azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሐዘንሽ አመመኝ ደበበ ሰይፉ

ውል አልነበረንም የፍቅር ቀጠሮ
ቃልም አላኖርንም በወግ ተቀምሮ፤
እኔ አንቺን እንዳላይ
አንቺ እኔን እንዳታይ አምባችን ተቃጽሮ
ዕጣችን ተካሮ፤
ቀለምሽ ከዐይኔ አሻራሽ ከጣቴ ባይጠፋ ተማትሮ
(እትብት እምብርት ሁኖ እንዲኖር ደድሮ)
ይኸው አካሄደን በድንገት ዘንድሮ።
የገጽሽ ብርሃን ቢጠይም ፀዳሉ
ድምፅሽ ቢቀጥንብኝ ቢሠልብኝ ቃሉ
ወዘናሽ ቢማስን ዛሬ ያለውሉ
በእጆችሽ ጨበጠኝ ሐዘንሽ ሥዕሉ
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጀንበር ነሽ አበባ ሕይወት ተስፋ ዘቦ
ፋሲካ ዕንቁጣጣሽ ማኅሌተ ገንቦ
በዬ ያወደስኩበት ታዘበኝ ዘመኔ የትላንታት ቀኔ
ዛሬ ሊጮህብኝ ቅኔ እንዳይደል እውኔ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
የገደል ማሚቶን ታዘብኳት ተኝታ
በጩኽትሽ ማየል አኩርፋና ታክታ
ላንቃዋ ይታየኛል ደም ለብሶ ደም ጐርሶ
ቃልሽ ያለፈበት በጭንቅ ተለውሶ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጽጌሬዳይቱ ንቦችሽ አለቁ ሰዎችሽ ደቀቁ
ጨፌ ላይ ተኝተው ባድማ ላይ ነቁ፤
ዐዋይን ሰማኋት ስታለቅስ በይፋ
ከጐጆሽ ስትወጣ ትቢያዋን አራግፋ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
አላውቅልሽ ብዬ አታውቂልኝ ብዬ
እምነትሽን ጥዬ ፍቅርሽን ገድዬ
አኩርፌሽ ስቀመጥ ያው እንደ ባላንጣ
ይኸው ነጭ ማተብሽ ሊያስታርቀን መጣ፤
ሐዘን ነው ውበትሽ ውበት ነው ፍቅርሽ
ብርሃን – ጥለት አልቦ ከል ነጠላሽ
ዐይኔን የገለጠው ጥቁር ጨለማሽ፤…
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።

ግንቦት 1966ዓ.ም.

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

“ እመዬ እሁድን ትወጃታለሽ ? ” አለ ' አንድ እሁድ እንደ ልማዳቸው ምሳቸውን በልተው በሚያወሩበት ጊዜ።

“ በጣም እወዳታለሁ ” አለች እናቱ።

“ ለምን ? ”

“ አንተን የማይባት ቀን ስለ ሆነች።”

“ መልክዋ እንዴት ያለ ነው ?”እንዴት ያለች ሆና ትታይሻለች ?”

“ እንዴ ! እሁድ ሰው ናት ?” ቀን አደለችም ?” አለች ደመቀች ' ከልብዋ እዬሳቀች።”

“ ቀን መሆንዋንማ አውቃለሁ ” አለ ተከስተም እዬሳቀ  “ ብቻ እኔ ሳስባት — በቀይና በጠይም መሀከል ያለ መልከ ምን ይባ ላል ?”

