azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8863

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ድንቅ አዲስ መጽሐፍ ብቅ ብሏል
ይነበብ !!!

እነሆ ከመጽሐፉ ለቅምሻ !!!







እግዜር ሸማኔ ነው።
ይሸምናል ሕይወት
ይቋጫል ነጠላ
ዳሩ አይመሰገን እጁ በሽመና
አዳውሮ መተርተር ልማዱ ነውና።

ይህ የእንጉርጉሮ ውዳሴ በሲጋራ ሽታ እና በሁካታ ድብልቅ በተሞላው ጠጅ ቤት ውስጥ በአንድ አዝማሪ ልሳን ለመለኮት የቀረበ ዝማሬ ነው፡፡ አዝማሪው  ከሁካታው በላይ ድምፁን ጎላ አድርጎ እያንጎራጎረ፣ መሰንቆውን እየተጫወተ ዓይኑን ባዶው ቦታ ላይ ያንከራትታል፡፡

ግንባሩን ቁጥር እና አገጩን ከፍ አድርጎ ዙሪያውን ይገረምማል፡፡ በጠጅ ቤቱ ውስጥ የተሰባሰቡት በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎች አፍላአፍ ገጥመው ወጋቸውን መጠረቅ ይዘዋል፡፡ ልጅ እግሩ አዝማሪ ከሁሉም በላይ ድምጹን ከፍ አድርጎ ማንጎራሩን ቀጠለ፡፡ ድምፁ በሁሉም አቅጣጫ የሚያስተጋባ ኃይለኛ ቢሆንም የቅዳሜ ከሰዓቱን የጠጅ ቤት ግለት እና ሁካታ ማሸነፍ የሚችል አልነበረም፡፡

ይህ ልጅ እግር አዝማሪ ስሙ ጥጋቡ ይሰኛል፡፡ በጥንቱ ዘመን ነገሥታቱን ከሚያጫውቱ በትውልድ አዝማሪዎች ከሆኑ ቤተሰቦች ይወለዳል፡፡  አዝማሪዎች ለዘመናት ነገሥታቱን እና መሳፍንቱን የሚያገለግሉ፣ ፖለቲካውን የሚሸረድዱ፣ ለድሃው የልቡን በሰምና ወርቅ በዜማ አዋዝተው የሚናገሩ፣ የሰላ ማኅበረሰባዊ ነቀፌታ የሚሰነዝሩ አስቂኝና ቧልተኞች ብቻ ሳይሆኑ የማኅበረሰብ ሐያሲዎች ነበሩ፡፡

ለዘመናት ለዙፋኑ ቅርብ ሆነው አንዳንድ ጊዜም ከዙፋኑ ተጋፊዎች ጎራ ተሰልፈው የአጫዋችነቱን ሚና ወስደው ባህልን በማሳለጥ፣ በማጎልበት ሂደት ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡

ጥጋቡ ከጠጅ ቤት ወደ ጠጅ ቤት ይንከራተታል፡፡ የሰከሩ ደንበኞች ቢጎነትሉም ወይም ለዜማ ጥሪው ትኩረት ቢነፍጉትም በጽናት አዝማሪነቱን ቀጥሎበታል፡፡ መጀመሪያ የጨዋታ ማሟሻ ይሆነው ዘንድ ወዲያውም የአዝማሪነት ችሎታውን ለመግለጥ የእግዚአብሔርን ኃያልነት፣ የሕይወትን ኃላፊ ጠፊነት የሚያመሰጥር ግጥሙን በዘለሰኛ እንጉርጉሮ ለታዳሚዎቹ አቀረበ፡፡

ቀስ በቀስ ስልቱን እየለወጠ ወደ የፍቅር ዝማሬ፣ ጎንደር ከተማንና ጎንደር ያፈራቻቸውን ታላላቅ ሰዎች የሚያወዳድሱ እዚያው በዚያው የተሰናኙ ግጥምና ዜማዎች ወደ ማቅረብ ተሸጋገረ፡፡ ደንበኞች የቱንም ያህል በሚያቀርባቸው ዜማዎች ቢፈነድቁ አዝማሪው ግን ስሜቱን ገዝቶ መጫወቱን ይቀጥላል፡፡
-
-
-
-

(የፒያሳ ቆሌዎች፣ የአዝማሪው እግዚኦታ፣  ገጽ 27-28)

ተጻፈ፣  በኢተሱሺ ካዋሴ (ዶ/ር)


