azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8863

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ለልጆች የመጽሐፍ ቅድስ ታሪኮች

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በመደብራችን ይገኛሉ ትንሽ ኮፒዎች አስገብተናል

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ፎቶዎች በከፊል !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የሐዋዝን ግጥሞች አየኋቸው። የዘመን መታመም፣ የሀገር አጓጉርጉሮ፣ የነፍስም መቃተቶች ናቸው። በአውን አና በህልም መካከል አንደኾነ ድንጉጥ ሰው ያስደነብራሱ። ሐዋዝ ወደማንም አጁን ከመቀሰሩ በፊት ህመም አና ሰቆቃውን ከራሱ ጋር ያወራርደዋል። በቃሳት ጋሻነት ህመሙን thላከለው ይከ ጅላል። አሱም የኩነቱ አካል ነው'ና የኩባችንን ጻማ ተሸክሞ አግዚአ ማለት ይጀምራል። በህመሙ ውስጥ የኹላችጓም አንቅልፋምነት አሰበት።

...ሀገር፣ ሕዝብ፣ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ሃይማኖት አና የመሳሰሱት የአብሮነት ውሎች ግድ ፀሰጡታል። አየተነቀነቀ ያለው የጋራ ጎጇችን አንጀቱን ያባውሰዋል። በብላሽ የምጓጓደው፣ የሰye ባይ የምጓሸረሸረው የስሪታችጓጓ ማገር በጓቃት በሚታዘብ ዋይ ሰልስ የስብሳል። ሐዋዝ ይ533 አያየ ነው በግጥሞቹ ደጋግሞ የሚቆጨው ። ገጣሚ ነው ' ና ህመሙጓ አጓረዳሰታሰጓ። ባጓረዳበትም አሱ ሰርክ ለሚጠይቀው ጥያቄ ህLናው መልስ መስጠቱን አያቆምም።

የሐዋዝ ግጥሞች ደፋር ናቸው። አንደ አድር ባይ አሮሮ አይመጠመጡም። ግጥም የጸና የራስ መታመጓጓ ይሻል' ና። ከራሱ የተፋታ ገጣሚ፣ ለመተያያ የሚዳክር የጥበብ ሰው ከኩቡ አስቀድሞ ራሱን ይንቃል ' ና። ግጥም ከንቀት ጋር በመቆም የሞከረች ቀን ቃል ከሰመ አጓሳሰን። ቃል ፈረሶቿ3 ኮርትማ ታስቀምጣለች ' ና።

ውብአረገ አድምጥ (ገጣሚ )

ሐዋዝ በዚህ መድብል ውስጥ ኩበት ደስ የሚሱ ነገሮችን ይዞ የመጣ ይመስለኛል። አንደኛው ነገር : - ግጥሞቹ ኹሱም ሰው ቢረዳቸው በሚችሰው መልኩ መጻፋቸው ሲኾን ኹለተኛው ደግሞ የግስዝ ቅኔዎችን ከነትርጓሜያቸው ፀዞ መምጣቱ ነው። የግአዝ ቅኔዎችን ከነትርጓሜያቸው በማቅረብ በኩል ከገጣሚ ኤፍሬም ሥዩም በቀር ሐዋዝን የሚቀድመው ያለ አይመስለኝም። ስለዚህም አመጣጡ ፀበል ብሰናል።
የሐዋዝ ግጥሞች ፎርጅድ ግጥሞች አለመኮናቸውን አና የሐዋዝን ፎርጅድ ገጣሚ አለመħጓ ግጥሞቹን ካነበብሁ በኋላ በአሥሩም ጣቶቼ በመፈረም አረጋግጫለሁ። ምክንያቱም በዚህ መድብል ውስጥ የሱ ቃላት የገጣሚው ሽርፍራፊ አካል፤የገጣሚው ፍቅፋቂ ገባ አንጂ መደዴ የቃላት ድርድሮች አይደሱም።

መልካም ንባብ!

