azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8863

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 ለማዘዝ @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከገበያ ጠፍቶ የነበረው አንድሮሜዳ ቁጥር 1እና 2 በድጋሚ ታትመው ላንባቢያን ቀርበዋል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ ጥናታዊ መጽሐፍ

(ሒሳዊ ንባብ)
**********

ደራሲ፦ ናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ

የመጽሐፉ አርእስት፦ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ሕይወቱ፥ ቀደምት ሥራዎቹና በሥራዎቹ ላይ ያተኮረሩ ጥናታዊ ጽሑፎች

የመጽሐፉ ይዘት፦ ግለ ታሪክ፥ ታሪክ፥ ረጅም ልቦለድ እና አጭር ልቦለድ፥ የሥነ ጽሑፍ ጥናት

ዘመን፦2013 ዓ.ም

አሳታሚ፦ ወገግታ አሳታሚ እና ኤዞፕ መጽሐፍ መደብር

ዐማርኛ መነገር የጀመረው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ7ኛውና በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መካከል ሲሆን፣ ቋንቋው በጽሑፍ የሠፈረው ደግሞ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ዐምደ ጽዮን መሆኑ በእርግጠኝነት ይነገራል፡፡ ዐማርኛ የአፄ ልሳን በመሆን ማገልገል የጀመረው በ13ኛው ክፍለ ዘመን የአገው ሥርወ መንግሥት በአፄ ይኩኖ አምላክ ተነጥቆ የሰለሞን ሥርወ መንግሥት“በዳግማዊነት” ሲቋቋም እንደነበር ያስረዳሉ።

የአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ በኢትዮጵያ የአማርኛ እድገትና ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ አድርጓል። በዚህ መጽሐፉ ውስጥ በውበታቸው ወይም በአጻጻፍ ሥልታቸው ወይም በያዟቸው ሐሳቦች (ቁም ነገሮች) ሳቢያ ህልው ሆነው የሚቆዩ የ1901 ዓ.ም ዘመን እንመለከትባቸዋለን።


እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን፣ የአፈወርቅ በመጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው የቋንቋቸው ውብና በአጻጻፍ ሥልታቸው አንባቢዎችን ማራኪ ወይም ያቀፏቸው ቁም ነገሮች ወይም ሐሳቦች ሁለንተናዊና መሠረታዊ መሆናቸውን ለማሳየት በአማርኛ ቋንቋ ታሪካችንና ሥነ ጽሑፎቻችን ብሎም የመንግሥት የሥራ ቋንቋ አማርኛ መሆን እንዳለበት በማራኪ ትረካዎች አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ "ዳግማዊ አጤ ምኒልክ" በሚል ርዕስ በ1901 ዓ.ም ከታተመው መጽሐፍ ለማሳያነት የሚከተሉትን አንቀጾች እንጠቅሳለን።

«ዳሩ ግን ማን ነው በመልካም አማርኛ አጣፍጦ አሳምሮ ላንባቢው እንዲቀና፥ ለሰሚው እንዲገባ፥ ትንሽ ትልቁ፥ እሴት ወንዱ እንዲያነበው፤ እንዲያደንቀው፤ እንዲቀና አድርጐ የሚጥፈው ?

የተማሩት ሊቃውንቱም ቅዳሴ፣ ምስጢረ ሥላሴ፣ ድጓ፥ቅኔ፥ መዋሲት፥ ዝማሬ ይመስል በጥንት ባሮጌው ቋንቋ በግዕዝ ብቻ ነው መጣፍ የሚወዱ። ይሄን አሮጌ ቋንቋ ለቤተ ክርስቲያን ትተው የቀረውን የዓለሙን ነገር የዓለሙን ሥራ ግን ሁሉ በሚአውቀው ሁሉ በሚናገረ ቋንቋ በአማርኛ ቢፅፍ ደግ ነበረ።

ደግሞም ለንግድ፣ ለጥበብ ለመንግሥት የሚጠቅመውን አማርኛውን ማረም፥ ማሳመር፥ ማስተማር፥ ማልማት ይሻላል፤ ይገባልም። ዛሬ አለቃ ታየ የሚሉት ደቀመዝሙር ያጤ ምኒልክን ታሪከ ነገሥት ሊጥፋ ታዝዟል ይባላል። እስቲ ተሆነ እናያለን፡፡ አግዚአብሔር ይገዘው፡፡ ነገር ግን ሁሉ እንዲያነበውና እንዲገባው በግዕዝ ትቶ ባማርኛ ባደረገው ደግ ነበረ።

አማርኛው ግን ገጥ ያለ፣ ቅልጥፍ ያለ ላንደበት የተስማማ፣ ለጆሮ ያልገማ ላንባቢው የሚመች፣ ለሰሚው ማይሰለች እንዲሆን አድርጎ መጣፍ ነው።

ግዕዝ ብቻ ማሳመር አባቱን ንቆ ግዕዝ ብቻ ማክበር፣ አባቱን ገሎ ላማቹ ይነጭ፣ አማቱን ጋርዶ እናቱን ያስፈጭ የሚሉት ነገር ነው። አማርኛ ማልከስከስ አሮጌ ቋንቋ ማደስ የተገባም አይደል፡፡ አማረኛን ማረም፣ ማሳመር ማስተማር ነው፡፡ አማርኛን የሚአሳምር ጠፋ እንጂ ለመዶግዶግማ ፊደል ሳይቆጥር በመጋፊያ እየጣፈ፣ በገል3 እየጫረ ጽሕፈት የተማረ ሁሉስ ይዶገዱግ የለምን?

ያም ሆነ ያም አለቃ ታየን የመሰለ ብልህ የተማረ ሰው አማረኛውን አስተውሎ ይጥፍ ዘንድ ተስፋ አለን። ያጤ ምንልክን ታሪክ በግዕዝ የጣፈ እንደሆነ ግን ታልተፃፈ ቁጥር ነው። ሮማይስጡን ለቤተ ክርስቲያናቸውና በፈረንጅ አገርም የጥንቱን ቋንቋ ለሌላ ነገር ትተው ሁሉም አዲስ ቋንቋቸውን እያረሙ፣ ለልጆቻቸውም ያስተምራሉ። ኢትዮጵያ እንዲሁ ማድረግ ይገባታል (ከገጽ 83 - 84)።

* * * * *

«ኮንት አንቶኔሊ አንሥቶ ውጫሌ የተዋዋልንበት ወረቀት በፈረንሳዊ ቋንቋ የተጻፈው ይታይ አለ። እቴጌ ጣይቱ ግን እኛ የምናውቀው ባማረኛ የተጻፈውን ነው እንጂ የፈረንጅ ቋንቋ አናውቅም:: አንተ ግን የኛን ቋንቋ ታውቃለህና ባማረኛ የተጻፈውን እየው አሉት።

