azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

« አንድዋ ልጅ እምቢ አላትና፣ ተቀሚሷ ሥር መአት ጨርቅ ጐዝጉዛ ባሏን አርግዣለኹ እያለች ስትዋሽለት መክረም»

«ማታ ሲተኙ አያያትም?» ስትል ታንጉት ጠየቀች፣ ነገሩ አስገረሟት።

« ያመኛል እያለች ለብቻዋ እየተኛች ነዋ! ዘጠኝ ወር ተሞላት በኋላ ምን ታርገው። አውራ ዶሮዋን አርዳ ደሙን ታልጋው ላይ አፈሰሰችና «አስወረደኝ» አለች ይባላል። ታዲያ ምን ተብሎ ተዘፈነላት መሰለሽ?
ጌጤ ነው ስሟ፣ እንግዲህ፦

የጌጤ አውራ ዶሮ ዘንድሮ ከበረ
ዘጠኝ ወር ተረግዞ ዐልጋ ላይ ሠፈረ

« እኔን ይንገሩኝ የምለው ገብርዬ መካን ቢሆንስ? ብለው የጀመሩትን ነው። ምን አለ እርሶማ የልጅ ልጅ አይተዋል» ስትል በመከፋት አንገቷን አቀረቀረች።

« ታልሽ ምን ቸገረኝ! አየሽ፣አንድ ልጅ እናቱ እንጂ አባቱ በእርግጠኛነት የሚታወቅ አይደለም። አባቱ ማን መሆኑን ምንአልባት በእርግጠኛነት የምታውቅለት እናቱ ብቻ ነች። አሁን ለምሳሌ እኔ ልጆቹን ለአባታቸው ልጆችህ ናቸው አልኩት እንጂ ተሌላ አርግዤአቸው ቢሆን በምን ያውቅ ነበር? እና አሁንም የሆነ እንደሆነ ፞ · ·» መጨረሱ የከበዳቸው ይመስል ተውት።

ወይዘሮ ደብሬ እንደሰጉት ሐሳቡን ታንጉትን በጣም አላስደነገጣትም። «እና ለገብርዬ ልጅ ተሌላ ወንድ ላርግዘለት ማለት ነው? » ስትል ከመገረም ጋር ጠየቀች።

«አንቺን አርጊው አላልኩሽም፤ ንገሪኝ ስላልሽ ነው፤ ባላቸው መካን ተሆነ የሚያደረጉ ሴቶች ግን አሉ።»

—ከብርሃኑ ዘርይሁን ፣«የታንጉት ምስጢር» 1979 ዓ.ም

ኤዞፕ መጽሐፍት የምንጊዜም ምርጥ ሙጽሐፍት አቅራቢ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ ሞት ተፈርዶብኛል፧ በቃ በሰይፍ ተቀልቼ እንድሞት፣ በሕይወት ከሚኖሩት ወገን እንድስረዝ ተበይኗል፡፡ እሺ መሞቱን ልሙት ለምን ስይፉን አይስሉትም? ይኼም ተንኮል እኮ ነው፧ቶሎ ሲጥ እንዳልል የተሸረበ ሴራ፤ በህይወት እና በሞት መካከል ያለን በግ እያየ የሚስቅ በግ አራጅ አለ? እኔን የገጠሙኝ ግን እየገዘገዙ የሚገድሉ ሰው አራጆች ናቸው፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

.
....💚...💛..❤.....

" ጥ ሩ : መ ጽ ሐ ፍ ቶ ች : ማ ን በ ብ : ካ ለ ፉ ት : መቶ : ዘ መ ና ት : ም ር ጥ : አ ዕ ም ሮ ዎ ች : ጋ ር: እ ን ደ መ ወ ያ የ ት : ነ ው ::"

ኢማኑኤል ካንት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ወደ_ኢነርጂ_ባህር_ለመጥለቅ_የሚያስችሉህ_4_መንገዶች

#አንድ
• ብቻህን ስትሆን ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል ለመዝፈን ሞክር

#ሁለት
• ከውሃ ጋር በፍቅር ውደቅ። በወንዝ አቅራቢያ የእግር ጉዞን አድርግ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ሰውነትህን ውሃ ውስጥ ንከረው፤ የራስህን ነጸብራቅ በውሃ ውስጥ ተመልከት፤ ውሃ ውስጥም የሚፈጠሩ ሽክርክሮታዊ ቅርጾችን አስተውላቸው። ይህን ማድረግህ በዩኒቨርስ ውስጥ ያለው የኢነርጂ ፍሰት ምን እንደሚመስል ማስታወሻ ይሆንሃል።

#ሶስት
• በጽሞና ውስጥ ሁን። ከጫጫታ ራቅ። ምንም አይነት ሙዚቃም ሆነ ዜናዎችን ለአንድ ሳምንት ያህል ላለመስማት ሞክር። የራስህን አእምሮ ብቻ አዳምጥ። ይህን ልምምድ ለአንድ ሳምንት ያህል አድርገው። ቀስ በቀስም እያሳደግከው ሂድ፡፡

#አራት
• የምታየውን እና ባንተ ላይ የተከሰተውን ለውጥ ሁሉ በማስታወሻ ደብተርህ ላይ አስፍር።

አሁን ላይ ያለህበት የሕይወት ወቅት ላንተ የጨለመ ክረምት እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል፤ ሆኖም ግን የጸደይ ወቅት መምጫው ተቃርቧልና ብርታትህን ጨምር። በራስህ እምነት ይኑርህ። አትወድቅምም!

ጥሩ የስነልቦና መጽሐፍ አንብቢት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ሺ ከአንድ ሌሊት እነሆ በመደብራችን ተገኝታለች ብቅ ብለው ለወዳጅ ዘመድ ስጦታ ይሸምቱ።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት ትግርኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት
1948

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እውነትም “ጠቢበ ጠቢባን”!
===+++===
ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው በግሩም ኹኔታ ተርጉሞ ያሳተመውን “ጠቢበ ጠቢባን” መጽሐፍ ፈርሞ ልኮልኝ አነበብኩት። ከገመትኩትም ከጠበኩትም በላይ ሆኖ አገኘሁት። ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም የሠራው ከትርጉምም በላይ ነው። (ስለ ሥራው ያለኝን ምልከታ ከታች በመጠኑ አነሳለሁ፤) በጣም የደነቀኝ ነገር ቅድሚያ ስለ መጽሐፉ ሕትመት ጥቂት ላንሣ።

