ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21
መርሳት፤ አንዱ ጥበብ፣ ሌላው ጀሃነብ!
__
(Written by ዓለማየሁ ገላጋይ)
_
❨...ለመዳረስ ያሰብኩባትን ሃያት ሬጀንሲ ረስቼ በማለፍ ራሴን መገናኛ ሳገኝ አለቅጥ ስለተለጠጠው ዝንጉነቴ ተሸማቀቅሁኝ። ይኼ ጦማር ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞም እንደገለጠኝ....❩
____
ስለመርሳት ሳስብ ሁለት ሰዎች አስታውሳለሁ፤ አንዱ… በመርሳት የታወቀ፣ ወይም የመርሳት ተሰጥኦ ያለው አለበለዚያም የመርሳት ችግር ያለበት አንድ ልጅ አለ፡፡ ለመርሳት ፣ የሚያሳየው ፍጥነት ከዕለት ወደ ዕለት ጨምሮ ወደ መጨረሻ ገደማ እያወራም መዘንጋት ጀመረ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡-
አንድ የጎረቤት ሰው መጥቶ ‹‹ቹቹ፤ እናትህ አለች?›› ሲለው
‹‹የለችም›› ብሎ ይመልሳል
‹‹የት ሄደች?›› የሚል ጥያቄ ሲደገምለት እረስቶ
‹‹ማን?›› ብሎ መልሶ ይጠይቃል
‹‹እናትህ?›› ሲሉት
‹‹እራስህ እናትን›› ሲል ለፀብ ይጋበዛል፡፡
…ሌላኛውን የተዋወቅሁት ነፍሱን ይማርና በአያሻረው (አስማማው ኃይሉ) ወግ ነው፡፡ አሜሪካ ውስጥ ለሠላሳ አምስት አመታት የኖረ የኢህአሠ (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ሠራዊት) ታጋይ ነው፡፡ በመጨረሻ ዕድሜው ላይ ሁሉን በመርሳት የአእምሮ ህመም (Alzheimer) ተያዘ፡፡ ዘመድ፣ አዝማድ ብቻ ሳይሆን ቋንቋ ሁሉ ጠፋው የአፍ መፍቺያ ቋንቋ ተራ ቱማታ በሆነበት ወቅት አንድ ቃል ብቻ አልጠፋውም ነበር፤ ያም ቃል የትግል ሥሙ የነበረ ነው፡፡ ‹‹በትግል ስሙ ሲጠሩት ይዞራል›› ብሎ አያሻረው አለቀሰ፡-
በእርግጥም ያስለቅሳል፡፡ ያ የትግል ሥም ምን ትኩረት ቢሰጠው፣ እየትኛው የአንገሉ ጥግ ቢወሽቀው ትውስታን ሁሉ ከሚያጠፋው የአእምሮ ወረርሽኝ ተረፈ? ከበሽታው በላይ የትግል ሥሙ ተአምር አይሆንም? ከበሽታው ባሻገር በዓመታት መግፋት በራሱ ጊዜ ሊጠፋ አይገባውም ነበር?
….. ሰው እራሱ ተአምር ነው፡፡ ትኩረት የማይሠጠው በሰከንዶች ሽራፊ ከአእምሮው ሲያስወግድ፤ አክብዶ ያየውን ደግሞ እንደ መክሊት ላያተርፍበት አእምሮው ውስጥ ቀብሮት ይኖራል፡፡ ከማስታወስ ይልቅ መርሳት እንደ ጉድለት ስለሚታይ፣ የሰው ልጅ የመሳትን ምንጭ ለማግኘት ብዙ ዳክሯል፡፡ የሥነ ልቡና ምሁራን፤ ለምን እንረሳለን? ለተሰኘው አውራ ጥያቄ መንታ ምላሾችን ያቀርባሉ፡፡ አንዱ ሊታወስ የሚባው መረጃ፣ ከቦታው ሲጠፋ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መረጃው ቢኖርም አንቅቶ ለመጠቀም ሲያዳግት ነው ይለሉ፡፡ ነገርየው የቀበሌ መዝገብ ቤት መሰለ እንዴ? ‹‹ፋይልህ ጠፍቷል›› ለካ ተፈጥሯዊ ነው? ስንቀጥል….
….. ስለመርሳት ሳስብ ሌሎች ሁለት ሰዎች ትዝ ይሉኛል፡፡ አንዱ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ በርናንዶ ሾ ነው፡፡ በባቡር ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ እየተጓዘ ነው፡፡ ፊርማታ ላይ ትኬት ተቆጣጣሪው፤ ሾ ወዳለበት ፋርጎ ገብቶ፡-
‹‹ትኬት አውጡ፣ ትኬት›› ሲል ጮኸ፡፡
ሾ ከተመሰጠበት ተናጥቦ ትኬቱን መፈለግ ይጀምራል፡፡ የደረት ኪስ፣ የጎን ኪስ፣ የኋላ ኪስ፣ የውስጥ ኪስ፣ የቦርሳ ኪስ፣ የምስጢር ኪስ፣ የፓንት ኪስ…. ትኬት የለም፡፡ ተበሳጨ፡፡ የፈተሻቸውን ኪሶች መልሶ ፈተሸ፤ አጣው፡፡
ትኬት ተቆጣጣሪው ትኬቱን እንዳጣው ስለገባው፤
‹‹ሚስተር ሾ፣ እርስዎን የማያውቅ ሰው የለም፡፡ ቀስ ብለው ይፈልጉት፤ ካጡትም ግዴለም፤ እርስዎ ያጭበረብራሉ ተብሎ ስለማይታሰብ ይጥፋ!›› አለ፡፡
ሾ ቱግ ብሎ፤ ‹‹ትኬቱን ላንተ የምፈልገው መስሎሃል? ለእኔ ነው፤ የምሄድበት‘ኮ የተፃፈው ትኬቱ ላይ ነው›› ለካ መሄጃው ጠፍቶታል፡፡ ይሄ መርሳት የጭንቀትላት ጉድለት አይሆን እንዴ? የሾን የመርሳት ልክፍት በሁለተኛው በአይዛክ ኒውተን እናፅናው፡፡
የሒሳብ ሊቅ ሰር አይዛክ ኒውተን፤ በሥራ ከሚጠመድበት ክፍል ፊት ለፊት ጠረጴዛ ላይ የሚመገበው ይቀመጥለት ነበር፡፡ እንዳይረበሽ ነው፡፡ በሆነ ሰዓት ወጥቶ ይመገብና ተመልሶ ይገባል፡፡ አንድ ቀን ግን አንድ ወዳጁ በቀጠሮ መጥቶ ሲጠብቀው፣ የምግቡን ጥሪ መቋቋም ተሳነው፡፡ በዚህ ላይ ርቦታል፡፡ ቀርቦ መመገብ ጀመረ እስኪጨርስ ድረስ ኒውተን አልወጣም፡፡ በኋላ ብቅ ሲል ሰሃኑ ባዶ ነው፡፡ እንዲህ አለ፡-
‹‹አይ የኛ ፈላስፎች ነገር! እራት ያልበላሁ መስሎኝ ልበላ መውጣቴ ነበር፡፡ ለካ አቀላጥፌው ኖሯል፡፡ (How absent we philosophers are, I realy thought that I had not dined)
አለማስታወስ የበሽተኞች ወይም የደደቦች አለበለዚያም የልበ-ቢሶች ብቻ እንዳልሆነ በበርናርድ ሾ እና በኒውተን ያረጋገጥነው ጉዳይ ይመስላል፡፡ ታዲያ መርሳት ምንድነው? የማነው? ጉዳት አለው? ጉዳቱ እንዳለ ሆኖ ጥቅምስ? እያልን በጥያቄ መታጠር የሰው ልጅ ሁሉ ባህርይ ነው፡፡ የቼኩ ደራሲ ሚላን ኩንዴራ (Milan Kundera) መርሳት ላይ ያተኮረ አንድ ልቦለድ አለው፡፡ “The book of Laughter and Forgetting” የሚል፡፡ ገፀ-ባህሪዎቹ እንደ ደሴት የተከፋፈሉ ታሪኮችን የሚያስተዳድሩ (እንደ አዳም ረታ) ናቸው፡፡ የአንዱ አንባ ታሪክ ገዢ ሚርክ (Mirek) ማስታወስን የሥልጣንና የበላይነት ምንጭ አድርጎ የሚናገርበት ጥቅስ አለው፡፡ (The struggle of man against power is the struggle of memory against forgetting) ይላል፡፡ ትውስታውን የሚያነቃ የኃይል ባለቤት ከሆነ፣ የማያነቃው የደካማነት ድልድል ውስጥ ይገባል ማለት ነው? እንዲህ ከሆነ በዝንጋኤ ታሪክ የተጥለቀለቀ የህይወት ታሪክ ያላቸው ደራሲዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ የሂሳብ ሊቆች … እንዴት ማስደግደግ ቻሉ?