” ዳማ ! '”

“ አዎ ዳማ ወይዘሮ መስላ ትታየኛለች። ጥርስዋ ከንቅሳቱ ጋር በጣም የሚያምር ፣ አይንዋን የተኩዋለች ፣ ጠጉርዋ በጣም የሚያምር ሆኖ በትንሹ ሽበት ያሰረገው ነው። ብቻ ፊትዋ የልጅ ፊት ስለሆነ ሽበቱ አውቃ ለጌጥ ያደረገችው ይመስላል። ሁልጊዜ ክንፈርዋን ሳትከድን ፈገግ ብላ ፊትዋን ደስ ብሎት በጥልፍ ቀሚስ ዋና በጥበብ ኩታዋ ላይ ካባ ደርባ ፣ ረጋ ብላ ካንቺ ፊት ፊት በዚህ በምዕራብ በር ስትገባ አያታለሁ። ታዲያ እስዋን ሳይ ሁልጊዜም አንቺን በሁዋላዋ አይሻለሁ። ስለዚህ — አንቺን ይዛልኝ ስለምትመጣ ነው መሰለኝ በጣም እወዳታለሁ : ትናፍቀኛለች።”

“ በቃ ! እንግዲህ ያችን እሁድን አልወዳትም ! ” አለች ደመቀች ግንባርዋን በውሸት ኮስተር አድርጋ።

“ ለምን ? ”

“ አንተ ስለምትወዳት ! እንዲህ አስጊጠህ አሳምረህ የምታያት ከኔ የበለጠ ብትወዳት አደል ?”

“ ይህን የተናገረ አፍሽ መቀጣት አለበት ! ” አለና ተከስተ የናቱን አፍ ለመምታት እስዋ ለመከልከል ትንፋሻቸው እስኪቆረጥ እዬሳቁ ሲታገሉ ቆይተው በሁዋላ ሲደክማቸው ' ትግሉን ትተው እንደገና ወሬያቸውን ቀጠሉ”

“ “ እስዋ እንዲህ አጊጣ አምራ አያታለሁ ” አልሁ እንጂ የማስጌጣትና የማሳምራት እኔ እደለሁም። የምወዳትም የምወዳትን እመዬን ስለምታመጣልኝ ነው ” ሲል ተከስተ ድንገት ሳያስበው አንገቱን እቅፍ ' ጭንቅ አድርጋ ይዛ ሳመችው እናቱ።”

“ ታዲያ እሁድ እንዲህ ሆና ትታዬኛለች ” ብዬ ለዚያ' ይወደኛል ላልሁሽ አስተማሪ ለጋሽ ሀይሉ ስነግረው ያለኝን ልንገርሽ ? ” አለ ተከስተ ቀጥሎ።

“ ምን አለህ ? ”

“ እሁድ ሁልጊዜ አጊጣ አምራ ፣ ፈገግ ብላ ፣ ፊትዋ በደስታ ሰርቶ  ረጋ ፣ ኮራ ብላ የወይዘሮ አካሄድ እዬሄደች እናትህን ይዛ ስትመጣ የምታያት እሁድ የረፍት ፣ የደስታ፣ የጭዋታ የጌጥ ቀን ስለ ሆነችና የምትወዳትን እናትህን የምታይባት ቀን ስለሆነች ህቡእ “ አእምሮህ ”  ላንተ ሳይሰማህ ይህን ሁሉ አሳብ ባንድ ላይ አስማምቶ ይህ ሁሉ አሳብ ባንድ ላይ የሚታይባት ወይዘሮ አሳምሮ ስሎ ለ “ ክሱት አእምሮህ ስላቀበለው ፡ ‛ ክሱት ' አእምሮህ ያችን ከ “ ህቡእ ˚ አእምሮህ የተቀበላትን ከረፍት፣ ከደስታ፣ ከጭዋታ ከጌጥ ቀለም የተሳለች እሁድ የዚያችን ጥሩ ወይዘሮ ስእል እያሳዬህ ነው ” አለኝ።”

“ ጥሩ ነው ፤ እንግዲህ ስእል መሳል ተማርና እሁድን ብቻ ሳይሆን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ያሉትን ቀኖች ሁሉ ወይዛዝርና መኩዋንንት እያደረግህ በዚያ — ምንድነው ? * ህቡእ — ክሱት ” አእምሮ ባልኸው ቀለም እንደ እሁድ እያሳመርህ እዬሳልህ ታሳዬኛለህ !” ስትል ደመቀች ' በልጅዋ ለመቀለድ ተከስተ በፈንታው ፡ እናቱ “ ህቡእና ክሱት ” አእምሮ ፡ የስእል ቀለም መስሎዋት ፡ በተናገረችው በጣም ሲስቅ ቆዬና '

“ ህቡእና ክሱት አእምሮ ” ቀለም አደለምኮ ፣ እምዬ ” አለ።

“ አንተኮ ነህ — ከ' ህቡእ ' – ከ “ ክሱት አእምሮ የተሳለች ያልህ ! አላልህም ?”