የመጽሐፉ ጥራዙ የተመጠነ፤ መጠኑ መካከለኛ፣ ባለ ሙሉ ቀለም፣ ወረቀቱ ብራና አከል እና መሰል ነው። ሲገልጡት ለዓይን ተስማሚ መሆኑ አንባቢን በግድ ይጋብዛል። የሽፋን ገጹ መስሕብነት አለው፣ የውስጥ ገጾቹ ሐረጋት ጥበብ ልዩ ነው። በዘመናዊ ሕትመት ያልተለመደውን ስመ አምላክን እንዲሁም አርዕስቶችን በቀይ ቀለም በወጥነት ማስቀመጥ ምን ያህል አድካሚ ሊሆን እንደሚችል በበተለይ በሥራው ያለፈ ሰው የሚረዳው ነው። እንኳን ይዘቱ (ውስጡ) አምሮ ተሠርቶ ይሄ በራሱ ትልቅ ምሥጋና የሚያሻው ነውና ወንድማችን ኤፍሬም የኔሰው  ና ምሥጋናህን ውሰድ። ማተሚያ ቤቱም ሊመሠገን ይገባዋል።

ከወራት በፊት “ጠቢበ ጠቢባንን እየተረጎምኩ ነው” ብሎ ዲ/ኤፍሬም ሲጽፍልኝ ደስታዬ ብዙ ነበር፤ አሁን አልቆ ሳየው ከመደሰቴ የተነሣ ይህን የመሰለ፣ ጥንቅቅ ያለ ሥራ ነፍስ ሔር ፕ/ር ጌታቸው በሕይወት በኖሩና በመረቁት ብዬ ከልቤ ተመኘሁ። የትርጉም ሥራ ከባድ ጥንቃቄን የሚፈልግ እና በኮሌጅ ደረጃ ራሱን የቻለ ትምህርትም የሚሰጥበት የሙያ ዘርፍ ነው። የመገኛ ቋንቋውን እና ተቀባይ ቋንቋውን ማውቅ ብቻ በቂ አይደለም። እኔ እንደተመለከትኩት ከሆነ ዲያቆን ኤፍሬም ይህን “ጠቢበ ጠቢባን” መጽሐፍ ተረጎመው ብቻ ሳይሆን አመሠጠረው፣ ተነተነው፣ አብራራው እና የመጽሐፉን ክብር በተገቢ መልኩ ገለጠው ቢባል ማጋነን ሊሆን አይችልም። እንዲህ ያልኩበትን በሦስት ነጥብ ላሥረዳ፦

አንደኛ የተስተካከለ ትርጉም ነው፦
የመልክእ ምሥጋናን መተርጎም እንደሌሎች ጽሑፎች አይደለም። ይልቁንም ደግሞ መልክኡ በተዘጋጀበት ጥበብ በሥነ ግጥም ሲቀርብ ለጥንቱ የተጠጋ ይሆናል። በዚህ ረገድ ዲያቆን ኤፍሬም የግዕዙን መሠረት ሳይለቅ ምሥጢሩንም ዘይቤውንም ጠብቆ መስመር በመስመር ተርጉሞታል። ይህ ከፍተኛ የሆነ የሥነ ጽሑፍ ችሎታን የሚጠይቅ እና በግዕዝ ቋንቋ መዋኘትን ያጠይቃል። በዚያውም ላይ እናቱን (የግዕዙን ዘር) በተጓዳኝ ገጽ፣ አቻ ትርጉሙን (የአማርኛን) በትይዩ ማቅረቡ አንባቢውን ለዳኝነትም ለምርጫም ይጋብዛል፤ ማለፊያ ሥራ!

ኹለተኛ ጥንቅቅ ያለ አርትዖት፦
ታትሞ ለሕዝብ የሚቀርብ ነገር ከፍተኛ የአርትዖት ሥራ ያሻዋል። አንዳንድ መጽሕፍት (እንዲሁም ጋዜጦች) በሳል መልዕክት በውስጣቸው ይዘው በርካታ የፊደል ግድፈት፣ የሥርዓተ ነጥብ አለመስተካከል፣ እንዲሁም የጽሑፍ ፎርማቱ የተዘበራረቀ ስለሚሆን ጥራታቸውን ዝቅ ያደርገዋል። ዲ/ኤፍሬም የቀደመ የአርትዖት ሥራ ልምዱን በበለጠ በዚህ መጽሐፉ ላይ እንዳዋለው በግልጽ ይታያል። የፊደላቱ ለቀማ፣ የቃላቱ አመራረጥ፣ የቁጥሮች አጠቃቀሙ፣ ሥርዓተ ነጥብ አጠባበቁ ወዘተ ... የተዋጣለት ስለሆነ ይበል ወንድማችን ያሰኛል።

ሦስተኛ ማብራሪያና ትንታኔ የያዘ ሥራ፦
አብዛኞቻችን ስለ “ጠቢበ ጠቢባን” ምንነት ያለን ግንዛቤ አናሳ ነው፤ የመጽሐፉን ይዘት የሚያውቁት ደግሞ ጥቂቶች እንደሆኑ ይገመታል። “ጠቢበ ጠቢባን”ን የመሰለ ለፈጣሪ የቀረበ ልዩ ምሥጋና አለማወቅ ምን ያህል እንደሚያስቆጭ አሁን ስናነበው ይገባናል። መጽሐፉ መቼ እና በማን እንደተደረሰ የቀደሙ ሥራዎችን አመሳክሮ፣ የራሱንም ንባብ ጨምሮበት ወንድማችን ኤፍሬም ሰፊ ማብራሪያ አቅርቦልናል። በግዕዙ ድርሰት ላይ አማራጭ ቃላትን ሲጠቀም በምክንያት መሆኑን ለማወቅ በየገጹ ያሉትን የግርጌ ማስታዎሻዎች መመልከት ነው።  “እንዲህ የሚል ዘርም ይገኛል” ብሎ ይገልጻል።  ይህ ዓይነቱ ሥራ በፊሎሎጂ (የጥንታውያን ጽሑፎች ጥናት) ባለሙያዎች የተመሳከረ ሕትመት (critical edition) የሚሉት ዓይነት ነው። ይህን ሥራ ይበልጥ የተደከመበት እንደሆነ የሚያሳየው ዐሥር የሚያህሉ ተመሳሳይ የብራና ቅጂዎችን መዘርዘሩ፣ የታተሙ የጸሎት መጻሕፍትንም ማካተቱ ነው። ይህም ለሌሎች ተርጓሚዎች በጎ ምሳሌ ነው፤ (በእርግጥ ይህም የተሻለ እንዲሆን በቀጣይ ቢጨምራቸው የምላቸውን ሁለት ያህል ነጥቦች ከታች እገልጻለሁ)።