ጀርመናዊው ፈላስፋ ፍሬዲሪክ ኒች (Friedrich Nietzsche) በመርሳት ላይ የኩንዴራ ተቃራኒ አቋም ያለው ይመስላል፡፡ ነገሮችን ለመርሳት አለመቻል፤ ለመኖር አለመቻል ነው በሚል፡፡ ታሪክን (ታሪክ ማስታወስ አይደል?) የሚያብጠለጥል አንድ መፅሐፍ አዘጋጅቷል- “Disadvantage of History for life” የሚል እዚህ መፅሀፍ ውስጥ እንዲህ የሚል አባባል አለ፡-
“መርሳት ባይኖር መኖር ጨርሶ አዳጋች ይሆን በነበር” (without forgetting it is quite impossible to live at all)
ለሰው ልጅ የማስታወስ ጥበብ ብቻ ሳይሆን የመርሳት ክህሎትም ያስፈልገዋል ማለት ነው፡፡ ነገሮችን በመርሳት የሚቸገሩ እንዳሉ ሁሉ ለመርሳት ባለመቻልም የሚሰቃዩ ሞልተዋል፡፡ በቀላሉ የጦርነት፣ የግርግር የሽብር ሰለባ የሆኑ ግለሰቦችን ማሰብ ይበቃል፡፡ በቀይ ሽብር ዘመን ልጆቸውን ያጡ አንዲት እናት ታሪካቸውን ሰምቻለሁ፡፡ ልጃቸው ከተገደለ ከአርባ ዓመት በላይ ቢያስቆጥርም እናቲቱ አሁንም የልጁን አልጋ እያነጠፉ፣ ቤቱን እየጠረጉና ውኃ በጠርሙስ እየሞሉ ‹‹አትንጫጩ፣ ይተኛበት” ይላሉ አሉ፡፡ ይሄ መርሳት አለመቻል፣ ከእውነታ ሲያቆራርጥ አይደለም? ታዲ ኒች… ይሄን እንጂ ሌላ ምን አለ?
ስቲፈን ካርፔንተር (Stephen Carpenter) የኒቼን ሀሳብ የሚደግፍና የሚያስደግፍ አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ካርፔንተር መዘንጋት ያለባቸውን በብዛት ይመጥናቸዋል እንጂ እንደ ኒቼ በጅምላ አይፈርጅም፡፡ እንዲህ ይላል፡-
“ከሦስት ዓመት በፊት ዕድሜያቸው በሠላሳዎቹ ያሉ ባለጠጋ የሚባሉ ጥንዶች ለምክር ወደ እኔ ይመጣሉ፡፡ ከተጋቡ ገና ሁለት ዓመት አልሞላቸውም፡፡ ከጋብቻ በፊትም ብዙም አይተዋወቁም፡፡ ፍቅር ጠናብን
ብለው በችኮላ ነው ሰርጉንም ያጣደፉት፡፡ ትዳር ጣፋጩንም መራራውንም አጣምራ የያዘች እንቆቅልሽ መሆኗንም አልተረዱትም
ነበር፡ ጫጉላ ሽርሽሩ ሁሌም የሚቀጥል ሳይመስላቸው አልቀረም፡፡
“ሚስትም በተደጋጋሚ የምታነሣው አያዳምጠኝም የሚል ነበር፡፡ ባል በቅሬታዋ ግራ ሳይጋባ አልቀረም፡፡ ስትናገር እንኳን አቋርጫት አላውቅም፡፡ እርሷ ራሷ ምስክር ናት ይላል ደጋግሞ፡፡ ለካስ ነገሩ ሌላ ነው፡፡ “ስሜቴን አይረዳልኝም፤ ሲከፋኝ እንኳ ልብ አይለውም፡፡ ፍላጎቴን ለመረዳት ትዕግሥት የለውም፡፡ እያዋራሁት ዓይኑ ሌላ ቦታ ነው
የሚያዬው፤ ጆሮው ቢሰማም ወደ ልቡ አይዘልቅም' እያለች ሚስት ናዳውን አወረደችው፡፡
“እንዲያውም በሚገርም ሁኔታ ሲከፋኝ ከባለቤቴ ይልቅ ውሻችን መከፋቴን ዐውቃ ከጎኔ ተኮራምታ ትቀመጣለች፡፡ ሳለቅስ ቆይቼ ፊቴ ተለዋውጦ እርሱ ወደ ቤት ሲገባ እንኳ ምን እንደ ሆንኩ ስለማያስተውለው አይጠይቀኝም' አለች
“ያንጊዜ ነው ባል የባነነው፡፡ በእርግጥ አስተዋይ ሰው ነበረ፡፡ በሴትና በወንድ መካከል ያለውን የስሜትና የአረዳድ ልዩነት ለማስረዳት ስሞክር ነው ነገሩ የገባው፡፡ መፍትሔ ባይኖርህ እንኳ ሚስት ችግሯን ስትረዳላት መፍትሔ ያገኘች ያክል ይሰማታል፡፡ ሴት አዛኝ የመሆኗን ያህል ቶሎ መደሰትም ቶሎ መከፋም ያጋጥማታል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ጠባያቸው እንደ ማዕበል ይወጣልም ይወርዳልም፡ ዋናው ቁም ነገሩ ማዳመጥ ማለት በሚስህ ጫማ ራስህን አድርገህ ስሜቷንም፣ ፍላጎቷንም፣ ነገሯንም
በአጽንዖት መከታተልና ለብሶቷ ዕውቅና መስጠቱ ላይ ነው፡፡ ስትከፋ ስታባብላት ኀዘኗን ፈጥና ትረሳዋለች፡፡ ከማንም ይልቅ ተስፋ
የምታደርገው አንተን ነውና የሚሉ ሐሳቦችን ተለዋወጥንና ተሰነባበትን” አለና ዶ/ር ኦባንግ በዝምታ ተዋጠ
📚ትዳር ወግ
✍በትእዛዙ ካሣ
ለንባብ መጎልበት ሁሌም እንተጋለን።
አንዳንድ ሰዎች ይዘነጋሉ፦ እንደ ዘበት
ሕያውነት ያለው ታሪካቸው ከካፍቴሪያ እና ከባልኮኒ እንዲህ ነበር ከሚል ተረት ከፍ ሳይል፤ ወረቀት ሰማይ ላይ ኮከብ ሕይወታቸው ሳይጻፍ፣ ብራና ቀፎ ላይ ማር መሰል ምስላቸው ሳይቀለም፣ ክንፋም ደራሲያን ዘንግተዋቸው፣ ውበት ናፋቂ ሠዓሊያን ቸል ብለዋቸው፤ የአዳማጩን መዳፍ በአንደበት ላይ ማስቀመጥ የሚችል አስገራሚነታቸው፣ በግድየለሽነት ተዘንግቶ አስቀድመው እነርሱ… ቀጥሎም ታሪካቸው ሕይወት መዳፍ ላይ እንደ ቅዠት እይታ ይሆናል፡፡
ተረስቶ ምክንያቱም ይሄ ሕልም መሰል ዓለም ለእንዲህ አይነት እውነተኞች ጆሮው ዝግ ነውና፡፡ ምክንያቱም ይሄ የአመንዝራዎች ዓለም ለእውነተኛ አፍቃሪዎች ዓይኖቹ ክዱን ናቸውና፡፡ ምክንያቱም ይሄ ኤሊ ዓለም ለሕይወት በክንፋሞች መጠን አይደለምና፡፡ የዚህ ዓለም መጠኑ በሌብነቱ አንቱ ለተሰኘ ሰርቆ በማግኘቱም ለሚጨበጨብለት ከድሆች ጉረሮ እና ጉረኖ መንትፎ በገነባው ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ለተመሸገው ነው፡፡ ይህ ዓለም ለእንዲህ አይነቶቹ እንጂ በየጥጋጥጉ ላሉት ለአንዳንዶቹ አይደለም፡፡ በየጥጋጥጉ ጥቂቶች አሉ፡፡
ከብዙዎቹ የተለዩ ፀጥ ያሉ ሲመስለን የሌሉ ሲመስለን ተሰምቶ የማይጠገብ ውብ የሆነ የግላቸውን ዜማ ዘምረው የሄዱ፡፡ ደብዛዛ ሲመስሉን በህይወት ሰማይ ላይ ከብርሃን ይልቅ ያንፀባረቁ
… … በየጥጋጥጉ የሚረሱ የሚዘነጉ አንዳንድ ሰዎችን ድርሰት ሆነው ሳሉ ሳይጻፉ ስለመቅረታቸው እያሰብኩ፡፡ ሕያው ሆነው ሳሉ ከታሪክ በመፋቃቸው ተዘንግተው ማሸለባቸውን እያሰብኩ፡፡
አንዳንድ ሰዎችን እያስታወስኩ.....