ከዚህ ወዲያ ኮንት አንቶኔሊ ነገሩ ሁሉ እንዳልሆነለት አይቶ በንዴት ያን የታተመውን ደብዳቤ ብጭቅጭቅ አድርጐ ቀዳዶ ጣለና እንግዴህ ፍቅራችን ፈረሰ ብሎ የጦርነቱን ነገር ገልጦ ተናግሮ ወጣ።

እቴጌ ጣይቱ ከት ከት ብለው ስቀው የዛሬ ሳምንትም አድርገው። በዚህ የሚደነግጥልህ የለም። ሂድ የፈከርህበትን አድርግ። እኛም የመጣውን እናነሣዋለን፡፡ እግሩን ለጠጠር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው ከዚህ ያለ አይምሰል። የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነው እንጂ ሞት አይባልም። አሁንም ሂድ አይምሽብህ፤ የፈከርህበትን በፈቀደህ ጊዜ አድርገው። እኛም ከዚህኸው እንቆይሃለን አሉት።

ያው ፈረንጅ በንዴት እጅና እግሩ እየተንቀጠቀጠ ፊት እንዲያውም እንዲአ ነበረና ጭው ብሎ ላዳን እንዶድ የጨረሱበት ሸማ መስሎ እጅ ሳይነሣ ተወርውሮ ወጣ (ገጽ 127)።

---------------------------------------

እስከዛሬ በእኔ ትሑት አስተያየት ታሪክና ሥነ ጽሑፍን በአንድ ላይ አዋሕዶ በጥናትና በምርምር የተዘጋጀ መጽሐፍ በናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ የተዘጋጀው "የአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ" ሥራ ይመስለኛል። መጽሐፉ ሁለቴ የታተመ ሲሆን፣ ወደፊት ሦስተኛው እትም የሚታተም ከሆነ መጥቍም ቢኖረው መልካም ነው። ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ ጥናታዊ በመሆኑ ተመራማሪዎች፥ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ጋዜጠኞች የሚፈልጉት ጥናት ለማግኘት በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። እርግጥ የመጽሐፉ ማውጫ ላይ በየክፍሉ የተዋቀረው ምዕራፍ እያንዳንዱ ዓብይ ጉዳይ የሚገልጽ ቢሆንም የቦታ ስምች፣ የሰው ስም፣ በፊደል ቅደም ተከተል በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል። በተረፈ ናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ በለመደው እጅ ሌላ ጥናታዊ መጽሐፍ እንደምታበረክት ተስፋ አለ።

በመጨረሻም መጽሐፍ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ልቦለድ (1900 ዓ.ም) እንጎቻ ወግ (አጭር ልቦለድ) ከ1900 ዓ.ም ጀምሮ የታተመው የፈጠራ ሥራዎች፣ የኢትዮጵያ ታሪክን በተለይ የዐፄ ምኒልክ ከልጅነት አስከ ንጉሠ ነገሥትነት ዘመነ መንግሥት ደረስ ያለውን ታሪክ ሸጋ በሆነ አማርኛ ያስቃኛል።

አንባቢያን ሆይ መጽሐፉን አንብቡት ። ታዲያ መጣፉኑ በምታነቡበት ወቅት የእርጋታ ጊዜ፥ የመንፈስ ጸጥታን፥ በአመዛዛኝ ኅሊና፥ በአስተዋይ ልቦና ይሁን። መልካም ንባብ !


ፀጋየ ገብረመድን ሮበሌ እንደፃፈው

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

" THE POWER OF NOW" እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1997 በኤክሃርት ቶሌ ድንቅ
መጽሐፍ ነው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ በጉዞየ ካጋጠመኝ የነጋድራስ ገብረ ህይዎት ባይከዳኝ መንግስትና የህዝብ አስተዳደር መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ትርጉም !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የዘፈን ግጥም ደራሲና ጋዜጠኛ ፤ የሴቶች መብት ተከራካሪ የሸዋሉል መንግስቱ በሃረር በአፋን ኦሮሞ የሬድዩ ስርጭት ፕሮግራም ከእውቁ ጋዜጠኛ የሙዚቃ ግጥም ፀሃፊና ደራሲ የአፍራን ቀሎ ባንድ መስራችና ዋና አሰልጣኝ አቡበከር ሙሳ ጋር በመሆን በርካታ የሬዲዩ ፕሮግራሞች በጋራ ይሰሩ ነበር ፣ ከሰሯቸው የሬዲዩ ፕሮግራም መካከል ቅናተኛዋ ሚስት "Jaarti hinaaftu" በሚል የሰሩት የሬድዬ ድራማ በወቅቱ ተወዳጅ ነበር ።

ደራሲና ጋዜጠኛ የሸዋሉል መንግስቱ ከዚህ ቀደም ብሎ በሃረር ከተማ 1962 ዓ/ም ጽፋው በ1968 ዓ/ም በፊንፊኔ የታተመው "እስከ መቼ ወንደላጤ " የሚለው ተወዳጅ ድርሰቷ ይህ ነበር :

በነገራችን ላይ የሸዋሉል መንግስቱ ሀረርጌ ካበቀላቸው የዘፈን ግጥም ደራሲያን ውስጥ እንቁ የጥበብ ባለሙያ ነበረች። የዘፈን ግጥሞቿን ለተለያዩ ድምፃውያን ያበረከተች ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ለድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ፣ ለድምፃዊ መሀሙድ አህመድ፣ ለክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ፣ ለክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ እና ድምፃዊ አስናቀች ወርቁ በዋናነት ይገኙበታል። ለምሳሌ :-
☞ለድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ
♪ አካም ነጉማ

☞ለድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ
♪ጀመረኝ
♪ትዝታ
♪ህልም ሆነሽ ቅሪ
♪ጉብል ቀዘባ
♪የምንጃር ሸጋ
♪በእኔ ሞት
♪ውብ አበባ
♪መውደድሽን ብታውቂው
♪ባይሽ ደስ ይለኛል
♪ከሴት እሷ ብቻ

☞ለድምፃዊ መሀሙድ አህመድ
♪አሸወይና
♪ትዝታ
♪ኦሆሆ ገዳማ
♪ስደተኛ ነኝ
♪እንዴት ነሽ ገዳዎ
♪መላ መላ
♪አታውሩልኝ ሌላ
♪መቼ ነው
♪ሳምራዬ

