ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21
Ibe Moral of the Story offers a remarkably effective approach that helps students
understand and evaluate moral issues. Through storytelling and story analysis,
using examples from fiction and film, Rosenstand brings classical moral theories to
life and shows students how these theories are applied to the world around them.
This sixth edlition has been thoroughly updated to reflect recent research, events,
and films. It also expands the applied ethics chapter to include the topics of media
bias, abortion, euthanasia, business ethics, and environmental ethics with emphasis
on the isue of global warming.
።በድጋሜ አንድ ኮፒ የተገኘች
እምየ አፍሪካ !!
ታሪክሽን ያላጠና
ያልፈተሸስ ማን አለ ?
እነዚህን ታላላቅ አፍሪካዊ ዶክመንቶች እነሆ !!
መዝሙረ ዳዊት እንዴት ተተረጎመ !!
የትርጓሜውስ ዋና ጥቅም ምንድን ነውና
የትርጓሜውም ፡ ዋና፡ ጥቅሙ ፡ምስጢሩን፡ ሳያውቁ የሚጸልዩበት' ምእመናን ፡ ምስጢሩን ፡ ዐውቀው ፡ እንዲጸልዩ ፡ ማድረግ ፡ ነው ።
የሚጠቅምና ፡ የሚያድን ፡ ሃይማኖት ፡ ቢሆንም ፡ ምስጢሩን ' ሳያ ውቅ ፡ የሚጸልየውን ፡ ሰው ፡ አበው ፡ በዐይነ፡ስውር፡ መስለው፡ «ዐይነ፡ ስውር ፡ በሚሄድበት ፡ ጐዳና ፡ ግራና ፡ ቀኝ ፡ በበትሩ ፡ እየዳበሰ ፡ ሲሄድ ፡ በቅርብ ፡ የሚገኙ ፡ አራዊት ፡ በትር ፡ መያዙን ፡ እንጂ ፡ ዐይነ ' ስውርነ ቱን ፡ ባለማወቅ ፡ እንደሚሸሹና ፡ እንደሚርቁ፤ አጋንንትና ' የክፉ ' ወ ገን ፡ የሆነ ፡ ሁሉ ፡ ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃሉ ፡ መናገሩን ' እንጂ ' የርሱን ፡ አለማወቅ ፡ ስለማይፈልጉ፡ ይርቃሉ፡ ብለዋል»፡ ሐዊ ።
ቢሆንም ፡ ምስጢሩን ፡ ሳያውቁ ፡ ከመጸለይና ፡ ከማንበብ ፡ ዐውቆ መጸለይና ፡ ማንበብ ፡ እንደሚበልጥ ፡ የታወቀ ፡ ነው።
ስለዚህ ፡ ይኸ ፡ መዝሙረ ፡ ዳዊት ፡ ከጥንት፡ አባቶች ፡ እንደ ፡ ተረ ጐሙትና ፡ ሲወርድ ፡ ሲዋረድ ፡ እንደ ፡ መጣው ፡ ንባቡና ትርጓሜው፡ ተጽፎና ፡ ታርሞ ፡ በግርማዊ ፡ ጃንሆይ ፡ ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ' ትእ ዛዝ ' በብፁዕ ፡ አቡነ ፡ ባስልዮስ ፡ ፈቃድ ፡ ባ፲፱፻፶ ' ዓ 'ም' ታተመ።
አባ፡ ቴዎፍሎስ ፡
የሐረር ፡ ጳጳስና ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሊቀ ፡ ጳጳሳት፡ ዋና' እንደራሴ"
የዓለማየው ዋሴ እሸቴ 7ኛ አዲስ መፅሐፍ #ፍካሬ ነገ ከሶስት ሠዓት ጀምሮ ከ ጥሩ ቅናሽ ጋር በመደብራችን ያገኙታል።
Читать полностью…ድንቅ አዲስ መጽሐፍ ብቅ ብሏል
ይነበብ !!!
እነሆ ከመጽሐፉ ለቅምሻ !!!
