ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21
ጽንዐ ተዋሕዶ የተሰኘው ይህ የበአማን ነጸረ መጽሐፍ ከካቶሊክ፣ ከቅብዓት፣ ከጸጋና ከተዋሕዶ ጋር በተያያዘ የሚነሡ ብዙ ታሪካዊ ነገሮችን ያጠራል። ከአስተምህሮ አንጻር የሚነሡ ነገሮችንም ተላውያነ ሐዋርያት (Apostolic Fathers) ከሚባሉት የሁለተኛው ክፍለ ዘመን ሊቃውንት አንሥቶ በዘመናችን እስካሉት ሊቃውንት ድረስ ሥራዎቻቸውን በማቅረብ ይመረምራል። በቅርቡ በታተሙ መጻሕፍት ውስጥ ያሉ የተቀብዐ ተኮር ጥቅሶች ትርጓሜ ላይ ያስተዋላቸውን ዋና ዋና ስሕተቶችም ነቅሶ በማውጣት ከጥንት አባቶች ጀምሮ በመጣው ኦርቶዶክሳዊ ትርጓሜ ያበጥራቸዋል። ሌሎች ጉዳዮችንም በጥንቃቄ ይመረምራል። እስካሁን በተጻፉ መጻሕፍት ላይ የያዝናቸውንም ትውፊታዊ ታሪካዊ መቼቶችን ቀዳማይ ምንጮችን በማሳየት በተገቢው መንገድ ይሞግታል። በዚህም ምክንያት ነገረ ተቀብዐን ከነታሪካዊ ዐውዱ በአግባቡ እንድንረዳው ለማገዝ ይህን የበአማን ነጸረን ጽንዐ ተዋሕዶን የሚመስል ሌላ መጽሐፍ እስካሁን አላገኘሁም።
በሥነ ጽሑፋዊ አቀራረቡም በእጂጉ አስተማሪ ነው። ታሪካዊ ጉዳዮችን የሁለቱንም ወገን ቀዳማይ ምንጮች በማቅረብ እያከራከረ፣ እየመረመረ በዲስኩር ትንተና (Discourse Analysis) በማቅረብ _ ለአንባቢ ፍሬ ነገሮችን ያስጨብጣል። የተቀብዐን ጉዳይ ሲያቀርብም ከጥንቶቹ ሊቃውንት በማሳየት ጀምሮ በቅርብ ጊዜ የወጡ መጻሕፍት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ስሕተታቸውን በአጉሊ መነጽር በማቅረብ ለእኛ ዘመን ግልብ አንባቢ ለማሳየት የሔደበት ርቅት አስደንቆኛል። ስለዚህም አቀራረቡ ራሱ በቅንነት መማር ለሚሹ ሁሉ መማሪያ እንደሚሆን እምነቴ ነው።
ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ (በሥነ ድርሳን ሁለተኛ ዲግሪ)
ኤዞፕ መፃሕፍት !!!
ወደ መክሊት ሽሽት፤ ‹‹ራስ››
(ዮናስ ታምሩ ገብሬ - አዲስ አድማስ፣ 19፣09፣15)
#መነሻ - ‹‹ራስ›› የደራሲ ፍሬ ዘር ሥራ ነው፤ በ275 ገጽ ዕድሜው በነጠላ ውጤት የተቋጨ ልብ-ወለድ ሲሆን፣ በዋና ገጸ-ባሕርይው (በራስ) ተራዳኢነት እየታገዘ ጭብጡን ተርኳል። ‹‹ራስ›› ለምርጫችንና ለመክሊታችን ቁብ የማይሰጠውን የትምህርት ሥርዐት በወጉ የሚያስቃኝ ድርሰት ነው ብዬ አምናለሁ። በድርሰቱ ውስጥ ‹‹ራስ›› የተባለ ብላቴና በአንገሽጋሹ የትምህርት ሥርዐት ምክንያት አልጋው ቀጋ ይሆንበታል፤ እክፍል ተገኝቶ ትምህርት ከሚከታተል በደዌ ተሰቅዞ የአልጋ ቁራኛ ቢሆን ይመርጣል። ታዲያ ይኼ ብላቴና ያልተጠራበት ድግስ እንደሚቀላውጥ ሰው ውርክብ ውስጥ ይዘፈቃል። ቆሞ መሄድ ሳይችል ብዙ ቁምነገር ይጠበቅበታል፤ ውጤታማ ሊሆን ባለመቻሉ ወደ አያቶቹ ቀዬ ይከተታል - ወደ ገጠር። እዚያ ዛፍ ተካይ ሆነ፤ በትምህርቱ ቢወቀስም መንደሩንና ሀገሩን ታደጋቸው። ‹‹ራስ›› ከተነባቢነት በተረፈ በርከት ያሉ ረድኤቶችን ጀባ የሚለን ድርሰት ነው የሚል እምነት አለኝ። እንሆኝ…
#ሽፋን እና ርእስ - የመጻሕፍ ሽፋኑ ሙሉ በሙሉ ዋናውን ገጸ-ባሕርይ ‹‹ራስ››ን የመግለጽ ሙከራ ነው። ሽፋኑ እንደምንመለከተው የገጸ-ባሕርይውን ሥራ/ተግባር በከፊል ይወክላል ብዬ አምናለሁ። ብሎም ስዕሉ ከድርሰት ሐሳቡ ጋር የማይቃረንና ግልጽ የሆነ መሆኑ ዕሙን ነው። በግሌ እንደ አለመስማማት የማነሳው ሐሳብ ቢኖር፣ የመጻሕፉን ርእስ የሚወክል ስዕል ተስሎ ሳለ ሥሙ አብስትራክት መሆን መቃጣቱን ነው፤ ለዚህም ‹ራ›ን መመልከት ይቻላል፤ የሰው ፊት የመሰለ ድብቅ ስሜት በርእሱ የመጀመሪያ ፊደል ላይ መካተቱ ድረታ ይመስለኛል።
#የገጸ-ባሕርይ አሳሳል - የሀገሬ ሰው ‹‹ሥምን መልአክ ያወጣል›› የሚላት ብሒል አለችው። በድኅረ-ዘመናዊ ሥነ-ጽሑፍ ሥም ግለሰብን፣ ቦታን፣ ድርጊትን… ወዘተ. ይወክላል። የድርሰት ጭብጥና የገጸ-ባሕርይ አሳሳል የጠለቀ ቁርኝት አላቸው። በድርሰት ለተቀረጸ ገጸ-ባሕርይ ሥራውንና ሥሙን የሚሸት የሥራ ድርሻ መስጠት የተለመደ ነው። የሥራ ድርሻን መሠረት አድርገን የምንሰይመው ሥም ተውላጠ-ሥም በመባል ይጠራል። ድርሰቱ ከቀጥተኛ ሥም ይልቅ ተውላጠ-ሥምን መሠረት በማድረግ ገጸ-ባሕርያትን ሠይሟል፤ ገጸ-ባሕሪያቱም በልካቸው የተሰፋላቸውን ሥራ ሲከውኑ እናስተውላለን። ለአብነት ‹‹ራስ›› የተባለ ማቲ በንጡልነት የራሱን የስኬት ዓለም ሲኖር አስተውለናል።
