ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21
በጣም ቀደምት የመጀመሪያው በኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የታተመው ቅዱስ ቁርዓን እጃችን ላይ አለን !!!!!!
ምንጊዜም ለንባብ ባህል መጎልበት እንተጋለን !!!!!!!
አንድ ኮፒ ብቻ አግኝተናል !!!
አንደምንጊዜውም ቅድሚያ ለመጣ ደምበኛችን እነኾ እንላለን !!!!!!
ኤዞፕ መጽሐፍት
ቀደምት መጽሐፍትን ምንጊዜም ከየያሉበት አሰባስበን ለደምበኞቻችን እናቀርባለን !!!!!!!!!
ቆየት ያሉ የፀሎት መጽሐፍትንንና ድርሳናትን አዘጋጅተናል።
ምንጊዜም ለንባብ ባህል መጎልበት እንተጋለን !!!!!!
#ጠመንጃና_ሙዚቃ
የፋሺስት ኃይሎች ለወታደሮቻቸው ከኢትዮጵያዊያን ጋር መገናኘት “መርከስ“ እንደሆነ ቢለፍፉም ሮም ግን ተወዳጅ በነበረው “ፋቼታ ኔራ” ሙዚቃ ከመደነስ አልቦዘነችም:: “ፋቼታ ኔራ” በጦርነቱ ወቅት የወጣ የፍቅር ዜማ ነው፡፡ ትርጉሙም አንድ የጣሊያን ወታደር በአካል የማያውቃትን ውብ የሐበሻ ሴት መናፈቁን ይገልፃል፡፡ “ስጦታ ይዤ መጣሁልሽ" ይላታል፡፡....ይህ ዜማ ወታደሩ በሰሜንና በምሥራቅ ወደ አዲስ አበባ ሲገፋ በሠራዊቱ ውስጥ የተለመደ የድል ዜማ ቢሆንም ፋሺስት የአገሪቱን መዲና በተቆጣጠረ በአሥራ አምስት ቀናት ወስጥ ግን በአዋጅ ታገደ፥፡ “ፋቼታ ኔራን" ብቻ ሳይሆን በሮም ሱቆች ውስጥ የተሰቁሉ ወጣቱን ያነሳሳሉ የተባሉ የሐበሻ ሴቶች ውብ ምስሎች እንዲወርዱ ተደረገ።
በራስ እምሩ ቤት የተመሰረተውን ቡድን በመከታተልና በማክሰም በኩል የሀገር ፍቅር ማኅበሩን መስራች መኮንን ኃብተወልድ ያህል የጣረ ግለሰብ አልነበረም።መኮንን በሳምንቱ መጨረሻ እየተገናኙ የሚመክሩትን ወጣቶች ከመሰለል አንስቶ ቡድኑ እንዲበተን የሚቻላቸውን አድርገዋል፡፡ ተመሳሳይ የውይይት ክበብን በመመስረትም አምዴ ወንድአፍራሽና ማሞ ታደሰን ወደ ሀገር ፍቅር ቡድን ለማዛወር ችለዋል፡፡ በዚህ ወቅት
ሥር ነቀል ለውጥን የሚሻው ግርማሜ ንዋይም አርፎ የሚቀመጥ አልሆነም።
እንዳይላሉ በአምሥቱ ዓመት የወረራው ዘመን ለአርበኞች መሣሪያ ያመላልስ የነበረ ዓይነ ሥውር ነው፡፡ ይህ ሰው አስቀድሞ ጥይት ለአርበኞች ለማድረስ በአኮፋዳው ይዞ ሲንቀሳቀስ ተያዘ፡፡ ይሁንና “ዓይነ ሥውር የእኔ
ቢጤ በመሆኔ ያዘኑልኝ የጣሊያን ወታደሮች እጃቸው ላይ ገንዘብ ቢያጡ የሰጡኝ ነው” ብሎ ነፃ ወጣ፡፡ነገር ግን ከወራት በኋላም የእጅ ቦምቦችን ባቄላ አልብሶ ለአርበኞች ሊያሻግር ሲሞክር በድጋሚ በቁጥጥር
ሥር ዋለ፡፡…
ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት መኮንን እንዳልካቸው በንጉሠ ነገሥቱ የሥልጣን ጠቅላይነት አባዜ በፖለቲካ ሰማያችን ላይ ጎልተው አልመታየታቸው እውነት ቢሆንም ከሤራው ይልቅ ለኪነ-ጥበብ
ማድላታቸው ግን የራሱ ሚና እንደነበረው አያጠያይቅም፡፡ ለዚህ ደግሞ በሚኒስትርነት ቦታቸው ላይ ሆነው በርካታ መጻሕፍትን ለንባብ ማብቃታቸውና በአገሪቱ አዲስ የሆነውን የሲምፎኒ ኦርኬስትራን
መመስረታቸው አብነት ይሆናል፡፡ መኮንን በፕሬዘዳንትነት የመሩት ቀዳሚው የሲምፎን ኦርኬስትራ “The society of friends of music” የሚል መጠሪያ ነበረው::
ሜሪ አርምዴ አገር ምድሩ ሁሉ“ኧረ ጥራኝ ጫካው" እያለ በሚያንጎራጉርበትወቅት ዝመታን አልመረጠችም፡፡ይልቁንስ በአፍላ ዕድሜዋ ብላታ ኅሩይ ከተባሉ የጦር አበጋዝ ጋር ወደ አምባላጌ ዘመተች፡፡ በእዚያም
ከሠራዊቱ ጎን ተሰልፋ ስትፋለም እግሯን በጥይት ተመታች፡፡ አጋጣሚው ያሳዘናቸው አርበኞች ወደ ቤቷ እንድትመለስ ጠይቀዋት ነበር፡፡ ነገር ግን በጄ አላለቻቸውም፡፡ እንዲያውም ከአርበኞች እኩል ጋራ
ሸንተረሩን እያቆራረጠች ወደ ሽሬ ተጓዘች፡፡
✍ ይነገር ጌታቸው(ማዕርግ)
📖መጽሐፉ የተወሰደ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
የመላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ የቅኔ መጽሐፍት ውስጥ ቁጥርሽረንድ የኾነውና ከገበያ የጠፋው ታላቅ መጽሐፍ እጃችን ላይ !!!
Читать полностью…#አንጥረኝነት
#ብረት ስራ
#ወርቅ ስራ
እደጥበብን የሚዳስስ ታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፍ !!!
ሥርዓት_ዘሰሙነ_ሕማማት ( ከሰኞ እስከ ዓርብ )