✍ኤፍሬም ስዩም
የይሁዳ ድልድይ መጽሐፍ "ፕሮፌሰሩ" ጽሑፍ ላይ የተወሰደ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏🙏
እጅጉን ተወዳጅ ተነባቢነትን አትርፏል በ2_ሳምንታት ውስጥ በድጋሜ ለመታተም በቅቷል
አኹን ደግሞ ትንሽ ቅጅዎች ብቻ ቀርቶናል !!!
በተመጣጣኝ ዋጋ።
አስቼጋሪውን ዘመን የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ያትታል እነሆ በረከት ለወዳጅ ዘመድዎ የሚጋብዙት ድንቅ መጽሐፍ !!!!!!
የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ
/channel/azop78
/channel/azop78
[..] ሜሪ ሐስከል ግን ባደረገችው ነገር ለአፍታም ሳትኩራራ አንዲት ሴት በእህትነት፣በእናትነት፣ በፍቅረኝነት፣ በጓደኝነት፣ በሰውነት ልትሰጠው የምትችለውን ፍቅር ሁሉ ቅንጣት ታህል ሳትሸራርፍ እየለገሰች፣ በሐምራዊ የንቃት ክንፎች እየበረረ እልፍ መሻገሮችን እንዲያስስ አስችላዋለች። በ1914 እ.ኤ.አ ክረምት በጻፈላት ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡-
"The day will come when I shall be able to say, 'I became an artist through Mary Haskell... You have the great gift of understanding, beloved Mary. You are a life-giver, Mary. You are like the Great Spirit, who befriends man not only to share his life, but to add to it. My knowing you is the greatest thing in my days,and nights, a miracle quite outside the natural order of things.>>
‹‹አንድ ቀን የሆነ ቀን ‹‹የጥበብ ሰው የሆንኩት በሜሪ ሀስከል ምክንያት ነው›› የምልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ [...] ውድ ሜሪ አንቺ እጅግ የበዛ ሰዎችን የመረዳት መክሊት የተሰጠሽ ሰው ነሽ፡፡ ሕይወትን አዳይ ነሽ። አንቺ ለመጋራት ሳይሆን ሕይወቱን ለማበልጸግ የሆነን ሰው እንደሚወዳጅ ታላቅ መልዓክ ነሽ፡፡ በኑረት ዘመኔ ከአንቺ ጋር መተዋወቄ ከምልዓተ ዓለሙ ተፈጥሯዊ ስልተ ምትና ስልተ ስሪት ውጪ የሆነ አስደናቂ ተዓምር ሆኖልኛል፡፡››
ሜሪ፣ ካህሊል በኪናዊ ምጥቀቱ ከፍ ባለበትም ይሁን በሞራል በተሽመደመደባቸው ጊዜያት ሁሉ ያለማመንታት ከጎኑ ነበረች።
ተፅዕኗቸው ከሜሪ ጋር ለንጽጽር የሚቀርብ ባይሆንም ሌሎች በርካታ ሴቶች በካህሊል ሕይወት ነበሩ፡፡ እርሱም ስለ ሴቶች እንዲህ ብሏል፡-
"womene open the window of my eyes and the dorrs of my spirit. Had it not been for the woman-mother, woman-sister and woman- friend, I would have been sleeping among those who disturbe the tranquility of the world with thier snoring.
‹‹የዓይኔን መስኮትና የመንፈሴን በሮች የሚከፍቱት ሴቶች ናቸው፡፡ እናቴ፣ እህቴና ጓደኛዬ የምላቸው ሴቶች ድጋፍ ባያደርጉልኝ ኖሮ፣ ዛሬ እኔም የዓለምን ጸጥታና እርጋታ
በማንኮራፋት ድምጽ ከሚረብሹት ሰዎች መካከል ተጋድሜ ሳንጎላጅ እገኝ ነበር፡፡››
አዎ የካህሊል አማልክት ሴቶች ናቸው፡፡ እህቱ፣ እናቱ፣ ሜሪ ሐስክል፣ ሜሪ ዚያዴ... ሌሎችም፡፡ የሁለቱ ጓደኛሞች ደብዳቤዎች የተጠናቀሩበትን የዚህን መጽሐፍ
(Beloved prophet) አርትኦት የሰራችው ቨርጂኒያ ሂሉ (Virginia Hilu) ለዚህ መጽሐፍ በጻፈችው መግቢያ እህቱ ማሪያና እና ሜሪ ሐስክል በካህሊል ዙሪያ ያደሩት የነበረውን የሕይወት ድር በተመለከተ እንዲህ ብላለች።
" both women had simple tastes ,a purity of heart ,and a common Goal: to help Gibran, to enable him to develop his fullest in whatever area he choose. They were united in their belief in his greatness.>>
ራሱ ካህሊል ጅብራን በየካቲት 12 1908 እ.ኤ.አ ለጓደኛው አሜን ጉሬብ ቦስተን ስለመገኘቱ ምክንያት ሲጽፍ የሚከተለውን ሐሳብ አንስቷል፡፡ ‹‹and now since
you have heared my story you will know that my stay in Boston is neither due to my love for this city, nor to my dislike for new York. My being here is due to the presence of a she-angle who is ushering me towards a splendid future and paving for me the path to intellectual and financial success.>>
‹‹እንግዲህ ታሪኬን ሰምተኸዋል፡፡ እናም ቦስተን የመገኘቴ ምሥጢር ለከተማዋ ባለኝ ፍቅርም ሆነ ለኒው ዮርክ ባለኝ ጥላቻ መነሻነት አይደለም፡፡ ይልቁንስ እዚህ የመገኘቴ
ምሥጢር ግሩም ድንቅ ወደ ሆነ የሚያስጎመጅ ነገዬ የምትመራኝ፣ በሐብትም ሆነ በዕውቀት ልቄ እገኝ ዘንድ መንገዴን የምትጠርግልኝ መልዓክ አከል እንስት፣ አዎ ያቺ
ሴት እዚህ በመሆኗ ምክንያት ነው፡፡››
ሜሪ ሐስከል ትቀጥላለች፡፡ እ.ኤ.አ የካቲት 6 1912 ከቦስተን በጻፈችለት ደብዳቤዋ ላይ እንዲህ ትላለች፡-
"God lends me his heart to love you with l asked for it when l found my own was too small, and it really holds you, and leaves you room to grow. I do long to see your beautiful new picture. >>
‹‹እግዚአብሔር አንተን እወድበት ዘንድ ልቡን አውሶኛል፡፡ የእኔዋ ሚጢጢ ሆና አንተን ለመሸከም፣ ለማቀፍ ቢቸግራት እግዜር የእርሱን ይቸረኝ ዘንድ ጠየቅኹት። እናም በሚገባ ከመያዝ አልፋ የምታድግበት ሰፊ ክፍተት ትታልሃለች፡፡ አዲሱን ውብ የስዕል ሥራህን ለማየት ናፍቄያለሁ፡፡››
እውነትም ካህሊል ጅብራን ሁሉንም በመፈለግና ሁሉንም በማጣት ቅዝምዝም መሀል ተሰንቅሮ የጠፋ የቅጽብት ብልጭታ ነበር፡፡ ለሌላኛዋ በአካል አግኝቷት የማያውቅ
በካይሮ ነዋሪ የሆነች ዝነኛ ሊባኖሳዊት ወዳጁ ሜሪ ዚያዴ በጻፈላት አንድ ደብዳቤው ላይ ይህን የማረካ የነፍስ ጥማቱን እንዲህ ገልጾት ነበር፡፡
"l know that a little love does not please me either. niether you nor me are satisfied with little. we both want much. we both want everything. we want perfection."
