azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ ይገኛል።
!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሲደኒ ሼልደን እያንዳንዱ ሰው በሕይወት ጉዞ ውስጥ ሊገጥመው የሚችለውን ውጣ ውረድ እንዴት ማለፍና ከፍተኛ ስኬት ላይ ለመድረስ እንደሚቻል ያስተማረበት የበሰለ መጽሐፍ።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኣንዳንድ ጸሓፊዎች የኣሁኗን ኢትዮጵያን በፊውዳል ዘመን ክነበረችው ኣውሮፓ ጋር
በማወዳደር የዚህችን ኣገር ሥርዓተ ማኅበር hፊውዳል ሥርዓተ ማኅበር ጋር ተመሳሳይ
እንደሆነ ይጽፋሉù ግን ይህ ኣባባል ትክል ነው ወይ? የፊውዳል ሕብረተሰብ የመጀመሪያው ምልክት የመደብ ክፍፍል መኖር መሬትን መደባዊ ጥቅሞች በውርስ የሚተላለፉ መሆናቸው ነው ግን እነዚ ነገሮች በሓበሻ ውስጥ ኣይታዩም፡ በዚህች ኣገር ሹመት ስላላቸው ብቻ ማለትም በኣሁኑ ጊዜ ሥልጣን ላይ ስለሆኑ ብቻ እንደ መኳንንት የሚቆጠሩ ሰዎች ነጋዴዎች፣ ካህናት፣ መነኩሴዎች ወታደሮችና ገበሬዎች ይገኛሉ ግን እነኝ ሰዎች በሹመታቸውና በሚያከናውኑት ሥራ ይለያያሉ እንጂ ራላቸውን የቻሉና እርስ በእርስ የማይገናኙ መደቦች ኣይደሉም፡

ምርኮኞች በገፍ የሚያዙባቸው ጦርነቶች ያለማቋረጥ የሚካሄድና የገዢው መደብ ኣባላት የኣኗኗር ዘይቤ ብዙ ሠራተኞችን የሚፈልግ መሆኑ ባርነት በኣገሪቱ ውስጥ
እንዲኖር ኣድርጓል፡፡ ነገር ግን ይህ ባርነት እኛ ባርነት ብለን ከምንጠራው ነገር ጋር
የሚመሳሰለው በስም ብቻ ነው በኣሁኑ ጊዜ ባርነት በተቋም ደረጃ የለም ኣጤ ምኒልክ
በኣዋጅ ባርነትን ያጠፉ ሲሆን ባሪያ መሸጥና መግዛትም ስለተከለከለ ሲሽጡ የተገኙ
ሰዎች እጃቸው ይቆረጣል

ሓበሻን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመጠኑ ለማወዳደር ብንፈልግ ይህ ሕዝብ
የሚገለጾው በሚከተለው መሠረት ነው፡፡ እሱም እንደ ፈረንሳይ ልዩ ስጦታ ያለውና
ኣስተዋይ፣ እንደ እንግሊዝ እርምጃ የመውሰድ በሥሩ የሚገኙ, ሕዝቦችን የማስተዳደርና የመሪነት ችሎታ ያለው፣ እንደ ስፔይናዊ ኩሩ፣ እንደ ሩስያዊ ሃይማኖቱን የሚወድ ጠባየ ለስላሳና ታጋሽ፣ እንደ ይሁዳዊ የመነገድ ችሎታ ያለውና በጣም ደፋር ብልጥና ተጠራጣሪ ነው።

ከመጽሐፉ የውስጥ ገፅ የተወሰዱ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አስተሳሰብህ ላይ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጣ፣ ባነቡበከው ቅጽበት ሕይወትህን
በደስታ የሚቀይር፡፡

ኦፕራ ዊንፍ

የአሁን ጊዜ ትሩፋትን (The Power of Now) ለመቋደስና በሁለመናችን ሽቅብ
ለመመንደግ በሚደረገው ጉዞ፣ በሀሳብ የሚባዝነውን አዕምሯችንና ይኸው
እዕምሯችን የፈጠረውን የውሸት ማንነት ከበስተኋላችን አራግፈን እልፍ ማ
ግድ ይለናል።