#Ethiopia | ሰሙነ ህማማት ማለት :- ሰመነ - ማለት ሳምንት አደረገ ማለት ነው ፡፡ ይሔውም ከእለተ ሆሳዕና ሰርክ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ እና ቀናት የሚያመለክት ነው ፡፡
ሀመ - ማለት ታመመ ማለት ሲሆን ይህም የሰውን ዘር ሁሉ ከዳቢሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ፅዋተ መከራዎች የሚያሳስብ ነው ፡፡
የሰሙነ ህማማት እለታት የአመተ ኩነኔ ወይም የአመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት የሚያለቅሱበት የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ አምላካቸውን የሚማፀኑበት ጥዋት ማታ አምላካቸውን ደጅ የሚጠኑበት ፥ ሀጢያታቸውን በቤተክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት ፥ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው ፡፡
መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ ፣ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጠን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት፣ አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሠመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ “እንስቀለው… እንግደለው” ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ ይህንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡
ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ “እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት” ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ፥ ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም፤ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን “ሰላም ለኪ” ብሎ ነው ያታለላት፣ የዲያቢሎስ እና የይሁዳ ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡
ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኸው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ሥርወ መሠረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል።
በሳምንቱ ስርአተ ፍትሀት አይደረግም ፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ህይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሀን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወራት ምሳሌ በመሆኑ ነው ፡፡
በእለተ ምፅአት መላእክት የመለከትን ድምፅ እንደሚያሰሙ የዳግም ምፅአትን እለት በማሰብ ምዕመናን ጥሪውን ሰምተው ከዚያም አስቀድመው የበአሉ ታዳሚዋች መሆናቸውን ለማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭሉን እያቃጨለ ምዕመናኑን ያሳስባል ፡፡
በዚህ የህማማት ሳምንት የስግደት የፀሎትና የፆም ስርዐታችን እንደሚከተለው ነው።
† #ሰግደት
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ፣ 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። ይህም ክርስቶስ ስለኛ በደልና ኃጢት በሰው እጅ ተይዞ የቀበለውን መከራና ስቃይ ለማሰብ ነው። ክርስቶስ ለኛ ፍቅሩን አንዴ ሞቶ ገልፆልናል። እኛ ግን ስለበደላችን ፣ በፍርድ ሰዓት በግራ እንዳንቆም አብዝተን ንስሐ በመግባት ስጋችንን እናደክማለን።
† #ጸሎት
በስሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውሰጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ። እኒህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት ፣ 3 ሰዓት ፣ 6 ሰዓት ፣ 9 ሰዓት ፣ 11 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት ፣ ፣ 3 ሰዓት ፣ 6 ሰዓት ፣ 9 ሰዓት ፣ 11 ሰዓት ናቸው ።
በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኀያዊ አብዝተው ይጸለያሉ። ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሚደረግ የፀሎት ስርዓት ሲሆን ምዕመናን ተገኝተው ፀሎቱን ተካፋይ ይሆናሉየግል ፀሎታቸውም ከመዝሙረ ዳዊት ፣ ከውዳሴ ማርያምና ከውዳሴ አምላክ ፣ ከሰይፈ ስላሴና ሰይፈ መለኮት ሲሆን መልክዓ መልክዕና ድርሳናት እንዲሁም ተዓምራት በህማማት ሳምንት ባሉ ቀናት ውስጥ አይፀለዩም።
ይልቁንም ከቅዱሳን መፃህፍት የጌታን ያምላካችንን መከራውንና ድካሙን የሚያስታውሱ ከትንቢተ ኢሳያስ ፣ ከትንቢተ ኤርሚያስ ፣ ከመዝሙረ ዳዊት ፣ ግብረ ህማማት በየሰአቱ ይነበባል፡፡
† #ጾም
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም ። ይልቁንስ በመራብ በመጠማት በመስገድ በመፀለይ በመፆም በየሰአቱ የጌታችን የአምላካችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራውን ህማሙን ግርፋቱን ድካሙን በማሰብ ይዋላል እንጂ፡፡ በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም ይኸውም ቆሎ ዳቦ ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።
†
***
+ በሰሞነ ህማማት የሚጸለዮና የማይጸለዮ የጸሎት መጽሐፍት አሉ
=> የማይጸለዮ በሰሞነ ሕማማት የማይደገሙ የጸሎት መጽሐፍት :-
1.ድርሳናት
2.ገድላት
3.መልካ መልክ (መልኮች)
=> የሚጸለዮት ደግሞ:-
1. ውዳሴ ማርያም
2.መዝሙረ ዳዊት በብዛት ከወትሮ በተሐየ ቢያንስ የየዕለቱን ሙሉዉን
3. ሰይፈ መለኮት፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ውዳሴ አምላክ
4. ድርሳነ ማኀየዊ የጌታችን ሕማማትና እንግልቱ ያደረጋቸው ተዓምራትና ዐርኬ መልከአ ማኀየዊ አንድ ላይ የየዕለቱ አለው
5.ላሓ ማርያም የእመቤታችን ለቅሶ ሐዘን
+ የጸሎት መጽሐፍቶቹ ያለን በርትተን እንጸልይባቸው ያልገዛን በዚሁ አጋጣሚ በተለይ ድርሳነ ማኀየዊና ላሓ ማርያምን ገዝተን የጌታችንንም የእመቤታችንን ስቃይ እንግልት ሀዘን እንካፈል በረከት እናግኝ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም ለቤተክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት ተግተን እንጸልይ አንዘንጋ
" መልካም ሰሞነ ሕማማት "
ከጌጡ ተመስገን የፌስቡክ ፔጅ የተወሰደ
""ጥበብ ይናፍቀኛል፣ ተቻችሎ የሚኖር ሕዝብ ያስቀናኛል፣ ድንቁርና ያስፈራኛል፣ ጦርነት ያስጠላኛል"" ጋሽ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
Читать полностью…አታልቅስ አትበሉኝ
(ደበበ ሰይፉ)
አትሳቅስ በሉኝ
ግዴለም ከልክሉኝ፤
የፊቴን ፀዳል
አጠልሹት በከሰል፤
የግንባሬን ቆዳ
ስፉት በመደዳ፤
ጨጓራ አስመስሉት።
ግዴለም።
አትጫወት በሉኝ
ዘፈኔን ንጠቁኝ
ግዴለም።
ብቻ ፤ አታልቅስ አትበሉኝ
አትጩህ አትበሉኝ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
#በቅርብ_ቀን
በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት በእንደርታ ወረዳ ለሰሰማት ትኩል ምዕራፈ ቅዱሳን ቤተ ደናግል ገዳም ሙሉ ገቢው የሚውለው "ከሞት ባሻገር" መጽሐፍ ሁለተኛ እትም
እና
ለኳታር ዶሃ ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ሕንፃ ማሠሪያ ሙሉ ገቢው የሚውለው አበረታች መድኃኒት መጽሐፎች በዘመነ ትንሣኤ በአዲስ አበባና በዶሃ ታትመው በገበያ ላይ ይውላሉ::
ሁለቱም መጻሕፍት ለሁለተኛ ጊዜ የታተሙ ሲሆን ከሞት ባሻገር በገጽ ብዛት ጭማሪ የተደረገበት ክልስ እትም (revised edition) ነው::
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
#ካህሊል_ጂብራን
ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ! በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ?
በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ? እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ? ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?
በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም።
ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት።
በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት። መሪዎች ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት።
አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት።
ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት።
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
…
ከልጅነቴ ጀምሮ በምሽት ስንሸራሸር በዙሪያዬ የማያቸው ዛፎች ሁኔታ ይገርመኛል፡፡ የሌሉ ያህል ጭምት፣ ትዝታን፣ ቁዛሜን የሚጠሩ ንጹህ ፍጥረታት... በተለምዶ ውኃ ቅዱስ እንላለን አይደል? በቅድስና ዛፎቹን የሚስተካከል ነገር አለ እንዴ? ዛፎች የሚሰጡ፣ የሚያበረክቱ፣ የሚያስጠልሉ እንጂ ከማንም ምንም የማይጠብቁ ጽኑ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን እንዳሉት የሰው ልጅ ከሆነ ያለማወቅ ድንግርግር ወደ ፍዝ ንቃት ሲንደረደር መጀመሪያ የተቀበሉት፣ ያስጠለሉት፣ የመገቡት ዛፎች ነበሩ፡፡ ዛሬም ቢሆን!
ከመጽሐፉ የተወሰደ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
The prophet
የመጀመሪያው ትርጉም ነብዩ በዋቅጅራ ጎባ የተተረጎመ !!!!!
እጃችን ላይ
በምግባሩ ጸጥታና እርጋታን ገንዘቡ ያደረገ ነው።ስብዕናው የሚነበብ መጽሐፍ ነው፡፡ከአንደበቱ ጠባቂ ያለው አርምሞን ገንዘብ ያደረገ ነው፡፡በከተማ የሚኖር፣ቆብ ያልደፋ፣ቀሚስ ያለበሰ፣አሸንክታብ ለብሶ በአደባባይ የማይወጣ ተሃራሚ ስውር መነኩሴ ነው፡፡መጽሐፍቶቹ እጅግ ጥብቅና እንደ አለት የጠነከሩ መለኮታዊ ቃል የነጠበባቸው ናቸው፡፡እጅግ ሲበዛ ለቤተ ክርስቲያን ቀናተኛ ወታደር ነው፡፡ብዙ አኀው የዘመን መክፈያ፣ዳግማዊ ቄርሎስ ወዘተ ይሉታል፡፡እርሱ ግን ሙገሳ ይቅርና ልከኛ ክብር እንኳን አጥብቆ ይሸሻል፤ይጸየፋልም፡፡ነገረ ሃይማኖትንና የዓለምን ርዕዮት ጠንቅቆ በጥልቀት የተረዳ ባለአእምሮ ነው፡፡በመንፈሳዊ ዕይታ እንደ አባቶቹ ነገሮችን እንደ ንስር የሚመለከት ብርሃን ክርስቶስ የሆነለት ብዕረኛ ነው፡፡ንባብና ጽሞና፤ትሕትና እና ትጋት፣ፍቅርና እውቀት በተአቅቦ የተዋሐዱለት እውነተኛ አገልጋይ ገብር ኄር ነው፡፡
ምንፍቅናን እራቁቱን ያስቀረ፣የተኩላውን ለምድ የገፈፈ፤በአውሮጳ የምንፍቅና እና ኦርቶዶክስ ጠል እርዮት ዓለም እንደ አሽከላ የተተበተበችውን ዓለም በወንጌል ስብከት የበጣጠሰ ቅን አገልጋይ ነው፡፡በዓለማዊ ከንቱ ልፍለፋና፣በእነ ዳሪዊን እንስሳዊ የሽቅድድም ንድፈ ሃሳብ(theory) ግብዝነት ባለው እውቀት የተበተነውን አህዛብ ወደ እራሱ የመለሰ የበጎች እረኛ ክርስቶስ ያሰማራዊ የመከሩ ሰራተኛ ነው፡፡
