azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8863

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ከከበደ_ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ ፩

እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ'ነው።

                 *****
ከማዘዝ በፊ
ት አስቀድሞ መታዘዝን ማወቅ ያስፈልጋል ።

                  ******

ጥሩም ነገ
ር ቢሆን ከመጠን ካለፈ ሁልጊዜምመጥፎ ነው ።

                 *****

ትዕቢትና
ውርዶት አካልና ጥላ ናቸው ሳይለያዩ ሁልጊዜ
ቀዳሚና ተከታይ ሆነው  ተያይዘው  ሊሄዱ ይኖራሉ።

                ***

እህልና ውሃ ዕው
ነትን እንደሚመግቡት ሁሉ  መጻሕፍትን ማንበብም አንደዚሁ መንፈስን ይመግበዋል።

           ****

ከበላይህ  ያሉት
ን ሰዎች እያየህ በልብህ ቅናት አይደርብህ።
ይልቅስ ካንተ በታች ያሉትን ችግረኞች  እየተመለከትሀ  ዕድ
ልህ ከነሱ የተሻለ በመሆኑ ፈጣሪህን አመስግነው ።

           ******

ማንም ሰው  ቢሆ
ን መከራ ወድቆበት ባየሀ ጊዜ  አትፍረድበት  ወይም  እትጨክንበት  በእሱ  ላይ  የደረሰ መከራ ምናልባት  ባንተም  ላይ ወደፊት ሳይደርስብህ  አይቀርም ይሆናል ።

             ***

ምንም እን
ኳን የሚያስመሰግንህ ትልቅ ሥራ ብትሠራ
ምን ጊዜም ቢሆን አትመካበት ትምክሕት ማንኛውንም ዋጋ
ቢሆን ያቀለዋል ትሕትና ግን ከሁሉ  ሞያ የበለጠ ዋጋ ያለው
ባሕርይ ነው ።

               ***

ሰው  በሕይወቱ 
ሲኖር የሚያገኘውን መልካም ነገር ሁሉ
የሚቀበለው ከተወለደባት እገር ስለ ሆነ አስፈላጊ ምክንያት
በመጣ ጊዜ ያለው  መልካም  ነገር  ሁሉ ሕይወቱን እንኳን
ሳይቀር  ሳያመነታ ላገሩ ሲል ሊሠዋ ይገባዋል ።

             ~ ~

        ደስ ደስ የሚሉ ጠቃሚ ሀሳቦች 
            በታሪክና ምሳሌ  መፅሐፍ

  የቴሌግራም ቻናላችን @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን @azopbook

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
📚📚📚📚📚📚📚📚

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የታሪክ መጽሐፍትን ለመሸመት ተመራጭ ቤት
ኤዞፕ መጽሐፍት !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እጅግ ቀደምት መጽሐፍ ቅዱስ እጃችን ላይ ይገኛል !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህንን መጽሐፍ በተደጋጋሚ አስተዋውቀነዋል።
ለምን ይኾን ቢሉን ? በአተረጓጎም ስልቱም ኾነ በታሪካዊ ይዘቱ እጅግ ላቅ ያለ አፃፃፍ ስልትና የአተረጋጎም ዘይቬን ተከትሎ የተዘጋጀ መጽሐፍ መኾኑ አነሳስቶን ጭምር ነውን


መጽሐፉ በመደብራችን በ250 ብር ብቻ እየተሸጠ ይገኛል።

እነኾ ትንሽ ቅጅዎች አሉን !!
ቀድመው ይሸምቱ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሥለመጽሐፉ የተሰጡ አስተያየቶች

'The plot to kill grazing" የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በግራዚያኒ ላይ ተቃጥቶ የነበረውን የግድያ ሙከራ እና ያስከተውን የአሰቃቂ ውጤት ሙሉ ታሪኩን መልሶ ማስቃኘት የቻለ፤ ግንባር ቀደም የተዋጣለት መጽሐፋ ነው፡፡ የመጽሐፍ ስኬታማና ጠንካራ ጎን በብዙ መልኩ ከጣሊያኖች ዘንድ በተገኙ የመረጃ ምንጮች ያልታጨቀ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ (መጽሐፉ) ከግድያ ሙከራው ተሳታፊዎች የቤተሰብ አባላት ወይም ከተከታዮቻቸው አሊያም ከወዳዶቻቸው አንደበት በተቀዱ መረጃዎች ትክክለኛነት ይበልጡኑ ለማረጋገጥ ጥሬ ሀቆችን' በኢትዮጵዊያን በኩል በብዛት ከሚገኙ የጽሀፍ ምንጮች ጋር ያነጻጽራቸዋል፡፡ መጽሐፉ ለአንባቢያን በዚያ ክስተት ውስጥ የነበሩትን ዋና ዋና ሰዎች ማንነት በጥንቃቄ ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ የታሪኩ ፍሰትና አገላለጽ ቀላልና ሳያድበሰብስ የቀረበ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በፋሽስት ጣሊያን የተያዘችበትን የአምስት ዓመቱን ታሪክ የማወቅ ፍላጎት ባላቸው ሰዎች ሁሉ' ሊነበብ የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡



ሽፈራው በለ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 11 ምሪተስ ፕሮፌሰር



ይህ መጽሐፍ ያበረከተው ትልቅ አስተዋጽኦ ውስብስብ የነበረውን የሴራውን ባህሪ አፍታቶ ግልጥልጥ አድርጎ ማሳየት ማቻሉ ነው፡፡ ቀደም ባሉ ዘመናት በተለምዶ አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ተብለው ከሚታወቁ ሁለት ስሞች ጋር ብቻ ተያይዞ የቆየውን ክስተት፤ አሁን በስደት ላይ የነበሩትን ንጉሠ-ነገሥት ጨምሮ በርካታ ሰዎች እና ቡድኖች የተሳተፉበት ፈርጀ ብዙ ሴራ ሆኖ ብቅ እያለ ነው፡፡ በቃ ከተነገሩ የመረጃ ምንጮች፤ ምስጋናን ጨምሮ የሰነድ አያያዙ የተሟላና የተደራጀ ነው፡፡ በተጨማሪም መጽሐፉ በስፊው በስዕላዊ መግለጫዎች የተብራራ ነው፡፡ ይህም በድርጊት የተሞላና በርካቶችን በአስገራሚ ሁኔታ ላሳተፈው ለዚህ ዓይነቱ ታሪካዊ ክስተት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡




ባህሩ ዘውዴ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ኢምሪተስ ፕሮፌሰር

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የተለያዩ
#ግዕዝ አማርኛ
#አማርኛ በአማርኛ
#እንግሊዝኛ በእንግሊዝኛ
#ትግርኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#ኦሮምኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#አገውኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#አርጎብኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#ሲዳምኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#ቀደምት ትግርኛ በትግርኛ

መዝገበ ቃላቶች እኻችን ላይ ናቸው !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በልሳነ ግዕዝ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ እጃችን ላይ ነው !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የፕሬፈሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ታላላቅ የምርምር ሥራዎች መካከል በጥቂቱ እነኾ !!!!


ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ከ400 በላይ የሚኾኑ ታላላቅ የምርምር ሥራዎችን ያበረከቱ ምኹር ሲኾኑ በመጽሐፍ መልኩ ከታተሙት መካከል በጥቂቱ እነኾ እጃችን ላይ ይገኛሉ!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ፍኖተ መድሀኒት

- የሰው ልጅ የሺህ ዘመናት ጉዞን በመድሀኒት በኩል ለማሳያት ይሞክራል፡፡

- የሰው ልጅ በሽታ የፈጣሪ ቁጣ ነው ብሎ ያምን ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ አሁን ላይ እንዴት የዘረ መል ህክምና እንደደረሰ ለማሳየት ይሞክራል፡፡

- የፍልስፍና ጥማት ካለብዎ፣ ከቀደምት የግሪክና የሮማ እና ከአረብ ፈላስፋዎች ጋር ያስተዋውቃል፡፡

- መድሀኒት በዘመናዊ መንገድ ለማግኘት የሚያልፍባቸው ሳንይሳዊ መንገዶች በዝርዝር ያስቃኛል፤ የተመረጡ መድሀኒቶች ከየት ተነስተው የት እንደደረሱ ያመላክታል፤ የሰው ልጅ ለሳይንስ ያለውን ቁርጠንኝት ያደንቃሉ፤ይደማመሉ፡፡

- መድሀኒቶች ለማግኘት ገፊ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይፈተሻሉ፡፡ ምን አይነት ማህበራዊና ኢኮኖሚ ሁነት ስለነበር ነው መድሀኒቶቹ ሊገኙ የቻለው የሚለውን ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

- የፖለቲካ ጥማት ካለብዎ ሶሻሊዝም፣ ካፒታሊዝምና ዮጄኒክስ አስተሳሰብ/እንቅስቃሴ ከመድሀኒት ጋር ተላቁጠው ቀርበዋል፡፡ ከናዚ እስከ ታሊባን፣ ከከቴዎዶር ሩዝቬልት እስከ አዶልፍ ሒትለር፣ ከአዶልፍ ሒትለር እስከ ሙላህ ኡመር እና ኦሳማ ቢላደን ተቃኝተዋል፡፡

- መድሀኒት በተመለከተ የሚነሱ ሀይማኖታዊ እና ፖቲካዊ ሙግቶች/ክርክሮች፣ የሞራል ተጠየቆች በሚገባ ከታሪካዊና ሳይንሳዊ ጉዳዮች ጋር ተሰናስለው ቀርበዋል፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አለቃ ኪዳነ ዎልድ ክፍሌ
የህትመት ዘመን 1941
ኦሪጅናል መጽሐፍ እጃችን ላይ ነው

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ከባዶ ላይ መዝገን
#የካህሊል አማልክት
#የመሻገር ሲቃ
#ሰልስቱ ጣኦታት
#የማዕበል ጥንስስ

የተሰኙ ስራዎችን አበርክቶልናል። ታላላቆቹ ደራሲያን ስለተባ ብዕሩ ይመሰክሩለታል። በወጣትነቱ እንዲህ የሚያስደምመን በበሰለ ቁጥር እጅግ የሚጎመራ ጠንካራ ብዕር ያለው ሰውና ጥልቅ አንባቢነቱ ጎልቶ የሚታወቅበት ከሚከትባቸው ጠንካራ ሃሣቦቹ ውስጥ ብስለቱ የሚታይ የሥነ ጽሑፍ ሰው ነው ይሉታል። የሚመጡት ጊዜያት ላይ በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታላቅ ተስፋ የሚጣልበት ብዕረኛ ነው ሲሉ ይመሰክሩለታል።
#ያዕቆብ ብርሃኑ፣ የመሻገር ሲቃና የካህሊል አማልክት ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ አለን። አንብቡለት ብዙ የምታተርፉበት ብዕረኛ ነው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከሞት ባሻገር !