ይህንን ተአምረኛ መጽሐፍ ገና የመጀመሪያውን ገጽ ማንበብ በጀመርን ቅፅበት የእፎይታ አየር ወደ ምንተነፍስበትና በሁለመናችን ወደ ምንመነደግበት ወደ ላዋው ከፍታ ሽቅብ ይዞን ይጓዛል፡፡ ምንም እንኳ በሁለመናችን ለመመንግ ሽቅብ የምናደርገው ጉዞ ፈታኝ ቢሆንም፣ ጉዟችንን ቀሊል ያደርግልን ዘንድ፣
ኤhሀርት ቶል ንጥር ያለ ቋንቋና፣ አንባቢ ጠያቂ ጸሐፊው ደሞ መላሽ አካሔድን ተጠቅሟል፤ ብሥራት እውነቱም አሰምሮ ተርጉሞታል፡

መጀመሪያ ከታተመባት ጊዜ ጀምሮ ድፍን ዓለምን ያነጋገረ፣ በዘመናት ከተፃ ከስንት አንድ ከሆኑት ምርጥ መጽሐፍት የአሁን ሃያልነት (The power now) አንዱ ድንቅና ሁነኛ መጽሐፍ ሲሆን፣ አንባቢዎች ላይ ሁነኛ ለውጥ
መፍጠር የሚችል ብርቱ አቅም ያለው ተአምረኛ መጽሐፍ፡፡ የአንባቢዎችን ህይወት እስከ ወዲያኛው በበጎው መቀየር የሚችል ጥንቅቅ ያለ መጽሐፍ፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21



ጊዮርጊስ ጀባና ወደ አትክልት ተራ መድረክ ዋናው መንገድ ላይ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት የሶሻሊዝም መጽሐፍቶች አግኝተናል !!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከዙላ እሰከ መቅደላ ከእንግሊዝ ጦር ጋር የተጓዘ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ የዘገበው ታሪክ፡፡
በአፄ ቴዎድሮስ የመጨረሻዋ ሰ\ት በቦታው የነበረ የአይን ምስክር፡፡

አንድ ጊዜ ተወዳጅ ሀይለኛና ገናና የነበሩትን ንጉሥ የመጨረሻ ምዕራፍ ግልፅና ጥልቅ
በሆነ ሁኔታ ያቀርባል፡፡

ከመቅደላ በፊት የነበሩ ሁኔታዎችን ያስገነዝባል፡፡
መቅደላ እንደዚህ በዝርዝር ቀርቦ ያውቅም፡፡
ስለ እፄ ቴዎድሮስ መነበብ የሚገባው ፅሁፍ፡፡

ከመፅሐፉ የተወሰደ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን ።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

Well written in a beautiful early Victorian style, it follows the amazing saga of the adventures Of an appealing, well educated young Englishman in the previously unvisited by any European Wilds of upland modern-day Ethiopia, bringing vividly to light the customs and beliefs of that Exotic land at that time. This work is a factual narrative by Maj. William Cornwallis Harris, who was sent by Queen Victoria to head a mission as the first ambassador from the UK to the KingDom of Goa in the heart of modern Ethiopia. The kings of Goa became the Emperors of Ethiopia in later years. its worth the effort for the insight into local culture of the time and its resemblance in many ways to that of the present. His style is very "Victorian," with elaborately descriptive prose. "Florid" would be a good word to describe it. After a while, however, the reader falls into the rhythm of the prose and the reading becomes easier. The writing style places the reader with in the Victorian milieu.lt is written to provide a narrative of the mission, and a somewhat analyticcal record of observation of terrain, peoples, cultures and customs encountered. He faithfully describes the mission day by day as it moves through punishing terrain, tribal battles, and variOus dangers finally to reach the highlands. He faithfully describes the peoples along the way; their appearance, their customs, their culture culminating in an in-depth look at the culture of Goa; its monarchy, its court, its towns and townspeople, its Coptic Church, and modes of dress, in sufficient detail that the reader feels he has been there in that day and age. Any student of history as well as anyone interested in African history will find this book fascinating.