#ሥነ-ውበት/Aesthetic - በድርሰቱ የተካተቱ ውበታም ቃለት፣ ሐረጋትና ገለጻዎችን እንጥቀስ፡- ‹‹ያስኳላ ጠንቋይ›› (ገጽ 9)፣ ‹‹የንብ እናት ሆንኩ›› (ገጽ 29)፤ ‹‹ላስራ አምስት ደቂቃ እረፍት ሁለት ሰዓት ሙሉ መጓጓት የየለት ተግባሬ ነው›› (ገጽ 1)፣ ‹‹ዓይኑ ተሸነቆረ›› ገጽ 32)፤ ‹‹የቤት ሥራ ሲል ላዬ ላይ ቤት የተሰራብኝ ያህል ትንፋሽ ያጥረኛል›› (ገጽ 2)፣ ‹‹በውርርድ ተሸንፌ ያበሳጨሁት እኔ ሌላው ብስጭቱ ነኝ›› (ገጽ 40) እና ሌሎች በውበታቸው ልብን የሚያሞቁ ትረካዎችን መጥቀስ ይቻላል። በተጠቀሱ መዘርዝሮች አጽንኦት መስጠት ያሻው ጉዳይ እንዳለ መመልከት እንችላለን። የዓረፍተ-ነገር አጀማመር የሥነ-ውበት አንድ አካል ነው፤ የመጀመሪያ ዓረፍተ-ነገር ሰዓቢ፣ ግልጽ፣ እንዲሁም የተነባቢነትንና የአንባቢን ትኩረት የሚስብ መሆን እንዳለበት ይታመናል። ገጽ 1፡- ‹‹ትምህርት አልወድም።›› ብሎ ይጀምራል። ይኼ የሚያሳየው ደራሲው የመጻሕፉን ጽንሰ-ሐሳብ በመጀመሪያዋ ዓረፍተ-ነገር ለመወከል ሲል በተደጋጋሚ እንደከለሰ/እንደሠረዘ ነው።
#ቁስ አካላዊ መሣሪያዎች/Mechanical Devices - ቁስ አካላዊ መሣሪያዎች በኢታሊክስ የተጻፉ ዓረፍተ-ነገሮች፣ የተሠመረባቸው ሐረጋት፣ በቃለ-አጋኖ የሚያልቁ ገለጻዎችንና ሌላንም ያካትታል። የዚህ ቴክኒክ ጠቀሜታ በትረካ ወቅት የሚስተዋሉ የአቅጣጫ፣ የሂደትና የጊዜ መለዋወጦች እና የገጸ-ባሕርይውን ትኩረትና አጽንኦት መጠቆም ነው፤ በታሪኩ ውስጥ ምን እየሆነ እንደሆነ አመላካች ናቸው። ለማሳያ፡- ‹‹ኧረ በታባ!››፤ ‹‹እንደ ፈራሁት!›› (ገጽ 85)፤ ‹‹ዝም!›› (ገጽ 85)፤ ‹‹በታባ!›› (ገጽ 191)፣ ‹‹በሞትኩት!›› (ገጽ 177)፣ ‹‹በታባ ሞት!››፣ ኧረ ምንድነው በታባ!›› ገጽ 265) እና በርካታ በኢታሊክስ የሰፈሩ ዓረፍተ-ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል።
#የቃላት መረጣ እና ምጣኔ - በድኅረ-ዘመናዊ ሥነ-ጽሑፍ ደራሲ መረን ነክቶ የሥነ-ጽሑፍ ሐሳቡን ማካለብ የለበትም፤ በቋንቋ አጠቃቀም ረገድ የድርሰቱ ዋና ገጸ-ባሕርይ ልጅ ስለሆነ ቀላል አማርኛን በመጠቀም በእያንዳንዱ ክስተት መሀል ብቅ እያለ ግብረ-መልስን ሰጥቷል የሚል እምነት አለኝ። ብሎም፣ ደራሲው ለዋናው ገጸ-ባሕርይ ግዝፈትን ለመስጠት በማለም ከአድራጊ ወደ ተደራጊ (active voice) የመተረክ ቴክኒክን ተጠቅሟል።
ደራሲ በቋንቋ አጠቃቀሙ እና በብዕር አጣጣሉ ቁጥብ መሆን እንዳለበት ይነገራል። በንባብ ወቅት የሚከተል መታከትን፣ የሐሳብ መሸራረፍን፣ የፍሰት መወለካከፍን ለመቅረፍ ሲባል የድርሰት ሐሳብ በተንዠረገገ ቋንቋ ባይገለጽ መልካም እንደሆነ ስምምነት አለ። ‹‹ራስ›› በተመጠኑ ቃላቶች፣ በውስን ሐረጋት እና በአጫጭር ዓረፍተ-ነገሮች የመተረክ አባዜ ይታይበታል። ምሳሌ እንጥቀስ፡- ‹‹በገላጣ ስፍራ እየተራመድኩ እግሬ ይማታብኛል፣ ንፋስ ያደናቅፈኛል፣ የማውቀው መልሱ ይጠፋኛል፣ ስሜ ራሱ ይዘነጋኛል›› (ገጽ 11)፣ ‹‹ሰርቶ ማሳየት አይቸግረው፣ ለማስረዳት ቃል አያጥረው›› (ገጽ 139)፣ ‹‹በምንም አትደሰትም፣ ማንንም አትቀየምም፣ በምንም አትናደድም›› (ገጽ 158)፣ ‹‹ከውስጥ ስጠብቃት ከውጭ ተከሰተች። አብርታለች! ደሞ ደብተር ይዛለች›› (ገጽ 219)። ከላይ በምሳሌ የጠቀስኳቸውና ሌሎች ቃላት፣ ሐረጋትና ዓረፍተ-ነገሮች ቁልቁል ቢደረደሩ ግጥማዊ ለዛ እንደሚኖራቸው አልጠራጠርም።
#የአፈ-ታሪክ እና የምሳሌያዊ አነጋገር ፈጠራ - ደራሲ በትረካ ዐውድ ውስጥ፣ ወይም በሚቀርጸው ገጸ-ባሕርይ አስገዳጅነት ያልነበሩና አዳዲስ ተረቶችን፣ ምሳሌዎችን፣ አፈ-ታሪክን የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ‹‹ራስ›› በርካታ አፈ-ታሪኮች፣ ተረትና ምሳሌዎች፣ ሥነ-ቃል እና ምሳሌያዊ አነጋገሮች የተፈጠሩበት ልብ-ወለድ ነው። ነባሩን በአዲስ በመተካት (deconstruction) ደራሲ ፍሬ ዘር በትረካ ዐውዶቹ እንዲሁም በገጸ-ባሕርይው ጠባይ ምክንያት የተለያዩ ሥነ-ቃሎችን፣ ተረቶችንና አፈ-ታሪክን ፈጥሯል፤ ማሳያ እንጥቀስ፡-
