azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ጥሩ ግጽም ላስነብበወት


!!!!

ለእዚች ለሙት ዶሮ ይህን አልኩላት ብዬ ትንሽ ቆየት ብሎአል ጫርጫር አርጌ ነበር ዛሬ ተስፋ የፌቡ ጓደኛዬ እንደገና ፖስተው ብላ እንቅ አርጋ ብትይዘኝ ዳበስ ዳበስ አረኩትና ለሶስተኛ ጊዜ ለጠፍኩት። በሉ ይመቻችሁ።

እንዴት አርጎ ያማል
ጠቅጥቆ ውስጥን፤
ምን አያቁ ጫጩት
የእናት እሬሳን፤
ወጥተው ሰፍረውበት
በድን ገላዋን፤
መስሏቸው እንዳለች
የቱን፥ ምኑን ሲያውቁት፤
ይሰፍሩት ለፍቅር
መውደድ ሊገልፁበት፤
አእምሮ ካለን
ማዘን ብናውቅበት፤
እሷ ብትሆን ዶሮ
እነሱ ጫጩት፤
ሰዎች ነን፥
ካልንማ በእውነት፤
የቱ አንጀት ይችላል
ካሜራ ለማንሳት ፤
ብቻ ለምዶብን
በሰው አርገንበት፤
ለዚች ለዶሮማ
አርደው ለሚጥሏት፤
እረ ከየት መጥቶ
ሊኖር የቱ አንጀት።

እኔስ አመመኝ
እኔስ አዘንኩላት፤
አይታ ብታውቀው
እንዴት እንዲወዷት፤
እሬሳዋን ከበው
ከበድኗ ሰፍረው፤
ሲሉላት ዋይ ዋይ
በቋንቋው ጭው ጭው፤
አትነሽም ወይ
አንሄድም ወይ፤
ከእቤት መግቢያችን
ደረሰ ዋይ ዋይ፤
ኧረ እማ እባክሽ
ክንፍሽን ዘርጊልን፤
እረ እዘኝልን
ደከመን በረደን፤
ዛሬ ምን ሆነሽ ነው
እንዲህ ከፋሽብን፤
እረ ዋይ እረ ዋይ
አትነሽም ወይ
ተመልከች ጀንበሯን፤
እረ ዋይ እረ ዋይ
ደርሶ የለም ወይ
ከቆጥ መስፈሪያችን።

በቋንቋው
ጭው ጭው
ኧረ ዋይ እረ ዋይ፤
አይበቃሽም ወይ
አትነሽም ወይ
አንሄድም ወይ ……።

በቋንቋው ጭው ጭው እረ ዋይ እረ ዋይ ! ! ! !

ዳኛቸው ካሣ ወልደሥላሴ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቆየት ያለ ድርሳነ ሚካኤል እጃችን ላይ አለ!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ጅብራን ካህሊል ጅብራን አንድ ወቅት እንደዚህ ብሎ ነበር፡"ከአንድ ሰው ጋር ለመጋጨት አንድ ደቂቃ በቂ ሊሆን ይችላል።” " አንድን ሰው ለመውደድም አንድ ሰዓት አስተማማኝ ሊሆን ይችላል።" " አንድን ሰው ለማፍቀርም አንድ ቀን ብቻዋን በቂ ልትሆን ትችላለች .….......ግን ግን አንድን ሰው ለመርሳት የእድሜ ልክ ጥረት ይጠይቃል"


የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ። /channel/azop78


አንብቡት በሞቴ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በጥሩ ቅናሽ በመደብራችን ይገኛል


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መስማት የሚፈልጉትን ብቻ እንድትነግርዋቸው የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው። እነርሱ የሚያስቡትን ካላወራችሁ እናንተ ስህተተኞች ናችሁ። እነርሱ አረንጓዴና ቀይ ቀለም ከወደዱ እናንተ ቢጫ የመውደድ መብት የላችሁም፤ እንደውም ቢጫ የሚባል ቀለም የለም ሁሉ ሊልዋችሁ ይችላሉ። እናንተ እንጂ እነሱ ምንም የማለት መብት አላቸው። እነርሱ ያሰቡትን፥ እነርሱ የሚፈልጉትን ካላላችሁ እናንተ ልክ ብትሆኑም እንኳ ልክ አይደላችሁም። እንደ አህያ መልክ አንድ አይነት በሚዘመርበት "እኔን" ሆኖ መቆም በኛ ሀገር ኃጢአት ነውና።


ኤፍሬም ስዩም
የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች
ገጽ:-72


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40 /channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

💎➔በልክ መብቃት።

➔ሁሉም ሰው የራሱ መጠን አለው። መብቃት ወይም ስኬቱ በልኩ ነው የሚመዘነው። የልኩን ያህል ነው ማቀድና መንቀሳቀስ ያለበት። ሁሉም በእኩል መጠን ባንድ ክዋኔ እኩል አይደርስም። መንገዱም ይለያያል። ስለዚህ እንደራስ አስቦ የራስ የሆነን የህይወትና እምነት ማረፊያ እንዲሰራ ነው ልኩ።

➔አቅም ሲኖርህ ከራስህ ትወዳደራለህ። ራስህን ትተቻለህ። ከትናንትህ መሻልህን ትመዝናለህ። አቅም ካጣህ ግን ብቸኛ መውጫህ መውቀስ ይሆናል። የሰዎችን ጥረት በማኮሰስ ፀሎት ትጠመዳለህ።

©mohammed ali burhan

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የአለማችን ታዋቂ ሰዎች ስለ ንባብ ያሉትን ከጓደኛዬ የተዋስኩትን ላካፍላችሁ እንመልከት.....

