azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኣንዳንድ ጸሓፊዎች የኣሁኗን ኢትዮጵያን በፊውዳል ዘመን ክነበረችው ኣውሮፓ ጋር
በማወዳደር የዚህችን ኣገር ሥርዓተ ማኅበር hፊውዳል ሥርዓተ ማኅበር ጋር ተመሳሳይ
እንደሆነ ይጽፋሉù ግን ይህ ኣባባል ትክል ነው ወይ? የፊውዳል ሕብረተሰብ የመጀመሪያው ምልክት የመደብ ክፍፍል መኖር መሬትን መደባዊ ጥቅሞች በውርስ የሚተላለፉ መሆናቸው ነው ግን እነዚ ነገሮች በሓበሻ ውስጥ ኣይታዩም፡ በዚህች ኣገር ሹመት ስላላቸው ብቻ ማለትም በኣሁኑ ጊዜ ሥልጣን ላይ ስለሆኑ ብቻ እንደ መኳንንት የሚቆጠሩ ሰዎች ነጋዴዎች፣ ካህናት፣ መነኩሴዎች ወታደሮችና ገበሬዎች ይገኛሉ ግን እነኝ ሰዎች በሹመታቸውና በሚያከናውኑት ሥራ ይለያያሉ እንጂ ራላቸውን የቻሉና እርስ በእርስ የማይገናኙ መደቦች ኣይደሉም፡

ምርኮኞች በገፍ የሚያዙባቸው ጦርነቶች ያለማቋረጥ የሚካሄድና የገዢው መደብ ኣባላት የኣኗኗር ዘይቤ ብዙ ሠራተኞችን የሚፈልግ መሆኑ ባርነት በኣገሪቱ ውስጥ
እንዲኖር ኣድርጓል፡፡ ነገር ግን ይህ ባርነት እኛ ባርነት ብለን ከምንጠራው ነገር ጋር
የሚመሳሰለው በስም ብቻ ነው በኣሁኑ ጊዜ ባርነት በተቋም ደረጃ የለም ኣጤ ምኒልክ
በኣዋጅ ባርነትን ያጠፉ ሲሆን ባሪያ መሸጥና መግዛትም ስለተከለከለ ሲሽጡ የተገኙ
ሰዎች እጃቸው ይቆረጣል

ሓበሻን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመጠኑ ለማወዳደር ብንፈልግ ይህ ሕዝብ
የሚገለጾው በሚከተለው መሠረት ነው፡፡ እሱም እንደ ፈረንሳይ ልዩ ስጦታ ያለውና
ኣስተዋይ፣ እንደ እንግሊዝ እርምጃ የመውሰድ በሥሩ የሚገኙ, ሕዝቦችን የማስተዳደርና የመሪነት ችሎታ ያለው፣ እንደ ስፔይናዊ ኩሩ፣ እንደ ሩስያዊ ሃይማኖቱን የሚወድ ጠባየ ለስላሳና ታጋሽ፣ እንደ ይሁዳዊ የመነገድ ችሎታ ያለውና በጣም ደፋር ብልጥና ተጠራጣሪ ነው።

ከመጽሐፉ የውስጥ ገፅ የተወሰዱ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አስተሳሰብህ ላይ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጣ፣ ባነቡበከው ቅጽበት ሕይወትህን
በደስታ የሚቀይር፡፡

ኦፕራ ዊንፍ

የአሁን ጊዜ ትሩፋትን (The Power of Now) ለመቋደስና በሁለመናችን ሽቅብ
ለመመንደግ በሚደረገው ጉዞ፣ በሀሳብ የሚባዝነውን አዕምሯችንና ይኸው
እዕምሯችን የፈጠረውን የውሸት ማንነት ከበስተኋላችን አራግፈን እልፍ ማ
ግድ ይለናል።

ይህንን ተአምረኛ መጽሐፍ ገና የመጀመሪያውን ገጽ ማንበብ በጀመርን ቅፅበት የእፎይታ አየር ወደ ምንተነፍስበትና በሁለመናችን ወደ ምንመነደግበት ወደ ላዋው ከፍታ ሽቅብ ይዞን ይጓዛል፡፡ ምንም እንኳ በሁለመናችን ለመመንግ ሽቅብ የምናደርገው ጉዞ ፈታኝ ቢሆንም፣ ጉዟችንን ቀሊል ያደርግልን ዘንድ፣
ኤhሀርት ቶል ንጥር ያለ ቋንቋና፣ አንባቢ ጠያቂ ጸሐፊው ደሞ መላሽ አካሔድን ተጠቅሟል፤ ብሥራት እውነቱም አሰምሮ ተርጉሞታል፡

መጀመሪያ ከታተመባት ጊዜ ጀምሮ ድፍን ዓለምን ያነጋገረ፣ በዘመናት ከተፃ ከስንት አንድ ከሆኑት ምርጥ መጽሐፍት የአሁን ሃያልነት (The power now) አንዱ ድንቅና ሁነኛ መጽሐፍ ሲሆን፣ አንባቢዎች ላይ ሁነኛ ለውጥ
መፍጠር የሚችል ብርቱ አቅም ያለው ተአምረኛ መጽሐፍ፡፡ የአንባቢዎችን ህይወት እስከ ወዲያኛው በበጎው መቀየር የሚችል ጥንቅቅ ያለ መጽሐፍ፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21



ጊዮርጊስ ጀባና ወደ አትክልት ተራ መድረክ ዋናው መንገድ ላይ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት የሶሻሊዝም መጽሐፍቶች አግኝተናል !!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከዙላ እሰከ መቅደላ ከእንግሊዝ ጦር ጋር የተጓዘ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ የዘገበው ታሪክ፡፡
በአፄ ቴዎድሮስ የመጨረሻዋ ሰ\ት በቦታው የነበረ የአይን ምስክር፡፡

አንድ ጊዜ ተወዳጅ ሀይለኛና ገናና የነበሩትን ንጉሥ የመጨረሻ ምዕራፍ ግልፅና ጥልቅ
በሆነ ሁኔታ ያቀርባል፡፡

ከመቅደላ በፊት የነበሩ ሁኔታዎችን ያስገነዝባል፡፡
መቅደላ እንደዚህ በዝርዝር ቀርቦ ያውቅም፡፡
ስለ እፄ ቴዎድሮስ መነበብ የሚገባው ፅሁፍ፡፡

ከመፅሐፉ የተወሰደ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን ።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

