ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት ከዓመት እስከ ዓመት ለሚhናወነው ማንኛውም ሥርዓተ ጸሎትና አምልኮት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ነው፡ ማሕሌቱቅዳሴውፍትሐቱ ጥምeት ክርስትናው ወተ ሁሉ በዜማው መሪነት የሚክናወኑ ናቸው የዘመናቱ አከፋፈልም ሆነ በየዘመናቱ መከናወን ያለባቸው የጸሎት ክንውኖች የሚመራው ይህ የዜማ መጽሐፍ ነው፡ ከዚህም በተጨማሪ ራሱ ድርሰቱ በዋነኛነት ጸሎትን በብዛት የያዘ ነው hዚህም ሌላ የሥነ ምግባር ትምህርት የምስጋና እና የንስሐ ትምህርትን ያጠቃለለ በመሆኑ ለመንፈሳዊ ሕይወት ጥንካሬ የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ሆኖ ይገኛል፡፡
Читать полностью…ፈረንሳዊው ደራሲ ቪክቶር ሁጎ
led miserables
በአማርኛና ኦሪጅናል እንግሊዝ ኛው ቨርዥን እጃችን ላይ ይገኛል !!!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
ዛሬ ልዩ_ፕሮግራም
ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል።
-----
መግቢያ በነፃ
አቅራቢ : ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ
👉 ርዕስ:- ነገረ መሻገር - ሰውና ተፈጥሮ…
የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት
ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::
ቀን:- መጋቢት 9: 2015 ቅዳሜ እለት ምሽት ከ10:00 እስከ 12:30 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)
ማስታወሻ::
👉👉 ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።
በኤዞፕ መጽሐፍት ብር ብቻ ይሸምቱ
መጽሐፍ ቅዱስ 1980 በቅናሽ ዋጋ አለን !!
1980
የአቡነ ተክለሀይማኖት ዘመን የታተመ !!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
#ልዩ_ፕሮግራም
ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል።
-----
መግቢያ በነፃ
አቅራቢ : ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ
👉 ርዕስ:- ነገረ መሻገር - ሰውና ተፈጥሮ…
የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት
ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::
ቀን:- መጋቢት 9: 2015 ቅዳሜ እለት ምሽት ከ10:00 እስከ 12:30 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)
ማስታወሻ::
👉👉 ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።
መጵሐፉን በናሽ ዋጋ
በኤዜፕ መጽሐፍት 150 ብር ብቻ ይሸምቱ
እጅግ ቀደምት የሆነ የአስትሮሎጅ መጽሐፍ እጃችን ላይ ይገኛል ።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
ይህ መጽሐፍ 'መጽሐፍ አሚን ወሥርዓት' ተብሎ ተሠይሟል።አሚን ማለት ሃይማኖት ሲሆን ሥርዓትም ሃይማኖት የሚገለጽበትን ሕግጋት ያመለክታል ከቀድሞ አበው እና እማት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የትርጓሜ ስልትና የእምነት ሥርዓት፣እንዲሁም ትውፊት ሳይቀር እየጠቆመ ይነግረናል።
መጽሐፈ አሚንወሥርዓትን ያነበበ ሰው ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነቱ በቂ የሆነ መረጃ ያገኛል።
ሰው_የመሆን_ምስጢር
ሰው ማለት እኮ የትዝታውና የትውስታው ድምር ነው፡ ሕይወት የመርሳትና የማስታወስ ሚዛን ናት። መርሳት ያለብንን መርሳት ሲያቅተን ሕይወታችን ይመሳቀላል…..
ደግሞ ማስታወስ ያለብንን የሕይወት ልምዶች ጠቃሚ ሰዎችና ነገሮች ከረሳን ...የእኛነታችን መለያና የስብእናችን ድንበር ይጠፋና ሌላ ሰው እንሆናለን።"
ከሌላ ሰው መፅሃፍ የተወሰደ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
ሥውር ወግ መጽሐፍ በመደብራችን ይገኛል።
ሥለመጽሐፉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣውን አጭር መጻጠቁም እናጋራችኹ !!!