ዲያቆን ኄኖክ ኃይሌ

አዲስ መጽሐፍ !!
በገበያ ላይ ውሏል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የባህላዊና የውጭ አገር ምግቦች አዘገጃጀት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኸሊል ጂብራንን በጨረፍታ
------
አፈንዲ ሙተቂ
------
ሳታስቡት የሚያወዛግባችሁ ሰው ገጥሞአችኋል? አዎን! ይህ ሰው ሳታስቡት ያወዛግባችኋል። ነገር ግን የሚጽፈው ነገር ልብና አዕምሮን የሚያረካ በመሆኑ እርሱን ስታነቡት ውዝግቡን ትረሱትና የእርሱን መዝሙር ትዘምራላችሁ።

በዛሬዋ ምሽት ስለዚህ ድንቅ ሰው ጥቂት ነገሮችን እንጽፍ ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል (እናንተም በጥቂቱ ብቻ ብታነቡት ይሻላችኋል። ወደ እርሱ ባሕር ከገባን መውጣቱ ይከብደናልና)።
-------
ይህ ሰው ኸሊል ጂብራን ነው። ጂብራን ማን ነው? በሰፊው የሚያስጽፍ ርእስ ነው። በአጭሩ ግን እንዲህ እንግለጸው።

=> መካከለኛው ምሥራቅ ከጥንቶቹ አል-ገዛሊ፣ አል-ራዚ እና ባያዚድ በስጠሚ ወዲህ ያፈራው ታላቁ የምሳጤ አባት ነው።

=> መካከለኛው ምስራቅ ከታላላቆቹና ከጥንቶቹ አል-ኪንዲ፣ አል-ፈረቢ እና ኢብን ሩሽድ (Averroes) በኋላ ለዓለም ያበረከተው ታላቁ ፈላስፋ ነው።

=> መካከለኛው ምሥራቅ ከጥንቶቹ ሩሚ፣ ሰነዒ፣ ፊርደውሲ፣ ጃሚ እና አጣር ወዲህ ያስገኘው የልብ ምት ገጣሚ (mystic poet) ነው።

=> መካከለኛው ምሥራቅ ከአል-መተነቢህ እና ኢብን ሀውቃል ወዲህ ያፈራው ታላቁ የስነ-ጽሑፍ ንጉሥና ገጣሚ ነው።
------
"ኸሊል ጂብራን ሳታስቡት ያወዛግባችኋል" ብያለሁ። ለዚህም ቀዳሚ ምሳሌ ሆኖ የሚጠቀሰው ስሙ ራሱ ነው። ስሙን በዐረብኛ ሲጽፍ "ጁብራን ኸሊል ጁብራን" ነው የሚለው። ትክክለኛ ስሙም እንደዚያ ነው። ከሀገሩ ወጥቶ የአሜሪካ ነዋሪ ከሆነ በኋላ ግን አሜሪካዊያን በስሙ ተወዛገቡ። እርሱም ይህንን ተገንዝቦ ኖሮ የመጀመሪያውን "ጁብራን" ከስሙ ውስጥ አወጣው። አሜሪካዊያን ሊያነቡት የሚቸገሩትን የ"ኸ" ድምጽ "Kah" በማለት ጻፈው። ከዚያም የአባቱንና የአያቱን ስም አከታትሎ በመጻፍ Kahlil Gibran በሚል ስም ራሱን አስተዋወቀ (የአያቱን ስም ሲጽፍ "ጁ"ን ወደ "ጂ" ቀይሮታል)።

እንግዲህ የሀገራችን ሰዎች ስራዎቹን የሚያውቁት በአብዛኛው በእንግሊዝኛ ስለሆነ ነው የእንግሊዝኛውን ዓለም ተከትለው "ካህሊል ጂብራን" የሚሉት። የዐረብኛ መጽሐፎቹ ግን እስከ መጨረሻው ድረስ "ጁብራን ኸሊል ጁብራን" በሚለው ስም ነበር የሚወጡት። ይህንን ያየ ሰው በእንግሊዝኛ መጻሕፍቱ ላይ ከሚጻፈው ስሙ ጋር አለመመሳሉ ገርሞት ሊወዛገብ ይችላል።
-----
ኸሊል ጂብራን በሌሎች ብዙ ነገሮችም ያወዛግባል። ለምሳሌ ያህል ሁለቱን ብቻ እንጠቅሳለን።