እግዜር ሸማኔ ነው።
ይሸምናል ሕይወት
ይቋጫል ነጠላ
ዳሩ አይመሰገን እጁ በሽመና
አዳውሮ መተርተር ልማዱ ነውና።
ይህ የእንጉርጉሮ ውዳሴ በሲጋራ ሽታ እና በሁካታ ድብልቅ በተሞላው ጠጅ ቤት ውስጥ በአንድ አዝማሪ ልሳን ለመለኮት የቀረበ ዝማሬ ነው፡፡ አዝማሪው ከሁካታው በላይ ድምፁን ጎላ አድርጎ እያንጎራጎረ፣ መሰንቆውን እየተጫወተ ዓይኑን ባዶው ቦታ ላይ ያንከራትታል፡፡
ግንባሩን ቁጥር እና አገጩን ከፍ አድርጎ ዙሪያውን ይገረምማል፡፡ በጠጅ ቤቱ ውስጥ የተሰባሰቡት በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎች አፍላአፍ ገጥመው ወጋቸውን መጠረቅ ይዘዋል፡፡ ልጅ እግሩ አዝማሪ ከሁሉም በላይ ድምጹን ከፍ አድርጎ ማንጎራሩን ቀጠለ፡፡ ድምፁ በሁሉም አቅጣጫ የሚያስተጋባ ኃይለኛ ቢሆንም የቅዳሜ ከሰዓቱን የጠጅ ቤት ግለት እና ሁካታ ማሸነፍ የሚችል አልነበረም፡፡
ይህ ልጅ እግር አዝማሪ ስሙ ጥጋቡ ይሰኛል፡፡ በጥንቱ ዘመን ነገሥታቱን ከሚያጫውቱ በትውልድ አዝማሪዎች ከሆኑ ቤተሰቦች ይወለዳል፡፡ አዝማሪዎች ለዘመናት ነገሥታቱን እና መሳፍንቱን የሚያገለግሉ፣ ፖለቲካውን የሚሸረድዱ፣ ለድሃው የልቡን በሰምና ወርቅ በዜማ አዋዝተው የሚናገሩ፣ የሰላ ማኅበረሰባዊ ነቀፌታ የሚሰነዝሩ አስቂኝና ቧልተኞች ብቻ ሳይሆኑ የማኅበረሰብ ሐያሲዎች ነበሩ፡፡
ለዘመናት ለዙፋኑ ቅርብ ሆነው አንዳንድ ጊዜም ከዙፋኑ ተጋፊዎች ጎራ ተሰልፈው የአጫዋችነቱን ሚና ወስደው ባህልን በማሳለጥ፣ በማጎልበት ሂደት ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡
ጥጋቡ ከጠጅ ቤት ወደ ጠጅ ቤት ይንከራተታል፡፡ የሰከሩ ደንበኞች ቢጎነትሉም ወይም ለዜማ ጥሪው ትኩረት ቢነፍጉትም በጽናት አዝማሪነቱን ቀጥሎበታል፡፡ መጀመሪያ የጨዋታ ማሟሻ ይሆነው ዘንድ ወዲያውም የአዝማሪነት ችሎታውን ለመግለጥ የእግዚአብሔርን ኃያልነት፣ የሕይወትን ኃላፊ ጠፊነት የሚያመሰጥር ግጥሙን በዘለሰኛ እንጉርጉሮ ለታዳሚዎቹ አቀረበ፡፡
ቀስ በቀስ ስልቱን እየለወጠ ወደ የፍቅር ዝማሬ፣ ጎንደር ከተማንና ጎንደር ያፈራቻቸውን ታላላቅ ሰዎች የሚያወዳድሱ እዚያው በዚያው የተሰናኙ ግጥምና ዜማዎች ወደ ማቅረብ ተሸጋገረ፡፡ ደንበኞች የቱንም ያህል በሚያቀርባቸው ዜማዎች ቢፈነድቁ አዝማሪው ግን ስሜቱን ገዝቶ መጫወቱን ይቀጥላል፡፡
-
-
-
-
(የፒያሳ ቆሌዎች፣ የአዝማሪው እግዚኦታ፣ ገጽ 27-28)
ተጻፈ፣ በኢተሱሺ ካዋሴ (ዶ/ር)
ትርጉም፣ በያዕቆብ ብርሃኑና ዓለማየሁ ታዬ
በጉባኤ ቤት መኖር ደስ የሚያሰኘው በየዕለቱ አዲስ አዲስ ሰው ተፈጥሮ ስለሚያድር ነው። በአትክልት ስፍራ ብትኖሩ በየጊዜው ፍሬ የሚሰጡ፣ በመዓዛቸው ልብን የሚመስጡ ዕፀዋትን ልትመለከቱ ትችላላችሁ በዚህ
ከምትደሰቱት በላይ በየዕለቱ እግዚአብሔር ሰው ሲሠራ የምትመለከቱበት ቦታ ስለሆነ በጉባኤ ቤት የመኖርን ጣዕም ብትቀምሱት ደግሞ ከዚህ በላይ በጣም ትወዱታላችሁ። እኛ የተከልነውን፣ ያጠጣነውን እግዚአብሔር ደግሞ ዕለት ዕለት ያሳድግ ነበርና ይኸው ዛሬ ማደጉን የሚያስረዳ ፍሬውን አንዥርግጎ መታየት ከጀመረ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በመገብተ ኦሪት የቀመስነውን ፍሬ ደግመን እንድናጣጥመው ይዞልን ብቅ ብሏል። እንደ አባቶቹ ወምበር ተክሎ ጉባኤ አስፍቶ ያስተማረ በዐውደ ምሕረትም አንደበቱ የሚጣፍጥ የተወደደው ወንድማችን መምህር ምሥጢሩ ታየ ዛሬ በነገረ እግዚአብሔር ላይ ከመምህራን አፍ፣ ከከርሠ መጽሐፍ የሰበሰበዉን ቤተ ክርስቲያን ስለ ነገረ እግዚአብሔር የምትሰብከዉን ቃል በመጽሐፍ ይዞልን በመምጣቱ እያመሰገንሁ ለአንባብያን ደግሞ ቆላ ሳንወርድ ደጋ ሳንወጣ በቆላና በደጋ በሩቅና በቅርብ ያሉ መምህራን ያስተማሩትን በልዩ ልዩ ቋንቋ የተጻፉ መጻሕፍት ለዘመናት በውስጣቸው የተሸከሙትን የሕይወት ቃል ቤታችን ድረስ ስለመታልን በምስጋና ሁሉም እንዲያነበው እጋብዛለሁ። ጣዕም የሕይወት ስንቅ ይዞልን ስለመጣ ሁላችንም እጃችንን ዘርግተን እንድንቀበለው እጠይቃለሁ!
#ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
ይህ “ትምህርተ እግዚአብሔር ዘኦርቶዶክስ” በሚል ርእስ በመ/ር ምስጢሩ ታየ የተዘጋጀው መጽሐፍ፣ ስለ እግዚአብሔር አምላክነትና አሠራር እንዲሁም ስለ ሌሎች መሰል ጉዳዮች ልናውቃቻው የሚገቡ መሠረታ ሐሳቦችን የያዘ መጽሐፍ ነው። የሚያነሣቸውን ሐሳቦችም ኦርቶዶክሳዊ በሆነ ይዘትና ውበት ባለው የሥነ-ጽሑፍ ለዛ የሚያብራራ ጥሩ መጽሐፍ ነው። መ/ር ምስጢሩ ታየ ይህን መጽሐፍ ጽፈው ስላበረከቱልን ከልብ እያመሰገንብ
፣ ይህን መጽሐፍ ብታነቡ ትጠቀሙበታላችሁና ጊዜ ሰጥታችሁ ታነቡት ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ።
ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
የአርኖ ሚሼል ዳባዲ ‹‹በኢትዮጵያ ተራሮች ቆይታዬ›› ሶስተኛ ክፍል በገነት አየለ አማካይነት ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ቀርቧል፡፡ ከዚህ ቀደም ሁለቱን ክፍሎች ለአንባቢያን ያቀረበችው ታዋቂ ደራሲና ጋዜጠኛ በዚሁ ጥረቷ በርትታ ሦስተኛውን መጽሐፍ በአሁኑ ህትመት አቅርባልናለች፡፡
በዚህኛው ክፍል ላይ አርኖ ዳባዲ ከበጌምድር እስከ እናርያ ድረስ ያካለለውን ጉዞውን ያስቃኘናል፡፡ በ19ኛው መ/ክ/ዘ አጋማሽ ላይ ወደ መቋጫው እየቀረበ የነበረውን የ‹‹ዘመነ መሳፍንት›› የአውራጃ ገደም የፖለቲካ ስልጣን ሽኩቻ፤ በጎጃም፤ በጌምድር፤ ስሜንና ትግሬ በመሳሰሉት አውራጃ ገዢዎች መካከል የነበረውን እጅግ ተለዋዋጭ የትብብርና የፉክክር ግንኙነት፤ ካየውና ከሰማው ጋር በማስተጋበር ያቀርበዋል፡፡
በነገሥታቱ መናገሻ ጎንደር ከተማ በነበረው ቆይታ የአውራጃ ገዢዎች ጡንቻ ፈርጥሞ፤ ንጉሠ ነገሥቱን አሻንጉሊት አድርገው የነበሩትን የወረሴህ ሥርወ-መንግስት ጉልኃን የአስተዳደር ዘይቤ፤ የቤተ-መንግሥት ዋና ዋና የፖለቲካና ወታደራዊ ሁነቶች እንዲሁም በአስተምህሮ ልዩነት ውስጣዊ አንድነቷ ላልቶ የነበረውን ቤተ-ክርስቲያን ሁኔታ ያስረዳናል፡፡ በቆይታው
የተዋወቃቸውን ግለሰቦችና ማህበረሰቦች ማህበራዊ፤ ኃይማኖታዊ፤ ባህላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ስሪቶች ከጎንደር አማራዎች እስከ ጉዱሩ እና እናርያ ኦሮሞዎች ድረስ ያስቃኘናል፡፡ የወጣ የወረደበትን ተራራና ሸለቆ፤ የዱር አራዊት ዝርያዎች በልዩ ትኩረት መዝግቧቸዋል፡፡
መጽሐፉ በአማርኛ ተተርጉሞ መቅረቡ ለኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪዎችና አንባቢያን ያለው ፋይዳ የጎላ ነው፡፡ ለታሪክ፤ ሥነ-መለኮት፤ አንትሮፖሎጂ፤ ሶሲዮሎጂ እና መሰል ምርምር ዘርፎች ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን ይዟል፡፡ ከዚህ በፊት በፈረንሳይኛ ቋንቋ ክህሎት
ውስንነት የተነሳ ይህንን የሚሼል ዳባዲን ስራ ማንበብ ላልቻሉ ሁሉ መልካም ዜና ነው፡፡ ከትርጉም ባሻገር ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችና እርምት የሚፈልጉ ግድፈቶችን በግርጌ ማስታወሻ ላይ ማብራሪያ በመስጠት የታሪክ እውነታን ለማጥራት ጥረት የተደረገ ሲሆን ይህም ተርጓሚዋን ያስመሰግናታል፡፡ በመጨረሻም በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ መምጣት ዋዜማ የነበረችውንና በፖለቲካና ሀይማኖታዊ ውጥረቶች ውስጥ የከረመችውን ኢትዮጵያን ለመቃኘት የሚፈልግ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ ቀዳማይ የታሪክ ሰነድ ነው።
አውግቸው አማረ (ፒ ኤች ዲ)
የታሪክ መምሕርና ተመራማሪ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
...የአለምን ጣዕም። ከሞት በፊት ያየው አለም፣ በኋላ ከሚመጣው እንደሚሻል ባያውቅ እንደዚህ ህይወቱን የሙጥኝ ባላለ ነበር ብሎ አሰበ።ግን እሱ ነው ህይወቱን የሙጥኝ ያለው ወይንስ ህይወቱ እሱን? ህይወት እንደ እምነት ነው። ሳትፈልገው ይዞህ ሊቆይ አይችልም...።
ግን የአባቱ አደራ አለበት። የአባቱ አደራ ያን ያህል ገዶት ወይንም አጥንታቸው ወግቶት ሳይሆን፤ ከሞት በኋላ በወዲያኛው አለም ሲያገኙት የማይለቁት ስለሚመስለው ነው። ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ ያምናል።
ፅድቅ እና ኩነኔ በሚባል መደብ ግን እንደማይከፈል እርግጠኛ ነው። ሁሉም አንድ ቦታ ላይ ሄደው እንደገና ይከማቻሉ ብሎ ነው የሚያምነው። የሚያምነው የመሰለውን ነው። ያጠፋም ያለማም አንድ ላይ፡፡ ማጥፋት እና ማልማት ራሱ ፖለቲካ ነው ለሱ። ራሱን የቻለ እውነት አይመስለውም፡፡ የፈለገውን ካደረገ ለእሱ በቂው ነው። ማስመሰል እና መሸወድ የቻለ ንፁህ
ነው። የተነቃበት ደግሞ ጥፋተኛ። በሃይል አይደለም የሚመጣውን ጓጉቶ የሚጠባበቀው። ከሚመጣው ይልቅ የጨበጠውን ያምናል። ተስፋ የደሀ ህልም እንደሆነ ነው የሚያምነው። ከህይወት በኋላ ፅድቅ እና ኩነኔ ብሎ
ነገር አይዋጥለትም። በህይወትም መስዋአትነት ለምንም ነገር አይከፍልም፡፡ወቀሳ አልባ እንዳሻው የሚሆንበት ህይወት። ከሞት በኋላም ያው ነገር ይቀጥላል ብሎ ነው የሚጠብቀው። ግን ለዘላለም ያህል ረጅም ጊዜ ሆኖ
ተለጥጦ።
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ልዩ ዕትም