‹‹ምጥን መውደድ ሊያረካሽ እንደማይችል አውቃለሁ፡፡ እኔም በጥቂት መፈለግ የሚደሰት ሰው አይደለሁም፡፡ እኔም ሆንሁ አንቺ በጥቂቱ የምንረካ ሰዎች አይደለንም፡፡ እንዲያውም ሁሉንም ፈላጊ ነን፡፡ መሻታችን ምልዓቱን፣ ፍጽምናውን ነውና።››
#የካህሊል #አማልክት
#ለመጽሐፉ #የተጻፈ #መግቢያ
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቍጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል። ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
Читать полностью…የYacob Berhanouን "ከባዶ ላይ መዝገን
" መፅሐፍ ያነበብኩት '…እዚህ
ሀገር ግልብነት ሰልጥኗል፣ በባህል እና ሀይማኖት ስም የበዛ ሀሳባዊነት
ተንሰራፍቷል፣ ስለ-ዓለም ያለን ግምት የተንሻፈፈ ነው፣ ከፍጥረቱ ልዩ ነን
የሚለው አባዜ ያበሽቀኛል፣ ቀለማችን ተመሳሳይ የቀለም ቀንዶቻችን አመሳሳይ መሆናቸው ያበግነኛል...እያልኩ ብዙ ብዙ በምብሰለሰልበትና በማወራበት ጊዜ አንድ ሁነኛ ሰው ጠቁሞኝ ነበር፡፡
፡
ያዕቆብ በመፅሀፉ ውስጥ ያካተታቸው ፅሑፎች ዳራ ታሪክን፣ ፓለቲካን፣ ኪነ ጥበብን እና ፍልስፍናን የሚዳስስ ሲሆን፥ በሒየሳ አንጥሮ በተምሰልስሎት አዳውሮ የፈተሸበት፣ በሰፊ ንባብ እና ጥልቅ ማሰላሰል ጥንቅቅ ብሎ የታጀበ የአናቅፃት ስብስብ ነው፡፡
``ከባዶ ላይ መዝገን`` አንዴ አንብበው እንደሚከድኑት አይነት መፅሐፍ ሳይሆን፡፡ ሁሌም መገለጥ የሚችል ክላሲክ ነው!
፡
√ ፍላስፍናዋቹ ይማርኩኛል
√ ተምሰልስሎቶቹ ይመስጡኛል
√ ሒሶቹ ይደንቁኛል
መፅሐፉን አምብቤ ስጨርስ የተናገርኩት "the future of ethiopian letrature is on the safe hand
" ብቻ ነበር የተነፈስኩት!
***
እነሆ አሁን ደግሞ በሌላ ስራው እነሆ በረከት ሊለን በዝግጅት ላይ ነው!
#የመሻገር_ሲቃ
#ከአውሎ_ንፋስ_ጋር_መደነስ
በቅርብ ቀን በመደብራችን ያገኙታል።
የዚህች መጽሐፍ አዘጋጅ በሴማውያን ቋንቋዎች በትዩቢንጌን (ጀርመን) ዩኒቨርሲቲ በዶክትሬት ማዕረግ ከተመረቁ በኋላ ወዲያው
ወደ አገራቸው በመመለስ መጀመሪያ በቤተ መጻሕፍት ወመዘክር በዲሬክተርነት፣ ቀጥሎም በአዲስ አበባና በሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህርነት ከ40 ዓመታት በላይ ካስተማሩ በኋላ በአሁን ጊዜ በጡረታ ላይ ይገኛሉ ሆኖም ግን ደhመኝ ሳይሉ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ልሳንና በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሥነጽሑፍ ክፍል ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሑፍ ሲያቀርቡ በአማካሪነት ይረዳሉ።
በመጽሐፏ አዘጋጅ ከዚች የመጨረሻዋ መጽሐፋቸው ጋር 27 መጣጥፎችና መጻሕፍት አዘጋጅተዋል: አዘጋጁ በማስተማር ተግባር ብቻ ሳይሆን በአስተዳደር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሌሎች ተቋማት ሥራ ተካፍለዋል: እነዚህም የሚከተሉት ናቸው: የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍል ሊቀመንበር (2 ጊዜ)፣ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም ዲን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ዲሬክተር፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ዋና ጸሓፊ በመሆን አገልግለዋል።
"ኩሪፊያ የሸፈነው ፈገግታ" ከአንድ ግለሰብ የግል ሕይወት መዘክርነት የላቀ ጠቀሜታ ያለው መፅሐፍ ነው። በዚህ መፅሐፍ አማካይነት አንባቢ በርካታና አስገራሚ የሕይወት ገጠመኞችን መቅሰም ይቻላል።
Читать полностью…ይነበበቡ
የዕውቀት ማዕድ📖
-----------------------------
ይቺን መጽሐፍ አነበብኳት እና ወደድኳት! እግዚአብሔር ይመስገን፤እንኳንም አነበብኳት።
ሰው የምግብ ማዕድ ከቤተሰቡ ጋር በፍቅር እና በአብሮነት እንደሚቋደሰው በየቤቱ የዕውቀት ማዕድ ዓይነት መጽሐፎች መኖር አለባቸው። ሰው ለልብሱ ቁምሳጥን ፣ለቴሌቪዥኑ እንድሁም ለስልኩ የሚጠነቀቀውን ያህል ለአዕምሮው ምግብ በሚገባ ማሰብ ይኖርበታል ብዬ አስባለሁ። ''ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም!'' መባሉ ለዚህማይዴል ወይ?
ይቺ መጽሐፍ ጨምሮ ከክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ መጽሐፎች እንድሁም ''ወዴት እያመራን ነው?'' ጋር ያዙ !
መግቢያ
ማመልከቻ ለወላጆች ብቻ
እባካችሁ ልጆችን እንርዳ፣
ሀገር እንዳንጎዳ!
ክፍል ሁለት
ተረቶች እና ታሪኮች ከሚለው አንድ፦
☞አልበርት አንስታይን ለልጆች ያደረገው ንግግር !