1. “ማንበብ ትልቅ ሀብትን ያጎናፅፋል። እስከዛሬ በአለማችን ላይ ስለተከሠቱ እና በሌሎች ሰዎች ስለተሰሩ ነገሮች በሙሉ ማወቅ የምንችለው ማንበብ ስንጀምር ነው።” (አብርሃም ሊንከን)

2.  “በህይወቴ ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ መፀሀፍቶች ውስጥ አሉ። የኔ ምርጥ ጓደኛ ብዬ የምቀርበው ሰው ያላነበብኩትን መፀሀፍ “እንካ አንብብ” ብሎ የሚሰጠኝ ነው።” አብርሃም ሊንከን

3. “እዚህ ምድር ላይ ግዜ የማይሽረው ደስታን የሚሰጠን ብቸኛው ነገር መፀሀፍ የማንበብ ልምድ ነው። ሁሉም ደስታዎቻችን በወረት ከእኛ ሲለዩን መፀሀፍ የማንበብ ልምዳችን ግን ዘወትር ደስተኞች ያደርገናል።” (አንቶኒ ትሮሎፔ)

4."“ዘወትር ባነበብኩኝ ቁጥር ውስጤ የነበረውና ያለው ትልቁ የመቻል አቅም ይቀሰቀሳል።”(ማልኮምኤክሥ)

5. “የኔን የግል ህይወት ብቻ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ህይወት መለወጥ የቻሉ ሀሳቦችን መተግበር የቻልኩት መፀሀፍ በማንበቤ ነው።” (ቤል ሑክሥ)

6. "“መፀሀፍን የሚያነብ ሰው በህይወት ውጣ ውረዱ አያማርርም። ሠዎች ለምን ጎዱኝ፣ ለምንስ አያስቡልኝም ብሎም ሌሎችን አይወቅስም። ከሌሎች ጋርም አይቀያየምም ምክንያቱም መፀሀፍ የሚያነብ ሰው ለራሱ ስኬትና ደስተኛነት ራሱ ብቁ ነውና ከሌሎች ምንም ስለማይጠብቅ።”(ባሮው)

7. “ዛሬ ላይ ያለህ ማንነት የዛሬ አምስት አመት ከሚኖርህ ማንነት ጋር ፍፁም ለውጥ ሳይኖረው ተመሳሳይ ነው። ግን በነዚህ አመታቶች ውስጥ መፀሀፎችን ካነበብክ አዎ! ከአሁኑ ይልቅ የዛሬ አምስት አመት የተሻለ ማንነት ይኖርሃል።” (ቻርሊጃንሥ)

8. “ለአንድ ሠው መፀሀፍ ስትሸጥ የሸጥከው ብዙ ወረቀቶችን፣ የተፃፈበትን ቀለምና ጥራዙን አይደለም። ለርሱ የሸጥክለት ዋናው ነገር ሙሉ የሆነ አዲስ ህይወትን ነው።”(ክርስቶፈር ሞርሌይ)

9. “በዚህ ዘመን በየትኛውም ሁኔታ በጣም ግዜ የለኝም፣ እረፍት የለኝም ብለህ የምታስብ ቢሆን እንኳን ለማንበብ የግድ ግዜ መስጠት አለብህ። ይህን አላደረክም ማለት ግን በገዛ ፍላጎትህ ራስህን አላዋቂ እያደረከው ነው ማለት ነው።”(ኮንፊሽየሥ)

10.“ድሮ ልጅ ሣለሁ ወደ ትምህርት ቤት ስሔድ ዘወትር አፍንጫዬን በመፀሀፍ ደብቄ ነበር። ይኸው ዛሬ ላይ ታዲያ እዚህ ለመድረሴ ዋና ምክንያት ሆኖኛል።”(የሙዚቃ አቀንቃኙ ሱሊዮ)

11.“መፀሀፍትን በሚገባ ማንበብ ማለት በድሮ ዘመን
ይኖር ከነበረ በጣም አስተዋይ ሰው ጋር መወያየት ማለት ነው።”(ሬኔ ዴካርቴሥ)

12.“አዎ! የሚታኘክ ማስቲካ ለማምረት ከምናወጣው
ወጪ በላይ ለመፀሀፍቶች ብዙ ወጪን ባናወጣ ኖሮ ይህች ሀገራችን እንዲህ የሠለጠነችና የዘመነች አትሆንም ነበር።”(አልበርት ሀባርድ (አሜሪካዊ)

13.“ከየትኛውም ነገር በላይ ትልቁንና ከፍተኛውን ደስታ የማገኘው ሳነብ ነው።”(የፋሽን ዲዛይነሯ ቢልብላሥ)

14.“ማንበብ ከቻልክና አንዴ ማንበብ ከጀመርክ በቃ አንተ ነፃነት ያለህ ሠው ነህ።”(ፍሪድሪክ ዳግላሥ)

15.“ለመኖር ከፈለክ መፀሀፍ አንብብ።”(ጉስታሽ
ፍላውበርት)

16.“መፀሀፍን ከማቃጠል የባሰ በርካታ ወንጀሎች አሉ።ከነዚህ መሃል መፀሀፍትን አለማንበብ አንዱ ትልቁ ወንጀል ነው።”(ጆሴፍ ብሮድስኪ)

17.“አላዋቂነትንና ችኩልነትን የምንዋጋበት ብቸኛው ወሳኝ መሣሪያ ማንበብ ነው።”(ሌኖርድ ቤይንሥ ጆንሰን)

18.“ዛሬ ያነበበ ነገ መሪ ይሆናል።”(ማርጋሪት ፉለር)

19.“መፀሀፍን የማያነብ ሠው ማንበብን ከነጭርሱ
ከማይችል ሠው በምንም አይሻልም።”(ማርክትዌይን)

20.“በርካቶቻችን መፀሀፍ አንባቢ መሆን እንፈልጋለን። የምናነበው ግን ጥቂቶች ብቻ ነን።” (ማርክ ትዌይን)

21.“እኔ የተወለድኩት ማንበብ ከሚገቡኝ ግና አንብቤ ከማልጨርሣቸው የመፀሀፍት ዝርዝሮች ጋር ነው።”(ማውዲ ኬሲ)

22.“ለአንድ ጨቅላ ልጅ መፅሐፍ እንዲያነብ ከማድረግ በላይ ልንሠጠው የምንችለው ትልቅ ሥጦታ የለም።”(ሜይ ኤለን ቼሥ)

23.“አንድ መፀሀፍ ባነበብን ቁጥር እዚህ ምድር ላይ በሆነ ቦታ ለኛ አንድ በር እየተከፈተልን ነው።”(ቬራናዛሪያን)

24.“ለኔ ህይወት ማለት ጥሩ መፀሀፍ ማለት ነው።
የበለጠ ወደ ውስጡ በገባን ቁጥር የበለጠ ትርጉም እየሰጠን ይመጣል።”(ሀሮልድ ሱሽነር)

25.“እስከዛሬ በህይወቴ ካገኘኋቸው ምክሮች ትልቁ
እውቀት ሀይል ነው። ማንበብ ደግሞ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው የሚለው ነው።”(ተዋናይ ዳቪድ ቤይሊ)

