እውነትም “ጠቢበ ጠቢባን”!
===+++===
ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው በግሩም ኹኔታ ተርጉሞ ያሳተመውን “ጠቢበ ጠቢባን” መጽሐፍ ፈርሞ ልኮልኝ አነበብኩት። ከገመትኩትም ከጠበኩትም በላይ ሆኖ አገኘሁት። ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም የሠራው ከትርጉምም በላይ ነው። (ስለ ሥራው ያለኝን ምልከታ ከታች በመጠኑ አነሳለሁ፤) በጣም የደነቀኝ ነገር ቅድሚያ ስለ መጽሐፉ ሕትመት ጥቂት ላንሣ።
የመጽሐፉ ጥራዙ የተመጠነ፤ መጠኑ መካከለኛ፣ ባለ ሙሉ ቀለም፣ ወረቀቱ ብራና አከል እና መሰል ነው። ሲገልጡት ለዓይን ተስማሚ መሆኑ አንባቢን በግድ ይጋብዛል። የሽፋን ገጹ መስሕብነት አለው፣ የውስጥ ገጾቹ ሐረጋት ጥበብ ልዩ ነው። በዘመናዊ ሕትመት ያልተለመደውን ስመ አምላክን እንዲሁም አርዕስቶችን በቀይ ቀለም በወጥነት ማስቀመጥ ምን ያህል አድካሚ ሊሆን እንደሚችል በበተለይ በሥራው ያለፈ ሰው የሚረዳው ነው። እንኳን ይዘቱ (ውስጡ) አምሮ ተሠርቶ ይሄ በራሱ ትልቅ ምሥጋና የሚያሻው ነውና ወንድማችን ኤፍሬም የኔሰው ና ምሥጋናህን ውሰድ። ማተሚያ ቤቱም ሊመሠገን ይገባዋል።
ከወራት በፊት “ጠቢበ ጠቢባንን እየተረጎምኩ ነው” ብሎ ዲ/ኤፍሬም ሲጽፍልኝ ደስታዬ ብዙ ነበር፤ አሁን አልቆ ሳየው ከመደሰቴ የተነሣ ይህን የመሰለ፣ ጥንቅቅ ያለ ሥራ ነፍስ ሔር ፕ/ር ጌታቸው በሕይወት በኖሩና በመረቁት ብዬ ከልቤ ተመኘሁ። የትርጉም ሥራ ከባድ ጥንቃቄን የሚፈልግ እና በኮሌጅ ደረጃ ራሱን የቻለ ትምህርትም የሚሰጥበት የሙያ ዘርፍ ነው። የመገኛ ቋንቋውን እና ተቀባይ ቋንቋውን ማውቅ ብቻ በቂ አይደለም። እኔ እንደተመለከትኩት ከሆነ ዲያቆን ኤፍሬም ይህን “ጠቢበ ጠቢባን” መጽሐፍ ተረጎመው ብቻ ሳይሆን አመሠጠረው፣ ተነተነው፣ አብራራው እና የመጽሐፉን ክብር በተገቢ መልኩ ገለጠው ቢባል ማጋነን ሊሆን አይችልም። እንዲህ ያልኩበትን በሦስት ነጥብ ላሥረዳ፦
አንደኛ የተስተካከለ ትርጉም ነው፦
የመልክእ ምሥጋናን መተርጎም እንደሌሎች ጽሑፎች አይደለም። ይልቁንም ደግሞ መልክኡ በተዘጋጀበት ጥበብ በሥነ ግጥም ሲቀርብ ለጥንቱ የተጠጋ ይሆናል። በዚህ ረገድ ዲያቆን ኤፍሬም የግዕዙን መሠረት ሳይለቅ ምሥጢሩንም ዘይቤውንም ጠብቆ መስመር በመስመር ተርጉሞታል። ይህ ከፍተኛ የሆነ የሥነ ጽሑፍ ችሎታን የሚጠይቅ እና በግዕዝ ቋንቋ መዋኘትን ያጠይቃል። በዚያውም ላይ እናቱን (የግዕዙን ዘር) በተጓዳኝ ገጽ፣ አቻ ትርጉሙን (የአማርኛን) በትይዩ ማቅረቡ አንባቢውን ለዳኝነትም ለምርጫም ይጋብዛል፤ ማለፊያ ሥራ!
ኹለተኛ ጥንቅቅ ያለ አርትዖት፦
ታትሞ ለሕዝብ የሚቀርብ ነገር ከፍተኛ የአርትዖት ሥራ ያሻዋል። አንዳንድ መጽሕፍት (እንዲሁም ጋዜጦች) በሳል መልዕክት በውስጣቸው ይዘው በርካታ የፊደል ግድፈት፣ የሥርዓተ ነጥብ አለመስተካከል፣ እንዲሁም የጽሑፍ ፎርማቱ የተዘበራረቀ ስለሚሆን ጥራታቸውን ዝቅ ያደርገዋል። ዲ/ኤፍሬም የቀደመ የአርትዖት ሥራ ልምዱን በበለጠ በዚህ መጽሐፉ ላይ እንዳዋለው በግልጽ ይታያል። የፊደላቱ ለቀማ፣ የቃላቱ አመራረጥ፣ የቁጥሮች አጠቃቀሙ፣ ሥርዓተ ነጥብ አጠባበቁ ወዘተ ... የተዋጣለት ስለሆነ ይበል ወንድማችን ያሰኛል።
ሦስተኛ ማብራሪያና ትንታኔ የያዘ ሥራ፦
አብዛኞቻችን ስለ “ጠቢበ ጠቢባን” ምንነት ያለን ግንዛቤ አናሳ ነው፤ የመጽሐፉን ይዘት የሚያውቁት ደግሞ ጥቂቶች እንደሆኑ ይገመታል። “ጠቢበ ጠቢባን”ን የመሰለ ለፈጣሪ የቀረበ ልዩ ምሥጋና አለማወቅ ምን ያህል እንደሚያስቆጭ አሁን ስናነበው ይገባናል። መጽሐፉ መቼ እና በማን እንደተደረሰ የቀደሙ ሥራዎችን አመሳክሮ፣ የራሱንም ንባብ ጨምሮበት ወንድማችን ኤፍሬም ሰፊ ማብራሪያ አቅርቦልናል። በግዕዙ ድርሰት ላይ አማራጭ ቃላትን ሲጠቀም በምክንያት መሆኑን ለማወቅ በየገጹ ያሉትን የግርጌ ማስታዎሻዎች መመልከት ነው። “እንዲህ የሚል ዘርም ይገኛል” ብሎ ይገልጻል። ይህ ዓይነቱ ሥራ በፊሎሎጂ (የጥንታውያን ጽሑፎች ጥናት) ባለሙያዎች የተመሳከረ ሕትመት (critical edition) የሚሉት ዓይነት ነው። ይህን ሥራ ይበልጥ የተደከመበት እንደሆነ የሚያሳየው ዐሥር የሚያህሉ ተመሳሳይ የብራና ቅጂዎችን መዘርዘሩ፣ የታተሙ የጸሎት መጻሕፍትንም ማካተቱ ነው። ይህም ለሌሎች ተርጓሚዎች በጎ ምሳሌ ነው፤ (በእርግጥ ይህም የተሻለ እንዲሆን በቀጣይ ቢጨምራቸው የምላቸውን ሁለት ያህል ነጥቦች ከታች እገልጻለሁ)።
ይህን የመሠለ ውብ ሥራ ስላቀረበልን ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም ከልብ መመሥገን ይገባዋል። መጽሐፉም በሚገባ ሊተዋወቅና ሥራው ሊነገርለት ይገባል፤ ከምር በሆነ አስተያየት ብዙ ሊባልለት የሚገባው ነውና። ይህን ካልኩ ዘንድ to be fair እንዲል ፈረንጅ በሚቀጥለው ቢያሟላቸው የምላቸውን ሁለት አስተያየቶች ላቅርብ።
-የመጀመሪያው የተረጎመልን የየትኛውን ቅጂ ጠቢበ ጠቢባን እንደሆነ ግልጽ ቢያደርገው? ያደገበትን የፍኖተ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅጂ ነውን ከሆነስ የመቼ ዘመን? ወይስ የጎንደሩን? የጣናውን? ወይስ ከውጭ ሀገር ከሚገኙት የቱን? እርግጥ ነው ይሄ ሃሣብ ይበልጥ ትርጉም የሚሰጠው በጥናትና ምርምር ለሚሠማሩ ቢሆንም ለጠቅላላ አንባቢም ቢሆን ማለፊያ ነው።
