መኢሶን
ደርግ
ኢሕአፓ
የዚያ ዘመን ፣ የዚያ ትውልድ መጻሕፍት !!!!
እጃችን ላይ ይገኛሉ።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
@Mesay21
@Mesay21
መጽሐፍ ቅዱሶች እጅግ ኦሪጅናል።
ከጥንቱ እስካሁን ያሉት እጃችን ይገኛሉ።
በተመጣጣኝ ዋጋ እንሸጣለን።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
PEDRO PÁEZ'S HISTORY OF ETHIOPIΑ, 1622
VOLUME I and II
Edited by
ISABEL BOAVIDA, HERVÉ PENNEC AND MANUEL JOÃO RAMOS
Translated by
CHRISTOPHER J. TRIBE
Published by Asigane for
THE HAKLUYT SOCIETY
በጥሩ ዋጋ አግኝተናል።
አለመኖርን ከማንበባችኹ በፊት !?
መጽሐፉን ከማንበባችን በፊት ይህን ቀድማችሁ ብታነቡት እንዴት ደስ ይለኛል መሰላችሁ::
ለምን በሉኝ ?
ለምን? ማለት ጥሩ ነው፡፡
ይህ መጸሐፍ አላማው አድርጎ የተነሳው የተፃፈው የተለመደንና እውነት የሚመስለውን ሁሉ በመጠየቅ ማፍረስን ነው:: በመሆኑም ብዙ የተለመዱና ተገቢ የሆኑ የልብወለድ አጻጻፍ ዘዴዎችን በድፍረት የሚጥስ ሆኖ ታግኙታላችሁ፤ ምክንያቱም በመጽሐፉ ለማሳየት የሞከርኩትን ጠንካራ የሚመስል ሀሳብንና ልምድን የማፍረስ አካሄድ በአጻጻፍ ቴክኒክ ተገዥነት ላይ በመጨነቅ እንዳይበልሽ በመስጋት የተደረገ ቴክኒክ ነው።
አላማው መጠየቅ ነውና በመጽሐፉ ውስጥ በጥያቄ ለተፈተሹት ሀሳቦች መልስ ባታገኙ አይግረማችሁ፡፡ መልሱ ለናንተው የተተወ ነው:: ሰዎች፣ የመልካም አዕምሮ ባለቤት ስለሆንን መጠየቅን ከደፈርን መልሱ ጋር መድረስ አያቅተንም የሚል ጽኑ እምነትን ተገንዘቡ፡፡
አለመኖር
+ ለእንቅልፋሞች መልካም ዜና +
እንቅልፍ ሲበዛ የስንፍና ምልክት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው:: "ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፤ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ" ፤ "የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳል" የሚሉት ጥቅሶች ለዚህ ምስክር ናቸው:: (ምሳ. 20:13 ፤ 23:21)
ሆኖም በእንቅልፋቸው የተጠቀሙ ብዙ ሰዎችም አሉ:: አንቀላፍቶ ሚስቱን ያገኘው አዳም እንዴት ይረሳል? ከኤሳው ጋር ሲታገል የኖረው ያዕቆብ ሲባረክ ያደረውስ በእንቅልፉ አልነበር? ያዕቆብማ ምነው ባልነቃ ያሰኛል:: ሰማይ ድረስ መሰላል ወጥቶ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ያየው በእንቅልፉ ምክንያት ነበር:: በባቢሎን ምርኮ ዘመን የነበረው አቤሜሌክ ደግሞ የእንቅልፋሞች ንጉሥ ቢባል አያንስበትም:: የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየኝ ብሎ ሲጸልይ የነበረው ይህ ሰው በፈጣሪ ፈቃድ ለስድሳ ስድስት ዓመታት ያህል ተኝቶ ነበር:: ከእንቅልፉ ሲነሣም እንቅልፍ ሳይጠግብ እየተበሳጨ ነበር:: ማንቀላፋቱ ግን ብዙ ጉድ ከማየት አዳነው:: (ተረፈ ኤርምያስን ይመልከቱ)
ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የአቤሜሌክን የእንቅልፍ ክብረ ወሰን የሰበሩ ሰባቱ እንቅልፋሞች (The Seven Sleepers) የተሰኙ ቅዱሳንን እንተዋወቅ:: ወቅቱ የሮም ነገሥታት አላውያን የነበሩበት ክርስቲያኖች በግፍ እየተገደሉ የነበረበት ዘመነ ሰማዕታት ነው:: ክርስቲያን መሆን ወንጀል በነበረበት በዚያ ወቅት ክርስቲያኖች ከአንበሳ ጋር እየታገሉ በመስቀል እየተሰቀሉ በሰይፍ እየተቀሉ እየሞቱ የነበረበት ዘመን ነው::
በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት (249-251) ታዲያ በንጉሣዊ ምክር ቤቱ ውስጥ አባል የነበሩ ሰባት ወጣት ልዑላን ድንገት ክርስትናን ተቀብለው "ለጣዖት መሥዋዕት አንሠዋም" ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ ወጣቶቹ ይህን በማድረጋቸው የሚከተለውን ጽኑ ቅጣት ያውቁ ነበረና ፈርተውም በቅርብ ወዳለ አንድ ተራራ ሸሽተው በዋሻ ውስጥ ተደበቁ፡፡
በዚያ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው እያሉ ታዲያ ሰባቱንም እንቅልፍ ይጥላቸዋል፡፡ ንጉሥ ዳክዮስ አሳድዶአቸው ሲመጣ ተኝተው እንዳሉ ያያል:: አውሬው ንጉሥ ሁኔታውን ሲያውቅ እዚያው ዋሻ ውስጥ ይሙቱ ብሎ የዋሻውን መግቢያ በር በግንብ አስደፍኖት ሔደ፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ወጣቶቹ እንቅልፍ ላይ ናቸው::
ከመቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ዓመታት ገደማ ከሆነ በኋላ እነዚህ ወጣቶች ከእንቅልፋቸው ይነቁና የረሃብ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ከእነርሱ አንዱን ወደ ከተማ ሔዶ ምግብ እንዲገዛላቸው ይልኩታል፡፡
ዋሻው የተዘጋበት በር ከዘመን ብዛት ፈርሶ ነበርና የተላከው ወጣት ከዋሻው በቀላሉ ወጥቶ ወደ ከተማ አቀና፡፡ ወደ ከተማ ገብቶ ለሰባቱም የሚበቃቸውን ምግብ አገኘና ሂሳብ ሊከፍል ከኮሮጆው ሳንቲም አወጣ፡፡ ያወጣው ገንዘብ ግን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት መገበያያ የነበረውን ‘የጣዖት አምላኪዎቹን’ ነገሥታት የወርቅ ሳንቲም ነበር፡፡ ሰባቱ ያንቀላፉ ቅዱሳን ከእንቅልፍ የነቁበት ያ ዘመን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ የኤፌሶን ከተማ ሙሉ በሙሉ ክርስቲያናዊት ከተማ በሆነችበት ደግ ዘመን ነበር፡፡
የሰባቱ ወጣቶች ዝና ወዲያው በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያን ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ደረሰ፡፡ ወጣቱ ወደ ዋሻው ከተመለሰ በኋላ ግን ሰባቱም ቅዱሳን ድጋሚ እንቅልፍ ጣላቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሲተኙ ግን እስከወዲያኛው በክብር አሸለቡ፡፡ ለእነዚህ ሰባት ሰማዕታት በሥፍራው ትልቅ ቤተ መቅደስ ተሠርቶላቸዋል፡፡
"እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ" መዝ.3:5
[ደግሞ ይህችን አገኘን ብላችሁ እንዳትተኙ! ለእንቅልፍ ፍቅር ያለው ወዳጅ ካላችሁ ግን Mention በማድረግ ይህን ጽሑፍ አጋሩት! ]
"የኤፌሶን ወንዝ" ገፅ 64 የግርጌ ማስታወሻ ላይ የተወሰደ
ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እድሳት የሚውለው የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ የመጀመሪያ እትም እያለቀ ቀድመው ይሸምቱ
በቅድሚያ አንድ ውለታ ልጠይቃችሁ
ይህንን #ማስታወቂያ #በፌስቡክ ሼር በማድረግ ወይም በራሳችሁ ገጽ በመለጠፍ
#በቲክቶክ እና
#በሌሎችም ሚዲያዎች በማስተዋወቅ አግዙኝ ብሏችኃል ደራሲው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔐ማስታወቂያ!!!