“ እንደሱ አላልሁም።”

“ እሺ መቸም “ ህቡእና ክሱት አእምሮ ' ያልኽውን ከስእል ጋር አያይዘህ ነው የተናገርኸው ፤ ታዲያ እንግዲያ - የስእል መሳያ ወረቀት ነው ?” ተከስተ አሁንም እዬሳቀ የናቱን አንገት አቅፎ ራስዋን ( ግን ባርዋንና ፊትዋን ሁሉ ሲስም ቆዬና  “ ኣእምሮ አታውቂም እመዬ ?” አለ።

“ አእምሮማ አውቃለሁ ፤ አእምሮ የምናስብበት ነው። የማላውቀው — እሁድን ባለካባ ወይዘሮ የሚያደርገውን ' ያን ያንተን " “ ህቡእ - ክሱት ” የሚባለውን አዲስ አይነት አእምሮ ነው ” አለች ደመቀችም እዬሳቀች።

📖📖 የልምዣት
  ✍✍ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#በምናልባት_ኑሮ

አይቦዝን አንቀልባው
አይሞላም ጉድጓዱ
ሺሆች ሞተው ሲያድሩ
ሺሆች ተወለዱ
ይመሻል ይነጋል
ያው እንደልማዱ

መሬት ባሕር ሆኖ ፥ድሀን ሰለቀጠው
ትልልቁ ቪላ፥ ትንሹን ቤት ዋጠው
በመስታወት ጫካ፥ በጡብ በብረት ደን
ዐየሁ ባደባባይ ፥ሰው በሰው ሲታደን::


LA VIE PEUT-ÊTRE

Le berceau ne chôme pas
le trou n'en finit pas de se remplir
morts par milliers la nuit venue
nés par milliers
soir et matin
comme d'habitude
Telle océan la terre engloutit le pauvre
le manoir gobe la bicoque
jungle de verre - forêt de brique et d'airain
vu sur la Place, l'homme chasse à l'homme

  ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
        🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የእንዳለ ጌታ ከበደ


አስራ አራተኛ የኾነው !!!


እስረኞቹ የተሰኘው መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ደግ ሰው በፈረስ ከሩቅ ሃገር ወደ መንደሩ ሲመለስ በጫካ ውስጥ አንድ ሌባ ሰው የታመመ በመምሰል

" ጌታው አትለፈኝ እባክህ?! ከባድ የሆነ ሆድ ቁርጠት ይዞኛል። በምትወደው ከዚህ ጥለሀኝ ከሄድ እየመሸ ስለሆነ አውሬ ይበላኛል" ብሎ ይማጸነዋል::

ደጉም ሰው ያዝንለትና "አይዞክ ወንድሜ" ብሎ ከፈረሱ ላይ ተሸክሞ ያወጣዋል።

የፈረሱንም ሉጋም ይዞ በእግሩ ፊት ፊት ይመራዋል።

ሌባውም "ጌታው በግርህ ለራስክ ከመሄድ ይልቅ የፈረሱን ልጓም ይዘክ ስትመራኝ ጀንበር እያዘቀዘቀች ስለሆነ እንቅፋት ይመታካል:: ተሰናክለክም ብትወድቅ ጉዳት ይሆናልና እርካቡን አስቆንጥጠሀኝ ሉጋሙን አሲዘኝ ቀስ እያልኩ አዘግማለው" ይለዋል::