☞ለድምፃዊ አሊ ቢራ
♪ አዋሽ
♪ወይ ሆቢ ሆቢ

☞ለድምፃዊት አስናቀች ወርቁ
♪ እህ ልበል
♪ሰላ በልልኝ

☞ለድምፃዊ አያሌው መስፍን
♪ ሄደች ጋራ ዞራ
ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ
Negash Qemant


አንድ ኮፒ መጽሐፏ እጃችን ላይ አለን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አለመኖርን ተመኝቶ ፣
አለመኖርን ፈልጎ ያውቃል፡፡

“አለመኖር ምንድነው?” ተብሎ ቢጠየቅ ግን መልስ የለውም፡፡

“መኖር ራሱ ምንድነው? ለምንድነው የምኖረው?” ጥያቄዎቹ ናቸው፡፡

“ሰው ካለአንዳች ዓላማ ወደ ምድር አልመጣም! ወደ ምድር አይመጣም!” ሲባል ሰምቷል፡፡

ባይረዳውም፡፡

“ሰው ካለአንዳች ዓላማ ወደ ምድር አልመጣም!” ማለት ምን ማለት ይሆን?

ዓላማ ራሱ ምንድነው?

የማንን ዓላማ ነው የሚያስፈጽመው?

“ዓላማህን አስሰህ አሳካው!” ብሎ የላከውስ ማነው?

ሰው በምድር ሲኖር የግድ ዓላማ መሰነቅ ይጠበቅበታል?

ምናልባት የአንድ ሰው ዓላማ ያለ ዓላማ ኖሮ ማለፍ ሊሆን አይችልም?...

"ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የኰለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ገጽታ

****

ርዕሰ ፦ ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ
ደራሲ ፦ ሥዩም ወልዴ
የመጽሐፉ ይዘት፦ ግለ ታሪክ
ዘመን ፦ 2002 ዓ.ም
( ሒሳዊ ንባብ)

በቸኛው የሥነ ጥበብ ኀያሲ ሥዩም ወልዴ፤ «ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ»የተባለው መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕትመት የበቃው በ2002 ዓ.ም ሲሆን፣ እሱም ከፍተኛ ግምትና አድናቆት አትርፏል። ይህ መጽሐፍም በ2007 ዓ. ም ለሁለተኛ ጊዜ ታትሟል ። ሆኖም ግን ደራሲው የመጽሐፉን የሕተመት ብርሃን ሳያይ ሞት ቀደመው።

ይህ መጽሐፍ የሥዩም ወልዴ የአምሳ ዓመታት ጉዞው የገጠመውና ያየውን ለዛ ባለው የትረካ ስልት ተከትሎ የዕድሜ ዘመኑን ትውስታ የመዘገበበት ነው።

«ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ» በሦስት መዕራፎች የተከፈለ ነው። አሥራ አምስት ፎቶዎች እና የደራሲው የሥዕል የፈጠራ ወጤቶች የተካተቱበት ሲሆን፣ በ345 ገጾች የቀረበ ነው።

መዕራፍ አንድ«ደማቁ ጠዋት»የሚል ሥያሜ ይዟል። ይህ ክፍል የልጅነት ጊዜያቱን፣ ከቄስ ትምህርት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሕይወቱ ላይ ያተኩራል።

ሁለተኛው ምዕራፍ፣«መንገዳማው ረፋድ» የሚል የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርስቲ የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝቶ በመጓዝ በትምህርቱ ቆይታው ያጋጠመውንና የታዘበውን ሁኔታ ሲሆን፣ በሥነ ጥበብ ታሪክ የጥበብ ንድፈ ሐሳብና የኀያሲነት ትምህርቶች ወስዶ የኤም, ኤ, ዲግሪ ተመርቆ ወደ አገሩ ሲመለስ የሚተረክበት ምዕራፍ ነው።

ሦስተኛው መዕራፍ፣ «ያልጠረረ ቀትር» የተሰኘ ነው፤ ይህ ክፍል ደግሞ በሕይወቱ የገጠመውን ግላዊና አገራዊ ድርጊቶች የሚያስነብብበት ነው።

የመጽሐፉ ተራኪ በመግቢያው እንዲህ ይላል፦«ይህ ነበር ጉዞዬ ብዬ በዚህች ጽሑፍ ውስጥ ያቀረብኩት ሁሉንም አይደለም፤በጣም ጥቂቱ ነው፤ ያስታወስኩትን ያህል፤ አንባቢዬን እየፈራሁና እየተባው ነው የፃፍኩት፤ ምክንያቱም በአገሬ «እኔ» ብሎ መፃፍ ባለ መለመዱና የግል ሕይወት ገጠመኝ ታሪክ አጻጻፍ ሊዳብር ባለመቻሉ እንግዳነት እየተሰማኝ ነው፤ ትውስቴን ያሰፈርኩት፤ስለዚህም አንባቢዬን ከዚህ ይልቅ የሌላ ነገር ብጽፈለት የበለጠ ይረካ ነበር እያልኩ የፈራሁት» (ገፅ 7 ላይ)።

የደራሲው ሥጋት እውነትነት ያለሁ ነው፤ ምክንያቱም በአንደኛ መደብ (እኔ) ትረካ የተአማኒነት ጥያቄ የሚያጭሩ ጉዳዮች መኖራቸው ሐቅ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥም ለመቀበል የሚከብዱ ታሪኮች ያጋጥማሉ፤ ከነዚህም መካከል የፊደል ካስትሮ ወደ ኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ሆኖ ምጣታቸውን ተከትሎ በአደባባይ ላይ የጓድ መንግሥቱና የኩባው መሪ የነበሩት የፊደል ካስትሮ ፎቷቸው በሥነ ጥበብ ባለ ሙያ የተሠረው ምስል መሠራት ተከትሎ የሚፈጠረውን የወዝግብ ሁኔታ ተራኪው ስዩም ያቀረበውን ቀጥለን እንመልከት።

«ከተሰጡኝ ተግባሮች አንዱና አጣዳፊው በዘጠኝ ቀን ተሠርተው እንዲያልቁ የታዘዙት የክብር እንግዳ የኩባው ፊደል ካስትሮ እና የደርጉ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሰምንት የአደባባይ ትላልቅ ምስሎች ሥራ ነው። አንድ ነባር ሠዓሊና አንድ በዚያው ዓመት የተመረቀ ወጣት ሠዓሊ ምስሎቹን እንዲሠሩ ተደረገ፤ ነባሩ የሊቀመንበሩን፤ ወጣቱ የእንግዳውን ከሠሩ በኋላ ጳግሜ 5 ቀን በየተወሰነላቸው ሥፍራዎች ተሰቀሉ።