"ሥውር ወግ" የሚል መጽሐፍ ከእጄ ገባ። ደራሲው ያለምዘውድ ይታየው ይባላል። መጽሐፉ የታተመበት ጊዜ ኅዳር 2015ዓ.ም ነው። የመጽሐፉ የገፅ ብዛት 330 ሲሆን የመሸጫ ዋጋውም 330 ብር ይላል።
የመጽሐፉ የመጀመሪያ ዓረፍተ ነገር "ጥበብ ጠርታኝ ሳይሆን ሕይወት በፈተናዋ ገፍታኝ ብዕሬን አነሳሁ" ይላል። ደራሲው በሙያው የምህንድስና ባለሙያ ነው። በልጅነቱም በሥነ መጽሀፍ ዘርፍ ውስጥ አልፋለሁ የሚል ምኞት ኖሮት አያውቅም። እንዲጽፍ ያስገደደው በልጅነት አስተዳደጉና ተማሪ እያለ ያሳለፋቸው የሕይወት ውጣ ውረዶች ናቸው። የመጽሐፉ ይዘትም የሚናገረው የደራሲውን አስተዳደግና ውጣ ውረድ ነው። እንዲያውም ደራሲው እንደ ሥነ ጽሁፍ አልቆጠረዉም እንጂ ሳያውቀው መጽሐፉ ሥነ ጽሁፍ ሆኗል። ምክንያቱም በትረካው ውስጥ አገርኛ ዘይቤዎች፣ ምሳሌአዊና ፈሊጣዊ ንግግሮች ይገኙበታል።
መጽሐፉ የአገር ቤት ወጎችን ይነግረናል። እነዚህን ወጎች የሚያውቃቸው ምናልባትም በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ያደገ ሊሆን ይችላል። ደራሲው በቀጥታ በአደገበት ማህበረሰብ ውስጥ እያየና እየሰማ ያደገውን ነው የጻፈው። የመጽሐፉ መቼት በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን ክፍል ያለውን የጎጃም አካባቢን ወግና ባህሎችን የሚያሳይ ነው።
የአንድን አካባቢ ወግና ባህል ማወቅ ወይም የአንድን ግለሰብ ውጣ ውረድ ማወቅ በዚያ ውስጥ የኛን ህይወት እንድናገኝ ያደርገናል።
ደራሲ ሲባል የግድ ስመ ገናና የሆኑትን ብቻ ከመሰለን በጣም ስህተት ነው። በውጭው ዓለም በአንዲት ነጠላ ጉዳይ ላይ ብቻ ግዙፍ መጽሐፍ ይጻፋል። በሀገራችን ግን ይህ የተለመደ አይደለም። ብዙዎች "እኔ መጻፍ አልችልም፣ እኔ ደራሲ አይደለሁም፣ እኔ የሥነ ጽሁፍ ተማሪ አይደለሁም...." በሚል መጽሐፍ ለመጻፍ አይነሳሱም። ከዚህ ልማድ ልንላቀቅ ይገባል።
ሐኪሙም፣ መሐንዲሱም፣ የሕግ ባለሙያውም፣ ግንበኛውም ደራሲ መሆን ይችላሉ። ምክንያቱም እነዚህ የተሰጡ ሰዎች ሁሉም ሀሳብ አላቸው። መጽሐፍ ደግሞ ሀሳብ እንጂ ሌላ አስማታዊ ነገር አይደለም።
ስለዚህ እንደዚህ ከሥነ ጽሁፍ ውጭ ያሉ ሰዎች ሲጽፉ በርቱ እንላለን።
#አዲስ_ዘመን_ጋዜጣ_የካቲት 2/2015ዓ.ም
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
"እንዳይነጋ እንዳይመሽ ብልኃት ተገኝቶ፣
ጊዜውን መከልከል እንዳይቻል ከቶ፤
እንዲሁም ባ'ለም ላይ አለ ብዙ ነገር፣
በዚያም ቢሉት በዚህ፥ መኾኑ የማይቀር።"
(በክቡር ከበደ ሚካኤል)
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
/channel/azop78
/channel/azop78
ይህችን የጠፋች የኦስካር ትውልድ መጽሐፍ በተደጋጋሚ የጠየቃችኹኝ አንድ ኮፒ ተገኝታለች
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
እጅግ ተፈላጊዋ የሀመር መጽሔት ልዩ እትም እጃችን ላይ ነው።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
ለካስ ሰው መሆን እዳ ነው
ለካስ ሰውነት ባዳ ነው
እህል ውሃ ቢያደነድነው
ሲያጣ ሲነጣ በድን ነው፡፡
የኛስ ይሁን እንዳሻው ለእጥፍ ፈተና ከፈጠርከን
ለፍታችሁ ተፍታችሁ ኑ ካልከን
ለቀብር አፈር ከወጠንከን
ግን ፡- ግን ብላቴኖች ምን በደሉ
የማንን አደራ በልተው የማነን አማና አጎደሉ
እንብርታቸው ያላረረ
አጥንታቸው ያልከረረ
ሰማይ በቀል እንደቋጠረ
እጣቸውን እየመጠረ
መንገዳቸውን በእሾህ እያጠረ
እንደ ደራሽ ውሃ አግተልትሎ
በራብ አኮርማጅ ተልትሎ
ከእናት እቅፍ በግፍ ነጥቆ
ሲሰልፍብን ባጭር ታጥቆ
እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ!