=> ጂብራን ሲጽፍ ከዐረቡ ዓለም የተገኙ በርካታ ዓሊሞችና ፈቂሆችን ይጠቅሳል። በተለይም ኢማም አል-ገዛሊን በጣም ይወደዋል። ጂብራን ቅዱስ ቁርኣንን እና ሐዲስን በደንብ ያውቃል። በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች በእምነቱ ላይ ይወዛገባሉ። ቢሆንም ጂብራን ሙስሊም ሳይሆን በሊባኖስ እና በሶሪያ ከሚኖሩት ማሮናይት የካቶሊክ ክርስቲያኖች ነው የተወለደው።

=> ጂብራን የተወለደበት መንደር በአሁኗ ሊባኖስ ውስጥ ነው የሚገኘው። ሆኖም አንዳንዶች ሶሪያዊ ይሉታል። ታዲያ እርሱም ተቃውሞአቸው አያውቅም። ሊባኖስ ለብዙ ክፍለ ዘመናት የሶሪያ አካል ነበረችና።
-----
ውዝግቦቹን ስታልፏቸው ጂብራንን የልብ አድርስ ሆኖ ነው የምታገኙት። ግጥሞቹም ሆኑ በስድ ንባብ የጻፋቸው መጽሐፎቹ ልብን ከማረስረስ አልፈው እውነትን የመናገር ሃይላቸው ከፍተኛ ነው። ለዚህም ነው ላለፉት መቶ ሃያ ዓመታት በፍቅር እየተነበበ ያለው።

ጂብራን ሶስት ዓይነት አጻጻፍ የሚከተል የልብ-ምት (mystic) ገጣሚ እና ጸሐፊ ነው። ሲፈልግ መጽሐፎቹን በግጥም ይጀምርና በግጥም ይጨርሳል። ሲያሻው ግጥምን እንደ አዝማች እያቀነቀነ በየጣልቃው በጣም የሚነሸጡ እና ቀልብን የሚነኩ ታሪኮችን እንደማብራሪያ ያመጣቸዋል። ሲፈልግ ደግሞ በስድ-ንባብ ይጀምርና በስድ ንባብ ይጨርሳል።
------
ኸሊል ጂብራን በኔ ብዕር ሊገለጽ የሚከብድ ግዙፍ ስም፣ ግዙፍ ገጣሚ እና ግዙፍ ጸሐፊ ነው። እኔም ስለእርሱ የሚሰማኝን ከመጫር በቀር ጂብራንን በተሟላ ሁኔታ እገልጸዋለሁ የሚል እሳቤ የለኝም። ምክንያቱም ጂብራን ማለት በመቶ ዓመት አንድ ጊዜ ውልብ ብለው ከሚጠፉት አብሪ ከዋክብት መካከል አንዱ ነው።

በጂብራን ድርሰቶች ውስጥ ገንነው የሚታዩት አራት ህልዮቶች ናቸው። እነርሱም ፍቅር፣ ትህትና፣ ይቅርታ እና ቅንነት ናቸው። የእርሱ ርእዮት በአንድ ላይ ተጠቃልሎ እና ተከሽኖ ሲቀርብ "የሰው ልጆች ሁሉ ቅን ሊሆኑ እና ፍቅርን ሊሰብኩ ነው የተፈጠሩት። እንደዚያ መሆንም ይችላሉ" የሚል ይሆናል። ለዚህም ነበር በፍቅር ሰባኪነቱ የሚታወቀው ነቢዩላህ ዒሳ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በጂብራን መጻሕፍት ውስጥ በጣም ገንኖ የሚታየው።
---------
ኸሊል ጂብራን ከጻፋቸው መጻሕፍት መካከል እጅግ ምርጥ የተባሉት ሁለት ናቸው። አንደኛው በዐረብኛ የተጻፈ ሲሆን ሌላኛው በእንግሊዝኛ የተደረሰ ነው። በዐረብኛ ከተጻፉት መጽሐፎቹ መካከል በጣም ተወዳጅና ድንቅ ተብሎ የተጨበጨበለት "አል-አጅኒሃ ሙክተሲራ" ይባላል። ወደ አማርኛ ሲተረጎም "የተሰበሩ ክንፎች" እንደማለት ነው። ይህ መጽሐፍ በ20 ቋንቋዎች ተተርጉሞአል። በየጊዜው Bestseller እየሆነ በኒውዮርክ ታይምስ እና በሌሎች የአሜሪካ ጋዜጦች ይጠቀሳል። ኢርቱዕ አምላክ የተባሉ ሰው በ2001 ወደ አማርኛ ተርጉመውት እንደነበረ አስታውሳለሁ።
----
ጂብራን በእንግሊዝኛ ከጻፋቸው መጻሕፍት መካከል ደግሞ ምርጥ የተባለው "The Prophet" ይሰኛል። ከጅብራን ስራዎች መካከል ደጋግሜ ያነበብኩት እርሱን ነው። በዓለም ዙሪያ በጣም የሚታወቀው የጂብራን ስራም ይህ "The Prophet" ነው። መጽሐፉ ከ100 በሚበልጡ ቋንቋዎች የተተረጎመ ሲሆን ብዙ ከተሸጡት (Bestsellers) መካከልም ነው። እስቲ በጥቂቱ እንተዋወቀው።

"The Prophet" የተጻፈው በአብዛኛው በግጥም ነው። የመጽሐፉ መግቢያ እና መውጫ ግን በስድ-ንባብ ነው የተጻፈው። ይህ መጽሐፍ የአንድን ልብ-ወለዳዊ ነቢይ ትምህርታዊ ተልዕኮ ነው የሚተርከው።