ይህን የመሠለ ውብ ሥራ ስላቀረበልን ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም ከልብ መመሥገን ይገባዋል።  መጽሐፉም በሚገባ ሊተዋወቅና ሥራው ሊነገርለት ይገባል፤ ከምር በሆነ አስተያየት ብዙ ሊባልለት የሚገባው ነውና። ይህን ካልኩ ዘንድ to be fair እንዲል ፈረንጅ በሚቀጥለው ቢያሟላቸው የምላቸውን ሁለት አስተያየቶች ላቅርብ።
  -የመጀመሪያው የተረጎመልን የየትኛውን ቅጂ ጠቢበ ጠቢባን እንደሆነ ግልጽ ቢያደርገው? ያደገበትን የፍኖተ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅጂ ነውን ከሆነስ የመቼ ዘመን? ወይስ የጎንደሩን? የጣናውን? ወይስ ከውጭ ሀገር ከሚገኙት የቱን? እርግጥ ነው ይሄ ሃሣብ ይበልጥ ትርጉም የሚሰጠው በጥናትና ምርምር ለሚሠማሩ ቢሆንም ለጠቅላላ አንባቢም ቢሆን ማለፊያ ነው።  
  -ኹለተኛው ነጥብ ያሉን በርካታ የጠቢበ ጠቢባን ቅጂዎች መሆናቸው ይታወቃል፤ ሁሉንም መዘርዘር ባይጠበቅበትም ግን በርካቶች እንዳሉ ቢገልጽና እሱ ግን የተረጎመልን ይሄን እሱ ያገኘውን መሆኑን ቢጠቁመን ጥሩ እንደነበር ይሰማኛል።

ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም ሆይ፦
ጠቢበ ጠቢባን የሆነ ልዑል እግዚአብሔር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን ገልጾልህ፣ ትጋቱንም አድሎህ ወደ ፊትም ሌሎች መጻሕፍትን በነካ እጅህ ጽፈህ፣ ተርጉመህ እንድታደርሰን አደራ እንልሀለን
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የመጀመሪያው እትም
ፍቅር እስከ መቃብር ጨረታ በሚያስደንቅ ኹኔታ ተጠናቃላች !!!

ሀሳባችን ብዡ ይጠይቁን የነበሩትን ወዳጆቻችንን ማስደሰት ነበር ከልብ ከሚፈልጋት ሰው እጅ ገብታለች!!!!



ይኽ መጽሐፍ እጃችኹ ላይ ካለ እስኪ በድጋሜ እናሳስባችኹ የትኛው ቅጅ ነው ያለዎት !!!!


ካለውት እሰየው ብለናል !!!

ከሌለዎትም ድጋሜ ጨረታ እናወጣለን !!!
ይጠብቁን !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በገበያ ላይ



የሃያኛው ክፍለ ዘመን  መግቢያን የኢትዮጵያ ታሪክ ያወሳል።

የልጅ ኢያሱ፣ የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እና የተፈሪ መኮንን ታሪክ
ሀገራችን አሁን ያለችበት በቅጡ ለመረዳት የሃያ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምረን ማጥናት እንደሚጠበቅብን ምሁራን ያስረዳሉ ለዚህም ይረዳን ዘንድ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ትእዛዝ ተሰንዶ የነበረው መጽሐፍ ተዘጋጅቶ ቀርቦልናል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ ነሐሴ 10
የምንወደውን የምናከብረው ደራሲ አበራ ለማ መደብራችን ተገኝቶ ነበር።

ጋሽ አበራ ለማ ብዙ የግጥም መጽሐፍትንና አጫጭር ልቦለዶችን አሳትሟል።
በተለይም ሞገደኛው ነውጤ የተሰኘው ልቦለድ ሥራው ዘመን አሽሬና በአንባቢያን ዘንድ አይረሴነት ያለው የመካከለኛ አጭር ልቦለድ ታሪክ ነው።


ጋሽ አበራ የደራሲ በብርሃኑ ዘሪሑን ሥራዎች ላይ ሀሳብ አንስተን ብዙ ተወያየን። ለብርሃኑ ዘሪሁን የነበራቸውን ታላቅ እክብሮትና የብርሃኑ እምቅ ችሎት እሳቸው ካላቸው ረጅም የስነ ጽሑፍ ልምድ ጋር እያገናዘቡ ብዙ ታሪክና ልምድን አካፈሉኝ።

ታዲያ በጽሑፎቻቸው ኮትኩተው ያሳደጉንን ታላላቅና አንጋፋ ደራሲያንን እድሜና ጤና ይስጥልን እያልኩ ጋሸንም ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን ብየ ሸኘዋቸው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"የአምላክ እናት ሆይ አልተለየሽኝም"
ታላቅ የምሥራች (የፍልሰታ ስጦታ) ለመጻሕፍት አንባብያን 27ኛው ዐዲሱ የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 2" መጽሐፍ ታትሞ ለአንባብያን ቀረበ። ይኽ መጽሐፍ ልዩ የሚያደርገው ከ4ኛው - 9ኛው ክፍለ ዘመን የተነሡ 26 ታላላቅ ሊቃውንት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትን ያካተተ ሲኾን፤ እነዚኽም፦
✍️ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘሳለሚስ
✍️ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
✍️ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
✍️ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

👉 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
👉 አንፊሎኪየስ ዘኢኮንየም
👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
👉 አምብሮስ ዘሚላን

💥 ቅዱስ ጀሮም
💥 አውግስጢኖስ ዘኂጶ
💥 ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
💥 ፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ

☀️ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ
☀️ ካኤሉስ ሴዱሊስ
☀️ ጴጥሮስ ክሪሶሎጎስ (ቃለ ወርቅ)
☀️ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

✍️ ቅዱስ ያሬድ
✍️ ሮማኖስ ማሕሌታይ
✍️ አካቲስት መዝሙር
✍️ ጎርጎርዮስ ዘቶረስ

💧 ቬናንትዩስ ፍርቱናቱስ
💧 ጎርጎርዮስ ታላቁ
💧 ኢሲዶሬ ዘሳቪሌ
💧 ጀርመኑስ ዘቁስጥንጥንያ
💥 እንድርያስ ዘክሪቴ
💥 ዮሐንስ ዘደማስቆ ይገኙበታል።

💥 ይኽንን በሕይወት ዘመንዎ ሊያነቡት ሊኖሮት፤ የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጣትን ክብር የሚያሳውቆት መጽሐፍ ነው።
💥ከ5 ዓመት በፊት ወጥቶ የነበረው "ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1" ከ1ኛው - 3ኛው ክፍለ ዘመን የተነሡትን የ25 ሊቃውንት ትምህርት ያካተተ ሲኾን በኹለቱ መጻሕፍት የ51 አባቶች የነገረ ማርያም ትምህርትን ለአንባብያን አቅርቤያለሁ። በሱባኤያችሁ እያነበባችሁ ተጠቀሙበት።
"ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዐተ ወልዳ"
(የእመቤታችን ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን)

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቤባንያ በመደብራችንይገኛል።

!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

<ሞት እንደሁ ልሙት በሴኮንድ መቶኛ፣
እንቅልፍ እንደሬሳ ዘለዓለም ልተኛ።
ሰማየ ሰማያት እመዘብራለሁ
የተዘጋውን በር እበረግዳለሁ።
የሌለ እስቲፈጠር የሞተ እስቲነቃ
በትልቅ እርምጃ ከመሬት ጨረቃ
ከጨረቃ ኮከብ
ካንዱ ዓለም ወዳንዱ
ስጓዝ እፈጥናለሁ
በፀሐይ ላይ ቤቴን ጎጆ እቀልሳለሁ።
.......መንገድ ስጡኝ ሰፊ
ፀሐይ ልሁን ፀሐይ
እንደ ፅርሐ አርያም ሁሉንም የሚያሳይ
እሳተ ገሞራ አመድ ዕረመጡን
ጎርፍ የእሳት ጎርፍ ልሁን።
......መንገድ ስጡኝ ሰፊ
ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እነዚህን አራት መጽሐፍት
እጅግ በማይታመን ዋጋ

በ200 ብር ብቻ !!