አያ ሙሌ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
የጠፋ መጽሐፍት እጃችን ላይ ናቸው !!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
"በአፍላ ትጀምሩታላችሁ በወረት ትተውታላችሁ
። ያወቃችሁትን ትረሱታላችሁ፣ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፡ ምኞታችሁ ልክ የለውም፣ አእምሮአችሁ ብዙ
ነው። ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል። ተው የተባላችሁትን
ትሰራላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ። ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተ መቅደሱን በመስታወት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ
ማየት ትፈልጋላችሁ። ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ በአንዱም ግን አትጠቀሙበት። ሁሉ አላችሁ ፣ ግን ባዷችሁን ናችሁ። ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም!" ቀጠሉ አባ። ሰውነታቸው እንደ ቅኔ ዘራፊ ይናጣል።
"መድኃኒት ነው ያልከው? መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ
መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ብቻ ትሄዳለህ። ጥበብን "ሀ ግእዝ" ብዬ
ላስተምርህ ብሞክር መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ
በመሰልቸት "ሆ ሳብዕ" ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ። የግል ታሪካችሁ ቢታይ
ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተለከፈከፈ የተማሪ ኩፋዳ ውስጥ ያለ
እህል ይመስላል። ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፣ ሠርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ። ትቀጥላላችሁ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ። ትቸኩላላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ። በጽኑ ታማችኋል!"
ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ። ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፣ እናም ወደ ኋላ ስለ ታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል።
ስለሆነን ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትና
የተሸናፊነት ትርጉም የያዙ ሃውልቶች በአንድ ላይ ታቆማላችሁ። ለግልፅነትና ለነፃነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ እርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ።
ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ። በዚህ አለም ጥድፊያ ታማችኋል።
ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፣ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፣ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ በቁማችሁ የናቃችሁትን የሃገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ። ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ።
