azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ መፅሐፍ

#እሰሩኝ!
"እሰሩኝ" የሚለው ጥቂት ቢሆንም "ፍቱኝ" ስላለ ሚፈታ ግን ማንም የለም።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ዛሬ_የት_እንዳላችሁ_አትጨነቁ!

"... እያንዳንዱ ሳይንቲስት የሆነ ቀን ላይ የሚያለቅስ ህጻን ልጅ ነበር፤ እያንዳንዱ ታላቅ ኪነ ሕንፃም የሆነ ቀን ላይ ባዶ ካርታ ብቻ ነበር። 

ዛሬ የት እንዳላችሁ መጨነቁ አስፈላጊ አይደለም ነገር ግን ነገ የት እንደምትደርሱ ማለምና ማስኬድ ላይ ነው ትልቁ ቁም ነገር ያለው።

ልብ በሉ አልበርት አንስታይን ሲወለድ ከንፅፅር ፅንሰ ሀሳብ ጋር አልተወለደም፤ አይዛክ ኒውተንም የእንቅስቃሴ ህጎቹን በእናቱ ማህፀን ውስጥ ቀምሮ አልወጣም፤

ዱባይ ውስጥ የሚገኘው ስምንት መቶ ሠላሳ ሜትር ገደማ የሚረዝመው “ቡርጅ ካሊፋ” የተሰኘው የዓለማችን ረዥሙ ኪነ ህንፃም ከሆነ ጊዜ በፊት ሕንፃ ሳይሆን ባዶ ካርታ ብቻ ነበር።

ሁሉም ነገር ከባዶ ነው የሚጀምረው።

ስለዚህ እናንተም በሙሉ ተስፋ ከጣራችሁ እና ዓላማችሁን ለማሳካት ቁርጠኛ ከሆናችሁ ከምንም እና ከየትም ተነስታችሁ የስኬትን ጫፍ መቆናጠጥ ትችላላችሁ” በማለት ሰሎሞን ተሰናብቷቸው ከክፍሉ ራመድ ራመድ ብሎ ወጣ።

#ከስሙር_መጽሐፍ_የተቀነጨበ

ከአንድ አብራክ የወጡ በደራሲ #በረደድ ገዳሙ የተጻፉ ሶስት ምርጥ መጽሐፍት

#ሉባር
#ሰርዲዮን እንዲሁም አዲሱ መጽሐፉ
#ስሙር

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በኔ ግምት ለታሪክ ለባህልና ለቋንቋ ትኩረት የሚሰጥ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ምን_ክፍት
ደስታ መቼ ጠፉ
ገንዘብ መች ቸገረ
ህሊናውን በሆድ ቀይሮ ላደረ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በሀርድ ክብር የተጠረዙ ጦቢያ ዜጋና ኢትዮጵስ መጽሔቶች እጃችን ላይ አለ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ፊየዶር ሚካሂሎቪች ዶስቶቭስኪ (1821 — 1881 ) ታላቅ ሩሲያዊ ደራሲ፣ ሃያሲ ፣ አጭር ልብ ወለድ ፀሐፊ ' ጋዜጠኛ እና ፈላስፋ ነው፡፡ ለስራዎቹ የሰው ልጅ ስኑልቦና በፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ቀውሶች ውስጥ -
ብተለይም በ19ኛው ክ/ዘመን ሩስያ - ምን ይዘት እንደነበራት ያሳያል፡፡

ከ1846 — 1880 ባሉት አመታት ለአንባቢያን ያበረከተው ስራዎች - The Brother Karamazov (1879) Damons (1871) ፤ The Idiot (1868) Notes from The Underground (1864) እንዲሁም “ወንጀልና ፍርድ "በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተመለሰው ይህ መፅሐፍ Crime and Punishement (1866) ተጠቃሾች ናቸው

ዶስቶቭስኪ በፅሑፎቹ በጥልቀት ከሚዳስሳቸው ርዕሳን መካከል ኃይማኖት
ስነ - ልቦና እንደሁም ፍልስፍና ይገኙበታል የእርሱ ስራዎች ድህነትን፣ ራሰማጥፋትን፣ ማታለልን እንደሁም የስነ - ምግባር ፈተናን ይዳስሳል። Crime and Punishment ከ170 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በመላው አለም የተነበበ ስራው ነው በበርካታ አገራት የቲያትር መድረክን የተቆጣጠረወ
ይህ ድርሰቱ በ1935 ደግሞ ወደ ፊልም ተቀይሮለታል።