" የጥንታዊ የጎጃም ታሪክ 1ኛ መጽሐፍ" ዳጎስ ያለ #ባለ400 ገጽ ሲሆን በርካታ መጻሕፍት ተነበው ለዚህ መጽሐፍ ማጣቀሻነት የዋሉት #130 መጻሕፍቶችን ተጠቅሟል።
#መጽሐፉን ማንኛውም አንባቢ አንብቦ #የሚደሰትበትና ጥሩ የታሪክ ዕውቀት እንደሚያገኝበት እናምናለን።
የታሪኩ ክፍሎች በማስረጃ_የተረጋገጡ_ናቸው!!!
ስለሆነም፤
"የጎጃም ታሪክ 2ኛ መጽሐፍ" በቅርብ ቀን ታትሞ ይቀርባል። ከዚህ በፊት ግን "ጥንታዊ የጎጃም ታሪክ 1ኛ መጽሐፍን" ማንበብ ታሪኩን ሙሉ ያደርገዋልና።
ከእነዚህ ድርድር መጽሐፍት ውስጥ ምን አይነት ለየት ያለ መጽሐፍ ይታያችኋል።
ካያችኹት እርሱ አንድ ኮፒ ብቻ አንድ ለእናቱ እጃችን ላይ አለን ።
ኤዞፕ መጽሐፍቶች ነን !!!
የምንግዜም ቀደምት መጽሐፍት መገኛ !!
Red land
Black land
Daily life and ancient history
📚 African ethiopan and Egypt history
.......................................
ኤዞፕ መጻሕፍቶች ነን !!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ምንጊዜም እጅግ የተመረጡና ለአንባቢያን ጥቅም ይሰጣሉ ብለን የምናምንባቸውን መጻሕፍት እናስተዋውቃለን !!!
በመሆኑም የቴሌግራም ቻናላችንን jon እያደረጋችሑ የመጻሕፍት መረጃዎቻችን እንዲደርሷችኹ አድርጉ
✍. 📚📚 የንባብ ባህል እንዲሰፋ ከምንም በላይ እንተጋለን
✍ መገኛችን ፣ የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ ምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
✍✍✍✍
/channel/azop78
/channel/azop78
የቲክቶክ ፔጃችን ይቀላቀሉ mesayazop" rel="nofollow">http://tiktok.com/@mesayazop
መልካም የንባብ ጊዜ ተመኘንለዎት !!!!
ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጅ ነው" ብለው አየተከሪከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ:: ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና
"ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው:: አነደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል አውነተኛዋ አናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትወለደው" አለች:: እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ::
ነገሥ. ፫፡፲፮ ፳፻
ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከአግዚአበሔር ጋር ላይሆን ይችላል:: ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል:: በሱስ ውስጥ ተዘፍቀህ ፣እንደ ሶሞሶን በደሊላ እቅፍ ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል:: እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም::
“ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ከእናት በላይ የሚራራልህ ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እሱ ሳይጠራህ ራስህን ጎድተህ እንድትሞት አይፈልግም:: ሕጉን ጠብቀህ ከእርሱ ጋር ባትኖርም መቆየትህ የንስሓ ዕድሜ ነውና መኖርህን ግን ይፈልጋል:: "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፧ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ.፲፲፡፴፪
ኤዞፕ መጻሕፍቶች ነን !!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ምንጊዜም እጅግ የተመረጡና ለአንባቢያን ጥቅም ይሰጣሉ ብለን የምናምንባቸውን መጻሕፍት እናስተዋውቃለን !!!