ትርጉም፣ በያዕቆብ ብርሃኑና ዓለማየሁ ታዬ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መርጣቹህ የምታነቧቸው ድንቅ መፅሐፍት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በጉባኤ ቤት መኖር ደስ የሚያሰኘው በየዕለቱ አዲስ አዲስ ሰው ተፈጥሮ ስለሚያድር ነው። በአትክልት ስፍራ ብትኖሩ በየጊዜው ፍሬ የሚሰጡ፣ በመዓዛቸው ልብን የሚመስጡ ዕፀዋትን ልትመለከቱ ትችላላችሁ በዚህ
ከምትደሰቱት በላይ በየዕለቱ እግዚአብሔር ሰው ሲሠራ የምትመለከቱበት ቦታ ስለሆነ በጉባኤ ቤት የመኖርን ጣዕም ብትቀምሱት ደግሞ ከዚህ በላይ በጣም ትወዱታላችሁ። እኛ የተከልነውን፣ ያጠጣነውን እግዚአብሔር ደግሞ ዕለት ዕለት ያሳድግ ነበርና ይኸው ዛሬ ማደጉን የሚያስረዳ ፍሬውን አንዥርግጎ መታየት ከጀመረ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በመገብተ ኦሪት የቀመስነውን ፍሬ ደግመን እንድናጣጥመው ይዞልን ብቅ ብሏል። እንደ አባቶቹ ወምበር ተክሎ ጉባኤ አስፍቶ ያስተማረ በዐውደ ምሕረትም አንደበቱ የሚጣፍጥ የተወደደው ወንድማችን መምህር ምሥጢሩ ታየ ዛሬ በነገረ እግዚአብሔር ላይ ከመምህራን አፍ፣ ከከርሠ መጽሐፍ የሰበሰበዉን ቤተ ክርስቲያን ስለ ነገረ እግዚአብሔር የምትሰብከዉን ቃል በመጽሐፍ ይዞልን በመምጣቱ እያመሰገንሁ ለአንባብያን ደግሞ ቆላ ሳንወርድ ደጋ ሳንወጣ በቆላና በደጋ በሩቅና በቅርብ ያሉ መምህራን ያስተማሩትን በልዩ ልዩ ቋንቋ የተጻፉ መጻሕፍት ለዘመናት በውስጣቸው የተሸከሙትን የሕይወት ቃል ቤታችን ድረስ ስለመታልን በምስጋና ሁሉም እንዲያነበው እጋብዛለሁ። ጣዕም የሕይወት ስንቅ ይዞልን ስለመጣ ሁላችንም እጃችንን ዘርግተን እንድንቀበለው እጠይቃለሁ!

#ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

ይህ “ትምህርተ እግዚአብሔር ዘኦርቶዶክስ” በሚል ርእስ በመ/ር ምስጢሩ ታየ የተዘጋጀው መጽሐፍ፣ ስለ እግዚአብሔር አምላክነትና አሠራር እንዲሁም ስለ ሌሎች መሰል ጉዳዮች ልናውቃቻው የሚገቡ መሠረታ ሐሳቦችን የያዘ መጽሐፍ ነው። የሚያነሣቸውን ሐሳቦችም ኦርቶዶክሳዊ በሆነ ይዘትና ውበት ባለው የሥነ-ጽሑፍ ለዛ የሚያብራራ ጥሩ መጽሐፍ ነው። መ/ር ምስጢሩ ታየ ይህን መጽሐፍ ጽፈው ስላበረከቱልን ከልብ እያመሰገንብ
፣ ይህን መጽሐፍ ብታነቡ ትጠቀሙበታላችሁና ጊዜ ሰጥታችሁ ታነቡት ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ።

ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የአርኖ ሚሼል ዳባዲ ‹‹በኢትዮጵያ ተራሮች ቆይታዬ›› ሶስተኛ ክፍል በገነት አየለ አማካይነት ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ቀርቧል፡፡ ከዚህ ቀደም ሁለቱን ክፍሎች ለአንባቢያን ያቀረበችው ታዋቂ ደራሲና ጋዜጠኛ በዚሁ ጥረቷ በርትታ ሦስተኛውን መጽሐፍ በአሁኑ ህትመት አቅርባልናለች፡፡

በዚህኛው ክፍል ላይ አርኖ ዳባዲ ከበጌምድር እስከ እናርያ ድረስ ያካለለውን ጉዞውን ያስቃኘናል፡፡ በ19ኛው መ/ክ/ዘ አጋማሽ ላይ ወደ መቋጫው እየቀረበ የነበረውን የ‹‹ዘመነ መሳፍንት›› የአውራጃ ገደም የፖለቲካ ስልጣን ሽኩቻ፤ በጎጃም፤ በጌምድር፤ ስሜንና ትግሬ በመሳሰሉት አውራጃ ገዢዎች መካከል የነበረውን እጅግ ተለዋዋጭ የትብብርና የፉክክር ግንኙነት፤ ካየውና ከሰማው ጋር በማስተጋበር ያቀርበዋል፡፡

በነገሥታቱ መናገሻ ጎንደር ከተማ በነበረው ቆይታ የአውራጃ ገዢዎች ጡንቻ ፈርጥሞ፤ ንጉሠ ነገሥቱን አሻንጉሊት አድርገው የነበሩትን የወረሴህ ሥርወ-መንግስት ጉልኃን የአስተዳደር ዘይቤ፤ የቤተ-መንግሥት ዋና ዋና የፖለቲካና ወታደራዊ ሁነቶች እንዲሁም በአስተምህሮ ልዩነት ውስጣዊ አንድነቷ ላልቶ የነበረውን ቤተ-ክርስቲያን ሁኔታ ያስረዳናል፡፡ በቆይታው
የተዋወቃቸውን ግለሰቦችና ማህበረሰቦች ማህበራዊ፤ ኃይማኖታዊ፤ ባህላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ስሪቶች ከጎንደር አማራዎች እስከ ጉዱሩ እና እናርያ ኦሮሞዎች ድረስ ያስቃኘናል፡፡ የወጣ የወረደበትን ተራራና ሸለቆ፤ የዱር አራዊት ዝርያዎች በልዩ ትኩረት መዝግቧቸዋል፡፡