ነቢዩ "አል-ሙስጠፋ" ይባላል። "አል-ሙስጠፋ" ኦርፋሌስ በምትባል አንዲት የወደብ ከተማ ለ12 ዓመት ይኖራል። ከዚያም ወደ ትውልድ መንደሩ ለመመለስ ፈልጎ መርከብ ይጠብቃል። መርከቧን በመጠበቅ ላይ ሳለ የከተማዋ ሰዎች አጠገቡ መጥተው ስለተለያዩ ነገሮች ይጠይቁታል። እርሱም ጥያቄዎቻቸውን መመለስ ይጀምራል። እነርሱም የሚሰጣቸውን መልስ በአንክሮ እና በገረሜታ ይሰሙ ጀመር።

ሰዎቹ ስለፍቅር፣ ስለጋብቻ፣ ስለንግድ፣ ስለእርሻ፣ ስለህግ፣ ስለጉዞ፣ ስለመጽሐፍ....ወዘተ ተራ በተራ ይጠይቁታል። አል-ሙስጠፋም እጅግ በተዋበ እንግሊዝኛ እና ልዩ ጥበባዊ ልቅና በሚታይበት ትህትና የተጠየቀውን ሁሉ እየመለሰ ያስተምራቸዋል። አል-ሙስጠፋ እንዲያ ሲያደርግ የአድማጮቹ ልቦና እና አዕምሮ ቀስ በቀስ እየተቀየረ ይሄዳል። በኋላም ሁላቸውም የትህትና እና የፍቅር ተገዥዎች ይሆናሉ።
-----
በወደቡ ወደ አል-ሙስጠፋ መጥተው ጥያቄ ከጠየቁት መካከል አንዷ አል-ሚጥራ ትባላለች። አል-ሚጥራ ነቢዩ ስለፍቅር እንዲነግራት ነበር የጠየችው። ጂብራን የአል-ሚጥራን ጥያቄ እና የአል-ሙስጠፋን መልስ እንዲህ ነበር የጻፈው።

Then said Almitra, "Speak to us of Love."

And he raised his head and looked upon the people, and there fell a stillness upon them.

And with a great voice he said:

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ኮፒ ብቻ እጃችን ላይ አለ !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ከከበደ_ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ ፩

እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ'ነው።

*************
ከማዘዝ በፊት አስቀድሞ መታዘዝን ማወቅ ያስፈልጋል ።

**************

ጥሩም ነገር ቢሆን ከመጠን ካለፈ ሁልጊዜምመጥፎ ነው ።

*************

ትዕቢትና ውርዶት አካልና ጥላ ናቸው ሳይለያዩ ሁልጊዜ
ቀዳሚና ተከታይ ሆነው ተያይዘው ሊሄዱ ይኖራሉ።

***************

እህልና ውሃ ዕውነትን እንደሚመግቡት ሁሉ መጻሕፍትን ማንበብም አንደዚሁ መንፈስን ይመግበዋል።

****************

ከበላይህ ያሉትን ሰዎች እያየህ በልብህ ቅናት አይደርብህ።
ይልቅስ ካንተ በታች ያሉትን ችግረኞች እየተመለከትሀ ዕድ
ልህ ከነሱ የተሻለ በመሆኑ ፈጣሪህን አመስግነው ።

******************

ማንም ሰው ቢሆን መከራ ወድቆበት ባየሀ ጊዜ አትፍረድበት ወይም እትጨክንበት በእሱ ላይ የደረሰ መከራ ምናልባት ባንተም ላይ ወደፊት ሳይደርስብህ አይቀርም ይሆናል ።

***********

ምንም እንኳን የሚያስመሰግንህ ትልቅ ሥራ ብትሠራ
ምን ጊዜም ቢሆን አትመካበት ትምክሕት ማንኛውንም ዋጋ
ቢሆን ያቀለዋል ትሕትና ግን ከሁሉ ሞያ የበለጠ ዋጋ ያለው
ባሕርይ ነው ።