✍. 📚📚 የንባብ ባህል እንዲሰፋ ከምንም በላይ እንተጋለን
✍ መገኛችን ፣ የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ ምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
✍✍✍✍
/channel/azop78
/channel/azop78
የቲክቶክ ፔጃችን ይቀላቀሉ mesayazop" rel="nofollow">http://tiktok.com/@mesayazop
መልካም የንባብ ጊዜ ተመኘንለዎት !!!!
JOHANN WOLFGANG GOETHE
Bor on 28th August 1749
at Frankfort-on-Main
BIOGRAPHICAL NOTE
lN an old burgher-house, full of books and antiquities, Gocthe had
his fint education ftom his facher, a severe lawyer. His vivacious
yomng mother supplied the fun The boy came under French in-
fluence, through quartered officers and theatre, and later at Leipzig,
where, at sixteen, he went to study Law. He led there a gay Hife,
studied art, fell in love and, in 1768, recurned ill having writtca
Ivey lyris and two small plays.
some Afer convalescence, with deeply religious thought and some tool of the occult, in he Laws, went was to attracted Strasburg, to where in two years he study Medicine, and tured his degree the Germanic, to Shakespeare and Folksong, from lighter to arts to infucnced by Gothic splendour and by the youn g critie Hlerder.
Wich his historic play, Coetz, and a tragic romance, Werther, Gocthe was now hailed as leader of the Germans in their Roman- tic Revolt, Fiction in Werthier was near cnough to an actual love- tiangle to start undying biographical curiosity. Gioethe's Mvrie start poctry was now of the grcatest.
I 1775, Gocthe was invited to Weimar, where Karl August soon made him Minister (Finance; Agriculture; Mincs), and where
love of Frau von Stcin was to Prove main infuence for the next twelve years.
In 1786 Gocthe broke away to Itly, for nearly two years; and He realized SO fally his longing for the calm strength of andiquity hat his whole Hife was changed. Germany scemed to him sall Revole' and immature, He now (1788) lived in semi-retirement.
with Christiane Vulpius (n. 1806), taking less part in public Peministration, except for the State Theatre, which he directed fot over tenty years, He devoted himself to cassical plays (egIphigenie, 17$7; Tasso, 1790), to his F'aust and to scientific work in Evolutionary Botany, Anatomy and Theory of Colour.
The death of Schiller (t8o5) ended nine inspiring yrears of friendship, the time of Gocthe's great Ballads, of Herman and Dorothed, and of the fnishing of his masterpiece Faust, Part One. The rest is quiet, strong work, the later ilhielm Meister, The Divan, Autobiography, Coversations (Eckermann) and Part Two of
Faust, £nished in the poet's last ycars.
Goethe died on 22nd March 1832.