26.“የህይወታችን ትልቁ ደስታ መፀሀፍ ከማንበብ የሚገኝ ነው ብዬ በድፍረት ላውጅ እችላለሁ። ወደፊት እኔ የራሴ መኖሪያ ቤት ሲኖረኝ አንድ ጥሩ ላይብረሪ በውስጡ ካላካተትኩኝ ምን እንደሚውጠኝ አላውቅም።”(ደራሲ ጆን ኦውስተን)

27.“መፀሀፎች ወረት የማያውቁ ምርጥ ወዳጆች ናቸው። እጅግ መልካም አማካሪዎችና የችግር ግዜ ደራሾችም ናቸው።እንዲሁም ከምንም በላይ ታላቅ መምህር ናቸው።”(ቻርሊ ኢሊዬት)

28.“ማንበብ ከምንገምተው በላይ ዘላቂ የሆነ ደስታን
ነው የሚሰጠን።”(ላውራቡሽ)

29.“መልካም ህይወት መኖር ከፈለግን ዛሬ ነገ ሳንል
ማንበብ መጀመር አለብን።”(ሞርታይመር አልዴር)

30.“አንድ ሠው ምን አይነት ማንነት እንዳለው
ያነበባቸውን መፀሀፎች አይቶ መናገር ይቻላል።” (ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን)

31.“አንድ ባህል ወደ ቀጣይ ትውልድ እንዳይተላለፍ
ከተፈለገ መፀሀፎችን ማቃጠል አያስፈልግም። ይልቅ ሠዎቹ መፀሀፍ ማንበብን እንዲያቆሙ ማድረግ በቂ ነው።” (ራይ ብራድበሪ)

32.“የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአካላችን የሚጠቅመውን ያህል ንባብም ለአእምሯችን ይጠቅማል።”(ሪቻርድ ስቲላ)

33.“ሸረሪቶች እንደተወለዱ በተፈጥሮ ድርን የመስራት ክህሎትን እንደሚያገኙ ሁሉ ህፃናትም ሲወለዱ የመናገር ጥበብና ችሎታ አብሯቸው ይወለዳል። ግና ማንበብ መቻልን እኛ ነን ልናለማምዳቸውና ልናስተምራቸው የሚገባን።”(ስቴቨን ፒንከር)

34.“መርከበኞች በአንጸባራቂ ደሴት ላይ ከሚያገኙት
ሀብት በላይ ብዙ ሀብት የሚገኘው መፅሀፍቶች ውስጥ ነው።”(ዋልት ዲስኒ)

35.“አንተ ጋር ሲመጡ መፀሀፍ በእጃቸው ያልያዙ ሠዎችን በፍፁም አትመን።”(ሊሞኒ ስኒኬት)

36.“ለማንበብ ግዜ የለኝም ካልን ለማውራትና ለመፃፍ
እንዴት ግዜ እናገኛለን?”(ስቴቨን ኪንግ)

37.“ህፃናት እንደሚያደርጉት ለመገረም ብለው መፀሀፍን አያንብቡ። ለመማርም ሆነ ህልመኛ ለመሆንም ፈልገው አያንብቡ። ይልቅ አዎ! ለመኖር ሲሉ ነው ማንበብ ያለብዎት።”(ጉስታቮ ፍላውበርት)

38.“እኔና ጥቂት ሰዎች ስለራሳችን መልካም ነገር
የምናስበውና ጥሩ ስሜት የሚሠማን መፀሀፍ ስናነብ ነው።”(ጄን ስሜይሊ)

39.“የልጆቻችንን ቀጣይ ህይወት ብሩህ ልናደርግላቸው የምንችልባቸው ጥቂት መንገዶች አሉ። ከነዚህ መንገዶች መሃል ሠፊውና አስተማማኙ በውስጣቸው የንባብ ፍቅርን መዝራት
ነው።”(ማያ አንጄሎ)

40.“መፀሀፍ ማንበብ ነገሮችን እንድንረዳ ብቻ ሳይሆን ሌሎች እኛን በቀላሉ እንዲረዱን ይጠቅመናል።” (ጆን ግሬን)

41.“አንተ ያላነበብከውን መፀሀፍ አንብብ ብለህ ለልጅህ አትስጠው።”(ጆርጅ በርናንድ ሾው)

42.“አንተ ወይም እኛ የማናውቃቸው ነገሮች በሙሉ መፀሀፍት ውስጥ እንዳሉ እናውቃለን?”(ሲድኒ ስሚዝ)

43.“እኔ አንብቤ ባስቀመጥኳቸውና በማነባቸው
መፀሀፎች ካልተከበብኩ እንቅልፍ በፍፁም አይወስደኝም።”(ጆርጅ ሉዊሥ በርጌሥ)

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የእምነት ተቋማት ግንባታ ከሀገር ግንባታ በተለይም ከግብረ ገባዊ ትውልድ ግንባታ ጋር በቀጥታ ይያያዛል። ተቋማቱ የአስተምህሮ ማዕከል ኾነው ትውልድን በእምነትና በምግባር ያንፃሉ:: በሕንፃነታቸው ደግሞ የሀገር ቅርስ የትውልድ ውርስ ናቸው። ዛሬ ላይ አሉን የምንላቸው ሀገርን ያኮሩና ያስከበሩ ቅርሶች ትናንት በነበረው አማኝና ጨዋ ትውልድ የተገነቡት ናቸው። አሁን የምንገነባቸው ቤተ እምነቶችም የነገ ቅርስ ናቸው። ለልጆቻችን ከዚህ የበለጠ የምናወርሰው ውርስ፣ ለሀገርም ከዚህ የሚልቅ የምናስቀምጠው ቅርስ አይኖርም። እናም የእምነት ተቋማትን ለመገንባት መሮጥ ትውልድንም የሚያንፅ ውድ የሕንፃ ቅርስን የማስቀመጥ ሩጫ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ካበረከተቻቸው ውድ ቅርሶች ዋነኞቹ ሕንፃ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። በአሠራር ጥራትም ኾነ በጥበባዊ ውበት በልዩ ኹኔታ ታንፀው ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገሩበት ምሥጢርም ከልብ በኾነ እምነትና ትብብር ነገን በማሰብ ለልዕልና ለቅድስና የሚገነቡ መኾናቸው ነው። በውስጣቸው ሥዕላትን፣ መጻሕፍትንና ሌሎች ቅርሶችን ይይዛሉ። መንፈሳዊው/የማይዳሰሰው ቅርስ ደግሞ ብዙ ነው። መልካም ትውልድ ከሚቀረፅበት ሥርዓት በላይ ውድ ቅርስ የለም። ይህን መልካም መንገድ ማስቀጠል ይኖርብናል። ትናንት ታንፀው ዛሬ ቅርስ በኾኑልን መቅደሶች እንደምንደሰተው ኹሉ እኛም ዛሬ ላይ በራሳችን አሻራ አንፀን ለልጅ ልጆቻችን ቅርስ የማቀመጥ ዕድል አግኝተናል። በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በመታነፅ ላይ ለምትገኘዋ የጽርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ግንባታ መፋጠን እምነት ሳይለየን የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ።
ለሀገር ቅርስና ለትውልድ ውርስ እንሩጥ።
-+-+-+-
የግርጌ ማስታወሻ፥
ቅርሶች የኹሉም ዜጎች ብሎም ለዓለም ሕዝብ ኹሉ ውድ ሀብት ናቸው። በአማኞች ቢገነቡም ቅርሶች በራሳቸው እምነት የላቸውም። ለሰው ልጆች የእምነት መገለጫ ቢኾኑም ቅርሶችን በሰዎች በእምነት ለይቶ ማየት አይገባም። ቤተ ክርስቲያንም ኾነ መስጊድ ወይም ሌላ ቅርስ ሀብትነቱ የሀገር ነው። ኩራትነቱም የኹሉም ዜጋ ነው። ስለኾነም ሙስሊም ክርስቲያን ሳንል ነገ ቅርስ የሚኾኑ ቤተ እምነቶችን እንገንባ።