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- /channel/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
Ibe Moral of the Story offers a remarkably effective approach that helps students
understand and evaluate moral issues. Through storytelling and story analysis,
using examples from fiction and film, Rosenstand brings classical moral theories to
life and shows students how these theories are applied to the world around them.
This sixth edlition has been thoroughly updated to reflect recent research, events,
and films. It also expands the applied ethics chapter to include the topics of media
bias, abortion, euthanasia, business ethics, and environmental ethics with emphasis
on the isue of global warming.
ስለ መጽሐፉ በጥቂቱ
ይህ ብሩህ ዐይን የተሰኘው መጽሐፍ ኹሉን አቀፍ መጽሐፍ ነው፡፡ በውስጡም ነገረ ድኅነትን፣ ነገረ ሰብእን፣ ነገረ ሥጋዌን፣ የሰውን ልጅ ውድቀት እና ከውድቀት መዳንን፣ ዕፀ በለስን ከዕፀ መስቀል
ስለ ነጻፈቃድ እና አጠቃቀሙ
ሔዋንን ከእመቤታችን፤ እባብን ከመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል፤ አዳምን ከፈያታዊ ዘየማን
የእግዚአብሔርን ድምፅ በገነት ለአዳም እና በመስቀል ለፈያታዊ ዘየማን፤ የዲያብሎስን ክፋት ከኩይናተ ለንጊኖስ እያነጻጸረ ያስተምራል ሌሎችንም ዘርፈ ብዙ እና መሠረታውያን ሐሳቦች እያነሣ ያብራራል፡፡ ለማመላከት ያክል ይህን ካልኩ ሌላውን ገብታችሁ አንብቡት፤ እያልኩ በዚህ ሥራ ውስጥ ብዙ ክፍተት እንደሚኖር አምናለሁ፤ ነገር ግን ችግር ይኖራል ብዬ ከምቀመጥ እኔ ሞክሬው እናንተ የጎደለውን ሞልታችሁ የጠመመውን አቅንታችሁ ብታነቡት ስል ጋበዝኳችሁ፡፡ ለምትሰጡኝ አስተያየት ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡
Africa is mired in a range of intra- to inter-state
conflicts, caused by the fragile nature of the African
states, endemic poverty, economic inequality and
exclusionary governance systems that do not allow
participatory political arrangements.
The 17 essays of this book address the ongoing
conflicts in Africa and present solutions for overcoming
these conflicts and sustaining peace. Topics discussed
include the sources, management, resolution, and
prevention of conflict; building democracy; and the
necessary public policy reforms throughout the African
continent.
The discoveries made in these essays provide a
useful and novel approach to the promotion of peace
in an African and international context. The book is
a must read for everyone concerned with peace and
conflict studies.
International Books
with OSSREA
ISBN 90 5727 049 8 (PB)
1SBN 90 5727 051 X (HC)
The essays were first presented at the seventh Organ-
ization for Social Science Research in Eastern and
Southern Africa (OSSREA) congress in December 2002.
The editor, Dr. Alfred G. Nhema, is the Executive
Secretary of OSSREA.
"The Quest for Peace in Africa challenges orthodox
views on the relationship between development
democracy and public policy in Africa. The book
offers fresh insights, first hand materials and accounts
collected and analyzed by African scholars with a
distinct African perspective. A superb contribution to
the literature on African conflict and democracy.
M.A. Mohamed Salih, professor, Institute of Social
Studies, The Hague, and the Department of Political
Science, University of Leiden, The Netherlands.
ይህንን አጭር መልዕክት እስኪ በጽሞኔ አንብቡልኝ !!!