-ኹለተኛው ነጥብ ያሉን በርካታ የጠቢበ ጠቢባን ቅጂዎች መሆናቸው ይታወቃል፤ ሁሉንም መዘርዘር ባይጠበቅበትም ግን በርካቶች እንዳሉ ቢገልጽና እሱ ግን የተረጎመልን ይሄን እሱ ያገኘውን መሆኑን ቢጠቁመን ጥሩ እንደነበር ይሰማኛል።
ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም ሆይ፦
ጠቢበ ጠቢባን የሆነ ልዑል እግዚአብሔር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን ገልጾልህ፣ ትጋቱንም አድሎህ ወደ ፊትም ሌሎች መጻሕፍትን በነካ እጅህ ጽፈህ፣ ተርጉመህ እንድታደርሰን አደራ እንልሀለን
/channel/azop78
የመጀመሪያው እትም
ፍቅር እስከ መቃብር ጨረታ በሚያስደንቅ ኹኔታ ተጠናቃላች !!!
ሀሳባችን ብዡ ይጠይቁን የነበሩትን ወዳጆቻችንን ማስደሰት ነበር ከልብ ከሚፈልጋት ሰው እጅ ገብታለች!!!!
ይኽ መጽሐፍ እጃችኹ ላይ ካለ እስኪ በድጋሜ እናሳስባችኹ የትኛው ቅጅ ነው ያለዎት !!!!
ካለውት እሰየው ብለናል !!!
ከሌለዎትም ድጋሜ ጨረታ እናወጣለን !!!
ይጠብቁን !!!
በገበያ ላይ
የሃያኛው ክፍለ ዘመን መግቢያን የኢትዮጵያ ታሪክ ያወሳል።
የልጅ ኢያሱ፣ የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እና የተፈሪ መኮንን ታሪክ
ሀገራችን አሁን ያለችበት በቅጡ ለመረዳት የሃያ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምረን ማጥናት እንደሚጠበቅብን ምሁራን ያስረዳሉ ለዚህም ይረዳን ዘንድ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ትእዛዝ ተሰንዶ የነበረው መጽሐፍ ተዘጋጅቶ ቀርቦልናል።
ዛሬ ነሐሴ 10
የምንወደውን የምናከብረው ደራሲ አበራ ለማ መደብራችን ተገኝቶ ነበር።
ጋሽ አበራ ለማ ብዙ የግጥም መጽሐፍትንና አጫጭር ልቦለዶችን አሳትሟል።
በተለይም ሞገደኛው ነውጤ የተሰኘው ልቦለድ ሥራው ዘመን አሽሬና በአንባቢያን ዘንድ አይረሴነት ያለው የመካከለኛ አጭር ልቦለድ ታሪክ ነው።
ጋሽ አበራ የደራሲ በብርሃኑ ዘሪሑን ሥራዎች ላይ ሀሳብ አንስተን ብዙ ተወያየን። ለብርሃኑ ዘሪሁን የነበራቸውን ታላቅ እክብሮትና የብርሃኑ እምቅ ችሎት እሳቸው ካላቸው ረጅም የስነ ጽሑፍ ልምድ ጋር እያገናዘቡ ብዙ ታሪክና ልምድን አካፈሉኝ።
ታዲያ በጽሑፎቻቸው ኮትኩተው ያሳደጉንን ታላላቅና አንጋፋ ደራሲያንን እድሜና ጤና ይስጥልን እያልኩ ጋሸንም ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን ብየ ሸኘዋቸው።
"የአምላክ እናት ሆይ አልተለየሽኝም"
ታላቅ የምሥራች (የፍልሰታ ስጦታ) ለመጻሕፍት አንባብያን 27ኛው ዐዲሱ የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 2" መጽሐፍ ታትሞ ለአንባብያን ቀረበ። ይኽ መጽሐፍ ልዩ የሚያደርገው ከ4ኛው - 9ኛው ክፍለ ዘመን የተነሡ 26 ታላላቅ ሊቃውንት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትን ያካተተ ሲኾን፤ እነዚኽም፦
✍️ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘሳለሚስ
✍️ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
✍️ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
✍️ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
👉 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
👉 አንፊሎኪየስ ዘኢኮንየም
👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
👉 አምብሮስ ዘሚላን
💥 ቅዱስ ጀሮም
💥 አውግስጢኖስ ዘኂጶ
💥 ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
💥 ፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ
☀️ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ
☀️ ካኤሉስ ሴዱሊስ
☀️ ጴጥሮስ ክሪሶሎጎስ (ቃለ ወርቅ)
☀️ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
✍️ ቅዱስ ያሬድ
✍️ ሮማኖስ ማሕሌታይ
✍️ አካቲስት መዝሙር
✍️ ጎርጎርዮስ ዘቶረስ
💧 ቬናንትዩስ ፍርቱናቱስ
💧 ጎርጎርዮስ ታላቁ
💧 ኢሲዶሬ ዘሳቪሌ
💧 ጀርመኑስ ዘቁስጥንጥንያ
💥 እንድርያስ ዘክሪቴ
💥 ዮሐንስ ዘደማስቆ ይገኙበታል።
💥 ይኽንን በሕይወት ዘመንዎ ሊያነቡት ሊኖሮት፤ የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጣትን ክብር የሚያሳውቆት መጽሐፍ ነው።
💥ከ5 ዓመት በፊት ወጥቶ የነበረው "ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1" ከ1ኛው - 3ኛው ክፍለ ዘመን የተነሡትን የ25 ሊቃውንት ትምህርት ያካተተ ሲኾን በኹለቱ መጻሕፍት የ51 አባቶች የነገረ ማርያም ትምህርትን ለአንባብያን አቅርቤያለሁ። በሱባኤያችሁ እያነበባችሁ ተጠቀሙበት።
"ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዐተ ወልዳ"
(የእመቤታችን ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን)
<ሞት እንደሁ ልሙት በሴኮንድ መቶኛ፣
እንቅልፍ እንደሬሳ ዘለዓለም ልተኛ።
ሰማየ ሰማያት እመዘብራለሁ
የተዘጋውን በር እበረግዳለሁ።
የሌለ እስቲፈጠር የሞተ እስቲነቃ
በትልቅ እርምጃ ከመሬት ጨረቃ
ከጨረቃ ኮከብ
ካንዱ ዓለም ወዳንዱ
ስጓዝ እፈጥናለሁ
በፀሐይ ላይ ቤቴን ጎጆ እቀልሳለሁ።
.......መንገድ ስጡኝ ሰፊ
ፀሐይ ልሁን ፀሐይ
እንደ ፅርሐ አርያም ሁሉንም የሚያሳይ
እሳተ ገሞራ አመድ ዕረመጡን
ጎርፍ የእሳት ጎርፍ ልሁን።
......መንገድ ስጡኝ ሰፊ
ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ
ታላቅ የመጽሐፍ ምርቃት
==============
የደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ "የአማርኛ ጥበበ ቃላት"የተሰኝው አዲስ መጽሐፍ ቅዳሜ ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት በሐገር ፍቅር አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
መግቢያ በነፃ
ሐገር የታመመች ሰሞን ፪
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*
ኦስካር ዋይልድ ‹‹እውነቱን ስትነግራቸው አስቃቸው፡፡ ካላሳቅካቸው ይሰቅሉሃል፡፡›› ማለቱን ሰምቻለሁ፡፡ ቧልተኞች ያልተመዘገቡ የኅብረተሰብ የስነልቦና ሀኪሞች መሆናቸውንም አውቃለሁ፡፡ እኔ ግን እላለሁ - ሁሉም ነገር ቧልት ሲሆን ሀገር ሥርዓት ያጣል፡፡ ቧልት እንክብል ነው፡፡ ለዚያውም የማደንዘዣ እንክብል... ውሎ ሲያድር አምጡ ድገሙ የሚያስብል ሱስ የሚሆን ‹ድራግ›... ሕመማችን እያከከ እንድንላመደው፣ እንድንዋሃደው የሚያባብል አደንዛዥ እጽ... እንዲህ ዓይነት ኅብረተሰብ ደግሞ በየትኛውም ነገር ውስጥ አቋራጩን ያስሳል፡፡ ለጨቋኝ አገዛዞች ምቹ ነው፡፡ ግልብ ነው፡፡ ከእውነተኛ ጀግኖች ይልቅ ተዋኒያንና ትወና ይወዳል፡፡
እኛው ነን እኮ...
ከውጤቱ ይልቅ ሂደቱ እንደሚሰራን ከረሳን ቆይተናል፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያችን ምድር የሆነው የሚሆነው ይሄው ነው፡፡ በአያቶች ዘመን በተረታችን አማካኝነት ከመማርና እና መስራት ይልቅ ከደህና መወለድ ካልሆነም ከደህና መጠጋት ብልሃት እንደሆነ ይነገረን ነበር፡፡ (ከደህና ተወለድ ወይ ከደህና ተጠጋ) ትናንት - ለመሾም ለመክበር - ከመማር መስራት ይልቅ መሞዳሞድ ይበጅ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን አገዛዙን የተጠጋጉ ብቻ ድንገቴ ቱጃር ሆነው ብቅ ብለው ያስገርሙናል፡፡ እንደገና ከአገዛዙ ጋር አብረው መደብዘዛቸው ባይቀርም ቅሉ...
እንዲህ ዓይነት ኅብረተሰብ ግን የአቋራጭ ልክፍተኛ ነው፡፡ አቋራጭ ደግሞ ልህቀትን (merit, excellence) ያደኸያል፡፡ ሁሉም ነገር ለችርቻሮ ቀርቦ በገበያ ዋጋ ስለሚተመን ሰው መሆንን ይበድላል፡፡ የምትመዘነው በመክፈል አቅምህ እንጂ በምታበረክተው ልክ አይደለም፡፡ ቅዱስ እንደሆነ የሚሰበክልን ትዳር እንኳን ለገበያ ቀርቦ በደራ ጨረታ ሲወሰን ይታያል፡፡ እናም ሰው ከስምና ከቁጥር የሚያልፍ አሻራ ያለው ፍጥረት ይሆን ዘንድ ይሄን ዘመን ያልሻረው አደገኛ አዝማሚያ መዋጋት ያስፈልገው ይመስለኛል፡፡
ሀገርን፣ ሕዝብን፣ ዘመንና ግለሰብን በምን ትመዝነዋለህ? ለሚለኝ ‹በጀግኖቹ› ይሆናል መልሴ... በጀግኖቹ እመዝነዋለሁ፡፡ ጀግናህን አሳየኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ፡፡ ማንንም በጀግናው፣ አርዓያ በሚያደርገው ነገር በዚያ ማንነቱን፣ ምኞቱን፣ ኪሎውን፣ ትልሙንና ሕልሙን መመዘን ይቻላል፡፡ በእርግጥ ሰው እንደ ጅረት በየደረሰበት እንደ ሁኔታው መልኩን የሚገልጥ ነውና ሁሉም ሰው የሕይወት ዘመን ነጠላ ጀግና ይኖረዋል ማለት ዘበት ነው፡፡
ነገር ግን እላችኋለሁ የትኛውንም ኅብረተሰብ ንቃት ለመመዘን ወንዞቹን አትዩ፡፡ መንገዶች፣ ግድቦች፣ አደባባዮች፣ ድልድዮችም... በችሮታ ሲገነቡ አይተናል፡፡ ይልቁንስ የየትኛውንም ኅብረተሰብ የንቃት ደረጃ የሚበ˚የነው አሰላሳዮቹን (thinkers) የሚይዝበት መንገድ ነው፡፡ ኅብረተሰብ አሰላሳዮቹን በሚይዝበት አኳኋን በዚያ የየንቃት ደረጃው (collective consciousness) ይመዝናል፡፡ ማኅበረሰብ አሰላሳዮቹን በሚይዝበት መንገድ የወደፊት ዕጣው - የባርት ወይስ የአርነት - የሚለውን መገምገም ቀላል ነው፡፡
ዛሬ ዘመናችን ሆኖ ተገልጦ ስናየው - ቢያምርም ቢከረፋም - ያኔ በአብርሆቱ ዘመን የአውሮፓን ሥልጣኔ የቀየሱት ባልተኞች አልነበሩም፡፡ እንዲያውም እነ ማርጋሬት ፖሬት፣ ጆርዳኖ ቡሩኖ፣ ኤድዋርድ ዊትማን ዓይነት እና ሌሎችም... ማኅበረሰብ በሁለንተናዊ ግንዛቤው ጥቂት ፈቀቅ ይል ዘንድ ሲሉ - ለነፍሳቸውም ሀቅ ሲሉ - እንደ ጧፍ የተንቀለቀሉቱ፣ እንደ ችቦ ተንቦግቡገው በነፍሳቸው መራር የሕይወት ዋጋ የከፈሉቱ እንጂ...