ስብከቶቹ ደርዝ ያላቸው።ምስጢራቸው የረቀቀ፤አስተውሎት የሚፈልጉ፣ከአሮጊቶች ወግና ከዓለም ልፍለፋና ቧልት የነጹ ናቸው፡፡ተጠየቃዊ ንጽጽራዊ ነገረ መለኮት(Comparative theology) መዓዛ የሚሸቱ ናቸው፡፡ 'ሞልቶልኛል፣ድኛለሁ፣ሁሉ የኔ፤' ወዘተ ከሚል የሰይጣን ትምህርት የተላቀቀ በአንጻሩ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ፦" ምሳር በዛፉ ሥር ተቀምጧል..." ብሎ የክርስቶስን ቤዛነት ሳይዘነጋ በዚህ መሠረትነት በምግባር፣በቱርፋት፣በጸጋ ክርስቶስን መምሰል(theosis) የሚያደርስ የወንጌል ቃል የሚመግብ እውነተኛ መንገድ ጠራጊ የዘመኔ ዮሐንስ ነው ዲ/ን ያረጋል አበዝ፡፡
እኔም እላለሁ፦ተወዳጆቼ መጽሐፍቱን አንብባችሁ ነፍሳችሁን በእግዚአብሔር መንፈስ አስጊጧት፤የእንግድነት ዘመናችሁን ዋጁት፤በክርስቶስ ባለው ፍቅር እለምናችሗለሁ መንፈሳዊ እረፍት ታገኛላችሁ፡፡በመጨረሻም ለምስጢራት በቅታችሁ እግዚአብሔርን ወደ መምሰል ታድጉበታላችሁ፡፡ይሄ ደግሞ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት መድረሻ የቀናዉ መንገድ ነው፡፡
(ዲ/ን መልካሙ ኃይሉ )
/channel/azop78
ቶ '' ያልተነገረው ጥንታዊው የአባይ ሸለቆ ህዝቦች ፍልስፍና !!!
ይህንን መጽሐፍ ብዙ አንባቢያን አላወቁትም !!
ይህ ማለት ደግሞ መጽሐፉ በውስን ሰወች እጅ ብቻ እንዲቀር አድርጎታል።
የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት የጥንቱ የኢትዮጵያ ፍልስፍና መሰረታዊ አስተሳሰብ ላይ የሚያወራ ቢሆንም ግን የንባብ ባህላችን እጅጉን አናሳ መሆኑና የሚነበቡትም መጽሐፍት በቲፎዞ የሚጮህላቸው መጽሐፍት በመሆናቸው ተደብቆ የመቅረት እንዲህ አይነት እጣ ፈንታ ከገጠማቸው መጽሐፍት አንዱ ሆኗል።
ብልህ አንባቢያን እጅ ላይ ግን አልፎ አልፎም ቢሆን መመልከት ችያለሁ።
እነሆ ቢያነቡት የሚያተፉበት መጽሐፍ ነው !!!!!
መልካም በዓል እየተመኘሁ የበዓል ጥቆማ ቢሆን ብየ አጋራዋችሁ።
/channel/azop78
ውድ የኤዞፕ መጽሐፍት መደብር ደምበኛችን እነዚኽን ኹለት መጽሐፍትበመደብራችን ሸምተህ ረስተህ ኼደሓልና በክብር ተቀምጠውልኻልና መጥተህ መውሰድ ትችላለህ !!!!
ምንጊዜም ለንባብ ባህል መጎልበት እንተጋለን !!!!!!
ምድረበዳ ሌሊት
(በእውቀቱ ስዩም)
ስንት ዘመን ሆነ?
ጥላሁን ገሰሰ
“በምሽት ጨረቃ” ብሎ ከዘፈነ?
አንዳንዴ ሳስበው፥ በጥላሁን ዘመን፥
ልክ እንደ አባት እቅፍ፥ ሌሊቱ ሲታመን
ባውሬ በቀማኛ
በሮንድ ፥በዘበኛ
ላፍታ ሳይሸበር
ፍቅር በፈቃዱ፥ ውጭ አዳሪ ነበር::
ዘመን ተቀይሮ ፥
እንኳን በሌት፥ በቀን ፍርሀት ሲሰፈን
ማነው ዛሬ ደፍሮ
“ በምሽት ጨረቃ?” ብሎ የሚዘፍን?
ያስፈራል መንገዱ
ያስፈራል፥ አጸዱ
ያስፈራል አልፎሂያጅ
ያስፈራል ጎረቤት
የሁሉም ሰው መርህ-በጊዜ ወደ ቤት!
