመት በላይ ቢያስቆጥርም እናቲቱ አሁንም የልጁን አልጋ እያነጠፉ፣ ቤቱን እየጠረጉና ውኃ በጠርሙስ እየሞሉ ‹‹አትንጫጩ፣ ይተኛበት” ይላሉ አሉ፡፡ ይሄ መርሳት አለመቻል፣ ከእውነታ ሲያቆራርጥ አይደለም? ታዲ ኒች… ይሄን እንጂ ሌላ ምን አለ?
ስቲፈን ካርፔንተር (Stephen Carpenter) የኒቼን ሀሳብ የሚደግፍና የሚያስደግፍ አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ካርፔንተር መዘንጋት ያለባቸውን በብዛት ይመጥናቸዋል እንጂ እንደ ኒቼ በጅምላ አይፈርጅም፡፡ እንዲህ ይላል፡-
“ከሦስት ዓመት በፊት ዕድሜያቸው በሠላሳዎቹ ያሉ ባለጠጋ የሚባሉ ጥንዶች ለምክር ወደ እኔ ይመጣሉ፡፡ ከተጋቡ ገና ሁለት ዓመት አልሞላቸውም፡፡ ከጋብቻ በፊትም ብዙም አይተዋወቁም፡፡ ፍቅር ጠናብን
ብለው በችኮላ ነው ሰርጉንም ያጣደፉት፡፡ ትዳር ጣፋጩንም መራራውንም አጣምራ የያዘች እንቆቅልሽ መሆኗንም አልተረዱትም
ነበር፡ ጫጉላ ሽርሽሩ ሁሌም የሚቀጥል ሳይመስላቸው አልቀረም፡፡
“ሚስትም በተደጋጋሚ የምታነሣው አያዳምጠኝም የሚል ነበር፡፡ ባል በቅሬታዋ ግራ ሳይጋባ አልቀረም፡፡ ስትናገር እንኳን አቋርጫት አላውቅም፡፡ እርሷ ራሷ ምስክር ናት ይላል ደጋግሞ፡፡ ለካስ ነገሩ ሌላ ነው፡፡ “ስሜቴን አይረዳልኝም፤ ሲከፋኝ እንኳ ልብ አይለውም፡፡ ፍላጎቴን ለመረዳት ትዕግሥት የለውም፡፡ እያዋራሁት ዓይኑ ሌላ ቦታ ነው
የሚያዬው፤ ጆሮው ቢሰማም ወደ ልቡ አይዘልቅም' እያለች ሚስት ናዳውን አወረደችው፡፡
“እንዲያውም በሚገርም ሁኔታ ሲከፋኝ ከባለቤቴ ይልቅ ውሻችን መከፋቴን ዐውቃ ከጎኔ ተኮራምታ ትቀመጣለች፡፡ ሳለቅስ ቆይቼ ፊቴ ተለዋውጦ እርሱ ወደ ቤት ሲገባ እንኳ ምን እንደ ሆንኩ ስለማያስተውለው አይጠይቀኝም' አለች
“ያንጊዜ ነው ባል የባነነው፡፡ በእርግጥ አስተዋይ ሰው ነበረ፡፡ በሴትና በወንድ መካከል ያለውን የስሜትና የአረዳድ ልዩነት ለማስረዳት ስሞክር ነው ነገሩ የገባው፡፡ መፍትሔ ባይኖርህ እንኳ ሚስት ችግሯን ስትረዳላት መፍትሔ ያገኘች ያክል ይሰማታል፡፡ ሴት አዛኝ የመሆኗን ያህል ቶሎ መደሰትም ቶሎ መከፋም ያጋጥማታል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ጠባያቸው እንደ ማዕበል ይወጣልም ይወርዳልም፡ ዋናው ቁም ነገሩ ማዳመጥ ማለት በሚስህ ጫማ ራስህን አድርገህ ስሜቷንም፣ ፍላጎቷንም፣ ነገሯንም