‹‹ባንድ ድንጋይ ሁለት ጊዜ ተፈነከትኩ›› (ገጽ 4)፣ ‹‹ከተማ - ከሌሎች ተፋፍጎ ማደር›› (204)፣ ‹‹ወማ - ወንድማለም›› (ገጽ 34)፤ እንዲሁም በገጽ 21፣ 35፣ 39፣ 43፣ 53፣ 127፣ 252 (ሥነ-ቃል)… ወዘተ. የተካተቱ ሐሳቦችን መጥቀስ ይቻላል። ከላይ የጠቀስኳቸው ማሳያዎች የዋናውን ገጸ-ባሕርይ መገለጫዎች የሚወክሉ ናቸው የሚል እምነት አለኝ።
#ዘይቤአዊነት - ፍሬ ዘር ድንቅ የሆነ ተምሳሌት ይቀምማል። በSimulation/ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ ሁለት ሐሳቦችን በማገናኘት ጉዳዩ ትኩረት እንዲስብ ያደርጋል። ዘይቤዎቹ በአብዛኛው አነጻጻሪ ሲሆኑ ዋናው ገጸ-ባሕርይ ቋንቋን በመጠቀም ፍትሐዊነትን፣ እውነታን፣ የሐቅ መዛባትን፣ የነገሮች አለመገጣጠምን፣ ግነትን… ይመረምራል። ደግሞ ዘይቤዎቹ ሙድ ዓይነት ትረካ መምሰላቸው ነው።
#ከከበደ_ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ ፩
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ'ነው።
*************
ከማዘዝ በፊት አስቀድሞ መታዘዝን ማወቅ ያስፈልጋል ።
**************
ጥሩም ነገር ቢሆን ከመጠን ካለፈ ሁልጊዜምመጥፎ ነው ።
*************
ትዕቢትና ውርዶት አካልና ጥላ ናቸው ሳይለያዩ ሁልጊዜ
ቀዳሚና ተከታይ ሆነው ተያይዘው ሊሄዱ ይኖራሉ።
***************
እህልና ውሃ ዕውነትን እንደሚመግቡት ሁሉ መጻሕፍትን ማንበብም አንደዚሁ መንፈስን ይመግበዋል።
****************
ከበላይህ ያሉትን ሰዎች እያየህ በልብህ ቅናት አይደርብህ።
ይልቅስ ካንተ በታች ያሉትን ችግረኞች እየተመለከትሀ ዕድ
ልህ ከነሱ የተሻለ በመሆኑ ፈጣሪህን አመስግነው ።
******************
ማንም ሰው ቢሆን መከራ ወድቆበት ባየሀ ጊዜ አትፍረድበት ወይም እትጨክንበት በእሱ ላይ የደረሰ መከራ ምናልባት ባንተም ላይ ወደፊት ሳይደርስብህ አይቀርም ይሆናል ።
***********
ምንም እንኳን የሚያስመሰግንህ ትልቅ ሥራ ብትሠራ
ምን ጊዜም ቢሆን አትመካበት ትምክሕት ማንኛውንም ዋጋ
ቢሆን ያቀለዋል ትሕትና ግን ከሁሉ ሞያ የበለጠ ዋጋ ያለው
ባሕርይ ነው ።
***************
ሰው በሕይወቱ ሲኖር የሚያገኘውን መልካም ነገር ሁሉ
የሚቀበለው ከተወለደባት እገር ስለ ሆነ አስፈላጊ ምክንያት
በመጣ ጊዜ ያለው መልካም ነገር ሁሉ ሕይወቱን እንኳን
ሳይቀር ሳያመነታ ላገሩ ሲል ሊሠዋ ይገባዋል ።
~~~~~~~ ~~~~~~~
ደስ ደስ የሚሉ ጠቃሚ ሀሳቦች
በታሪክና ምሳሌ መፅሐፍ
የቴሌግራም ቻናላችን @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን @azopbook
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
📚📚📚📚📚📚📚📚
ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል :- መጽሐፍ የሚያነብ ሰው አስቀድሞ የመጽሐፉን ባለቤት ይናገርና ከዚያም መጻፉን ያንብ ይላል፡፡ ስለኾነም እኛም የዚህን መጽሐፍ ማንነት በአጭሩ እናስተዋውቃቹ። ይህንን መጽሐፈ ገነት ዘውእቱ ዜና አበው የተባለውን መጽሐፍ የጻፈው አባት የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሶፍሮንዮስ ሲኾኑ በሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አጽፈው አስቀመጡት። ስሙንም መጽሐፈ ገነት ውእቱ ዜና አበው አሉት።
በገነት ውስጥ የተለያየ ፍሬ እንዳለ በገዳምም ውስጥ የተለያየ ፈተናና የተለያየ ተጋድሎ አለ እንደማለት ሲኾን ስለዚህም መጽሐፈ ገነት የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል፡፡
መጽሐፉ የአባቶችንና የእናቶችን መነኰሳት ተጋድሎና ትምህርታቸውን የአስቸጋሪውን ዓለም _ ከዲያብሎስና ከሠራዊቱ ጋር እየተዋጉ እንዴት እንዳለፉ፣ የሕይወታቸውን ተጋድሎ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው፡፡
በመኾኑም መጽሐፉን ወደ አማርኛ ቋንቋ የተረጎሙት መምህር ክፍለ ማሪያም ደስ አለው ሲኾኑ እስካኹን ተተርጉመው ለህትመት ከበቁላቸው 17. መጽሐፍት መካከል አንዱ ይኽ መጽሐፈ ገነት ዘውዕቱ ዜና አበው አንዱ ነው።
ለአብነት ያኽል
፩ ዜና ሥላሴ
፪ ገድለ አብሳዲ
፫ ገድለ አቡነ ሙሴ
፬ ገድለ አቡነ ፊሊጶስ
፭ ገድለ አቡነ ዩሐንስ