ወትሮ እያባረረው፥
እየገፈተረው
ሀቁና ፈጠራው፥ ባንድ ላይ አድሞ
ወደ ቤቱ ገባ፥ ሰው ከጀንበር ቀድሞ
ደጁ ተቆለፈ
በሰአት እላፊ የታጠረ ትውልድ
የሌሊቱን ውበት፤ ሳይቀምሰው አለፈ::
በሰዎች ልብ ውስጥ፤ ዜማ መቀስቀሷ
ባፍለኞች ልብ ውስጥ፥ ፍቅር መጸነሷ
እያፍለቀለቃት
እስክታስለቅቃት
ከቦታዋ ደርሳ፥ የማለዳ ጀንበር
ጨረቃ ሰማይ ላይ ትንሰራፋ ነበር::
ዛሬ ሰው ቸግሯት
ብቸኝነት ገርፏት
መሪር እያነባች
ዘግይታ፥ ብቅ ብላ፥ ያለጊዜ ገባች::
ሐዘንሽ አመመኝ ደበበ ሰይፉ
ውል አልነበረንም የፍቅር ቀጠሮ
ቃልም አላኖርንም በወግ ተቀምሮ፤
እኔ አንቺን እንዳላይ
አንቺ እኔን እንዳታይ አምባችን ተቃጽሮ
ዕጣችን ተካሮ፤
ቀለምሽ ከዐይኔ አሻራሽ ከጣቴ ባይጠፋ ተማትሮ
(እትብት እምብርት ሁኖ እንዲኖር ደድሮ)
ይኸው አካሄደን በድንገት ዘንድሮ።
የገጽሽ ብርሃን ቢጠይም ፀዳሉ
ድምፅሽ ቢቀጥንብኝ ቢሠልብኝ ቃሉ
ወዘናሽ ቢማስን ዛሬ ያለውሉ
በእጆችሽ ጨበጠኝ ሐዘንሽ ሥዕሉ
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጀንበር ነሽ አበባ ሕይወት ተስፋ ዘቦ
ፋሲካ ዕንቁጣጣሽ ማኅሌተ ገንቦ
በዬ ያወደስኩበት ታዘበኝ ዘመኔ የትላንታት ቀኔ
ዛሬ ሊጮህብኝ ቅኔ እንዳይደል እውኔ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
የገደል ማሚቶን ታዘብኳት ተኝታ
በጩኽትሽ ማየል አኩርፋና ታክታ
ላንቃዋ ይታየኛል ደም ለብሶ ደም ጐርሶ
ቃልሽ ያለፈበት በጭንቅ ተለውሶ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጽጌሬዳይቱ ንቦችሽ አለቁ ሰዎችሽ ደቀቁ
ጨፌ ላይ ተኝተው ባድማ ላይ ነቁ፤
ዐዋይን ሰማኋት ስታለቅስ በይፋ
ከጐጆሽ ስትወጣ ትቢያዋን አራግፋ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
አላውቅልሽ ብዬ አታውቂልኝ ብዬ
እምነትሽን ጥዬ ፍቅርሽን ገድዬ
አኩርፌሽ ስቀመጥ ያው እንደ ባላንጣ
ይኸው ነጭ ማተብሽ ሊያስታርቀን መጣ፤
ሐዘን ነው ውበትሽ ውበት ነው ፍቅርሽ
ብርሃን – ጥለት አልቦ ከል ነጠላሽ
ዐይኔን የገለጠው ጥቁር ጨለማሽ፤…
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ግንቦት 1966ዓ.ም.
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
“ እመዬ እሁድን ትወጃታለሽ ? ” አለ ' አንድ እሁድ እንደ ልማዳቸው ምሳቸውን በልተው በሚያወሩበት ጊዜ።
“ በጣም እወዳታለሁ ” አለች እናቱ።
“ ለምን ? ”
“ አንተን የማይባት ቀን ስለ ሆነች።”
“ መልክዋ እንዴት ያለ ነው ?”እንዴት ያለች ሆና ትታይሻለች ?”
“ እንዴ ! እሁድ ሰው ናት ?” ቀን አደለችም ?” አለች ደመቀች ' ከልብዋ እዬሳቀች።”
“ ቀን መሆንዋንማ አውቃለሁ ” አለ ተከስተም እዬሳቀ “ ብቻ እኔ ሳስባት — በቀይና በጠይም መሀከል ያለ መልከ ምን ይባ ላል ?”