አንዱን በሚገዙበት ዋጋ አራቱን መጽሐፍት ይሸንቱ !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ታላቅ የመጽሐፍ ምርቃት
==============
የደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ "የአማርኛ ጥበበ ቃላት"የተሰኝው አዲስ መጽሐፍ ቅዳሜ ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት በሐገር ፍቅር አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።

መግቢያ በነፃ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

" THE POWER OF NOW" እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1997 በኤክሃርት ቶሌ ድንቅ
መጽሐፍ ነው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ በጉዞየ ካጋጠመኝ የነጋድራስ ገብረ ህይዎት ባይከዳኝ መንግስትና የህዝብ አስተዳደር መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ትርጉም !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የዘፈን ግጥም ደራሲና ጋዜጠኛ ፤ የሴቶች መብት ተከራካሪ የሸዋሉል መንግስቱ በሃረር በአፋን ኦሮሞ የሬድዩ ስርጭት ፕሮግራም ከእውቁ ጋዜጠኛ የሙዚቃ ግጥም ፀሃፊና ደራሲ የአፍራን ቀሎ ባንድ መስራችና ዋና አሰልጣኝ አቡበከር ሙሳ ጋር በመሆን በርካታ የሬዲዩ ፕሮግራሞች በጋራ ይሰሩ ነበር ፣ ከሰሯቸው የሬዲዩ ፕሮግራም መካከል ቅናተኛዋ ሚስት "Jaarti hinaaftu" በሚል የሰሩት የሬድዬ ድራማ በወቅቱ ተወዳጅ ነበር ።

ደራሲና ጋዜጠኛ የሸዋሉል መንግስቱ ከዚህ ቀደም ብሎ በሃረር ከተማ 1962 ዓ/ም ጽፋው በ1968 ዓ/ም በፊንፊኔ የታተመው "እስከ መቼ ወንደላጤ " የሚለው ተወዳጅ ድርሰቷ ይህ ነበር :

በነገራችን ላይ የሸዋሉል መንግስቱ ሀረርጌ ካበቀላቸው የዘፈን ግጥም ደራሲያን ውስጥ እንቁ የጥበብ ባለሙያ ነበረች። የዘፈን ግጥሞቿን ለተለያዩ ድምፃውያን ያበረከተች ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ለድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ፣ ለድምፃዊ መሀሙድ አህመድ፣ ለክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ፣ ለክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ እና ድምፃዊ አስናቀች ወርቁ በዋናነት ይገኙበታል። ለምሳሌ :-
☞ለድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ
♪ አካም ነጉማ

☞ለድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ
♪ጀመረኝ
♪ትዝታ
♪ህልም ሆነሽ ቅሪ
♪ጉብል ቀዘባ
♪የምንጃር ሸጋ
♪በእኔ ሞት
♪ውብ አበባ
♪መውደድሽን ብታውቂው
♪ባይሽ ደስ ይለኛል
♪ከሴት እሷ ብቻ

☞ለድምፃዊ መሀሙድ አህመድ
♪አሸወይና
♪ትዝታ
♪ኦሆሆ ገዳማ
♪ስደተኛ ነኝ
♪እንዴት ነሽ ገዳዎ
♪መላ መላ
♪አታውሩልኝ ሌላ
♪መቼ ነው
♪ሳምራዬ

☞ለድምፃዊ አሊ ቢራ
♪ አዋሽ
♪ወይ ሆቢ ሆቢ

☞ለድምፃዊት አስናቀች ወርቁ
♪ እህ ልበል
♪ሰላ በልልኝ

☞ለድምፃዊ አያሌው መስፍን
♪ ሄደች ጋራ ዞራ
ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ
Negash Qemant


አንድ ኮፒ መጽሐፏ እጃችን ላይ አለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አለመኖርን ተመኝቶ ፣
አለመኖርን ፈልጎ ያውቃል፡፡

“አለመኖር ምንድነው?” ተብሎ ቢጠየቅ ግን መልስ የለውም፡፡

“መኖር ራሱ ምንድነው? ለምንድነው የምኖረው?” ጥያቄዎቹ ናቸው፡፡

“ሰው ካለአንዳች ዓላማ ወደ ምድር አልመጣም! ወደ ምድር አይመጣም!” ሲባል ሰምቷል፡፡

ባይረዳውም፡፡

“ሰው ካለአንዳች ዓላማ ወደ ምድር አልመጣም!” ማለት ምን ማለት ይሆን?

ዓላማ ራሱ ምንድነው?

የማንን ዓላማ ነው የሚያስፈጽመው?

“ዓላማህን አስሰህ አሳካው!” ብሎ የላከውስ ማነው?

ሰው በምድር ሲኖር የግድ ዓላማ መሰነቅ ይጠበቅበታል?

ምናልባት የአንድ ሰው ዓላማ ያለ ዓላማ ኖሮ ማለፍ ሊሆን አይችልም?...

"ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የኰለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ገጽታ

****

ርዕሰ ፦ ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ
ደራሲ ፦ ሥዩም ወልዴ
የመጽሐፉ ይዘት፦ ግለ ታሪክ
ዘመን ፦ 2002 ዓ.ም
( ሒሳዊ ንባብ)

በቸኛው የሥነ ጥበብ ኀያሲ ሥዩም ወልዴ፤ «ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ»የተባለው መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕትመት የበቃው በ2002 ዓ.ም ሲሆን፣ እሱም ከፍተኛ ግምትና አድናቆት አትርፏል። ይህ መጽሐፍም በ2007 ዓ. ም ለሁለተኛ ጊዜ ታትሟል ። ሆኖም ግን ደራሲው የመጽሐፉን የሕተመት ብርሃን ሳያይ ሞት ቀደመው።

ይህ መጽሐፍ የሥዩም ወልዴ የአምሳ ዓመታት ጉዞው የገጠመውና ያየውን ለዛ ባለው የትረካ ስልት ተከትሎ የዕድሜ ዘመኑን ትውስታ የመዘገበበት ነው።

«ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ» በሦስት መዕራፎች የተከፈለ ነው። አሥራ አምስት ፎቶዎች እና የደራሲው የሥዕል የፈጠራ ወጤቶች የተካተቱበት ሲሆን፣ በ345 ገጾች የቀረበ ነው።