ወጣት ገጣሚ ነው።
አንድ ግጥሙን እንጋብዘወ።
አንኳኩ ይከፈታል።
አንኳኩ ይከፈታል የችግራችሁ ጠር፤
ችጋር ይቀደዳል የጽልመት አንቀጽ በር፡፡
አለኝና ጌታ ብሏልና እየሱስ፣
እየዞርኩ ሳንኳኳ በየቤቱ ሁሉ ሆኖብኝ እንደ ሱስ፡፡
አጣሁኝ አንድ ሰው ከማጀት ከቤቱ፤
እንደ እኔው ሊያንኳኳ ከቤት በመውጣቱ፡
አንኳኩ ይከፈታል።
አንኳኩ ይከፈታል ቃለ ወንጌል ሰምቶ፤
በሌሊት ሲያንኳኳ ጎረቤቴ መጥቶ፣
በቅዠት ሽውታ በሕልም ብቻ እንዳይቀር፥
ሕልም እልም አልኩና በሩ ሲቀረቀር፤
ከፍቼው ተኛሁኝ በሩን ወዲያ ጥዬ፣
እኔም በተራየ
ለማንኳኳት ስሄድ እንዳልዘገይ ብዬ፡፡
ይህ መፅሀፍ የ1928ን የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራና በሰሜን ምእራቡ ግንባር የተፈፀሙትን ድርጊቶች በወፍ በረር ሰንሰማ የነበረውን የወረራውን አስከፊነትና ጭፍጨፋ ለማንም ባልወነ mah የሚተርክ ሲሆን የኢትዮጵያውያንን ጀግንነት የአመራሩን ደካማ የሠሚያ ዝግጅትና ያለተ መባ ትጥቅ በሚገባ ይገልፃል፡፡ ደራሲው የውጭ ዜጋ ቢሆንም ባህላችንን በሚገባ ስለሚያውቅ የብዙ ወራትን ውጊያ፤ መከራና የአለት በአለት ድርጊት በማይሰለችና አጓጊ በሆነ መልኩ ይገልፃል። ተርጓሚዎችም ይህንን የማይረሳ ታሪክ የኢትዮጵያ ህዝብ በአማርኛ እንዲያነበው ባማረ መልኩ በመተርጎማቸው መፅሀፉን በቀላሉ ተነባቢ እንዲሆን አድርገውታል፡፡
መፅሐፍ ከመተርጎም መፅሐፍ መድረስ ይቀላል፡፡ በመጀመሪያ ይህን ጠቃሚ መፅሐፍ ለመተርጎም ጊዜያቸውን መስዋዕት ያደረጉትን ማመስገን እወዳለሁ፡፡ ከምርምር እንፃር መፅሐፉ አጅግ ጠቃ መሆኑን መጠቆም ኣፈልጋለሁ፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ስንወርሰው የቆየነው የሀገራችን ታሪክ ከገዢዎች አንፃር የተፃፈ እየሆነ ትከከለኛውን የህዝብ ተሳትፎ ማወቅ አልተቻለም ነበር፡፡ ይህ መፅሐፍ ከዚህ አኳያ ብዙ ለታሪክ ጥናት የሚጠቅሙ ነጥቦችን አስተላልፎልናል ..
እውነተኛ ታሪክ፤ ሚዛናዊ ፅሁፍ) አገራቸውን ለመጠበቅ ኢትዮጵያውያን የደረሰባቸውን መከራና ግፍ በስዕላዊ ሁኔታ የዘገበ ፅሁፍ፡፡ ሌሎችም ርዕሶች፥ ስለጥሬ ሥጋ አበላል እጀማመር ስለ እያሌው ሞኙ ሰው አማኙ" ታሪካዊ ምክንያት፡ አሰድናቂ የከምባታ ተወላጆች ጀብድና ሌpify መፅሐፉን ማንበብ ጀምረው ማቆም ያልቻሉ ዕንቅልፍ አጥተው ማደራቸውን የመሰከሩለት ዕሁፍ::
ኤዞፕ መጻሕፍቶች ነን!!
እነሆ ምንጊዜም ጠቃሚ መጽሐፍትን እንጠቁማችኋለን።
The ultimate form of power is mastery.
Robert Greene has spent a lifetime studying the laws of power: now he shares the secret path to greatness travelled by history's most powerful people. Each one of us has within us the potential to be a Master if we choose to follow them along a challenging but clear course that is described here for the first time.
እጅግ በጣም ንፁህ
80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
በትልቁ ሳይዝ የታተመው።
በአቡነ ተክለ ሀይማኖት ዘመን የታተመው
እጅግ ንፁህ !!