” ዳማ ! '”
“ አዎ ዳማ ወይዘሮ መስላ ትታየኛለች። ጥርስዋ ከንቅሳቱ ጋር በጣም የሚያምር ፣ አይንዋን የተኩዋለች ፣ ጠጉርዋ በጣም የሚያምር ሆኖ በትንሹ ሽበት ያሰረገው ነው። ብቻ ፊትዋ የልጅ ፊት ስለሆነ ሽበቱ አውቃ ለጌጥ ያደረገችው ይመስላል። ሁልጊዜ ክንፈርዋን ሳትከድን ፈገግ ብላ ፊትዋን ደስ ብሎት በጥልፍ ቀሚስ ዋና በጥበብ ኩታዋ ላይ ካባ ደርባ ፣ ረጋ ብላ ካንቺ ፊት ፊት በዚህ በምዕራብ በር ስትገባ አያታለሁ። ታዲያ እስዋን ሳይ ሁልጊዜም አንቺን በሁዋላዋ አይሻለሁ። ስለዚህ — አንቺን ይዛልኝ ስለምትመጣ ነው መሰለኝ በጣም እወዳታለሁ : ትናፍቀኛለች።”
“ በቃ ! እንግዲህ ያችን እሁድን አልወዳትም ! ” አለች ደመቀች ግንባርዋን በውሸት ኮስተር አድርጋ።
“ ለምን ? ”
“ አንተ ስለምትወዳት ! እንዲህ አስጊጠህ አሳምረህ የምታያት ከኔ የበለጠ ብትወዳት አደል ?”
“ ይህን የተናገረ አፍሽ መቀጣት አለበት ! ” አለና ተከስተ የናቱን አፍ ለመምታት እስዋ ለመከልከል ትንፋሻቸው እስኪቆረጥ እዬሳቁ ሲታገሉ ቆይተው በሁዋላ ሲደክማቸው ' ትግሉን ትተው እንደገና ወሬያቸውን ቀጠሉ”
“ “ እስዋ እንዲህ አጊጣ አምራ አያታለሁ ” አልሁ እንጂ የማስጌጣትና የማሳምራት እኔ እደለሁም። የምወዳትም የምወዳትን እመዬን ስለምታመጣልኝ ነው ” ሲል ተከስተ ድንገት ሳያስበው አንገቱን እቅፍ ' ጭንቅ አድርጋ ይዛ ሳመችው እናቱ።”
“ ታዲያ እሁድ እንዲህ ሆና ትታዬኛለች ” ብዬ ለዚያ' ይወደኛል ላልሁሽ አስተማሪ ለጋሽ ሀይሉ ስነግረው ያለኝን ልንገርሽ ? ” አለ ተከስተ ቀጥሎ።
“ ምን አለህ ? ”
“ እሁድ ሁልጊዜ አጊጣ አምራ ፣ ፈገግ ብላ ፣ ፊትዋ በደስታ ሰርቶ ረጋ ፣ ኮራ ብላ የወይዘሮ አካሄድ እዬሄደች እናትህን ይዛ ስትመጣ የምታያት እሁድ የረፍት ፣ የደስታ፣ የጭዋታ የጌጥ ቀን ስለ ሆነችና የምትወዳትን እናትህን የምታይባት ቀን ስለሆነች ህቡእ “ አእምሮህ ” ላንተ ሳይሰማህ ይህን ሁሉ አሳብ ባንድ ላይ አስማምቶ ይህ ሁሉ አሳብ ባንድ ላይ የሚታይባት ወይዘሮ አሳምሮ ስሎ ለ “ ክሱት አእምሮህ ስላቀበለው ፡ ‛ ክሱት ' አእምሮህ ያችን ከ “ ህቡእ ˚ አእምሮህ የተቀበላትን ከረፍት፣ ከደስታ፣ ከጭዋታ ከጌጥ ቀለም የተሳለች እሁድ የዚያችን ጥሩ ወይዘሮ ስእል እያሳዬህ ነው ” አለኝ።”
“ ጥሩ ነው ፤ እንግዲህ ስእል መሳል ተማርና እሁድን ብቻ ሳይሆን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ያሉትን ቀኖች ሁሉ ወይዛዝርና መኩዋንንት እያደረግህ በዚያ — ምንድነው ? * ህቡእ — ክሱት ” አእምሮ ባልኸው ቀለም እንደ እሁድ እያሳመርህ እዬሳልህ ታሳዬኛለህ !” ስትል ደመቀች ' በልጅዋ ለመቀለድ ተከስተ በፈንታው ፡ እናቱ “ ህቡእና ክሱት ” አእምሮ ፡ የስእል ቀለም መስሎዋት ፡ በተናገረችው በጣም ሲስቅ ቆዬና '
“ ህቡእና ክሱት አእምሮ ” ቀለም አደለምኮ ፣ እምዬ ” አለ።
“ አንተኮ ነህ — ከ' ህቡእ ' – ከ “ ክሱት አእምሮ የተሳለች ያልህ ! አላልህም ?”