የፈረሱም ባለቤት በየዋህነት ፈረሱን ለሌባው ይለቅለታል።

ይን ጊዜ ሌባው ፈረሱን ኮርኩሮ ሉጋሙን አላልቶ ሽምጥ ጋለበ።

በስላቅም እንግዲህ ደህና አምሽ ጌታው ብሎ ተፈተለከ

ሲጋልብም ሳለ ያ ደግ ሰው ተጣርቶ አንተ ሰው ፈረሱንስ ውሰደው ግን እባክህ አንድ ነገር ልንገርህ ስማኝ አለው

ሌባውም እየጋለበ "ምንድነው እሱ?!"

"ይህን ያረከውን ነገር ማንም ሰው እንዳይሰማው ሰው የሰማ እንደሆነ በእውነት ለታመመና ለወደቀ የደግ ሃሳብ ርህራሄ እንዳያደርግለት ይፈራልና ነው!" ብሎ ቢነግረው

ሌባው በዚህ ነገር ልቡ ተነክቶ ተጸጽቶ ፈረሱን መለሰለት ይባላል::

" ፍቅር ሁሌ እኔ ምን እሆናለው። ሳይሆን ወንድሜ ምን ይሆናል? ነው የሚለው! እንዲህ አይነት ሰው በዚህ ዘመን ይገኝ ይሆን? "

✍✍ከ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
📖📖ታሪክና ምሳሌ 3ኛ መጽሐፍ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በረከተ መርገም


አንድ ኮፒ ብቻ

ለቀደመ እንሰጣለን !!!!!!


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የግራኝ አህመድ ወረራ የተሰኘው የተክለፃድቅ መኩሪያ መጽሐፍ እጃችን ላይ ነው


!!!!!!!!!!!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቆየት ያሉ የኦሾ መጽሐፍት አሉን !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሁሉም ሰው ብሩህ ጭንቅላት አለው ። ነገር ግን አሳን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሳ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ ።

ዓይነ ህሊና ከእውቀት የላቀ አስፈላጊ ነው ።

መቀራረብ በፍቅር ለመውደቅ ዋስትና አይሆንም ።

ጎበዝ ሰው ችግሮችን ይፈታል ። ብልህ ሰው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል ።

ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት ። ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ ።

ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ የስኬት ፍላጎትህ እወድቃለሁ ብለህ ከምትፈራው ፍሪሃትህ በእጅጉ የበለጠ መሆን አለበት ።

አንድን ነገር በቀላል ቋንቋ መግለፀ ካልቻልክ ነገሩን አልተረዳኸውም ማለት ነው

ደስተኛ ህይወት ለመኖር ከፈለክ አንተነትህን ከሰዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር እራስህን እሰር ።

✍ አልበርት አንስታይን

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ለእብደት_አንድ_ቀን

      ሕይወት እጅ እጅ ሲል ፣ እርጋጭ እርጋጭ፣

      ትዝታ ከተስፋ ፣ እውን ከህልም ሲጋጭ ፣

      ኑሮ ጉቶ ሲሆን ፣ ማቆጥቆጥ ሲሳነው ፣

      የማሰብን ብርታት ደመ ነፍስ ሲሰልበው ፣

      ህይወት ፍቺ ሲያጥራት ስትሆን ሰመመን ፣

      የሚገኝ  በሆነ  ለእብደት  አንድ  ቀን


           ✍️  በድሉ ዋቅጅራ

   ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የጠፋ መጽሐፍት እጃችን ላይ ናቸው !!!