በእርግጥ አውሮፓዊው ሥልጣኔው የሰውን ልጅ በነፍስ ያራመደ ወይስ ያደኸየ? የሚለውን ለጊዜው እንተወው፡፡ ዛሬ እግርህን አንፈራጠህ ቆሞህ ‹ሰልፊ› ያምትነሳበትን ሥልጣኔ የፈጠሩት ግን ፌዘኞች አልነበሩም፡፡ እንዲያውም ሰው ከአስተሳሰብ ባርነት እንዲላቀቅ፣ ወንጌልን በወንጀል ከሚግት እስራት እንዲፈታ፣ እንደ ስፒኖዛ ያሉ ፈላስፎች አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ እርግማን ውግዘትና መገለል አስተናግደዋል፡፡ ከስለት ጥቃት ለጥቂት ተርፈዋል፡፡ ምስኪኑ ስፒኖዛ የሀያ ሁለት ዓመት ልጅ እያለ ከምኩራብ ሲወጣ ከተሰነዘረበት የስለት ጥቃት ለጥቂት ተረፈ፡፡ ከስለት ጥቃቱ ያተረፈውን የተዘለጠለ ካባ ዘወትር በየአደባባዩ ለብሶ ይታይ ነበር አሉ፡፡ - ለአመጻ! -
ይህም ሁሉ ሆኖ የአውሮፓ የሕዳሴ ጉዞ ሂደቱን የሚያቀጣጥሉ አሳቢያንን የሚያሰናዝር የሚጠብቅ ሆደ ሰፊነት ነበረው፡፡ ለአብነትም ቮልቴር የመሳሰሉ አዋኪ ጠቢባን እልፍ ጊዜ ቢጋዙም፣ አንዳንዴ በጥንቃቄ ቢጎሻሸሙም ሥራዎቻቸውን ለማሰላሰል ሙሉ ለሙሉ ገደብ አልተጣለባቸውም፡፡
ዣን ዣክ ሩሶ፣ አርስቶትል፣ አንስታይን፣ ካርል ማርክስ፣ ጆን ሎክ፣ ኤሚል ዞላ... በአጠቃላይ ሁሉም አፈንጋጭ ፈላስፎች፣ ደራሲያን ወይ ታስረዋል አሊያም ቢያንስ አንድ ጊዜ ተግዘዋል፡፡ የካርል ማርክስማ መብከንክንማ ይለያል፡፡ ከጀርመን ፈረንሳይ፣ ስዊዝ፣ ቤልጄም እንደገና ጀርመን መልሶ ፈረንሳይ በመጨረሻ ወደ ሎንዶን እንዲችው እንደተንከራተተ ዘመኑን ተወጣት፡፡ በተደጋጋሚ አንዳይጽፍ ጋዜጣ እንዳያዘጋጅ ማዕቀብ ቢጣልብትም አንድ ሦስተኛውን የዓለም ሕዝብ ለአብዮት ከማሰለፍ ግን ማንም አላገደውም፡፡
ቢሆንም ምዕራባዊያኑ እንደ እኛ አፍንጫ በመፎነኑ፣ ምላስ በመስለቡ ሙጭጭ አላሉበትም፡፡ ይሄም መለሳለሳቸው በረከት ሆኖላቸው ዛሬ ዘመናዊውን ሙሉ ዓለም የሚያሾር የትርክት የበላይነት አቀዳጅቷቸዋል፡፡
የእኛ ግን ይለያል፡፡ ‹‹ነገሥታት ሸንጋይ ምላስን ይወድዳሉ›› እንዲል አፍሪካዊው ፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ ከነገሥታቱ ዘመን ጀምሮ ከአሰላሳዮቹ ይልቅ ተራቢዎች ለመኳንንት እና ለሕዝብ ቅርብ ነበሩ፡፡ ከአሳቢዎቹ ይልቅ አጫዋቾቹን የሚያጀግን ኅብረተሰብ ደግሞ ከእምቢ አሻፈረኝ፣ ከለውጥ ጋር ኩርፍ እንደሚሆን፣ ወደ ንቅዘት እንደሚያዘግም፣ ቧልት፣ እንቶፈንቶ (nugatory) እንደሚያነፈንፍ ግልጽ ነው፡፡
ቧልቱስ ስንኳ ምግባርና ለዛ የለውም፡፡ ስሪቱ ስድና መደዴ ቅይጥ ነው፡፡ መንጋነት ይጠናወተዋል፡፡ ይበልጥ እንዲገርምህ ‹‹ቧልተኝነትን›› ከ‹ጅነሲቲ› ጋር አመሳክሮ ሲራቀቅ ታገኘዋለህ፡፡ ለዚህስ ይሆን በትርክታችን ውስጥ ከአሰላሳዮች ይልቅ ተረበኞች የመበርከታቸው ምክንያቱ? ለዚህ ማመሳከሪያ መዝገብ ድርሳን ማገላበጥ ለምንህ? የቧልቱ ሰሌዳ ‹ቲክቶክ› ብቅ ያለ ሰሞን ከየትኛውም ዓለም በላይ የተረባረበው የእኛው ሰው መሆኑን ልብ ማለት ብቻ ይበቃህ የለምን? የፌስቡኩስ ቢሆን?
ነገርግን አሰላሳዮች ኅብረተሰብን፣ በዘመኑ ቋንቋ ‹አክቲቪስቶች› ደግሞ መንግስትን ይተገትጋሉ፡፡ አሰላሳዮች ስለለምን ኅብረተሰብን ከተባለ ኅብረተሰብን መለወጥ መንግስትን የመለወጥ ዋነኛ መንገድ ስለሆነ... ማንኛውም ኅብረተሰብ የሚመስለውን መንግስት ይሰራል፡፡ ኅብረተሰብ በችሮታ የሚያገኘው አንዳችም ዓይነት መብት አይኖረውም፡፡
በአጭር የተቀጩት የ20ኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያዊ ምሁር ገብረሕይወት ባይከዳኝ ‹አጤ ምኒሊክ እና ኢትዮጵያ› በተሰኘ መጽሐፋቸው ይሄን ሃሳብ ሲያብራሩት...
…………………
ድ…ን…ገ…ት ባነኑ!!!!