................... አንኪ የእኔን ምቾት ማጣት ችላ ብሎ እየተሳሳቀ፣ እየተቀላለደ በዚሁ አካባቢ ስለሚወሩ ሃሜቶች፣ በቀጣይ ስለሚሰራው የሙዚቃ ድግስ ያወጋል፡፡ ሰዎቸን በአማርኛና በትግርኛ ላዋራቸው ብጥር ስንኳ ጠበኛ አተያያቸው ሊቀየር ቀርቶ የቤቱ ከባድ የሚጫን ድባብ ሊቀረፍልኝ አልቻለም፡፡
‹‹ኢትዮጵያ መኖር ለምን ፈለክ?››
‹‹ኢትዮጵያ ምን ስትሰራ ነበር?››
‹‹ሰላይ ነህን?››
ወደዚህ ቦታ በመምጣቴ ብጸጸትም ተንኮል ያዘሉ ጥያቄዎቻቸውን አንድ በአንድ በትህትና መለስኩ፡፡
ሌላጊዜ በዚሁ ዋሺንግተን ‹ዩ› ጎዳና የስታርባክስ ቡና መጠጫ መዝናኛ ዓይቼ ለመግባት ስንደረደር አንኪ ‹‹ ተው ባክህ ይህ ቤት ቱሪስቶችና መጤዎች የሚያዘወትሩት ካፍቴሪያ ነው፡፡›› ብሎ አስቆመኝ፡፡
‹‹እና አንተ በዚህ ሀገር ምንድን ነህ?›› ብዬው ዓይን ለዓይን ተያይተን ተሳሳቅን፡፡
ከአንኪ ጋር ያሳለፍኳቸው አስደሳች ጊዜያት በፍጥነት አለፉ፡፡ ‹ዩ› ጎዳናን የምሰናበትበት ጊዜ ደረሰ፡፡ ወፍ ነኝ፡፡ እንደወፍ እሄዳለሁ፡፡ ከመሬት ወደ ሰማይ እንደምትበር ወፍ እሄዳለሁ፡፡ ይሄ የጎንደሬዎች የስንበት መንገድ ነው፡፡ ጎንደሬዎች ለወዳጅነት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፡፡ ለሰው በማዘንም የሚያህላቸው የለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጎረቤቶቻቸው ጉዳዮች ጭምር ከጉዳዩ ባለቤቶች በበለጠ ተጠምደው ሲጨነቁ ይገኛሉ፡፡ እናስ ይሄን መሰል ወዳጅነትን በቀላሉ አንደ ድንገት ማቋረጥ ይሆንላቸዋልን? ከጊዜያት በኋላ በጥብቅ ወዳጅነት አንዱ የአንዱን ስሜት በቀላሉ እስከመረዳት የደረሰ መቀራረቡ የጠነከረ መተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ እናም ከመለያየት በፊት መዓድ መጋራት የግድ ነው፡፡ ምናልባት የሚሄደው ሰው የስንብት ንግግር ያደርጋል፡፡ ጊዜው ሲደርስ ውልቅ ነው፡፡ በወዳጆች መካከል ምንም የተንዛዛ ምስጋና አስፈላጊ አይደለም፡፡
እና በዚያ ምሽት አንኪ ዘወትር በየሣምንቱ ወደ ወደሚጫወትበት ባር ጎራ አልኩኝ፡፡ ብዙ ውለታ የዋለለኝ ሰው ደህና ሁን ብዬ በቀጥታ ወደ ኤርፖርት ለማምራት ነበር እቅዴ፡፡ ግን ምንም ያህል ሰዓት ብጠብቅ አንኪ ብቅ ሊል አልቻለም፡፡ አስተናጋጇን ‹‹አንኪ ዛሬ የቀረው ምን እየሰራ ነው›› ብዬ ጠየኳት፡፡ አንኪ በሳምንት ለተወሰኑ ቀናት ‹በመኪና ጥበቃ - ፓርኪን ሎት› ውስጥ እንሚሰራ ሊነግረኝ አልፈለገም ነበር፡፡ ከሙዚቃ ስራው ጎን ለመኖር ሲል የትርፍ ሰዓት ስራዎች እንደሚሰራ ለእኔ መናገር ሀፍረት ሆኖበታል፡፡
ከባሩ ወጥቼ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ቸግሮኝ ‹በዩ› ጎዳና ስወዛወዝ አንኪ ከየት መጣ ሳይባል ድንገት ፊቴ ተደቀነ፡፡ ዓይኖቹ አንባ አቅርረዋል፡፡ ምንም ሳይናገር ጥቂት የአሜሪካ ገንዘብ ኖቶችን ወደ ጃኬቴ ኪስ ሸጎጠልኝ፡፡ ምናልባትም በእጁ ላይ ያለውን ገንዘብ በሙሉ ይሆናል የሰጠኝ፡፡
‹‹አይ አይ ግድ የለህም፡፡ ይሄ ገንዘብ ለእኔ አያስፈልገኝም፡፡››
‹‹ግድየለህም! ያስፈልግሃል ያዘው፡፡››
‹‹አይ አይ በጭራሽ አይሆንም አልቀበልህም፡፡››
‹‹እሺ በለኝና ያዘው..››
የፒያሳ ቆሌዎች፡
የመሰንቆው ንጉሥ ገጽ 130 -132
ተጻፈ፣ በኢተሱሺ ካዋሴ (ዶ/ር)
ትርጉም፣ በያዕቆብ ብርሃኑና ዓለማየሁ ታዬ
መጽሐፉን በመደብራችን በጥሩ ቅናሽ ታገኙታላችኹ!!!