፮ ገድለ ክርስቶስ ሰመራ
፯ ገድለ መቃሪዮስ
፰ ራየ ባሮክ
ወ
ዘ
ተ
ተርጉመው አስነብበውናል !!!!
ውድ የዚኽ ቻናል ቤተሰቦች የምንችለውን አንብበን አናላይስ ሰርተን የተረዳነውን በማካፈል አልያም መጽሐፉን በመለጠፍ እንድታነቡት እንጋብዛችኋለን።
መጽሐፉ ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ አለን !!!
የቴሌግራም ቻናላችን join ብታደርጉት ደስ ይለናል !!!!
/channel/azop78
/channel/azop78
ኤዞፖች ነን መልካም ንባብ
class and revolution in Ethiopia
by John markakis & nega ayele
published by the red sea press
ኦሪጅናል የውጭ እትም እጃችን ላይ !!!
የህትመት ዘመን 19 41
ኦሪጅናል በዚያው ዘመን የታተመ
ጥራቱን የጠበቀ እጅግ ንፁህ
መጽሐፈ ሰዋሰው ድግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ !!!
#አፈወርቅ_ገብረ_ኢየሱስ የመጀመሪያው "አፍሪካዊ/ ትዮጵያዊ ፕሮፌሰር''
የመጀመሪው የአማርኛ ልብ ወለድ ድርሰት ‹‹ጦቢያ›› ፀሀፊ
በኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገር ተጉዘው ዘመናዊ ትምህርት ከቀሰሙ ሊቃውት አንዱ
በመጀመሪያው የመንግስትን ዲፕሎማሲያዊ ሥራ ለመሥራት በአምባሳደርነት ከተላኩት
ምሁራን አንዱ
የኢትዮጵያን ኋላ ቀር የንግድ ስርዓት ወደ ዘመናዊ የንግድ ስርዓት የቀየሩ
የውጫሌን ውል ስምምነት _ በሮማ ለተገኘውና በራስ መኮንን ለሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የተጭበረበረ የፊርማ ሰነድ በመሆኑ ሃገራቸው ኢትዮጵያን አደጋ ላይ እንደሚጥላት ለልዑኩ መሪ በመግለጥ ከጣሊያንኛው ወደ አማረኛ ሲተረጎም እንደማይስማማ ያጋለጡ
ይህ መጽሐፍ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ጋዜጦች ላይ የጻፏቸው
አጫጭር ታሪክ ቀመስ ልብ ወለዶችና መጣጥፎች ከብዙ በጥቂቱ ከተለያዩ ምንጮች ተሰባስበውበታል ...!!!
አሰናኝ ናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ
የቴሌግራም ቻናላችን azop78
ለንባብ መግልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏
ዘወትር ሲራመድ ከራሱ ቀና ብሎ ነው፤ ዓይኖቹም የፈጣሪን ነበልባል ከውስጣቸው ያመነጩ ነበር። ነገር ግን ሁልጊዜ ሀዘንተኛ ነበር፤ ሀዘኑ በስቃይ ውስጥ ለሚገኙት ከሚመነጭ ርኀራኄና በብቸኝነት ለሚቆዝሙትም ወዳጃቸው ሆኖ ከመቆም የሚፈልቅ ነው::
ፈገግታው የማያውቁትን ለመረዳት በውስጣቸው የሚራቡትን በዕውቀት የሚያጠግብ ነበር፡፡ በሕፃናት ሽፋሽፍቶች ላይ እንደሚወድቁ የክዋክብት ብናኞች ፈገግታው ያንፀባርቃል፡፡በተራቡት ጉሮሮ ደግሞ
እንደሚወድቅ ጉርሻ ነበር፡:
ነገር ግን ሁልጊዜ ሀዘንተኛ ነበር፤ ሀዘኑ ግን በሌሎች ከንፈር ላይ ወድቆ ሳቅን ይፈጥራል የእሱ ፈገግታ በመጸው ወራት በጫካዎች ላይ
እንደሚጣል ወርቃማ መጋረጃ ይመሰላል ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሽለቆዎች ሰርጥ ላይ እንደወደቀ የጨረቃ ብርሃን ይሆናል። ፈገግ ሲል ከንፈሮቹ በሰርግ ግብዣ ላይ ጣፋጭ ዝማሬን የሚያሰሙ ይመስላሉ።
ይሁንና ኢየሱስ ሐዘንተኛ ነበር፤ ከክንፍ አልባ
ወዳጆቹ ከፍ ብሎ የማይበር ባለክንፋም ሐዘንተኛ።
📖#ኢየሱስ_የሰው_ልጅ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏😂
የመጽሐፍ ቅድስ አስተምህሮ መግቢያ
#ስልታዊ_ነገረ_መለኮት ቅጽ 1እና 2 እጃችን ላይ ይገኛል።
ርቱዓነ ሃይማኖት አበዉ ሊቃውንተ ቤተከርስቲያን የሚያምኑትን ያውቁታል የሚያውቁትን ይኖሩታል የኖሩትን ጽፈው ደጉሰው በትውፊት ለትውልድ ያስላልፉታል
በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ከምናደርጋቸው መጻሕፍት መካከል ደግሞ አንዱ መድበላተ አሚን ወምግባር ተሰባስበው የተካተቱበት የአበው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ጽንዐ ሃይማኖት የተንጸበረቀበት መጽሐፈ ሐዊ ነ ው ::