መስከረም 1 ቀን 1971 ዓ, ም, ከፍተኛ ግርግር ተፈጠረ፤ «ሠዓሊዎቹ እንግዳውን አሳምረው (ካስትሮን) አስተናጋጁን ሊቀመንበር (መንግሥቱን) እጅግ አስቀያሚ አድረገው ነው የሠሩት» ተብሎ ሰለተተቸ የበዓሉ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት በሙሉ በከፍተኛ መደናገጥ ትርምስ ፈጠሩ» ካለ በኋላ ተራኪው ሥዩም የተጠየቀውንና ለማመን የሚከብደውን አስገራሚ መልስ እንዲህ ይመልሳል።

«እንደዚያ አበላሽቶ የሥራውን ሠዓሊ በአስቸኳይ ፈልጌ እንዳቀርብ ታዘዝኩኝ፤ የእምነቱንና አመለካከቱን፤ ፀረ- አብዮተኛ መሆን አለመሆኑ፤ በሊቀመንበሩ ላይ ጥላቻ ያለው ወይም የሌለው መሆኑን ተጠየቅሁ። በበኩሌ አፍራሽ መልስ ከመስጠት በስተቀር የተጠየቀውን ጥያቄ ሁሉ የሚደግፍ መልስ አልሰጠሁም። ነፍሴን ስላስጨነቋት የሰጠውት መልስ አንድ ነገር ነው፤ ለሊቀመንበሩ ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን መልክ ሠዓሊው በምንም መንገድ መለወጥ እንዳልነበረበትና ለሥራ እንዲረዳው ሞዴል ሆኖ በተሰጠው ፎቶግራፍ ላይ አሳድጎ ከመሥራት ውጪ ምንም ዓይነት የአሠራር ሰሕተት እነዳልነበረ ያበጠ ይፈንዳ ከሚል አቋም በድፈረት የጭንቄን ሳረጋግጥ «በያሉበት የተሰቀሉት ሁሉ ወርደው በተቻለ መጠን ይስተካከሉ፣ ይመሩ፣ ይቆንጁ እባክህ» ወደሚለው ሐሳብ አዘነበሉ። አራቱም ምስሎች ከየተሰቀሉበት ወርደው ሌሎች ሠዓሊዎች ተፈልገው ተፈጥሮ ያስገኘችው እውነት በጥበብ ተለውጦና ተውቦ እንዲቀርብ ተደረገ።» ይለናል።

በእኔ ትሑት አስተያየት ሥዩም ወልዴ «ለሊቀመንበሩ ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን መልክ ሠዓሊው በምንም መንገድ መለወጥ » አይችልም ብሎ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ይህንን መልስ በዘመነ ደርግ ይመልሳል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል። ለማንኛውም መጽሐፉ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉት። አንብቡት።

ፀጋየ ገብረ መድህን ሮበሌ !!!


/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አስራ አንደኛው በተሰኛው መጽሐፏ የምናውቃት ይቱስራ ምትኩ ድንቅ መጽሐፍ ይዛ እየመጣች ነው።


በቅርብ ቀን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት እትም የታሪክ መጽሐፍት !!
እነኾ ከኤዞፕ መጽሐፍት !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ግልጽ ጨረታ በሉት !!!

ይኽንን ፍቅር እስከ መቃብር አይታችኹታል።
እስካኹን ባለኝ የመጽሐፍት ሽያጭ ዘመኔ የመጀመሪያ የኾነውን ምንም ያልተነካካ ያልተበረዘ ያልተከለሰ እትም የ1958 ዓም እትም ገጥሞኝ አያውቅም።

እነኾ ይኽንን የመጀመሪያ እትም መጽሐፍ በደምበኛ ትዕዛዝ መቀበያ ደብተራችን ላይ ያለንን ትዕዛዝ ስመለከተው ከ25 ይበልጣል። በመኾኑም ለማን ሰጥቸ ለማን የለኝም ልበል። ስለዚኽ ይኽንን ጽሑፍ ቀድሞ አይቶ ለደወለልልን፣ ላዘዘን ፣ ደምበኛችን ብቻ የምንሰጠው ይኾናል ።

አስታውሱ ይኽ ቅጅ የ1958 ዓም ነው።

ትዕዛዝ _ እስኪ እጅወ ላይ ያለውን የፍቅር እስከ መቃብር እትም ይመልከቱ ?

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የተወሰነ ኮፒ እጃችን ላይ ይገኛል

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

" ዛሬ ቅዳሜ አይደለም " የተሰኘው መጽሐፍ እየተነበበ ነው ::

" ...ከመውለዷ በፊት የህክምና ክትትል የሚባል ነገር አድርጋ አታውቅም፡፡
ይህን ታደርግ ዘንድ አልደላትም፡፡

እንደብዙዎች እናቶች የምትወልድበትን ፣
ሕይወት ወደ ምድር የምታመጣበትን ፣
እድሜ ልኳን ስትሳሳለት ከምትኖርለት ፍጡር ጋር የምትገናኝበት ቀን አልናፈቃትም፡፡

ልጅ እኮ የፈጣሪ ጸጋ ነው ፣ ስጦታ ነው ፣ በረከት ነው ፣ ሲሳይ ነው… የሚሉ ቃላት አልሸነገሏትም፡፡

ልጅነቷን ቀርጥፎ ልጅነቱ የሚያብብ ፣
ወዟን አርግፎ የሚወዛ ፣
ጉልበቷን አፍስሶ ጉልበቱን የሚያጠነክር ፣
ቅስሟን ሰብሮ ተስፋውን የሚፈነጥቅ ፣
ተስፋዋን ንዶ ድሎቱን የሚገነባ ፣
ድሎቷን ሰውቶ ምቾቱን የሚያደላድል ፣
እሷን ገድሎ እሱ የሚኖር እርግማን በማህፀኗ ስላለመሸከሟ እርግጠኛ አይደለችም፡፡

እንቡጥ ሴትነቷን ለቀጠፈ አምሳያ ይሆን ዘንድ ትውልድ አትፈልግም፡፡
የእሱ አይነት ዘር ሊጠፋ እንጂ ሊተካ ፣ ሊመነጠር እንጂ ሊበዛ አይገባውም፡፡

ወለደች፡፡

ተስፋዋ ጨልሞ ተስፋ አመጣች፡፡

እሷ ስትታረዝ ሊለብስ ፣ ስትራብ ሊጠግብ ፣ ስትጠማ ሊረካ… ወለደች፡፡... " :