1980 ዓም
ዶ/ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ፤ ስመ ጥር የታሪክ ሊቅ፤
(ከስሜነህ ጌታነህ)
----------------
ምሁሩ ህይወታቸው ካለፈች 21 አመት ይሆናቸዋል ፤፤ የሰሩት ስራ ግን ዛሬም አለ፤፤ እስቲ ስለ ዶ/ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ ጥቂት ልበል ፤፤
ዶ/ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ ከአባታቸው ከመሪጌታ ሐብለ ሥላሴ ዘውዴና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዲቱ ደስታ ሰኔ 8 ቀን 1921ዓ. ም. አዲስ አበባ ከተማ ነበር የተወለዱት። ባገራችን ሥርአትና ባህል መሰረትም እድሜአቸው ለቀለም ትምህርት በደረሰ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው የልደታ ደብር ፊደል ቆጥረው ዳዊት ደግመዋል። ከዚያም በኋላ ዘመናዊ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ የቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት አጠናቀቁ። በጊዜው ተመርጠው ከቀረቡት የኢትዮጵያ ተማሪዎች አንዱ ሆነው ግሪክ አገር ቆሮንቶስ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እዚያ ከሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት 1941 ዓ. ም. ተላኩ።
ይህንን ትምህርት አጠናቅቀው እዚያው ግሪክ አገር ባለው አቴና ዩኒቨርስቲ ገብተው ከአራት ዓመት በኋላ የባችለር ዲግሪያቸውን በቲዎሎጂ ጥናት ተቀበሉ። ከፍተኛ ትምህርታቸውን በመቀጠል ከ1950እስከ 1952 ዓ. ም. ድረስ በጀርመን አገር በሚገኘው ቦን ዩኒቨርሲቲ በጥንታዊ ታሪክ ምርምር የዶክትሬታቸውን ማዕረግ ተቀበሉ። ከዚያም በኋላ አገራቸውን ለማገልገል ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ 1970 ዓ. ም. ድረስ ለ17 ዓመታት በጊዜው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ (የዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ) የጥንታዊና መካከለኛ ዘመን ስልጣኔና ታሪክ የመጀመሪያ ምሁር ሆነው ሠርተዋል። በተጨማሪም ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቲዎሎጂ አስተማሪ በመሆን አገልግለዋል። አገልግሎታቸውን በመምህርነት ብቻ ሳይወሰኑ ተመራማሪነታቸውንም አጣምሮ በተመለከተ እንደ London University ፤ በአሜሪካንም አገር እንደ Harvard University እና Princeton Univeristy ፤ በጀርመን አገር Heidlberg University፤ እንዲሁም በሆላንድ Lieden University በመሳሰሉት በዓለም በታወቁ ዩኒቨርስቲዎች በፌሎሽፕ እየተመረጡ በተለያየ ጊዜያት በከፍተኛ ደረጃ ልዩ ልዩ ጥናቶችን አከናውነዋል።
ዶ/ር ሥርግው ፤ በትምህርት ዓለም ካሳለፏቸው ዘመናት በላይ በመምህርነትና በምርምር እስከ ሕይወታቸው ፍፃሜ ድረስም ሠርተዋል። በዚህም መሠረት ለተማሪዎችና ለተመራማሪዎች እጅግ ጠቃሚ ሆነው የሚገኙ መጻሕፍትንና ስነጽሁፎችን አዘጋጅተው አሳትመዋል። ከድርሰቶቻቸው ውስጥ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ብቻ ያህል፦
• በእንግሊዘኛ ቋንቋ 1961ዓ. ም. የታተመው Bibliography of Ancient and Medieval Ethiopian History