የመንገድ መልኮች - የፒያሳ ቆሌዎች
(ምጥን ዳሰሳ ላይ የተቀነጨበ -
በውብአረገ አድምጥ)
የፒያሳ ቆሌዎች ውስጥ የተካተቱት ከህይወት ቅምምስ የተቀዱ 17 ታሪኮች የመንገድ ውጤት ናቸው። ራሳችውም መንገድ ናቸው። የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ካዋሴም መንገደኛ ነው። ከጃፓን ኢትዮጵያ፣ ከእንግሊዝ አሜሪካ ከጀርመን ካናዳ እያለ የሚከንፍ።
ባለፉት አርባ ዓመታት እኛ ስለሩቅ ምስራቋ ጃፓን ስናቀነቅን ነበር። ሩቅ ምስራቅ ሳለሁ ጃፓኗን ወድጄ እያልን ዘምረናል። ተያይዘን በዝማሜ ወደማናውቃት ጃፓን በሃሳብ ተጉዘናል። የጃፓኑ መንገደኛ ዶ/ር ካዋሴ በጎንደር ፒያሳ ጎዳናዎች ተመላልሶ የከተበውን መልካችንን አስነበበን።
ካዋሴ ከሳሙራዮች ሀገር መጥቶ ስለ ቴዎድሮስ ጀግንነት አንዳች የሚለን የለም። ስለ ገብርዬ ታማኝነት ትንፍሽ አይልም። ስለ ፋሲለደስ ግንብ ውበት፣ ስለ ርብ፣ አባወርቄ፣ ጉማራ ወንዞች ጸባይ አንዳች አይናገርም። ስለ አርባራቱ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክና ተዓምር፣ ስለ እነ እቴጌ ምንትዋብ አመራር፣ ስለ እነ ተዋበች ውበትና ታማኝነት ተሳስቶ ለመመስከር አይዳዳም።
እና ምኑን ስለ ጎንደር ጻፈው ብሎ መጠየቅ ይቻላል። ካዋሴ መልስ አለው።
ከፒያሳ መንገድ ዳር፣ ከኢትዮጵያ ሆቴል ክፍል 11 ውስጥ ሆኖ ዙሪያውን የሚርመሰመሱ የእኛው መልኮቻችንን አብጠጥሮ አሳየን እንጂ። ምክንያቱም ሰውየው አንትሮፖሎጂስት ነው። ካሸበረቁ የድንጋይ ፎቆች፣ በጉልበተኛ ከተጻፉ ገናን የጸሐፌ ትዕዛዝ ታሪኮች ይልቅ ሰው መሆን ከጎዳና ላይ እንደ ውሃ ይፈቀዳልና፡፡ በቀላጤ አፍ ከሚነበነቡ የሰርክ ጀብዱና የተለመዱ ትርክቶች ይልቅ ያልተጻፈው፣ ያልተብራራው፣ ልብ ያልተባለው፣ ለውውይትና ለዲስኩር ያልቀረበው፣ ማህበረሰብን ግጥም አድርጎ ያሰረው ስውር ገመድ ቸል ባልነው ህይወት ውስጥ ተሰግስጎ ይገኛል።
አንድን ማህበረሰብ ለመረዳት የታሪክ መዛግብትን ማገላበጥ ትክክልኛ መልኩን ላያሳይ ይችላል፡፡ ማህብረሰብ እንደ ማህብረሰብነቱ፣ ሀገር እንደ አብነቱ ይቀጥል ዘንድ ትውልድን ለመተለም ተስፋ የሚደረግባቸውን ሴትና ህጻናትን የሚመለከትበትንና የሚይዝበትን መንገድ ማየት ይበቃልና፡፡ የዛሬና የነገ እናቶቿን በትና፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናቶቿን ለጎዳና አስረክባ ሰው የምትሰራ ሀገር አናውቅምና፡፡ ይሄ ክሽፈታችን፣ ይሄ መርገምታችን በፒያሳ ቆሌዎች በደማቁ ተጽፏል፡፡ ዳሩ ዛሬም እንደተጣባን ነው፡፡ ያውም ባይብስበት፡፡
እንዲሁም ከመይሳው ሽፍትነትና ንግስና ይልቅ የአቱ የጎዳና ላይ ህይወት እልፍ ይናገራል። በዱልዱም አንደበቷ አንቱ ለማለት አቱ እያለች ጡቶቿን አውጥታ የዕለት ጉርስ የምትለምነዋ አቱ የእኛን መልክ ትወክላልች። እሱን መልክ ካዋሴ ጻፈልን። አንቱታን ያላስጣለ፣ ማክበርን ያላስወለቀ እብደት እኛን ይገልጻል፡፡ ከገብርየ መታመንና ቀድሞ መውደቅ ይልቅ በካውሴ የማስታወሻ ደብተር ላይ በዘፈቀደ የሚሳሉት አብስትራክት የህጻን ሙሉ ዘንዶዎች፣ የቃልኪዳን ዘዮሐንስ ሙንጭርጭር የስዕል ንድፎች የተሸከሙት መዓት ትርጉም አለ።