መዕራፍ አንድ«ደማቁ ጠዋት»የሚል ሥያሜ ይዟል። ይህ ክፍል የልጅነት ጊዜያቱን፣ ከቄስ ትምህርት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሕይወቱ ላይ ያተኩራል።

ሁለተኛው ምዕራፍ፣«መንገዳማው ረፋድ» የሚል የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርስቲ የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝቶ በመጓዝ በትምህርቱ ቆይታው ያጋጠመውንና የታዘበውን ሁኔታ ሲሆን፣ በሥነ ጥበብ ታሪክ የጥበብ ንድፈ ሐሳብና የኀያሲነት ትምህርቶች ወስዶ የኤም, ኤ, ዲግሪ ተመርቆ ወደ አገሩ ሲመለስ የሚተረክበት ምዕራፍ ነው።

ሦስተኛው መዕራፍ፣ «ያልጠረረ ቀትር» የተሰኘ ነው፤ ይህ ክፍል ደግሞ በሕይወቱ የገጠመውን ግላዊና አገራዊ ድርጊቶች የሚያስነብብበት ነው።

የመጽሐፉ ተራኪ በመግቢያው እንዲህ ይላል፦«ይህ ነበር ጉዞዬ ብዬ በዚህች ጽሑፍ ውስጥ ያቀረብኩት ሁሉንም አይደለም፤በጣም ጥቂቱ ነው፤ ያስታወስኩትን ያህል፤ አንባቢዬን እየፈራሁና እየተባው ነው የፃፍኩት፤ ምክንያቱም በአገሬ «እኔ» ብሎ መፃፍ ባለ መለመዱና የግል ሕይወት ገጠመኝ ታሪክ አጻጻፍ ሊዳብር ባለመቻሉ እንግዳነት እየተሰማኝ ነው፤ ትውስቴን ያሰፈርኩት፤ስለዚህም አንባቢዬን ከዚህ ይልቅ የሌላ ነገር ብጽፈለት የበለጠ ይረካ ነበር እያልኩ የፈራሁት» (ገፅ 7 ላይ)።

የደራሲው ሥጋት እውነትነት ያለሁ ነው፤ ምክንያቱም በአንደኛ መደብ (እኔ) ትረካ የተአማኒነት ጥያቄ የሚያጭሩ ጉዳዮች መኖራቸው ሐቅ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥም ለመቀበል የሚከብዱ ታሪኮች ያጋጥማሉ፤ ከነዚህም መካከል የፊደል ካስትሮ ወደ ኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ሆኖ ምጣታቸውን ተከትሎ በአደባባይ ላይ የጓድ መንግሥቱና የኩባው መሪ የነበሩት የፊደል ካስትሮ ፎቷቸው በሥነ ጥበብ ባለ ሙያ የተሠረው ምስል መሠራት ተከትሎ የሚፈጠረውን የወዝግብ ሁኔታ ተራኪው ስዩም ያቀረበውን ቀጥለን እንመልከት።

«ከተሰጡኝ ተግባሮች አንዱና አጣዳፊው በዘጠኝ ቀን ተሠርተው እንዲያልቁ የታዘዙት የክብር እንግዳ የኩባው ፊደል ካስትሮ እና የደርጉ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሰምንት የአደባባይ ትላልቅ ምስሎች ሥራ ነው። አንድ ነባር ሠዓሊና አንድ በዚያው ዓመት የተመረቀ ወጣት ሠዓሊ ምስሎቹን እንዲሠሩ ተደረገ፤ ነባሩ የሊቀመንበሩን፤ ወጣቱ የእንግዳውን ከሠሩ በኋላ ጳግሜ 5 ቀን በየተወሰነላቸው ሥፍራዎች ተሰቀሉ።

መስከረም 1 ቀን 1971 ዓ, ም, ከፍተኛ ግርግር ተፈጠረ፤ «ሠዓሊዎቹ እንግዳውን አሳምረው (ካስትሮን) አስተናጋጁን ሊቀመንበር (መንግሥቱን) እጅግ አስቀያሚ አድረገው ነው የሠሩት» ተብሎ ሰለተተቸ የበዓሉ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት በሙሉ በከፍተኛ መደናገጥ ትርምስ ፈጠሩ» ካለ በኋላ ተራኪው ሥዩም የተጠየቀውንና ለማመን የሚከብደውን አስገራሚ መልስ እንዲህ ይመልሳል።

«እንደዚያ አበላሽቶ የሥራውን ሠዓሊ በአስቸኳይ ፈልጌ እንዳቀርብ ታዘዝኩኝ፤ የእምነቱንና አመለካከቱን፤ ፀረ- አብዮተኛ መሆን አለመሆኑ፤ በሊቀመንበሩ ላይ ጥላቻ ያለው ወይም የሌለው መሆኑን ተጠየቅሁ። በበኩሌ አፍራሽ መልስ ከመስጠት በስተቀር የተጠየቀውን ጥያቄ ሁሉ የሚደግፍ መልስ አልሰጠሁም። ነፍሴን ስላስጨነቋት የሰጠውት መልስ አንድ ነገር ነው፤ ለሊቀመንበሩ ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን መልክ ሠዓሊው በምንም መንገድ መለወጥ እንዳልነበረበትና ለሥራ እንዲረዳው ሞዴል ሆኖ በተሰጠው ፎቶግራፍ ላይ አሳድጎ ከመሥራት ውጪ ምንም ዓይነት የአሠራር ሰሕተት እነዳልነበረ ያበጠ ይፈንዳ ከሚል አቋም በድፈረት የጭንቄን ሳረጋግጥ «በያሉበት የተሰቀሉት ሁሉ ወርደው በተቻለ መጠን ይስተካከሉ፣ ይመሩ፣ ይቆንጁ እባክህ» ወደሚለው ሐሳብ አዘነበሉ። አራቱም ምስሎች ከየተሰቀሉበት ወርደው ሌሎች ሠዓሊዎች ተፈልገው ተፈጥሮ ያስገኘችው እውነት በጥበብ ተለውጦና ተውቦ እንዲቀርብ ተደረገ።» ይለናል።

በእኔ ትሑት አስተያየት ሥዩም ወልዴ «ለሊቀመንበሩ ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን መልክ ሠዓሊው በምንም መንገድ መለወጥ » አይችልም ብሎ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ይህንን መልስ በዘመነ ደርግ ይመልሳል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል። ለማንኛውም መጽሐፉ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉት። አንብቡት።

ፀጋየ ገብረ መድህን ሮበሌ !!!


/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አስራ አንደኛው በተሰኛው መጽሐፏ የምናውቃት ይቱስራ ምትኩ ድንቅ መጽሐፍ ይዛ እየመጣች ነው።


በቅርብ ቀን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት እትም የታሪክ መጽሐፍት !!
እነኾ ከኤዞፕ መጽሐፍት !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ግልጽ ጨረታ በሉት !!!