መጽሐፉ በአማርኛ ተተርጉሞ መቅረቡ ለኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪዎችና አንባቢያን ያለው ፋይዳ የጎላ ነው፡፡ ለታሪክ፤ ሥነ-መለኮት፤ አንትሮፖሎጂ፤ ሶሲዮሎጂ እና መሰል ምርምር ዘርፎች ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን ይዟል፡፡ ከዚህ በፊት በፈረንሳይኛ ቋንቋ ክህሎት
ውስንነት የተነሳ ይህንን የሚሼል ዳባዲን ስራ ማንበብ ላልቻሉ ሁሉ መልካም ዜና ነው፡፡ ከትርጉም ባሻገር ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችና እርምት የሚፈልጉ ግድፈቶችን በግርጌ ማስታወሻ ላይ ማብራሪያ በመስጠት የታሪክ እውነታን ለማጥራት ጥረት የተደረገ ሲሆን ይህም ተርጓሚዋን ያስመሰግናታል፡፡ በመጨረሻም በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ መምጣት ዋዜማ የነበረችውንና በፖለቲካና ሀይማኖታዊ ውጥረቶች ውስጥ የከረመችውን ኢትዮጵያን ለመቃኘት የሚፈልግ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ ቀዳማይ የታሪክ ሰነድ ነው።

አውግቸው አማረ (ፒ ኤች ዲ)
የታሪክ መምሕርና ተመራማሪ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

...የአለምን ጣዕም። ከሞት በፊት ያየው አለም፣ በኋላ ከሚመጣው እንደሚሻል ባያውቅ እንደዚህ ህይወቱን የሙጥኝ ባላለ ነበር ብሎ አሰበ።ግን እሱ ነው ህይወቱን የሙጥኝ ያለው ወይንስ ህይወቱ እሱን? ህይወት እንደ እምነት ነው። ሳትፈልገው ይዞህ ሊቆይ አይችልም...።

ግን የአባቱ አደራ አለበት። የአባቱ አደራ ያን ያህል ገዶት ወይንም አጥንታቸው ወግቶት ሳይሆን፤ ከሞት በኋላ በወዲያኛው አለም ሲያገኙት የማይለቁት ስለሚመስለው ነው። ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ ያምናል።
ፅድቅ እና ኩነኔ በሚባል መደብ ግን እንደማይከፈል እርግጠኛ ነው። ሁሉም አንድ ቦታ ላይ ሄደው እንደገና ይከማቻሉ ብሎ ነው የሚያምነው። የሚያምነው የመሰለውን ነው። ያጠፋም ያለማም አንድ ላይ፡፡ ማጥፋት እና ማልማት ራሱ ፖለቲካ ነው ለሱ። ራሱን የቻለ እውነት አይመስለውም፡፡ የፈለገውን ካደረገ ለእሱ በቂው ነው። ማስመሰል እና መሸወድ የቻለ ንፁህ
ነው። የተነቃበት ደግሞ ጥፋተኛ። በሃይል አይደለም የሚመጣውን ጓጉቶ የሚጠባበቀው። ከሚመጣው ይልቅ የጨበጠውን ያምናል። ተስፋ የደሀ ህልም እንደሆነ ነው የሚያምነው። ከህይወት በኋላ ፅድቅ እና ኩነኔ ብሎ
ነገር አይዋጥለትም። በህይወትም መስዋአትነት ለምንም ነገር አይከፍልም፡፡ወቀሳ አልባ እንዳሻው የሚሆንበት ህይወት። ከሞት በኋላም ያው ነገር ይቀጥላል ብሎ ነው የሚጠብቀው። ግን ለዘላለም ያህል ረጅም ጊዜ ሆኖ
ተለጥጦ።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ባይራ ዲጂታል መጽሔት


ልዩ ዕትም



በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም- /channel/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok)  bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ውብ ኦሪጅናል የታሪክ ሰነዶች !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ዐይነ_ልቡና
(ትምህርተ ጽድቅ ቅጽ ኹለት)

ርጡብ ነፋስን ከባሕር፣ ደረቅ ነፋስን ከምድር አስነሥቶ የመብረቅ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማናል፤
ከምድር ዳርቻ ደመናትን የሚያወጣ አምላክ ለዝናም መብረቅን ማምጣት አይሳነውምና። ለዚህም ዘመን እንደ መብረቅ የሚወረወሩ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ የማያስፈሩ ወጣት መምህራንን ባየሁ ቁጥር “ለዝናም ጊዜ መብረቅን አደረገ" የሚለው የዳዋት መዝሙር ትዝ ይለኛል። ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት የተወለዱ መሆናቸው መብረቅ ያሰኛቸዋል። እኔ በዘመኔ ትውልድ እንድኮራ ከሚያደርገኝ ወጣት አገልጋዮች
እንዲ መምህር ዮሐንስ ነው። በትምህርተ ጽድቅ መጽሐፉ ብዙ ነፍሳትን ወደ እውነተኛው ትምህርት
እጃቸውን ይዞ መርቷል ዛሬ ደግሞ ዓይነ ልቡናችንን የሚ ያበራ በኦርቶዶክሳዊ የአበው አስተምህሮ የተቃኘ ትምህርት ያለበት መጽሐፍ ይዞልን በመምጣቱ ለገበሬ ዘርን ለእንስሳ ሳርን የሚሰጥ አምላክ ለመምህራንም በየጊዜው የሚጽፉትን የሚ ያስተምሩትን አይከለክልምና ሞገስ እነዲሆኑን በዦጥረ መባርቅት አምሳል በቤተ ክርስተያን ሰማይ ላይ ለገልጣቸው ሳይ ደስ ይለኛል።