“እ -ሃ- ሃ——!ይሄ ነገርማ አንዳች ሚልኪ ቢኖረው ነው እንጂ እንዴት ሆኖ ነው እንዲህ ያለ የግራ ግጥምጥሞሽ ዝም ብሎ የሚገጣጠመው?” ብለው አሰቡ።
ለግራ ዘመም ድርጅታቸው፤ ግራ ከተጋቡ ጓዶቻቸው ጋር፤ ግራ ክንዳቸውን ተመትተው ከዋናው የእስር ቤት በር በስተግራ ካለ ቤት፤ ከባልንጀራቸው ከግራኝ ጎን፤ ለ…ዛውም ከጓደኛቸው ከግራኝ በስተግራ ተኝተው፤ ግራ ተጋብተው አራሳቸውን አገኙት።
ይሄ የግራ ግጥምጥሞሽ ለጥቂት ቀናት ግራ እያጋባቸው ቆየ። በዛ ላይ የግራ ክንዳቸው ቁስል ይጠዘጥዛቸዋል፤ ዝምምምም ብለው ከቆዘሙበት የሃሳብ ባህር ድንገት ወዳጃቸው ግራኝ በስተግራ ጆሯቸው በኩል ተጠግቶ ይነዘንዛቸዋል ግራ ያጋባቸዋል፤ ግራ ገባቸው።
አንድ ሌሊት የአብዮት ጠባቂዎች የእስር ቤቱን በር እንደልማዳቸው ድንገት በይል በርግደው ገቡ። የቆሰለውን የግራ ክንዳቸውን በከስክሳቸው እየረገጡ ያስጮኋቸው ጀመር። “አንተን ብሎ ግራ ዘመም ግራ የገባህ አናርኪስት!!! እውነተኛ ግራ ዘመም እኛ ነን!! ደግሞ
ላንተ ግራ የሰጠህ ማን ነው !" እያሉ እያዳፉ እና እየቀጠቀጡ ከነበሩበት ቤት በስተግራ ካለ
ሌላ ጨለማ ቤት ወሰዷቸው። ያኔ ይበልጥ ግራ ገባቸው።
"ካልጠፋ አቅጣጫ ሰው እንዴት ግራን ይመርጣል? እንዴት በግራ ይጣላል? ግራ እንዴት ከግራ ይለያል? እያሉ በሃሳብ ተዋጡ። "ግራ ዘመም ነኝ" ብለው ህይወታቸውን የሰጡትን ግራ “ግራ አይደለም! ግራ እናሳይሃለን" እያሉ በሚደነፉ ግራ ዘመም ወታደሮች ንግግር ይበልጥ ግራ ገባቸው።
ያን እለት አካላቸው በግርፋት ተተልትሎ እራሳቸውን ስተው አደሩ።
ሲነቁ በግርፋት የቆሰለው የገላቸው ጥዝጣዜ አላስቆም አላስቀምጥ አላቸው፤ አለቀሱ፤ ጮሁ!!!! ሊነጋጋ አካባቢ የጀርባቸውን ቁስል በእራፊ ጨርቅ እየጠረገ በልቅሶ የሚነፈርቅ አንድ ወጣት፤ ወዳጃቸው ግራኝ ሌሊት ማረፉን ሳግ እየተናነቀው አረዳቸው።
ደነገጡ!!! ለግዜው የቁስላቸውን ጥዝጣዜ እረሱት። እንደ ትልቅ ጉርሻ ጉሮሯቸውን አንቆ የያዛቸውን ሳግ እና እንባ ድንገት ዘረገፉት፡
ትኩስ እንባ የቀኝ ጉንጫቸውን እያቋረጠ ሲንዠቀዠቅ ይሰማቸዋል። የቀኝ ጉንጫቸውን ብቻ!። ግራ ጉንጫቸውን ዳበሱ፤ እንባ የለውም፤ ግራ ጉንጫቸውን የሚዳስሱበት እጆቻቸው በቀኝ አይናቸው ብቻ ይታዩዋቸዋል።................
📖📖 ጠያይም_መላእክት
የኮምዩኒ ዝም ርኩስ መንፈስ
✍✍ቤተማሪያም ተሾመ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏🙏
ለካ ሁለት ቃላት የሠውንልጅ ህይወት የመከራ ቋት ውስጥ መክተት ይችላሉና።ለካ ሁለት ቃላት ብቻ ማንነትን እልም ያለ ውልአልባ ቀውስውስጥ ለመጨመር ብቃቱ አላቸውና።
ሠማይናምድሩ ዞረብኝ ያለችኝን ሁለት ቃላት ደግሜ ሣስታውሳቸው ውስጤ መቃጠል ይጀምራል።እና በምድር ላይ እንደ ሣር የበቀልኩ ብቸኛ የሠውፍጡር የሆንኩ ያህል ይሠማኛል። " እናትሽ አይደለሁም " ነበር ያለችኝ።
"የጭን ቁስል"
የፍልስፍና ጽንሰ ሐሳብ
አንድ የሩቅ ምስራቅ ፈላስፋ ወደ ንጉሡ ችሎት ተጠርቶ ቀረበ፡፡ ፈላስፋው በሕገቡ ዘንድ በምድር ላይ ታይቶ እንደማይታወቅ ታላቅ ሎጂሽያን ተገምቶ ነበር፡፡ ፈላስፋው ማንኛውም ነገር ተጨባጭ እንዳልሆነ ያስተጋባ ነበር፡ ሁሉም ነገር የተመሠረተው ከሕልም ጋር ልዩነት በሌለው አኳኋን መሆኑን በማስረዳት አበክሮ ይሟገት ነበር፡፡ ንጉሡ የተግባር ሰው (ፕራግማቲክ) ነበር። ሕገ በሙሉ ወደ ቤቱ እንዲከት ትእዛዙን አስተላፈና አንድ ዕብድ ዝኆን በአውራ ጎዳና ላይ እንዲለቀቅ አደረገ፡፡ ፈላስፋው መንገዱ ላይ የፊጢኝ ታስሮ ቆሟል። ፈላስፋው የሚከንፈውን ዝኆን ከርቀት እንደተመለከተ አድነኝ ዝኆኑ ተጨባጭ ነው!›› በማለት ወተወተ፡፡
የሁኔታውን አደገኝነት በመመልከት በዕብደት የሚከንፈው ዝኆን ከጉዞው እንዲገታ ተደረገ፡፡ ፈላስፋውም ዳግም ወደ ንጉሡ ችሎት ቀረበና፤ «አሁንስ ስለፍልስፍናህ ምን ትላለህ?›› ተብሎ ተጠየቀ።
«ሁሉም ነገር ተጨባጭ አይደለም›› አለ፡፡
‹‹ዝኆኑስ?›› ንጉሡ ጥያቄውን ሰነዘረ፡፡
የሚጮኸው ፈላስፋ ተጨባጭ አይደለም:: ፈላስፋውን ከሞት ያዳነውም ንጉሥ ተጨባጭ አይደለም፡፡ ሁሉም ነገር ተጨባጭ አይደለም፡፡ ሆኖም እዚያ አውራ ጎዳና ላይ ደግማችሁ አትሰሩኝ፡፡ ምክንያቱም እኔ ፈላስፋ ነኝ፡ ዝግጁ የሆንኩት ለመስሪ ከር ብቻ ነው፡፡ ከዝኆን ጋር መከራከር ደግሞ አይቻልም፡ በንጉሡ ግዛት ፈላስፎች ካሉ፤ አቅርቧቸውና በመከራከር ለማሳመን ዝግጁ ነኝ›› አለ ይባላል።
የምብግዜም ተመራጭ ቤተ መጽሐፍት ቤታችኹ ኤዞፕ
በሽያጭ ላይ ነን
ግልጽ ጨረታ በሉት !!!
ይኽንን ፍቅር እስከ መቃብር አይታችኹታል።
እስካኹን ባለኝ የመጽሐፍት ሽያጭ ዘመኔ የመጀመሪያ የኾነውን ምንም ያልተነካካ ያልተበረዘ ያልተከለሰ እትም የ1958 ዓም እትም ገጥሞኝ አያውቅም።
እነኾ ይኽንን የመጀመሪያ እትም መጽሐፍ በደምበኛ ትዕዛዝ መቀበያ ደብተራችን ላይ ያለንን ትዕዛዝ ስመለከተው ከ25 ይበልጣል። በመኾኑም ለማን ሰጥቸ ለማን የለኝም ልበል። ስለዚኽ ይኽንን ጽሑፍ ቀድሞ አይቶ ለደወለልልን፣ ላዘዘን ፣ ደምበኛችን ብቻ የምንሰጠው ይኾናል ።
አስታውሱ ይኽ ቅጅ የ1958 ዓም ነው።
ትዕዛዝ _ እስኪ እጅወ ላይ ያለውን የፍቅር እስከ መቃብር እትም ይመልከቱ ?