ሥለዚህ በእንዲህ አይነት ትውፊት አበው በደም ጸንተው በቀለም በርትተው ባቆዩልን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለን ውሉደ ጥምቀት ደቂቀ ሊቃውንት ክርስቲያኖች ደግሞ በዚህ መንገድ ተተርንሞ የቀረበው መጽሐፍ ተደራሽ መሆናችን በአምላክ ቸርነት በአባቶቻችን ትጋት በቆየችው ሃይማኖት ለመጽናት አይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡
ይህን ቆየት ያለ መጽሐፍ እጅግ በብዙ ድካም ተርጉመው የአቀረቡልን የአቋቋም እንዲሁም የቅኔ መምህር ብሎም የነገረ መለኮት ምሩቅ ሊቀ ጠበብት መሠረት ምሕረቱም ኩላዊት ኦርቶዶካሳዊት ቤተከርስቲያን በትውፊት እና በሊቃውንት ትግሐ ሃይማኖት የመጽናቷ አንዱ ማሳያ ናቸው:: ከቡር መምህራችን አምላከ አበው ሊቃውንት በጽንአ አበው ያቆይልን !!!
መጋቤ ሐዲስ ያዕቆብ አስፋው ለመጽሐፈ ሀዊ የሰጡት አስተያየት ነው። መጽሐፉ ገበያ ላይ የጠፋ ቢኾንም ትንሽ ኮፒወች እጃችን ላይ ይገኛል።
ኤዞፕ መጽሐፍት !!!
አዳዲስና ጥንታዊ መጽሐፍትን ለማግኘት
ቴሌግራማችን ጆይን አድርጉ
/channel/azop78
ምሳሌ፡- ‹‹እንዲያውም ጎበዝና ሰነፍ ተማሪዎችን የሚያመሳስለን አንድ ነገር ሁለታችንም ትምህርት አለመውደዳችን እንደሆነ ደርሼበታለሁ›› (ገጽ 1)፤ ‹‹እሱ ሙስሊም አይደለም። ግን የነቢዩ ሞሐመድ ልደት ከከድር ይልቅ ያሳስበዋል›› (ገጽ 2)፤ ‹‹ኮሶ በመድኀኒት ይሽራል። አውግቸው ግን ማርከሻ የለውም›› (ገጽ 12)፤ ‹‹የመምህር አውግቸውን ፊት ከማይ የሚመጣው እንቁጣጣሽ ልብስ ሳይገዛልኝ ቢቀር ይሻለኛል›› (ገጽ 12)፤ ‹‹ራሱ ክላሽ ታጥቆ ሲያበቃ ግን እናባዬን ሊቀማ መሞከሩ ጅል መሰለኝ›› (ገጽ 37)፣ ‹‹ጎሊያድን ያለወንጭፍ የምገጥምበት ሰዓት አሁን መጣ›› (ገጽ 70)፣ ‹‹አምስተኛ ክፍል ት/ቶቹ በዙ። እኔም አበሳዬ በዛ›› (ገጽ 161)፣ ‹‹አባዬ ሲያወራ ያዲሳባው ቤተመንግስት ሦስት አጥር ነው ያለው ይላል። የእኔ ሦስት አጥር እህቴ ናት›› (ገጽ 169) እና ሌሎችም።
#ኑረታዊነት/Existentialism - ይኼ ነጥብ በትረካ ውስጥ ቦግ-ሕልም የሚል አንድ ቴክኒክ ነው፤ ኤግዚስቴንዣሊስም የኑረታዊነት ወ የፍጥሐዊነት መብሰክስክ ነው፤ Existentialists explore questions related to the meaning, purpose, and value of human existence. Common concepts in existentialist thought include existential crisis, dread, and anxiety in the face of an absurd world, as well as authenticity, courage, and virtue…እንዲል ደራሲው በትረካ ዐውድ እና በገጸ-ባሕርይ ሥሜት እየተመራ የተለያዩ ኑረታዊ፣ ፍትሐዊ፣ ፍልስፍናዊ ጥያቄዎችን ያነሳል። ለምሳሌ ገጽ 73፣ 81፣ 138፣ 140፣ 142፣ 144፣ 145፣ 201፣ 250-251 የተነሱ ሐሳቦችን መመልከት እንችላለን።
#ምልክት/Symbolism - ምልክት የድርሰት ማኅበረሰብን ባሕል፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ወግ ይወክላል። እውነት የሚመነጨው ከምልክትና ከማኅበረሰብ ፎክሎር እንደሆነ ይታመናል። አብነት እንጥቀስ፡- የዛፍና የደብር፣ የእረኛና የሥም ቁርኝት፤ የገጠሩን ውበት፣ እንዲሁም የተፈጥሮአዊ ውበትና የጥበብን ተጋምዶ፣ ንባብና ማኅበረሰብ (አንባቢ ራሱን የሳተ ተደርጎ እንደሚታይ)፣ ዛፍ መትከል?... ወዘተ. እንደምልክትነት ተካትተዋል።
#ከራስ ጋር ንግግር/Interior Monologue - ዋናው ገጸ-ባሕሪይ በተለያዩ ስሜቶች መካከል በመቸንከር ጊዜውን/ሁኔታውን የሚመጥኑ ጥያቄዎችን ለእራሱ ያቀርባል፤ ምላሹንም ራሱ ይሰጣል። ከራስ ጋር ንግግር።
‹‹ፋሲካ ግን መቼ ነው? ሩቅ ነው መሰል›› (ገጽ 165)፣ ‹‹ከክፍሉ ተማሪ እኔ ብቻ ሁለት ጊዜ ተገረፍኩ። ምን ስላደረግሁ? ስለመለስኩ›› (ገጽ 189) እና የመሳሰሉትን።
#ሴራ - (ሀ)፣ የድርሰቱ ዋና ገጸ-ባሕርይ ያለመክሊቱ የሚከታተለው ትምህርት የእግር እሳት ይሆንበታል። (ለ)፣ በቤትም በት/ቤትም ስንፍናውን እየተናገሩ የባሰ እንዲያንገሸግሸው ያደርጉታል። (ሐ)፣ የሥነ-ልቡናዋ መምህርት በት/ቤት ተገኝታ ስለመክሊትና ፍላጎት ብሎም እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ታወያያቸዋለች። ይኼኔ ‹‹ራስ›› በጣም ይንገሸገሻል፤ ጥልቅ ሕልምም ያልማል። (መ)፣ ሰበብ ፈልጎ ትምህርቱን ጥሎ አያቶቹ ዘንድ ይኮበልላል። (ሠ)፣ ሌጣ መሬት ላይ ዛፍ ተክሎ መንደሩንና አገሩን ይታደጋል። (ረ)፣ የከንቲባው ገዳይ በቁጥጥር ሥር ይውላል። ከሞላ ጎደል ሴራው የምስራቻዊ ድምዳሜ (surprise ending) ዓይነት መልክ አለው።