Well written in a beautiful early Victorian style, it follows the amazing saga of the adventures Of an appealing, well educated young Englishman in the previously unvisited by any European Wilds of upland modern-day Ethiopia, bringing vividly to light the customs and beliefs of that Exotic land at that time. This work is a factual narrative by Maj. William Cornwallis Harris, who was sent by Queen Victoria to head a mission as the first ambassador from the UK to the KingDom of Goa in the heart of modern Ethiopia. The kings of Goa became the Emperors of Ethiopia in later years. its worth the effort for the insight into local culture of the time and its resemblance in many ways to that of the present. His style is very "Victorian," with elaborately descriptive prose. "Florid" would be a good word to describe it. After a while, however, the reader falls into the rhythm of the prose and the reading becomes easier. The writing style places the reader with in the Victorian milieu.lt is written to provide a narrative of the mission, and a somewhat analyticcal record of observation of terrain, peoples, cultures and customs encountered. He faithfully describes the mission day by day as it moves through punishing terrain, tribal battles, and variOus dangers finally to reach the highlands. He faithfully describes the peoples along the way; their appearance, their customs, their culture culminating in an in-depth look at the culture of Goa; its monarchy, its court, its towns and townspeople, its Coptic Church, and modes of dress, in sufficient detail that the reader feels he has been there in that day and age. Any student of history as well as anyone interested in African history will find this book fascinating.

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዎልትዝ ዛሬ ጧት በማይታወቅ ምክንያት ቀደም ብሎ ተስቷል። ከአልጋው ግርጌ የታየውን የተለመደ የፈረስ ራስ ቅርጽ ምንነት ለማጣራት በክርኑ ዳኸና የራስጌ መብራቱን አበራ። ድንጋጤው በመላ ሰውነቱ ህመም አሰራጨበት፡ በትልቅ መዶሻ ደረቱን የተመታ ይመስል የልብ ትርታው እንጣጥ እንጣጥ እያላ አቅለሸለሸው፡፡

     ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
            🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከመማሪያ መጽሐፍት ውጭ ያሉ መጻሕፍቶችን እንገዛለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

“እዚህ ነው ምወርደው አቁም አቁም - ኦ! ኦ! አቁም
አልኩህ… እዚህ አውርደኝ "
ይኸኔ አዲሱ አርቲስቲክ ፎቅ ደርሰናል ሴትዮዋ ልትወርድ
ስትል
አምስት ስድስት ሰባት
“በል ስሙኒህን እሳቸው ይከፍሌሀል” አለችው''
“ሌላውስ ስሙኒ?”
“የምን ሌላ 'ባክህ?
“እንዲያውም ሰባ አምስት ነበረ”
“እሱን ተወው!”
“አሁን ጭቅጭቁ ይቅርና ሀምሳ ሳንቲም እፈልጋለሁ”
“ስንት ነው ያለባቸው?” አልኩት:
“ሀምሳ ሳንቲም”
ከፈልኩላት የራሴንም ከፈልኩ እና ከመኪናው ወጣሁ::
ፂሜን ለመላጨት ወደ ፀጉር አስተካካይ ቤት አመራሁ::
… ከሰአት በኋላውን ከስህነ ጋር ነበር ያሳለፍኩት፡፡
“ሰሞኑን ብዙ ሳጠና ነበር፡፡ ዛሬ ማታ አባባ የፈቀዱልኝ
እንደሆነ ሲኒማ ትወስደኛለህ?” ብላኝ ነበር::
“በደስታ”
“የት ነው 'ምንገባው?”
የትም ጥሩ ፊልም የለም' ዝምብለን ብሄራዊ ቲያትር እንግባ"
ከሁሉም እሱ ይሻላል?"
“አይ! መሻሉንስ ኢትዮጵያ ይሻላል"
“ታዲያ ለምን ኢትዮጵያ አትወስደኝም?
ወምበሩ ይቆረቁረኛል 'ባክሽን' ብሄራዊ ግን ሶፋው…
“ቀበጥ ነህ”
“ውሸቴን ነው፡፡ ለሶፋው አይደለም"
“ታዲያ ለምንድነው?”
“ሚስጥር ነው፡፡ ለልጆች አይነገርም”
“ንገረኝ”
“እእ!” - ራሴን እያነቃነቅኩ
“እባክህን” - በፈገግታ
“እእ!”
“ተወዋ! _ ይቅር፡፡ እኔ ደሞ ካልነገርከኝ አብሬህ ሲኒማ
አልገባም”
“እሺ-ሺ! እነግርሻለሁ"
“ንገረኛ”
“ብሄራዊ የገባን እንደሆነ፣ ፎቅ ወጥተን ወደ ኋላ መጨረሻ
ተርታ ያለው ወምበር ጋ እንቀመጥና አንቺ ፊልሙን ታያለሽ”

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የቼክ ሪፐብሊኩ ተወላጅ የዚህ ተወላጅ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮችን የጎበኙ ሲሆን እ.ኤ.አ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመምጣት ከንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቀርበው የኢትዮጵያን መኰንንነት ማዕረግ ከተሾሙ በኋላ የሰሜኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ለነበሩት ራስ ካሣ ኃይሉ የጦር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡ በዚሁ ወቅት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጎን ሆነው ታግለዋል፡ መጽሐፉ ሃበሽስካ ኦዴሳ (Habešská Odyssea) የሃበሻ ጀብዱ የዚያን የገበሬጦር ጀግንነት ለመዘከር የጻፉት ነው፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ጠመንጃና ሙዚቃን ተጋበዙልኝ! ... ከአገሬው የኪን ፍልስፍና ተነስቶ፥ በ40ዎቹ አርመናውያን አመጣጥ ጎዳና ተምሞ፥ ማርሽ ኢትዮጵያ እና ማርሽ ተፈሪን ተዝቶ፥ የኬቦርክ ናልባንዲያን እና የየኔታ ዮፍታሄ ንጉሴን ፍጥጫ አውስቶ፥ በፋቼታ ኔራ ኩርባ ታጥፎ፥ መሰንቆ እንደ ጦር መሣሪያ የተቆጠረበትን አውድ አውግቶን ይነጉዳል። የሀገር ፍቅር ማኅበርን ከአመሠራረቱ ጀምሮ የነበረውን ታሪክ ለመሰነድ የሄደበት ርቀት እሚደንቅ ነው። የቀብር ቀኑን በገዛ ሙዚቃው ከታጀበለት አሰፋ አባተ፥ እስከ ሙዚቃ የዋጠው ፖለቲካ (አሊ ቢራ)፥ ከሜሪ አርምዴ ታሪክ የአበበ ፍቅር እስካናወዛት አስናቀች ወርቁ ድረስ ያሉ የሕይወት ታሪክ መድብል ብዙ የተለፋበት ሥራ መሆኑን ያሳብቃል። የተለያዩ የሙዚቃ ባንድ ታሪኮችን ማካተቱ ሲገርመን፥ ዓይነስውራን ሙዚቀኞችን ማውሳቱ ደግሞ እጅግ አስደንቆኛል። የ700 ሙዚቃዎች "ካታሎግ" ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው።