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የግዕዝ ማስተማሪያ መጽሐፍትን በብዛት አስገብተናል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በኤዞፕ መጽሐፍት የታተሙ በረከቶች !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"በአፍላ ትጀምሩታላችሁ በወረት ትተውታላችሁ
። ያወቃችሁትን ትረሱታላችሁ፣ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፡ ምኞታችሁ ልክ የለውም፣ አእምሮአችሁ ብዙ
ነው። ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል። ተው የተባላችሁትን
ትሰራላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ። ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተ መቅደሱን በመስታወት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ
ማየት ትፈልጋላችሁ። ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ በአንዱም ግን አትጠቀሙበት። ሁሉ አላችሁ ፣ ግን ባዷችሁን ናችሁ። ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም!" ቀጠሉ አባ። ሰውነታቸው እንደ ቅኔ ዘራፊ ይናጣል።

"መድኃኒት ነው ያልከው? መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ
መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ብቻ ትሄዳለህ። ጥበብን "ሀ ግእዝ" ብዬ
ላስተምርህ ብሞክር መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ
በመሰልቸት "ሆ ሳብዕ" ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ። የግል ታሪካችሁ ቢታይ
ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተለከፈከፈ የተማሪ ኩፋዳ ውስጥ ያለ
እህል ይመስላል። ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፣ ሠርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ። ትቀጥላላችሁ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ። ትቸኩላላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ። በጽኑ ታማችኋል!"

ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ። ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፣ እናም ወደ ኋላ ስለ ታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል።
ስለሆነን ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትና
የተሸናፊነት ትርጉም የያዙ ሃውልቶች በአንድ ላይ ታቆማላችሁ። ለግልፅነትና ለነፃነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ እርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ።

ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ። በዚህ አለም ጥድፊያ ታማችኋል።

ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፣ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፣ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ በቁማችሁ የናቃችሁትን የሃገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ። ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ።
ግብዝነታችሁ መጠን የለውም። ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፣ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቂያ ታስባላችሁ። ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖሩም። ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል። ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም።


በዚህም የተነሳ ምስጥር ለመካፈል ቅርስ ለመረከብ የሚያስችል ስብዕና አልገነባችሁም። እኛ የመገናኛውን ድልድይ ስላልሰራንና ከእናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት ወይም ማየት ስለማትፈልጉት አለበለዚያ እንደ ልብወለድ ገፀ ባህርይ የራሳችሁን ያሸበረቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈልጋችሁ ስለምታጡት ነው። እኛ ደግሞ እናንተ ታዩት
ዘንድ አላሸበረቅንም፣ ማሸብረቅም አንፈልግም። በዚህ ምክንያት ለእናንተ
ምስጥር ለመንገር ቅርስ ለማውረስ ከባድ ሆኗል። እኛ አባቶቻችንን እናምናለን። በእነርሱም ደስ ይለናል። የነገሩንን ተቀብለን ቃልኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን።

"ፅላተ ሙሴ አክሱም ፂዮን እንዳለች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን ሳጥን ከፍተን እንይ አላልንም"

"ጌታ የተሰቀለበት ግማደ መስቀሉ ክፋይ ግሸን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንይ አላልንም"

"ቅዱሱ ፅዋ መንዝ ውስጥ አለ ሲሉንም ዋሻ እናስስ አላልንም"

አባቶቻችንን አምነን ሀገራችን የበረከት ምድር መሆኗን ተረድተን የጌታችንን የጸጋ ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራለን። ምንም የለንም ሁሉ ግን የእኛ ነው። ድሆች ብንባልም ባለጸጎችም ነን። የተራቆትን ብንመስልም የጸጋ ልብስ አለን። ሐዘንተኞች። ብንመስልም ደስተኞች ነን። ስለ ሀገራችን መባረክ ፣
ቅድስት ሀገር መሆን፣ ቅዱስ ቅርስ በእጃችን እንዳለ አለም እንዲያረጋግጥልን አንፈልግም። የሌለንን አለን፣ ያልተሰጠንን ተቀበልን ብለን የምንኮፈስ ግብዞችም አይደለንምና። የሌለን ነገር ለመጠበቅና ለመታመን ስንል ሥጋችንን
እየጎሰምን በገዳም ለመኖር የምንወስን ጅሎችም አይደለንምና"።

✍ ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
📖 እመጓ

  ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን
       🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የጠፋ መጽሐፍ እጃችን ላይነው

ትንሽ ኮፒዎች ብቻ አሉን !!!