(ለነገሩ ድከም ቢለኝ እንጅ የእኛ ሕዝብ ለዚህ ነጋሪም መካሪም አያሻውም። በኢትዮጵያ ምድር ቤተ ክርስቲያን በክርስቲያኖች ብቻ ወይም መስጊድ በሙስሊሞች ብቻ ተገንብቶ አያውቅምና።)


መላኩ አላምረው ነው
ሃሳቡን እንዲህ አጋርቷችሓል።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
የረባባህርይ ድርሰቶች መጽሐፍ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የጉራጌን ማህበረሰብ
ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ታሪክ ለማዎቅ የሚጠቅም ድንቅ የታሪክ ጥናታዊ መጽሐፍ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የመሲሆች እድር
ቡርሃን አዲስ

ይህ መጽሐፍ 38ኛ መጽሐፉ ነው.!!
ገና በወጣትነቱ ብዙ መጽሐፍትን አሳትሞ አስነብቦናል።

በፍልስፍናው አለም ፍልስምናን ህይወታቸው አድርገው ከሚኖሩ ጠቢባኖቻችን መካከል ቡርሃን ብርቅየ ጠቢባችን ነው።

መጽሐፉ ገበያ ላይ ነው።

ኤዞፕ መጽሐፍት ።


/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"ስምህ?" የተለመደው የዳኛ ጥያቄ ለሦስተኛ ምስክር ቀረበለት።

"ተኸተል ባንዣው" አለ ሦስተኛው ምስክር።

"ዕድሜህ?"

"አላውኧውም...እርግጡን።"

"መች እንደ ተወለድክና ስንት ዓመት እንደሆነህ አታውቅም?"

" ታንዠቴ ነው፤ አላውኧውም፤ ባውኧው ምን ገዶኝ?"

" በግምት ስንት የሚሆንህ ይመስልሃል?"

" አባቴ ያሥራ ስድስት ዓመት ልጅ ሳለ ነው የተወለድሁት። እናቴም ገና እጣን ነበረች ይላሉ። እንግዲህ ሁለቱም አርዥተው አፍጅተው ከሞቱ አምስትና ስድስት ዓመት ሆኗቸዋል፤ ግምቱን በዚህ ይውሰዱት እንግዲህ።"

"አልተግባባንም... የዕድሜህን ልክ በቁጥር ብትነግረን ነበረ እንጂ የሚረዳን ፤ ይኽማ..." አሉና ዳኛው በቅሬታ ፈገግታ እንደተዋጡ፤ ሦስተኛ ምስክር ተከተል አቋረጧቸው።

"ሰማንያ ልበልዎት ይሆን?"

"አልበዛም?"

"እንግዲያ እኔን ተሚያደክሙ እርስዎ ቢገምቱትስ?" ግልፅ አነጋገሩ ከቅንነት የመነጨ ነው።

"ባንተ ያምራል ብዬ ነው፤ ለምሳሌ..." ዳኛው ችሎት ባይሆንባቸው ኖሮ ሳቃቸውን የሚቆጣጠሩት አይመስሉም። ቀይ ፊታቸው ድልህ መስሎ ዓይኖቻቸው ይቁለጨለጫሉ።

"እንግዲያ ቢያንስ አምሳ ቢተልእ መቶ ታምሳ ተብሎ ይመዝገብ ጌታው።" ዳኛውም ሌላውም ተያይዘው ሳቁ። ተከተል ተደናገጠ።

ሞገደኛው ነውጤ:
አበራ ለማ



ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 091172 3656
092074 5740
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሰንዙ ዘመን አይሽሬው
መጽሐፍ

3000 ዓመታትን የተሻገረ ጥበብ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
!!!!!!!!!!

"ያንተ ያልሆነውን ከመውሰድ እጆችህን ሰብሰብ ለማድረግ ሞክር፡፡ ጣዕም የላቸውምና ቀጣፊ እጆችን አትውደዳቸው፡፡ ክብሩ ሳይገባህ የተነቀስከውን አምላክ ከቻልክ ከሰውነትህ ላይ ፈቅፍቀው፡፡ አዝለኸው አትዘሙት ፤ በቆዳህ ላይ ለጥፈኸው በቆሸሹ ውሎዎችህ ዳግም ቀራንዮ አትሁንበት.. አትስቀለው!

እምነት ማለት ... በስራና በምግባር የሚዘራ ፣ ዝቅ ብለህ በትሁት ልብ የምታጭደው የነፍስ አዝመራ መሆኑን አትርሳ፡፡" ንግግሩ ደንቆኝ ይበልጥ ላወራው ፈጠንኩኝ፡፡

"ለመሆኑ እግዚአብሔር አለ?" አልኩት.. የተስፋ መቁረጤ ዳርቻ የፀነሰው የዕለታት ጥያቄዬ ነበር፡፡

"እኔ መኖሬን በምን አወክ?" አለኝ በመደነቅ፡፡

"አንተማ ይኸው ከጎኔ ቆመሃል፡፡ ስጠይቅ ትመልሳለህ፡፡ እግዚአብሔር ግን መች በችግሬ ደረሰ?" እንባዬ ይብስ ከፍ እያለ መርከፍከፍ ሲጀምር.. ትክ ብሎ ተመለከተኝና!