ደራሲውን እጅ ነስተናል! በንባብ ይለቅ ብለናል! በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር፥ በሀገር ፍቅር ማኅበር፥ የሙዚቃ ባንዶች ማኅበር ... ተጋግዘው መሥራት የነበረባቸውን የቤት ሥራ በአንድ ሰው ትከሻ ብቻ መሞከሩ አጃኢብ እንድንል አሰኝቶናል።

#ጠመንጃና_ሙዚቃ
#ይነገር_ጌታቸው


በመደብራችን ያገኙተል👍👍

የቴሌግራም ቻናላችን 👉👉👉 @azop78
 

  የሚፈልጉትን መፅሀፍ ለማዘዝ  @Mesay21

     የቻናላችን ተከታይ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው ።
                  🙏🙏🙏🙏🙏🙏
   ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
            📚📚📚📚📖📖

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

(ሕይወት)
ሕይወት ጭለማ ነው የምንጓዝበት
የደስታችን መብራት፤
መንገድ አሳይቶን ወዲያው የሚጠፉ
የመከራ ዝናም ችግሩ ሲያካፉ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

/ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር፤/

ልጄ ሆይ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ ሆነ ግን፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም፡

ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ፣ ሲያዝኑ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል፡፡

ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል?

የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡

ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን፤ የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡

ልጄ ሆይ፤ ሰው ምንም ብልህና አዋቂ ቢሆን በራሱ ሥራ ብቻ ራሱን ችሎ እንደማይኖር ዕወቅ:: ነገር ግን ሁሉም በየሥራው ጸንቶ እርስ በርሱ በሥራ ይፈላለጋል:: ስለዚህ ሰውን ሁሉ አክብረህ ኑር እንጂ ሰውን አትናቅ ሥራውንም አትንቀፍ::

ልጄ ሆይ: አካልህና ልብስህ ዘወትር ንጹህ ይሁን:: እጅህን ለሥራ: ዓይንህን ለማየት: ጆሮህን ለመስማት ፈጣኖች አድርግ:: አፍህን ግን በጠንካራ ልጓም ለጉመህ ያዝ:: አረጋገጥህ በዝግታ አነጋገርህ በለዘብታ ይሁን:: ያልነገሩህን አትስማ: ያልስጡህን አትቀበል: ያልጠየቁህን አትመልስ:: ሽቅርቅር አትሁን: ንብረትህ ተጠቅላላ ይሁን: ምግብና መጠጥህ በልክ ሆኖ ያው የጠዳና የጣፈጠ ይሁን::

ልጄ ሆይ ፈቃደ ሥላሴ፤ አሳብ አታብዛ፤ ወደ ፊትም ምን ነገር ይመጣ ይሆን ብለህ አትጨነቅ፤ ምንም አሳብና ጭንቀት ብታበዛ የሚሆን ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወደ ፊትም እሾማለሁ፤ እሸለማለሁ፤ ብለህ በአሳብህ ደስ አይበልህ፡፡ ለሰውም አትናገር፤ ምናልባት ከተናገርህ በኋላ ሳታገኘው የቀረህ እንደ ሆነ ታላቅ ኀፍረት ይሆንብሃልና፡፡ ወደ ፊት የሚያናድድ ሥራ አትሥራ፡፡ በገዛ እጅህ በሠራኸውና ባለፈው ሥራ አትናደድ፡፡ ልጄ ሆይ፤ ጌታ ለመሆን ትፈልግ እንደ ሆነ ጌትነት ማለት ያለ አሳብና ያለ ጭንቀት መኖር ነው፡፡ አሳብህም ሁሉ ከሞትህ በኋላ ወዲያኛው ዓለም ስለሚሆነው ስለ ነፍስህ ነገር ይሁን እንጂ በዚህ ዓለም በሥጋህ ስለሚሆነው ነገር እጅግ አትጨነቅ፡፡

   

የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
       የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉  @azopbook

             #ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነውና ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏



  ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
           🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሕፃኑ የሆነ ድምፅ አወጣ። ዮሲ ውሻዋን ትቶ በሩን ዘግቶ ወደ ልጁ ሄደ ። ሙዳዩን አንስቶ መኝታ ቤት ይዞት ገባ ። ዐልጋ ላይ አብራው እዚህ ቤት የገባቸው ምትክ የተባለችው ልጅ ጋቢ ደርባ ተኝታለች ።
  -- አመጣሁት አለ
-- ለምን?
  -- እንጃ ፈራሁ.....
         ምትክ የለበሰችውን ጋቢ ገለጠችና ቁጭ አለች ፡፡ እጅዋን ወደ ዮሴፍ ዘረጋች ።
-- ዮሴፍዬ ልጄን ልየው በማርያም አለች
  -- ለመሆኑ የልጁን ስም ማን ትይዋለሽ ምትክ?
--እ ስሙን? እ? 'ማኩታ' ። አንድ የእኔ ቢጤ አሮጊት ማኩታ ሁኚ ይሉኝ ነበር ። ትርጉሙን አላውቅም ዮሲዬ ። ምንም እንጃ ።
-- ማኩታ እንዴት ስም ሊሆን ይችላል? ትርጉሙን ካላወቅሽ?
  -- እንጃ
  -- ግን ሲመርቁኝ ነው እንደዛ የሚሉት....ስለዚህ በቃ ስም ይሆነዋል
      ዮሴፍ ፈገግ እያለ ሄዶ ልጅዋን ከነሙዳዩ ሰጣትና ዐልጋ ዳር ተቀመጠ ። ምትክ ተቀብላ ፍጡሩን አየችና በአመልካች ጣትዋ በቀስታ ፊቱን ነካካችው ።  ሳቅ ተሰማ  
  -- ይስቃል! አለች..... አይኖቿ በመገረም ተከፈቱ
     ዮሴፍ መዳይ ያልያዘ እጅዋን አነሳና ሳመው ።
-- መስኮቱን ልክፈት? አለ
  -- እሺ ክፈተው አለች ዓይኖቿን ከልጁ ሳታነሳ
       ዮሴፍ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሄደና ግራና ቀኝ አንድ ሰፊ መስኮት ከፈተ ። ቢጫ ብርሃን ተገድቦ እንደነበረ ውሃ ጎርፎ ገባ ። ደነገጠ ።
-- እዪ ምትክ የዚህ ዐይነት ብርሃን አይተሽ ታውቂያለሽ?   
      ምትክ ወደቆመበት ዞር ብላ በድንጋጤ ፡
  -እንዴ- ? ዮሲ! አለች ።