ከእነ ምንትዋብ የመሪነት ጥበብ ባልተናነሰ መቶዎች ብሮቿን ተሰርቃ ቦርሳዋ ሲመለስላት በምርቃት የተቀበለች እናት ያስተሳሰረንን ክር ታስመለክታለች፡፡ ይሄ ሁሉ ታሪክ ከዚህ መጽሐፍ አለ፡፡
ለምንና እንዴት ብሎ ለመመለስ በሚያስቸግር መልኩ ከፒያሳ ንጥፍ ጎዳና ላይ ተዘርተው ለተገኙት ባካና ነፍሶች ካዋሴ “የጸሐይ ቅምጥል” በሚለው መጣጥፉ እንዲህ ሲል ጥብቅና ይቆምላቸዋል።
“ለመሆኑ አንተ እና መሰሎችህ የጎዳና ልጆች የመጣችሁት ከየትኛው ዓለም ይሆን?” ሲል ይጠይቃል። ሌት በቁር ቀን በሀሩር ከፒያሳ ጎዳናዎች ጥግ ላይ ሲመናተል እየዋለ በጭቃ ለተለወሰ ድመት ቤት ለመስራት ደፋ ቀና የሚለው የካንጋሮ ድርጊት ህሊናን ይቆረቁራል። ካዋሴ ይሄን ትዝብቱን እንዲህ ይገልጸዋል።
“ቤት አልባው ካንጋሮ በጎዳና ላይ እየኖረ ነገር ግን ለተጣለ ለተረሳ፣ የመነመነ ድመት በጭቃ ተለውሶ ቤት ሲገነባ ማየት በጣም አስቂኝ ነበር። ካንጋሮ እንደዚያ ጊዜ ደግ ሆኖ አይተኸው አታውቅም ” ይላል። ምን ወቅት ቢከፋ መገለጫዋ እንደ ሞኝነት የሆነች ደግነት የሰው ልጆች ሁሉ የወል ባህርይ አይደለችምን ብለን እንጠይቃለን።
ለፒያሳ መንገዶችና ለጎንደር አዝማሪዎች ሸሪክ የሆነው ካዋሴ ጎንደርን በጎንደሬ ሳይሆን በጃፓን ዓይን አያት። አዋዋሉና ነገረ ስራው ጎንደሬ ሆነ። አይኑ ግን ጃፓናዊነቱን አልለቀቀም።
-
-
-
የፒያሳ ቆሌዎች
ተጻፈ፣ በኢተሱሺ ካዋሴ (ዶ/ር)
ትርጉም፣ በያዕቆብ ብርሃኑና ዓለማየሁ ታዬ
…በእድሜ ዘመኑ ሌላው ቀርቶ የዚህን ጫካ ወለል ምን እንደሌለው፣ ምን እንዳለው እንኳን አይቶት የማያውቅ፤ ጨርሶ ስለኛ የማወቅ ፍላጎት የሌለው እኮ ነው፡፡ ንሥር እኮ በእኛ ላይ የሚኖር፣ ከእኛ ጋር ግን የሌለ፤ ለእኛ ቅርብ የሆነ፡ ከእኛ ግን ሩቅ የሆነ ፍጥረት መሆኑን አታውቅምን?…..'
'…..እንደምታውቁት ተፈጥሯችን ከአንድ ቦታ ተተክለን እንድንኖርያስገድደናል፡፡ ይህ ውብ ተፈጥሯችን ግን የተለየ ጸጋ ነበር፡፡ ፈጣሪ ከአንድ ቦታ ተተክለን እንድንኖር አድርጎ ሲፈጥረን ትልቁ ምሥጢር ችግር መፍታት እንጅ ችግርን መሸሽ ተፈጥሯችን እንዳልሆነ ሲያጠይቅ ነበር…. እኛ እንደ እንስሳት ችግር በመጣ ጊዜ እየፈረጠጥን ከአንዱ ወደ አንዱ ልንሄድ አይገባንም፤ አያስፈልገንምም…….'
-መቸም እኛ ዕፅዋት … ነፋስ በነፈሰ ቁጥር መወዛወዛችን የነበረና ያለ ነው፣ ወደፊትም የሚኖር ነው…. ዕፅዋት ልብ በሉ! የምንወዛወዘው ከነፋስ ጋር አላስፈላጊ ግብግብ ላለመግጠም እና ትንሽ አወዛውዞን አልፎ እንዲሄድ እንጅ ከሥራችን እንዲነቅለን አይደለም፡፡
'…..ታምሚያለሁ ብሎ ያላመነ መድኃኒት አይሻም፤ በህመም ያልተሰቃየም በፈውስ አይደሰትም! ጤነኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ባለ መድኃኒት ይፈልጋልን? አዋቂ ነኝ የሚልስ መካሪ ይሻል?........
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
ታላቅ ዝክር !!
ታላቅን ማክበር!!
አንጋፋዎችን መዘከር !!!
ተጠርታችኋል።
አይቀርም፣ጋሽ አስፋው ዳምጤ በብሄራዊ ቲያትር አዳራሽ ዘጠናኛው ዓመታቸውን ምክንያት በማድረግ ይዘከራሉ።
ታላቅ ሥነጽሑፋዊ ድግስ !!!/
አይቀርም !!!
ኤዞፕ መጻሕፍት !!!!!