ከሰማይ በታች ያሉ ምዕመናንን የሚያስደነግጥ ሳይሆን የሚያንፅ ሆኖ ስላገኘሁት እሳት መስሎ
በታችሁ እነ ኢሳይያስ ከንፈራችሁን የሚ ያነጻ እንጅ የሚያቃጥል እሳት ስላልሆነ ከናፍረ ምዕመናንን የነጻ ዘንድ የተገለጠ መጽሐፍ መሆኑን ባነበብሁት ወቅት ተረድቻለሁና እነሆ በሃይማኖቱ ኦርቶዶክሳዊዋ፣ በትውልዱ መጽሐፍ ቅዱሳዋ፣ በነገዱ ቄርሎሳዊ፣ በግብሩ ዐቃቤ ልቡና መሆኑን ለማስረዳት ምስክር ሆኜ መጥቻለሁ
ምስክርነቴን ከተቀበላችሁኝ ከአበው ትምህርት የተወለደ ለመሆኑ እናንተም ሩቅ ሳትሄዱ የአነጋገሩን ለዛ ስታዩት ብሔረ ሙላዱ መጻሕፍት፣ አባቶቹ ሊቃውንት መሆናቸውን እንደምታረጋግጡ ያለኝን እምነት እየገለጽሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ብቻ ሳይሆኑ በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ላይ ያልጠራ አመለካከት ያለው ሁሉ ቢያነበው ምኞቴ መሆኑን እገልጻለሁ።
#ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ ለመፅሐፉ የሰጡት አስተያየት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ መፅሐፍ

#የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ እና ምሳሌነቱ

በዚህ በጾም ሠአት የሚነበብ

አከፋፋይ ኤዞፕ መጻሕፍት !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህ ጽሑፍ ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ነው፤ ምክንያቱም እስከ አሁን የማናውቃቸውን ብዙ ነገሮች ስለሚያሳውቀን እና ከዚህ በፊት የምናውቃቸው ጉዳዮች ከሆኑም ሰለሚያጠናከራቸው፤ ወይም ስለሚቃረናቸው ነው። መጽሐፉን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። ከፍል አንድ እስከ ደርግ መቋቋም ድረስ ያለው የጸሐፊው ትውስታ ሲሆን፣ ከፍል ሁለት ደግሞ የደርግ ዘመን ይሆናል። ሁለቱም ዋጋ አላቸው። ሁለቱም ከፍሎች ... ለታሪክ ተመራማሪው ብዙ መረጃ ይሰጣሉ። የመጀመሪያው ክፍል ማለትም ቅድመ ደርግ ክፍል ለሁለተኛው ክፍል ታሪካዊ ዐውዱን (historical context) ይሰጠዋል። በዚህ የተነሣ ኋላ ላይ ትላልቅ የፖለቲካ ወይም ወታደራዊ ሥልጣን ይዘው በሀገርደረጃ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ግለሰቦችን በወጣትነታቸው እናገኝበታለን፡-ጌታቸው ናደው፣ ደምሴ ቡልቶ፣ ተፈሪ ተከለ ሃይማኖት፣ ወዘተ…፡: ከጀነራሎችም ቢሆን አንዳንዶቹን ቀድመን እንተዋወቃቸዋለን፡ ጀኔራል አማን ሚካኤል አንዶም፣ ጀኔራል ነጋ ተገኝ ሊጠቀሱ ይችላሉ። ስለዚህ የመጀመሪያው እና የሁለተኛው ከፍል አንድ አምሳል ናቸው ማለት ይቻላል። የዚህ ትውስታ ትልቅ አስተዋጽዖ በስፋት መቅረቡ፣ ብዙ ጉዳዮችን በዝርዝር ማየቱ ነው። ...

• ፕሮፌስር ሺፈራው በቀለ፣ ለረጅሙ ረቂቅ ጽሑፍ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ



/channel/azop78


ኤዞፕ መጻሕፍት

የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉@azop78
#ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ  @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። መጻሕፍትን ለሚወዱ ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

/channel/azop78

ቆየት ያሉ መጽሐፍ ቅዱሶችና መዝሙረ ዳዊቶች እጃችን ላይ።



የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉@azop78
#ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ  @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። መጻሕፍትን ለሚወዱ ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

/channel/azop78


የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉@azop78
#ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። መጻሕፍትን ለሚወዱ ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የመካከለኛው ዘመ7 ታሪክ በነገረ-ሃይማኖታዊ ድርሳኖቻቸው ስመ ጥር ከሆኑ ሊቃው3ት መካከል ቅዱስ ሳዊሮስ ዘእስሙናይገ (987 ዓ.ም እ.ኤ.አ ያረፈ) ግ3ባር ቀደም ነው:: ሳዊሮስ ኢብኑ እልሙቃፋ እየተባለም ይጠራል። የጻፈው በአረብኛ ቋንቋ መሆኑ ደግሞ የግብጽ ቤተ ክርስቲያ3 አስልምና 3 ተከትሎ እየገነነ በመጣው ጸረብኛ ቋ3ቋ አስተምሀሮዋ3 ለመግለጽ ካስለፈቻቸው ታላላቅ ሊቃው3ት ቀዳሚው ያይርገዋል። ሊቀ ጳጳስ ላዊሮስ በታሪክ፣ ነገረ-ሃይማኖት እና ሥርዓታት ዙሪያ በጻፋቸው ድገቅ ዕቅበተ-እምነታዊ ድርሳናቱ ቤተ ክርስቲያጓጓ አገልግሎ ያለፈ ትጉህ ሊቅ ነው። ከእነዚህ ድርሳናቱ አጓዴ በግእዝ መጽሐፈ ሳዊሮስ በሚል የምናውቀው १४८६ ९१० १६-१.९४( )حاضي إلا بات ك PC ይህ መጽሐፍ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ድርሰት ነው። PAD