"አየህ... ሰው ነህና የምታየውን ትተቻለህ.. ተነቃፊው እግዚአብሔር ቢወርድ እንኳ ስላየኸው አታመልከውም፡፡ ስለዚህም ህግ ነውና .. እንዳትንቅ ፣ እንዳትዳፈር ያመንከውን አታየውም፡፡

ከመጽሐፉ የተወሰደ

👉ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ የሴት ሎሬትነት ማዕረግ የተሰጣት
ገጣሚ

!!!!!!!!

የግጥም መጽሐፍ !!!

ከበደች ተክለ አብ

;!!!!!!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

1947 መጽሐፍ ቅዱስ እጃችን ላይ ነው !!!!!

ሞዓ አንበሳ ዘምነገደ ይሑዳ

ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኤዞፕ  ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብና መጽሐፍት መደብር
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:-  09 11 72 36 56
           09 20 74 57 40

/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#የጉዞሽ_ምርኩዝ

#አንዲት_ምድር_አንዲት_ቤት

" እምትኖሪባትም እምታቋርጫትም ምድር ያንቺ ነች ። ከቶም ባይተዋርና መንገደኛ አይደለሽም ። እግሮችሽን በምታሳርፊባት ምድር ሁሉ ዱካሽንም እንዲሁ ታኖሪያለሽ ። ዳናሽ በንፋሱም በጎርፉም ታብሳ ትጠፋለች ። በምድር ማህፀን ውስጥ ያሳረፍሻት እያንዳንዷ አሻራ ግን ዘለአለማዊት ነች ። ከምታልፊባት ምድር ሁሉ አፈሯንም ጥበቧንም ትጠቅሻለሽ ። ጉድፉም ሆነ ትዝታው በሳሙናም በጊዜም ታጥቦ ይከስማል ። ከነፍስሽ የተከተበችው ጣዕመን ግን ዘለአለማዊት ነች ።

ከቶም ይህች አገር " የነእንቶኔ ነች " አትበይ ምድር " የኛ ነች " ለሚሏት እንጂ " የኔ ነች " ለሚሏት ሆና አታውቅም ። ስጋሽ ያረፈችባት ጎጆ ሁሉ የነፍስሽም ጭምር ነች ። ማዕዷ ያፈራቻቸው ሁሉ ያንቺም ናቸው ። እንደልብሽ እሾት በነፃነት ተቋደሻቸው ። የተከልካይነት ስሜት ከቶም አትደርብሽ ። ሰው ሊከለክልሽ የሚችላት የምድር ሆና አታውቅም ። እናት ምድር ዘንድ ስስት የለም ። ከምድር የመቋደስን ነፃነት በምታውቅ ነፍስ ዘንድም ስስት የለም ። የምድር እናትነት ያለው ከለጋስነቷ ነው ። የምድር በኩር የሆንሽው ያንቺም እውነተኛ ማንነት እሚገለጠው በምትሰጪው ነው ። ከምትኖሪባትም ከምታቋርጭባትም ምድር በምትቋደሻት ማንኛይቱም ነገር ፍፁም ለጋስ ሁኚ ። "

👉 " ይህች እንደ ማር እንጀራ የምትጣፍጥ መጽሐፍ ነች ።
👉ይዘሻት በዞርሽበት ሁሉ ንቦች ይከተሉሻል "

" የትኛውም መጽሐፍ ባህላዊ ቅርስ ነው ። በፍቅር መጻፍ በፍቅር መታተም ፣ በፍቅር መሰራጨት ይገባዋል
ይህ መግቢያውና መውጫው ነው ።
መሐሉን እንመለስበታለን !!!

መልካም ቀን 💚


ከፈላሱ መንገድ ላይ ሀይማኖት በላቸው እንደከተበችው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#እዚህ_ሱቅ_ሠላም_ይሸጣል?

ሠላም ማጣት በወል መታወር፣ በወል መደንቆር ነው። ሠላም በሌላት ሐገር ዘንድ ቀዳሚው የኢኮኖሚ ዕድገት አይደለም። ቀዳሚው የፓርቲዎች ድርድር አይደለም። የዚያች ሐገር በኩር ጥያቄዋ ሠላም ነው። አዎን ሠላም ነው።

የሚጮኽ፣ የሚያቃስት፣ የሚተፋ፣ "ወይኔ" የሚል በሌለበት ስፍራ መተኛት፣ መዋል፣ መኖር ዋጋው ስንት ነው?

ጥይት፣ መድፍ፣ ታንክ በማይጮኽበት እጅ እና እግር ከማይወድቅበት፣ ዓይን ከማይጠፋበት፣ ለቅሶ ከማይሰማበት ሐገር መኖር ዋጋው ስንት ነው?

እዚህ ሱቅ ሠላም ይሸጣል?

ስንት ነው?…



ሠላም የሌላት ሐገር፣ ጤና እንደሌለው ግለሰብ ናት። ሠላም የጤና የወል ሥም ናት።

"የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሀሳቦች"
በኤፍሬም ሥዩም

Jion
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

➡️ቦቆሎ ወደ ወፍጮ ቤት የምንወስደው የቦቆሎውን ዱቄት ፈልገን ነው። ወፍጮው እንዴት እንደፈጨው ማወቅ አያስጨንቀንም።

➡️በመኪና ተሳፍሮ መሄድንና ካሰብንበት መድረሳችንን እንጂ መኪናው በምን ስልትና መርህ እንደሚሽከረከር ለማወቅ ደንታ የለንም።...በቆሎውን አስገብቶ ዱቄቱን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ወፍጮው እንዴት እንደፈጨው ማወቅ አለብህ። ያ ነው የሳይንስ ሰው የሚያደርግህ። ገጽ፦16

📚ዓለማየሁ ዋሴ



ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

44.“አንዳንድ መፀሀፎች የፈለግነውን እንድናስብ ነፃ ያደርጉናል። አንዳንድ መፀሀፍት ደግሞ ከጭንቀታችን ነፃ ያደርጉናል።”(ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን)

45.“ምናባችንን ከተኛበት የሚቀሠቅስልን ሞተር መፀሀፍ ማንበብ ነው።” (አለን ቤኔት)

