ማነው ናቅፋን የያዘውና እንዳለ ያለቀው ሠራዊት ሦስተኛ ክ/ጦርና 17ኛው ክ/ጦር አይደለም እንዴ ? አይው የ3y h/me sur ኰለኔል ተሻገር ይማም ይባላል፡ የጐንደር ልጅ ነው፡፡ የ17ኛው ክ/ጦር አዛዥ ኩለኔል መኮንን ወልዴ ይባላል፡ ጠና ያለ መኰንን ነበር፡፡ የግንባሩ አዛዥ እዛው በጦሩ ፊት የተሾመ ወጣት መኰንን ጄነራል ውበቱ ፀጋዬ ይባላል፡፡ እነኚህ ናቸው የተሰጣቸውን መመሪያ በትክክል ሥራ ላይ ያዋሉት፡፡ በስልት በጣም አስቸጋሪ በሆነ የተፈጥሮ አቀማመጥ ላይ ዳገት ቧጠው ጠላት ላያውቅና ሳይነቃ ደርሰው ዱብዕዳ ተኩስ ነው የከፈቱበት፡፡ ጠላት ቁርበቱን ጠቅልሎ ናቅፋን ለቆ ለመሸሽ በመዋለል ላይ እያለ በውቃውና በመበረቅ ዕዝ ግንባር ተስልፎ ከነበረው ጦር አንስቶ በደረሰለት ተጠባባቂ ጦር ከኋላም ከፊትም መጥቶ ተረባረበባቸው።
✍ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም በቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት (1974 የካቲት)
ብዙ ቀይ እምቡጦች ብናጣም ድሉ የእኛ ሆኖአል፡ በዚህ ዕለት ዘጠኝ መቶ የጠላት ሬሣ ተቆጠረ፡ በቦምብ ከጋዩት ሌላ አያሌ መሣሪያዎች በወገን ጦር እጅ ገቡ፡ የቀይ እምበጥ ዘመቻ አርማ ከከፍታ ነጥብ 1702 ላይ ሲተከል የነበረው ስሜት አጅግ አድርጎ ልብ የሚነካ ነበር፡ ሁሉም የሞቱት የጀግና ሞት ነበር፡ አብዛኛዎቹ የሞቱት የእጅ ቦምብ እንደጨበጡ ጠላት ምሽግ ውስጥ ዘሎ በመግባት ነበር፡፡ ብቻውን የወደቀ አንድም የቀይ እምቡጥ ጦር አላየሁም፡ የጠላቅን አንገት አንቀው የወደቁ ብቻ ነበሩ፡፡ አስደናቂ ድል ነው፡ ግን ድሉ የቀይ እምቡጥ ብቻ አይደለም፡ ከጥሩ ቅንብርና ዕቅድ የተገኘ የጋራ ድል ነው፡፡
✍ ከቡር አቶ በአሉ ግርማ - የማስታዎቂያ ም/ሚኒስቴርበናቅፋ ጦር ግንባር በመገኘት ስለ አጥፍቶ መጥፋት ጦር የሰጡት ምስክርነት ነበር ።
📚📚 ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
የእነዚህ መጽሐፍ አዘጋጅ ንቡረ ዕድ ኤርሚያስ ከበደ በ ፲፱፻፳፰ በአዲስ አበባ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ተወለዱ። ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ፡ ገና በትምህርት ቤት ግሉ፡ በአሥራ ስነT ዓመት ዕድሜያቸው: "ምናሴ፥ የመከራዬ ደስታ፡ ዓለምን ረታ በሥራ ዓለምና በደርግ፡ የእሥራትና የግዞት፥ ኋላም የስደት ዘመን ሣሎም ከደረሷቸው መጸሕፍት መካከል፣ "ኢትዮጵያዊው፡ በማንነቱ ፍለጋ “ኢትዮጵያ፡ የዓለሙ መፋረጃ!: Ethiopia: The Classic Case እና “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት” የተባሉትን፡ ለንትመትና ለንባብ አብቅተዋል። በ፲፱፻፶፪ ዓ. ም. የመጀመሪያውን፡ የኢትዮጵያ ድርስት ማኅበር: ከጥቂት ደራስያን ጋር አቋቁመው: እስከ፲፱፻፷፩ ዓ. ም. ድረስ: በዋና ጸሓፈነት፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎታቸውን አበርከተዋል፡፡
በ፫ ዓ. ም. በአዲስ አበባ: ደቡብ ሕዝብ ተመርጠው: የመናገሻ ከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ምክር ቤት አባል፥ በ፲፱፻፶፮ ዓ. ም. የቀድሞው: የኢትዮጵያ ቤተ ሕዝብ፡ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባል፥ በTU፻፷፩ ዓ. ም. በንቡረ እድነት ማዕርግ፡ የኢትዮጵያ ቤተ ሕዝብ፡ ቤተ ምልክናና ቤተ ክህነት ሙሉ ተጠሪ በመኾን: የአኵስም ጽዮን ኣስተዳዳሪ፣ በ36 ዓ. ም. የቀድሞው: የኢትዮጵያ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያሃጅ : በ፲፱፷y ዓ. ም. በቀድሞው የኢትዮጵያ ቤተ ምልክና: የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ኾነው አገልግለዋል።
መጽሐፍቶቹ በመደብራችን ይገኛሉ
ኤዞፕ መጽሐፍት !!!