300 ብር ብቻ


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አታልቅስ አትበሉኝ
(ደበበ ሰይፉ)

አትሳቅስ በሉኝ
ግዴለም ከልክሉኝ፤
የፊቴን ፀዳል
አጠልሹት በከሰል፤
የግንባሬን ቆዳ
ስፉት በመደዳ፤
ጨጓራ አስመስሉት።
ግዴለም።
አትጫወት በሉኝ
ዘፈኔን ንጠቁኝ
ግዴለም።
ብቻ ፤ አታልቅስ አትበሉኝ
አትጩህ አትበሉኝ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#በቅርብ_ቀን
በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት በእንደርታ ወረዳ ለሰሰማት ትኩል ምዕራፈ ቅዱሳን ቤተ ደናግል ገዳም ሙሉ ገቢው የሚውለው "ከሞት ባሻገር" መጽሐፍ ሁለተኛ እትም

እና

ለኳታር ዶሃ ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ሕንፃ ማሠሪያ ሙሉ ገቢው የሚውለው አበረታች መድኃኒት መጽሐፎች በዘመነ ትንሣኤ በአዲስ አበባና በዶሃ ታትመው በገበያ ላይ ይውላሉ::

ሁለቱም መጻሕፍት ለሁለተኛ ጊዜ የታተሙ ሲሆን ከሞት ባሻገር በገጽ ብዛት ጭማሪ የተደረገበት ክልስ እትም (revised edition) ነው::

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ካህሊል_ጂብራን


ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ! በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ?

በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ? እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ? ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?

በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም።

ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት።

በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት። መሪዎች ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት።

አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት።

ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት።

   ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የአባ ማበፍ የኑሮ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ወረደ።ያላቸውን ሁሉ ሸጠው መፅሀፎቻቸው ብቻ ቀሯቸው፣በቤታቸው ውስጥ እሳት አይነድም፣ሻማ ለመቆጠብ ሲሉ ፅሀይ ገና ከመግባቷ ወደ መኝታቸው ሔደው ይተኛሉ።በስተርጂና መደህየት ክፋ ፈተና ነው።

«ራት የምገዛበት የለኝም» አለች ባለቤታቸው

«በዱቤ ለመግዛት ሞክሪ» አሏት

«ዱቤማ እንቢ ብለውኛል!»

ሙሴ ማበፍ የመፅሀፍ መደርደሪያቸውን ከፍተው መፅሀፍቶቻቸውን በአይናቸው ቃኟቸው።መፅሀፎቻቸውን እንደወለዷቸው ልጆቻቸው ስለሚወዷቸው አውጥተው ለመሸጥ ያሳዝኗቸዋል።አንዱን መፅሀፍ ከመደርደሪያው አንስተው ይዘው ወጡ።ከ ሁለት ሰአት በኋላ ሲመለሱ መፅሀፉ እጃቸው ላይ አልነበረም።የሸጡበትን 35 ሱ ጠረጴዛው ላይ አኖሩትና «በይ ለእራት አንዳች የሚቀመስ ነገር ግዢበት» አሏት።ከዚያን ቀን ጀምሮ በየ ቀኑ መፅሀፎቻቸውን አንድ ባንድ ይሸጧቸው ጀመር።

ተገደው እንደሚሸጧቸው የተገነዘቡት ነጋዴዎች በርካሽ ዋጋ ይገዟቸዋል፣አንዳንድ ጊዜ መፅሀፉን ራሳቸው የገዙበት ሱቅ ሔደው ዋጋውን ሰብረው ይሸጡ ነበር አባ ማበፍ።መፅሀፎቻቸውን እንዲሁ እየሸጡ ሲቃረቡ «እኔም እንግዲህ ብዙ አልቀረኝም ...እድሜየም ሰማንያ አመት ደርሷል» አሉ አንድ ቀን ።