        መኝታ ቤቱ ወለል ላይ ሰፊ አራት ማዕዘን የፀሐይ ርግብግብታ አርፏል ። የተቃቃ ወፍራም ቢጫ ኩታ ይመስላል ። ዮሲ ጐንበስ ብሎ እጁን እዚህ ሥነ-ጸዳል ውስጥ አስገባ ፡፡ አጁ በቢጫ እሳት የተያያዘ ጥጥ መሰለ ፡፡ እጁን ወደ ጥላው መለሰው ፡፡ እንደገና መልሶ ብርሃን ውስጥ ከተተው ። ምትክ በጋቢ ተጠቅልላ ከዐልጋዋ ተነሳችና ሙዳዩን ፀሐዩ ብርሃን መሃል አመቻችታ አስቀመጠችው ። ሞሳው መሳቅ ጀመረ ። የልጁ ሙዳይ ብቻ ሳትሆን መኝታ ክፍሉ በውህዋሄ ተሞላ ። እውጭ ባለው እርጥበት የተነካ ያልመሰለ ሙቀት ክፍሉ ውስጥ ተረጋግቶ ተቀመጠ ። ከወዲያ ከውጭ መኪናዋ ከቆመችበት ጀምሮ እስከ ቤቱ ግድግዳ ጥግ ያለው የሲሚንቶና የአፈር መሬት በነፀረፃይ በማለለ አደይና ጨሌ
ተሸፈነ ።
         ቀድሞ ያልነበሩ በጎችና ላሞች ከየት እንደመጡ ሳይታወቅ እዛ ላይ ፈሰሱ ። አንድ ሁለቱ ወደተከፈተው መስኮት ተጠግተው ፊታቸውን ልጁ ወዳለበት አዙረው የጋጡትን ሳር ማመንዠካቸውን ቀጠሉ ። ዮሴፍና ምትክ ተቃቅፈው ወደ ዐልጋው ሄዱና ጎን ለጎን ተቀመጡ ። በመለዋወጥ ላይ ያለውን ግቢ አፋቸውን ከፍተው ያያሉ ። ዮሴፍ የምትክን ጉንጭ በእጁ ዳበሳት ። እንዳፈረች ሁሉ ኣይኖቿን ጨፍና ኩታ ፊቷ ላይ ደረበች ። በቀስታ ገፈፋትና አተኩሮ አያት ፡፡ 
  -- ምነው ? አለችው
         ወደ ደረቱ አጥብቆ ሳባትና አናቷ መሃል ሳማት ። በመከሰት ላይ ያለውን ተአምር ማየታቸውን ቀጠሉ ።..

      📖 #የስንብት_ቀለማት
      ✍ #አዳም_ረታ
   ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋልን።
          🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የትግራይና የኤርትራ ተወላጆች በአጠቃላይ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

በሺህ ዓመታት በሚቆጠር ታሪካችን ውስጥ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ለማድረግ በየጊዜው በሕይወታቸው መስዋዕትነት ከከፈሉት ውስጥ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች ከማንም ያላነሰ ክብር ተጎናጽፈው ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ስንናገር ጉልሁ እውነት ይህ ነው። የኤርትራም ሆኑ የትግራይ ተወላጆች በአጠቃላይ አሁን በኢትዮጵያ ላይ በደረሰው አዲስ ነገር የታሪክ ሐፍረት ተሸካሚዎች አይሆኑም ያንን ለሻቢያና ለወያኔ ብቻ እንተውላቸው፡፡ ክብርም ከሆነ ይከበሩበት፤ ሐፍረትም ከሆነ ይፈሩበት።

በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው ከኢጣልያ ወረራ ጋር የተያያዘ ነው። የምድረ ባሕርን ወይም የመረብ ምላሽን ስም ኤርትራ ብላ የለወጠች ኢጣልያ ነች፤ የመሬቱን ክልል በውል ያሰወሰነች : ኢጣልያ ነች፡፡ ይህ የሃምሳና የስድሳ ዓመት ታሪክ በሺህ ዓመታት የሚቆጠረውን የኢትዮጵያ ታሪክ በክህደት ለውጦ፣ ኤርትራ በኃይል _ ከኢትዮጵያ አንድትለይ አድርጎአል፡

ችግሩን በትክክል ለይተው ካላወቁት መፍትሔ የተባለው ሌላ ችግር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር የሥልጣን ባለቤትነቱን የነጠቀው የአገዛዝ ሥርዓት ሆኖ ሳለ ችግሩ አማራ ነው ተብሎ በጦርነት ኤርትራ ተገነጠለች፣ በዚህም ምክንያት አንድ የአገዛዝ ሥርዓት በነበረበት አገር ሁለት የአገዛዝ ሥርዓቶች በቀሉበት፡፡ አሁን ደግሞ ችግሩ ትግርኛ ተናጋሪ ነው ይባላል፣ ሌላ ስሕተት፣ የሚሠራውም ወደሌላ የስሕተት ውጤትና አገርን ወደማፍረስ ነው፡፡ ተገድደን የገባንበትን ቁልቁለት ሳንጨርሰው መንቃትና አቅጣጫችንን ለመለወጥ ቆርጠን መነሣት አለብን፡፡ እስቲ ከየት ተነስተን የት እንደደረስን እንመርምረው፡፡