***************

ሰው በሕይወቱ ሲኖር የሚያገኘውን መልካም ነገር ሁሉ
የሚቀበለው ከተወለደባት እገር ስለ ሆነ አስፈላጊ ምክንያት
በመጣ ጊዜ ያለው መልካም ነገር ሁሉ ሕይወቱን እንኳን
ሳይቀር ሳያመነታ ላገሩ ሲል ሊሠዋ ይገባዋል ።

~~~~~~~ ~~~~~~~

ደስ ደስ የሚሉ ጠቃሚ ሀሳቦች
በታሪክና ምሳሌ መፅሐፍ

የቴሌግራም ቻናላችን @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን @azopbook

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
📚📚📚📚📚📚📚📚

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የለልጆችዎ የሚኾን የስፔስ ኢንሳይክሎፒዲያ እጃችን ላይ አለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል :- መጽሐፍ የሚያነብ ሰው አስቀድሞ የመጽሐፉን ባለቤት ይናገርና ከዚያም መጻፉን ያንብ ይላል፡፡ ስለኾነም  እኛም የዚህን መጽሐፍ ማንነት በአጭሩ እናስተዋውቃቹ።  ይህንን መጽሐፈ ገነት ዘውእቱ ዜና አበው  የተባለውን መጽሐፍ የጻፈው አባት የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሶፍሮንዮስ ሲኾኑ በሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አጽፈው አስቀመጡት።  ስሙንም መጽሐፈ ገነት ውእቱ ዜና አበው አሉት።

በገነት ውስጥ የተለያየ ፍሬ እንዳለ በገዳምም ውስጥ የተለያየ ፈተናና የተለያየ ተጋድሎ አለ እንደማለት ሲኾን ስለዚህም መጽሐፈ ገነት የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል፡፡

መጽሐፉ የአባቶችንና የእናቶችን መነኰሳት ተጋድሎና ትምህርታቸውን የአስቸጋሪውን ዓለም _ ከዲያብሎስና ከሠራዊቱ ጋር እየተዋጉ እንዴት እንዳለፉ፣ የሕይወታቸውን ተጋድሎ የሚያስረዳ  መጽሐፍ ነው፡፡


በመኾኑም መጽሐፉን ወደ አማርኛ ቋንቋ የተረጎሙት መምህር ክፍለ ማሪያም ደስ አለው ሲኾኑ እስካኹን ተተርጉመው ለህትመት ከበቁላቸው 17. መጽሐፍት መካከል አንዱ ይኽ መጽሐፈ ገነት ዘውዕቱ ዜና አበው አንዱ ነው።

ለአብነት ያኽል
፩ ዜና ሥላሴ
፪ ገድለ አብሳዲ
፫ ገድለ አቡነ ሙሴ
፬ ገድለ አቡነ ፊሊጶስ
፭ ገድለ አቡነ ዩሐንስ
፮ ገድለ ክርስቶስ ሰመራ
፯ ገድለ መቃሪዮስ
፰  ራየ ባሮክ





ተርጉመው አስነብበውናል !!!!
ውድ የዚኽ ቻናል ቤተሰቦች የምንችለውን አንብበን አናላይስ ሰርተን የተረዳነውን በማካፈል አልያም መጽሐፉን በመለጠፍ እንድታነቡት እንጋብዛችኋለን።

መጽሐፉ ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ አለን !!!

የቴሌግራም ቻናላችን join ብታደርጉት ደስ ይለናል !!!!

/channel/azop78
/channel/azop78

ኤዞፖች ነን መልካም ንባብ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ ይገኛሉ
ዋጋው እጅግ ቅናሽ ተደርጎበታል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

class and revolution in Ethiopia

by John markakis & nega ayele

published by the red sea press


ኦሪጅናል የውጭ እትም እጃችን ላይ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የህትመት ዘመን 19 41
ኦሪጅናል በዚያው ዘመን የታተመ
ጥራቱን የጠበቀ እጅግ ንፁህ


መጽሐፈ ሰዋሰው ድግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#አፈወርቅ_ገብረ_ኢየሱስ የመጀመሪያው "አፍሪካዊ/ ትዮጵያዊ ፕሮፌሰር''

የመጀመሪው የአማርኛ ልብ ወለድ ድርሰት ‹‹ጦቢያ›› ፀሀፊ

በኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገር ተጉዘው ዘመናዊ ትምህርት ከቀሰሙ ሊቃውት አንዱ
በመጀመሪያው የመንግስትን ዲፕሎማሲያዊ ሥራ ለመሥራት በአምባሳደርነት ከተላኩት
ምሁራን አንዱ

የኢትዮጵያን ኋላ ቀር የንግድ ስርዓት ወደ ዘመናዊ የንግድ ስርዓት የቀየሩ

የውጫሌን ውል ስምምነት _ በሮማ ለተገኘውና በራስ መኮንን ለሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የተጭበረበረ የፊርማ ሰነድ በመሆኑ ሃገራቸው ኢትዮጵያን አደጋ ላይ እንደሚጥላት ለልዑኩ መሪ በመግለጥ ከጣሊያንኛው ወደ አማረኛ ሲተረጎም እንደማይስማማ ያጋለጡ

ይህ መጽሐፍ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ጋዜጦች ላይ የጻፏቸው
አጫጭር ታሪክ ቀመስ ልብ ወለዶችና መጣጥፎች ከብዙ በጥቂቱ ከተለያዩ ምንጮች ተሰባስበውበታል ...!!!

አሰናኝ ናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ

የቴሌግራም ቻናላችን  azop78
      ለንባብ መግልመስ ሁሌም እንተጋለን።
             🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዘወትር ሲራመድ ከራሱ ቀና ብሎ ነው፤ ዓይኖቹም የፈጣሪን ነበልባል ከውስጣቸው ያመነጩ ነበር። ነገር ግን ሁልጊዜ ሀዘንተኛ ነበር፤ ሀዘኑ በስቃይ ውስጥ ለሚገኙት ከሚመነጭ ርኀራኄና በብቸኝነት ለሚቆዝሙትም ወዳጃቸው ሆኖ ከመቆም የሚፈልቅ ነው::

ፈገግታው የማያውቁትን ለመረዳት በውስጣቸው የሚራቡትን በዕውቀት የሚያጠግብ ነበር፡፡ በሕፃናት ሽፋሽፍቶች ላይ እንደሚወድቁ የክዋክብት ብናኞች ፈገግታው ያንፀባርቃል፡፡በተራቡት ጉሮሮ ደግሞ
እንደሚወድቅ ጉርሻ ነበር፡:

ነገር ግን ሁልጊዜ ሀዘንተኛ ነበር፤ ሀዘኑ ግን በሌሎች ከንፈር ላይ ወድቆ ሳቅን ይፈጥራል የእሱ ፈገግታ በመጸው ወራት በጫካዎች ላይ
እንደሚጣል ወርቃማ መጋረጃ ይመሰላል ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሽለቆዎች ሰርጥ ላይ እንደወደቀ የጨረቃ ብርሃን ይሆናል። ፈገግ ሲል ከንፈሮቹ በሰርግ ግብዣ ላይ ጣፋጭ ዝማሬን የሚያሰሙ ይመስላሉ።