ከመጽሐፉ የተወሰደ "ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የታሪክ ተመራማሪው ባህሩ ዘውዴ ሥራዎች በጥቂቱ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

https://vm.tiktok.com/ZM2caeVbo/

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

2016 ዓ.ም.
የኪዳነ ምሕረት ዓመት

የዘንድሮው ጾመ ፍልሰታ ብዙ ጥይቄ የሚመለስበት እንዲሆን እንጠብቃለን:: እመቤታችን በፍልሰትዋ ከሀገራችንም ከቤተ ክርስቲያናችንም የፈለሰውን ሰላምና ፍቅር በምልጃዋ እንድትመልስልንና የእርስዋን ትንሣኤ ሐዋርያት ባዩበት ጾም እኛም የቤተ ክርስቲያናችንንና ተስፋ የማንቆርጥባትና ብዙ ታውፋንያዎች የተረባረቡባትን የሀገራችንን ትንሣኤ የምናይበት ያድርግልን:: የድንግሊቱን ትንሣኤ የማያምኑ እንዳሉ ሁሉ የቤተ ክርስቲያንና የሀገር ትንሣኤ ከዚህ በኋላ ተስፋ የለውም የሚሉም ይኖራሉ:: እኛ ግን በቶማሳዊ የእምነት ደመና ላይ ሆነን የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን የሰላም ትንሣኤ እንጠብቃለን:: የሀገራችንን ችግር የሚፈታ ምንም ዓይነት ምድራዊ ጠቢብ የለም ጠቢበ ጠቢባን ልዑል እግዚአብሔር እርሱ ብቻ እጁን እንዲያስገባና እጅዋን ወደ እርሱ የምትዘረጋውን ሀገር "ወዳጄ ሆይ ተነሽ" ብሎ እንዲያስነሣት እንጠብቃለን:: በዕንባ የቀረበ ጸሎት የማይፈጽመው ነገር የለምና 2016 የኪዳነ ምሕረት ዓመት እንዲሆን በዚህ ሱባኤ እንማጸናለን::

ለሱባኤው አንድ ውብ የጸሎት መጽሐፍ ሥጦታ ሆኖ ቀርቦልናል:: ጸሎቱ እጅግ ጥንታዊ ጸሎት ሲሆን እጅግ ውብ አድርጎ ከግእዝ ወደ አማርኛ ከቅኔያዊ ለዛው ጋር የመለሰው ደግሞ ኤፍሬም የኔሰው ነው:: መጽሐፉን ከሱባኤ መልስ በደንብ እንተነትነዋለን:: ሰሞኑን ግን ብትጸልዩበት መንፈሳዊ ደስታ የምታገኙበት መሆኑን ስታነቡት ታምኑኛላችሁ::

ሱባኤውን የስርየት ያድርግልን የነደደውን እሳት ያብርድልን ለግፉዓን የሚበቀልላቸው አምላክ ፍትሕ ርትዕን ያድርግልን:: 2016 ዓ.ም. የኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ቃልኪዳን) ዓመት ይሁንልን

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እንደ ወሸባ ከአንድ ቤትና ከhንድ ቤተሰብ የማይወጣ ትርክትመሆኑን ያጤኩት መጽሐፉን ጨርሼ ካጠፍኩት በኋላ አባትቶ እስደንቆኛል:

አንዳንዴ ብቻ እንዲህ ይገጥማል:: እንደ ውሃ አሳስቆ የሚወስድ ትርክት ማረፊያውን ለጥ ያለ ሜዳ ላይ ሲያደርግ ያኔ ጥያቄ ያስከትላል::

"የዚህ ቤተሰብ አባል አልነበርኩም? ታዲያ የተዘጋ ደጃፋቸውን አልፌ እንዴት ወደ ቤታቸው ዘለቅሁ? እንደ መርፌ የወጋኝ ስጋነት
ከየት መጣ? _ ሲስቁ አላጀብኩም? ሲያለቅሱ አልተንሰቀሰኩም? ይሄ ሁሉ ከት መጣ?"

'ወድቆ የተገኘ ሐገር' ካዳንዶቹ ትርክቶች አንዱ ነው:: ወድቀን እንደተገኘን ሁሉ ጉዲፈቻ ለመቀበል ቀድሞ እጆቹን ይዘረጋል::
በሂደት 'ስጋነትን' በውስጣችን ያኖራል:: ከዚያ ወዲያማ ለቤተሰባዊ ጥቃት 'ቤተሰባዊ መብከንከን ገጥሞን ባላለፍን' ስንል ራሳችንን እናገኘዋለን::
እስቲ አንብቡና ፍረዱኝ:

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

« አንድዋ ልጅ እምቢ አላትና፣ ተቀሚሷ ሥር መአት ጨርቅ ጐዝጉዛ ባሏን አርግዣለኹ እያለች ስትዋሽለት መክረም»

«ማታ ሲተኙ አያያትም?» ስትል ታንጉት ጠየቀች፣ ነገሩ አስገረሟት።

« ያመኛል እያለች ለብቻዋ እየተኛች ነዋ! ዘጠኝ ወር ተሞላት በኋላ ምን ታርገው። አውራ ዶሮዋን አርዳ ደሙን ታልጋው ላይ አፈሰሰችና «አስወረደኝ» አለች ይባላል። ታዲያ ምን ተብሎ ተዘፈነላት መሰለሽ?
ጌጤ ነው ስሟ፣ እንግዲህ፦

የጌጤ አውራ ዶሮ ዘንድሮ ከበረ
ዘጠኝ ወር ተረግዞ ዐልጋ ላይ ሠፈረ

« እኔን ይንገሩኝ የምለው ገብርዬ መካን ቢሆንስ? ብለው የጀመሩትን ነው። ምን አለ እርሶማ የልጅ ልጅ አይተዋል» ስትል በመከፋት አንገቷን አቀረቀረች።

« ታልሽ ምን ቸገረኝ! አየሽ፣አንድ ልጅ እናቱ እንጂ አባቱ በእርግጠኛነት የሚታወቅ አይደለም። አባቱ ማን መሆኑን ምንአልባት በእርግጠኛነት የምታውቅለት እናቱ ብቻ ነች። አሁን ለምሳሌ እኔ ልጆቹን ለአባታቸው ልጆችህ ናቸው አልኩት እንጂ ተሌላ አርግዤአቸው ቢሆን በምን ያውቅ ነበር? እና አሁንም የሆነ እንደሆነ ፞ · ·» መጨረሱ የከበዳቸው ይመስል ተውት።