ግብዝነታችሁ መጠን የለውም። ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፣ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቂያ ታስባላችሁ። ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖሩም። ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል። ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም።
በዚህም የተነሳ ምስጥር ለመካፈል ቅርስ ለመረከብ የሚያስችል ስብዕና አልገነባችሁም። እኛ የመገናኛውን ድልድይ ስላልሰራንና ከእናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት ወይም ማየት ስለማትፈልጉት አለበለዚያ እንደ ልብወለድ ገፀ ባህርይ የራሳችሁን ያሸበረቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈልጋችሁ ስለምታጡት ነው። እኛ ደግሞ እናንተ ታዩት
ዘንድ አላሸበረቅንም፣ ማሸብረቅም አንፈልግም። በዚህ ምክንያት ለእናንተ
ምስጥር ለመንገር ቅርስ ለማውረስ ከባድ ሆኗል። እኛ አባቶቻችንን እናምናለን። በእነርሱም ደስ ይለናል። የነገሩንን ተቀብለን ቃልኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን።
"ፅላተ ሙሴ አክሱም ፂዮን እንዳለች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን ሳጥን ከፍተን እንይ አላልንም"
"ጌታ የተሰቀለበት ግማደ መስቀሉ ክፋይ ግሸን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንይ አላልንም"
"ቅዱሱ ፅዋ መንዝ ውስጥ አለ ሲሉንም ዋሻ እናስስ አላልንም"
አባቶቻችንን አምነን ሀገራችን የበረከት ምድር መሆኗን ተረድተን የጌታችንን የጸጋ ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራለን። ምንም የለንም ሁሉ ግን የእኛ ነው። ድሆች ብንባልም ባለጸጎችም ነን። የተራቆትን ብንመስልም የጸጋ ልብስ አለን። ሐዘንተኞች። ብንመስልም ደስተኞች ነን። ስለ ሀገራችን መባረክ ፣
ቅድስት ሀገር መሆን፣ ቅዱስ ቅርስ በእጃችን እንዳለ አለም እንዲያረጋግጥልን አንፈልግም። የሌለንን አለን፣ ያልተሰጠንን ተቀበልን ብለን የምንኮፈስ ግብዞችም አይደለንምና። የሌለን ነገር ለመጠበቅና ለመታመን ስንል ሥጋችንን
እየጎሰምን በገዳም ለመኖር የምንወስን ጅሎችም አይደለንምና"።
✍ ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
📖 እመጓ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን
🙏🙏🙏
የጠፋ መጽሐፍ እጃችን ላይነው
ትንሽ ኮፒዎች ብቻ አሉን !!!
300 ብር ብቻ
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
የመጽሐፉ ርዕስ :- ግራጫ ቃጭሎች
ደራሲ:- አዳም ረታ
ምንቸት አብሽ
አንድ ፋሲካ እነ ወሰን የለሽ ቤት ተልኬ መልዕክቴን ካደረስኩ በሁዋላ እንድቀመጥ ተነገረኝና ከዋናው በር ጎን ያጋጠመኝን የጉሬዛ አጎዛ የለበሰ የሳጠራ ወንበር ላይ ኮሰስ ብዬ ቁጭ አልኩ፡፡ (መንኩዋሰሴ ለራሴ ይታወቀኛል) ብዙም ሳይቆይ እንዲህ ሆነ ………………