------------------------------------------------------
ውድ ልጆች! ዛሬ እናንተን በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል። እናንተ የዚች ብርሃናማና መልካም መሬት ወጣት ፍሬዎች ናችሁ። አስታውሱ! ዛሬ በትምህርት ቤቶቻችሁ የምትማሯቸው ጠቃሚ እባ ድንቅ ነገሮች ሁሉ የብዙ ትውልዶች የሥራ ውጤቶች ናቸው።በእነዚህ የሥራ ውጤቶች ላይ ብዙ የዓለም ህዝቦች ያለማቋረጥ ጉልበታቸውን አፍስሰውበታል።ይህ የሥራ ውጤት አሁን እናንተ የወረሳችሁት ታላቅ ጸጋ ነው። ይህንን ታላቅ ጸጋ ልትይዙት፣ልታከብሩት፣ልትንከባከቡት፣ ልትጨምሩበትና በታማኝነት ለልጆቻችሁ ልታስተላልፉት ይገባል። እኛ ሰዎች ሟቾች ነን፤ዘላለማዊ የምንሆነው በጋራ በሠራናቸው ቋሚ በሆኑ ነገሮች ነው።እነዚህን ቋሚ ነገሮች ስትይዙ የሕይወት እና የሥራ ምንነት ትገነዘባላችሁ።በተጨማሪ ለሌሎች ህዝቦች እና በተለያዩ ዕድሜ ላሉ ሰዎች ትክክለኛ አመለካከት ይኖራችኋል።
ልጆች ሆይ!!
ዕውቀት የሰዎች የልፋት ውጤት ነው።ዕውቀት ማለት የእውነት መፈለጊያ መሳሪያ ነው፤ ይህ ድንቅ ነገር ነው። እውነትን ፍለጋ በሰዎች ቅብብል ከዚህ ደርሷል፤ግን አላበቃም።ቅብብሎሹን ለማስቀጠልና እናንተም የድንቅ ነገሮች ባለቤት እንድትሆኑ በርትታችሁ ልትሠሩ ይገባል።
(ገጽ- ➑➍)
ከክፍል ሦስት
ድንቃድንቅ የተፈጥሮ ሁነቶች ደግሞ አንድ፦
☞የውሃ ጢንዚዛ !
…………………………
የውሃ ጢንዚዛ በውሃ ውስጥ ይኖራል።በውሃ ላይ እየተንሳፈፈ እያለ ከኋላው ጥላት ሲመጣበት የሚያመልጠው በፊንጢጣው ሣሙና መሰል ነገር በማመንጨት እና ወደ ኋላው በመርጨት ነው።ይህ ሣሙና መሰል ፈሳሽ በሚረጭበት ወቅት በሁለት መንገድ ከጠላት ይከላከለዋል።አንደኛ፣ፈሳሹ ከፍንጢጣው አስወጥቶ ወደ ኋላው በሚረጭበት ወቅት ራሱን ወደፊት ልክ እንደሮኬት ስለሚያስፈነጥረው በፍጥነት ያመልጣል።ሮኬት ወደ ሰማይ ሲተኮስ ጭሱ ወደ መሬት በሚወረወርበት ጊዜ ሮኬቱ ወደ አየር እንዲመጥቅ እንደሚያደርገው ማለት ነው። ይህ ሕግ የኒውተን ሦስተኛው ሕግ በመባል ይታውቃል።
ሁለተኛው ደግሞ ሣሙና መሰሉ ነገር በውሃው ላይ በሚጭውመርበት ወቅት የውሃውን የእርስ በርስ መሳሳብ ይቀንሰውና የውሃው መያያዝ ስለሚቀንስ ጠላቱ ወደ ውስጥ ይሰምጣል።
ልጆች ሆይ!!
ተፈጥሮ በብዙ አስደናቂ ነገሮች የተሞላች ናት።እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሲገጥሙን እንድናስብ እንድንመራመር መንገድ ይከፍቱልናል።የሰው ልጅ የተፈጥሮ ድንቃድንቅ ነገሮችን በመኮረጅ ብዙ ሥራ ሠርቷል፤ተመራምሯል፤እየተመራመረም ይገኛል።ስለዚህ ታዳጊ ወጣቶች በተፈጥሮ አስደናቂ ነገሮች መደነቅ ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደተከሰቱ፣ለምን እንደተከሰቱም ማሰብ እና መመራመር አለባችሁ።
(ገጽ -➊➊➎)
መልካም ቀን
እጃችን ላይ !!!!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
እጃችን ላይ !!!!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
እጃችን ላይ !!!!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
አንድ ፒስ ብቻ ናት
ብዙ ደምበኞቻችን ስለጠየቁን ለቀደመው መስጠት ግድ ይለናል !!!!
“መኖርን ለማስቀጠል ካሻህ መረሳት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡” (There are things that have to be forgotten if you want to go on living) እዚህም ላይ የማስታወስ ብቻ ሳይሆን የመርሳት ጥበብን መማር ሊጠበቅብን ነው ማለት ነው፡፡ የሥነ ልቦና ኮርስ 101 (መተዋወቂያ) የማስታወስ ብቃትን እንዴት ማዳበር እንደሚቻልና እራሱ የማስታወስ ባህርይ ምን እንደሚመስል የሚተነትን ምዕራፍ አለው፡፡ አእምሮ መረጃዎችን የሚደረድረውና ሲያስፈልግ የሚያቀርበው ነገሮችን ዘርፍ፣ ባህሪና አዝማሚያ እያለ በመደልደል ነው አሉ፡፡ መቅደስ አና ቅድስት የተባሉ ስሞችን በባህሪና በድምፅ ዘርፍ ስለሚመሳሰሉ አእምሯችን መመዝገብና ሲያስፈልግ ፋይሉን አውጥቶ ማቅረብ የሚቸገረው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ የነገሮችን አምታቺ ባህሪያት አራግፎ ለአእምሮ ማቅረብ ለማስታወስ አይነተኛ መፍትሄ ነው፡፡
ለምሳሌ ስልክ ቁጥሮችን በጥሬው ለመያዝ ከመሞከር፣ ከሁነቶች ጋር አዛምዶ ማጥናት ከተወለድንበት ቀን ጋር፣ ከአውቶቡስ ቁጥር ጋር ከፔሬዲክ ቴብል ንጥረ ነገሮች ቁጥር ጋር … የስልክ ቁጥሩን ማዳበል፡፡
ማስታወስ መቻል ለመርሳት ከመቻል በላይ ቀላል ነገር ይመስላል፡፡ ከባድ ጉዳት ያላቸውን መጥፎ ገጠመኞች መርሳት እንጂ የሚያስፈልገንን መዘንጋት አይደለም፡፡ ውጥንቅጡ የአእምሮ ጉዳይ ውስጥ ገብተን ጨዋታችንን ውጥንቅጥ ውስጥ ከማስገባታችን በፊት ወደ ታላላቆቹ ዝንጋዜ ነገር እናምራ፡፡ አንድ እንጥቀስ፡፡ አሜሪካዊው ተመራማሪ ቶማስ አልኤዲሰን፤
ኤዲሰን እረጅም ጊዜውን የሚያሳልፈው የምርምር ክፍል ውስጥ ነው፡፡ ግድ ካልሆነት አይወጣም፡፡ ማርጋሬት ካውሲን የፃፈችው የህይወት ታሪክ መፅሐፍ (The man who heighted )ውስጥ አንድ ጊዜ የረሳውን ነገር ትተርካለች፡-
ለሚሰራቸው ስራዎች የመንግስት ግብር ለመክፈል ወደ ከተማው ማዘጋጃ ቤት ሄዶ ነው አሉ፡፡ የግብር መክፈያ ጊዜው ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታልና ወረፋው ረጅም ነበር፡፡ ኤዲሰን ተሰለፈ፡፡ ቢሰለፍም የሚያውጠነጥነው ስለ ሳይንስ ምርምሩ ነውና ከቀልቡ አልነበረም፡፡ ወረፋው ደርሶት ግብር ተቀባዩ መስኮት ጋ ሲደርስ አንድ ጥያቄ ቀረበለት፡-
‹‹ሥም የሚል?››
‹‹የፈጣሪ ያለህ ዘንግቼዋለሁ፡፡ ኧረ ስሜን እረስቼዋለሁ›› አለ፡፡ አሰብ፡፡ አውጠነጠነ፡፡ ስሙ ጠፋው፡፡
‹‹ሥምም ከጠፋዎ ምንም ማድረግ አልችልም፤ ዘወር ይበሉ›› ብሎ ቀጣዩን ግብር ከፋይ ተካ፡፡
ኤዲሰን ግብር ሳይከፍል ዛሬን ካሳለፈ ለነገ ቅጣቱ ብዙ ብር ነውና ጨነቀው፡፡ ከግቢው በመውጣት ሰዎች እያስቆመ፤ ‹‹ታውቁኛላችሁ? ሥሜ ማው?›› እያለ መጠየቅ ጀመረ፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ አንድ የሚያውቀው ሰው አግኝቶ ስሙን ነገረው፡፡ እ-ፎ-ይ!!