" ዛሬ ቅዳሜ አይደለም " የተሰኘው መጽሐፍ እየተነበበ ነው ::
" ...ከመውለዷ በፊት የህክምና ክትትል የሚባል ነገር አድርጋ አታውቅም፡፡
ይህን ታደርግ ዘንድ አልደላትም፡፡
እንደብዙዎች እናቶች የምትወልድበትን ፣
ሕይወት ወደ ምድር የምታመጣበትን ፣
እድሜ ልኳን ስትሳሳለት ከምትኖርለት ፍጡር ጋር የምትገናኝበት ቀን አልናፈቃትም፡፡
ልጅ እኮ የፈጣሪ ጸጋ ነው ፣ ስጦታ ነው ፣ በረከት ነው ፣ ሲሳይ ነው… የሚሉ ቃላት አልሸነገሏትም፡፡
ልጅነቷን ቀርጥፎ ልጅነቱ የሚያብብ ፣
ወዟን አርግፎ የሚወዛ ፣
ጉልበቷን አፍስሶ ጉልበቱን የሚያጠነክር ፣
ቅስሟን ሰብሮ ተስፋውን የሚፈነጥቅ ፣
ተስፋዋን ንዶ ድሎቱን የሚገነባ ፣
ድሎቷን ሰውቶ ምቾቱን የሚያደላድል ፣
እሷን ገድሎ እሱ የሚኖር እርግማን በማህፀኗ ስላለመሸከሟ እርግጠኛ አይደለችም፡፡
እንቡጥ ሴትነቷን ለቀጠፈ አምሳያ ይሆን ዘንድ ትውልድ አትፈልግም፡፡
የእሱ አይነት ዘር ሊጠፋ እንጂ ሊተካ ፣ ሊመነጠር እንጂ ሊበዛ አይገባውም፡፡
ወለደች፡፡
ተስፋዋ ጨልሞ ተስፋ አመጣች፡፡
እሷ ስትታረዝ ሊለብስ ፣ ስትራብ ሊጠግብ ፣ ስትጠማ ሊረካ… ወለደች፡፡... " :
ከመጽሐፉ የተወሰደ "ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"
2016 ዓ.ም.
የኪዳነ ምሕረት ዓመት
የዘንድሮው ጾመ ፍልሰታ ብዙ ጥይቄ የሚመለስበት እንዲሆን እንጠብቃለን:: እመቤታችን በፍልሰትዋ ከሀገራችንም ከቤተ ክርስቲያናችንም የፈለሰውን ሰላምና ፍቅር በምልጃዋ እንድትመልስልንና የእርስዋን ትንሣኤ ሐዋርያት ባዩበት ጾም እኛም የቤተ ክርስቲያናችንንና ተስፋ የማንቆርጥባትና ብዙ ታውፋንያዎች የተረባረቡባትን የሀገራችንን ትንሣኤ የምናይበት ያድርግልን:: የድንግሊቱን ትንሣኤ የማያምኑ እንዳሉ ሁሉ የቤተ ክርስቲያንና የሀገር ትንሣኤ ከዚህ በኋላ ተስፋ የለውም የሚሉም ይኖራሉ:: እኛ ግን በቶማሳዊ የእምነት ደመና ላይ ሆነን የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን የሰላም ትንሣኤ እንጠብቃለን:: የሀገራችንን ችግር የሚፈታ ምንም ዓይነት ምድራዊ ጠቢብ የለም ጠቢበ ጠቢባን ልዑል እግዚአብሔር እርሱ ብቻ እጁን እንዲያስገባና እጅዋን ወደ እርሱ የምትዘረጋውን ሀገር "ወዳጄ ሆይ ተነሽ" ብሎ እንዲያስነሣት እንጠብቃለን:: በዕንባ የቀረበ ጸሎት የማይፈጽመው ነገር የለምና 2016 የኪዳነ ምሕረት ዓመት እንዲሆን በዚህ ሱባኤ እንማጸናለን::
ለሱባኤው አንድ ውብ የጸሎት መጽሐፍ ሥጦታ ሆኖ ቀርቦልናል:: ጸሎቱ እጅግ ጥንታዊ ጸሎት ሲሆን እጅግ ውብ አድርጎ ከግእዝ ወደ አማርኛ ከቅኔያዊ ለዛው ጋር የመለሰው ደግሞ ኤፍሬም የኔሰው ነው:: መጽሐፉን ከሱባኤ መልስ በደንብ እንተነትነዋለን:: ሰሞኑን ግን ብትጸልዩበት መንፈሳዊ ደስታ የምታገኙበት መሆኑን ስታነቡት ታምኑኛላችሁ::
ሱባኤውን የስርየት ያድርግልን የነደደውን እሳት ያብርድልን ለግፉዓን የሚበቀልላቸው አምላክ ፍትሕ ርትዕን ያድርግልን:: 2016 ዓ.ም. የኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ቃልኪዳን) ዓመት ይሁንልን
#10_ምክሮች_ከ_ኢትዮጵያዊው_የበረሃ_መልእክተኛ_መጽሐፍ
የኢትዮጵያውያንና ግብጻውያን የበረሃ መልዕክተኞችን ጥበብና ምክር ከያዘው #ኢትዮጵያዊው_የበረሃ_መልእክተኛ መጽሐፍ የተወሰዱ አስር ሕይወት ቀያሪ መልእክቶች
#አንድ
አባ ዮሐንስ ሐጺር እንዲህ ይሉናል “በየቀኑ ብትወድቅ አትደናገጥ፤ ትልቁ ችግር ያለው ከመውደቅህ ላይ ሳይሆን፣ ለመነሳት አለመፈግህ ላይ ነው።”
#ሁለት
አንድ አባት እንዲህ አሉ “ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ የሚለውን ቃል የሰው ልጅ ቢያስታውስ፣ ዝምታ መልካም መሆኑን ያውቅ ነበር”
#ሶስት
አንድ አባት እንዲህ ይሉናል “እንደ አንበሳ ያለስ ጠንካራ አውሬ የታለ? ሆኖም ለሆዱ ሲል ወጥመድ ውስጥ ይወድቃል፤ ሆዱ ደካማ ጎኑም ነው። እኛም ሆዳችንን ካስቀደምን እንወድቃለን”
#አራት
እማሆይ ሲንቅላጢቃ እንዲህ ይሉ ነበር “ስንጀምረው ብዙ ውጊያዎች ይኖሩብናል፤ መልካም በማድረግና በእኩይ ሃሳቦቻችን መሃልም እንወጠራለን። ልክ እሳትን እንደማንደድ ነው፤ እሳቱን ማያያዝ ስንጀምር ጭስ ይኖራል፣ ያስለቅሰናልም፤ እናም በዚህ ሁኔታ የምንፈልገውን እናገኛለን።"
#አምስት
እማሆይ ሳራ እንዲህ ይሉ ነበር “ሁሉም ሰው መልካም ሆኖ በስርዓት ውስጥ ይኑር ካልሁ፣ ራሴን በእያንዳንዱ ሰው ክፋት ሲከፋ አገኘዋለሁ፤ ሆኖም የምጸልየው የእኔ ልብ ለሁሉም ሰው ንጹህ እንዲሆን ብቻ ነው”
#ስድስት
አባ ዮሐንስ ሐጺር እንዲህ ይላሉ “እኔ ልክ በዛፍ ስር እንደተቀመጠ ሰው ነኝ፤ ብዙ አራዊቶችና የምድር ተሳቢዎች ወደኔ ሲመጡ ካየሁም፣ በቶሎ ወደ ዛፉ እወጣለሁ። በዚሁ መንገድ በበኣቴ ላይ ተቀምጬ፣ እኩይ ሃሳቦች ወደኔ ሲመጡ ካየሁ፣ እነሱን መቋቋም አልችልምና ወደ አምላኬ በጸሎት እሮጣለሁ፣ ከጠላቶቼም ያድነኛል፣ ዘላለምም እኖራለሁ”
#ሰባት
አንድ ወንድም ወደ አባ ጴሜን ቀረበና ጠየቃቸው “አባ፣ ስለኃጢአቶቼ ምን ላድርግ?” ሽማግሌውም መለሱለት “ኃጢአቶቹን ማጽዳት የፈለገ ያልቅስ፣ መልካም ማድረግን የፈለገም ያልቅስ፣ መጽሐፍ እና አባቶች እንዳስተማሩንም ከእንባ በቀር መንገድ የለም”
#ስምንት