ታዴዎስ አዲሱ (ገጣሚ)

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሞት በትንሿ ሔዋን ጆሮ ተፀንሶ እንደተወለደ፦ የዘላለም
ጆሮ ሕይወት ደግሞ በአዲሷ ሔዋን በድንግል ማርያም
ተፀንሶ ተወለደ። ትንሿ ወይም የመጀመሪያዋ ሔዋን ጆሮ
የእባብን ቃል ሰምቶ ሞትን ወለደብን። የትልቋ ወይም
የዳግሚት ሔዋን የእመቤታችን ጆሮ የመልአኩን ቃል ሰምቶ ሕይወትን ወለደልን።

አዳም በሥጋ መሻት የሞት ሞትን እንደሞተ ኢየሱስ
ክርስቶስም በሥጋው ሞተ፤ አዳም በሞተ ጊዜ በገነት ውስጥ እንደተደበቀ ኢየሱስ ክርስቶስም በመቃብር ተቀበረ፤ አዳም ከበለስ በዃላ ወደምድረ ፋይድ እንደተላክ ኢየሱስ ክርስቶስም ወደመቃብር ወረደ።

ከመቃብር ተነሥቶም በበደል የወደቀውን አዳምን አስነሣው፤ ሙሽራው ክርስቶስ አዳምን ከገነት መቃብር በክብር ወደ ገነት የሠርግ በዓል እመጣው። በዲያብሎስ በገነት የሞተ አዳምን በዓለሙ _ ኹሉ በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ አነገሠው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የቀዳማዊ ኋይለ ሥላሴ ን ታርክና በፎቶ ግራፍ የተደገፈ መጽሐፍ።
አሳታሚ ቡክ ወርልድ
በከፍተኛ ጥራት የታተመ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህ በመጋቤ ምስጢር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ ተጽፎና ተዘጋጅቶ ለንባብ የቀረበው የቅኔና የልሳነ ግእዝ
መማሪያና ማስተማሪያ የሆነው መስተዋድድ የተሰኘውን ድንቅ መጽሐፍ ከጫፍ እስከ ጫፍ አንብቤዋለሁ፡ በመሆኑም መጽሐፉን ለሀገርና ለወገን፣ ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ለጉባኤ ቤት መምህራንና ለደቀ
መዛሙርቶቻቸው ፥ ከሁሉም በላይ ደግሞ የቅኔ ሞያን ከነሙሉ ይትበሀሉ ለማወቅ ብዙ ዐመታትን በጉባኤ ቤት ለሚያሳልፉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ድካማቸውን በእጅጉ
የሚቀንስ በመሆኑ እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ መጽሐፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከዚህ በተጨማሪም ለእያንዳንዱ አገባብ ማስረጃ በጥቅስ መልክ ስለ ተዘጋጀና ጥቅሱ የሚገኝበት ቦታም በምዕራፍና በቍጥር የተደገፈ በመሆኑ አንባብያንን ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር በቀላሉ የሚያስተዋውቅና የሚያዛምድ፣ በሁሉም የዕውቀት ዘርፎች ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፣ ከዕውቀት አድማስ ወደ ዕውቀት አድማስ የሚያሸጋግር፣ ጥርት ባለ የቋንቋ አገላለጽና አቀራረብ ለአንባብያን ጣፍጦ የቀረበ፣ ይህ ቀረሽ የማይባል ውብና ውድ መጽሐፍ መሆኑን እያስገነዘብኩኝ ውድ ጊዜያቸውን መሥዋዕት በማድረግ ይህንን ውድና ውብ መጽሐፍ ላዘጋጁልን ለመጋቤ ምስጢር ያሬድ ዘርአ ቡሩክ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ሊቀ ሊቃውንት ዳንኤል ሐይሉ የቅኔና የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የበአማን ነፀር

አኮ ከመዝ

በመደብራችን !!!

ለረፍታችኹ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ፍሬነው ቀድሞ የደወለ ይወስደዋል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ለቅዳሜያችኹ !!!

ለዳኞች
ለጠበቆች
ለህግ ተማሪዎች
ህግን ለሚወዱ ሁሉ
በጠቅላላው ለህግ ባለሙያወች

የሚሆኑ መጻሕፍት !!!

ኤዞፕ የናንተው!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"ባለፉት ሁለት ሺህ ዘመናት ነገሥታቱንና ጳጳሳቱን "ተሳስታችኋል” ብሎ መጻፍና መናገር ማለት ሰማይን ቀና ብሎ በርግጫ የመምታት ያህል የሚቆጠር ነበር፡፡ ጥሩ መሪዎችን ማከበራችን ጥሩ ባህላችንና ይበል የሚያሰኝ ሲሆን ማጎብደዳችን ግን መጥፎ ውርሳችን ነው

ከመጽሐፉ የተወሰደ፡፡

....እስከ መቼ ይሆን መሪዎቻችን በሥልጣን ላይ ሊሆኑ ባፍ ጢማችን እየተደፋን ስናጎበድድ ኖረን ሲሻሩና ሲሞቱ ብቻ ኃጢአታቸውን የምናበዛው? ለምን ይሆን በሥልጣን ዘመናቸው እንደነ ተቀቀለ ፓስታ የምንጥመለመለውና ድከመታቸውን የማንነግራቸው? እስከ መቼ ይሆን የሙት ወቃሽ ሆነን የምንኖረው??..."