በስድስት ክፍሎች የሚተርከው የመጽሐፉ እውነታ አንባቢን እየሞገተ በምናብ እያከራከረ ከፍፃሜ ይደርሳል፡

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
      🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በነገራችን ላይ የአሊ በርኬ የህያወት ታሪክ በመጸሐፍ ከተዘጋጀ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡መጽሐፉን በኦሮምኛ ያሰናዳው ጋዜጠኛና ደራሲ ኢሳያስ ሆርዶፋ ሲሆን እህቱ ደግሞ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡ ኢሳያስ ሆርዶፋ በርካታ መጸሕፍትን በአፋን ኦሮሞ ያሰናዱ ሲሆን በኦሮምኛ በሚጽፉት የሬድዮ ድራማዎችም ይታወቃሉ፡፡የሚገርመው ደራሲ ኢሳያስ አሊን ከደርግ ዘመን ጀምሮ ኢንተርቪው ሰርቼዋለሁ ይላል ይሁን እንጂ ለመጽሐፉ ሽፋን የተጠቀመው ግን የሻምበል ባሻ መኮንን ከበደን ምስል ነው፡፡ሻምበል ባሻ መኮንን ከበደ አሁንም በሕይወት አሉ፡፡እኔ ከወራት በፊት የአሊ በርኬን የህይወት ታሪክ መጽሐፍ እያነበቡ ተገናኝተን አውግተናል፡፡ አስፈላጊ ከሆን ለጥቂት ሰዎች ስልካቸውን እልካለሁ፡፡ከስር የምትመለከቱት ምስል የደራሲው ነው፡፡

ከእንዳለ ጌንቦ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ማኅቶተ ምግባር ወሃይማኖት፣ መጋቤ ምሥጢር ወጥበብ፣ መፍቀሬ ትሕትና ወፍቅር፣የተባለው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዘመኑ እውነተኛውን ሕይወት የኖረ ነው፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ፀሐይ አብርተው፤ እንደጨረቃ ደምቀው፤ እንደ ከዋክብት አሸብርቀው፤ ወንጌልን በቃላቸው፣ በመጻሕፍቶቻቸው፣ በምግባራቸው ሰብከው ካለፉ ቅዱሳን ሊቃውንት አባቶች መካከል አንዱ ነው፡፡

ተወልዶ ካደገበት ሀገር ተነሥቶ ወንጌልን ዞሮ ባስተማረበት ሁሉ ምስክሮቹ የሚሆኑ የወንጌል አበርክቶዎቹ አሉ፡፡ እርሱ ያልተረጎመው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፣ ያዳሰሰው ነገረ ሃይማኖት፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ ቤተ ክርስቲያን የለም ብለን ብንጠቅስም ካገኘናቸው መካከል ከብዙ በጥቂቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ
ከመጡት መጻሕፍት መካከል የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል የተረጎመበት ድርሳኑ አንዱ
ነው፡፡

በብዙ ረቂቅና ምጡቅ ሰፊና ጥልቅ በሆኑ መጻሕፍቶቹ የምናውቀውን ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል እንዴት አድርጎ ተርጉሞት ይሆን የሚለውን
እንድናነብ ዕድሉን የሰጠን ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ባስነበበን እነኋት
ክርስትና፣ ስምንተኛው ቀን፣ የነፍስ ወግ፣ የትኅርምት ሕይወት፣ ኅብረ ወንጌል፣ ድንቅ
እውነትና በሌሎችም መጻሕፍቶቹ ስለምናውቀው “የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ” የሚለውን በሚገባ ተርጉሞ አቅርቦልናል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዮሐንስን ወንጌል የተረጎመበትን መንገድ፣ ያመሳጠረበትን
የስብከት ዘዴ ከመጽሐፉ ተረድተናል፡፡ ለምሳሌ “ቀዳሚሁ ቃል፤ መጀመሪያ ቃል ነበረ”
የሚለውን የተረጎመበትን መንገድ እያደነቅን ሳንጨርስ፣ በምዕራፍ ሁለት ስለ ቃና
ዘገሊላው ተአምር፣ ስለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ያብራራል፡፡ ቀድሞም ስለእመቤታችን ጽፎ የማይጠግበው፣ ሰብኮ የማጨርሰውን ሊቁ፤
እዚህ ላይ አገኛትና እንዴ አድርጎ እንደተረጎመው ስናነብ ዛሬም አፈወርቅ እንድንል አድጎናል፡፡