አባ ጴሜን እንዲህ ይሉ ነበር “ኃጢአትን ሰርቶ ከማያውቅ ሰው ይልቅ ኃጢአትን ሰርቶ የተጸጸተን እመርጣለሁ። የመጀመሪያው ፍጹም በመሆኑ ሲታበይ፣ ሁለተኛው በትህትና ውስጥ ይኖራል።
#ዘጠኝ
አባ ጴሜን እንዲህ ይሉ ነበር “የክፋት ስራ በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መሃል እንደ አጥር ሆኖ ይጋርዳል፤ ሆኖም ይህን አጥር ለማለፍ የሰው ልጅ እንዲህ ማለት አለበት - በአምላኬ ቅጥሩን እዘልላለሁ። (መዝ ፲፰፥ ፳፱) ስራው ሁሉ መልካም የሆነው እግዚአብሔርም ቅጥሩን ያሻግረዋል።”
#አስር
አንድ አባት ስለ ፍትወት ምኞት እንዲህ አሉ “ልክ በሆቴል ቤት ደጃፍ እንደሚያልፍ ሰው ሁን፤ የሚቀቀለው ስጋ ሽታ ወደ ውስጥ ይጠራዋል፣ ሆኖም መግባት አይፈልግም አልፎ ይሄዳል። ከነዚህም መጥፎ ሃሳቦች ይሸሻል “የእግዚአብሔር ልጅ፣ እርዳኝ” ይላል። ስለሃሳቦችም ተመሳሳይ ማለት ይቻላል፤ የሃሳቦቻችን ምንጭ እኛ አይደለንም፣ ምን ማሰብ እንዳለብንም መምረጥ አንችል ይሆናል። ሆኖም ግን የትኛው ሃሳብ በእኛ ላይ ሃይል ይኑረው የሚለውን መምረጥ እንችላለን።”
ይህ ድንቅ መጽሐፍ በመላው ኢትዮጵያ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
#ኢትዮጵያዊው_የበረሃ_መልእክተኛ መጽሐፍ
‹‹ትምህርት የሌለው ሕዝብ ዘንድ ንጉሥ ማለት እና መንግሥት ማለት ትርጉሙ አንድ ነው፡፡ ንጉሣቸው የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ መላው ሕዝብ ባሮቹ ናቸው፡፡ አዕምሮ ባላቸው ሕዝቦች ዘንድ ግን መንግስት ማለት ማኅበር ነው፡፡ ንጉሣቸው የማኅበራቸው አለቃ ነው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ የፈቀደውን ያደርግ ዘንድ አይችልም፡፡ ሥልጣኑ የሕዝቡ ማኅበር በደነገገው ሕግና ወግ የተወሰነ ነው፡፡ አዕምሮ የሌለው ሕዝብ ሥርዓት የለውም፡፡ ሥርዓት የሌለው ሕዝብ የደለደለ ኃይል የለውም፡፡ የኃይል ምንጭ ሥርዓት እንጂ የሠራዊት ብዛት አይደለም፡፡ ሥርዓት ከሌለው ሰፊ መንግስት ይልቅ በሕግ የምትኖር ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች፡፡...››
አጤ ምኒሊክና እና ኢትዮጵያ ገጽ 9 - 10
ራሳቸው ገብረሕይወት ባይከዳኝ ላጠነጠንነው ሐሳብ ተገቢ ማሳያ ሊሆኑን ይችላሉ፡፡ እኒህ ሰው ከዘርዓያዕቆብ በኋላ ብቅ ያሉት ትልቁ አሰላሰይ እንደነበሩ የብዙዎች ስምምነት አለ፡፡ ከኤሮፓ በተመለሱ በጥቂት ዓመታት ልዩነት እቴጌ ጣይቱ ሥልጣን የጨበጡ ሰሞን ለሀገሪቱ የሚበጅ የተለየ ሐሳብ በማንሳታቸው እቴጌይቱ ስለተጣሏቸው ወደ ሱዳን ለመሰደድ ተገደዱ፡፡ እዚያ በጽኑ በሽታ ተይዘው ከሞት አፋፍ ተረፉ፡፡ አጤ ምኒሊክና ኢትዮጵያን የጻፉት በዚህ የስደት ዘመን ነው ይባላል፡፡ ግን በመጽሐፋቸው ውስጥ አንዳችም ዓይነት የጥላቻ ስሜት አላንጸባረቁም፡፡ እንደሚባለው እቴጌይቱ ገለል ብለው ልጅ እያሱ በሞግዚት ማስተዳደር እንደጀመሩ ሲሰሙ ወደ ሀገር ቢመለሱም እያሱም በአጫዋቾች እየታጀቡ መኳንንቱን በማታገል ከመዝናናት በቀር ለሀገር ዕድገት ለሚበጅ ምክክር በጄ የሚሉ አልሆኑም፡፡
የተፈሪም መንገድ ከልጅ ኢያሱ የሚሻለው በጥቂቱ ብቻ ይመስለኛል፡፡ በዘመኑ በአንጻራዊነት የተራመዱ የነበሩቱ ሁለቱ ሰዎች (ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝና ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም) በበቂ ሁኔታ ሁለቱን መንግስታት የማማከር ዕድል አላገኙም፡፡ ተክለሐዋሪያት እንዲያውም ለጥቂት ጊዜ ታስረዋል፡፡ ብዙውን ዘመናቸውን አገዛዙን ተቀይመው ገለል ብለው እንዳሳለፉም ተጽፏል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅንም የቅርብ ጊዜ ጸጸታችን ናቸው፡፡ ሁሉንም እዚህ ላይ መዘርዘር አይቻለኝምና የምናውቅ የማናውቃቸውን ቤቱ ደጁ ይቁጠረው፡፡
ይሄ ግን የየዘመናቱ አገዛዞች ብቻ ሳይሆን ፊደል ቀመስ የሆነው የከተሜው ሁሉ ልክፍት ይመስለኛል፡፡ ዛሬም የመዝናናት ሕልማችን ከመብላት፣ መጠጣት፣ መዋሰብ፣ ንባባችን ‹ስቶሪን ኢንተርቴይን› ከማድረግ አያልፍም፡፡ አጉል አርበኝነት ይጠናወተናል፡፡ የብሔርተኝነት ሥሜት የሚጋልበው ሥር የሰደደ ‹ሚሊታንሲ› ስሜት እንደበልግ ነፋስ እንዳሻው ያሰግረናል፡፡ ከአሰላሳዮች ይልቅ አርበኞች የጀግና ግጥም ይደረደርላቸዋል፡፡ ነጋድራስ ገብረሕይወት ምንይልክ የጀመሩት የለውጥ ጉዞ ገና እሳቸው አፈር ሳይቀምሱ ማዝገም መጀመሩ ተስፋ አስቆርጧቸው በቁጭት ሲጽፉ [ቃልበቃል ባይሆንም] ‹‹ማን ያስቀጥለው፡፡ መኳንንቱ እንደሁ ሹመት ዝና ቀርብኝ ብሎ ሽፍቶ አገር ምድሩን አጥፍቶ መሞትን እንደ ሙያ ይቆጥረዋል፡፡ እንዲህ ቢያደርግ ሕዝቡም እንደ ጀግና ይመለከተዋል›› ብለዋል፡፡
አንዳንዱ ነገር ዘመን በራሱ ተፈጥሯዊ ግፊት ሊያመጣው ይችላል፡፡ ባለፉት መቶ ዓመታት ሀገራችንንና ነጻነታችን ለምናብጠለጥላቸው ቅኝ ገዥዎች በአራጣ አስጨምድደን ከገነባናቸው ጥቂት ድልድዮ፣ መንገዶችና፣ ግድቦች እኛ የሚመስለው የቱ ነው? ባለፉት መቶ ዓመታት እንደ ሕዝብ ከነበሩን በጎነቶች መካከል እስከዚህች ዕለት ከእኛ ጋር ማቆየት የተቻለንስ ምን ያህሉን ነው? እናስ ከአንድ ያጣ ጎመን ተረቱ የሚገባው ለእኛ መሆኑ አይደለምን?