Lህ መጽሐፍ ጥጓታዊው፣ ኦርቶዶከላዊ የቤተ ከርስቲያ3 አስተምህሮ ከዘመነኛው ተግዳሮት (በተለይ እስላማዊው የአስተምህሮ ትችት) አጓጻርቃኝቶ ያዘጋጀው ድርሰቱ ነው። ምሥጢረ ሥላሴ፣ በአብዛኛው በኩነታት እጓጻር ሲያብራራ እናገኘዋለጓ። ይህም ለእስላማዊው 777 የተሻለ የሚሆነው በኩነታት ላይ የተመሠረተው ሐተታ በመሆኑ ነው። ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆጓም ይህ ኩነታት7 በሰፊው የመጠቀም እዝማሚያ ወደ ኢትዮጵያ ሊቃው37 ዘጓድ የደረሰው በዚህ ሊቅ ድርሳናት በኩል ሳይሆጓ አይቀርም። የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰት በሆነው መጽሐፈ ምሥጢር ውስጥ የምናገኘው ጉዳዩ፣ በጥንቃቄ የማየት አካሄድ ለዚህ 63650 የሚሰጥ ነው።

ይህ መጽሐፍ በሳዊሮስ እና በሌሎች አረብ-ክርስቲያጓ ሊቃውጓት ድርሳናት በተለመደ መልኩ ጥልቅ እና ረቂቅ የሆኑ ተመስጦጸዊ ሐተታዎች 7 የያዘ መጽሐፍ ነው። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ነገረ ገረ-ሃይማኖታዊ ሳይሆ፣ ጥልቅ የሆኑ የመጓፈሳዊ ሕይወት መመሪያዎች3 እና ተሞክሮዎች 3 የያዘ እጅግ ጠቃሚ መጽሐ ሐፍ መሆኑ ነው።

ኤፍሬም ከጓዴ ዬ ይህጓ በቀላሉ የማይገኝ ውድ መጽሐፍ ከ ግዕዝ ወደ አማርኛ ተርጉመው ለአገባ ገባብያ፣ ማብቃታቸው በእጅጉ የሚ ያስመ ►:: ለመ/ር ኤፍሬም እግዚእብrሔር ብዙ የሚያገለግሉበትን ጸጋ ያድልል!

ዷ /3 በረከት አዝመራው

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኦሪጅናል
ክለር ፉል ህትመት !!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የራስ መኰንንን ሞት በሰሙበት ቀን አጼ ምኒልክ እግራቸው
ከመቃብር መግባቱ ተሰማቸው ፡፡ በ፰፪ ዓመታቸውም ንጉሠ ነገሥቱ ማርጀታቸውን ፤ መድከማቸውንና ዕድል የጠመመባቸው መሆናቸው ተሰማቸው ። ከሞት ይልቅ ያስፈራቸውና ያሳሰባቸው ያገሪቱ የወደፊት ዕድል ነበር ። ራስ መኰንን በሌሉበት የሸዋ መንግሥት እንዴት ሊሆን ነው ? ሀገሪቱ በዕድገት ፤ በፖለቲካና በአስተዳደር ? ረገድ እንዴት ልትሆን ነው ? የሚል ጥያቄ በሐሳባቸው ይመላለስ ጀመር።


በ፲፱፻፲ ዓ ም ልጅ ኢያሱ ዐሥር ዓመታቸው ነበር ። እሳቸ
ውም መልከ መልካም ፤ ትሑትና የተከበሩ ነበሩ ። ኣጼ ምኒልክም
እያደር አጠኗቸው ። ስለሳቸውም የነበራቸው ፍቅርና እምነት እየ
ተቀነሰ ሔደ ። ለወራሽነትም በፍጹም አልፈለጓቸውም ። እንደ
ትልቅ ሰው ልጆች ብልህ ወይም አዋቂ መስለው አልታዩም ። ካባ
ታቸውም የትንቢትና የመንግሥት ሀብት እንደ ዳዊትና እንደ መልከ
ጼዴቅ ጊዜ ዓይነት አልተሰጣቸውም ።

የአጼ ምኒልክ ዓይይ ያረፈው በዘመዳቸውና በወዳጃቸው በራስ
መኰንን ልጅ ላይ ነበር ። የራስ መኰንን ልጅ ዓይናቸው ብሩህ ፤
ብልህና የትንብልና ስጦታ ያላቸው ነበሩ ። ለብዙ ጊዜም አጼ
ምኒልክ ከሁለቱ የትኛውን እንደሚመርጡ ተቸግረው ከእግዚአብሔር ምልክት
ይጠብቁ ነበር ።

▀▄▀▄▀▄Æ🅂🄾🄿 🄱🄾🄾🄺▀▄▀▄▀▄
👉👉👉Telegram channel:- @azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ታላቅ ዝክር !!
ታላቅን ማክበር!!
አንጋፋዎችን መዘከር !!!