ከመጽሐፉ የተወሰደ፡፡

ከአሁን በኋላ "ተከድኖ ይብሰል!” በሚል አጉል ፈሊጥ ተተብትበን የተከደነው ሳይማሰል ቀርቶ አሮ ሲሸት እያየን አፍንጫችንን መያዝ አንፈልግም! ከአሁን በኋላ የነበረውና ያለው ስሕተት በማጎብደድ መንፈስ ተውጠን ባለመቃወም የታሪክ ተወቃሾች መሆንን አንሻም!፡፡ የአባቶቻችንን ዕዳ ለማቃለል እንሞክራለን እንጂ በዕዳ ላይ ዕዳ ጨምረን በልጆቻችን ጫንቃ ላይ አንጭንም..*

ከመጽሐፉ የተወሰደ፡፡

ስለ አዘጋጁ በጥቂቱ፡- መምህር ቡሩክ ገብረ ሊባኖስ ተስፋዬ ከሕፃንነቱ ጀምሮ ዕድገቱ በቆሎ /አብነት/ ትምህርት ቤት ነው፡፡ የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማዎች፣ አቋቋምና ቅኔ አጠናቋል፡፡ በመጨረሻም በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሚሰጠውን የትርጓሜ መጻሕፍትና ባሕረ-ሐሳብ በ1991 ዓ.ም አጠናቆ ተመርቋል፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ አድባራትና ገዳማት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ሆኖ ለዘጠኝ ዓመታት ያህል አገልግሏል፡፡ አሁንም በአውስትራሊያ ቤተ-ከርስቲያን በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የሰሎሞን መዝሙር ከመዝሙሮቹ ሁሉ የተለየ መዝሙር ነው፡፡ ውጫዊ ንባቡን ሲመለከቱት ዓለማዊ መጽሐፍ /ልብ ወለድ/ የሚመስል ሲሆን ውስጣዊ ምሥጢሩ ግን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መልእክት ያለው ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ሰሎሞን መዝሙሩን በዚህ ዓለም ለምትኖረው ወዳጁ የጻፈው ደብዳቤ እየመሰላቸው እንደ መንፈሳዊ መጽሐፍ አያዩትም፡፡

ቅዱስ ያሬድ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን /የሰሎሞን መዝሙር/ ስለ ቤተክርስቲያን /ስለ ምእመናን/ እና ስለ ድንግል ማርያም እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተነገረ ተረድቶ ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል ማርያምን እያመሰገነ ዘምሮታል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዜማ የደረሰለት የሰሎሞን መዝሙር በቤተክርስቲያናችን በዘመነ ጽጌ ቅዳሜ ቀን ይዘመራል፡፡ ዘመነ ጽጌ /የአበባው ዘመን/ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ
የሚዘመርበት ወቅት ነው፡፡ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን /የሰሎሞን መዝሙር/ የሚዘመርበት ጊዜ ዘመነ ጽጌ /የአበባው ዘመን/ አንዲሆን የተመረጠው ሰሎሞን ቤተ ክርስቲያንን፣ ጌታችንንና እመቤታችንን
ድንግል ማርያምን/ በአበባና በፍሬ እየመሰለ ስለተናገረ ነው፡፡

ስለሆነም ይህንን መጽሐፍ የሚያነብ ሰው የተሳሳተ ግንዛቤ እንደ ቆሸሸ ልብስ አውልቆ ጥሎ ሕይወት አድሶ የሰሎሞንን መዝሙር ሊጸልየው የሚጠብቅ በረከተ ትርጓሜ እነሆ፡፡



ከውስጥ ገጽ የተወሰደ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

In September 2004 acquired SiX diaries written by Richard George Tyndall
Bright, British army officer. They cover his participation in African
exploration expeditions from June 1897 to September 1908. This archive had
belonged to Humphrey Winterton, a British collector whose African reference
library was well known


In acquiring these diaries it was my intention to make one or more of them
available to a wider audience in a published format. Bright was a candid
observer of places which were at the time largely unknown. He was a
meticulous record-keeper, with a keen eye for details. His diaries thus offer an
unusual insider's look at the evolution of British colonial policy, as well as
providing a factual account of daily life on these expeditions.