ለመሆኑ እናንተ ሥሙ የጠፋው ሰው መንገድ ላይ ቢያጋጥማችሁ ምን ይሰማችኋል? ቂል፣ የአእምሮ ህመምተኛ? አጭበርባሪ?... ወይስ ምን? መጠርጠር ደግ ነው፤ እርሱ የአምፖልን መብራት ጨምሮ ከአንድ ሺህ በላይ ሳይንሳዊ በረከት ጀባ ያለን ቶማስ አልቫ ኤዲሰን ሊሆን ይችላልና፡፡
በፈረንጆች 2015 ላይ ፡ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ፡ የቅዳሜ እትሙ እንዳስነበበው
____
''ለሰባት ዓመታት፣ እንደ ተራ አገልጋይ በመሀከላችን ጠብ ርግፍ ብሎ አገለገለን - ርግት ያለ፣ ንቁ፣ ፈፅሞ ሰው የማያስቀይም፣ ትሁት፣ ባልተፈለገበት ቦታ ጥልቅ የማይል እና የገዳሙን ባልደረቦች የትኛዋንም ትዕዛዝ ለመፈፀም ወደ ኋላ የማይል ነበር፡፡ ሲሄድ በዓየር ላይ የሚንሳፈፍ ነው የሚመስለው፡፡ አንዲትም ቃል ከአፉ አትወጣም፡፡
ቃላት ሳይወጡት በአርምሞ ለመክረም ቃል ሳይገባ አልቀረም ብለን ደምድመናል፡፡ መጀመሪያ አካባቢ የተወሰንነው በሹፈት ልንጎነትለው ሞከረን፡፡ እሱ ግን ሹፈት እና ስላቃችንን ከምድር ባልሆነ ርጋታ አሳለፈው፤ ይህም አርምሞውን እንድናከብርለት አስገደደን፡፡
“በሚያባብል ርግት ያለ መንፈሱ ሐሴት ከሚያደርጉት ሰባቱ ባልደረቦች በተቃራኒ፣ ርጋታውና አርምሞው እረፍት ይነሳኝ፣ ያበሳጨኝ ጀመር፡፡ ልረብሸው ብዙ ጣርኩ፤ ጥረቴ ሁሉ ግን ከንቱ ሆነ፡፡
ሥሜ ብሎ የነገረን ሚርዳድ ነው፡፡ በሌላ ቢጠሩት አይሰማም፡፡ ይህን ብቻ ነው ስለእሱ የምናውቅ፡፡ ቢሆንም ግን … የመንፈሱ ግዝፈት በአንዳች ኃይሉ ለሁላችንም ይሰማል፡፡ ለዚህም ነው … እሱ ወደ ማደሪያው ካልገባ በቀር ምን ወሳኝ ጉዳይ ቢገጥመን አናወራም፡፡''
የመጽሐፉ ርዕስ:- መጽሐፈ ሚርዳድ
ተርጓሚ:- ግሩም ተበጀ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
/ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር፤/
ልጄ ሆይ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡
ልጄ ሆይ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ ሆነ ግን፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም፡
ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ፣ ሲያዝኑ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል፡፡
ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል?
የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡
ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን፤ የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡
ልጄ ሆይ፤ ሰው ምንም ብልህና አዋቂ ቢሆን በራሱ ሥራ ብቻ ራሱን ችሎ እንደማይኖር ዕወቅ:: ነገር ግን ሁሉም በየሥራው ጸንቶ እርስ በርሱ በሥራ ይፈላለጋል:: ስለዚህ ሰውን ሁሉ አክብረህ ኑር እንጂ ሰውን አትናቅ ሥራውንም አትንቀፍ::
ልጄ ሆይ: አካልህና ልብስህ ዘወትር ንጹህ ይሁን:: እጅህን ለሥራ: ዓይንህን ለማየት: ጆሮህን ለመስማት ፈጣኖች አድርግ:: አፍህን ግን በጠንካራ ልጓም ለጉመህ ያዝ:: አረጋገጥህ በዝግታ አነጋገርህ በለዘብታ ይሁን:: ያልነገሩህን አትስማ: ያልስጡህን አትቀበል: ያልጠየቁህን አትመልስ:: ሽቅርቅር አትሁን: ንብረትህ ተጠቅላላ ይሁን: ምግብና መጠጥህ በልክ ሆኖ ያው የጠዳና የጣፈጠ ይሁን::
ልጄ ሆይ ፈቃደ ሥላሴ፤ አሳብ አታብዛ፤ ወደ ፊትም ምን ነገር ይመጣ ይሆን ብለህ አትጨነቅ፤ ምንም አሳብና ጭንቀት ብታበዛ የሚሆን ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወደ ፊትም እሾማለሁ፤ እሸለማለሁ፤ ብለህ በአሳብህ ደስ አይበልህ፡፡ ለሰውም አትናገር፤ ምናልባት ከተናገርህ በኋላ ሳታገኘው የቀረህ እንደ ሆነ ታላቅ ኀፍረት ይሆንብሃልና፡፡ ወደ ፊት የሚያናድድ ሥራ አትሥራ፡፡ በገዛ እጅህ በሠራኸውና ባለፈው ሥራ አትናደድ፡፡ ልጄ ሆይ፤ ጌታ ለመሆን ትፈልግ እንደ ሆነ ጌትነት ማለት ያለ አሳብና ያለ ጭንቀት መኖር ነው፡፡ አሳብህም ሁሉ ከሞትህ በኋላ ወዲያኛው ዓለም ስለሚሆነው ስለ ነፍስህ ነገር ይሁን እንጂ በዚህ ዓለም በሥጋህ ስለሚሆነው ነገር እጅግ አትጨነቅ፡፡
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏🙏
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቍጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል። ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
#ከባዶላይ መዝገን
#የካህሊል አማልክት
እና
#ሰልስቱ ጣኦታት በሚሉ ሥራዎች የምናውቀው ያዕቆብ ብርሃኑ
#የመሻገር ሲቃ ከአውሎ ነፋስ ጋር መደነስ በሚል ታላቅ መጽሐፍ በቅርብ ቀን ልንቀበለው ዝግጅታችንን ጨርሰናል !!!!
ውድ አንባቢያን ዝግጁ !????
ሳምንት ቅዳሜ ጠብቁን !!!!