መጻሕፍትን የማመሥጠር አቅማቸው፣ ሰብእናን ሳይነኩ ሐሣብን በሐሳብ የመሞገት ትጋታቸው፣ ነገሮችን የመረዳትና ሕገ-አመክንዮን ሳያፋልሱ የመተንተን አቅማቸው፣ ባገራችን ያሉ ልዩ ልዩ ሃይማኖታውያን ክርክሮችን የሚረዱበትና ይትባህላቸውንም የአንዱን ከአንዱ ሳይደባልቁ በጥንቃቄ የሚገልጡበት ዘዴ፣ ለቀደሙት አበው ያላቸው አድማስ-የለሽ ፍቅርና ተቆርቋሪነት፣ ለተተኪ ወጣቶች ያላቸው ስስት፣ በ1920ዎቹ በሀገር ላይ ያንዣበበውን አደጋ የተረዱበት መንገድ፣ በ1950ዎቹ ላይ ሆነው በሃይማኖት ብረዛና ክለሳ ረገድ ትውልዱ የተጋረጠበትን መጻኢ ፈተና ተረድተው በቅኔያትና በመጽሐፍ የመቱት የንቃት ደወል፣… ሁሉም አስደናቂ ነው፡፡ በእርግጥም ቅድስናውንና መንፈሳዊውን ሕይወት ሳይለቁ ዘመናቸውን በመረዳት በኩል ከፊት ቀድመው የሚገኙ አብነትነት ያላቸው ሊቅ ጥራ ብባል በትምክህት የምጠራቸው መልአከ ብርሃን አድማሱ ናቸው፡፡ እናም እኒያን ሁለት ክፍለ ዘመናትን ከሁለት ትውልድ አጋምደው ያለፉ ርጉዕ ሊቅ ባረፉበት የ፶ኛ ዓመት ዋዜማ ላይ ቆመን ከሥራዎቻቸው ጋራ መዘከራችን ክብሩና ረድኤቱ ለእኛ እንጂ ለእርሳቸው አይመስለኝም፡፡
በአማን ነጸረ
#ደብተራና የሕግ ባለሙያ
አድማሱ ጀንበሬ ከዘመናቸው ሊቃውንት ውስጥ
ፈርጥ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ዘመን ከነበሩ ሊቃውንት ጋር ሊጠሩ ሊመደቡ የሚችሉ መሆናቸውን ሥራዎቻቸው በግልጽ እንደሚመሰክሩ አምናለሁ። ሃይማኖታቸውን፣ የሃይማኖታቸውን አስተምህሮ፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ምስክርነትና እውነተኝነት ጠንቅቀው ያውቃሉ። የተችወቻቸውን ሀሳብም ነቅሰው ይረዳሉ፡፡ ለሁሉም እውነትን ብቻ መሠረት አድርገው መልስ ይሰጣሉ፡፡ የሚከራከሩትን አካል ያከብራሉ፡፡ በታሪካቸው አይመጻደቁም። ለማንም
ተገቢውን ክብር አይነፍጉም፡፡ ከዐውድና ከጭብጥ በፍጹም አይወጡም፡፡ በምንም ዐይነት መሥፈሪያ ጎድለው ሊገኙ አይችሉም፡፡ እርሳቸው ራሳቸው ለፍጹምነት ሲጋደሉ ስለኖሩ ሥራቸውም ፍጹምነት እንዲያገኝ ከአምላካቸው ተችረዋል ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህም ይህን መጽሐፍ አለማንበብ በእውነት ያጎድላል። ይልቁንም ይህን አንብበን ሥራዎቻቸውንም ደጋግመን አንብበን ዕውቀትን ብቻ ሳይሆን የእርሳቸውንና የመሰል ሊቃውንትን የጸጋና የመዐርግ ዕርገት እንደ ኤልሣዕ በእምነት አይተን የበረከት ዐጽፋቸውን በእምነት እንቀበል ዘንድ አሳስባለሁ፡፡
መምህር ብርሃኑ አድማስ
በፊሎሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ)
Copy Print
ከመጽሐፉ የተወሰደ
‹‹ሰው እንዲህ ነው ማለት ይቻላል የኔ ልዥ? ዕድሜህ እየገፋ ሲኸድ ዝጌር ተፈጠራቸው መሀል ሁሉ ሚስጥሩ ሰው እንደሆነ ትረዳለህ። የምንደራችን ሰዎች እርስ
በርስ እየተላለቁ ምንደራችንን የወላድ መካን አርገዋል። ወንድም ወንድሙን ጭምር እየገደለ ሞትን ንቀዋል። ካወቁ ግና ሞት አይናቅም። ጦር ሜዳ ላይ ሞት የሰውን ልዥሲንቅ አይቻለሁ።››
ያንን ሰፊ የጦር አውድማ፣ ያንን ገላጣ መሬት የከበቡትን ተራሮች አንድ በአንድ አየና ግዝፈታቸው አስፈራው፤ ግርማ ሞገሳቸው አክብሮት፣ አድናቆትና ፍርሐት ጫሩበት። በነሱ ፊት ከሰናፍጭ ያነሰ መሆኑ ታወቀው። ‹‹ተይመር ወዲያ››የሚለው ፈሊጡ ብልጭ አለለት፤ ልኩን አለማወቁን ጠቆመው። አቀረቀረ።
እንደገና ቀና ብሎ ያንን ከሠዐታት በፊት ለምለም የነበረ መሬት አየው፤ጠፍ ሆኗል። ሰማዩ በመድፍና በጥይት ጭስ ጠቁሯል። የባሩዱ ሽታ አፍንጫ ይሰነፍጣል።
በየቦታው ሬሳቸው የተዘረረው ፈረሶችና በቅሎዎች ያገልግሎት ዋጋቸው ያ መሆኑ አሳዝኖታል።
ዙርያውን ያየው ውድመት በውስጡ የሆነ ነገር አርግዟል። ‹‹ምንዲነው? የሆነ ነገር አርግዟል?›› ሲል ጮኸ። የዓድዋን ተራሮች በዐይኑ አዳረሳቸው፣ ‹‹አዎ
ያረገዘው ድል ነው!‹‹ ሲሉ ሰማቸው።
የድል መዓዛ አወደው! መሬት ሳመ።
ኤዞፕ የእናንተው የምንግዜም ቀደምትና ምርጥ መጽሑፍት ምርጫ !!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21