ነጭ የላስቲክ ሳህን ፊት ለፊቴ ተቀምጧል… ከትሪው ላይ ከሳህኑ ጎን ጠይም ድፍን ዝቡቅቡቅ እንጀራ እንደ ቱባ ተጠቅልሎ ተጋድሞአል፡፡ የወሰን እናት ከጓዳ ባለ አበባ ጎድጓዳ ሳህን ይዘው መጡና ለወሰን አቀበሉዋት፡፡ … ጎድጉዋዳው ሰሀን በአበባ ስዕል ባሸበረቀ እፊያ ተከድኖአል፡፡ በእፊያውና በሳህኑ ከንፈሮች መሀል ብር መሰለ የሚያበራ ጭልፋ ወደ አየር ውስጥ ተዘርግቷል:: ወሰን እፍያውን ስትከፍተው ዐይኖቼን ወደ ጎድጓዳው ሳህን ሆድ ዕቃ ወረወርኩ፡፡ ታላቅ ቀይ ወጥ አየሁ፡፡ ንጉሠነገሥት ኃይለሥላሴ፣ ደጃዝማች ክፍሎም፣ አፈንጉሥ ዘለቀ፣ አባ ጆቢር፣ አባ ጅፋር የሚባሉት የሚበሉት ዐይነት ቀይ ወጥ፡፡ የተጌጠ ጠይም ደም ይመስላል፡፡ በቅባት የሰከረ፡፡ ከዚህም ሰካራም ወጥ ደካማ ጢስ ቀስ እያለ ወደ ላይ ይነሳል (ምን አድርጌው ነው እንዲህ በቀስታ የሚነሳው? ልቤን ሊሰልበው ነበርን?)፡፡
ከዚያ በጭልፋው ተረበሸ፡፡ እና ውፍረቱ፡፡ ወሰን መሰል፣ መሰል…መሰልሰል አደረገችው፣ በቀስታ ከውስጡ የአልማዝ ቀለበት ለማውጣት እንደምትፈልግ፡፡ ከዚያ በጭልፋው እፍኝ ያህል አውጥታ ነጩ ሰሀን መሀል 'ጣል' አደረገችው፡፡ የሚፈስ አይመስልም፡፡ እና ጣል፡፡ መረቁ ከደቀቀው ሥጋ ጋር በማር የተያያዘ ይመስል ነበር፡፡ የነጩ ሰሀንና የወጡ ቀለም ግጭት ከላይ እስከ ታች በጠበጠኝ፡፡ ከዚያ በጠረኑ፣ በዚያ የተስፋ ጣዕሙ ምክንያት ከጉሮሮዬ እስከ እምብርቴ ስር ቀላል ነጎድጓድ ሰማሁ፡፡ ቶሎ እንድትሄድልኝ ፈለግሁ፡፡ የመኩራሪያ ጊዜ አልነበረኝም፡፡ በሆድ ነገር ኮርቼ አላውቅም፡፡ ወሰን ስቃዬ ስላልገባት፣ እኔንም ለማስደሰት፣ ሁለተኛ ጊዜ ከወጡ ጨልፋ ሰሀኑ ላይ አደረገች፡፡ "ብላ እንጂ" አለች፡፡ ረሳሁዋት፡፡ ጠቅላላ ገላዬ ዐይን እጅ አፍ ሆድ ሆነ…ከዚያ ከጠይሙ እንጀራ ስቀድ… በመቅደዴና ወጡ ውስጥ በመንከሬ መሀል ያለው ጊዜ የሶማ በረሀን እንደማቋረጥ ያለ ሥቃይ… በሚንቀጠቀጡ ጣቶቼ ከደቀቀው ሥጋ በእንጀራው አፍኜ ዘገንኩ፡፡ የወጡ ለዘዝ ያለ ሙቀት (በምን ለኩት እቴ፡፡ አንዳንድዋ ሴት የማትሠራው ታብ የለ) ጣቶቼ ጥፍር ውስጥ ሁሉ ይሰማኛል፡፡ ስጎርሰው እጅግ በፍጥነት ነበር…ሮጦ ወይም በሮ እንደሚያመልጠኝ፡፡ አፍ ውስጥ ደሞ ይለሰልሳል፡፡ ትናንሾቹ የስጋ ጥንጎች ጥርሶቼ መሐል ሲፈነዱ መጠው የያዙትን ቅባትና የበሰለ ውሀ ወደ ጉሮሮዬ ሲደፉ…
እመቤቴ ማርያም ሆይ በመላኩ በቅዱስ ገብርኤል ሠላምታ ሠላም እልሻለሁ…ሠከርኩ፡፡
*
‹‹ . . . እኔ ቮሊቮል አልወትም ነበር . . . እንደ ሴት? ማየት አይ ነበር፡፡ ማየት ምንም አይደለም፡፡ ታዲያ እህቴን አንድ ቀን ከአበበ ጋር አየኋት፡፡ አብረው ጎን ለጎን ቢሄዱ ጥሩ፡፡ ግን ያን የማይረባ ቮሊቮል የተጫወተበት እጁን ቂጥዋ ላይ ሲያስቀምጥ አየሁት፡፡ ቂጥዋ ላይ ቢያስቀምጥ ምንም አይደለም እንበል፣ ግን ጣቶቹን በቀስታ ያነቃንቃቸዋል፡፡ እጁን አስቀምጦ ጣቶቹን ቢያነቃንቅ ምንም አይደለም እንበል፣ ግን እህቴ ደስ ብሎአት በዳሌዋ ነካ ነካ ፣ ነካ አድርጋው እየተሸኮረመመች በሳቅ ፍርስ አለች፡፡ ምን ያስቃል? አንድ ሴት እጇን ቂጤ ላይ ብታስቀምጥ ተሸኮርምሜ በሳቅ እፈርሳለሁ እንዴ? ወላ ዐይንዋን ነው የማጠፋው፡፡ አበበ ጀጋው የእህቴን ቂጥ እዚያ ሲነካ ወላ እኔ ራቅ ብዬ እበግናለሁ፡፡ ደ'ሞ ደስ ይላታል፡፡ ደ'ሞ እሱ በሰው ስም ይነግዳል፡፡ አበበ ቢቂላ ፤ የቢቂላ ልጅ ሯጭ እንጂ ሻፋዳ አይደለም፡፡ ይኼኛው አበበ የሚሰራው ትልቅ ነገር ቢኖር የኩዋስ ከመነዳሪ ማስተንፈስ ነበር፡፡ ለአስተማሪዎች ቾክ ማምጣት ነበር፡፡ ለዳይሬክተሩ ገበያ መላክ ነበር፡፡ ግን በእህቴ ቂጥ ምን አገባኝ፡፡
ቂጧ መአት ነበር፡፡ ቢነካትም የሚሰማት አይመስለኝም፡፡ ቢሰማት እንኳን ዓርብ ነክቷት እንደሆነ ከሁለት ቀን ቀኖች በኋላ እሁድ ይሆናል፡፡ ከሻማ ጨርቅ የተሰራው ልብስዋ እንኩዋን መንኳኳቱ አያሳፍራትም፡፡ ምን አገባኝ፡፡ ግን አበበ በሰው ስም ይነግዳል . . .