ይሁንና ኢየሱስ ሐዘንተኛ ነበር፤ ከክንፍ አልባ
ወዳጆቹ ከፍ ብሎ የማይበር ባለክንፋም ሐዘንተኛ።
      
   📖#ኢየሱስ_የሰው_ልጅ

   ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
            🙏🙏😂

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የስንብት ቀለማት ሁለቱንም ቅጽ አንድ ላይ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የመጽሐፍ ቅድስ አስተምህሮ መግቢያ

#ስልታዊ_ነገረ_መለኮት ቅጽ 1እና 2 እጃችን ላይ ይገኛል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ ነገር ለልጆቻችሁ፣ ለልጆቻችን
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

“ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው አትከልክሏቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነርሱ ላሉት ናትና አለ፡፡” ሉቃስ 18፥16

የብሉይ ኪዳን ለሕፃናት ተከታይ ክፍል የሆነው
'ሐዲስ ኪዳን ለሕፃናት' ፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች

ሁለተኛው ዕትም በሥርጭት ላይ ይገኛል
_

የመጽሐፉ መግቢያ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
የተወደዳችሁ አንባቢዎች፤ ይህ በእጃችሁ ያለው መጽሐፍ ከልጆቻችሁ ጋር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮችን በቀላሉ በየዕለቱ እንድታነቧቸው ሆነው የተዘጋጁት የሁለቱ ተከታታይ መጻሕፍት (ብሉይ እና ሐዲስ ኪዳን) አንዱ ክፍል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም ዕድሜዎች ለሚገኙ ለሁሉም ሰዎች መረዳትን የሚሰጥ መለኮታዊ ጥበብን ያስተላልፋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን በእምነት መንፈስ የሚያነበው ሁሉ እግዚአብሔርን ለማወቅ ይጥራል፤ እግዚአብሔር ለሁሉም የሰው ዘር ያለውን የተትረፈረፈ ፍቅርም በሕይወቱ ይለማመዳል፡፡
1. ልጆቻችሁ ጥቅሶቹን እንዲያውቋቸው፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ጥቅሶች አልተለወጡም፡፡
2. ለልጆቻችሁ፣ ይህን መጽሐፍ ዕለት ተዕለት በምትጠቀሙበት ቋንቋ አንብቡላቸው፤ ልጆቻችሁም በቀላሉ ሊከተሏችሁ ይችላሉ፡፡ ልጆቻችሁ ሲያድጉም ማብራሪያዎች ያሉበትን ይህን መጽሐፍ ራሳቸው እንዲያነቡት ፍቀዱላቸው፤ በዚህም ልጆቻችሁ በሂደት መጽሐፍ ቅዱስን ያለረዳት ማንበብ ይችላሉ፡፡
__

ስለመጽሐፉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯
ከስመ ጥሩ ካህን ቀሲስ ታድሮስ ማላቲ ላቅ ያለ ጠቀሜታ ያላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትረካዎች ባማረ ሁኔታ ተጠናቅረው በዚህ መጽሐፍ ቀርበዋል፡፡
ይህ መጽሐፍ ከሕፃናት ጀምሮ እስከወላጆች እንዲሁም በወጣቶች ሃይማኖታዊ ትምህርት ላይ አደራና ሓላፊነት እስካለበት ማንኛውም ሰው ድረስ ሐዲስ ኪዳንን እና በውስጡ የተካተቱትን እጅግ ወሳኝ ታላላቅ ክስተቶች በአስደናቂ ሁኔታ የያዘ በሁሉም እድሜዎች ለሚገኙ ሁሉ የሚጠቅም ነው፡፡
ይህ የከበረ መጽሐፍ አማርኛው ለሁሉም በሚገባ መልኩ የተዘጋጀና በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ በደስታ እንድንጓዝ የሚጋበዝ ሲሆን ለበርካታ ቀጣይ ትውልዶችም ትልቅ ዋጋ ያለው ሐብት ነው፡፡
_
ቀሲስ ታድሮስ ያዕቆብ ማላቲ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከከህን ሲሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ አንድምታ (ኮሜንታሪ) መጻሕፍትን በመጻፍ የታወቁ ሊቅ ናቸው።
__
ዘኤልያስ ወልደ ሚካኤል የታላቁ ደብር የደብረ ገነት ቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን (ጎጃም፣ ደብረ ኤልያስ) የአቋቋም መምህር የመምህር ወልደ ሚካኤል ልጅ ነው። ከቤተ ክርስቲያኒቱ የአብነት ትምህርቶች በተጨማሪ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በሥነ መለኮት (BTh) በማዕረግ ተመርቋል። ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት የመጀመሪያ ዲግሪውን ይዟል።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ በርካታ
መንፈሣዊ መጻሕፍት መካከል ከ12 በላይ የሚሆኑትን በመተርጎም ለአንባቢያን አድርሷል። አብርሃምና ይስሐቅ እና ዮሴፍና ቀሚሱ የተሰኙ የልጆች አኒሜሽን ፊልሞችን ተደራሽ አድርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ፣ እንዲሁም የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር በመሆን ሠርቷል።

በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር እየተዘጋጀ በሚገኘው የአማርኛ ማጥኛ መጽሐፍ ቅዱስ ዝግጅት ፕሮጀክት ውስጥ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በዝግጅት ሥራው ከፍተኛ ተሳትፎ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅት የሙሉ ጊዜ የመጽሐፍ የትርጉም እና የአርትዖት ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል።




ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በኢትዮጵያ 
     የካህኑ የመልከ ጼዴቅ ልጅ
ኢትኤል የግዕዝ ፊደልና ጽሕፈት በሱ ተጀመረ
  በምድያም ካህን በዮቶር ተሻሻለ