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዎልትዝ ዛሬ ጧት በማይታወቅ ምክንያት ቀደም ብሎ ተስቷል። ከአልጋው ግርጌ የታየውን የተለመደ የፈረስ ራስ ቅርጽ ምንነት ለማጣራት በክርኑ ዳኸና የራስጌ መብራቱን አበራ። ድንጋጤው በመላ ሰውነቱ ህመም አሰራጨበት፡ በትልቅ መዶሻ ደረቱን የተመታ ይመስል የልብ ትርታው እንጣጥ እንጣጥ እያላ አቅለሸለሸው፡፡

     ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
            🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከመማሪያ መጽሐፍት ውጭ ያሉ መጻሕፍቶችን እንገዛለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

“እዚህ ነው ምወርደው አቁም አቁም - ኦ! ኦ! አቁም
አልኩህ… እዚህ አውርደኝ "
ይኸኔ አዲሱ አርቲስቲክ ፎቅ ደርሰናል ሴትዮዋ ልትወርድ
ስትል
አምስት ስድስት ሰባት
“በል ስሙኒህን እሳቸው ይከፍሌሀል” አለችው''
“ሌላውስ ስሙኒ?”
“የምን ሌላ 'ባክህ?
“እንዲያውም ሰባ አምስት ነበረ”
“እሱን ተወው!”
“አሁን ጭቅጭቁ ይቅርና ሀምሳ ሳንቲም እፈልጋለሁ”
“ስንት ነው ያለባቸው?” አልኩት:
“ሀምሳ ሳንቲም”
ከፈልኩላት የራሴንም ከፈልኩ እና ከመኪናው ወጣሁ::
ፂሜን ለመላጨት ወደ ፀጉር አስተካካይ ቤት አመራሁ::
… ከሰአት በኋላውን ከስህነ ጋር ነበር ያሳለፍኩት፡፡
“ሰሞኑን ብዙ ሳጠና ነበር፡፡ ዛሬ ማታ አባባ የፈቀዱልኝ
እንደሆነ ሲኒማ ትወስደኛለህ?” ብላኝ ነበር::
“በደስታ”
“የት ነው 'ምንገባው?”
የትም ጥሩ ፊልም የለም' ዝምብለን ብሄራዊ ቲያትር እንግባ"
ከሁሉም እሱ ይሻላል?"
“አይ! መሻሉንስ ኢትዮጵያ ይሻላል"
“ታዲያ ለምን ኢትዮጵያ አትወስደኝም?
ወምበሩ ይቆረቁረኛል 'ባክሽን' ብሄራዊ ግን ሶፋው…
“ቀበጥ ነህ”
“ውሸቴን ነው፡፡ ለሶፋው አይደለም"
“ታዲያ ለምንድነው?”
“ሚስጥር ነው፡፡ ለልጆች አይነገርም”
“ንገረኝ”
“እእ!” - ራሴን እያነቃነቅኩ
“እባክህን” - በፈገግታ
“እእ!”
“ተወዋ! _ ይቅር፡፡ እኔ ደሞ ካልነገርከኝ አብሬህ ሲኒማ
አልገባም”
“እሺ-ሺ! እነግርሻለሁ"
“ንገረኛ”
“ብሄራዊ የገባን እንደሆነ፣ ፎቅ ወጥተን ወደ ኋላ መጨረሻ
ተርታ ያለው ወምበር ጋ እንቀመጥና አንቺ ፊልሙን ታያለሽ”

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የቼክ ሪፐብሊኩ ተወላጅ የዚህ ተወላጅ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮችን የጎበኙ ሲሆን እ.ኤ.አ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመምጣት ከንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቀርበው የኢትዮጵያን መኰንንነት ማዕረግ ከተሾሙ በኋላ የሰሜኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ለነበሩት ራስ ካሣ ኃይሉ የጦር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡ በዚሁ ወቅት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጎን ሆነው ታግለዋል፡ መጽሐፉ ሃበሽስካ ኦዴሳ (Habešská Odyssea) የሃበሻ ጀብዱ የዚያን የገበሬጦር ጀግንነት ለመዘከር የጻፉት ነው፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ጠመንጃና ሙዚቃን ተጋበዙልኝ! ... ከአገሬው የኪን ፍልስፍና ተነስቶ፥ በ40ዎቹ አርመናውያን አመጣጥ ጎዳና ተምሞ፥ ማርሽ ኢትዮጵያ እና ማርሽ ተፈሪን ተዝቶ፥ የኬቦርክ ናልባንዲያን እና የየኔታ ዮፍታሄ ንጉሴን ፍጥጫ አውስቶ፥ በፋቼታ ኔራ ኩርባ ታጥፎ፥ መሰንቆ እንደ ጦር መሣሪያ የተቆጠረበትን አውድ አውግቶን ይነጉዳል። የሀገር ፍቅር ማኅበርን ከአመሠራረቱ ጀምሮ የነበረውን ታሪክ ለመሰነድ የሄደበት ርቀት እሚደንቅ ነው። የቀብር ቀኑን በገዛ ሙዚቃው ከታጀበለት አሰፋ አባተ፥ እስከ ሙዚቃ የዋጠው ፖለቲካ (አሊ ቢራ)፥ ከሜሪ አርምዴ ታሪክ የአበበ ፍቅር እስካናወዛት አስናቀች ወርቁ ድረስ ያሉ የሕይወት ታሪክ መድብል ብዙ የተለፋበት ሥራ መሆኑን ያሳብቃል። የተለያዩ የሙዚቃ ባንድ ታሪኮችን ማካተቱ ሲገርመን፥ ዓይነስውራን ሙዚቀኞችን ማውሳቱ ደግሞ እጅግ አስደንቆኛል። የ700 ሙዚቃዎች "ካታሎግ" ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው።