#ከጣምራ ጦር የተወሠደ
በጠላት ጥይት የቆሰለ ጓደኛው “ግደለኝ ' ጨርሰኝ…”
እያለ የሚያስቸግረው ሰው ፣ ዙሪያው በጠላት ተከቦ ማምለጫ መንገድ ያጣ ወታደር ምን ያደርጋል ?
በጠላት መድፍ እተደበደበች ከተማ ውስጥ የነበሩት
ቤተሰቦቹ በሕይወት መኖራቸውን ፡ ካሉም የደረሱበትን
የማያውቅ ሰው ምን ይሰማዋል ?
በብዙ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ካለው የወገን ጦር ጋር
ለመገናኘት ሳይችል ቀርቶ ፡ ውሃ ጥሙና ርሃቡ እያሰቃየው
በጠላት እየታደነ በረሃ ለበረሃ የሚንከራተት ወታደርስ ?
መጽሐፍዋ ቆራጥነትን ፡ ብልሃትን ፡ ትዕግስትን ' ጀግ
ንነትን ... በሚጠይቀው በዚህ አስቸጋሪ ስፍራ ፡ ሁኔታና
ጊዜ ውስጥ የነበሩት ገፀባህሪያት የተጫወቱትን ሚናና የደረሱበትን ግብ ታሳያለች ።
📖ጣምራ ጦር
📖ስደተኛው
📖ዕንባና ሳቅ
✍✍✍ገበየሁ አየለ
የዶ/ር መስከረም ለቺሣ ሁለት ድንቅ መፅሐፎችን
#የፀሐይ_ከተማ
በመጽሓፉ ውስጥ የተብራሩ ጉዳዮች፡
~ ጣልያናዋው ቶማሶ ካምፓኔላ፦ “የፀሓይ ከተማ” የሚላት ማንን ነው?
~ አክሱማውያን ምን ዓይነት ሕዝቦች ነበሩ?
~ የ16ኛው ክፍለ ዘመን የጣልያን ኅዳሴ ምስቅልቅሎች፤
~ የአክሱም ሥልጣኔ፦ በጣልያን ኅዳሴ ያበረከተው አስተዋጽኦ፤
~ ሴትነት፣ ድንግልና፣ ወንድነት፣ ጀግንነት... በአክሱማውያን አይታ፤
~የባቢሎንና የጽዮን ፍጥጫ፦ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፤
~ ደቀቀ አስጠፋኖስ አነማን ናቸው?
~ “ሪፐብለክ” ምንድን ነው?
~ የኢየሱሳውያን (Jesuits) ተልዕኮ፦ በዘመናዋው ዓለም፤ አና ሌሎችም
`
`````````
(ኢ)ዩቶፕያ
ከመጽሓፉ የተወሰደ
...ባላባቶቹና ባለሥልጣናቱ፡ ብፁዓን የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ፡ ቀድሞ መሬቱ የሚያስገኝላቸው የኪራይ ክፍያ አላረካ እያላቸው፡ የማይኾን ውሳኔ በሕዝቡ ላይ ወስነው ሕዝቡን ይጎዳሉ። እነርሱ ያለችግር ስለሚኖሩ ለሕዝቡ
ደኅና ነገር መሥራት እንደሚገባቸው እንኳ አያስቡም። የእርሻን ሂደት ያስቆማሉ፤ አብያተ ክርስቲያናትን ብቻ እያስቀሩ፡ ቤቶችንና ትናንሽ ከተሞችን ያፈርሳሉ...
**
ለዚህም እንደሽፋን የተጠቀሙት ማሞኛ፡ _ ይኽን ባዕድ አምልኮ፡ “Secularism” ወይም “ዓለማዊነት” የሚል ስም ሰጥተው፡ “ከሃይማኖት ነጻ ነው” በሚል እንዲታይ ማድረግን ነው። በዚያ ረገድም ተሳክቶላቸዋል።
***
ኢትዮጵያውያን ግን፡ እንደአገርና እንደሕዝብ፡ ላለፉት በርካታ ክፍለ-ዘመናትና አኹንም እየደረሰብን ያለው ፈተና፡...ከዚሁ፡ ከ“ቄሱ ንጉሥ” ዘመን ጀምሮ፡ እስካኹን ድረስ የቀጠለው የመልካም ሕይወት (ዩቶፕያን
የመጠበቅና የመመከት፥ አልያም፡ የመነጠቅና በከሓዲነትም የማስነጠቅ ውጥረት ጋራ በቀጥታ የተያያዘ መኾኑን፡ በበቂ ኹኔታ አልተገነዘብነውም።
ድብ አንበሳ
ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህል እና የተፈጥሮ መስህብ
በኃይለማርያም ኤፍሬም
***
የአንድ ማህበረሰብ ማንነት መገለጫዎችና የቱሪስት መስህቦች ከሚባሉት ዋናዋና ጉዳዮች ውስጥ የተፈጥሮ መልክዓ ምድርና በውስጡ አቅፎ የያዛቸው ፍጥረታት ዓይነትና ስብጥር፣ የባህል መገለጫ የሆኑት የምግብና የመጠጥ አይነቶች እስከ መሉ ስርዓቱ፣አልባሳትና መጊያጊያጫዎች፣ የቤትና የመስክ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ የወራት የቀናትና የወቅቶች ስያሚዎችና የዘመን አቆጣጠር፣የተለያዩ በዓላትና ስያሚ እስከ ስርዓታቸው፣ የሰርግና የሐዘን ስርዓት፣ መንፈሳዊ ቅርሶችና ሥነ ስርዓቶች፣ ታሪካዊ ቅርሶች የሙዚቃ ስራዎችን ያካትታል፡፡ ለትውልድ ማንነትን ለማውረስ እነዚህን ሁሉ በአግባቡ ሰንዶ ማቅረብና ማስተማር የግድ ይሆናል፡፡በተለምዶ በቃልና በክዋኔ እንጂ በሰነድ አስደግፎ ትውልድን ማስተማር በሀገራችን ብዙ አልተለመደም፡፡ የቱሪስት መስህብ ብለን የምናቀርበው ከብዙ በጥቂቱ ወይም በከፊል ብቻ በመሆኑ ጥልቅ ዕሴትና መስህብ ያለን ብንሆንም የአቅማችንን ያህል አልተጠቀምንም፡፡ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ አንደ ተቀናበረው ከላይ የተጠቀሱትን አንኳር ጉዳዩች ለቅሞና ሰንዶ ለማቅረብ ሲሞከር እኔ እስከማውቀው ድረስ ኃይለማርያም ፋና ወጊ ሊባል ይችላል፡፡ ለልጆችና ወጣቶች ማስተማሪያ ሊሆን ከመቻሉም በላይ ከአማርኛ ወደ ውጭ ቋንቋዎች ቢተረጎም የቱሪስትን ቆይታ ለማራዘምና እኛነታችንን የበለጠ ለማሳወቅ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስራ ጥቃቅን ለሚመስሉ ጉዳዮች ትኩረት መስጠትን፣ በራስ መተማመንና መኩራትን ብሎም በትጋት ለሌሎች ለማጋራት መፍቀድን ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም ወጣት ኃይለማርያምን አለማመስገንና አለማድነቅ አይቻልም፡፡