የክህደት ቁልቁለት መጽሐፋቸው ገጽ 17 የተወሰደ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በነገራችን ላይ የአሊ በርኬ የህያወት ታሪክ በመጸሐፍ ከተዘጋጀ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡መጽሐፉን በኦሮምኛ ያሰናዳው ጋዜጠኛና ደራሲ ኢሳያስ ሆርዶፋ ሲሆን እህቱ ደግሞ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡ ኢሳያስ ሆርዶፋ በርካታ መጸሕፍትን በአፋን ኦሮሞ ያሰናዱ ሲሆን በኦሮምኛ በሚጽፉት የሬድዮ ድራማዎችም ይታወቃሉ፡፡የሚገርመው ደራሲ ኢሳያስ አሊን ከደርግ ዘመን ጀምሮ ኢንተርቪው ሰርቼዋለሁ ይላል ይሁን እንጂ ለመጽሐፉ ሽፋን የተጠቀመው ግን የሻምበል ባሻ መኮንን ከበደን ምስል ነው፡፡ሻምበል ባሻ መኮንን ከበደ አሁንም በሕይወት አሉ፡፡እኔ ከወራት በፊት የአሊ በርኬን የህይወት ታሪክ መጽሐፍ እያነበቡ ተገናኝተን አውግተናል፡፡ አስፈላጊ ከሆን ለጥቂት ሰዎች ስልካቸውን እልካለሁ፡፡ከስር የምትመለከቱት ምስል የደራሲው ነው፡፡

ከእንዳለ ጌንቦ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ማኅቶተ ምግባር ወሃይማኖት፣ መጋቤ ምሥጢር ወጥበብ፣ መፍቀሬ ትሕትና ወፍቅር፣የተባለው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዘመኑ እውነተኛውን ሕይወት የኖረ ነው፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ፀሐይ አብርተው፤ እንደጨረቃ ደምቀው፤ እንደ ከዋክብት አሸብርቀው፤ ወንጌልን በቃላቸው፣ በመጻሕፍቶቻቸው፣ በምግባራቸው ሰብከው ካለፉ ቅዱሳን ሊቃውንት አባቶች መካከል አንዱ ነው፡፡

ተወልዶ ካደገበት ሀገር ተነሥቶ ወንጌልን ዞሮ ባስተማረበት ሁሉ ምስክሮቹ የሚሆኑ የወንጌል አበርክቶዎቹ አሉ፡፡ እርሱ ያልተረጎመው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፣ ያዳሰሰው ነገረ ሃይማኖት፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ ቤተ ክርስቲያን የለም ብለን ብንጠቅስም ካገኘናቸው መካከል ከብዙ በጥቂቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ
ከመጡት መጻሕፍት መካከል የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል የተረጎመበት ድርሳኑ አንዱ
ነው፡፡

በብዙ ረቂቅና ምጡቅ ሰፊና ጥልቅ በሆኑ መጻሕፍቶቹ የምናውቀውን ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል እንዴት አድርጎ ተርጉሞት ይሆን የሚለውን
እንድናነብ ዕድሉን የሰጠን ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ባስነበበን እነኋት
ክርስትና፣ ስምንተኛው ቀን፣ የነፍስ ወግ፣ የትኅርምት ሕይወት፣ ኅብረ ወንጌል፣ ድንቅ
እውነትና በሌሎችም መጻሕፍቶቹ ስለምናውቀው “የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ” የሚለውን በሚገባ ተርጉሞ አቅርቦልናል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዮሐንስን ወንጌል የተረጎመበትን መንገድ፣ ያመሳጠረበትን
የስብከት ዘዴ ከመጽሐፉ ተረድተናል፡፡ ለምሳሌ “ቀዳሚሁ ቃል፤ መጀመሪያ ቃል ነበረ”
የሚለውን የተረጎመበትን መንገድ እያደነቅን ሳንጨርስ፣ በምዕራፍ ሁለት ስለ ቃና
ዘገሊላው ተአምር፣ ስለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ያብራራል፡፡ ቀድሞም ስለእመቤታችን ጽፎ የማይጠግበው፣ ሰብኮ የማጨርሰውን ሊቁ፤
እዚህ ላይ አገኛትና እንዴ አድርጎ እንደተረጎመው ስናነብ ዛሬም አፈወርቅ እንድንል አድጎናል፡፡

ቀጣዮቹንም ምዕራፎች የተረጎመበትን መንገድ እየገለጽን ስለማንዘልቀው ለቅዱሱ የገለጠውን ምሥጢር ለእኛም እንዲገልጥልን ጸሎቱ ትርዳን፡፡

  ከመጻሕፍት ዝግጅትና አርትዖት ክፍል

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
      🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኦሪጅናል ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
ሰዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህ መጽሐፍ የብር መዶሻ፣ የወርቅ ሚስማር፣ የዳይንድ ብሎኬት እያቀበለ
ሀብት እንድንገነባ የሚረዳ ጽሐፍ ነው!!!

ሀብትህን ማስፋፋት እና ማሳደግ ትፈልጋለህ? ይህን መጽሐፍ ማንበብ አለብህ

ትምህርት ላይ ጎበዝ አይደለህም?... በትምህርት ወድቅሃል? በፍጹም እንዳታዝን!
በዚህ መጽሐፍ ምክንያት ሕይወትህን መቀየር ትችላለህ!

ወላጅ ነህ? ልጆችህ ከስር ጀምሮ ሀብት የሚገነቡበትን ጥበብ ለማስተር ይህ መጽሐፍ ይረዳሀል።

ተቀጣሪ ሰራተኛ ነህ? ተማሪ ነህ? ነጋዴ ነህ?... ይህ መጽሐፍ ያስፈልግሃል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዘጋጅ:- መምህር ለይኩን ጸጋ
የድጓና የመጻሕፍት ሐዲሰት ትርጓሜ መምህር

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የንቡረዕድ ኤርሚያስ ከበደ መጽሐፍቶች እጃችን ላይ ይገኛሉ !!!!


ኤዞፕ መጻሕፍት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከ500 በላይ የመንጃ ፍቃድ ጥያቄዌችን የያዘ ምርጥ መጽሐፍ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኦሪጅናል ቨርዥን
1962 ዓ ም የታተመ።

በደጅ አዝማች ከበደ ተሰማ
የታሪክ ማስታወሻ !!!