In presenting one section of the first diary, it is my hope that an obscure but
important aspect of the history of East Africa in the late 19th century will be
illuminated. The introductory material is designed to make its significance
more apparent to those who are not familiar with the times and places
involved.


As in the past, I am indebted to Richard Pankhurst, Professor at the Institute of
Ethiopian Studies in Addis Ababa, for his insights and suggestions; to Glenn
Mitchell of Maggs in London for his assistance with research; and to Nancy
TenBroeck for transcription and editing for publication.


Frederic A. Sharf
November, 2005

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ብቻ ለቀደማት !!!
በቃ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል።
እነሆ መጽሐፍት ቤታችን ቀደምትና አዳዲስ መጽሐፍትን ሰድሮ ለእናንተው ምቹ አድርጎ ይጠብቃችዃል።

ትንሽ ስለ መጽሐፉ

……እይታችሁ ስለምን ፊትና ኋላ ሆነ? የቆማችሁበትን ማን ይይላችሁ? ተፈጥሮላይ መጀመሪያውንም መጨረሻውንም አናውቀውም።የምናውቀውን መካከሉን ብቻ እንኑር።መጀመሪያውን ለማየት ወደኋላ አትጎተቱ።መጨረሻውንም ለማወቅ ወደፊት አትጋልቡ።በዛሬላይ አምላክ ሁናችሁ ኑሩ እንጅ።ወደኋላ ካያችሁ ደካሞች ትሆናላችሁ፤ወደፊት ካያችሁ ደግሞ በአምሮት ትቃጠላላችሁ።
የተስተካከለ እይታ ይኖራችሁ ዘንድ ሁለት ዓይኖቻችሁን በውረንጦ አወጣላችኋለሁ።ሌላም ንፁህ የልብ ዓይናችሁን አበራላችኋለሁ።ከዚያም ከብሄርተኞች ጋር ብሄርተኛ፤ከሀይማኖተኞች ጋር ሀይማኖተኛ፤ ከዘረኞች ጋር ዘረኛ አትሆኑም። ከዜጎችም ጋር ዜግነት አይኖራችሁም።ከማህበረሰብ ባርነት ተላቃችሁ የጠራችሁ ግለሰብ ትሆናላችሁ። እናንተ ራሳችሁ እንደሰው ያለም ዜጋ፤እንደተፈጥሮ የዩንቨርስ አባል እንደሆናችሁ ራሳችሁን ታያላችሁ፣ታስባላችሁ።
የምታዩትን ሳይሆን የሚታየውን ታያላችሁ። (ገጽ:216)
        ከዓይናውጣ መጽሐፍ የተወሰደ።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኮምፕሌት አራቱንም ቮሊሞች እየሸጥን እንገኛለን !!!

ሁለት ኮምፕሌቶ ቀርተውናል

ኤዞፕ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ለቀደመ ብዙ ኮፒዎች የሉንም !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ባይራ ዲጂታል መጽሔት



ቅጽ ሁለት ቁጥር አንድ




በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!


ቴሌግራም- /channel/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የመሪራስ አማን በላይ
መፅሐፍ በገባያ ላይ ውላል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የቀዳማዊ ኋይለ ሥላሴ ን ታርክና በፎቶ ግራፍ የተደገፈ መጽሐፍ።
አሳታሚ ቡክ ወርልድ
በከፍተኛ ጥራት የታተመ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ለማና ዘመዶቹ
በታላቅ ቅናሽ !!

በመደብራችን !!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ መፅሐፍ በገባያ ላይ ባአጭር ጊዜ ሁለተኛ እትም

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እጹብድንቅ ስለሽ እጹብ የሆነ መጽሐፍ ጽፎልናል።
እውነት እፁብ !!!