ደራሲውን እጅ ነስተናል! በንባብ ይለቅ ብለናል! በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር፥ በሀገር ፍቅር ማኅበር፥ የሙዚቃ ባንዶች ማኅበር ... ተጋግዘው መሥራት የነበረባቸውን የቤት ሥራ በአንድ ሰው ትከሻ ብቻ መሞከሩ አጃኢብ እንድንል አሰኝቶናል።

#ጠመንጃና_ሙዚቃ
#ይነገር_ጌታቸው


በመደብራችን ያገኙተል👍👍

የቴሌግራም ቻናላችን 👉👉👉 @azop78
 

  የሚፈልጉትን መፅሀፍ ለማዘዝ  @Mesay21

     የቻናላችን ተከታይ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው ።
                  🙏🙏🙏🙏🙏🙏
   ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
            📚📚📚📚📖📖

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

(ሕይወት)
ሕይወት ጭለማ ነው የምንጓዝበት
የደስታችን መብራት፤
መንገድ አሳይቶን ወዲያው የሚጠፉ
የመከራ ዝናም ችግሩ ሲያካፉ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

/ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር፤/

ልጄ ሆይ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ ሆነ ግን፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም፡

ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ፣ ሲያዝኑ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል፡፡

ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል?

የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡

ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን፤ የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡

ልጄ ሆይ፤ ሰው ምንም ብልህና አዋቂ ቢሆን በራሱ ሥራ ብቻ ራሱን ችሎ እንደማይኖር ዕወቅ:: ነገር ግን ሁሉም በየሥራው ጸንቶ እርስ በርሱ በሥራ ይፈላለጋል:: ስለዚህ ሰውን ሁሉ አክብረህ ኑር እንጂ ሰውን አትናቅ ሥራውንም አትንቀፍ::

ልጄ ሆይ: አካልህና ልብስህ ዘወትር ንጹህ ይሁን:: እጅህን ለሥራ: ዓይንህን ለማየት: ጆሮህን ለመስማት ፈጣኖች አድርግ:: አፍህን ግን በጠንካራ ልጓም ለጉመህ ያዝ:: አረጋገጥህ በዝግታ አነጋገርህ በለዘብታ ይሁን:: ያልነገሩህን አትስማ: ያልስጡህን አትቀበል: ያልጠየቁህን አትመልስ:: ሽቅርቅር አትሁን: ንብረትህ ተጠቅላላ ይሁን: ምግብና መጠጥህ በልክ ሆኖ ያው የጠዳና የጣፈጠ ይሁን::

ልጄ ሆይ ፈቃደ ሥላሴ፤ አሳብ አታብዛ፤ ወደ ፊትም ምን ነገር ይመጣ ይሆን ብለህ አትጨነቅ፤ ምንም አሳብና ጭንቀት ብታበዛ የሚሆን ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወደ ፊትም እሾማለሁ፤ እሸለማለሁ፤ ብለህ በአሳብህ ደስ አይበልህ፡፡ ለሰውም አትናገር፤ ምናልባት ከተናገርህ በኋላ ሳታገኘው የቀረህ እንደ ሆነ ታላቅ ኀፍረት ይሆንብሃልና፡፡ ወደ ፊት የሚያናድድ ሥራ አትሥራ፡፡ በገዛ እጅህ በሠራኸውና ባለፈው ሥራ አትናደድ፡፡ ልጄ ሆይ፤ ጌታ ለመሆን ትፈልግ እንደ ሆነ ጌትነት ማለት ያለ አሳብና ያለ ጭንቀት መኖር ነው፡፡ አሳብህም ሁሉ ከሞትህ በኋላ ወዲያኛው ዓለም ስለሚሆነው ስለ ነፍስህ ነገር ይሁን እንጂ በዚህ ዓለም በሥጋህ ስለሚሆነው ነገር እጅግ አትጨነቅ፡፡