ቀጣዮቹንም ምዕራፎች የተረጎመበትን መንገድ እየገለጽን ስለማንዘልቀው ለቅዱሱ የገለጠውን ምሥጢር ለእኛም እንዲገልጥልን ጸሎቱ ትርዳን፡፡

  ከመጻሕፍት ዝግጅትና አርትዖት ክፍል

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
      🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኦሪጅናል ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
ሰዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህ መጽሐፍ የብር መዶሻ፣ የወርቅ ሚስማር፣ የዳይንድ ብሎኬት እያቀበለ
ሀብት እንድንገነባ የሚረዳ ጽሐፍ ነው!!!

ሀብትህን ማስፋፋት እና ማሳደግ ትፈልጋለህ? ይህን መጽሐፍ ማንበብ አለብህ

ትምህርት ላይ ጎበዝ አይደለህም?... በትምህርት ወድቅሃል? በፍጹም እንዳታዝን!
በዚህ መጽሐፍ ምክንያት ሕይወትህን መቀየር ትችላለህ!

ወላጅ ነህ? ልጆችህ ከስር ጀምሮ ሀብት የሚገነቡበትን ጥበብ ለማስተር ይህ መጽሐፍ ይረዳሀል።

ተቀጣሪ ሰራተኛ ነህ? ተማሪ ነህ? ነጋዴ ነህ?... ይህ መጽሐፍ ያስፈልግሃል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዘጋጅ:- መምህር ለይኩን ጸጋ
የድጓና የመጻሕፍት ሐዲሰት ትርጓሜ መምህር

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የንቡረዕድ ኤርሚያስ ከበደ መጽሐፍቶች እጃችን ላይ ይገኛሉ !!!!


ኤዞፕ መጻሕፍት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከ500 በላይ የመንጃ ፍቃድ ጥያቄዌችን የያዘ ምርጥ መጽሐፍ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኦሪጅናል ቨርዥን
1962 ዓ ም የታተመ።

በደጅ አዝማች ከበደ ተሰማ
የታሪክ ማስታወሻ !!!

አንድ ኮፒ ብቻ አለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ታህሳስ 9 ቀን 1921 ዓ.ም. ሐረር፣ መቂ ጋሪ ሙለታ ባዕት የተወለደው ህጻን አድጎ ጎልምሶ
ኢትዮጵያን እንደሚያስጠራ የአፍሪቃዊነት አተያይና የአንድነት ሀሳብን ከግብር እንዲውል
የሚያደረግ ታላቅ ዲፕሎማት ይወጣዋል ብሎ የጠረጠረ አልነበረም፡፡ ይሁንና አቶ ከተማ ይፍሩ ግን ውጣ ውረዱን አልፎ፣ ስቃይና መከራውን ተቋቁሞ የሀገር መጠሪያ ሆነ ይህ የአቶ ከተማ ታሪክ የትላንቱን የአባቶቻችንና የእናቶቻችንን ልፋትና ግረት አመልካች ተምሳሌ ነው፡ ከህይወቱ ጉዞ የተቀነጨበ አንዱን ሰበዝ - እንጎ ታሪኩ ብቻ ነው የቀረበው

የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት የነበረው ውዝግብና ገመድ ጉተታ፤ ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ
ለማድረግ የተጓበት ርቀት፣ በሀገር ውስጥ በግሉ የደረሰበት ጉንተላና ግፊያ፣ የውጭ ባዕዳን የሚያጠምዱትን ወጥመድና እንቅፋት የማለፍ ጥበቡን ታዩበታላችሁ፡ ሌሎችን ታሪካዊ ኹነቶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ላይ እንዳለ፣ በንግሰ ነገስቱ ጸሀፊነቱ ወቅትም የነበረውን ፈተና በአቶ ከተማ ታሪክ አቋራጭነት ታጤኑበታላችሁ፡