አባ ማበፍ የአትክልት አብቃዮች ማህበር አባል ነበሩ።እየደከሙ አንዳንዴም በምግብ እጦት እየወደቁ መሄዳቸውን ሲረዳ።የእርሻ ሚኒስትሩን እንደሚያናግሩላቸው ተስፋ ሰጧቸው።በተስፋው መሰረት አነጋገሩላቸውና ሚኒስትሩ አባ ማበፍን ለእራት ግብዣ ጠራቸው።በጣም ደስ ብሏቸው በግብዣው እለት ወደ ሚኒስትሩ ቤት አመሩ።ከዚያ ሲደርሱ ግን አጋፋሪዎቹ መናኛ አለባበሳቸውን አይተው አናስገባም አሏቸው።ከአሁን አሁን የሚቀበለኝና የሚያነጋግረኝ ሰው አገኛለሁ በሚል ተስፋ እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ ቆዩ።ነገር ግን ማንም ከምንም ሳይቆጥራቸው ቀረና ዝናብ እየደበደባቸው በውድቅት ጨለማ ወደ ቤታቸው ተመለሱ።

በርካታ ሳምንታት ካለፉ በኋላ ይባስ ብሎ ባለቤታቸው ወ/ሮ ፕሉታርክ በድንገት ታመመች።መድሀኒት መግዣ በቤቱ የለም ሀኪም ቤት ሄዳ ውድ መድሀኒት ታዞላት ነበር።በዚያን ጊዜ በቤታቸው  ከ አንድ መፅሀፍ በስተቀር  አልቀራቸውም ነበር አባ ማበፍ።ይህ መፅሀፍ በግሪከኛ የተፃፈና ከመፅሀፎቻቸው ሁሉ አብልጠው የሚወዱት ደግመው ደጋግመው የሚያነቡት ነበር።ይህን መፅሀፍ ይዘውት ወጡና በመቶ ፍራንክ ሸጠውት ተመለሱ።ገንዘቡን ለባለቤታቸው ሰጧትና አንዳች ቃል ሳይተነፍሱ ወደ ክፍላቸው አመሩ።

በማግስቱ ከሰአት በኋላ ፓሪስ ውስጥ ጫጫታና ሁካታ በዛ።እቤታቸው ደጂ ተቀምጠው የነበሩት ማበፍ አንድ አትክልተኛ በዚያ ሲያልፍ አዩና «ጫጫታው ምንድን ነው?» ሲሉ ጠየቁት።

«ረብሻ ተነስቷል!» አላቸው አትክልተኛው

«የምን ረብሻ?»

«ሰው ርስበርስ እየተጋጨ ነው»

«መነሻው ምንድን ነው?»

«እኔ ምን አውቃለሁ»

«ረብሻ ያለው ወዴት አቅጣጫ ነው?»

«የመሳሪያ ግምጃ ቤት አካባቢ»

አባ ማበፍ ክፍላቸው ገብተው ባርኔጣቸውን ደፍተው፣ረብሻ ተነሳበት ወደተባለው ቦታ ያዘግሙ ጀመር።

የሰኔ 5 ቱ ረብሻ ህዝባዊ አመፅንጂ ተራ ረብሻ አልነበረም በዚህም ረብሻ አባ ማበፍን ጨምሮ በርካቶች ክቡር ህይወታቸውን አጡ

ከመከረኞች መፅሀፍ የተወሰደ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የእንዳለ ጌታ ከበደ መፅሐፎችን በቅናሽ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እነዚህ እጅጉን ከገበያ የጠፉ መጽሐፍት እጃችን ላይ ይገኛሉ !!!!




ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በድሮ ጊዜ ውስጥ ታስራችሁ እንዳትቀሩ!