ይኽንን ፍቅር እስከ መቃብር አይታችኹታል።
እስካኹን ባለኝ የመጽሐፍት ሽያጭ ዘመኔ የመጀመሪያ የኾነውን ምንም ያልተነካካ ያልተበረዘ ያልተከለሰ እትም የ1958 ዓም እትም ገጥሞኝ አያውቅም።

እነኾ ይኽንን የመጀመሪያ እትም መጽሐፍ በደምበኛ ትዕዛዝ መቀበያ ደብተራችን ላይ ያለንን ትዕዛዝ ስመለከተው ከ25 ይበልጣል። በመኾኑም ለማን ሰጥቸ ለማን የለኝም ልበል። ስለዚኽ ይኽንን ጽሑፍ ቀድሞ አይቶ ለደወለልልን፣ ላዘዘን ፣ ደምበኛችን ብቻ የምንሰጠው ይኾናል ።

አስታውሱ ይኽ ቅጅ የ1958 ዓም ነው።

ትዕዛዝ _ እስኪ እጅወ ላይ ያለውን የፍቅር እስከ መቃብር እትም ይመልከቱ ?

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የተወሰነ ኮፒ እጃችን ላይ ይገኛል

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

" ዛሬ ቅዳሜ አይደለም " የተሰኘው መጽሐፍ እየተነበበ ነው ::

" ...ከመውለዷ በፊት የህክምና ክትትል የሚባል ነገር አድርጋ አታውቅም፡፡
ይህን ታደርግ ዘንድ አልደላትም፡፡

እንደብዙዎች እናቶች የምትወልድበትን ፣
ሕይወት ወደ ምድር የምታመጣበትን ፣
እድሜ ልኳን ስትሳሳለት ከምትኖርለት ፍጡር ጋር የምትገናኝበት ቀን አልናፈቃትም፡፡

ልጅ እኮ የፈጣሪ ጸጋ ነው ፣ ስጦታ ነው ፣ በረከት ነው ፣ ሲሳይ ነው… የሚሉ ቃላት አልሸነገሏትም፡፡

ልጅነቷን ቀርጥፎ ልጅነቱ የሚያብብ ፣
ወዟን አርግፎ የሚወዛ ፣
ጉልበቷን አፍስሶ ጉልበቱን የሚያጠነክር ፣
ቅስሟን ሰብሮ ተስፋውን የሚፈነጥቅ ፣
ተስፋዋን ንዶ ድሎቱን የሚገነባ ፣
ድሎቷን ሰውቶ ምቾቱን የሚያደላድል ፣
እሷን ገድሎ እሱ የሚኖር እርግማን በማህፀኗ ስላለመሸከሟ እርግጠኛ አይደለችም፡፡

እንቡጥ ሴትነቷን ለቀጠፈ አምሳያ ይሆን ዘንድ ትውልድ አትፈልግም፡፡
የእሱ አይነት ዘር ሊጠፋ እንጂ ሊተካ ፣ ሊመነጠር እንጂ ሊበዛ አይገባውም፡፡

ወለደች፡፡

ተስፋዋ ጨልሞ ተስፋ አመጣች፡፡

እሷ ስትታረዝ ሊለብስ ፣ ስትራብ ሊጠግብ ፣ ስትጠማ ሊረካ… ወለደች፡፡... " :

ከመጽሐፉ የተወሰደ "ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የታሪክ ተመራማሪው ባህሩ ዘውዴ ሥራዎች በጥቂቱ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

https://vm.tiktok.com/ZM2caeVbo/

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

2016 ዓ.ም.
የኪዳነ ምሕረት ዓመት

የዘንድሮው ጾመ ፍልሰታ ብዙ ጥይቄ የሚመለስበት እንዲሆን እንጠብቃለን:: እመቤታችን በፍልሰትዋ ከሀገራችንም ከቤተ ክርስቲያናችንም የፈለሰውን ሰላምና ፍቅር በምልጃዋ እንድትመልስልንና የእርስዋን ትንሣኤ ሐዋርያት ባዩበት ጾም እኛም የቤተ ክርስቲያናችንንና ተስፋ የማንቆርጥባትና ብዙ ታውፋንያዎች የተረባረቡባትን የሀገራችንን ትንሣኤ የምናይበት ያድርግልን:: የድንግሊቱን ትንሣኤ የማያምኑ እንዳሉ ሁሉ የቤተ ክርስቲያንና የሀገር ትንሣኤ ከዚህ በኋላ ተስፋ የለውም የሚሉም ይኖራሉ:: እኛ ግን በቶማሳዊ የእምነት ደመና ላይ ሆነን የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን የሰላም ትንሣኤ እንጠብቃለን:: የሀገራችንን ችግር የሚፈታ ምንም ዓይነት ምድራዊ ጠቢብ የለም ጠቢበ ጠቢባን ልዑል እግዚአብሔር እርሱ ብቻ እጁን እንዲያስገባና እጅዋን ወደ እርሱ የምትዘረጋውን ሀገር "ወዳጄ ሆይ ተነሽ" ብሎ እንዲያስነሣት እንጠብቃለን:: በዕንባ የቀረበ ጸሎት የማይፈጽመው ነገር የለምና 2016 የኪዳነ ምሕረት ዓመት እንዲሆን በዚህ ሱባኤ እንማጸናለን::

ለሱባኤው አንድ ውብ የጸሎት መጽሐፍ ሥጦታ ሆኖ ቀርቦልናል:: ጸሎቱ እጅግ ጥንታዊ ጸሎት ሲሆን እጅግ ውብ አድርጎ ከግእዝ ወደ አማርኛ ከቅኔያዊ ለዛው ጋር የመለሰው ደግሞ ኤፍሬም የኔሰው ነው:: መጽሐፉን ከሱባኤ መልስ በደንብ እንተነትነዋለን:: ሰሞኑን ግን ብትጸልዩበት መንፈሳዊ ደስታ የምታገኙበት መሆኑን ስታነቡት ታምኑኛላችሁ::

ሱባኤውን የስርየት ያድርግልን የነደደውን እሳት ያብርድልን ለግፉዓን የሚበቀልላቸው አምላክ ፍትሕ ርትዕን ያድርግልን:: 2016 ዓ.ም. የኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ቃልኪዳን) ዓመት ይሁንልን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#10_ምክሮች_ከ_ኢትዮጵያዊው_የበረሃ_መልእክተኛ_መጽሐፍ

የኢትዮጵያውያንና ግብጻውያን የበረሃ መልዕክተኞችን ጥበብና ምክር ከያዘው   #ኢትዮጵያዊው_የበረሃ_መልእክተኛ መጽሐፍ የተወሰዱ አስር ሕይወት ቀያሪ መልእክቶች

#አንድ
አባ ዮሐንስ ሐጺር እንዲህ ይሉናል “በየቀኑ ብትወድቅ አትደናገጥ፤ ትልቁ ችግር ያለው ከመውደቅህ ላይ ሳይሆን፣ ለመነሳት አለመፈግህ ላይ ነው።”