እና ያ ከጋራሙለታ የወጣው ኢትዮጵያዊ ራሱን መስዋዕት በማድረግ ባገለገላት ሀገር በግፍ
ዘብጥያ በተወረወረበት ክፉ ጊዜ በማስታወሻው ላይ (ጥር 1968 ላይ ) እንዲህ ብሎ ነበር“እውነት ትመነምናለች እንጂ አትሞትም እንደሚባለው በአለኝ አቅም ጊዜው ሁኔታውና አቅሙ በሚፈቅደው ለአገሬ ያደረጉትንና ለማድረግም የሞከርኩትን ጊዜ ወደፊት እንደሚገልጠው ስለማምን
እጽናናለሁ: በተለይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በነበርኩ ጊዜ የኢትዮጵያን የውጭ ፖለቲካ ከምን አንስቼ ምን ደረጃ ላይ እንዳደረስኩት ስራውና የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ምስክሬ ነው'' እውንም የአቶ ከተማን ስራ ጊዜ ይገልጠዋል፡ ይህ መጽሐፍም የመጀመሪያ ነው፡፡

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ወንጌል_ቅዱስ

ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ

ኢየሱስ ክርስቶስ


ግብረ ሐዋሪያት
ወመልእክተ ሐዋርያት
በልሳነ ግእዝ ወአማርኛ

የአስመረ እትም

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ማሰብ_ዋጋ_ይኖረው_ይሆን?
የአንድ መጽሐፍ ዋጋ የወረቀቱ፣ የቀለሙና የማሳተሚያው ዋጋ እንጂ የሐሳቦች ዋጋ አይደለም። ለሐሳቦች ዋጋ ቢሰጣቸው ዋጋቸው እጅግ በጣም ውድ ስለሚሆን ሊገዙም ሆነ ወይም ሊሸጡ አይችሉም፤ ሊሰጡ ብቻ እንጂ።
ሓሳቦች ከአንዱ ሰው አእምሮ ወደ ሌላው ሰው አእምሮ እና ከአንዱ ሰው ልብ ወደ ሌላ ሰው ልብ ብርሃን የሚያበሩ ሻማዎች ናቸው። ይህን የብርሃን ጮራቸውን በሚወዷቸው እና ሂስ በሚሰጧቸው ሰዎች ላይ ይፈነጥቃሉ።
ስለሆነም የአንድን መጽሐፍ ዋጋ ስትመለከቱ ይህ ዋጋ የሐሳቦችን ዋጋ የሚጨምር አድርጋችሁ አታስቡ፤ መጽሐፉ የተፈለገውን ያህል ዋጋ ቢወጣ ሊገዛው የማይችለው አንድ አሳብ በውስጡ አቅፏልና።
ከዋጋው አንጻር አትራፊ ዋጋ ያለው ወደሚመስለው መጽሐፍ ስንመጣም ደራሲው ወይም ሌሎች ሰዎች ስለፍላጎታቸው ከሚያወጡት ወጭ በስተቀር ትርፉ ምንድን ነው? ይህ የሐሳቦች ዋጋ አይደለም።
የጥሩ መጽሐፍ ጥቅም የሚወሰነው በውስጡ በሚገኙት ሐሳቦች ብቻ አይደለም። በአንባቢው አእምሮና ልብ ውስጥ የሚያመነጫቸው ሌሎች ሐሳቦች ጭምር እንጂ። ታዲያ ለነዚህ የሚመነጩ ሐሳቦችና ስሜቶች ሊተመንላቸው የሚችል ዋጋ ይኖራል ብላችሁ ታስባላችሁ? እነርሱ ከዋጋ በላይ ናቸው!!!
                የሕይወት ልምድ
        #አዘጋጅ አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ
        #ትርጉም አያሌው ዘ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"አውቀሃል አይደል?"
"ምኑን?"
"የማታውን ተኩስ ነዋ!....እናቴ የጠጅ በርሜል ውስጥ ልትከተኝ ምንም አልቀራት።"