አንድ ኮፒ ብቻ አለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ታህሳስ 9 ቀን 1921 ዓ.ም. ሐረር፣ መቂ ጋሪ ሙለታ ባዕት የተወለደው ህጻን አድጎ ጎልምሶ
ኢትዮጵያን እንደሚያስጠራ የአፍሪቃዊነት አተያይና የአንድነት ሀሳብን ከግብር እንዲውል
የሚያደረግ ታላቅ ዲፕሎማት ይወጣዋል ብሎ የጠረጠረ አልነበረም፡፡ ይሁንና አቶ ከተማ ይፍሩ ግን ውጣ ውረዱን አልፎ፣ ስቃይና መከራውን ተቋቁሞ የሀገር መጠሪያ ሆነ ይህ የአቶ ከተማ ታሪክ የትላንቱን የአባቶቻችንና የእናቶቻችንን ልፋትና ግረት አመልካች ተምሳሌ ነው፡ ከህይወቱ ጉዞ የተቀነጨበ አንዱን ሰበዝ - እንጎ ታሪኩ ብቻ ነው የቀረበው

የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት የነበረው ውዝግብና ገመድ ጉተታ፤ ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ
ለማድረግ የተጓበት ርቀት፣ በሀገር ውስጥ በግሉ የደረሰበት ጉንተላና ግፊያ፣ የውጭ ባዕዳን የሚያጠምዱትን ወጥመድና እንቅፋት የማለፍ ጥበቡን ታዩበታላችሁ፡ ሌሎችን ታሪካዊ ኹነቶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ላይ እንዳለ፣ በንግሰ ነገስቱ ጸሀፊነቱ ወቅትም የነበረውን ፈተና በአቶ ከተማ ታሪክ አቋራጭነት ታጤኑበታላችሁ፡

እና ያ ከጋራሙለታ የወጣው ኢትዮጵያዊ ራሱን መስዋዕት በማድረግ ባገለገላት ሀገር በግፍ
ዘብጥያ በተወረወረበት ክፉ ጊዜ በማስታወሻው ላይ (ጥር 1968 ላይ ) እንዲህ ብሎ ነበር“እውነት ትመነምናለች እንጂ አትሞትም እንደሚባለው በአለኝ አቅም ጊዜው ሁኔታውና አቅሙ በሚፈቅደው ለአገሬ ያደረጉትንና ለማድረግም የሞከርኩትን ጊዜ ወደፊት እንደሚገልጠው ስለማምን
እጽናናለሁ: በተለይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በነበርኩ ጊዜ የኢትዮጵያን የውጭ ፖለቲካ ከምን አንስቼ ምን ደረጃ ላይ እንዳደረስኩት ስራውና የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ምስክሬ ነው'' እውንም የአቶ ከተማን ስራ ጊዜ ይገልጠዋል፡ ይህ መጽሐፍም የመጀመሪያ ነው፡፡

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከገበያ ጠፍት የነበረችው የነበረችው #ሚትራሊዮን
በመደብራችን ተገኝታለች

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መጽሐፈ ድጓ
ቅዱስ ያሬድ እንደደረሰው
በሦስት ረድፍ የታተመ
በቀዳማዊ ኋይለስላሴ ዘመን የታተመ!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ጠመንጃና _ሙዚቃን_ተጋበዙልኝ!
ከአገሬው የኪን ፍልስፍና ተነስቶ፥ በ40ዎቹ አርመናውያን አመጣጥ ጎዳና ተምሞ፥ ማርሽ ኢትዮጵያ እና ማርሽ ተፈሪን ተዝቶ፥ የኬቦርክ ናልባንዲያን እና የየኔታ ዮፍታሄ ንጉሴን ፍጥጫ አውስቶ፥ በፋቼታ ኔራ ኩርባ ታጥፎ፥ መሰንቆ እንደ ጦር መሣሪያ የተቆጠረበትን አውድ አውግቶን ይነጉዳል። የሀገር ፍቅር ማኅበርን ከአመሠራረቱ ጀምሮ የነበረውን ታሪክ ለመሰነድ የሄደበት ርቀት እሚደንቅ ነው። የቀብር ቀኑን በገዛ ሙዚቃው ከታጀበለት አሰፋ አባተ፥ እስከ ሙዚቃ የዋጠው ፖለቲካ (አሊ ቢራ)፥ ከሜሪ አርምዴ ታሪክ የአበበ ፍቅር እስካናወዛት አስናቀች ወርቁ ድረስ ያሉ የሕይወት ታሪክ መድብል ብዙ የተለፋበት ሥራ መሆኑን ያሳብቃል። የተለያዩ የሙዚቃ ባንድ ታሪኮችን ማካተቱ ሲገርመን፥ ዓይነስውራን ሙዚቀኞችን ማውሳቱ ደግሞ እጅግ አስደንቆኛል። የ700 ሙዚቃዎች "ካታሎግ" ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው።

ደራሲውን እጅ ነስተናል! በንባብ ይለቅ ብለናል! በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር፥ በሀገር ፍቅር ማኅበር፥ የሙዚቃ ባንዶች ማኅበር ... ተጋግዘው መሥራት የነበረባቸውን የቤት ሥራ በአንድ ሰው ትከሻ ብቻ መሞከሩ አጃኢብ እንድንል አሰኝቶናል።

📖#ጠመንጃና_ሙዚቃ
✍#ይነገር_ጌታቸው

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ሐምሌ 8፣ 1914 
#ኒው ዮርክ 

   ውድ ሜሪ አንቺ እጅግ የበዛ ሰዎችን የመረዳት መክሊት የተሰጠሽ ሰው ነሽ። ሕይወትን አዳይ ነሽ ። አንቺ ለመጋራት ሳይሆን ሕይወቱን ለማበልጸግ የሆነን ሰው እንደሚወዳጅ ታላቅ መልዓክ ነሽ። በኑረት ዘመኔ ከአንቺ ጋር መተዋወቄ ከምልዓተ ዓለሙ ተፈጥሯዊ ስልተ ምትና ስልተ ስሪት ውጪ የሆነ አስደናቂ ተዓምር ነው። 
     "ዘማድማን" በተሰኘ መጽሐፌ እንደገለጽኩት የሚረዱን ሰዎች  ከሕይወታችን ውስጥ የሆነውን ነገር ይቆጣጠሩብናል። አንቺ ጋ ይሄ  የለም። የአንቺ እኔን መረዳት ከማውቃቸው ሁሉ በተለየ ነጻነትን  የሚያጎናጽፍ ሰላማዊ ነው። ባለፈው የመጨረሻ ጉብኝትሽ ልቤን በመዳፍሽ ይዘሽ ከላዩዋ ላይ ነቁጥ የምታክል ጥቁር ነገር አገኘሽ። 
በዚያችው ቅጽበት ጥቁሯ ነጥብ ለዘለዓለም ከልቤ ላይ ተፋቀች እኔም ሙሉ ለሙሉ ከእሥራቴ ነጻ ወጣሁ። 