ወዳጄ ዘመዴ አጋሬ ወገኔ አበበ ቢቂላ ቢሞት ይሔኛው አበበ በሕይወት ቆሞ የሚያደርገው ነገር ቢኖር በስብ ያበጠ የገብስ እንጀራ በላተኛ ሴቶችን ቂጥ በመጋፊያ እጁ ጨበጥ ለቀቅ ማድረግ ነበር፡፡››
~~~~
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
አዝናኝ ታሪኮች ከ መግባትና መውጣት
.... የበጎች ቅንነት በወንጌል ውስጥ ብቻ ነው ።ጉሮኗቸው ውስጥ ቢገቡም 'ተርበናል 'ለማለት አፋቸውን ወደ እንጀራ አባቴ ምኝታ ቤት አነጣጥረው የሮሮ በኡኡታቸውን አቀለጡት ።የእንጀራ አባቴም ለበጎችም የሣር አባታቸው ነበርና ክሳቸውን ሰምቶ ከወገቡ በታች ጋቢ አገልድሞ ከመኝታ ቤቱ ወጥቶ "በጎች እየጮሁ ነው! "አለኝ በቀዘቀዘ ድምፅ ፣ እየሰማኋቸው ነው! "አልሁት ።
"መጮሀቸው ምንን ይገልፃል? "ቀጠለ ፤
"ያው መጮህ እንደሚችሉ ይገልጻል! " ብዬ መለስኩለት ።
የስምንተኛ ክፍል የታሪክ መምህሬ አንድ ቀን ፣ 'የሠራተኛው መደብ ከከበርቴው መደብ በምን ይለያል 'ብለው ጠየቁኝ ፤እኔም 'የሠራተኛው መደብ ከጭቃ የተሰራ ሲሆን አልፎ አልፎ አጎዛ ጣል ያደረግበታል ' አልኋቸው ።
ፈላስፎች ፣መሪዎች እና ደራሲዎች ዐለምን ለመለወጥ ቃል ይገባሉ ።የሚቻል ነው? ይሄ ነገር (ወደ ቴሌ ቪዥኑ እየጠቆመ) ከአስር ደቂቃ በፊት በአልጄዚራ ጣቢያ በኩል የጋዛን ጦርነት ሲያሳየን ነበር ።መክሊት ወደ ኅብረ ትርኢት ፕሮግራም ቀየረችው ።መክሊት ልክ ናት ።የሰው ልጅ የቴሌ ቪዥኑን ቻናል እንጂ ዐለምን መቀየር አይችልም ።
አሁን እንግዲህ ከራዲዮኔ ውስጥ ያለው ጋዜጠኛ ፣ በቅርቡ ኃይል ቆጣቢ አምፖሎች ለኅብረተሰቡ እንደሚታደሉ ተገልፃል ።ይሁን እንጂ የኀይል ቆጣቢ አምፖሎች ለወትሮ ከምንጠቀምባቸው አምፖሎች ጋራ ሲነጻጸሩ የብርሀን መጠናቸው አነስተኛ ነው የሚል አስተያየት አለ ፤ እርስዎ ምን ይላሉ? " ሲል ጠየቀ ።
ባለስልጣኑም " አምፖሎቹ ደብዛዛ ቢሆኑም ገረዳችንን ከሚስታችን ለመለየት የሚያስችል በቂ ብርሀን ይኖራቸዋል ።"
...አቤት አባተ ፣ ወሬ ማደናቀፍ ሲወድ!! ባለፈው የመክሊት ፍቀረኛ አቶ ያን "የምኖርበት ከተማ ከበርሊን መቶ ኪሎ ሜትር ይርቃል ።"ብሎ ሲናገር አባተ ጥልቅ አለና "መቶ ኪሎ ሜትር በኛ ስንት ይሆናል? " ብሎ ጠየቀ ።በጥፊ ብወለውለው ደስ ይለኝ ነበር ።መክሊት ግን ሕጻን እንደምታስጠና ሁሉ ፣ "የእነሱ መቶ ኪሎ ሜትር በኛም ያው መቶ ነው ።"አለችው ።
" የዋጋው ግሽበት ያልነካው ኪሎ ሜትሩን ብቻ ነው ማለት ነው? "አላት ትሪውን ይዞ እየሄደ ።
፨... በጉዞ ላይ የሠራዊቱ ስንቅ ስላለቀ ወታደሮች የጠላት ጦር እንደሚያደረገው አፈር እና ስኳር ቀላቅለው እንዲመገቡ አዘዝሁዋቸው ።ምን ዋጋ አለው! ስኳር እና አፈር እየተቀላቀሉ የተመገቡ ወታደሮች ከወር በኋላ ሸንኮራ አገዳ መፀዳዳት ጀመሩ ።
📖📖መግባት እና መዉጣት
✍✍ በበዕውቀቱ ስዩም
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
#ካህሊል_ጂብራን
ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ! በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ?
በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ? እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ? ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?
በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም።
ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት።
በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት። መሪዎች ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት።
አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት።
ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት።
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
EGo is The ENEMY
በመደብራችን ይገኛል !!!
በአካሉ ቢረዳ የተተረጎመውን የአማርኛ ትርጉሙን በዚያው ያገኛሉ።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
#ካህሊል_ጂብራን
ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ! በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ?
በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ? እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ? ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?
በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም።
ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት።
በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት። መሪዎች ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት።
አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት።
ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት።
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
/channel/azop78
/channel/azop78
ለልጆችዎ እጅግ አስፈላጊ የተረቶች ስብስብ መጽሐፍ በመደብራችን ይገኛል።
የተዎዳጁ የኤዞፕ ተረቶች
ምርጥ ምርጥ ተረቶችን አካቷል
ብዙዎች እጅ ገብቷል
ሁለተኛ እትም ልንገባ ትንሽ ኮፒዎች ብቻ ቀርተውና!!
ያልደራችሑ አንባቢያን ባሉበትም እንልክልዎታለን !!!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
/channel/azop78
/channel/azop78
.......በአንድ ውብ ቀን የሃሳብ ጅረት አዕምሮዬን ሲወጥረው የከተማዋን ጠርዝ ይዤ ፍርስራሹ ብቻ በቀረ አንድ የተዘነጋ ቤት በራፍ አለፍኩ፡፡
በፍርስራሹ ውስጥ አንድ ውሻ በቆሻሻውና በአመዱ ላይ ተኝቶ አየሁ፡፡ ቆዳው ቆሳስሏል፣ የተጉዳ አካሉን ህመም ሰቅዞታል። የምትጠልቀውን ፀሃይ ደጋግመው የሚመለከቱት አይኖቹ ሃፍረት፣ ተስፋ መቁረጥና ስቃይ ይነበብባቸዋል፡፡
የእንስሶችን ቋንቋ ባውቅና ሃዘኔን ልገልፅለት ብችል ብዪ እየተመኘሁ በቀስታ ተጠጋሁት። ወደ እሱ መቅረቤ ግን አስፈራውና በተልፈሰፈሱ እግሮቹ ለመነሳት እንዲሞክር አደረገው፡፡ መልሶ እየወደቀ ቁጣና ልመና በተቀላቀለበት አስተያየት ዞሮ ተመለከተኝ፡፡ አስተያየቱ ከወንድ ንግግር የጠራ፣ ከሴት እንባ የቀደመ ነበር፡፡ እንዲህ ያለኝ
መሰለኝ:
«ሰውዬ ፣ በአንተ ጭካኔ እና ክፋት ሳቢያ ብዙ ስቃይ አይቻለሁ ...