   

የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
       የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉  @azopbook

             #ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነውና ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏



  ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
           🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በሀርድ ክብር የተጠረዙ ጦቢያ ዜጋና ኢትዮጵስ መጽሔቶች እጃችን ላይ አለ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ፊየዶር ሚካሂሎቪች ዶስቶቭስኪ (1821 — 1881 ) ታላቅ ሩሲያዊ ደራሲ፣ ሃያሲ ፣ አጭር ልብ ወለድ ፀሐፊ ' ጋዜጠኛ እና ፈላስፋ ነው፡፡ ለስራዎቹ የሰው ልጅ ስኑልቦና በፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ቀውሶች ውስጥ -
ብተለይም በ19ኛው ክ/ዘመን ሩስያ - ምን ይዘት እንደነበራት ያሳያል፡፡

ከ1846 — 1880 ባሉት አመታት ለአንባቢያን ያበረከተው ስራዎች - The Brother Karamazov (1879) Damons (1871) ፤ The Idiot (1868) Notes from The Underground (1864) እንዲሁም “ወንጀልና ፍርድ "በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተመለሰው ይህ መፅሐፍ Crime and Punishement (1866) ተጠቃሾች ናቸው

ዶስቶቭስኪ በፅሑፎቹ በጥልቀት ከሚዳስሳቸው ርዕሳን መካከል ኃይማኖት
ስነ - ልቦና እንደሁም ፍልስፍና ይገኙበታል የእርሱ ስራዎች ድህነትን፣ ራሰማጥፋትን፣ ማታለልን እንደሁም የስነ - ምግባር ፈተናን ይዳስሳል። Crime and Punishment ከ170 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በመላው አለም የተነበበ ስራው ነው በበርካታ አገራት የቲያትር መድረክን የተቆጣጠረወ
ይህ ድርሰቱ በ1935 ደግሞ ወደ ፊልም ተቀይሮለታል።

በስድስት ክፍሎች የሚተርከው የመጽሐፉ እውነታ አንባቢን እየሞገተ በምናብ እያከራከረ ከፍፃሜ ይደርሳል፡

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
      🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በነገራችን ላይ የአሊ በርኬ የህያወት ታሪክ በመጸሐፍ ከተዘጋጀ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡መጽሐፉን በኦሮምኛ ያሰናዳው ጋዜጠኛና ደራሲ ኢሳያስ ሆርዶፋ ሲሆን እህቱ ደግሞ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡ ኢሳያስ ሆርዶፋ በርካታ መጸሕፍትን በአፋን ኦሮሞ ያሰናዱ ሲሆን በኦሮምኛ በሚጽፉት የሬድዮ ድራማዎችም ይታወቃሉ፡፡የሚገርመው ደራሲ ኢሳያስ አሊን ከደርግ ዘመን ጀምሮ ኢንተርቪው ሰርቼዋለሁ ይላል ይሁን እንጂ ለመጽሐፉ ሽፋን የተጠቀመው ግን የሻምበል ባሻ መኮንን ከበደን ምስል ነው፡፡ሻምበል ባሻ መኮንን ከበደ አሁንም በሕይወት አሉ፡፡እኔ ከወራት በፊት የአሊ በርኬን የህይወት ታሪክ መጽሐፍ እያነበቡ ተገናኝተን አውግተናል፡፡ አስፈላጊ ከሆን ለጥቂት ሰዎች ስልካቸውን እልካለሁ፡፡ከስር የምትመለከቱት ምስል የደራሲው ነው፡፡