#ሁለት
አንድ አባት እንዲህ አሉ “ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ የሚለውን ቃል የሰው ልጅ ቢያስታውስ፣ ዝምታ መልካም መሆኑን ያውቅ ነበር”

#ሶስት
አንድ አባት እንዲህ ይሉናል “እንደ አንበሳ ያለስ ጠንካራ አውሬ የታለ? ሆኖም ለሆዱ ሲል ወጥመድ ውስጥ ይወድቃል፤ ሆዱ ደካማ ጎኑም ነው። እኛም ሆዳችንን ካስቀደምን እንወድቃለን”

#አራት
እማሆይ ሲንቅላጢቃ እንዲህ ይሉ ነበር “ስንጀምረው ብዙ ውጊያዎች ይኖሩብናል፤ መልካም በማድረግና በእኩይ ሃሳቦቻችን መሃልም እንወጠራለን። ልክ እሳትን እንደማንደድ ነው፤ እሳቱን ማያያዝ ስንጀምር ጭስ ይኖራል፣ ያስለቅሰናልም፤ እናም በዚህ ሁኔታ የምንፈልገውን እናገኛለን።"

#አምስት
እማሆይ ሳራ እንዲህ ይሉ ነበር “ሁሉም ሰው መልካም ሆኖ በስርዓት ውስጥ ይኑር ካልሁ፣ ራሴን በእያንዳንዱ ሰው ክፋት ሲከፋ አገኘዋለሁ፤ ሆኖም የምጸልየው የእኔ ልብ ለሁሉም ሰው ንጹህ እንዲሆን ብቻ ነው”

#ስድስት
አባ ዮሐንስ ሐጺር እንዲህ ይላሉ “እኔ ልክ በዛፍ ስር እንደተቀመጠ ሰው ነኝ፤ ብዙ አራዊቶችና የምድር ተሳቢዎች ወደኔ ሲመጡ ካየሁም፣ በቶሎ ወደ ዛፉ እወጣለሁ። በዚሁ መንገድ በበኣቴ ላይ ተቀምጬ፣ እኩይ ሃሳቦች ወደኔ ሲመጡ ካየሁ፣ እነሱን መቋቋም አልችልምና ወደ አምላኬ በጸሎት እሮጣለሁ፣ ከጠላቶቼም ያድነኛል፣ ዘላለምም እኖራለሁ”

#ሰባት
አንድ ወንድም ወደ አባ ጴሜን ቀረበና ጠየቃቸው “አባ፣ ስለኃጢአቶቼ ምን ላድርግ?” ሽማግሌውም መለሱለት “ኃጢአቶቹን ማጽዳት የፈለገ ያልቅስ፣ መልካም ማድረግን የፈለገም ያልቅስ፣ መጽሐፍ እና አባቶች እንዳስተማሩንም ከእንባ በቀር መንገድ የለም”

#ስምንት
አባ ጴሜን እንዲህ ይሉ ነበር “ኃጢአትን ሰርቶ ከማያውቅ ሰው ይልቅ ኃጢአትን ሰርቶ የተጸጸተን እመርጣለሁ። የመጀመሪያው ፍጹም በመሆኑ ሲታበይ፣ ሁለተኛው በትህትና ውስጥ ይኖራል።

#ዘጠኝ
አባ ጴሜን እንዲህ ይሉ ነበር “የክፋት ስራ በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መሃል እንደ አጥር ሆኖ ይጋርዳል፤ ሆኖም ይህን አጥር ለማለፍ የሰው ልጅ እንዲህ ማለት አለበት - በአምላኬ ቅጥሩን እዘልላለሁ። (መዝ ፲፰፥ ፳፱) ስራው ሁሉ መልካም የሆነው እግዚአብሔርም ቅጥሩን ያሻግረዋል።”

#አስር
አንድ አባት ስለ ፍትወት ምኞት እንዲህ አሉ “ልክ በሆቴል ቤት ደጃፍ እንደሚያልፍ ሰው ሁን፤ የሚቀቀለው ስጋ ሽታ ወደ ውስጥ ይጠራዋል፣ ሆኖም መግባት አይፈልግም አልፎ ይሄዳል። ከነዚህም መጥፎ ሃሳቦች ይሸሻል “የእግዚአብሔር ልጅ፣ እርዳኝ” ይላል። ስለሃሳቦችም ተመሳሳይ ማለት ይቻላል፤ የሃሳቦቻችን ምንጭ እኛ አይደለንም፣ ምን ማሰብ እንዳለብንም መምረጥ አንችል ይሆናል። ሆኖም ግን የትኛው ሃሳብ በእኛ ላይ ሃይል ይኑረው የሚለውን መምረጥ እንችላለን።”

ይህ ድንቅ መጽሐፍ በመላው ኢትዮጵያ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

#ኢትዮጵያዊው_የበረሃ_መልእክተኛ መጽሐፍ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

‹‹ትምህርት የሌለው ሕዝብ ዘንድ ንጉሥ ማለት እና መንግሥት ማለት ትርጉሙ አንድ ነው፡፡ ንጉሣቸው የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ መላው ሕዝብ ባሮቹ ናቸው፡፡ አዕምሮ ባላቸው ሕዝቦች ዘንድ ግን መንግስት ማለት ማኅበር ነው፡፡ ንጉሣቸው የማኅበራቸው አለቃ ነው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ የፈቀደውን ያደርግ ዘንድ አይችልም፡፡ ሥልጣኑ የሕዝቡ ማኅበር በደነገገው ሕግና ወግ የተወሰነ ነው፡፡ አዕምሮ የሌለው ሕዝብ ሥርዓት የለውም፡፡ ሥርዓት የሌለው ሕዝብ የደለደለ ኃይል የለውም፡፡ የኃይል ምንጭ ሥርዓት እንጂ የሠራዊት ብዛት አይደለም፡፡ ሥርዓት ከሌለው ሰፊ መንግስት ይልቅ በሕግ የምትኖር ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች፡፡...››

አጤ ምኒሊክና እና ኢትዮጵያ ገጽ 9 - 10

ራሳቸው ገብረሕይወት ባይከዳኝ ላጠነጠንነው ሐሳብ ተገቢ ማሳያ ሊሆኑን ይችላሉ፡፡ እኒህ ሰው ከዘርዓያዕቆብ በኋላ ብቅ ያሉት ትልቁ አሰላሰይ እንደነበሩ የብዙዎች ስምምነት አለ፡፡ ከኤሮፓ በተመለሱ በጥቂት ዓመታት ልዩነት እቴጌ ጣይቱ ሥልጣን የጨበጡ ሰሞን ለሀገሪቱ የሚበጅ የተለየ ሐሳብ በማንሳታቸው እቴጌይቱ ስለተጣሏቸው ወደ ሱዳን ለመሰደድ ተገደዱ፡፡ እዚያ በጽኑ በሽታ ተይዘው ከሞት አፋፍ ተረፉ፡፡ አጤ ምኒሊክና ኢትዮጵያን የጻፉት በዚህ የስደት ዘመን ነው ይባላል፡፡ ግን በመጽሐፋቸው ውስጥ አንዳችም ዓይነት የጥላቻ ስሜት አላንጸባረቁም፡፡ እንደሚባለው እቴጌይቱ ገለል ብለው ልጅ እያሱ በሞግዚት ማስተዳደር እንደጀመሩ ሲሰሙ ወደ ሀገር ቢመለሱም እያሱም በአጫዋቾች እየታጀቡ መኳንንቱን በማታገል ከመዝናናት በቀር ለሀገር ዕድገት ለሚበጅ ምክክር በጄ የሚሉ አልሆኑም፡፡