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ ይገኛል።
!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሲደኒ ሼልደን እያንዳንዱ ሰው በሕይወት ጉዞ ውስጥ ሊገጥመው የሚችለውን ውጣ ውረድ እንዴት ማለፍና ከፍተኛ ስኬት ላይ ለመድረስ እንደሚቻል ያስተማረበት የበሰለ መጽሐፍ።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኣንዳንድ ጸሓፊዎች የኣሁኗን ኢትዮጵያን በፊውዳል ዘመን ክነበረችው ኣውሮፓ ጋር
በማወዳደር የዚህችን ኣገር ሥርዓተ ማኅበር hፊውዳል ሥርዓተ ማኅበር ጋር ተመሳሳይ
እንደሆነ ይጽፋሉù ግን ይህ ኣባባል ትክል ነው ወይ? የፊውዳል ሕብረተሰብ የመጀመሪያው ምልክት የመደብ ክፍፍል መኖር መሬትን መደባዊ ጥቅሞች በውርስ የሚተላለፉ መሆናቸው ነው ግን እነዚ ነገሮች በሓበሻ ውስጥ ኣይታዩም፡ በዚህች ኣገር ሹመት ስላላቸው ብቻ ማለትም በኣሁኑ ጊዜ ሥልጣን ላይ ስለሆኑ ብቻ እንደ መኳንንት የሚቆጠሩ ሰዎች ነጋዴዎች፣ ካህናት፣ መነኩሴዎች ወታደሮችና ገበሬዎች ይገኛሉ ግን እነኝ ሰዎች በሹመታቸውና በሚያከናውኑት ሥራ ይለያያሉ እንጂ ራላቸውን የቻሉና እርስ በእርስ የማይገናኙ መደቦች ኣይደሉም፡

ምርኮኞች በገፍ የሚያዙባቸው ጦርነቶች ያለማቋረጥ የሚካሄድና የገዢው መደብ ኣባላት የኣኗኗር ዘይቤ ብዙ ሠራተኞችን የሚፈልግ መሆኑ ባርነት በኣገሪቱ ውስጥ
እንዲኖር ኣድርጓል፡፡ ነገር ግን ይህ ባርነት እኛ ባርነት ብለን ከምንጠራው ነገር ጋር
የሚመሳሰለው በስም ብቻ ነው በኣሁኑ ጊዜ ባርነት በተቋም ደረጃ የለም ኣጤ ምኒልክ
በኣዋጅ ባርነትን ያጠፉ ሲሆን ባሪያ መሸጥና መግዛትም ስለተከለከለ ሲሽጡ የተገኙ
ሰዎች እጃቸው ይቆረጣል

ሓበሻን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመጠኑ ለማወዳደር ብንፈልግ ይህ ሕዝብ
የሚገለጾው በሚከተለው መሠረት ነው፡፡ እሱም እንደ ፈረንሳይ ልዩ ስጦታ ያለውና
ኣስተዋይ፣ እንደ እንግሊዝ እርምጃ የመውሰድ በሥሩ የሚገኙ, ሕዝቦችን የማስተዳደርና የመሪነት ችሎታ ያለው፣ እንደ ስፔይናዊ ኩሩ፣ እንደ ሩስያዊ ሃይማኖቱን የሚወድ ጠባየ ለስላሳና ታጋሽ፣ እንደ ይሁዳዊ የመነገድ ችሎታ ያለውና በጣም ደፋር ብልጥና ተጠራጣሪ ነው።

ከመጽሐፉ የውስጥ ገፅ የተወሰዱ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አስተሳሰብህ ላይ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጣ፣ ባነቡበከው ቅጽበት ሕይወትህን
በደስታ የሚቀይር፡፡

ኦፕራ ዊንፍ

የአሁን ጊዜ ትሩፋትን (The Power of Now) ለመቋደስና በሁለመናችን ሽቅብ
ለመመንደግ በሚደረገው ጉዞ፣ በሀሳብ የሚባዝነውን አዕምሯችንና ይኸው
እዕምሯችን የፈጠረውን የውሸት ማንነት ከበስተኋላችን አራግፈን እልፍ ማ
ግድ ይለናል።