በአጽንዖት መከታተልና ለብሶቷ ዕውቅና መስጠቱ ላይ ነው፡፡ ስትከፋ ስታባብላት ኀዘኗን ፈጥና ትረሳዋለች፡፡ ከማንም ይልቅ ተስፋ
የምታደርገው አንተን ነውና የሚሉ ሐሳቦችን ተለዋወጥንና ተሰነባበትን” አለና ዶ/ር ኦባንግ በዝምታ ተዋጠ
📚ትዳር ወግ
✍በትእዛዙ ካሣ
ለንባብ መጎልበት ሁሌም እንተጋለን።
አንዳንድ ሰዎች ይዘነጋሉ፦ እንደ ዘበት
ሕያውነት ያለው ታሪካቸው ከካፍቴሪያ እና ከባልኮኒ እንዲህ ነበር ከሚል ተረት ከፍ ሳይል፤ ወረቀት ሰማይ ላይ ኮከብ ሕይወታቸው ሳይጻፍ፣ ብራና ቀፎ ላይ ማር መሰል ምስላቸው ሳይቀለም፣ ክንፋም ደራሲያን ዘንግተዋቸው፣ ውበት ናፋቂ ሠዓሊያን ቸል ብለዋቸው፤ የአዳማጩን መዳፍ በአንደበት ላይ ማስቀመጥ የሚችል አስገራሚነታቸው፣ በግድየለሽነት ተዘንግቶ አስቀድመው እነርሱ… ቀጥሎም ታሪካቸው ሕይወት መዳፍ ላይ እንደ ቅዠት እይታ ይሆናል፡፡
ተረስቶ ምክንያቱም ይሄ ሕልም መሰል ዓለም ለእንዲህ አይነት እውነተኞች ጆሮው ዝግ ነውና፡፡ ምክንያቱም ይሄ የአመንዝራዎች ዓለም ለእውነተኛ አፍቃሪዎች ዓይኖቹ ክዱን ናቸውና፡፡ ምክንያቱም ይሄ ኤሊ ዓለም ለሕይወት በክንፋሞች መጠን አይደለምና፡፡ የዚህ ዓለም መጠኑ በሌብነቱ አንቱ ለተሰኘ ሰርቆ በማግኘቱም ለሚጨበጨብለት ከድሆች ጉረሮ እና ጉረኖ መንትፎ በገነባው ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ለተመሸገው ነው፡፡ ይህ ዓለም ለእንዲህ አይነቶቹ እንጂ በየጥጋጥጉ ላሉት ለአንዳንዶቹ አይደለም፡፡ በየጥጋጥጉ ጥቂቶች አሉ፡፡
ከብዙዎቹ የተለዩ ፀጥ ያሉ ሲመስለን የሌሉ ሲመስለን ተሰምቶ የማይጠገብ ውብ የሆነ የግላቸውን ዜማ ዘምረው የሄዱ፡፡ ደብዛዛ ሲመስሉን በህይወት ሰማይ ላይ ከብርሃን ይልቅ ያንፀባረቁ
… … በየጥጋጥጉ የሚረሱ የሚዘነጉ አንዳንድ ሰዎችን ድርሰት ሆነው ሳሉ ሳይጻፉ ስለመቅረታቸው እያሰብኩ፡፡ ሕያው ሆነው ሳሉ ከታሪክ በመፋቃቸው ተዘንግተው ማሸለባቸውን እያሰብኩ፡፡
አንዳንድ ሰዎችን እያስታወስኩ.....
✍ኤፍሬም ስዩም
የይሁዳ ድልድይ መጽሐፍ "ፕሮፌሰሩ" ጽሑፍ ላይ የተወሰደ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏🙏
እጅጉን ተወዳጅ ተነባቢነትን አትርፏል በ2_ሳምንታት ውስጥ በድጋሜ ለመታተም በቅቷል
አኹን ደግሞ ትንሽ ቅጅዎች ብቻ ቀርቶናል !!!