• በ ፲1963ዓ. ም. የታተመው Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270 የተባሉት ይገኙበታል።
እነኚህ ሁለት መጻሕፍቶች ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ እውቅ በሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና መጻሕፍት ቤቶች ቀርበው የኢትዮጵያን ታሪክ ለሚያጠኑ ሁሉ እንደዋና የምርምር ዶክሜንት (reference document) ሆነው እስከ ዛሬ ድረስ ይገኛሉ፤ ወደፊትም ማገልገላቸውን ይቀጥላሉ። እነዚህም መጻሕፍት ከታተሙ በኋላ ዶ/ር ሥርግው የፕሮፌሰርነት ማዕረግን ለመሸለም በቅተዋል።
ዶ/ር ሥርግው በአማርኛ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበውን በ14 ቅጽ የተተነተነውን ሰፊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን መዝገበ ቃላት በአቀናባሪነት ያዘጋጁ ናቸው። ይህም ሥነጽሁፍ እስከ ዛሬ ድረስ ለቤተ ክህነት ሊቃውንት ተማሪዎችና ትልቅ አገልግሎትን በማበርከት ላይ ይገኛል። ከላይ ከተጠቀሱትም መጻሕፍት በተጨማሪ የኢትዮጵያን ጥንታዊ የሥነጽሁፍ አቀራረጽንና የመጻሕፍት አጠራረዝን የሚገልጽ Bookmaking in Ethiopia የተባለ መጽሐፍ አዘጋጅተው አቅርበዋል።
በመጨረሻም በ1992 ዓ. ም. የአፄ ምንሊክን የሕይወት ታሪክ በተለይ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጪው ዓለም ጋር ኢትዮጵያን እንዴት እንዳገናኝዋት የሚያብራራ ብዙ ኢትዮጵያውን ያደነቁትን ድርሰትም አበርክተዋል። ከነዚህ መጻሕፍት በተጨማሪ ከሃያ ያላነሱ የኢትዮጵያንና የቤተ ክርስቲያንን ጥንታዊ ታሪክ የሚመለከቱ ልዩ ልዩ ሠፊ ስነጽሁፎች በበርካታ የዓለም ቋንቋዎች አዘጋጅተው አቅርበዋል።
በተጨማሪ ዶ/ር ሥርግው ለአገራቸው ካበረከቱአቸው ዋና ሥራዎች አንዱ ሆኖ የሚቆጠረው የኢትዮጵያ ብራና መጻሕፍት ድርጅት መስራች ሆነው ያገለገሉበት ጊዜ ነበር። የዚህ ድርጅት የመጀመሪያ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ከ1962 እስክ 1971 ዓ. ም. በተለያዩ ገዳማትና አድባራት በመዘዋወር በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የጥንት ጽሑፎች በማይክሮፊልም ተቀርፀው ለታሪክና ለሚቀጥሉት ትውልድ እንዲቆዩ ያደረጉ ሰው ናቸው።
ከወይዘሮ ሰላማዊት መኰንን ጋር ሐምሌ 1958 ዓ. ም. በታዕካ ነገስት በዓታ ቤተ ክርስቲያን የሠርግ ስነ ስርዓታቸውን ፈፀሙ። ከዚህም ትዳር አምስት ልጆች ናዖድ፣ ብሌን፣ ፈቃደ ሥላሴ፣ ናብሊስና አሜንን አፍርተዋል። ከእነዚህም ልጆች መካከል የሦስቱን ትዳር ለማየት በቅተው፤ ሦስት የልጅ ልጆች ሆሣዕና፣ ልያና እምነትን ለማቀፍ ችለዋል። ዶ/ር ሥርግው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ታህሣሥ 29ቀን 1995 ዓ. ም. በሚዩኒክ ከተማ በጀርመን አገር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
መጽሐፉ ሁለት ኮፒዎች እጃችን ላይ አለን !!
ከእነዚህ ድርድር መጽሐፍት ውስጥ ምን አይነት ለየት ያለ መጽሐፍ ይታያችኋል።
ካያችኹት እርሱ አንድ ኮፒ ብቻ አንድ ለእናቱ እጃችን ላይ አለን ።
ያልናችኹ መጽሐፍ ይህ እኔና አብዮቱ መጽሐፍ ነው።
ኤዞፕ መጽሐፍቶች ነን !!!
የምንግዜም ቀደምት መጽሐፍት መገኛ !!