ወይዘሮ ደብሬ እንደሰጉት ሐሳቡን ታንጉትን በጣም አላስደነገጣትም። «እና ለገብርዬ ልጅ ተሌላ ወንድ ላርግዘለት ማለት ነው? » ስትል ከመገረም ጋር ጠየቀች።

«አንቺን አርጊው አላልኩሽም፤ ንገሪኝ ስላልሽ ነው፤ ባላቸው መካን ተሆነ የሚያደረጉ ሴቶች ግን አሉ።»

—ከብርሃኑ ዘርይሁን ፣«የታንጉት ምስጢር» 1979 ዓ.ም

ኤዞፕ መጽሐፍት የምንጊዜም ምርጥ ሙጽሐፍት አቅራቢ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ ሞት ተፈርዶብኛል፧ በቃ በሰይፍ ተቀልቼ እንድሞት፣ በሕይወት ከሚኖሩት ወገን እንድስረዝ ተበይኗል፡፡ እሺ መሞቱን ልሙት ለምን ስይፉን አይስሉትም? ይኼም ተንኮል እኮ ነው፧ቶሎ ሲጥ እንዳልል የተሸረበ ሴራ፤ በህይወት እና በሞት መካከል ያለን በግ እያየ የሚስቅ በግ አራጅ አለ? እኔን የገጠሙኝ ግን እየገዘገዙ የሚገድሉ ሰው አራጆች ናቸው፡፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

.
....💚...💛..❤.....

" ጥ ሩ : መ ጽ ሐ ፍ ቶ ች : ማ ን በ ብ : ካ ለ ፉ ት : መቶ : ዘ መ ና ት : ም ር ጥ : አ ዕ ም ሮ ዎ ች : ጋ ር: እ ን ደ መ ወ ያ የ ት : ነ ው ::"

ኢማኑኤል ካንት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

#ወደ_ኢነርጂ_ባህር_ለመጥለቅ_የሚያስችሉህ_4_መንገዶች

#አንድ
• ብቻህን ስትሆን ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል ለመዝፈን ሞክር

#ሁለት
• ከውሃ ጋር በፍቅር ውደቅ። በወንዝ አቅራቢያ የእግር ጉዞን አድርግ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ሰውነትህን ውሃ ውስጥ ንከረው፤ የራስህን ነጸብራቅ በውሃ ውስጥ ተመልከት፤ ውሃ ውስጥም የሚፈጠሩ ሽክርክሮታዊ ቅርጾችን አስተውላቸው። ይህን ማድረግህ በዩኒቨርስ ውስጥ ያለው የኢነርጂ ፍሰት ምን እንደሚመስል ማስታወሻ ይሆንሃል።

#ሶስት
• በጽሞና ውስጥ ሁን። ከጫጫታ ራቅ። ምንም አይነት ሙዚቃም ሆነ ዜናዎችን ለአንድ ሳምንት ያህል ላለመስማት ሞክር። የራስህን አእምሮ ብቻ አዳምጥ። ይህን ልምምድ ለአንድ ሳምንት ያህል አድርገው። ቀስ በቀስም እያሳደግከው ሂድ፡፡

#አራት
• የምታየውን እና ባንተ ላይ የተከሰተውን ለውጥ ሁሉ በማስታወሻ ደብተርህ ላይ አስፍር።

አሁን ላይ ያለህበት የሕይወት ወቅት ላንተ የጨለመ ክረምት እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል፤ ሆኖም ግን የጸደይ ወቅት መምጫው ተቃርቧልና ብርታትህን ጨምር። በራስህ እምነት ይኑርህ። አትወድቅምም!

ጥሩ የስነልቦና መጽሐፍ አንብቢት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ሺ ከአንድ ሌሊት እነሆ በመደብራችን ተገኝታለች ብቅ ብለው ለወዳጅ ዘመድ ስጦታ ይሸምቱ።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቀደምት ትግርኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት
1948

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እውነትም “ጠቢበ ጠቢባን”!
===+++===
ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው በግሩም ኹኔታ ተርጉሞ ያሳተመውን “ጠቢበ ጠቢባን” መጽሐፍ ፈርሞ ልኮልኝ አነበብኩት። ከገመትኩትም ከጠበኩትም በላይ ሆኖ አገኘሁት። ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም የሠራው ከትርጉምም በላይ ነው። (ስለ ሥራው ያለኝን ምልከታ ከታች በመጠኑ አነሳለሁ፤) በጣም የደነቀኝ ነገር ቅድሚያ ስለ መጽሐፉ ሕትመት ጥቂት ላንሣ።

የመጽሐፉ ጥራዙ የተመጠነ፤ መጠኑ መካከለኛ፣ ባለ ሙሉ ቀለም፣ ወረቀቱ ብራና አከል እና መሰል ነው። ሲገልጡት ለዓይን ተስማሚ መሆኑ አንባቢን በግድ ይጋብዛል። የሽፋን ገጹ መስሕብነት አለው፣ የውስጥ ገጾቹ ሐረጋት ጥበብ ልዩ ነው። በዘመናዊ ሕትመት ያልተለመደውን ስመ አምላክን እንዲሁም አርዕስቶችን በቀይ ቀለም በወጥነት ማስቀመጥ ምን ያህል አድካሚ ሊሆን እንደሚችል በበተለይ በሥራው ያለፈ ሰው የሚረዳው ነው። እንኳን ይዘቱ (ውስጡ) አምሮ ተሠርቶ ይሄ በራሱ ትልቅ ምሥጋና የሚያሻው ነውና ወንድማችን ኤፍሬም የኔሰው  ና ምሥጋናህን ውሰድ። ማተሚያ ቤቱም ሊመሠገን ይገባዋል።

ከወራት በፊት “ጠቢበ ጠቢባንን እየተረጎምኩ ነው” ብሎ ዲ/ኤፍሬም ሲጽፍልኝ ደስታዬ ብዙ ነበር፤ አሁን አልቆ ሳየው ከመደሰቴ የተነሣ ይህን የመሰለ፣ ጥንቅቅ ያለ ሥራ ነፍስ ሔር ፕ/ር ጌታቸው በሕይወት በኖሩና በመረቁት ብዬ ከልቤ ተመኘሁ። የትርጉም ሥራ ከባድ ጥንቃቄን የሚፈልግ እና በኮሌጅ ደረጃ ራሱን የቻለ ትምህርትም የሚሰጥበት የሙያ ዘርፍ ነው። የመገኛ ቋንቋውን እና ተቀባይ ቋንቋውን ማውቅ ብቻ በቂ አይደለም። እኔ እንደተመለከትኩት ከሆነ ዲያቆን ኤፍሬም ይህን “ጠቢበ ጠቢባን” መጽሐፍ ተረጎመው ብቻ ሳይሆን አመሠጠረው፣ ተነተነው፣ አብራራው እና የመጽሐፉን ክብር በተገቢ መልኩ ገለጠው ቢባል ማጋነን ሊሆን አይችልም። እንዲህ ያልኩበትን በሦስት ነጥብ ላሥረዳ፦