#‹‹ራስ››ና ስንፍና ሽሽት/A travelling character - ‹‹ራስ›› ከጅምሩ ተንገሽጋሽ ማቲ ነው። አለፍላጎቱ ተማሪ ቤት ተዱሎ ፍዳውን የሚበላ ዓይነት፤ በጉያው ያሉ ግለሰቦች በነገር እየጎነታተሉ፣ ስንፍናውን ብቻ እየደረቱ ያስመርሩት ጀመር። ቢጥር፣ ቢግር ስኬት ጀርባዋን ሰጠቺው። ቢያስር፣ ቢሠራ የትምህርት ፍላጎቱ ነጠፈ። በቤትም በት/ቤትም ተነቀፈ። ስኬትን፣ ራስን ፍለጋ አያቶቹ ጋር ሄደ፤ ተጓዘ። ከአጀብ ተነጥሎ የሚመጥነውን ዓለም ኖረ። ራስን ፍለጋ!
#በአጠቃላይ ‹‹ራስ›› እንደ ጣኦስ መልከ ብዙ ቴክኒኮችን ያጨቀ ድርሰት ነው። ከላይ የተገለጹት እና ሌሎች ብዙ ‹ቦግ› ብለው ወዲያው ‹እልም› ያሉ የትረካ ቴክኒኮችን አጭቃለች፤ ደራሲው በቀጣይ ቁስ አካላዊ መሣሪያዎችን፣ እንግዳ ክስተትን፣ ከራስ ጋር ንግግርን፣ የምልክት ፈጠራን እና ሌሎች ቴክኒኮችን በይበልጥ ያዳብራቸዋል ብዬ አምናለሁ።
#አገር ማለት
‹‹አገር ልብስ ነው፤›› «ሰው ኹሉ በልብሱ እርቃነ አካሉን እንደሚሰውር ኹሉ አገርም ለሰው ልጅ ልብስ፣ ከለላ፣ መጋረጃ ነው፡፡››
አገር ማለት ሕዝብና መሬት በአንድ ላይ ሆነው በመንግሥት ሲያያዙ ነው፡፡ አገር ያለመሬት አይኖርም፤ አገር ያለሕዝብ አይኖርም፤ አገር ያለድርጅት ያለ መንግሥት፣ ያለ አገዛዝ አይኖርም፡፡ መሬትና ሕዝብም ያለድርጅት አገር አይሆንም፤ ሕዝብና ድርጅትም ያለመሬት አገር አይሆንም። መሬትና ድርጅትም ያለሕዝብ ትርጉም የላቸውም፡፡ ያንድ ንጉሥ ግዛት፣ አገሩም፣ ሕዝቡም ባንድነት መንግሥት ይባላል፡፡› ሕዝብ የሰፈረበትና በድርጅቱ ውስጥ ያለ መሬት አገር ይባላል።
አገሩንም ለመገንባት ሕዝብ ድንበር አቋርጦ የሚመጣን ወራሪ መክቶ ሰላምና ደህንነት ጠብቆ ሀይማኖቱን አስጠብቆ በሚከፈሉት መሥዋዕትነት ኹሉ አጥንትና ደሙን ገብሮ የሚገነባው ድንበር ላይ በአንድ ዓይነት መብትና ግዴታ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ የአገሩ ባለቤቶች ይባላሉ።
ባለቤትነትንና ባለሥልጣንነትን የሚያመለክተው ሉዓላዊነት ሕዝብ ነው፡፡ በአንድ ሕዝብ ውስጥ ብዙ ዓይነት ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ እነዚህ ልዩነቶችን የሚያስተሳስራቸውና ከመከፋፈል ይልቅ ወደኀብረት፣ ከመናናቅ ወደመከባበር፤ ከመጠላላት ወደፍቅር፣ ከመበላለጥ ወደ እኩልነት የሚመሩበት ሕግና ሥርዓት ልዩነቶችን ተቀብሎ የዜግነት አንድነትን በማረጋገጥ ሁኔታም በአንድ ላይ የአገሩ ባለቤት ያደርጋቸዋል፡፡
የአንድ አገር ሕዝብ ስንል በአንድ በተወሰነ ጊዜ በዚያ አገር ውስጥ ያሉትን ሰዎች ድምር ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከተቆረቆረች ጀምሮ ለዚች አገር ክብርና ነፃነት የሞቱትን ሁሉ ይጨምራል፤ ወደፊትም የሚነሱትንና የእነሱንም ልጆች ያካትታል፡፡ ከኋላ የነበረውንና አሁን የሌለውን ወደፊትም የሚወለደውንና አሁን የሌለውን አብረንና አያይዘን ካላየነው የታሪክ አካሄድንና ሕዝቡ የተሳሰረበትን ሰንሰለት ውሉን እንስታዋለን፡፡ ኢትዮጵያ አኹን የገጠማት ይኽ ነው። ውሉን ስተነዋል። መሳታችን ዋጋ እያስከፈለን መጥቷል።
"አገሮች ሁሉ መሬታቸው በተቻለ መጠን በትክክል በድንበር የተከለለ ነው: የትም ቢሆን የእያንዳንዱ አገር የድንበር ታሪክ በጦርነትና በደም የተጻፉ ታሪኮች አሉት፡፡ አገር ህዝቦቿ ሕይወታቸውን መስዋዕት እያደረጉ የጠበቁት መሬት ነው፡፡
የሰው ልጅ ከግለኛነት አስተሳሰብ ወጥቶ የአገርን መሬት ዳር ድንበር አስከብሮ መኖር የአንድ ትውልድ ግዴታ ሳይሆን የተከታታይ ትውልዶች ግዴታ ነው፡፡ አያትህ ለአባትኽ ያወረሰውን አገር አባትህ ለአንተ ካወረሰኽ አንተ ለልጅህ ዳር ድንበሯን ጠብቀህ በውስጧ የሚቀመጡ ቅርሶችን ሰርተኽ የማውረስ ግዴታ አለብኽ።
መነሻ ሀሳቡ ካነበብኩት የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም መጽሐፍ የተወሰደ ሲኾን !!