46.“በአሁኑ ሰአት እየተቃጠሉ ካሉ መፀሀፍት በላይ
የሚያሳስበኝ በአሁኑ ሰዓት እያልተነበቡ ያሉ መፅሀፎች ናቸው።”(ጁዲ ብሉሜ)

47.“ልጆቼ ወደፊት ሲያድጉ ማንበብ የሚወዱና
ለእናታችን ትልቅ መፀሀፍ መደርደሬ እንስራላት ብለው የሚጨነቁ ቢሆኑ ደስታዬ ወደር አይኖረውም።”(አና ክዊድሰን (የኒዮርክ ታይምስ ፀሃፊ)

48.“መፅሀፍት ማለት መቼም ቢሆን የማይርቁን፣
የማያስቀይሙን፣ የማይከዱንና መቼም ቢሆን ተስፋችንን የማያጨልሙብን ወዳጆቻችን ናቸው።” (ቻርልሥ ኤሊዮት)

49.“ከውሻ ውጪ የሠው ልጅ ታማኝ ወዳጅ መፀሀፍት ናቸው። ከውሻ ጋር ወዳጅ ስንሆን ግን የማንበብ እድላችን በጣም ያነሠ ነው።”(ጉርቾ ማርክሥ)

50.“በመመገቢያ ጠረጴዛህ ላይ መፀሀፎች ይሙሉ።ከዛም በጣም ደስተኛ ትሆናለህ። ትራስህም መፀሀፍቶችን ይሁኑ ከዛም ፍፁም የሠላም እንቅልፍ ትተኛለህ።”(ፊይዶር ዶስቶኸስኪ)

51.“መፅሀፍ ማለት በኪሳችን ይዘነው የምንዞረው
በመልካም ፍሬዎች የተሞላ እርሻ ነው።” (ቻይናውያን)

52.“መፅሀፍ ስናነብ ወደ ውስጣችን በጣም ጠልቀን በመግባት ስለራሳችን የበለጠ ብዙ ነገሮችን ማወቅ እንጀምራለን።”(ዊልያም ሀዝሊት)

53.“ትንሽዋ የመፅሀፍ መደርደሪያ እስከዛሬ በአለማችን ላይ ከቀረቡ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በላይ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ሃሣቦችን ይዛለች።” (አንድሪው ሮስ)

54.“ለአንድ ሰአት ብቻ ካነበብክ ወይም የማንበብ ልምድ ካለህ መጨነቅህ አይቀርም። ከሁለት ሰአታት በላይ የማንበብ ልምድ ካለህ ግን በምድር ላይ እንዳንተ ደስተኛ ሰው አይኖርም።”(ቻርለስ ዴ ሴኮንዳት)

55.“ከአጠገብህ ፋኖስ ለኩሰህ ወይም ሻማ አብርተህ ቁጭ ብለህ መፀሀፍ ማንበብን የመሰለ ምን ነገር አለ? አስበው በዚያ በምታነብበት ሰዓት ሌላው ቀርቶ እዚህ ምድር ላይ አብረውህ ያልነበሩትን የቀድሞ ትውልድ ሰዎችና አብረውህ የማይኖሩትን የመጪው ትውልድ ሰዎችን ማውራት ትችላለህ።ይህ ደግሞ ከምንም በላይ ትልቅ ዋጋና ትርጉም ያለው አስደሳች እሴት ነው።”(ኬንኮ ዮሺዳ)

56.“ሠዎች ህይወትን አንድ የሆነ ነገር ነው ብለው
ይገልፃሉ። ለእኔ ግን ህይወት ማለት ማንበብ ማለት ነው።” (ሎጋ ስሚዝ)

57.“ማንበባቸውን ተከትሎ በየዘመናቸው ታላቅ ስራን የሰሩ ጀግኖች ቁጥራቸው ስንት ይሆን?”(ሔነሪ ዳቪድ)

58.“መፅሀፍትን ስናነብ አእምሯችን ራሱን የቻለ አንድ አስደሳች ኮንሰርት ተዘጋጀለት ማለት ነው። ታዲያ አእምሯችን ደስተኛ በሆነበት ሰዓት ደግሞ የሚያስባቸው ሃሣቦች ምን ያህል ጠቃሚና የጠለቁ እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን።” ስቴፋኒ ማላርሜ)

59.“መፅሀፍ የሚያነቡ ሠዎች ብቸኝነት አያጠቃቸውም።”(አጋታ ክርስቲ)

60.“መፅሀፍ ማንበብ ነፍስን ያክማል።”(በቴክሳስ
ላይብረሪ መግቢያ ላይ የተፃፈ)

61.“መፅሀፍ የሌለበት መምሪያ ቤት ማለት መስኮት የሌለበት ቤት ማለት ነው።”(ሎነሬች ማን)

62.“ሠው መንፈሱን መመገብ የሚችለው መፀሀፍትን በማንበብ ብቻ ነው።”(ኤድዊን ማርክሃም)

63.“የተራበ ከብት ሳር ሲግጥ የሚሰማውን ደስታ ይህል ነው የሠው ልጅም መፅሀፍትን ሲያነብ ከፍተኛ ደስታን የሚያገኘው።”(ሎርድ ቸስተርፌልድ)

64.“አንድ ሠው ለልጁም ሆነ ለመላው ማህበረሰብ ከሚሰጠው ስጦታዎች ሁሉ ትልቁ አንብቦ ሰዎችን እንዲያነቡ ማስቻሉ ነው።”(ካርል ካጋን)

65.“ልጆቻችንን ዝም ብለን አይደለም አንብቡ ብለን እንዲያነቡ ማድረግ ያለብን። ይልቁንም በማንበባቸው በጣም ደስተኞች እንዲሆኑና ደጋግሞ የማንበብ ፍቅር እንዲያድርባቸው የሚያደርጉ ነገሮችንም አብረን ማድረግ ይጠበቅብናል።”(ካትሪና ፒተርሠን)

66.“ከየትኛውም መዝናኛ በላይ እንደማንበብ ዋጋው ርካሽ ሆኖ በቀላሉ የሚያዝናና ነገር የለም። ደግሞም በማንበብ እንደሚገኘው ዘለቄታዊ ደስታ ሌሎች መዝናኛዎች ዘላቂ ደስታን አይሠጡም።”(ሌዲ ሞንታኑ)