መልካም ንባብ
ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)
***
ኢትዮጵያዊነት ከድል አድራጊነት እና ጀብደኝነት ታሪካችን ሌላ ያለውን ገጽታ እና ከእያንዳንዱ ባህላዊ ድርጊቶቻችን፣ንግግራችን እና አለባበሳችን ጀርባ ያለውን የራሳችን የሆነውን ስልጣኔያችንን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህም ጥለናት የሄድናትን አገራችንን ዞር ብለን እንድናውቃት እና እንድንሻት ይረዳናል፡፡አገራችንን ላወቅናትም ላላወቅናትም ለራሳችንም ለልጆቻችንም እንዲሆን አድርጎ ታሪክን ቀለል ባለ ዘዴ ለመንገር ይህንን መጽሐፍ ላዘጋጀልን ልምዱን፣እውቀቱን፣ጊዜውንም ላጋራን ለኃ/ማርያም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡
ዶ/ር ፅጌማርያም አበበ ቢሆነኝ
***
የሀገራችንን የቱሪዝም መስህቦች በዝርዝር ያቀረበ፣በባለቀለም ምስሎችና ማስረጃ የተደገፈ፣በዓይነቱ ልዩ የሆነ ለቱሪስቶች፣ቱርኦፕሬተሮች እና የቱሪዝም ቤተሰቦች አጋዥ የሆነ በቀላል እና ሊገባ በሚችል ቋንቋ የተዘጋጀ የቱሪዝም ማስተማሪያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ትኩረት ያልተሰጣቸው ተደብቀው የነበሩ ብርቅ እና ድንቅ የቱሪዝም መስህቦቻችንን ለማስተዋወቀ ግሩም ፍሬ ያለው ለቱሪዝም ሊህቃን ታላቅ ግብዓት የሚሰጥ ለታሪካችን፣ ለባህላችን፣ መዳበር የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው፡፡በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ቢተረጎም ለሀገራችን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል፡፡
ፋንቱ ጎላ ስዩም የቱሪዝምና ሆቴሎች ከፍተኛ አማካሪ
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ልዩ ዕትም
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- /channel/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
ሰሞኑን
የአስቻለው ደሴ ምርጥ ሙዚቅ ሲወጣ ጥበብ በጠቢባኑ ስትከየን ምን ያህል ውብ እንደሆነች ያየውበትን የጥበብ ሥራ በማድመጤ እጅጉን ደስ አለኝ።
እናም በእናትዋ ጎንደር ሁለተኛ ሙዚቃ ላይ ራስ አሞራው ውብ ነህ ተሰማ እንደዚያ እጅግ ተዘክረው ስሰማው ደስ አለኝና ይህችን ጽሑፍ ከአርበኛው የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ላይ ቀንጭቤ አስነበብኳችኹ።
...በዚህ ጊዜ ግራ አዝማች አሞራው ውብነህ ሕዝባቸው ተስፋ ቆርጦ ለጠላት እጁን እንዳይሰጥ ያለመሰልቸት ለሌት ተቀን በመንቀሳቀስ ማስተባበር ጀመሩ። ይU መረጃ የደረሰው የኢ የኢጣልያ ጦር በግራ ማቹ ሰቢያ በመረዳቱ እርሳቸውን ለገደለ ወይም ከነሕይወታቸው ይዞ ለቀረበ ማንኛውም ሰው ዳጎስ ያለ ሽልማትና ሹመት እንደሚሠጥ አስነገረ። ይሁን እንጅ የጠላት ሴራ ውጤታማ ሳይሆን ቀረ። ግራ አዝማች ውብ ነህ ወገራ ናቸው ሲባል በለሳ፣ በለሳ ናቸው ሲባል ወገራ እየሆኑ ጥላት” ይሀስ አሞራ ነው ብሎ ስም አወጣላቸው።
...በሌላ በኩል ራስ አሞራው ውብነህ ራሳቸውን ጨምሮ ሃያ ሰዎቻቸውን ይዘው ከአምባ ጊዮርጊስ ወደ መረባ ሊወርድ የተዘጋጀውን ጦር ለመግጠም ገስግሰው በመሄድ እንቃሽ ወይበኝ ሲደርሱ ግራ አዝማች በላይ ዘወልዴ ከተባሉ የጥንት አርበኛ አዛውንት ቤት ጎራ እሉ። አዛውንቱ ግራ አዝማች አሞራውን ልብ ብለው ሲመለከቷቸው ከቆዩ በኋላ፣ 'ምን ልታደርግ መጣህ? ሲሉ ጠየቋቸው። አሞራውም ፈጠን ብለው፣ “ጠላት ኢጣልያን ልወጋ ነው የመጣሁ።" ብለው መለሱላቸው።
ግራ አዝማች በላይ ወደ ራስ አሞራው ሰዎች አማተሩና፣ "እነዚህ ሰዎች ይዘህ ነው ኢጣልያን ምትገጥመው?" ሲሉ በመገረም ጠየቋቸው።
አሞራውም...........................