ለውሏችኹ ይኹናችኹ ፣
በቸር ዋሉ
በቀጣይ ያገር ፍቅር ማለት
ምን እንደኾን እንከትባለን
#ከከበደ_ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ ፩
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ'ነው።
*****
ከማዘዝ በፊት አስቀድሞ መታዘዝን ማወቅ ያስፈልጋል ።
******
ጥሩም ነገር ቢሆን ከመጠን ካለፈ ሁልጊዜምመጥፎ ነው ።
*****
ትዕቢትና ውርዶት አካልና ጥላ ናቸው ሳይለያዩ ሁልጊዜ
ቀዳሚና ተከታይ ሆነው ተያይዘው ሊሄዱ ይኖራሉ።
***
እህልና ውሃ ዕውነትን እንደሚመግቡት ሁሉ መጻሕፍትን ማንበብም አንደዚሁ መንፈስን ይመግበዋል።
****
ከበላይህ ያሉትን ሰዎች እያየህ በልብህ ቅናት አይደርብህ።
ይልቅስ ካንተ በታች ያሉትን ችግረኞች እየተመለከትሀ ዕድ
ልህ ከነሱ የተሻለ በመሆኑ ፈጣሪህን አመስግነው ።
******
ማንም ሰው ቢሆን መከራ ወድቆበት ባየሀ ጊዜ አትፍረድበት ወይም እትጨክንበት በእሱ ላይ የደረሰ መከራ ምናልባት ባንተም ላይ ወደፊት ሳይደርስብህ አይቀርም ይሆናል ።
***
ምንም እንኳን የሚያስመሰግንህ ትልቅ ሥራ ብትሠራ
ምን ጊዜም ቢሆን አትመካበት ትምክሕት ማንኛውንም ዋጋ
ቢሆን ያቀለዋል ትሕትና ግን ከሁሉ ሞያ የበለጠ ዋጋ ያለው
ባሕርይ ነው ።
***
ሰው በሕይወቱ ሲኖር የሚያገኘውን መልካም ነገር ሁሉ
የሚቀበለው ከተወለደባት እገር ስለ ሆነ አስፈላጊ ምክንያት
በመጣ ጊዜ ያለው መልካም ነገር ሁሉ ሕይወቱን እንኳን
ሳይቀር ሳያመነታ ላገሩ ሲል ሊሠዋ ይገባዋል ።
~ ~
ደስ ደስ የሚሉ ጠቃሚ ሀሳቦች
በታሪክና ምሳሌ መፅሐፍ
የቴሌግራም ቻናላችን @azop78
የቴሌግራም ጉሩፓችን @azopbook
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
📚📚📚📚📚📚📚📚
ይህንን መጽሐፍ በተደጋጋሚ አስተዋውቀነዋል።
ለምን ይኾን ቢሉን ? በአተረጓጎም ስልቱም ኾነ በታሪካዊ ይዘቱ እጅግ ላቅ ያለ አፃፃፍ ስልትና የአተረጋጎም ዘይቬን ተከትሎ የተዘጋጀ መጽሐፍ መኾኑ አነሳስቶን ጭምር ነውን
መጽሐፉ በመደብራችን በ250 ብር ብቻ እየተሸጠ ይገኛል።
እነኾ ትንሽ ቅጅዎች አሉን !!
ቀድመው ይሸምቱ !!!