በቃ ራሳችሁን ሁኑ እንጂ ስለ ዓለም በትንሹም እንኳን ግድ አይስጣችሁ።ከዚያ በኋላ በልባችሁ ውስጥ አስደናቂ የመዝናናት እና ጥልቅ የሆነ የሰላም ስሜት ይሰማችኋል።
የዜን ሰዎች [ዋናው ፊታችሁ] ብለው የሚጠሩት ይህንኑ ነው። ውጥረቶች፣
ልታይ ልታይ ባይነት፣ ግብዝነት የሌለበት እንዲሁም እንዴት አይነት ባህሪይ ሊኖራችሁ እንደሚገባ የሚደነግጉ የስነ-ምግባር ደንብ ተብዬዎች የሌለበት
ዘና ያለ ሁኔታም ነው።
#ኦሾ
" የመኝታ ቤት ሚስጢሮች " (part 1 )
ቅንዝንዝ ነወ ፤ ቅብጥብጥ። ሴት አቅፎ ካላደረ ሰውነቱ አለቅጥ የሚፈታተነው ፤ እንደ ብረት ምጣድ እየጋለ የሚያስቸግረው። እና ሰብለ ውል አለችበት። ሰብለ የጓደኛው ሚስት ናት። ጓደኛው እና ሰብለ ከተጋቡ ሰባት ዓመት ሊሞላቸው ነው። ሰብለን አባብሎ ለመተኛት ብዙ ቀናት አልፈጀበትም። ያሸነፋት አትኩሮ በማየት ብቻ ፤ መልሶ መላልሶ በማየት ብቻ ነው። በዐይኑ አጥር ሰራባት ፤ አጠራት። ውብ ገላዋን የሚያሞካሹ ቃላት ተጠቅሞ ለራሷ የነበራትን ፍቅር በእጥፍ አሳደገው።የማታውቀውን የብልግና አለም አሳያት ....
እና ያቀን ከእሷ ጋር መሆን ነበር ያሰኘው። እሷም የጠበቀችው በደስታ ነበር። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ወሲባዊ ፊልም እያየች ነበር። ስታየው የቆየችውን ሕይወት እንዲኖራት እና እንዲሰሩት ገፋፋት። በምታየው ፊልም ሰውነቷ ፍም ሆኖ ነበር። እናም ሆነ። ግና እጅግ ከመጣደፋቸው የተነሳ ለካስ በሩን አልዘጉትም ኖሯል ! በዚያ ደስታ ውስጥ ሆነው ባለቤቷ በድንገት መጥቶ እፊታቸው ሲደቀን አቤት የተሰማቸው ድንጋጤ!
ወዲያውኑ ገላቸው ቀዘቀዘ። ፈገግታቸው ደበዘዘ።
አባወራው መጀመሪያ በፀጥታ በከባድ ፀጥታ ተውጦ ነው ያያቸው። ጓደኛው እና ሚስቱ ተቃቅፈው ከተኙበት አልጋ ጥቂት እርምጃ ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ- አደገኛ
መሳይ አይኖቹን ከአይናቸው ላይ ሳይነቅል። ከጥቂት ደቂቃ ዝምታ በኋላ ፣ እዚያና እዚህ የተበታተኑ ልብሶቻቸውን ሰብስቦ ፣ አፍንጫቸው ላይ ወረወረው፡፡
ልበሱ !”
ለበሱ።
አባወራው ሽጉጡን ከሳጥኑ ውስጥ አውጥቶ በፍቅር ይዳብሰው ጀመር። የሰብለ ለቅሶ ይሰማዋል። የአባወራው ጓደኛ ሰብለን አይዞሽ ብሎ ሊያባብላት ቀርቶ አይኗን ለማይት እንኳን ብርታት ጎድሎታል። ደግሞም እርግጠኛ ሆኗል። ዛሬ የመሞቻ ቀኑ ነው። ምን
ማድረግ እንዳለበት ግራ ሲገባው ቆየና ፣ በከባድ ፍጥነት ከአልጋው ላይ ወርዶ እግሩ ስር ተደፋ።
ምንድነው ?” አለ ፣ አለ አባወራው። ይቅርታ አድርግልኝ ... ሁለተኛ አይለመደኝም
ሁለተኛ አይለመደኝም !”
ዝም በል ! ሽጉጤን ያወጣሁት እንዲህ አይነቱን ዝብዝብ ለመስማት አይደለም !”
የአባወራው ጓደኛ አንገቱን እንደደፋ ዝም አለ።
ሁለተኛ አይለመደኝም ፤ እኔ ነኝ ጥፋተኛ ! እኔ ነኝ ....”
ይህን አንተ አትነግረኝም ፣ ንገረኝ ብዬም አልጠየኩህም። አውቅሃለሁኮ! አውቅሃለሁ። ቀበቶህን ባገኘህበት የምትፈታ ወንድ መሆንህን አውቃለሁ።
የምትተኛቸውን ሴቶች ቁጥር በማብዛት ፣ ግዳይ እንደጣለ ጀግና ለራስህ የምታጨበጭብ ሰው መሆንህን አውቃለሁ። የማላውቀው ነገር ቢኖር ሚስቴንና የልጆቼን እናት ...”
አባወራው ጥርሱን ማፋጨት ጀመረ። በዚህን ጊዜ ሰብለ ቤቱን በለቅሶ ሞላችው፡፡
ዝም በይ!
ዝም አላለችም፡፡
ሴትዮ ዝም በይ! እኔ በእንባና በለቅሶ ብዛት የሚሸነፍ ልብ የለኝም ” ዞረ ወደ ጓደኛው ፊት ተመለከተ። ቀረበው አንገቱንም በሽጉጡ ቀና አደረገ።
አንተንም ሚስቴንም በዚህ ሽጉጥ መድፋት እችል ነበር ፤ በተቃቀፋችሁበት አልጋ ላይ ሬሳችሁን ማጋደም እችል ነበር ” አለና የዕብደት ሳቁን አመጣው። ፍቅር እስከ
መቃብር! ድንቄም ጎደኝነት ! ድንቄም ሚስትነት። ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል አለ ሰውየው !”
ተወቃሾቹ ዝም ከማለት ውጪ የሚመልሱለት ነገር አልነበረም።
ስማ!”
አቤት !
አልገድልህም ! እሺ ? ሁለታችሁንም አልገድላችሁም። አልገድላችሁም ስል ግን በነፃ አሰናብታችኋለሁ ማለቴ አይደለም። በተለይ አንተ ! አሁን አንድ ነገር እንድታደርግልኝ እፈልጋለሁ። አድርግ የምልህን ነገር ማድረግ የማትፈልግ ከሆ ግን ዛሬ ሬሳህ ከዚህ
ቤት ይወጣል ...”
ምን ላድርግ ?*ተለሳልሶ ሊለምነው ሞከረ።
ይቀጥላል.......