67.“እኔ ዘወትር የማስበው በቀጣይ ስለማነበው መፀሀፍ ብቻ ነው።”(ሮኦልድ ዳህል)

68.“መፅሀፍትን ማንበብ መታደል ነው። ምክንያቱም ባነበብን ቁጥር አለማችንን በሚገባ እናውቃታለንና።”(ኒል ጌይንማን)

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋልና ሁላችንም በማንበብ ራሳችንን በእውቀት ልንገነባ ይገባል የዘወትር ምክሬ ነው::

/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የከበደ ሚካኤል
መጽሐፍት ሙሉ በመደብራችን ይገኛሉ!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የአቤ ጎበኛ ሥብስብ ሥራዎች መጽሐፍ
፩ እድል ነው በደል
፪ የሀሜት ሱሰኞች
፫ ሬትና ማር
፬ ከልታማዋ እህቴ
፭ መስኮት
፮ ጎብላንድ የተሰኙ ሥብስብ ሥራዎች ከአምስት አመታት በፊት በኤዞፕ መጽሐፍት በአንድ ጥራዝ ታትመው የነበረ ቢኾንም ከገበያ ጠፍተው ነበር።

አሑን አምስት ቅጅዎች ብቻ እጃችን ላይ ይገኛሉ !!


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እውቁ ተርጓሚና ደራሲ
አማረ ማሞ

የካታካምቡ ሰማእታት ታሪክ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የዓለም ሎሬት

ፀጋየ ገብረ መድኅን !!!

ሥራ የሆነው በልግ ትያትር !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ትንሽ ቅጅዎች ብቻ አሉን
ለገበያ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው መጽሐፍ የተቀነጨበ !!!!

👉...ምክንያቱም እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ የሰጠው ሥጋዊም መንፈሳዊም ሀብት ስለኾነ ኹሉም የተሟላ ስለኾነ ሕዝብም በሥጋዊም በመንፈሳዊም ዕድል ተጠቅመውበት ኖረዋል፡፡ ይኽም በመኾኑ በዓለም የተነሡ አምባገነኖች ኹሉ አንድ መንደርና አገር ሳይኾን አህጉርን እየደመሰሱ አንድ አድርገው የራሳቸውን ስም በአስጠሩበት በዚያ ረጅም የታሪክ ዘመን ኢትዮጵያ አልተደፈረችም፡፡

👉የዓለም ኃያላን እነታላቁ እስክንድር ፣ ናቡከደነፆር ፣ ፈርዖናውያን ፣ ምሥራቃውያን ሮማውያን ወይም የቊስጥንጥንያና ሌሎችም ቢኾኑ ብዙ ሀገሮችን እንዳልነበሩ አድርገው ክብራቸውን እየገሠሡ ሲረግጧቸው ፤ በኢትዮጵያ ግን ይኽ አልደረሰም ። የፈረንሳዩ ንጉሥ ናፖሊዮን ብዙ አገሮችን ከመድፈሩ የተነሣ እንግሊዞች”በአሁኑ ጊዜ የዓለምን ካርታ ጠቅልሎ ማስቀመጥ ነው እንጂ በምንም አይጠቅምም” ብለው ነበር፡፡

👉 ግን የኢትዮጵያ ክብር እስከአሁን ድረስ በቸርነቱ ተጠብቆ ኖሯል ። ለዚህ ኹሉ ጕልበቲቱ ቤተ ክርስቲያን ናት እንጂ ሰው አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን በትከሻዋ ተሸክማ የኖረች ዛሬ ልጆቿ ያጠቋት የናቋት የረገጧት ቤተ ክርስቲያን ናት እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ ይኽቺው ናት፡፡ ይኽም ታሪክ የሚያውቀው እውነት ነው፡፡ ዓለምን ሲያስቸግር የነበረው ገናና መንግሥት ታሪክ ኢትዮጵያን ተጋፍቷል፡፡ ግን አልቻለም አላሸነፏትም፡፡ ጣሊያን ግብፅ ድርቡሽ ያለአንበረከኳት”ታላቂቱ ኢትዮጵያ" ተብላ የኖረችበት ጕልበቱ የቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ያውም የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጕልበት ነው፡፡ በዚህ ብርሃን ኢትዮጵያ ተጠብቃ ኖራለች፡፡

👉 በዚያን ጊዜ”እንኳን አደረሳችሁ” ማለት እጅግ የሚያስደስ ትና የሚያኰራ ነበረ፡፡ ሕፃናት ልጀገረዶች አበባ ይዘው ሲዘፍኑ ጐልማሶች”ሆያ ሆዬ" ሲሉ የሚያስቀና ነበረ፡፡ ”ነበር” ብለን መናገር ብቻ ነው የምንችለው፡፡ አሁን አለ ማለት አንችልም፡፡ እንደታሪክ ይወራ ይኾናል ከዚህ የነበረው አለ ማለት ግን አንችልም፡፡ ጭምጭምታው ሊኖር ይችላል፡፡

👉 ነገር ግን ሥርዓቱም ኾነ ሕጉ ሙሉ በሙሉ የለም፡፡ ይኽ እንዴት ሊኾን ቻለ? በውጪ ኃይል አይደለም፡፡ ከራሳቸው ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ ኢትዮጵያ የተጐዳችው በልጆቿ እንጂ በባእድ ጠላት አይደለም አንበጣና ሸረሪት ጠላቶቻቸው ልጆቻቸው ናቸው ገድለው የሚበሏቸው፡፡ እናቶቻቸው ሌላ ጠላት የላቸውም፡፡

👉 ኢትዮጵያንም ከዚህ ማጥ የአስገቧት የራሷ ልጆች እንጂ ሌሎች አይደሉም፡፡ ባእዳን ሞክረው ሞክረው አቅቷ ቸው ቀርተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን የሌሎች ጥገኛ ኾነው የሌሎችን መርዝ እየቀሰሙ የሌሎችን ጠባይ እየተዋሱ እንደገና መልሰው እናት አገራ ቸውን በማጥቃት አገራቸውን አዳከሙ፡፡ ለጠላቶቿ አሳልፈው እየሰጧት ነው፡፡ እኔ በእውነት በዚህ ጊዜ ውስጥ”እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋ ገራችሁ” ብዬ ለመናገር ያቅተኛል፡፡ እንኳን ከሞት ወደሕይወት አሸጋገ ራችሁ ማለቱ ደግሞ ይቀፈኛል፡፡ በጣም የሚያስቸግር ነው፡፡