ተጠርታችኋል።
አይቀርም፣ጋሽ አስፋው ዳምጤ በብሄራዊ ቲያትር አዳራሽ ዘጠናኛው ዓመታቸውን ምክንያት በማድረግ ይዘከራሉ።

ታላቅ ሥነጽሑፋዊ ድግስ !!!/

አይቀርም !!!
ኤዞፕ መጻሕፍት !!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መጻሕፍትን የማመሥጠር አቅማቸው፣ ሰብእናን ሳይነኩ ሐሣብን በሐሳብ የመሞገት ትጋታቸው፣ ነገሮችን የመረዳትና ሕገ-አመክንዮን ሳያፋልሱ የመተንተን አቅማቸው፣ ባገራችን ያሉ ልዩ ልዩ ሃይማኖታውያን ክርክሮችን የሚረዱበትና ይትባህላቸውንም የአንዱን ከአንዱ ሳይደባልቁ በጥንቃቄ የሚገልጡበት ዘዴ፣ ለቀደሙት አበው ያላቸው አድማስ-የለሽ ፍቅርና ተቆርቋሪነት፣ ለተተኪ ወጣቶች ያላቸው ስስት፣ በ1920ዎቹ በሀገር ላይ ያንዣበበውን አደጋ የተረዱበት መንገድ፣ በ1950ዎቹ ላይ ሆነው በሃይማኖት ብረዛና ክለሳ ረገድ ትውልዱ የተጋረጠበትን መጻኢ ፈተና ተረድተው በቅኔያትና በመጽሐፍ የመቱት የንቃት ደወል፣… ሁሉም አስደናቂ ነው፡፡ በእርግጥም ቅድስናውንና መንፈሳዊውን ሕይወት ሳይለቁ ዘመናቸውን በመረዳት በኩል ከፊት ቀድመው የሚገኙ አብነትነት ያላቸው ሊቅ ጥራ ብባል በትምክህት የምጠራቸው መልአከ ብርሃን አድማሱ ናቸው፡፡ እናም እኒያን ሁለት ክፍለ ዘመናትን ከሁለት ትውልድ አጋምደው ያለፉ ርጉዕ ሊቅ ባረፉበት የ፶ኛ ዓመት ዋዜማ ላይ ቆመን ከሥራዎቻቸው ጋራ መዘከራችን ክብሩና ረድኤቱ ለእኛ እንጂ ለእርሳቸው አይመስለኝም፡፡

በአማን ነጸረ
#ደብተራና የሕግ ባለሙያ

አድማሱ ጀንበሬ ከዘመናቸው ሊቃውንት ውስጥ
ፈርጥ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ዘመን ከነበሩ ሊቃውንት ጋር ሊጠሩ ሊመደቡ የሚችሉ መሆናቸውን ሥራዎቻቸው በግልጽ እንደሚመሰክሩ አምናለሁ። ሃይማኖታቸውን፣ የሃይማኖታቸውን አስተምህሮ፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ምስክርነትና እውነተኝነት ጠንቅቀው ያውቃሉ። የተችወቻቸውን ሀሳብም ነቅሰው ይረዳሉ፡፡ ለሁሉም እውነትን ብቻ መሠረት አድርገው መልስ ይሰጣሉ፡፡ የሚከራከሩትን አካል ያከብራሉ፡፡ በታሪካቸው አይመጻደቁም። ለማንም
ተገቢውን ክብር አይነፍጉም፡፡ ከዐውድና ከጭብጥ በፍጹም አይወጡም፡፡ በምንም ዐይነት መሥፈሪያ ጎድለው ሊገኙ አይችሉም፡፡ እርሳቸው ራሳቸው ለፍጹምነት ሲጋደሉ ስለኖሩ ሥራቸውም ፍጹምነት እንዲያገኝ ከአምላካቸው ተችረዋል ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህም ይህን መጽሐፍ አለማንበብ በእውነት ያጎድላል። ይልቁንም ይህን አንብበን ሥራዎቻቸውንም ደጋግመን አንብበን ዕውቀትን ብቻ ሳይሆን የእርሳቸውንና የመሰል ሊቃውንትን የጸጋና የመዐርግ ዕርገት እንደ ኤልሣዕ በእምነት አይተን የበረከት ዐጽፋቸውን በእምነት እንቀበል ዘንድ አሳስባለሁ፡፡

መምህር ብርሃኑ አድማስ
በፊሎሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ)

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ማንኛውንም የጠፋባቹህ መፅሐፍ ቢኖር እዘዙን ባይኖረን ፈልገን እናቅርባለን።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

Copy Print


ከመጽሐፉ የተወሰደ

‹‹ሰው እንዲህ ነው ማለት ይቻላል የኔ ልዥ? ዕድሜህ እየገፋ ሲኸድ ዝጌር ተፈጠራቸው መሀል ሁሉ ሚስጥሩ ሰው እንደሆነ ትረዳለህ። የምንደራችን ሰዎች እርስ
በርስ እየተላለቁ ምንደራችንን የወላድ መካን አርገዋል። ወንድም ወንድሙን ጭምር እየገደለ ሞትን ንቀዋል። ካወቁ ግና ሞት አይናቅም። ጦር ሜዳ ላይ ሞት የሰውን ልዥሲንቅ አይቻለሁ።››

ያንን ሰፊ የጦር አውድማ፣ ያንን ገላጣ መሬት የከበቡትን ተራሮች አንድ በአንድ አየና ግዝፈታቸው አስፈራው፤ ግርማ ሞገሳቸው አክብሮት፣ አድናቆትና ፍርሐት ጫሩበት። በነሱ ፊት ከሰናፍጭ ያነሰ መሆኑ ታወቀው። ‹‹ተይመር ወዲያ››የሚለው ፈሊጡ ብልጭ አለለት፤ ልኩን አለማወቁን ጠቆመው። አቀረቀረ።

እንደገና ቀና ብሎ ያንን ከሠዐታት በፊት ለምለም የነበረ መሬት አየው፤ጠፍ ሆኗል። ሰማዩ በመድፍና በጥይት ጭስ ጠቁሯል። የባሩዱ ሽታ አፍንጫ ይሰነፍጣል።

በየቦታው ሬሳቸው የተዘረረው ፈረሶችና በቅሎዎች ያገልግሎት ዋጋቸው ያ መሆኑ አሳዝኖታል።

ዙርያውን ያየው ውድመት በውስጡ የሆነ ነገር አርግዟል። ‹‹ምንዲነው? የሆነ ነገር አርግዟል?›› ሲል ጮኸ። የዓድዋን ተራሮች በዐይኑ አዳረሳቸው፣ ‹‹አዎ
ያረገዘው ድል ነው!‹‹ ሲሉ ሰማቸው።

የድል መዓዛ አወደው! መሬት ሳመ።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

https://vm.tiktok.com/ZMBNtCLyp/

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኤዞፕ የእናንተው የምንግዜም ቀደምትና ምርጥ መጽሑፍት ምርጫ !!