«ጉዳት ከሚያደርስብኝ እግርህ ርቄ እዚህ ከትሜያለሁ፣ አፈርና አመድ ከሰው ልጅ ልብ ይልቅ ቅን ናቸውና፣ እነዚህ ፍርስራሾች ከሰው ነፍስ የላቀ ስቃይ የለባቸውምና፡፡ ሂድልኝ፣ ህግና ፍትህ ከሌለበት ዓለም የመጣህ አንተ ...
«የአዳምን ዘር በእምነት እና በክብር ያገለገልኩ የስቃይ ቋት ፍጥረት ነኝ፡፡ የሰውን ልጅ ጠዋትና ማታ በመጠበቅ ታማኝ ጓደኛው ነበርኩ፡፡ ከአጠገቤ ሲለይ አዝኛለሁ፣ ዳግመኛ ሲመለስ በደስታ ተቀብዬዋለሁ፡፡ ከሰሃኑ በሚረግፈው ፍርፋሪ ጠግቤያለሁ፣ ከጥርሶቹ በሚወድቀው አጥንት ተደስቻለሁ፡፡ ነገር ግን ዕድሜዩ ሲገፋና በታመምኩ ጊዜ ከቤቱ አባርሮ ለምህረት የለሾቹ የመንገድ ልጆች ወረወረኝ
«የአዳም ልጅ ሆይ፣ በእኔ እና ዕድሜ በተጫናቸው ዘመዶችህ መሀል አንድነት ይታየኛል። በአፍላ ዕድሜያቸው ለሃገራቸው ተዋግተው በኋላ ላይ አፈሯን የሚገፉ አሉ፡፡ አሁን ግን የህይወታቸው ክረምት ደርሶ እርባና የለሽ ተብለው ወደ ጎን ተገልለዋል ...
«በእኔ ዕድል እና ልጃገረጅ ሳለች የወጣት ወንዶችን ልብ በምታቀልጥ ሴት መሃልም አንድነት ይታየኛል፡ በኋላ ላይም እናት እንደመሆኗ ህይወቷን በሙሉ ለልጆቿ ትሰዋለች። አሁን ግን እድሜዋ ገፍቶ ተረስታለች፡ ተገፍታለች፡፡
እንዴት ጨካኝ ነህ! የአዳም ልጅ! እንዴት ጨካኝ ነህ!!»
ዲዳው እንስሳ ሊነግረኝ የፈለገውን ልቤ ተረዳችው፡፡
✍ካህሊል ጂብራን
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
/channel/azop78
/channel/azop78
" የዓለም መጥፊያዋ"
ደረሰ ይሉናል ዓለም ማለፊያዋ
ዋ ! የሰው ነገር ዋ !
ጊዜው መቼ ገና
መቼ ደረሰና ,
ሰው ነው በገዛ እጁ የራሱ መፍረሻ
ሌላ ነገር ሲሻ ,
አይበቃኝም ብሎ ሲሰስት ሲሻማ
የሌሎቹን ዓለም ሲናጠቅ ሲቀማ :
ይፈጥራል ጦርነት . . .
ይጠዛጠዛሉ ዓለማት ካለማት
ከኮከብ ጨረቃ ከጨረቃ መሬት
ያቶሚኩ ርችት . . . ይላካል ይመጣል
የክዋክብት መስመር ጉዞአቸው ይናጋል ::
ተጋጭቶ እየሄደ አንዱ ክበብ ካንዱ
ዓለሞች ሲወርዱ . . .
ዓለሞች ሲፈርሱ . . . ዓለሞች ሲናዱ ,
እልፊት የሚመጣው :
ወዮ !
ያን ጊዜ ነው ::
( ገብረ ክርስቶስ ደስታ )
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።