ዛሬም ፊደል ቀመሱ ትውልድ ሳይቀር የሚያነብ የሚጠይቅ ሰውን እንደ ጅል መመልከት ልንሻገረው ያልተቻለን ደዌ ሆኗል፡፡ ጀግኖቻችን ለሕመማችን ማደንዘዣ የሚያስታቅፉን ቧልተኞች አልሆኑብንምን? በዚህች በእኛ ምድር ጥንትም በዚህች ቅጽበትም ከትንሽ እስከ ትልቅ አሰላሳዮች የተወገዙ፣ የተነጠሉ ናቸው፡፡ የሚያሰናዝር፣ የኤኮኖሚ፣ የኅሊና ነጻነት የላቸውም፡፡ ማግለል፣ ማሳደድ፣ ማቆርቆዝ፣ ማደኅየት ይፈጸምባቸዋል፡፡ እድለኛ ከሆኑ ሲሞቱ ብቻ ከንፈር ይመጠጥላቸዋል፡፡
አሰላሰዮች ደራሲያን፣ የመንግስት ሹመኞች፣ መምህራን ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ምንም ላይጽፉ፣ ምንም ላይቀኙ ይችላሉ፡፡ የትርክት የበላይነት መፍጠር፣ ባህሉን ማሻሻል የሚፈልግ ሕዝብ ግን እየኮረኮመም ቢሆን በተጻፉም ባልተጻፉም ሕጎቹ እነዚህን አሳቢያን የሚያሰናዝርበት የፋይናንስ፣ የኅሊናና እና ደኅንነት ከለላ ይሰጣቸዋል፡፡
እናስ ያቆሙን መሰረቶች ምን ያህል ጽኑዓን ናቸው? እንደ ኅብረተሰብ የአቋራጩ፣ የቧልቱ ልክፍተኞች ሆነን ለመገኘታችን ምክንያቱ ምንድን ነው? የምንዋቀሰው፣ የምንናናቀው በድንቁርናችን ልክ አይደለምን? ለፍጥረት ሁሉ ከሚተርፍ በረከት፣ ኅሊና እና ርህራሄ ጋር ተፈጥረን ሳለ ስለንፍገታችን ራሳችንን በሰንደቅ ዓላማ ለሚያስለምን ችጋር አላጨንምን?
ጸጋዬ ገብረመድኅን በአንድ የጦቢያ መጽሔት ቃለመጠይቁ እንዳለው ‹‹የጨው ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልህ ያለቅሳል፡፡›› ያቆመን የጋራ መሰረት ሲናድ እንደሞኝ ቆመን ስንታዘብ ይታየኛል፡፡
.
.
.
--------
ምስል - ከድረገጽ በ1920ዎቹ ጉዞ ወደ ገበያ
ከያዕቆብ ብርሃኑ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ
ከዘመናት ፀሎት ሱባኤ በኋላ የሰው ጠረን ናፍቆኝ ከተማ ወጥቼ
ከአሕዛብ ሸንጎ ከዋናው ምስያጥ የሰው ሳቅ ሞርሙርኝ እዚያ ተገኝቼ
(ናፍቆትም አይወጣ የሰው ትንፋሽ ሙቀት ፈፅሞ አይሠለችም።)
ግና ምን ያደርጋል አሰኘኝ ምናኔ ሰው ሰውን ሲበላ ባይኔ ተመልክቼ
ምስጥ-ገበያ
« ጦርነት ሲጀምር ፖለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ፡፡ባለፀጎች ምግብ ያቀርባሉ፡፡ድሆች ልጆቻቸውን ይለግሳሉ፡፡ጦርነቱ ሲያበቃ ፖለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ፡፡ባለፀጎች ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፡፡ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ስፍራ ይፈልጋሉ »
Читать полностью…አመሰግናለኹ !!!!
የጎንደር ታሪክን መጽሐፍ አስፈልጎኝ በፖሰትኩ ጊዜ የተባበራችኹኝ ወዳጆች እጅግ አመሰግናለኹ።
ከአንድም ኹለት አግኝቻለኹና ምስጋናየ ላቅ ያለ ነው።
እንባ ተናነቀኝ።ዝቅ ብዬ ድንጋይ ፈላለግኩ፤ አገኘሁና አነሳሁ።ልወረውርበት አስብኩ። ምን ያህል እንደሚጎዳው ግን አላውቅም።
ብስተውስ? በህይወቴ የሚገጥመኝን ነገር አሰብኩት በማድረግ እና ባለማድረግ ውስጥ ሆኜ ታገለኝ# ማድረግ የሌለብኝን ነገር እየሞከርኩ እንደሆነ ገባኝ። የሆነ ነገር ባደርግ ስለማልገድለው የምጎዳው እኔ እንጅ እሱ አይደለም። መታገስ ነበረብኝ፣ የሰው ልጅ የሚታገሰው የውስጡን ብሶት እና ስሜቱን አፍኖ የሚይዘው፣ ስለፈለገ ብቻ ሳይሆን በግድ ጭምር እንደሆነተረዳሁ።የውስጤን ንዴት በትዕግስት አፍኜ በእጄ ልወረውረው ያነሳሁትን ድንጋይ ቀስ ብዬ መሬት ላይ ጣልኩት።
#ከኔጌር
ከመጽሐፉ የውስጥ ገጽ የተወሰደ