***
በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም በመጋቢት ወር ፀሐፌ ትዛዝ ኃይሌ ወልደ ሩፋኤል እና የእንግሊዝ ጦር ሹሞች በተገኙበት ጎንደር ላይ ስለሚገኘው የጠላት ጦር አጠቃላይ የአርበኞች ስብሰባ በሚደረግበት ወቅት በዚያ የተመደበው የእንግሊዝ ጦር ዋና አዛዥ ሜጀር ቤንቴክ በጦር ሰፈሩ የእንግሊዝን ባንዲራ አሰቀለ። ይሀን የተመለከቱት ራስ አሞራው ውብነሀ የባዕድ አገር ባንዲራ በእናት ምድራቸው አፈር ላይ ተተክሎ ሲውለበለብ ደማቸው ፈልቶ ኖሮ ወደ ሜጀር ቤንቴክ ቀርበው፣ "እኔ ውብነህ ወገኔን የማስጨርሰው ነጭ ሰድጄ ነጭ ልተካ ነውን!? በል ይህን ባንዲራ አውርድ።'' አሉት።
ሜጀር ጀኔራሉም ............................
...ራስ አሞራው ውብነህ ማሂን ከተባለ ቦታ ሰፍረው ሳለ የኢጣልያ ጦር ጠቅላይ ገዢ ከሆነው ጄኔራል ናዚ መልዕክት ደረሳቸው፡፡ መልዕክቱም እንዲህ የሚል
"እርስዎም ለአገርዎ እኔም ለአገሬ በእውነት ስንዋጋ ቆይተናል። እርስዎ መደለያ ሳያሸንፍዎ በቆራጥነትና በቅንነት ለአገርዎ ነጻነት እየታገሉ ነው፡፡ እንዲህ ላለው - ጀግና እጄን ብሰጥ አልቆጨም። ነገር ግን እጄን ለእርሰዎ ከሰጠው በኋላ አሳልፈው ለእንግሊዝ ባለ ሥልጣናት አሳልፈው እንደማይሰጡኝ ቃል ይግቡልኝ ይላል።
ከመጽሐፉ የተቀነጨበ ነው።
ምን ለማለት ነው አንብቡት እጅግ ገራሚ መጽሐፍ ነው።
እና ምን ለማለት ነው
መጽሐፉን ሸምቱ በኤዞፕ መጻሕፍት ይገኛል።
0911723656 ደውሉልን !!!
«ኃያላን አንዱት ወደቁ የሠልፉም ዕቃ አንዴት ጠፋ!»
ትንሽ ስለ መጽሐፉ !!
ገናና እና ታላቅ፥ ዝነኛና ታዋቂ፥ የተከበሩና አንቱ የተሰኙ ከዘመናት በኋላ ሳይታሰብ በሚያሳዝን ሁኔታ ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ብዙዎችንም «እንዴት ወደቁ?» አሰኝተዋል::
የታላላቆች አወዳደቅ መዝሙረኛውን ዳዊት በእግርሞት ድባብ ውስጥ ነክሮታል:: አዎ! በእግዚአብሔር ፊት ይጋርድ የነበረው ኪሩብ (መላዕክ) እንዴት ወደቀ? አዳም እንዴት ወደቀ? ታላላቅ መንፈሳዊ መሪዎች እንዴት ወደቁ? መልስ የሚሻ ብርቱ ጥያቄ ነው::
በእርግጥ ኃያላንን የሚጥል ለዝንተ ዓለም የሚፈታተንና እስከ ጌታ ኢየሱስ ዳግም ምፅአት ያለመታከት በመታገል ለመውደቃቸው ምክንያት የሆነ ባላጋራ አለ:: በዚህ የሰው ልጆች ቀንደኛ ጠላት ተጠልፎ ላለመዉደቅ እውነትን በማወቅ በእውነትና በጽድቅ መኖር ያስፈልጋል:: እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ስለመንፈሳዊ ውጊያ የሚሰጠውን ትኩረት በማመን ከመፍትሔዉ ጋር አብሮ በመራመድ ለተሳካ የክርስትና ሕይወትና ኣገልግሎት ራስን ማዘጋጀት በተለይ በዚህ ዘመን አስፈላጊ ነው::
ይሁን እንጂ የወንጌል አገልጋዮች የሆኑ ሁሉን በቸልታ እያዩት ትኩረት ያልሰጡት ነገር ለመውደቃቸው ምክንያት ስለሚሆን፤ ይህ ሊጤን ይገባል:: ታላላት የምንላቸው ሰዎች ሲወድቁና ሲስቱ «ኃያላን እንዴት ወደ» በማለት በአግርሞት እንዳንዋጥ የዳዊት ምልከታና ጥያቄ ለእኛ ትምህርት ይሆን ዘንድ ተፅፏል:: ስለዚህ አሁን ባለንበት ሁኔታ ራሳችንን እንይ!
ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ከተለያዩ አገልጋዮችና ከደራሲውም የሃያ አምስት ዓመት የነፃ መውጣት አገልግሎት የተገኙ መንፈሳዊ ልምምዶች በአንድ ላይ በመዳበል ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲጠቅም ተደርጎ ተዘጋጅቷልና ያንብቡት::
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መሸጫ
@Mesay21
@Mesay21
በጥሩ ዋጋ ይሸምቱ !!!
የኢትዮጵያን አያተ ቤተ ክርስቲያናት ታሪክ በደንብ የሚያብራራ
ኤዞፕ መጻሕፍት
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
መጽሐፉን ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
/channel/azop78
/channel/azop78
PEDRO PÁEZ'S HISTORY OF ETHIOPΙΑ, 1622
VOLUME II
Edited by
ISABEL BOAVIDA, HERVÉ PENNEC AND MANUEL JOÃO RAMOS
Translated by
CHRISTOPHER J. TRIBE
Hakluyt
Society
ምርጥ የታሪክ መጽሐፍ !!
በጥሩ ዋጋ አግኝተናል
ኤዞፕ መጻሕፍት
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
መጽሐፉን ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
ኤዞፕ መጻሕፍት
ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ !!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
መጽሐፉን ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
የአለማየው ሞገስ ሥራዎችን በብዛት ስትጠይቁን ለም በራችኹ ወዳጆቻችን ትንሽ ቅጅዎች እጃችን ላይ ይገኛሉ።
✍ ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
አዲስ የግጥም መድብል
ሺ ጊዜ እንዳፈቅር
ሞልቶ ከተረፈው፣
ከበዛ ስጦታህ፣
ከሞላ ማዕድህ፣
ጥቂት ጥበብ ስጠኝ፤
ጥቂት ጥበብ ብቻ፤ ማስተዋል ጨምረህ፣
በይቅርታህ ሙላኝ፣ ጥመቀኝ በፍቅርህ፡፡
ለይቅርታ ልትጋ፣
እንዳላመነታ፣ ልቤ እንዳይጽፍ በደል፣
ሺ ጊዜ እንዳፈቅር፣ ሺ ጊዜ ብበደል፡፡
ጥቂት ጥበብ ስጠኝ፤
ጥቂት ጥበብ ብቻ፣ መቻልን አክለህ፣
እንደ እናት ልብ አንጀት፣ ጫንቃዬን አስችለህ፤
ምን ልቤ ቢታመም፣ ፈገግ እንዲል አርገህ፡፡
ማንም ምን ቢጎዳኝ፣ በእኔ ላይ ቢፈካ፣
ቀኔን አጨልሞ መንፈሱን ቢያረካ፣
.......ሃሳቡን ቢያሳካ፣
ፖርቹጋላዊው ተጓዥንና የታሪክ ተመራማሪ እንዲህም ሀይማኖታዊ የካቶሊክ ሚሲዮን የፃፈው ባለ ሁለት ቅጽ የታሪክ መጽሐፍ እጃችን ላይ !!!!
PEDRO PÁEZ'S HISTORY OF ETHIOPIA, 1622
VOLUME 1 and volume 2
Edited by
ISABEL BOAVIDA, HERVÉ PENNEG AND MANUEL JOÃO RAMOS
Translated by
CHRISTOPHER J. TRIBE
በ1626 የታተመ !!!
በዛን ዘመን የነበረውን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ የሚያብራራ !!!
ድን ቅ መጽሐፍ እጃችን ላይ ነው።
!!!!!!!!