“ እንደሱ አላልሁም።”
“ እሺ መቸም “ ህቡእና ክሱት አእምሮ ' ያልኽውን ከስእል ጋር አያይዘህ ነው የተናገርኸው ፤ ታዲያ እንግዲያ - የስእል መሳያ ወረቀት ነው ?” ተከስተ አሁንም እዬሳቀ የናቱን አንገት አቅፎ ራስዋን ( ግን ባርዋንና ፊትዋን ሁሉ ሲስም ቆዬና “ ኣእምሮ አታውቂም እመዬ ?” አለ።
“ አእምሮማ አውቃለሁ ፤ አእምሮ የምናስብበት ነው። የማላውቀው — እሁድን ባለካባ ወይዘሮ የሚያደርገውን ' ያን ያንተን " “ ህቡእ - ክሱት ” የሚባለውን አዲስ አይነት አእምሮ ነው ” አለች ደመቀችም እዬሳቀች።
📖📖 የልምዣት
✍✍ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
#በምናልባት_ኑሮ
አይቦዝን አንቀልባው
አይሞላም ጉድጓዱ
ሺሆች ሞተው ሲያድሩ
ሺሆች ተወለዱ
ይመሻል ይነጋል
ያው እንደልማዱ
መሬት ባሕር ሆኖ ፥ድሀን ሰለቀጠው
ትልልቁ ቪላ፥ ትንሹን ቤት ዋጠው
በመስታወት ጫካ፥ በጡብ በብረት ደን
ዐየሁ ባደባባይ ፥ሰው በሰው ሲታደን::
LA VIE PEUT-ÊTRE
Le berceau ne chôme pas
le trou n'en finit pas de se remplir
morts par milliers la nuit venue
nés par milliers
soir et matin
comme d'habitude
Telle océan la terre engloutit le pauvre
le manoir gobe la bicoque
jungle de verre - forêt de brique et d'airain
vu sur la Place, l'homme chasse à l'homme
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
የእንዳለ ጌታ ከበደ
አስራ አራተኛ የኾነው !!!
እስረኞቹ የተሰኘው መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል !!!!
አንድ ደግ ሰው በፈረስ ከሩቅ ሃገር ወደ መንደሩ ሲመለስ በጫካ ውስጥ አንድ ሌባ ሰው የታመመ በመምሰል
" ጌታው አትለፈኝ እባክህ?! ከባድ የሆነ ሆድ ቁርጠት ይዞኛል። በምትወደው ከዚህ ጥለሀኝ ከሄድ እየመሸ ስለሆነ አውሬ ይበላኛል" ብሎ ይማጸነዋል::
ደጉም ሰው ያዝንለትና "አይዞክ ወንድሜ" ብሎ ከፈረሱ ላይ ተሸክሞ ያወጣዋል።
የፈረሱንም ሉጋም ይዞ በእግሩ ፊት ፊት ይመራዋል።
ሌባውም "ጌታው በግርህ ለራስክ ከመሄድ ይልቅ የፈረሱን ልጓም ይዘክ ስትመራኝ ጀንበር እያዘቀዘቀች ስለሆነ እንቅፋት ይመታካል:: ተሰናክለክም ብትወድቅ ጉዳት ይሆናልና እርካቡን አስቆንጥጠሀኝ ሉጋሙን አሲዘኝ ቀስ እያልኩ አዘግማለው" ይለዋል::
የፈረሱም ባለቤት በየዋህነት ፈረሱን ለሌባው ይለቅለታል።
ይን ጊዜ ሌባው ፈረሱን ኮርኩሮ ሉጋሙን አላልቶ ሽምጥ ጋለበ።
በስላቅም እንግዲህ ደህና አምሽ ጌታው ብሎ ተፈተለከ
ሲጋልብም ሳለ ያ ደግ ሰው ተጣርቶ አንተ ሰው ፈረሱንስ ውሰደው ግን እባክህ አንድ ነገር ልንገርህ ስማኝ አለው
ሌባውም እየጋለበ "ምንድነው እሱ?!"
"ይህን ያረከውን ነገር ማንም ሰው እንዳይሰማው ሰው የሰማ እንደሆነ በእውነት ለታመመና ለወደቀ የደግ ሃሳብ ርህራሄ እንዳያደርግለት ይፈራልና ነው!" ብሎ ቢነግረው
ሌባው በዚህ ነገር ልቡ ተነክቶ ተጸጽቶ ፈረሱን መለሰለት ይባላል::
" ፍቅር ሁሌ እኔ ምን እሆናለው። ሳይሆን ወንድሜ ምን ይሆናል? ነው የሚለው! እንዲህ አይነት ሰው በዚህ ዘመን ይገኝ ይሆን? "
✍✍ከ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
📖📖ታሪክና ምሳሌ 3ኛ መጽሐፍ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