   ይሄው አሁን ደግሞ የተራራ ላይ ብህትውና ላይ ነሽ። በበኩሌ በረቂቅ፣ ስውር፣ ውብ መሬቶች ላይ አርምሞን ከመለማመድ በላይ የሚያስደስት ምንም ነገር እንደሌለ አምናለሁ። ሆኖም ተወዳጄ ሆይ ምልዓቱን Uሰሳን የተራበች ነፍስሽ በአንድ ሰሞን ጀብድ ብቻ  እንደማትረካ ኣውቃለሁና አጉል መዳፈርን ተጠንቀቁ። ምክንያቱም  ለዳግም የUሰሳ ጉዞ ወደ ተራራ መውጣት ትችይ ዘንድ ደኅንነትሽ  መረጋገጥ አለበት። ቤቴ በላክሻቸው ‹አሪቲና ጠጅሳር መልካም መዓዛ ታውዶልሻል። ስለላክሽልኝ እግዚአብሔር ይባርክሽ። 
   

የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
       የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉  @azopbook

             #ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነውና ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ድርሰት ጂ-ኢ- ሌሲንግ
ርዕስ. ናትናኤል ጠቢቡ
ትርጉም. ነብይ መኮነን
ዘውግ. ትያትር

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

1. አገር ማለት

አለቃ ተሰማ ሀብተሚካኤል ግፅው የአገርን ትርጉም እንደሚከተለው ይገልጹለታል፤ ‹‹አገር ልብስ ነው፤›› ብለው ሲያብራሩ «ሰው ኹሉ በልብሱ እርቃነ አካሉን እንደሚሰውር፣ አገርም ልብስ፣ ከለላ፣ መጋረጃ ነው፡፡›› ይላሉ፡፡

አገር ማለት ሕዝብና መሬት በአንድ ላይ ሆነው በድርጅት ወይም መንግሥት ሲያያዙ ነው፡፡ አገር ያለመሬት አይኖርም፤ አገር ያለሕዝብ አይኖርም፤ አገር ያለድርጅት (ማለት ሲሆን መንግሥት፣ አለዚያ አገዛዝ አይኖርም፡፡ መሬትና ሕዝብም ያለድርጅት አገር አይሆንም፤ ሕዝብና ድርጅትም ያለመሬት አገር አይሆንም፤ መሬትና ድርጅትም ያለሕዝብ ትርጉም የላቸውም፡፡

አለቃ : ደስታ : በእንግሊዝኛ ስቴት steat የሚባለው ቃል ያዘለውን ትርጉም በአማርኛ መንግሥት ለሚለው ቃል ይሰጡታል፤ እንዲህ ይላሉ፤ ያንድ ንጉሥ ግዛት፣ አገሩም፣ ሕዝቡም ባንድነት መንግሥት ይባላል፡፡› አለቃ ደስታ ሕዝብ ሲሉ ሕዝብ የሰፈረበትን መሬት ጭምር ነው።

ሕዝብ የምንለው በዚያ በደም የተገነባ ድንበር ውስጥ በአንድ ዓይነት መብትና ግዴታ ተጠምደው የአገሩ ባለቤት ሆነው የሚኖሩትን ሰዎች በሙሉ _ ነው፡፡ ባለቤትነትንና ባለሥልጣንነትን የሚያመለክተው ሉዓላዊነት የሕዝብ ነው፡፡ በአንድ ሕዝብ ውስጥ ብዙ ዓይነት ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ እነዚህ ልዩነቶችን የሚያስተሳስራቸውና ከመከፋፈል ይልቅ ወደኀብረት፣ ከመናናቅ ወደመከባበር፤ ከመጠላላት ወደፍቅር፣ ከመበላለጥ ወደእኩልነት የሚመሩበት ሕግና ሥርዓት ልዩነቶችን ተቀብሎ የዜግነት አንድነትን በማረጋገጥ ሁኔታም በአንድ ላይ የአገሩ ባለቤት ያደርጋቸዋል፡፡
የአንድ አገር ሕዝብ ስንል በአንድ በተወሰነ ጊዜ በዚያ አገር ውስጥ ያሉትን ሰዎች ድምር ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከተቆረቆረች ጀምሮ ለዚች አገር ክብርና ነፃነት የሞቱትን ሁሉ ይጨምራል፤ ወደፊትም የሚወስዱትንና የእነሱንም ልጆች ያካትታል፡፡ ከኋላ የነበረውንና አሁን የሌለውን ወደፊትም የሚወለደውንና አሁን የሌለውን አብረንና አያይዘን ካላየነው የታሪክ አካሄድንና ሕዝቡ የተሳሰረበትን ሰንሰለት ውሉን እንስታዋለን፡፡ እየሳትነውም ይመስለኛል።

"አገሮች ሁሉ መሬታቸው በተቻለ መጠን በትክክል በድንበር የተከለለ ነው: የትም ቢሆን የእያንዳንዱ አገር የድንበር ታሪክ በጦርነትና በደም የተጻፉ ነው፡፡ 3 ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዜጎች ሕይወታቸውን መስዋዕት እያደረጉ የጠበቁት መሬት ነው፡፡ የሰው ልጅ ከግለኛና ስጋት ከተሞላበት ኑሮ ወጥቶ ይነስም ይብዛ በተደራጀ ኅብረት መኖር ከጀመረ አንሥቶ የገዛ መሬቱን ከጠላትና ከወራሪዎች ለመጠበቅ ብዙ የሕይወት መስዋዕት ተከፍሎአል። የአገርን መሬት አስከብሮ የመኖሩ ታሪክ የአንድ ትውልድ ግዴታ ሳይሆን ተከታታይ ትውልዶች በየጊዜያቸው የሚወጡት ግዴታቸው ነው፡፡




2. የአገር ፍቅር

የአንድ አገር መሬት በደንብና በሕግ የተከለለ ነው፤ ድንበር አለው፡ ለጥቂት አገሮች በዚህ ድንበር የተከለለው መሬት ሺህ ዓመታት ወደኋላ ተሂዶ ተሂዶ የማይደረስበት በጣም ረጅም ታሪክ አለው፤ ለምሳሌ ግብፅ፣ ፋርስ፣ የዛሬው ኢራቅና ቻይና ኢትዮጵያም የእንደዚህ ያለ ታሪክ ባለቤቶች ናቸው። በነዚህ አገሮች ውስጥ ሁሉ ተከታታይ ትውልዶች ያደረጉትን ተጋድሎና የከፈሉትን መስዋዕትነት ለመገመት አስቸጋሪ አይደለም፡፡ እነዚህ ተከታታይ ትውልዶች በሀሳብ፣ በሥራና በእምነት ያስተላለፉት የተከማቸ ታሪክ ለአገሮቹ የህልውናቸውና የክብራቸው መሠረት ነው፡፡ የአገር ፍቅር የሚባለው የሚመነጨውም ከዚህ ይመስለኛል፡፡