ከእንዳለ ጌንቦ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ማኅቶተ ምግባር ወሃይማኖት፣ መጋቤ ምሥጢር ወጥበብ፣ መፍቀሬ ትሕትና ወፍቅር፣የተባለው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዘመኑ እውነተኛውን ሕይወት የኖረ ነው፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ፀሐይ አብርተው፤ እንደጨረቃ ደምቀው፤ እንደ ከዋክብት አሸብርቀው፤ ወንጌልን በቃላቸው፣ በመጻሕፍቶቻቸው፣ በምግባራቸው ሰብከው ካለፉ ቅዱሳን ሊቃውንት አባቶች መካከል አንዱ ነው፡፡

ተወልዶ ካደገበት ሀገር ተነሥቶ ወንጌልን ዞሮ ባስተማረበት ሁሉ ምስክሮቹ የሚሆኑ የወንጌል አበርክቶዎቹ አሉ፡፡ እርሱ ያልተረጎመው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፣ ያዳሰሰው ነገረ ሃይማኖት፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ ቤተ ክርስቲያን የለም ብለን ብንጠቅስም ካገኘናቸው መካከል ከብዙ በጥቂቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ
ከመጡት መጻሕፍት መካከል የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል የተረጎመበት ድርሳኑ አንዱ
ነው፡፡

በብዙ ረቂቅና ምጡቅ ሰፊና ጥልቅ በሆኑ መጻሕፍቶቹ የምናውቀውን ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል እንዴት አድርጎ ተርጉሞት ይሆን የሚለውን
እንድናነብ ዕድሉን የሰጠን ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ባስነበበን እነኋት
ክርስትና፣ ስምንተኛው ቀን፣ የነፍስ ወግ፣ የትኅርምት ሕይወት፣ ኅብረ ወንጌል፣ ድንቅ
እውነትና በሌሎችም መጻሕፍቶቹ ስለምናውቀው “የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ” የሚለውን በሚገባ ተርጉሞ አቅርቦልናል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዮሐንስን ወንጌል የተረጎመበትን መንገድ፣ ያመሳጠረበትን
የስብከት ዘዴ ከመጽሐፉ ተረድተናል፡፡ ለምሳሌ “ቀዳሚሁ ቃል፤ መጀመሪያ ቃል ነበረ”
የሚለውን የተረጎመበትን መንገድ እያደነቅን ሳንጨርስ፣ በምዕራፍ ሁለት ስለ ቃና
ዘገሊላው ተአምር፣ ስለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ያብራራል፡፡ ቀድሞም ስለእመቤታችን ጽፎ የማይጠግበው፣ ሰብኮ የማጨርሰውን ሊቁ፤
እዚህ ላይ አገኛትና እንዴ አድርጎ እንደተረጎመው ስናነብ ዛሬም አፈወርቅ እንድንል አድጎናል፡፡

ቀጣዮቹንም ምዕራፎች የተረጎመበትን መንገድ እየገለጽን ስለማንዘልቀው ለቅዱሱ የገለጠውን ምሥጢር ለእኛም እንዲገልጥልን ጸሎቱ ትርዳን፡፡

  ከመጻሕፍት ዝግጅትና አርትዖት ክፍል

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
      🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኦሪጅናል ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
ሰዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህ መጽሐፍ የብር መዶሻ፣ የወርቅ ሚስማር፣ የዳይንድ ብሎኬት እያቀበለ
ሀብት እንድንገነባ የሚረዳ ጽሐፍ ነው!!!

ሀብትህን ማስፋፋት እና ማሳደግ ትፈልጋለህ? ይህን መጽሐፍ ማንበብ አለብህ

ትምህርት ላይ ጎበዝ አይደለህም?... በትምህርት ወድቅሃል? በፍጹም እንዳታዝን!
በዚህ መጽሐፍ ምክንያት ሕይወትህን መቀየር ትችላለህ!

ወላጅ ነህ? ልጆችህ ከስር ጀምሮ ሀብት የሚገነቡበትን ጥበብ ለማስተር ይህ መጽሐፍ ይረዳሀል።

ተቀጣሪ ሰራተኛ ነህ? ተማሪ ነህ? ነጋዴ ነህ?... ይህ መጽሐፍ ያስፈልግሃል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዘጋጅ:- መምህር ለይኩን ጸጋ
የድጓና የመጻሕፍት ሐዲሰት ትርጓሜ መምህር

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የንቡረዕድ ኤርሚያስ ከበደ መጽሐፍቶች እጃችን ላይ ይገኛሉ !!!!