ይህንን ተአምረኛ መጽሐፍ ገና የመጀመሪያውን ገጽ ማንበብ በጀመርን ቅፅበት የእፎይታ አየር ወደ ምንተነፍስበትና በሁለመናችን ወደ ምንመነደግበት ወደ ላዋው ከፍታ ሽቅብ ይዞን ይጓዛል፡፡ ምንም እንኳ በሁለመናችን ለመመንግ ሽቅብ የምናደርገው ጉዞ ፈታኝ ቢሆንም፣ ጉዟችንን ቀሊል ያደርግልን ዘንድ፣
ኤhሀርት ቶል ንጥር ያለ ቋንቋና፣ አንባቢ ጠያቂ ጸሐፊው ደሞ መላሽ አካሔድን ተጠቅሟል፤ ብሥራት እውነቱም አሰምሮ ተርጉሞታል፡

መጀመሪያ ከታተመባት ጊዜ ጀምሮ ድፍን ዓለምን ያነጋገረ፣ በዘመናት ከተፃ ከስንት አንድ ከሆኑት ምርጥ መጽሐፍት የአሁን ሃያልነት (The power now) አንዱ ድንቅና ሁነኛ መጽሐፍ ሲሆን፣ አንባቢዎች ላይ ሁነኛ ለውጥ
መፍጠር የሚችል ብርቱ አቅም ያለው ተአምረኛ መጽሐፍ፡፡ የአንባቢዎችን ህይወት እስከ ወዲያኛው በበጎው መቀየር የሚችል ጥንቅቅ ያለ መጽሐፍ፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21



ጊዮርጊስ ጀባና ወደ አትክልት ተራ መድረክ ዋናው መንገድ ላይ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት የሶሻሊዝም መጽሐፍቶች አግኝተናል !!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከዙላ እሰከ መቅደላ ከእንግሊዝ ጦር ጋር የተጓዘ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ የዘገበው ታሪክ፡፡
በአፄ ቴዎድሮስ የመጨረሻዋ ሰ\ት በቦታው የነበረ የአይን ምስክር፡፡

አንድ ጊዜ ተወዳጅ ሀይለኛና ገናና የነበሩትን ንጉሥ የመጨረሻ ምዕራፍ ግልፅና ጥልቅ
በሆነ ሁኔታ ያቀርባል፡፡

ከመቅደላ በፊት የነበሩ ሁኔታዎችን ያስገነዝባል፡፡
መቅደላ እንደዚህ በዝርዝር ቀርቦ ያውቅም፡፡
ስለ እፄ ቴዎድሮስ መነበብ የሚገባው ፅሁፍ፡፡

ከመፅሐፉ የተወሰደ

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን ።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

Well written in a beautiful early Victorian style, it follows the amazing saga of the adventures Of an appealing, well educated young Englishman in the previously unvisited by any European Wilds of upland modern-day Ethiopia, bringing vividly to light the customs and beliefs of that Exotic land at that time. This work is a factual narrative by Maj. William Cornwallis Harris, who was sent by Queen Victoria to head a mission as the first ambassador from the UK to the KingDom of Goa in the heart of modern Ethiopia. The kings of Goa became the Emperors of Ethiopia in later years. its worth the effort for the insight into local culture of the time and its resemblance in many ways to that of the present. His style is very "Victorian," with elaborately descriptive prose. "Florid" would be a good word to describe it. After a while, however, the reader falls into the rhythm of the prose and the reading becomes easier. The writing style places the reader with in the Victorian milieu.lt is written to provide a narrative of the mission, and a somewhat analyticcal record of observation of terrain, peoples, cultures and customs encountered. He faithfully describes the mission day by day as it moves through punishing terrain, tribal battles, and variOus dangers finally to reach the highlands. He faithfully describes the peoples along the way; their appearance, their customs, their culture culminating in an in-depth look at the culture of Goa; its monarchy, its court, its towns and townspeople, its Coptic Church, and modes of dress, in sufficient detail that the reader feels he has been there in that day and age. Any student of history as well as anyone interested in African history will find this book fascinating.