ታላቅ የጥበበ ሀረጋት መጽሐፍ እጃችን ላይ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

When love beckons to you follow him,
Though his ways are hard and steep.

And when his wings enfold you yield to him,
Though the sword hidden among his pinions may wound you.

And when he speaks to you believe in him,
Though his voice may shatter your dreams as the north wind lays waste the garden.

For even as love crowns you so shall he crucify you. Even as he is for your growth so is he for your pruning.

Even as he ascends to your height and caresses your tenderest branches that quiver in the sun,

So shall he descend to your roots and shake them in their clinging to the earth.
Like sheaves of corn he gathers you unto himself.

He threshes you to make you naked.
He sifts you to free you from your husks.
He grinds you to whiteness.

He kneads you until you are pliant;
And then he assigns you to his sacred fire, that you may become sacred bread for God's sacred feast.

All these things shall love do unto you that you may know the secrets of your heart, and in that knowledge become a fragment of Life's heart.

But if in your fear you would seek only love's peace and love's pleasure,
Then it is better for you that you cover your nakedness and pass out of love's threshing-floor,

Into the seasonless world where you shall laugh, but not all of your laughter, and weep, but not all of your tears.

Love gives naught but itself and takes naught but from itself.

Love possesses not nor would it be possessed;
For love is sufficient unto love.

When you love you should not say, "God is in my heart," but rather, I am in the heart of God.

And think not you can direct the course of love, if it finds you worthy, directs your course.

Love has no other desire but to fulfil itself.

But if you love and must needs have desires, let these be your desires:

To melt and be like a running brook that sings its melody to the night.

To know the pain of too much tenderness.
To be wounded by your own understanding of love;
And to bleed willingly and joyfully.

To wake at dawn with a winged heart and give thanks for another day of loving;
To rest at the noon hour and meditate love's ecstasy;

To return home at eventide with gratitude;
And then to sleep with a prayer for the beloved in your heart and a song of praise upon your lips.
-----
ጂብራን ግዙፍ ስብዕና ነው። ነገር ግን በጣም ትሁት ሰው ነበር። እኔ በአቅሜ እንዲህ ዘክሬዋለሁ። ወደፊት ደግሞ ከዚህ ይበልጥ ልንዘክረው እንሞክራለን። ኢንሻ አላህ!!
------

ያልተነበበውን የካህሊል አማልክትን አንብቡት !!!!!

-------

አፈንዲ ሙተቂ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#መተማመንን_አትስበረው!

መተማመን ልክ እንደ ሸክላ ሳህን ነው፡፡

💔አንድ ጊዜ ከሰበርከው በጣም በጥንቃቄና በከፍተኛ ትኩረት እንደገና አንድ ላይ ልታደርገው ትችል ይሆናል፡፡

💔💔 በድጋሚ ከሰበርከው ግን የበለጠ ወደ ብዙ ስብርባሪዎች ስለሚለወጥ እነዚያን ስብርባሪዎች ለመገጣጠም በጣም ረጅም ጊዜና ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡

💔💔💔 ለበለጠ ጊዜ እየሰበርከው ከመጣህ በመጨረሻ እንደገና ሊጠገን በማይችል አይነት ይደቅቃል፡፡

ከዚያ ብዙ ስብርባሪዎችና ብዙ ብናኝ ብቻ ይቀራል፡፡

ወዳጄ መተማመንን አትስበረው!

#በጥበብ_መኖር መጽሐፍ #5ተኛው ዕትም በገበያ ላይ
#The_#the_subtle_art_of_not_giving_a_

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

📗📙📕
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

👇
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የተወዳጁ ደራሲና ፈላስፋ እጓለ ገብረ ዩሐንስ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ መጽሐፍ የድጋሜ ህትመት ትሩፋት ደርሶናልና ይድረሳችኹ !!!!

Читать полностью…
Subscribe to a channel