ኤዞፕ መጻሕፍት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከ500 በላይ የመንጃ ፍቃድ ጥያቄዌችን የያዘ ምርጥ መጽሐፍ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኦሪጅናል ቨርዥን
1962 ዓ ም የታተመ።

በደጅ አዝማች ከበደ ተሰማ
የታሪክ ማስታወሻ !!!

አንድ ኮፒ ብቻ አለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ታህሳስ 9 ቀን 1921 ዓ.ም. ሐረር፣ መቂ ጋሪ ሙለታ ባዕት የተወለደው ህጻን አድጎ ጎልምሶ
ኢትዮጵያን እንደሚያስጠራ የአፍሪቃዊነት አተያይና የአንድነት ሀሳብን ከግብር እንዲውል
የሚያደረግ ታላቅ ዲፕሎማት ይወጣዋል ብሎ የጠረጠረ አልነበረም፡፡ ይሁንና አቶ ከተማ ይፍሩ ግን ውጣ ውረዱን አልፎ፣ ስቃይና መከራውን ተቋቁሞ የሀገር መጠሪያ ሆነ ይህ የአቶ ከተማ ታሪክ የትላንቱን የአባቶቻችንና የእናቶቻችንን ልፋትና ግረት አመልካች ተምሳሌ ነው፡ ከህይወቱ ጉዞ የተቀነጨበ አንዱን ሰበዝ - እንጎ ታሪኩ ብቻ ነው የቀረበው

የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት የነበረው ውዝግብና ገመድ ጉተታ፤ ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ
ለማድረግ የተጓበት ርቀት፣ በሀገር ውስጥ በግሉ የደረሰበት ጉንተላና ግፊያ፣ የውጭ ባዕዳን የሚያጠምዱትን ወጥመድና እንቅፋት የማለፍ ጥበቡን ታዩበታላችሁ፡ ሌሎችን ታሪካዊ ኹነቶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ላይ እንዳለ፣ በንግሰ ነገስቱ ጸሀፊነቱ ወቅትም የነበረውን ፈተና በአቶ ከተማ ታሪክ አቋራጭነት ታጤኑበታላችሁ፡

እና ያ ከጋራሙለታ የወጣው ኢትዮጵያዊ ራሱን መስዋዕት በማድረግ ባገለገላት ሀገር በግፍ
ዘብጥያ በተወረወረበት ክፉ ጊዜ በማስታወሻው ላይ (ጥር 1968 ላይ ) እንዲህ ብሎ ነበር“እውነት ትመነምናለች እንጂ አትሞትም እንደሚባለው በአለኝ አቅም ጊዜው ሁኔታውና አቅሙ በሚፈቅደው ለአገሬ ያደረጉትንና ለማድረግም የሞከርኩትን ጊዜ ወደፊት እንደሚገልጠው ስለማምን
እጽናናለሁ: በተለይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በነበርኩ ጊዜ የኢትዮጵያን የውጭ ፖለቲካ ከምን አንስቼ ምን ደረጃ ላይ እንዳደረስኩት ስራውና የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ምስክሬ ነው'' እውንም የአቶ ከተማን ስራ ጊዜ ይገልጠዋል፡ ይህ መጽሐፍም የመጀመሪያ ነው፡፡

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከገበያ ጠፍት የነበረችው የነበረችው #ሚትራሊዮን
በመደብራችን ተገኝታለች

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መጽሐፈ ድጓ
ቅዱስ ያሬድ እንደደረሰው
በሦስት ረድፍ የታተመ
በቀዳማዊ ኋይለስላሴ ዘመን የታተመ!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ጠመንጃና _ሙዚቃን_ተጋበዙልኝ!
ከአገሬው የኪን ፍልስፍና ተነስቶ፥ በ40ዎቹ አርመናውያን አመጣጥ ጎዳና ተምሞ፥ ማርሽ ኢትዮጵያ እና ማርሽ ተፈሪን ተዝቶ፥ የኬቦርክ ናልባንዲያን እና የየኔታ ዮፍታሄ ንጉሴን ፍጥጫ አውስቶ፥ በፋቼታ ኔራ ኩርባ ታጥፎ፥ መሰንቆ እንደ ጦር መሣሪያ የተቆጠረበትን አውድ አውግቶን ይነጉዳል። የሀገር ፍቅር ማኅበርን ከአመሠራረቱ ጀምሮ የነበረውን ታሪክ ለመሰነድ የሄደበት ርቀት እሚደንቅ ነው። የቀብር ቀኑን በገዛ ሙዚቃው ከታጀበለት አሰፋ አባተ፥ እስከ ሙዚቃ የዋጠው ፖለቲካ (አሊ ቢራ)፥ ከሜሪ አርምዴ ታሪክ የአበበ ፍቅር እስካናወዛት አስናቀች ወርቁ ድረስ ያሉ የሕይወት ታሪክ መድብል ብዙ የተለፋበት ሥራ መሆኑን ያሳብቃል። የተለያዩ የሙዚቃ ባንድ ታሪኮችን ማካተቱ ሲገርመን፥ ዓይነስውራን ሙዚቀኞችን ማውሳቱ ደግሞ እጅግ አስደንቆኛል። የ700 ሙዚቃዎች "ካታሎግ" ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው።