አንደኛ የተስተካከለ ትርጉም ነው፦
የመልክእ ምሥጋናን መተርጎም እንደሌሎች ጽሑፎች አይደለም። ይልቁንም ደግሞ መልክኡ በተዘጋጀበት ጥበብ በሥነ ግጥም ሲቀርብ ለጥንቱ የተጠጋ ይሆናል። በዚህ ረገድ ዲያቆን ኤፍሬም የግዕዙን መሠረት ሳይለቅ ምሥጢሩንም ዘይቤውንም ጠብቆ መስመር በመስመር ተርጉሞታል። ይህ ከፍተኛ የሆነ የሥነ ጽሑፍ ችሎታን የሚጠይቅ እና በግዕዝ ቋንቋ መዋኘትን ያጠይቃል። በዚያውም ላይ እናቱን (የግዕዙን ዘር) በተጓዳኝ ገጽ፣ አቻ ትርጉሙን (የአማርኛን) በትይዩ ማቅረቡ አንባቢውን ለዳኝነትም ለምርጫም ይጋብዛል፤ ማለፊያ ሥራ!

ኹለተኛ ጥንቅቅ ያለ አርትዖት፦
ታትሞ ለሕዝብ የሚቀርብ ነገር ከፍተኛ የአርትዖት ሥራ ያሻዋል። አንዳንድ መጽሕፍት (እንዲሁም ጋዜጦች) በሳል መልዕክት በውስጣቸው ይዘው በርካታ የፊደል ግድፈት፣ የሥርዓተ ነጥብ አለመስተካከል፣ እንዲሁም የጽሑፍ ፎርማቱ የተዘበራረቀ ስለሚሆን ጥራታቸውን ዝቅ ያደርገዋል። ዲ/ኤፍሬም የቀደመ የአርትዖት ሥራ ልምዱን በበለጠ በዚህ መጽሐፉ ላይ እንዳዋለው በግልጽ ይታያል። የፊደላቱ ለቀማ፣ የቃላቱ አመራረጥ፣ የቁጥሮች አጠቃቀሙ፣ ሥርዓተ ነጥብ አጠባበቁ ወዘተ ... የተዋጣለት ስለሆነ ይበል ወንድማችን ያሰኛል።

ሦስተኛ ማብራሪያና ትንታኔ የያዘ ሥራ፦
አብዛኞቻችን ስለ “ጠቢበ ጠቢባን” ምንነት ያለን ግንዛቤ አናሳ ነው፤ የመጽሐፉን ይዘት የሚያውቁት ደግሞ ጥቂቶች እንደሆኑ ይገመታል። “ጠቢበ ጠቢባን”ን የመሰለ ለፈጣሪ የቀረበ ልዩ ምሥጋና አለማወቅ ምን ያህል እንደሚያስቆጭ አሁን ስናነበው ይገባናል። መጽሐፉ መቼ እና በማን እንደተደረሰ የቀደሙ ሥራዎችን አመሳክሮ፣ የራሱንም ንባብ ጨምሮበት ወንድማችን ኤፍሬም ሰፊ ማብራሪያ አቅርቦልናል። በግዕዙ ድርሰት ላይ አማራጭ ቃላትን ሲጠቀም በምክንያት መሆኑን ለማወቅ በየገጹ ያሉትን የግርጌ ማስታዎሻዎች መመልከት ነው።  “እንዲህ የሚል ዘርም ይገኛል” ብሎ ይገልጻል።  ይህ ዓይነቱ ሥራ በፊሎሎጂ (የጥንታውያን ጽሑፎች ጥናት) ባለሙያዎች የተመሳከረ ሕትመት (critical edition) የሚሉት ዓይነት ነው። ይህን ሥራ ይበልጥ የተደከመበት እንደሆነ የሚያሳየው ዐሥር የሚያህሉ ተመሳሳይ የብራና ቅጂዎችን መዘርዘሩ፣ የታተሙ የጸሎት መጻሕፍትንም ማካተቱ ነው። ይህም ለሌሎች ተርጓሚዎች በጎ ምሳሌ ነው፤ (በእርግጥ ይህም የተሻለ እንዲሆን በቀጣይ ቢጨምራቸው የምላቸውን ሁለት ያህል ነጥቦች ከታች እገልጻለሁ)።

ይህን የመሠለ ውብ ሥራ ስላቀረበልን ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም ከልብ መመሥገን ይገባዋል።  መጽሐፉም በሚገባ ሊተዋወቅና ሥራው ሊነገርለት ይገባል፤ ከምር በሆነ አስተያየት ብዙ ሊባልለት የሚገባው ነውና። ይህን ካልኩ ዘንድ to be fair እንዲል ፈረንጅ በሚቀጥለው ቢያሟላቸው የምላቸውን ሁለት አስተያየቶች ላቅርብ።
  -የመጀመሪያው የተረጎመልን የየትኛውን ቅጂ ጠቢበ ጠቢባን እንደሆነ ግልጽ ቢያደርገው? ያደገበትን የፍኖተ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅጂ ነውን ከሆነስ የመቼ ዘመን? ወይስ የጎንደሩን? የጣናውን? ወይስ ከውጭ ሀገር ከሚገኙት የቱን? እርግጥ ነው ይሄ ሃሣብ ይበልጥ ትርጉም የሚሰጠው በጥናትና ምርምር ለሚሠማሩ ቢሆንም ለጠቅላላ አንባቢም ቢሆን ማለፊያ ነው።  
  -ኹለተኛው ነጥብ ያሉን በርካታ የጠቢበ ጠቢባን ቅጂዎች መሆናቸው ይታወቃል፤ ሁሉንም መዘርዘር ባይጠበቅበትም ግን በርካቶች እንዳሉ ቢገልጽና እሱ ግን የተረጎመልን ይሄን እሱ ያገኘውን መሆኑን ቢጠቁመን ጥሩ እንደነበር ይሰማኛል።

ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም ሆይ፦
ጠቢበ ጠቢባን የሆነ ልዑል እግዚአብሔር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን ገልጾልህ፣ ትጋቱንም አድሎህ ወደ ፊትም ሌሎች መጻሕፍትን በነካ እጅህ ጽፈህ፣ ተርጉመህ እንድታደርሰን አደራ እንልሀለን
/channel/azop78

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የመጀመሪያው እትም
ፍቅር እስከ መቃብር ጨረታ በሚያስደንቅ ኹኔታ ተጠናቃላች !!!