"እኔ ፀረ ሰላም አይደለሁም ፣ብጥብጥን አልደግፍም። አለም የበለጠ ውብ ፣የበለጠ ተስማሚ እንድትሆን እፈልጋለሁ። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ግን ግርግርን አሞካሻለሁ የሚለን ኦሾ። ስለ ምክንያቱ ምክንያት ሲሰጠን የበሰበሰውን ስርአት ለመንቀል ነው ይለናል።
አመፀኝነትን አሞካሻለሁ ለምን ካላችሁ አዲስ ነገር ይፈጠር ዘንድ የተገባ ነውና ፣ በአንድ ቦታ ላይ ረግቶ የበሰበሰ ስርአት ተጠራርጎ ይሄድ ዘንድ ነው። ተቀባይነት የሌላቸው ልማዶች ፣ ስምምነቶች ፣ ያረጁ ያፈጁ ባህሎችን እነሱንም እፃረራለሁ። ለምን ? ብትሉ አዳዲስ አለማትን መፍጠር እንድትችሉ ፣ በድሮ ጊዜ ውስጥ ታስራችሁ እንዳትቀሩ ፣ለወደፊቱ የተሻለ ነገር እንዲኖራችሁ ነፃ ላደርጋችሁ ስል ብቻ ነው። እኔ አጥፊ አይደለሁም።

ኦሾ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቍጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል። ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

የቴሌግራም ቻናላችን 👉👉 @azop78
  የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉 @azopbook
   
     የቻናላችን ቤተስብ ስለሆኑ  ምስጋናችን ላቅ ያለ ነውና ለወዳጅ ዘመደዎት ሼር ያድርጉት ።

  ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
           🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት ከዓመት እስከ ዓመት ለሚhናወነው ማንኛውም ሥርዓተ ጸሎትና አምልኮት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ነው፡ ማሕሌቱቅዳሴውፍትሐቱ ጥምeት ክርስትናው ወተ ሁሉ በዜማው መሪነት የሚክናወኑ ናቸው የዘመናቱ አከፋፈልም ሆነ በየዘመናቱ መከናወን ያለባቸው የጸሎት ክንውኖች የሚመራው ይህ የዜማ መጽሐፍ ነው፡ ከዚህም በተጨማሪ ራሱ ድርሰቱ በዋነኛነት ጸሎትን በብዛት የያዘ ነው hዚህም ሌላ የሥነ ምግባር ትምህርት የምስጋና እና የንስሐ ትምህርትን ያጠቃለለ በመሆኑ ለመንፈሳዊ ሕይወት ጥንካሬ የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ሆኖ ይገኛል፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ፈረንሳዊው ደራሲ ቪክቶር ሁጎ
led miserables

በአማርኛና ኦሪጅናል እንግሊዝ ኛው ቨርዥን እጃችን ላይ ይገኛል !!!!!





ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዳም ስሚዝ
the wealth of nations

book ፩-፫

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ ልዩ_ፕሮግራም
ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል። 
-----
መግቢያ በነፃ

አቅራቢ :  ደራሲ  ያዕቆብ  ብርሃኑ

👉 ርዕስ:-  ነገረ መሻገር - ሰውና ተፈጥሮ…

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ:  ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- መጋቢት  9: 2015 ቅዳሜ እለት ምሽት ከ10:00 እስከ 12:30 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

ማስታወሻ::

👉👉 ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።




በኤዞፕ መጽሐፍት  ብር ብቻ ይሸምቱ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መጽሐፍ ቅዱስ 1980 በቅናሽ ዋጋ አለን !!


1980

የአቡነ ተክለሀይማኖት ዘመን የታተመ !!!!


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ልዩ_ፕሮግራም
ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል።
-----
መግቢያ በነፃ

አቅራቢ : ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ

👉 ርዕስ:- ነገረ መሻገር - ሰውና ተፈጥሮ…

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- መጋቢት 9: 2015 ቅዳሜ እለት ምሽት ከ10:00 እስከ 12:30 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

ማስታወሻ::

👉👉 ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።


መጵሐፉን በናሽ ዋጋ

በኤዜፕ መጽሐፍት 150 ብር ብቻ ይሸምቱ

Читать полностью…
Subscribe to a channel