ደራሲውን እጅ ነስተናል! በንባብ ይለቅ ብለናል! በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር፥ በሀገር ፍቅር ማኅበር፥ የሙዚቃ ባንዶች ማኅበር ... ተጋግዘው መሥራት የነበረባቸውን የቤት ሥራ በአንድ ሰው ትከሻ ብቻ መሞከሩ አጃኢብ እንድንል አሰኝቶናል።

📖#ጠመንጃና_ሙዚቃ
✍#ይነገር_ጌታቸው

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ሐምሌ 8፣ 1914 
#ኒው ዮርክ 

   ውድ ሜሪ አንቺ እጅግ የበዛ ሰዎችን የመረዳት መክሊት የተሰጠሽ ሰው ነሽ። ሕይወትን አዳይ ነሽ ። አንቺ ለመጋራት ሳይሆን ሕይወቱን ለማበልጸግ የሆነን ሰው እንደሚወዳጅ ታላቅ መልዓክ ነሽ። በኑረት ዘመኔ ከአንቺ ጋር መተዋወቄ ከምልዓተ ዓለሙ ተፈጥሯዊ ስልተ ምትና ስልተ ስሪት ውጪ የሆነ አስደናቂ ተዓምር ነው። 
     "ዘማድማን" በተሰኘ መጽሐፌ እንደገለጽኩት የሚረዱን ሰዎች  ከሕይወታችን ውስጥ የሆነውን ነገር ይቆጣጠሩብናል። አንቺ ጋ ይሄ  የለም። የአንቺ እኔን መረዳት ከማውቃቸው ሁሉ በተለየ ነጻነትን  የሚያጎናጽፍ ሰላማዊ ነው። ባለፈው የመጨረሻ ጉብኝትሽ ልቤን በመዳፍሽ ይዘሽ ከላዩዋ ላይ ነቁጥ የምታክል ጥቁር ነገር አገኘሽ። 
በዚያችው ቅጽበት ጥቁሯ ነጥብ ለዘለዓለም ከልቤ ላይ ተፋቀች እኔም ሙሉ ለሙሉ ከእሥራቴ ነጻ ወጣሁ። 

   ይሄው አሁን ደግሞ የተራራ ላይ ብህትውና ላይ ነሽ። በበኩሌ በረቂቅ፣ ስውር፣ ውብ መሬቶች ላይ አርምሞን ከመለማመድ በላይ የሚያስደስት ምንም ነገር እንደሌለ አምናለሁ። ሆኖም ተወዳጄ ሆይ ምልዓቱን Uሰሳን የተራበች ነፍስሽ በአንድ ሰሞን ጀብድ ብቻ  እንደማትረካ ኣውቃለሁና አጉል መዳፈርን ተጠንቀቁ። ምክንያቱም  ለዳግም የUሰሳ ጉዞ ወደ ተራራ መውጣት ትችይ ዘንድ ደኅንነትሽ  መረጋገጥ አለበት። ቤቴ በላክሻቸው ‹አሪቲና ጠጅሳር መልካም መዓዛ ታውዶልሻል። ስለላክሽልኝ እግዚአብሔር ይባርክሽ። 
   

የቴሌግራም ቻናላችን👉👉👉 @azop78
       የቴሌግራም ጉሩፓችን👉👉👉  @azopbook

             #ማንኛውንም መፅሐፍ ለማዘዝ @Mesay21

   የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነውና ለወዳጅ ዘመደዎት ሊንካችንን  ያጋሩት።

    ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
         🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…
Subscribe to a channel