ሀሳባችን ብዡ ይጠይቁን የነበሩትን ወዳጆቻችንን ማስደሰት ነበር ከልብ ከሚፈልጋት ሰው እጅ ገብታለች!!!!



ይኽ መጽሐፍ እጃችኹ ላይ ካለ እስኪ በድጋሜ እናሳስባችኹ የትኛው ቅጅ ነው ያለዎት !!!!


ካለውት እሰየው ብለናል !!!

ከሌለዎትም ድጋሜ ጨረታ እናወጣለን !!!
ይጠብቁን !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በገበያ ላይ



የሃያኛው ክፍለ ዘመን  መግቢያን የኢትዮጵያ ታሪክ ያወሳል።

የልጅ ኢያሱ፣ የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እና የተፈሪ መኮንን ታሪክ
ሀገራችን አሁን ያለችበት በቅጡ ለመረዳት የሃያ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምረን ማጥናት እንደሚጠበቅብን ምሁራን ያስረዳሉ ለዚህም ይረዳን ዘንድ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ትእዛዝ ተሰንዶ የነበረው መጽሐፍ ተዘጋጅቶ ቀርቦልናል።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ ነሐሴ 10
የምንወደውን የምናከብረው ደራሲ አበራ ለማ መደብራችን ተገኝቶ ነበር።

ጋሽ አበራ ለማ ብዙ የግጥም መጽሐፍትንና አጫጭር ልቦለዶችን አሳትሟል።
በተለይም ሞገደኛው ነውጤ የተሰኘው ልቦለድ ሥራው ዘመን አሽሬና በአንባቢያን ዘንድ አይረሴነት ያለው የመካከለኛ አጭር ልቦለድ ታሪክ ነው።


ጋሽ አበራ የደራሲ በብርሃኑ ዘሪሑን ሥራዎች ላይ ሀሳብ አንስተን ብዙ ተወያየን። ለብርሃኑ ዘሪሁን የነበራቸውን ታላቅ እክብሮትና የብርሃኑ እምቅ ችሎት እሳቸው ካላቸው ረጅም የስነ ጽሑፍ ልምድ ጋር እያገናዘቡ ብዙ ታሪክና ልምድን አካፈሉኝ።

ታዲያ በጽሑፎቻቸው ኮትኩተው ያሳደጉንን ታላላቅና አንጋፋ ደራሲያንን እድሜና ጤና ይስጥልን እያልኩ ጋሸንም ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን ብየ ሸኘዋቸው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"የአምላክ እናት ሆይ አልተለየሽኝም"
ታላቅ የምሥራች (የፍልሰታ ስጦታ) ለመጻሕፍት አንባብያን 27ኛው ዐዲሱ የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 2" መጽሐፍ ታትሞ ለአንባብያን ቀረበ። ይኽ መጽሐፍ ልዩ የሚያደርገው ከ4ኛው - 9ኛው ክፍለ ዘመን የተነሡ 26 ታላላቅ ሊቃውንት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትን ያካተተ ሲኾን፤ እነዚኽም፦
✍️ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘሳለሚስ
✍️ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
✍️ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
✍️ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

👉 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
👉 አንፊሎኪየስ ዘኢኮንየም
👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
👉 አምብሮስ ዘሚላን

💥 ቅዱስ ጀሮም
💥 አውግስጢኖስ ዘኂጶ
💥 ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
💥 ፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ

☀️ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ
☀️ ካኤሉስ ሴዱሊስ
☀️ ጴጥሮስ ክሪሶሎጎስ (ቃለ ወርቅ)
☀️ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

✍️ ቅዱስ ያሬድ
✍️ ሮማኖስ ማሕሌታይ
✍️ አካቲስት መዝሙር
✍️ ጎርጎርዮስ ዘቶረስ

💧 ቬናንትዩስ ፍርቱናቱስ
💧 ጎርጎርዮስ ታላቁ
💧 ኢሲዶሬ ዘሳቪሌ
💧 ጀርመኑስ ዘቁስጥንጥንያ
💥 እንድርያስ ዘክሪቴ
💥 ዮሐንስ ዘደማስቆ ይገኙበታል።

💥 ይኽንን በሕይወት ዘመንዎ ሊያነቡት ሊኖሮት፤ የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጣትን ክብር የሚያሳውቆት መጽሐፍ ነው።
💥ከ5 ዓመት በፊት ወጥቶ የነበረው "ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1" ከ1ኛው - 3ኛው ክፍለ ዘመን የተነሡትን የ25 ሊቃውንት ትምህርት ያካተተ ሲኾን በኹለቱ መጻሕፍት የ51 አባቶች የነገረ ማርያም ትምህርትን ለአንባብያን አቅርቤያለሁ። በሱባኤያችሁ እያነበባችሁ ተጠቀሙበት።
"ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዐተ ወልዳ"
(የእመቤታችን ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን)

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቤባንያ በመደብራችንይገኛል።

!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

<ሞት እንደሁ ልሙት በሴኮንድ መቶኛ፣
እንቅልፍ እንደሬሳ ዘለዓለም ልተኛ።
ሰማየ ሰማያት እመዘብራለሁ
የተዘጋውን በር እበረግዳለሁ።
የሌለ እስቲፈጠር የሞተ እስቲነቃ
በትልቅ እርምጃ ከመሬት ጨረቃ
ከጨረቃ ኮከብ
ካንዱ ዓለም ወዳንዱ
ስጓዝ እፈጥናለሁ
በፀሐይ ላይ ቤቴን ጎጆ እቀልሳለሁ።
.......መንገድ ስጡኝ ሰፊ
ፀሐይ ልሁን ፀሐይ
እንደ ፅርሐ አርያም ሁሉንም የሚያሳይ
እሳተ ገሞራ አመድ ዕረመጡን
ጎርፍ የእሳት ጎርፍ ልሁን።
......መንገድ ስጡኝ ሰፊ
ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እነዚህን አራት መጽሐፍት
እጅግ በማይታመን ዋጋ

በ200 ብር ብቻ !!

አንዱን በሚገዙበት ዋጋ አራቱን መጽሐፍት ይሸንቱ !!!!

Читать полностью…
Subscribe to a channel