ይህንን የካራማራ ግራሮች” የተሰኘውን መጽሐፍ መቅደስ እንዳነበው እና አስተያዬቴን እንድሰጣት ስትጠይቀኝ በጣም ትልቅ ኃላፊነት እንደተጫነብኝ ነበር የተሰማኝ። መጽሐፉን እያነበብኩት ወደ ውስጥ እየገባሁ ስመጣ ደግሞ ሌላ ኃላፊነት እና ያልከፈልኩት እዳ ቁጭ ብሎ
ጠበቀች።
“ኑረትና ዙረት” እና “የመዳኛ መርከብ ኢትዮጵያ የሚሉትን ቀዳሚ መጽሐፍቶቿን ሳነብ የነበረኝ ጉጉት “ምን አለ እንደእነዚህ ያሉ ጸሐፊዎች ቢበዙልን?“ የሚል ነበር። መቅደስ በየመጽሐፍቶቿ የምታነሳቸው ሀሳቦች የምትጽፍበት መንገድ አንባቢው ያለ ምንም ወዲያ ወዲህ የጀመረውን ንባበ ልክ እንደሚጣፍጥ ለብ ያለ ወተት በእንድ ንባብ ፉት የሚያደርገው ነው።
“የካራማራ ግራሮች“ ኢትዮጵያ ለምን የጀግኖች ሀገር እንደተባለች፣ የሀገር ፍቅር ምን ያህል ዋጋ
እንድሚያስከፍል፣ ወታደርነት ምን እንደሚመስል ያሳዬ ከሁሉ በላይ አሁን አሁን በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ የሀገር ፍቅር ስሜት ምን ያህል ትኩሳቱ እንደበረደ ደግሞ የሚያሳይ ነው።
በመጽሐፉ ላይ “ነፍሴን ለሀገሬ” ያሉ ወታደሮች እናቶቻቸው በሀዘን እና በኩራት ፣ሚስቶቻቸው
በናፍቆት፣ በሰቀቀን፣ በቆራጥነት እና በታማኝነት አብረው ሲዋደቁ የሚያሳይ ነው። “የካራማራ
ግራሮች“ ባይጻፍ ኖሮ ስንቱ ታጋድሎ ተዳፍኖ ይቀር ነበር? በመጽሐፉ ውስጥ እንደተገለፀው መቶ አለቃ መንገሻ በየጦር ሜዳ ውሎው ያሳለፈውን ገድል ጽፎ ሲያበቃ ወረቀቱን ሰብስቦ የእሳት እራት አደረገው። “ለምን ቢሉ?” ተረካቢ በማጣቱና እሱና የጦር ሜዳ ጓዶቹ የከፈሉትን ዋጋ ሊከፍል አይደለም፤ ታሪኩን ለመስማት እንኳን ጆሮ የሌለው ትውልድ ተሰፋ ስላስቆረጠው ነበር።
ወታደር አረጋ ደግሞ ለእናት ሀገራችን ጥሪ መልስ ሊሰጥ ሄዶ በመጨረሻ ወደ ቤቱ ሲመለስ እናቱ
በልጃቸው መጥፋት በሀዘን ኖረው እንደሞቱ ሲረዳ እርሱም በእርሳቸው ሀዘን ጎዳና ሲወጣ “አይዞህ ወንድሜ” እንደማለት “እብድ” ነው ብለው ዋጋ ቢስ አድርገው በመንገድ ላይ በተሰራች የላስቲክ ቤት ውስጥ ተዘንግቶ እንዲኖር ተትቷል።
ይህና ሌሎች መሰል ታሪኮች የተካተቱበት “የካራማራ ግራሮች“ ባለእዳነታችንን፣ ጡት ነካሽነታችንንና አደራ መብላታችንን ያሳያል።
ለባለእዳዎች የተጻፈ ነው። ከፋይ ካለ . . .
ጋዜጠኛ ሮዝ ነጋሽ
አዲስ ግጥም በገበያ ላይ
#የባካኙ_ምልጃ
እግዚኦ ለሰው ልጅ - አቤት ለፍጥረቱ
ሥራውን ሳይጨርስ....
እንዴት ዳናው ጠፋ? - ጠቢብ መለኮቱ
ይኽ ኹሉ ምስቅልቅል - ይኽ ኹሉ ዝብርቅርቅ
አይታይም እንዴ? - ለመለኮት ከሩቅ?
ሰማይ ቤት የለውም? - ለማየት አሻግሮ
መስኮት አላበጀም? - እልፍኙን ሸንቁሮ
ምንድን ነው ማምታታት - የአዳኝ ገዳይ በዛ
ከጊዜ ሰንበሌጥ...
ዘለዕለት ይረግፋል - ዘለዕለት ይጠላል - ፍጥረት እንደ ጤዛ።
ከገዳይ አድኖ - ያዳኑትን መግደል
የሰው ልጅ ባሕሪ...
ከዓርብ እስከ ዓርብ ድፍርስ - አይጠራም ቢጠጠል።
ለወንዝ ጊዜ አለው - ለመንጻት ደፍርሶ
በሰው ልጆች እልፍኝ...
ተቃቅፈው ያድራሉ - ዕልልታና ለቅሶ።
የሰው ልጅ ግራ ቀኝ - ሕጉ ጉራማይሌ
በእሱ የጠላውን - ያውጃል በሎሌ።
ሥራውን ሳይጨርስ - አምላክ ከየት ጠፋ?
ጀምሮ የተወው...
የሰው ልጅ ባሕሪ - ለራሱ ሲከፋ።
አምላክ ወደየት ነህ...
"ና" ጅምርህ ይቋጭ - ይፈፀም የሰው ልጅ
አውሬና መለኮት....
አያድሩም በአንድ ልብ - አይኖሩም በአንድ ደጅ።
༺❀༻
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
የለበሰችው ጃኬትና ሱሪ ወንድ ቢያስመስላትም ረጂም ፀጉሯ ሴትነቷን ይናገራል፡፡ በድንገት ትከሻዋን ሰው ነካት፣ በፍጥነት ዞር አለች፡፡
“መፋቂያሽ ከየት ተላከልሽ? አላት እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ፡፡ ደንገጥ ብላ እጇን ከኪሳ አወጣችና፣
ከጃማይካ ብላ ጨበጠችው፡፡
***
አልጋዋ ላይ ተጋደመች፡ ደግሞ በደረቷ ተኝታ ትራሱን ጭንቅላታ ላይ ጫነች። መረጋጋት ግን አቃታት፡ የሆነው ሁሉ ሊሆን የሚችል መሆኑን ብትቀበልም፣
መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ብትሆንም ለእንዲህ ዓይነት የሃዘን ስሜት ግን ዝግጁ አልነበረችም፡፡ የሚመጣውን ሁሉ በቀላሉ የምትቀበል ይመስላት ነበር፣ ልትቀበለው ግን አልቻለችም። በላይሁን ከአይኖቿ አልሰወር አላት፡ አስቻለውን አስታወሰችው እናቱንም አሰበቻቸው፡፡ ቅዱስ አብሯት እንዲሆን ፈለገች፡ አጠገቧ ሆኖ አይዞሽ እንዲላት ያለመስዋዕትነት ድል የለም!” ብሎ እንዲያበረታታት ተመኘች፡፡ አንተነህ ግጥሞቹን እንዲያነብላት፡ የትግል ታሪኮችን እንዲነግራት… ሀሳቧ ትርምስምስ አለባት። ጋዲሳና ዘርዓይ ከሀሳቧ አልጠፋ አሏት፡ ይህን ጊዜ የት ይሆኑ? ምንስ እያደረጉ ይሆን? ጥያቄዎቹ ሰላም አልሰጥ አሏት። ትራሱን ወረወረችና ተነሳች፡ ፊቷን ጠራረገችና ሰዓቷን ተመለከተች፡፡ ወደነበላይሁን ቤት ለመሄድ ራመድ ስትል
ምን ብላ እንደምታጽናናቸው ጨነቃት፡፡
****
"ለአገር መሥራት በፖለቲካ ብቻ ነው ያለው ማነው? በሕይወታችን እያንዳንዱ ቀን
አንድ በጎ ነገር ማበርከት መቻል ላገር መሥራት ነው!"