በተመጣጣኝ ዋጋ።
አስቼጋሪውን ዘመን የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ያትታል እነሆ በረከት ለወዳጅ ዘመድዎ የሚጋብዙት ድንቅ መጽሐፍ !!!!!!
የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ
/channel/azop78
/channel/azop78
[..] ሜሪ ሐስከል ግን ባደረገችው ነገር ለአፍታም ሳትኩራራ አንዲት ሴት በእህትነት፣በእናትነት፣ በፍቅረኝነት፣ በጓደኝነት፣ በሰውነት ልትሰጠው የምትችለውን ፍቅር ሁሉ ቅንጣት ታህል ሳትሸራርፍ እየለገሰች፣ በሐምራዊ የንቃት ክንፎች እየበረረ እልፍ መሻገሮችን እንዲያስስ አስችላዋለች። በ1914 እ.ኤ.አ ክረምት በጻፈላት ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡-
"The day will come when I shall be able to say, 'I became an artist through Mary Haskell... You have the great gift of understanding, beloved Mary. You are a life-giver, Mary. You are like the Great Spirit, who befriends man not only to share his life, but to add to it. My knowing you is the greatest thing in my days,and nights, a miracle quite outside the natural order of things.>>
‹‹አንድ ቀን የሆነ ቀን ‹‹የጥበብ ሰው የሆንኩት በሜሪ ሀስከል ምክንያት ነው›› የምልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ [...] ውድ ሜሪ አንቺ እጅግ የበዛ ሰዎችን የመረዳት መክሊት የተሰጠሽ ሰው ነሽ፡፡ ሕይወትን አዳይ ነሽ። አንቺ ለመጋራት ሳይሆን ሕይወቱን ለማበልጸግ የሆነን ሰው እንደሚወዳጅ ታላቅ መልዓክ ነሽ፡፡ በኑረት ዘመኔ ከአንቺ ጋር መተዋወቄ ከምልዓተ ዓለሙ ተፈጥሯዊ ስልተ ምትና ስልተ ስሪት ውጪ የሆነ አስደናቂ ተዓምር ሆኖልኛል፡፡››
ሜሪ፣ ካህሊል በኪናዊ ምጥቀቱ ከፍ ባለበትም ይሁን በሞራል በተሽመደመደባቸው ጊዜያት ሁሉ ያለማመንታት ከጎኑ ነበረች።
ተፅዕኗቸው ከሜሪ ጋር ለንጽጽር የሚቀርብ ባይሆንም ሌሎች በርካታ ሴቶች በካህሊል ሕይወት ነበሩ፡፡ እርሱም ስለ ሴቶች እንዲህ ብሏል፡-
"womene open the window of my eyes and the dorrs of my spirit. Had it not been for the woman-mother, woman-sister and woman- friend, I would have been sleeping among those who disturbe the tranquility of the world with thier snoring.