ሥለመጽሐፉ የተሰጡ አስተያየቶች
'The plot to kill grazing" የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በግራዚያኒ ላይ ተቃጥቶ የነበረውን የግድያ ሙከራ እና ያስከተውን የአሰቃቂ ውጤት ሙሉ ታሪኩን መልሶ ማስቃኘት የቻለ፤ ግንባር ቀደም የተዋጣለት መጽሐፋ ነው፡፡ የመጽሐፍ ስኬታማና ጠንካራ ጎን በብዙ መልኩ ከጣሊያኖች ዘንድ በተገኙ የመረጃ ምንጮች ያልታጨቀ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ (መጽሐፉ) ከግድያ ሙከራው ተሳታፊዎች የቤተሰብ አባላት ወይም ከተከታዮቻቸው አሊያም ከወዳዶቻቸው አንደበት በተቀዱ መረጃዎች ትክክለኛነት ይበልጡኑ ለማረጋገጥ ጥሬ ሀቆችን' በኢትዮጵዊያን በኩል በብዛት ከሚገኙ የጽሀፍ ምንጮች ጋር ያነጻጽራቸዋል፡፡ መጽሐፉ ለአንባቢያን በዚያ ክስተት ውስጥ የነበሩትን ዋና ዋና ሰዎች ማንነት በጥንቃቄ ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ የታሪኩ ፍሰትና አገላለጽ ቀላልና ሳያድበሰብስ የቀረበ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በፋሽስት ጣሊያን የተያዘችበትን የአምስት ዓመቱን ታሪክ የማወቅ ፍላጎት ባላቸው ሰዎች ሁሉ' ሊነበብ የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡
ሽፈራው በለ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 11 ምሪተስ ፕሮፌሰር
ይህ መጽሐፍ ያበረከተው ትልቅ አስተዋጽኦ ውስብስብ የነበረውን የሴራውን ባህሪ አፍታቶ ግልጥልጥ አድርጎ ማሳየት ማቻሉ ነው፡፡ ቀደም ባሉ ዘመናት በተለምዶ አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ተብለው ከሚታወቁ ሁለት ስሞች ጋር ብቻ ተያይዞ የቆየውን ክስተት፤ አሁን በስደት ላይ የነበሩትን ንጉሠ-ነገሥት ጨምሮ በርካታ ሰዎች እና ቡድኖች የተሳተፉበት ፈርጀ ብዙ ሴራ ሆኖ ብቅ እያለ ነው፡፡ በቃ ከተነገሩ የመረጃ ምንጮች፤ ምስጋናን ጨምሮ የሰነድ አያያዙ የተሟላና የተደራጀ ነው፡፡ በተጨማሪም መጽሐፉ በስፊው በስዕላዊ መግለጫዎች የተብራራ ነው፡፡ ይህም በድርጊት የተሞላና በርካቶችን በአስገራሚ ሁኔታ ላሳተፈው ለዚህ ዓይነቱ ታሪካዊ ክስተት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ባህሩ ዘውዴ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ኢምሪተስ ፕሮፌሰር
የተለያዩ
#ግዕዝ አማርኛ
#አማርኛ በአማርኛ
#እንግሊዝኛ በእንግሊዝኛ
#ትግርኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#ኦሮምኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#አገውኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#አርጎብኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#ሲዳምኛ አማርኛ እንግሊዝኛ
#ቀደምት ትግርኛ በትግርኛ
መዝገበ ቃላቶች እኻችን ላይ ናቸው !!!!
የፕሬፈሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ታላላቅ የምርምር ሥራዎች መካከል በጥቂቱ እነኾ !!!!
ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ከ400 በላይ የሚኾኑ ታላላቅ የምርምር ሥራዎችን ያበረከቱ ምኹር ሲኾኑ በመጽሐፍ መልኩ ከታተሙት መካከል በጥቂቱ እነኾ እጃችን ላይ ይገኛሉ!!!
ፍኖተ መድሀኒት
- የሰው ልጅ የሺህ ዘመናት ጉዞን በመድሀኒት በኩል ለማሳያት ይሞክራል፡፡
- የሰው ልጅ በሽታ የፈጣሪ ቁጣ ነው ብሎ ያምን ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ አሁን ላይ እንዴት የዘረ መል ህክምና እንደደረሰ ለማሳየት ይሞክራል፡፡
- የፍልስፍና ጥማት ካለብዎ፣ ከቀደምት የግሪክና የሮማ እና ከአረብ ፈላስፋዎች ጋር ያስተዋውቃል፡፡
- መድሀኒት በዘመናዊ መንገድ ለማግኘት የሚያልፍባቸው ሳንይሳዊ መንገዶች በዝርዝር ያስቃኛል፤ የተመረጡ መድሀኒቶች ከየት ተነስተው የት እንደደረሱ ያመላክታል፤ የሰው ልጅ ለሳይንስ ያለውን ቁርጠንኝት ያደንቃሉ፤ይደማመሉ፡፡
- መድሀኒቶች ለማግኘት ገፊ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይፈተሻሉ፡፡ ምን አይነት ማህበራዊና ኢኮኖሚ ሁነት ስለነበር ነው መድሀኒቶቹ ሊገኙ የቻለው የሚለውን ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡
- የፖለቲካ ጥማት ካለብዎ ሶሻሊዝም፣ ካፒታሊዝምና ዮጄኒክስ አስተሳሰብ/እንቅስቃሴ ከመድሀኒት ጋር ተላቁጠው ቀርበዋል፡፡ ከናዚ እስከ ታሊባን፣ ከከቴዎዶር ሩዝቬልት እስከ አዶልፍ ሒትለር፣ ከአዶልፍ ሒትለር እስከ ሙላህ ኡመር እና ኦሳማ ቢላደን ተቃኝተዋል፡፡
- መድሀኒት በተመለከተ የሚነሱ ሀይማኖታዊ እና ፖቲካዊ ሙግቶች/ክርክሮች፣ የሞራል ተጠየቆች በሚገባ ከታሪካዊና ሳይንሳዊ ጉዳዮች ጋር ተሰናስለው ቀርበዋል፡፡
#ከባዶ ላይ መዝገን
#የካህሊል አማልክት
#የመሻገር ሲቃ
#ሰልስቱ ጣኦታት
#የማዕበል ጥንስስ
የተሰኙ ስራዎችን አበርክቶልናል። ታላላቆቹ ደራሲያን ስለተባ ብዕሩ ይመሰክሩለታል። በወጣትነቱ እንዲህ የሚያስደምመን በበሰለ ቁጥር እጅግ የሚጎመራ ጠንካራ ብዕር ያለው ሰውና ጥልቅ አንባቢነቱ ጎልቶ የሚታወቅበት ከሚከትባቸው ጠንካራ ሃሣቦቹ ውስጥ ብስለቱ የሚታይ የሥነ ጽሑፍ ሰው ነው ይሉታል። የሚመጡት ጊዜያት ላይ በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታላቅ ተስፋ የሚጣልበት ብዕረኛ ነው ሲሉ ይመሰክሩለታል።
#ያዕቆብ ብርሃኑ፣ የመሻገር ሲቃና የካህሊል አማልክት ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ አለን። አንብቡለት ብዙ የምታተርፉበት ብዕረኛ ነው።