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዎልትዝ ዛሬ ጧት በማይታወቅ ምክንያት ቀደም ብሎ ተስቷል። ከአልጋው ግርጌ የታየውን የተለመደ የፈረስ ራስ ቅርጽ ምንነት ለማጣራት በክርኑ ዳኸና የራስጌ መብራቱን አበራ። ድንጋጤው በመላ ሰውነቱ ህመም አሰራጨበት፡ በትልቅ መዶሻ ደረቱን የተመታ ይመስል የልብ ትርታው እንጣጥ እንጣጥ እያላ አቅለሸለሸው፡፡

     ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
            🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከመማሪያ መጽሐፍት ውጭ ያሉ መጻሕፍቶችን እንገዛለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

“እዚህ ነው ምወርደው አቁም አቁም - ኦ! ኦ! አቁም
አልኩህ… እዚህ አውርደኝ "
ይኸኔ አዲሱ አርቲስቲክ ፎቅ ደርሰናል ሴትዮዋ ልትወርድ
ስትል
አምስት ስድስት ሰባት
“በል ስሙኒህን እሳቸው ይከፍሌሀል” አለችው''
“ሌላውስ ስሙኒ?”
“የምን ሌላ 'ባክህ?
“እንዲያውም ሰባ አምስት ነበረ”
“እሱን ተወው!”
“አሁን ጭቅጭቁ ይቅርና ሀምሳ ሳንቲም እፈልጋለሁ”
“ስንት ነው ያለባቸው?” አልኩት:
“ሀምሳ ሳንቲም”
ከፈልኩላት የራሴንም ከፈልኩ እና ከመኪናው ወጣሁ::
ፂሜን ለመላጨት ወደ ፀጉር አስተካካይ ቤት አመራሁ::
… ከሰአት በኋላውን ከስህነ ጋር ነበር ያሳለፍኩት፡፡
“ሰሞኑን ብዙ ሳጠና ነበር፡፡ ዛሬ ማታ አባባ የፈቀዱልኝ
እንደሆነ ሲኒማ ትወስደኛለህ?” ብላኝ ነበር::
“በደስታ”
“የት ነው 'ምንገባው?”
የትም ጥሩ ፊልም የለም' ዝምብለን ብሄራዊ ቲያትር እንግባ"
ከሁሉም እሱ ይሻላል?"
“አይ! መሻሉንስ ኢትዮጵያ ይሻላል"
“ታዲያ ለምን ኢትዮጵያ አትወስደኝም?
ወምበሩ ይቆረቁረኛል 'ባክሽን' ብሄራዊ ግን ሶፋው…
“ቀበጥ ነህ”
“ውሸቴን ነው፡፡ ለሶፋው አይደለም"
“ታዲያ ለምንድነው?”
“ሚስጥር ነው፡፡ ለልጆች አይነገርም”
“ንገረኝ”
“እእ!” - ራሴን እያነቃነቅኩ
“እባክህን” - በፈገግታ
“እእ!”
“ተወዋ! _ ይቅር፡፡ እኔ ደሞ ካልነገርከኝ አብሬህ ሲኒማ
አልገባም”
“እሺ-ሺ! እነግርሻለሁ"
“ንገረኛ”
“ብሄራዊ የገባን እንደሆነ፣ ፎቅ ወጥተን ወደ ኋላ መጨረሻ
ተርታ ያለው ወምበር ጋ እንቀመጥና አንቺ ፊልሙን ታያለሽ”

ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የቼክ ሪፐብሊኩ ተወላጅ የዚህ ተወላጅ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮችን የጎበኙ ሲሆን እ.ኤ.አ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመምጣት ከንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቀርበው የኢትዮጵያን መኰንንነት ማዕረግ ከተሾሙ በኋላ የሰሜኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ለነበሩት ራስ ካሣ ኃይሉ የጦር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡ በዚሁ ወቅት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጎን ሆነው ታግለዋል፡ መጽሐፉ ሃበሽስካ ኦዴሳ (Habešská Odyssea) የሃበሻ ጀብዱ የዚያን የገበሬጦር ጀግንነት ለመዘከር የጻፉት ነው፡፡

Читать полностью…
Subscribe to a channel