መጽሐፍትን ለማዝዘዝ 👉👉@Mesay21
የቻናላችን ቤተስብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነውና ለወዳጅ ዘመደዎት ሼር ያድርጉት ።
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏🙏
የራስኮልኒኮቩ ራዕይ
ከኤሲያ ተንስቶ አውሮፓን ያዳረሰ ወረርሽኝ መላው ዓለምን ያንኳታኩታል።ከጥቂቱ በቀር ሁሉም ይጠፋሉ ። በአዳዲሶቹ ጀርሞች የሚለከፉ እብድና አመፀኛ ይሆናሉ ። በወረረሹኙ የተጠቁትን ያህል ራሳቸው እውነት በመሻት ብልህና ጠንካራ አድርገው የቆጠሩ ከዚህ ቀደም አልነበሩም ።
ዉሳኔቸው ሳይንሳዊ አካሄዳቸውም ስንአመክኖዊ ተጠየቅን የተከተለ የሞራል ህጋቸው የማይናወፅ አድርገው ይቆጥራሉ ።
መንደሩ ከተሞች በወረርሽኙ ተለክፈው ተናውጡ ፤ህዝቡ በስጋት ተዋጠ። እውነትም በነሡ ዘንድ ብቻ እንዳለች ስለሚሰማቸው ፣መሠሉን በተመለከተ ጊዜ ይከፋና ደረቱን ይደቃል ስሌላው እጁን አጣጥፎ ያለቅሳል ።
ማንን እንደሚከሱ አያውቁም ውሳኔ እንዴት እንደሚያስተላልፉ አያስተውሉም። ሠናዩን ና እኩዩን በመለየት ረገድ አንድ አቋም አይዙም ።
ማንን እንደሚወነጀል ማንስ ነፃነትን እንደሆነ አያውቁም ። በውሃ ቀጠነ አንዱ ሌላውን ይገድላል ። ጦር ሠራዊት ቢደረጃም ይህጦር ግስጋሴውን ሲጀምር አንዱ በሌላው ላይ ይነሳል እርበርስ ይፋለምና ይበተናል ። ወታደደሩ በሳንጃ እየተሞሻለቀ ይጠፋፋል ።
የከተማው ኗሪ ይሰበሰባል ማን እንደ ሰበሰበው አያውቅም ለምን እንደተሰበሰበም የሚያቅ የለም ሁሉም የየራሱን ንደፈ ሃሳብ ስለሚያቀርብ መስማማት ያቅታቸዋል ። ቀድሞ ይታወቁ የነበሩ ሙያዎች ቦታ ያጣሉ
ማረስም ይቀራል ።
በየቦታው ተኮልኩለው ሰዎች ውሳኔዎች ያሳልፋሉ ላለመለያየት ይማማላሉ። ከውሳኔያቸው በተቀራኒ መስራት ይጀምራሉ
እርስበርስ ይወንጃጀሉና እየተፋለሙ ያልቃሉ ። ሰደድ እሣት ረሃብ ይዛመታል ምድሪቱ ለውደመት ትዳረጋለች። ምድሪቱን ለማደስና ለማፅዳት አዲስ የሰው ዘርና ሕይወት ለመጀመር የተመረጡት ብቻ ከዚህ መአት ይድናሉ ።እነዚህን ሰዎች ግን ያየ ሆነ ድምፃቸውን የሰማ አንድስ እንኳ የለም።
#የሕይወት_ቀመሮች
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
#12_RULES_FOR_LIFE በሚል በጆርዳን ፒተርሰን የተጻፈው መጽሐፍ #የሕይወት_ቀመሮች በሚል ተተርጉሞ በገበያ ላይ ዋለ፡፡
እነሆ ከመጽሐፉ የተውጣጡ ሕይወታችንን የምንመራባቸው #12 መርሆች፡-
#መርሕ_1_ትከሻህን_ቀጥ_አድርገህ_ቁም
ትከሻህን ቀጥ አድርገህ ተንቀሳቀስ፡፡ የበላይነት ነው፣ አሸናፊነት ነው፣ ገዢነት ነው፡፡ እንደዚያ ስታደርግ ደግሞ በዛው ልክ ሰዎች በተለየ መንገድ እንዲመለከቱህና እንዲያስተናግዱህ ታደርጋለህ፡፡
#መርሕ_2_የምትወዳቸውን_እንደምትንከባከበው_ሁሉ_እራስህን_ተንከባከብ!
ራስህን የመንከባከብ የሞራል ግዴታ አለብህ፡፡ ለሚወዱህ እና ለሚያከብሩህ ሰዎች የምታደርገውን እንክብካቤ፣ እርዳታ እና ፍቅር ለራስህም መስጠት አለብህ፡፡
#መርሕ_3_ያንተን_ምርጥነት_ሊያወጡ_ከሚችሉ_ሰዎች_ጋር_ወዳጅ_ሁን
አላማ የሌላቸው ሰዎችን በጓደኝነት ከቀረብክ በተቃራኒው የአንተም ሕይወት ቁልቁል ወደ አዘቅት ውስጥ መግባቱን እርግጠኛ መሆን አለብህ፡፡ ጥሩውን ነገር ከሚመኙልህ ሰዎች ጋር ጓደኝነትን ፍጠር!
#መርሕ_4_ከሌላ_ሰው_ጋር_ሳይሆን_ትናንት_ከነበረው_ማንነትህ_ጋር_ራስህን_አነጻጽር
ራስህን ከትናንት ማንነትህ ጋር ብቻ አወዳድር እንጂ ከሌላ ከማንም ጋር አታወዳድር!
#መርሕ_5_ልጆችህ_እንድትጠላቸው_የሚያደርግ_ነገር_እንዲያደርጉ_አትፍቀድላቸው
ልጆችህን እንዳትወዳቸው የሚያደርግ ማንኛውንም ነገር እንዲያደርጉ አትፍቀድ!
#መርሕ_6_አለምን_ለማስተካከል_ከመነሳትህ_በፊት_ቤትህን_አስተካክል
ዓለምን ከመተቸትህ በፊት በመጀመሪያ የራስህን ቤት ስርዓት አስይዝ!
#መርሕ_7_ትርጉም_ያለውን_ነገር_ብቻ_ፈልግ
ምንም ነገር ሰዎች ስላደረጉት ብለህ አታድርግ፤ የህይወትን ትርጉም ካላወቅክ የምትፈልገውን ነገር ለማወቅ እንኳን ይከብድሀል፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ላንተ ትርጉም ያለውን ነገር ፈልግ፡፡
#መርሕ_8_በተቻለህ_አቅም_እውነት_ብቻ_ተናገር
ሁሌም ቢሆን የግልህን እውነት ያዝ፡፡ ስለምንም ነገር በጭራሽ አትዋሽ፡፡ ውሸት ወደ ሲኦል ከሚመሩ ነገሮች መካከል አንደኛው ነው፡፡
#መርሕ_9_ስማ_ሌሎችን_ስታዳምጥ_ስለራስህ_አስተውለኸው_የማትውቀውን_ብዙ_ነገር_ታውቃለህ።
አንተ ሁሉንም ነገር ላታውቅ ትችላለህ፡፡ እንደ ሶቅራጥስ ጥበበኛ ሰው መሆን ካለብህ አለማወቅህን እወቅ፤ እናም ሌላውን ሰው አድምጥ።
#መርሕ_10_ንግግርህ_ግልጽ_ይሁን
ነገሮችን መደበቅ ህይወትህን የሚያደናቅፍ እና የሚያጨልም ከሆነ ለምን ግልጽ አትሆንም? ሁሌም በንግግርህ ውስጥ ግልጽነትና ትክክለኛነት መኖሩን አረጋግጥ!
#መርሕ_11_ህጻናት_እየተጫወቱ_ሳሉ_አትረብሻቸው_ወይም_አታባራቸው
ህጻናት የሚፈልጉት ፈታኝ የሆኑ ነገሮችን ለማለፍ አደገኛ የመጫወቻ ቦታዎችን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እድገት እያገኙ ይሄዳሉ፡፡ ህጻናት እንደወደዱ ይጫወቱ ዘንድ አትከልክላቸው፡፡
#መርሕ_12_ለእንስሳት_የሚራራ_ልብ_ይኑርህ
እንሰሳት በውስጣችን የሆነ ከየት እንደመነጨ ለማወቅ የሚከብድ ደስታ የመፍጠር አቅም አላቸው። ራራላቸው!
በታዋቂው ጆርዳን ፒተርሰን የተጻፈው #12_RULES_FOR_LIFE መጽሐፍ #የሕይወት_ቀመሮች በሚል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በገበያ ላይ ውሏል።
እጃችን ላይ !!!!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
እጃችን ላይ !!!!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
እጃችን ላይ !!!!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
የምንወደው የመጽሐፍት ቤታችን ጥሩ ደምበኛ አንባቢውና መካሪያችን ዲያቆን አቤል ካሳኹን ይህንን ጣፋጭ ታረክ አጋርቷችኋል።
ጠዋቴን ያሳመረችልኝ ጽሑፍ !!!
እነኾ ጋበዝናችኹ !!!!
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።
ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?
እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል?
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
selam@dnabel.com
አዲስ አበባ
ከ50 በላይ የአለማችን ዝነኛ ደራሲያን ስራዎች እጃችን ላይ ይገኛል !!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብና መጽሐፍት መደብር
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78