እንብቡለትማ !!
መራር ሀቆችን በትዝብትና በጥያቄ፣ እየገሠፀ ሀቅ ሀቁን ያስተምራችኋል።



ትንሽ ከመጽሐፉ

ትዳር እንደመኪና ነው። ሁልጊዜ አብዝቶ አስካሪ እየጠጣ ኣሽከረክራለሁ የሚል እንድ ቀን ከመንገዱ ይወጣል። ሁሌ ከጠጡ እያግቡ። ካገቡ አይጠጡ-እስኪሰክሩ::

***

ቡና በገዛ እጁ ሱሰ ሁኖ ሲወቀጥ ይኖራል። ማን እነቃቃ እለዉ። የነቃና የሚያነቃ በዚህ ዓለም መከራው የበዛ መሆኑን ማን በነገረዉ? እስከዚያዉ እየወቀጡ ይደቁሱት፣እያፈሉም ይጠጡት። “ወደሽ ከተደፋሽ” አይደል ነገሩ፡፡

***

መንግሥት ተማሪ ሁኖ ህዝብ ቢያስተምረዉ፣ በህዝብ የተጠየቀዉን ባለመመለሱ ገና ድሮ በተባረረ ነበር።

***

የዛሬ ዘመን ትዉልድ እዉቀቱ ጥራዝ ነጠቅ፣ ትግሥቱ ሳይጀመር የሚያልቅ፣ ጊዜ የሌለው ግን ጊዜዉን ሁሉ የሚያባክን፣ ግላዊ ምሥጢር የሌለው ግን ከሰው በአካል የማያወራ፣ ስለሁሉም የሚናገር ግን ሰለምንም የማይማር ነው።

***

ሰው ጥንትም ገንዘብ ይወዳል። ያሁኑ ዘመን ፍቅረ ንዋይ ግን ከልክ ያለፈ ይመስላል።

የሐበሻ ሰዎች፣ ክንፍ አበቀሉ አሉ፣ ሲሄዱ ታይተዋል፣ ብርብር እያሉ፡፡

ለማለት ያስደፍራል።

***

ካድሬ ማለት “የፋሲካ ዕለት የዶሮዎች ጩኸት የቀነሰው፣ መንግሥት ጥያቄያቸውን ስለመለሰ ነው" ብሎ ህዝብን ለማታለል የሚሞክር ነው።



መጽሐፉ ትንሽ ኮፒዎች በመደብራችን ይገኛል

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ለቅዳሜያችኹ !!!

ለዳኞች
ለጠበቆች
ለህግ ተማሪዎች
ህግን ለሚወዱ ሁሉ
በጠቅላላው ለህግ ባለሙያወች

የሚሆኑ መጻሕፍት !!!

ኤዞፕ የናንተው!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከሚጠኑ ጉዳዮች አንዱ
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤው ነገር ነው። አስቀድሞ ሐዋርያት፤
በኋላም ሊቃውንት በመጽሐፍ የጻፉት በቃል የሰበኩት ትምህርት በመሆኑ ተስፋ ለምናደርገው ለትንሣኤ ዘጉባኤ ምስክር ሆኖልን በአንቀጸ ሃይማኖት ምዕመናን ከሚደርሱበት ቅርብ ስፍራ ላይ ተጽፎ በሁልጊዜ ጸሎታችን ውስጥ “#ወንሴፎ #ትንሣኤ #ሙታን #ወሕይወተ #ዘይመጽእ #ለዓለመ #ዓለም" እያልን በተስፋ ስንጸልየው እንኖራለን። በዘመናት ሁሉ የሚነሡ የቤተ ክርስቲያን መምህራን በቃልም ሆነ በመጽሐፍ በተቻላቸው ነገረ ሃይማኖትን መስክረው ሊያልፉ ይገባልና

መምህር ናትናኤል ከመምህራን የተቀበሉትን እውቀት በዚህ መጽሐፍ በኩል ለቤተ ክርስቲያን ሲያበረክቱ አንብበው የሚጠቀሙ ተስፋ ትንሣኤን በልባቸው ይዘው በሃይማኖት ደስ የሚላቸውን ምዕመናን በማሰብ ልቤ በደስታ ይሞላል። ይህን ትምህርተ ትንሣኤን የሚሰብክ መጽሐፍ አንብባችሁ ትንሣኤ ልቡና ይደረግላችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው።
#ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