የአገር ፍቅር የሚባለው : ስሜት : ከየአገሩ ታሪክ ዕድሜ ጋር የሚጠነክርና የሚላላ ይመስላል፡፡ በተለይም የተጻፈ ከሆነ የታሪክ ሽክም በከበደና በተከበረ መጠን የአገር ፍቅር ስሜት የጠነክራል የሚል አስተሳሰብ አለኝ። በአሁኑ ጊዜ ይህ ገለጻ መሠረታዊ ችግር አለበት፡፡ በዘመናችን የመመላለሻ አገልግሎቶች በየዓይነቱ ሰዎችን ከአንዱ አገር ወደሌላ አገር በተለያየ ምክንያት የሚያጓጉዙ በመሆናቸውና ሰዎችም በጥገኝነትም ሆነ ዜግነትን በመለወጥ በሌሎች አገሮች መኖር እየተለመደ በመምጣቱ የአገር ፍቅር የሚባለውን ስሜት የሚበርዙት ሌሎች ተወዳዳሪ ስሜቶች እየተፈጠሩ ነው፡፡ ስለዚህም አንዳንዴ ኃያላን አገሮች አዳዲስ አገሮችእንዲፈጠሩ ተጽእኖ እንደሚያደርጉ በቅርቡ በአውሮፓም ሆነ በአፍሪካ አይተናል፣ የኤርትራ ጉዳይ አንድ ምሳሌ ነው፡፡ ከዚያም በላይ ስለ አፍሪካ - ያልተሳካላቸው አገሮች በእንግሊዝኛ ፌይልድ ስቴትስ በሚል ርዕስ ከአሜሪካ አንድ : ሰነድ ወጥቶ ነበር፣ ዓላማው እነዚህን ያልተሳካላቸው የአፍሪካ አገሮችን በጎሣ ለመሸንሸንና ትንንሽ አገሮችን ለመፍጠር ነበር፣ በዓላማው ከአፍሪካ መሪዎች አንዱ ተስማምተዋል ተብለው የተጠቀሱት የኛው አቶ መለስ ናቸው፡፡ አፄ ገላውዴዎስ ያለውን ቢገነዘበለት አነሰ አይፈቅድ እርኢ ሙስናሁ ለሀገር አምጣነ ሀሎኩ በዛቲ ሕይወት ምድራዊት፤ ትርጉሙ በሕይወት እስካለሁ ድረስ አገር ሲጠፋ ማየትን አልፈልግም፡፡

ብዙ የአውሮፓና የሰሜንና የደቡብ : አሜሪካ አገሮች ትናንት የተፈጠሩ ናቸው ለማለት ይቻላል፤ የእነዚህ አገሮች ታሪክ በጥቂት ምዕተ ዓመታት የሚቆጠር ነው፡፡ የአገር ፍቅር ስሜታቸውም በዚያው መጠን ነው፡፡ ጭቆናና ግፍም የአገር ፍቅር ስሜትን በመቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ አሳቸው። በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች የአገራቸውን ሕይወት ከነሱ ኑሮ ጋር አቆራኝተው ይመለከቱታል። እነሱ ከደላቸውና ከተመቻቸው አገራቸውን ይወድዳሉ፤ ካልተመቻቸውና ካልደላቸው አገር የሚባል ነገር ጉዳያቸው አይደለም።

ሌሎች ደግሞ ሌላ ሚዛን ይዘው ‹አብዮታዊት እናት አገር ይላሉ፤ እናት አብዮታዊት ካልሆነች እናትነትዋን ሊክዱ የዳዳቸው ናቸው፤ ይህ ከማርክስ ፍልስፍና ጋር የሚጋጭ ነው፤ ምክንያቱም በማርከስ ፍልስፍና ህልውና ከንቃተ ኅሊና ይቀድማል፡፡ በእንደዚህ ዓነቶቹ ሰዎች አመለካከት የአገር ሕይወት በዚያ አገር ውስጥ የሚኖሩ የደላቸው ወይም አብዮተኞች የተባሉት ሰዎች ድምር ነው፤ ሌላው የእነሱ መሣሪያ ነው፤ ለእኔ ይህ አመለካከት የተዛባ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ለአገሩ የሚሞተው ሀብታሙና የደላው አይደለም፤ ትላልቅ ሹሞችም ቢሆኑ ሳይደላቸው ለአገር የሚሞቱ አሉ፤ አንድ ምሳሌ ብቻ ለመጥቀስ ደጃዝማች ባልቻ ደልቶአቸው አይደለም በኢጣልያ ላይ ተነስተው የሞቱት፡፡

የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ለአንድ ለዚያ ለሰውም ሆነ ለአገሩ ዋጋ የለውም :: ማለቱ : አይደለም፡፡ ዋጋ አለው፡፡ የእያንዳንዳችንን የግል የየቤታችንን ችግር ክበንና አጉልተን የአገር ችግር እናድርገው ለማለት ነው፤ የአገር ችግር የሁላችንም፤ የሕዝቡ በሙሉ ችግር ነው፡፡ አለዚያምየመንደሩን ችግርና የአገርን ችግር መለየት ያቅተናል፣ ይህ ስላቃተን ነው አሁን ያለንበት ማጥ ውስጥ የገባነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው ምናልባትም በሌላ አገር ታይቶ የማይታወቅ አዲስ ነገር ነው። አንደኛ፣ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ብለው ተዋግተው ኤርትራን ያስገነጠሉት ሰዎች ኤርትራን ከቅኝ አገዛዝ አላቅቀው ወደ እናት አገርዋ ወደኢትዮጵያ ለመመለስ የታገሉ፣ የሞቱና የቆሰሉ : ኢትዮጵያውያን ልጆች ናቸው። ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ያሉትንና የአባቶቻቸውን የኢትዮጵያዊነት መስዋዕትነት የካዱት፣ የረዱትና መለየቱን ያቃለሉላቸው የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን : ናቸው፡፡ ሁለቱም : ለልጆቻቸውና :: ለልጅ ልጆቻቸው የሚያወርሱትን የታሪክ ሐፍረት ለመገመት የሚያዳግት አይደለም። የዚህ የታሪክ ሐፍረት ተሸካሚ ማን ነው ትግርኛ ተናጋሪዎች በአጠቃላይ፣ ወይም

Читать полностью…
Subscribe to a channel