‹‹የዓይኔን መስኮትና የመንፈሴን በሮች የሚከፍቱት ሴቶች ናቸው፡፡ እናቴ፣ እህቴና ጓደኛዬ የምላቸው ሴቶች ድጋፍ ባያደርጉልኝ ኖሮ፣ ዛሬ እኔም የዓለምን ጸጥታና እርጋታ
በማንኮራፋት ድምጽ ከሚረብሹት ሰዎች መካከል ተጋድሜ ሳንጎላጅ እገኝ ነበር፡፡››
አዎ የካህሊል አማልክት ሴቶች ናቸው፡፡ እህቱ፣ እናቱ፣ ሜሪ ሐስክል፣ ሜሪ ዚያዴ... ሌሎችም፡፡ የሁለቱ ጓደኛሞች ደብዳቤዎች የተጠናቀሩበትን የዚህን መጽሐፍ
(Beloved prophet) አርትኦት የሰራችው ቨርጂኒያ ሂሉ (Virginia Hilu) ለዚህ መጽሐፍ በጻፈችው መግቢያ እህቱ ማሪያና እና ሜሪ ሐስክል በካህሊል ዙሪያ ያደሩት የነበረውን የሕይወት ድር በተመለከተ እንዲህ ብላለች።
" both women had simple tastes ,a purity of heart ,and a common Goal: to help Gibran, to enable him to develop his fullest in whatever area he choose. They were united in their belief in his greatness.>>
ራሱ ካህሊል ጅብራን በየካቲት 12 1908 እ.ኤ.አ ለጓደኛው አሜን ጉሬብ ቦስተን ስለመገኘቱ ምክንያት ሲጽፍ የሚከተለውን ሐሳብ አንስቷል፡፡ ‹‹and now since
you have heared my story you will know that my stay in Boston is neither due to my love for this city, nor to my dislike for new York. My being here is due to the presence of a she-angle who is ushering me towards a splendid future and paving for me the path to intellectual and financial success.>>
‹‹እንግዲህ ታሪኬን ሰምተኸዋል፡፡ እናም ቦስተን የመገኘቴ ምሥጢር ለከተማዋ ባለኝ ፍቅርም ሆነ ለኒው ዮርክ ባለኝ ጥላቻ መነሻነት አይደለም፡፡ ይልቁንስ እዚህ የመገኘቴ
ምሥጢር ግሩም ድንቅ ወደ ሆነ የሚያስጎመጅ ነገዬ የምትመራኝ፣ በሐብትም ሆነ በዕውቀት ልቄ እገኝ ዘንድ መንገዴን የምትጠርግልኝ መልዓክ አከል እንስት፣ አዎ ያቺ
ሴት እዚህ በመሆኗ ምክንያት ነው፡፡››
ሜሪ ሐስከል ትቀጥላለች፡፡ እ.ኤ.አ የካቲት 6 1912 ከቦስተን በጻፈችለት ደብዳቤዋ ላይ እንዲህ ትላለች፡-
"God lends me his heart to love you with l asked for it when l found my own was too small, and it really holds you, and leaves you room to grow. I do long to see your beautiful new picture. >>
‹‹እግዚአብሔር አንተን እወድበት ዘንድ ልቡን አውሶኛል፡፡ የእኔዋ ሚጢጢ ሆና አንተን ለመሸከም፣ ለማቀፍ ቢቸግራት እግዜር የእርሱን ይቸረኝ ዘንድ ጠየቅኹት። እናም በሚገባ ከመያዝ አልፋ የምታድግበት ሰፊ ክፍተት ትታልሃለች፡፡ አዲሱን ውብ የስዕል ሥራህን ለማየት ናፍቄያለሁ፡፡››
እውነትም ካህሊል ጅብራን ሁሉንም በመፈለግና ሁሉንም በማጣት ቅዝምዝም መሀል ተሰንቅሮ የጠፋ የቅጽብት ብልጭታ ነበር፡፡ ለሌላኛዋ በአካል አግኝቷት የማያውቅ
በካይሮ ነዋሪ የሆነች ዝነኛ ሊባኖሳዊት ወዳጁ ሜሪ ዚያዴ በጻፈላት አንድ ደብዳቤው ላይ ይህን የማረካ የነፍስ ጥማቱን እንዲህ ገልጾት ነበር፡፡
"l know that a little love does not please me either. niether you nor me are satisfied with little. we both want much. we both want everything. we want perfection."
‹‹ምጥን መውደድ ሊያረካሽ እንደማይችል አውቃለሁ፡፡ እኔም በጥቂት መፈለግ የሚደሰት ሰው አይደለሁም፡፡ እኔም ሆንሁ አንቺ በጥቂቱ የምንረካ ሰዎች አይደለንም፡፡ እንዲያውም ሁሉንም ፈላጊ ነን፡፡ መሻታችን ምልዓቱን፣ ፍጽምናውን ነውና።››
#የካህሊል #አማልክት
#ለመጽሐፉ #የተጻፈ #መግቢያ
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቍጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል። ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
Читать полностью…