የተፈሪም መንገድ ከልጅ ኢያሱ የሚሻለው በጥቂቱ ብቻ ይመስለኛል፡፡ በዘመኑ በአንጻራዊነት የተራመዱ የነበሩቱ ሁለቱ ሰዎች (ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝና ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም) በበቂ ሁኔታ ሁለቱን መንግስታት የማማከር ዕድል አላገኙም፡፡ ተክለሐዋሪያት እንዲያውም ለጥቂት ጊዜ ታስረዋል፡፡ ብዙውን ዘመናቸውን አገዛዙን ተቀይመው ገለል ብለው እንዳሳለፉም ተጽፏል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅንም የቅርብ ጊዜ ጸጸታችን ናቸው፡፡ ሁሉንም እዚህ ላይ መዘርዘር አይቻለኝምና የምናውቅ የማናውቃቸውን ቤቱ ደጁ ይቁጠረው፡፡

ይሄ ግን የየዘመናቱ አገዛዞች ብቻ ሳይሆን ፊደል ቀመስ የሆነው የከተሜው ሁሉ ልክፍት ይመስለኛል፡፡ ዛሬም የመዝናናት ሕልማችን ከመብላት፣ መጠጣት፣ መዋሰብ፣ ንባባችን ‹ስቶሪን ኢንተርቴይን› ከማድረግ አያልፍም፡፡ አጉል አርበኝነት ይጠናወተናል፡፡ የብሔርተኝነት ሥሜት የሚጋልበው ሥር የሰደደ ‹ሚሊታንሲ› ስሜት እንደበልግ ነፋስ እንዳሻው ያሰግረናል፡፡ ከአሰላሳዮች ይልቅ አርበኞች የጀግና ግጥም ይደረደርላቸዋል፡፡ ነጋድራስ ገብረሕይወት ምንይልክ የጀመሩት የለውጥ ጉዞ ገና እሳቸው አፈር ሳይቀምሱ ማዝገም መጀመሩ ተስፋ አስቆርጧቸው በቁጭት ሲጽፉ [ቃልበቃል ባይሆንም] ‹‹ማን ያስቀጥለው፡፡ መኳንንቱ እንደሁ ሹመት ዝና ቀርብኝ ብሎ ሽፍቶ አገር ምድሩን አጥፍቶ መሞትን እንደ ሙያ ይቆጥረዋል፡፡ እንዲህ ቢያደርግ ሕዝቡም እንደ ጀግና ይመለከተዋል›› ብለዋል፡፡

አንዳንዱ ነገር ዘመን በራሱ ተፈጥሯዊ ግፊት ሊያመጣው ይችላል፡፡ ባለፉት መቶ ዓመታት ሀገራችንንና ነጻነታችን ለምናብጠለጥላቸው ቅኝ ገዥዎች በአራጣ አስጨምድደን ከገነባናቸው ጥቂት ድልድዮ፣ መንገዶችና፣ ግድቦች እኛ የሚመስለው የቱ ነው? ባለፉት መቶ ዓመታት እንደ ሕዝብ ከነበሩን በጎነቶች መካከል እስከዚህች ዕለት ከእኛ ጋር ማቆየት የተቻለንስ ምን ያህሉን ነው? እናስ ከአንድ ያጣ ጎመን ተረቱ የሚገባው ለእኛ መሆኑ አይደለምን?

ዛሬም ፊደል ቀመሱ ትውልድ ሳይቀር የሚያነብ የሚጠይቅ ሰውን እንደ ጅል መመልከት ልንሻገረው ያልተቻለን ደዌ ሆኗል፡፡ ጀግኖቻችን ለሕመማችን ማደንዘዣ የሚያስታቅፉን ቧልተኞች አልሆኑብንምን? በዚህች በእኛ ምድር ጥንትም በዚህች ቅጽበትም ከትንሽ እስከ ትልቅ አሰላሳዮች የተወገዙ፣ የተነጠሉ ናቸው፡፡ የሚያሰናዝር፣ የኤኮኖሚ፣ የኅሊና ነጻነት የላቸውም፡፡ ማግለል፣ ማሳደድ፣ ማቆርቆዝ፣ ማደኅየት ይፈጸምባቸዋል፡፡ እድለኛ ከሆኑ ሲሞቱ ብቻ ከንፈር ይመጠጥላቸዋል፡፡

አሰላሰዮች ደራሲያን፣ የመንግስት ሹመኞች፣ መምህራን ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ምንም ላይጽፉ፣ ምንም ላይቀኙ ይችላሉ፡፡ የትርክት የበላይነት መፍጠር፣ ባህሉን ማሻሻል የሚፈልግ ሕዝብ ግን እየኮረኮመም ቢሆን በተጻፉም ባልተጻፉም ሕጎቹ እነዚህን አሳቢያን የሚያሰናዝርበት የፋይናንስ፣ የኅሊናና እና ደኅንነት ከለላ ይሰጣቸዋል፡፡

እናስ ያቆሙን መሰረቶች ምን ያህል ጽኑዓን ናቸው? እንደ ኅብረተሰብ የአቋራጩ፣ የቧልቱ ልክፍተኞች ሆነን ለመገኘታችን ምክንያቱ ምንድን ነው? የምንዋቀሰው፣ የምንናናቀው በድንቁርናችን ልክ አይደለምን? ለፍጥረት ሁሉ ከሚተርፍ በረከት፣ ኅሊና እና ርህራሄ ጋር ተፈጥረን ሳለ ስለንፍገታችን ራሳችንን በሰንደቅ ዓላማ ለሚያስለምን ችጋር አላጨንምን?

ጸጋዬ ገብረመድኅን በአንድ የጦቢያ መጽሔት ቃለመጠይቁ እንዳለው ‹‹የጨው ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልህ ያለቅሳል፡፡›› ያቆመን የጋራ መሰረት ሲናድ እንደሞኝ ቆመን ስንታዘብ ይታየኛል፡፡
.
.
.
--------
ምስል - ከድረገጽ በ1920ዎቹ ጉዞ ወደ ገበያ

ከያዕቆብ ብርሃኑ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

Читать полностью…
Subscribe to a channel