* *
ቢያንስ በሙያችን ለዓላማ የምንኖር መሆን አለብን። ለሕዝብ አስቦ ሕይወቱን የሰዋ ትውልድ አካል በመሆናችን ፖለቲካው ባይሳካልንም በሙያችን የጓዶቻችንን ዓላማ ተከትለን ለህዝብ አገልጋይ መሆን ከቻልን ባለዕዳነታችንን ከሕይወት መስዋእትነት በመመለስ ለመክፈል እንችላለን
📖📖 ምርኮኛ
✍✍ ቅንጅት ብርሃኑ
ወደው የሚያኑቡት ድንቅ መፅሐፍ
መጽሓፉ ለታሪክ ተመራማሪዎች ጥሩ የታሪክ መረጃ ቋት ሆኖ ያገለግላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ የደራሲው ዘመን ሲተረክ እንደ ታሪክ መመዝገቢያ መስኮት ሆኖ ሊወስድ ይችላል:: በእድሜ መስኮት ውስጥ በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ ጉዳዮችን መዝግቧል:: ብዙ ጠቀሜታ ያለቸውን መረጃዎች ያስተናገደ ጽሑፍ ነው፡፡እኔ በግሌ ብዙ እውቀት አግኝቼበታለሁ። የተበረከተው ምክር አዘል እይታም ለብዙ ግለስቦች በተለይ ለወጣቶቹ ከፍተኛ የተስፋ/ የምኞት ግብዓትም እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡
ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ
ሰው በኑሮ ጎዳና ያለፈበትን የእሱነቱን ታሪክ ለአንባቢያን በተመቸው መልኩ ሰንዶ ለሕትመት ሲያበቃ ! ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል:: የቀደመ ታሪክን ለዛሬው ትውልድ ያሳያል፡፡ ዛሬን ደግሞ ለነገ ያሻጋግራል፡፡ ባለታሪኩ የገጠሙትን ውጣ ውረዶች ለማሸነፍ ያደረገውን የሕይወት ፍልሚያና ያገኘውን የትግል ውጤት ለአንባቢያን ያካፍላል:: ትውልዱ ቆሞ ብሎ አካሔዱን እንዲመረመር እድል ይፈጥርለታል፡፡ የእኔ መንገድ.." በሚል ርዕስ የታተመው ይህ ግለ ታሪክ ከላይ ባነሳኋቸው ነጥቦች ዙሪያ የተገነባ ነው፡፡ የትናንቱን ትውልድ ትግል ስንዶ፤ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ መሠረት እንዲሆን አመቻችቶ ያቀረበ ነው:: እናም! በጥሞና ይነበብ ባይ ነኝ፡፡
አያልነህ ሙላቱ /መምህር/
ሰሞኑን
የአስቻለው ደሴ ምርት ሙዚቅ ሲወጣ ጥበብ በጠቢባኑ ስትከየን ምን ያህል ውብ እንደሆነች ያየውበትን የጥበብ ሥራ በማድመጤ እጅጉን ደስ አለኝ።
እናም በእናትዋ ጎንደር ሁለተኛ ሙዚቃ ላይ ራስ አሞራው ውብ ነህ ተሰማ እንደዚያ እጅግ ተዘክረው ስሰማው ደስ አለኝና ይህችን ጽሑፍ ከአርበኛው የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ላይ ቀንጭቤ አስነበብኳችኹ።
...በዚህ ጊዜ ግራ አዝማች አሞራው ውብነህ ሕዝባቸው ተስፋ ቆርጦ ለጠላት እጁን እንዳይሰጥ ያለመሰልቸት ለሌት ተቀን በመንቀሳቀስ ማስተባበር ጀመሩ። ይU መረጃ የደረሰው የኢ የኢጣልያ ጦር በግራ ማቹ ሰቢያ በመረዳቱ እርሳቸውን ለገደለ ወይም ከነሕይወታቸው ይዞ ለቀረበ ማንኛውም ሰው ዳጎስ ያለ ሽልማትና ሹመት እንደሚሠጥ አስነገረ። ይሁን እንጅ የጠላት ሴራ ውጤታማ ሳይሆን ቀረ። ግራ አዝማች ውብ ነህ ወገራ ናቸው ሲባል በለሳ፣ በለሳ ናቸው ሲባል ወገራ እየሆኑ ጥላት” ይሀስ አሞራ ነው ብሎ ስም አወጣላቸው።
...በሌላ በኩል ራስ አሞራው ውብነህ ራሳቸውን ጨምሮ ሃያ ሰዎቻቸውን ይዘው ከአምባ ጊዮርጊስ ወደ መረባ ሊወርድ የተዘጋጀውን ጦር ለመግጠም ገስግሰው በመሄድ እንቃሽ ወይበኝ ሲደርሱ ግራ አዝማች በላይ ዘወልዴ ከተባሉ የጥንት አርበኛ አዛውንት ቤት ጎራ እሉ። አዛውንቱ ግራ አዝማች አሞራውን ልብ ብለው ሲመለከቷቸው ከቆዩ በኋላ፣ 'ምን ልታደርግ መጣህ? ሲሉ ጠየቋቸው። አሞራውም ፈጠን ብለው፣ “ጠላት ኢጣልያን ልወጋ ነው የመጣሁ።" ብለው መለሱላቸው።
ግራ አዝማች በላይ ወደ ራስ አሞራው ሰዎች አማተሩና፣ "እነዚህ ሰዎች ይዘህ ነው ኢጣልያን ምትገጥመው?" ሲሉ በመገረም ጠየቋቸው።
አሞራውም...........................