የአራቱ ጉባኤያት መምህር እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ

መድኅነ ዓለም ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን ከፅንሰቱ እስከ ዕርገቱ በሠራችው ሥራዎች ፈጽሟል። በዚህ የአድኅኖተ ዓለም ጉዞው የተከናወኑ የተዋሕዶ፣ የተገናዝቦ፣ የከዊን፣ የተዐቅቦ፣ የግብረ ቤዝዎ እና የግብረ አርአያ ተግባራት በጥንቃቄ የሚታዩ እና የሚተረጎሙ ምሥጢራት አሉባቸው። ቅዱሳን ሊቃውንት አባቶቻችንም እድሜአቸውን ያሳለፉት እነዚህኑ ምሥጢራት በተገቢው መንገድ በማብራራት ነው።

በተለይም ጌታችን ከተነሣ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ የተናገራቸው ቃላት እና የሠራቸው ሥራዎች
ለአንዳንድ ተጠራጣሪውች የማሰናከያ ደንጋይ ሁነውባቸው እስከ ዘመናችን ዘልቀዋል።
በመ/ር ናትናኤል ባየ የተዘጋጀችው እና በክርስቶስ ትንሣኤ ዙሪያ ትኩረቷን ያደረገችው
“መጽሐፈ ትንሣኤ ለመናፍቃኑ ተሰናክሎ ማሰናከያ የሆኑ ምሥጢራተ ተዋሕዶን
በማብራራት እና ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ በመስጠት ሁነኛ መፍትሔ ሁና አግኝቻታለሁ:: ኦርቶዶክሳውያንም ከኦርቶዶክስ ውጭ ያሉትም ቢያነቧት ላሉት መጽኛ ለጠፉት መገኛ ትሆናለች እና አንብባችሁ ተጠቀሙ እላለሁ።

መ/ር ኀይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አሉላ አባ ነጋ !!
ማሞ ውድ ነህ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የታላቁ ባለቅኔ ሎሬት ፀጋየ ገብረ መድህን መጽሐፍቶች
፩ እሳት ወይ አበባ
፪ ምጥቀት በቅኔ አክናፍ

በገበያ ላይ ውለዋል።

አከፋፋይ ኤዞፕ መጻሕፍት !!


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እኒያ ገራሚ አባቶቻችን ያዘጋጁት መዝገበ ቃላት ነው

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የሱባ ቋንቋ

❖ ሉባ፡- ማለት ሰብዕ/ሰው/ሰብአዊ የአማረ አበባ ማለት፤ ለሁሉም ቋንቋ ነባር አላቸው

❖ ነባር የምንለው የሚጠሩበት ስም የአባቶቻችን የአገርየወንዝ፤ ስም በቋንቋው እንዲሰየምና ስሙ ከቋንቋ በፊት ስለነበረ ነባር ይባላል፡፡

10 አናባቢ አስማተ መለኮት

33 ተናባቢ ፊደሎች ያሉት ድንቅ መጽሐፍ በቅርቡ ገበያውን ይቀላቀለዋል።






በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ይውላል



ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ መጽሐፍ ወደ ገበያው ተቀላቅሏል።
ሻሞ
ብሩክ በቀለ



ለውጥ ግዙፉ ቅስመ አፈጣጠር _ ነው። _ ሁሉ ይለዋወጣል። አዘገመም ፈጠነም። በአንድዬ ፈጣሪም ሆነ በሥነ ሳይንስ ቢዘወር_ _ሁሉ ከለውጥ አያመልጥም፡፡ እዚህም "ሻሞ" ብለን ዓለም ብንፈጥርበጊዜና በሁኔታ ተለውጦ እኛ ጋር በደረሰን እውቀትና መረዳት ነው። ከአንደበታዊ ተረት ነጋሪነት_ _ወድጽሕፈታዊ ተረት ነጋሪነት ተሸጋግረን ነው። የአንደበቱ ባይቀርልንም(ተፈጥሮ ነውና) በስልጣኔም _ እገዛ ደግፈን ልናኖረው_ _ጽሕፈትን ፈጥረን ጽሑፋዊ ትረካንና ተራኪን አስገኘን።

የ"ሻሞ"ን ልቦለዳዊ ዓለም ገንቢና ጊዜን ፈጣሪ _ _ ጓድ ብሩክ በቀለ ንጉሴም_ _ባልሟሟ አንደበታቸው ሲተርኩ የኖሩ ቢሆንም ነገረ ልቦለዳዊነትንም ይዘው _ጽሕፈታዊ ተራኪ ሆነው አስራ ስድት አጫጭር ልቦለዶችን ይዘውልን ተከስተዋል።

ዮሐንስ ሀብተማሪያም

Читать полностью…
Subscribe to a channel