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሕይወት እንደገና በሦሥት ዓለሞች
የመጀመሪያው የሰው ሕይወት መነሻው ከሆነ ከዚህ ከተፈጠረበት መሬራዊ አላፊ ዓለም ይለያል፤

ዳግመኛው የሰው ሕይወት እንደገና በሦስተኛው ሰማይ ኢሩየ ከልል ውስጥ በጌል-ጌላ ( ኤዶም) ገነት ዓለም፡ እስከ ዳግመኛ ትንሣኤ ድረስ ይቆያል፤

ሦስተኛው ዘላለማዊ ሕይወት ከዳግመኛ ትንሣኤ በኋላ! በአምስተኛው እርእያ ሰማይ ከልል ውስጥ ወደ አርያም ዓለም ምድርና ወደ አዲሲቱ ሰማያዊት እየሩ ሳሌም ዓለም ውስጥ ይሻገራል! የማይፈርስና የማያረጅ መንፈሳዊ የክብርአካል ገላን ይለብሳል! የሰው ልጅ ሰውነት እንደ መላእከት ፈጣሪውን እያመሰገኑ በሕይወት ለዘላለም ይኖራል፤

የዚህ አድል እጣ የሌለው ሰው ግን፡ የመጨረሻ ሕይወቱ በገሃነም እሳት ባህር ውስጥ ዘግጦ! ሲማቅቅ ለዘላለም ሲሰቃይ ይኖራል፡ ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት እሁኑኑ! ለሕይወት ባለቤትና ጌታ ለእየሱስ ክርስቶስ እራስን አሳልፎ መስጠት ቃሉን ጠብቆ ትእዛዛቶቹን መፈጸም ነው።

ከመራራስ አማን በላይ

🙏🙏✍🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በፃም ሠዓት የምታነቧቸውን መንፈሳዊ መፅሐፍት ከፈለገቹህ ብቅ በሉ ደውላችሁ እዘዙን።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ROMAN EGYPT

ROMAN Egyptcrascal area of interdisciplinary rewatch, which has steadily expanded since the 1970s and owens to grose. Egypt played a pivotal role in the Roman empire, not only in terms of political, economic and military strategies, but also as part of an intricate coltural disease insolving themes that resonate today-cast and west, old world and new. acculturation and shutting kelentities, patterns of language use and religious bebet, and the management of agriculture and trade. Roman Tigrpt was a literal and figurative crossroads shaped by the timement of people, goods, and ideas, and framed by permeable boundaries of self and space

This handbook a unique in drawing together asany different strands of research on Roman Egypt, inoriler to suggest both the state of knowledge in the field and the possibilities for collaborative, synthetic, and interpretive research Arranged in seven thematic sections, each of which includes essays from a variety of disciplinary vantage points and multiple sources of information, it offers new perspectives from both established and younger scholars, leduring individual essay topics, themes, and intellectual juxtapositions.

Christina Riggs is Chair in the History of Visual Culture at the Department of History, Durham University !!


/channel/azop78



የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉@azop78
#ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ  @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። መጻሕፍትን ለሚወዱ ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ" ይባላል፡፡ ከስሚ ሰሚው ለከዋኔው የቀረበው Iሎ ይታመናልና፡፡ መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ለዚህ መልካም ኣብነት ነው፡፡

በዚህ መጽሐፍ ባለትዝታው አለቃ ለማ ከሚያወጉን አያሌ ቁም ነገሮች መሐል ለማመን የሚያስቸግሩና ተዓምር የሚመስሉ ጉዳዮች አሉ። የታሪክ ወይም የሶሲዎሎጂ ወይም የስነ ቃል አጥኚዎች ቢነግሩን የማንቀበላቸው። ራሳቸው ባለቤቱ በራሳሸው አተራረክ ዘይቤ በቀጥታ ስለነገሩን ግንተደመንም ቢሆን አምነን እንቀበላቸዋለን። ጠርጣሪ ልቦና ያለንም ብንሆን እንኳ, ቢያንስ ሙግት አንገጥምም።

መጽሐፈ ትዝታ አንድ የእውቀት አባት የሆኑ አዛውንት የወጡና የወረዱበትን ያዩትንና የሰሙትን፣ በቅርብ የሚያውቁትንና የኖሩበትን ሕይወት እንደጨዋታ የሚተርኩበት መጽሐፍ ነው! ድምፅና ምስል ያለው መጽሐፍ።

ተፈሪ አለሙ



/channel/azop78
ኤዞፕ መጻሕፍት


የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉@azop78
#ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ  @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። መጻሕፍትን ለሚወዱ ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

/channel/azop78

የጥንታዊውና የመካከለኛው ዘመን የኦሮሞ ታሪክን የሚዳስሱ መጻሕፍት !!!!


የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉@azop78
#ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ  @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። መጻሕፍትን ለሚወዱ ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የምሽት በረከቶች ናቸው።
ይነበቡ

/channel/azop78


የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉@azop78
#ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ  @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። መጻሕፍትን ለሚወዱ ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሰሞኑን አፍሪካውያን ፣ አፍሪካን ላፍሪካውያን የሚሉ ይመስላሉ።

በመዲናችን አዲስ አበባ እየመከሩ ነው።

የአፍሪካውያን ህብረት እንዴት ተመሰረተ ?


የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አ.አ.ድ.)  Organisation of African Unity (OAU))፣ ግንቦት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ተመሥርቶ የድርጅቱ መመሪያ ውል (OAU Charter) በ፴፪ቱ መሥራች አገር መሪዎች ጸድቆ ተፈርሟል። የድርጅቱም ጠቅላይ መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ እንዲቆይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ግብዣ መሠረት እስካሁን ድረስ እዚያው አዲስ አበባ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በ፲፱፻፺፬ ዓ/ም ተደምስሶ የአፍሪካ ኅብረት በሚባለው ድርጅት ተተክቷል።

ለብዙ ሺ ዓመታት ኢትዮጵያ ብቻዋን በአኅጉሩ ውስጥ ከአውሮፓውያኖች የቅኝ ግዛት ቀንበር ውጪ ቆይታ የሙሶሊኒ ፋሺስት ኢጣልያ በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ወርራት በነበረ ጊዜ አርበኞች ልጆቿ ውድ አገራቸውንና ነጻነታቸውን አሳልፈው ላለመስጠት አምስት ዓመታት ሙሉ ተዋጉ። ንጉሠ ነገሥታቸውም የእዚህን የግፍ ወረራ ለማጋፈጥ በዓለም መንግሥታት ማኅበር መድረክ ላይ ሲቀርቡ፣ ከአፍሪቃ አኅጉር ብቸኛዋ አባል ኢትዮጵያ ማንም አጋዥ አገር አልነበራትም።
ለአኅጉሩ ነጻነት በቅኝ ግዛት ሥርም የነበሩት ሕዝቦች፤ በነጻነትም ላይ የነበሩት አገራት የአውሮፓውያንን መዥገራዊ ልጥፍነት ለማላቀቅ ብዙ ከታገሉ በኋላ በሰሐራዊ አፍሪቃ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፵፱ ዓ/ም ጋና ነጻ ሆነች። ከዚያ አስከትሎ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት እስከተመሠረተ ድረስ በ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ጊኒ ነጻ ስትሆን በ ፲፱፻፶፪ ዓ/ም አሥራ አምስት አገራት፤ በ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ሦሥት አገራት፤ በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም ደግሞ አራት አገራት ነጻነታቸውን ተቀዳጁ።
የአኅጉሩ መሪዎች በዓለም መድረክ ላይ ለበለጠ ተሰሚነት የትብብርን ግንባር ማሳየት እንደነበረባቸው በመገንዘብና ገና ነጻ ላልወጡትም ወንድም አገሮች ሉዐላዊነት መታገል ስለነበረባቸው ዓላማቸውን ግብ ለማድረስ በሁለት ቡድን ተከፍለው ፣ ባንድ በኩል እራሱን “የዘመናዊ ተራማጅ” ብሎ የሚጠራው፣ በጋናው ፕሬዚደንት ክዋሜ ንክሩማ የሚመራው የ “ካዛብላንካ ቡድን” በ ፲፱፻፶፬ ዓ/ም ተመሠረተ። ይሄ ቡድን የአኅጉሩን መንግሥታት በኅብረት ለማዋሃድ ዓላማ የያዘ ሲሆን አባላቱ ጋና፣ አልጄሪያ፣ ጊኒ፣ ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ማሊ እና ሊቢያ ነበሩ።
ሁለተኛው ቡድን የ”ሞንሮቪያ ቡድን” ሲሆን የተመራው በ ሴኔጋል ፕሬዚደንት ሊዮፖልድ ሴዳር ሴንግሆር ነበር። አባላቱ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያ፣ ላይቤሪያ እና ኢትዮጵያ ሲሆኑ የነሱ የኅብረት አስተያየት ደግሞ የዱኛ ኅብረት ሳይሆን ፍላጎታቸው ረጋ ባለ ሁኔታ የዱኛኪን ኅብረት አንድነትን ያስከትላል የሚል ነበር።
መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ከተማ ይፍሩ ታላቅ ጥረትና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድጋፍ ሁለቱም ወገኖች አዲስ አበባ ላይ እንዲገናኙ በተደረገው ጥሪ መሠረት ተሰባስበው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን የስምምነት ውል ፴፪ ነጻ ሀገሮች ሲፈርሙ ድርጅቱ ተመሠረተ።

ይኸው ዛሬ ካለበት  ደረጃ ደርሷል።


መጻሕፍት ቤታችን ደግሞ ልዩ ልዩ የአፍሪካውያንን ታሪክና ፍልስፍና ፣ የስልጣኔ መነሻነትን የሚተነትኑ መጽሐፍትን አዘጋጅቷል።
ሳምንቱንም አፍሪካን ለአፍሪካውያን ብለን እነሆ እንድትጎመኙን በራችን ከፍተን እንጠብቃችሗለን!!!!


ኤዞፕ መጻሕፍት !!!



ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ በጣም ቆንጆ ዶክመንቶች አግኝተናል !!!

ብቅ ብለው ይጎብኙን !!

!ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የመፅሐፍ ቅድስ ታሪካዊ አመጣጥ ቅጽ1እና 2

Читать полностью…
Subscribe to a channel