***
በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም በመጋቢት ወር ፀሐፌ ትዛዝ ኃይሌ ወልደ ሩፋኤል እና የእንግሊዝ ጦር ሹሞች በተገኙበት ጎንደር ላይ ስለሚገኘው የጠላት ጦር አጠቃላይ የአርበኞች ስብሰባ በሚደረግበት ወቅት በዚያ የተመደበው የእንግሊዝ ጦር ዋና አዛዥ ሜጀር ቤንቴክ በጦር ሰፈሩ የእንግሊዝን ባንዲራ አሰቀለ። ይሀን የተመለከቱት ራስ አሞራው ውብነሀ የባዕድ አገር ባንዲራ በእናት ምድራቸው አፈር ላይ ተተክሎ ሲውለበለብ ደማቸው ፈልቶ ኖሮ ወደ ሜጀር ቤንቴክ ቀርበው፣ "እኔ ውብነህ ወገኔን የማስጨርሰው ነጭ ሰድጄ ነጭ ልተካ ነውን!? በል ይህን ባንዲራ አውርድ።'' አሉት።
ሜጀር ጀኔራሉም ............................
...ራስ አሞራው ውብነህ ማሂን ከተባለ ቦታ ሰፍረው ሳለ የኢጣልያ ጦር ጠቅላይ ገዢ ከሆነው ጄኔራል ናዚ መልዕክት ደረሳቸው፡፡ መልዕክቱም እንዲህ የሚል
"እርስዎም ለአገርዎ እኔም ለአገሬ በእውነት ስንዋጋ ቆይተናል። እርስዎ መደለያ ሳያሸንፍዎ በቆራጥነትና በቅንነት ለአገርዎ ነጻነት እየታገሉ ነው፡፡ እንዲህ ላለው - ጀግና እጄን ብሰጥ አልቆጨም። ነገር ግን እጄን ለእርሰዎ ከሰጠው በኋላ አሳልፈው ለእንግሊዝ ባለ ሥልጣናት አሳልፈው እንደማይሰጡኝ ቃል ይግቡልኝ ይላል።
ከመጽሐፉ የተቀነጨበ ነው።
ምን ለማለት ነው አንብቡት እጅግ ገራሚ መጽሐፍ ነው።
እና ምን ለማለት ነው
መጽሐፉን ሸምቱ በኤዞፕ መጻሕፍት ይገኛል።
0911723656 ደውሉልን !!!
እነዚህ በምስሉ የምታዩዋቸው ቀደምት በመጠናቸው ከ65 ገጽ የማይበልጡ ነገርግን በውስጣቸው የያዟቸው እጅግ ውብና ጠቃሚ ሀሳቦች ግን ከዘመናችን 1000 ገጽ መጽሐፍ የበለጡ ሆነው የምናገኝበት አጋጣሚ እጅጉን በጣም ሰፊ ነው።
ብታነቧቸው ጠቃሚነታቸውን ለመጠቆም ያህል ነው።
መጽሐፍቱ መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ናቸው።
የጎጃም ትውልድ ከአባይ እስከ አባይ
አለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ እንደፃፈው!
ግርማ ጌታሁን እንዳዘጋጀው።
ኤዞፕ መጻሕፍት
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
መጽሐፉን ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
/channel/azop78
/channel/azop78
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መጻሕፍቶችን የተወሰኑ ቅጅወችን አስገብተናል ።
ቀድመው በተመጣጣኝ ዋጋ ኦግደር ያድርግልን !!!
✍ የሀያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ
✍ የሀበሻ ጀብዱ
✍ የአክሊሉ ማስታወሻ
✍ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉስ
✍ ሰው ግብረገብና ስነምግባር
✍ ክብረ ነገስት
✍ የለውጥ ፍፋና ወጊዎች
✍ ካየውት ከማስታውሰው
✍ የትውልድ አደራ የሳይንስና አካዳዊ ህትመት !!
ኤዞፕ መጻሕፍት
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
መጽሐፉን ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋንቋዎች አካዳዊ ህይወት
ትመይ ውጤቶችን በቅናሽ ዋጋ።
የግዕዝ ቅኔያት ፩
የግዕዝ ቅኔያት ፪
የግእዝ ቅኔያት መንገገዶች ፩
በተመጣጣኝ ዋጋ