👉 አሁን ያለንበት ኹኔታ የሚያስቀይም አሳፋሪ ነው፡፡ የየትኛው አገር ሕዝብ ነው የራሱን ሕዝብ ወንድሙን ለይቶ በአሽሙረኞች በተንኰለኞች አድማና ሤረኛ ዐመፅ ለኹለት ተከፍሎ ሰዎቿ የሚፋጁባት አገር ? ከኢትዮጵያ በቀር የማንም አገር የለም፡፡ ምን መጣ? ከየት መጣ? ይኽ ዐይነቱ መናከስ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ታሪክን ተከትሎ አንዳንድ ነገሮችን መጥቀሱ ደግሞ ባለጋራ ከመፍጠር በስተቀር የሚጠቅም ነገር የለውም፡፡

👉 ይኽ ኹኔታ ወንዝ እየለዩ ሲዋጉ ከነበሩ ክፍሎች ተወርሶ ዛሬ ደግሞ መላው ኢትዮጵያ ከኹለት አካፍሎ የሚያስተላልፍ ሥርዐት እስከጦር የተደረሰበት ኹኔታ የሚያሳፍርም የሚያስቸግርም ነው፡፡ ይኽ ለምን ይኾናል? የዕድሜ ባለጠጐች የሉም፡፡”ዐዋቂ ዎች ነን" የሚሉ የሉም?
እንደድሮው መስቀል ይዘው ፅናሕ ይዘው ጸሎት አስይዘው በመኻል ተገኝተው የሚያስታርቁ ካህናት አሉ ማለት አልችልም፡፡ ትልቁም አሳፋሪ ነገር ይኸው ነው፡፡

👉 ከጳጳሳቱ እስከካህናቱ ድረስ እግዚአብሔርን የዘነጉ ክብራቸውን የተዉ አገራቸውን የጠሉ ዐመፀኞች በመነሣታቸው ምክንያት ሕዝቡ እርስ በርስ ሊጫረስ ተዘጋጅቷል ማለት ይቻላል፡፡

👉 ይኽቺን አገር አጥፍቶ ለሌላ ከማውረስ ተቻችሎ አገርን የራስ ከማድረግ የትኛው ነው የሚሻለው? የማይኾን ከኾነ የማይቻል ከኾነ በሌላ አገር ዜና እንደምንሰማው ሥልጣናቸውን እየለቀቁ የሚሔዱ መሪዎች መኖራቸውን ታሪክ የሚናገረው ነው፡፡ ራሳቸው አሳዳሪዎቹ ይኽ ነገር ከአቃታቸው ሕዝቡ ኹለቱንም መሪ አስቀምጦ ኹለቱንም ተዋጊዎች አሳርፎ አገሩን ለምን ራሱ አይመራም? ይኽ በጣም ያሳዝናል፡፡ በጣም አዝናለሁ፡፡ ለጥያ ቄያችሁ መልስ ለመስጠት ያቅተኛል፡፡

ሰማዕት ዘእንበለ ደም ዳግማዊው ዲዮስቆሮስ ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ባህልና ታሪክ በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ እንደተናገሩት።

ምንጊዜም ምርጥ ምርጥ መጽሐፍትን የምትሸምቱበት ቤት ኤዞፕ መጽሐፍት።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት መጽሐፍቶችን አስገብተናል።

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የተለያዩ የአማርኛ አጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህንን መጽሐፍ በተለይ ረጅም ጽሑፍ ማንበብ ለማይዎዱ ሰወች እንዲያነቡት የሚመከር እጅግ አጭርና ታላቅ ትምህርትን የሚያስተምር የኤፒክቲሲዝም ሥነ ምግባራዊ/ ሞራላዊ አስየምህሮ ያለው መጽሐፍ ነው።
ኤፒክቲተስ ከአለማችን ዝነኛ መጽሐፍት አንዱ ሆኖ ከ50 ሚሊየን ቅጅች በላይ የተነበበና ታላቅ ተቀባይነትን ካተረፉ ዝነኛ መጽሐፍት መካከከል የተመደበ መጽሐፍ ነው።

ከኤፒክ በኃላ የተነሱ ምሁራን የኤፒክቲተስ አስተምህሮ ኩለት አይነት አንድምታ እንዲኖረው አድርገውታል። #ሴፒክቲተስና ኤፒክቲተስ። ኤፒክቲተስ የዚህ መጽሐፍ ዋና አስተምህሮና ለትርጉም ያበቃነው ቀጥተኛው ትምህርት ነው።

#ኤፒክቲስ ሲሆን የአእምሮአዊ ፍልስፍናን ውስጣዊነትን የህይወትን ውስጣዊ አስተሳሰብን ማንበብን ማሰላሰልን ይወክላል። #ሴፒክቲተስ ሲሆን ግን ስጋዊነትን መብላትን መጠጣትን ወሲብ ማድረግን በስጋ የመኖርን አካልን የማስደሰትን ፍልስፍና ይወክላል።

#በመሆኑም ይህ መጽሐፍ ወደ ውስጥ መመልከትን ራስን መግራትን ማሰብን መልካምነትን ይሰብካል። መጽሐፉ የዛሬ 2000 ዓመት በፊት የተፃፈ ሲሆን መጽሐፉ የተሰየመው በመጽሐፉ ደራሲ በኤፒክቲተስ ስም ነው።

ዘመናዊው የ ፍልስፍና ትምህርት ኤፒክን የእስቶይኪዝም ፍልስፍና መሰረት አድርጎ ይወስደዋል። እስቶይኪዝም የአርምሞ ወደ.ራስ የመመልከት ውስጣዊ ስሜትን የመረዳት ፍልስፍናዊ መሰረትነት ያለው የፍልስፍና መስክ ነው።
በመሆኑም ይህ` መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አማርኛ በክብረወሰን ገብረ አምላክ ተተርጉሞ በናምሩድ ዘርዓ ያዕቆብና በያቆብ ብርሃኑ የአርትኦት ስራው ተሰንዶ ለንባብ በቅቷል። እነሆ ይህንን መጽሐፍ በትንሽ ሂሳብ ብዙ የምታተርፉበት በመሆኑ ሸምቱና የግለወት ያድርጉ.።
በእጅጉ ታተርፉበታላችሁ።

ንባብ ሰፍቶ እጅግ በዝቶ እውቀት በዝቶ ማየት ህልማችን ነው. ተቀላቀሉን ..!

Читать полностью…
Subscribe to a channel