ጥቂት ማብራሪያ ስለ ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ጉዞ ፪ መጽሐፍ
1. ከትንሿ ቤተ ክርስቲያን የቀጠለ መጽሐፍ አይደለም፤ ቢያንስ በጥር የሚጋቡ ዕጮኛሞች እንዳያመልጡኝ በሚል ቀደመ እንጂ ቁጥር ፩ ማንን ላግባ ለሚሉ የተዘጋጀና በዚህ ዓመት የሚወጣ ነው። ለባለትዳሮች የተዘጋጀ ቁጥር 3ም አለው።
2. ለዕጮኛሞች የተዘጋጀ ቢኾንም ከተነሡት ከ6ቱ ርእሰ ጉዳዮች ውስጥ 5ቱ ከዚህ በፊት ላገቡም ጭምር በደንብ የሚጠቅም ነው።
3. ትንሿን ቤተ ክርስቲያን ያነበበ ሰውም እነዚህን መጻሕፍት ማንበብ አለበት። ለምን ሲባል፥ አንደኛ የትዳር ጉዞ በሚል እየወጡ ያሉት በሌላ እይታ የተጻፉ ናቸው። ኹለተኛውና ዋናው ደግሞ ማሠልጠኛ ማኗሎች ናቸው። ማኗሎች ቢኾኑም በተቻለ መጠን የሚነበቡም ናቸው።
4. የትዳር ጉዞ ተከታታይ መጻሕፍት ማሠልጠኛ ማኗሎች እንደ መኾናቸው አጋዥ መምህር ይፈልጋሉ። ለምሳሌ መምህረ ንስሓ! በተጨማሪም ጥንዶች ይኹነኝ ብለው የሚወያዩባቸው፣ የሚተዋወቁባቸውና በዚሁ መሠረት የሚገናዘቡባቸው ናቸው።
ደራሲው ገብረ እግዚአብሔር ኪዲ እንደከተበው።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
በቅዱስ ያሬድ ላይ ትኩረት ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ጥቂት ቀናቶች ነው የቀሩት።
“ስምከ ሕያው ቅዱስ ያሬድ” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 11/ 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ፡፡
በብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ፣ የየምና የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፍቃድና ቡራኬ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ህንጻ አሠሪ ኮሚቴ እና በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት የሚካሄድ ይሆናል።
የቻለ ሁሉ የማይቀርበት ልዩ ጉባኤ!
ኑ! አንድ ሁነን ቅዱስ ያሬድን ዘክረን ከበረከቱ እንካፈል!
በዕለቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት፣ መምህራነ ወንጌል፣መዘምራንና ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ።
መግቢያ ዋጋ 100 ብር!
ትኬቱ በኤዞፕ መጽሐፍት መደብር ይገኛል።
ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000560510091
አቢሲኒያ ባንክ
145735858
አባይ ባንክ
146-101-9959527-013(9959527)
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
Our laws must be divorced from society. While they must aim at safeguard- ing the freedom. the happiness and the prosperity of the individual citizen, they must not lose sight of the interests of society as a whole.
KWAME NKRUMAH
Who are the components of 'the whole'? If you destroy all the individuals by taking away their rights, for whom do you keep the 'interests of society as a whole'? The idea that society is an end in itself must have caused the French King to ask: 'The State? Who is the State? I am the State!'
J. B. DANQUAH
ሞት ማለት፡-
ሞት አለመስጋት ነው የግዴለሽ ዓለም፤
ድንጋይ ተሸክሞ በውሀ ላይ መቆም፤
ጤንነት የለበት፤ አያጠቃው ሕመም
ትዝታ የለበት፤ አይታይበት ሕልም፤
ቡቃያው አያሽት፣ ፍሬው አይለመልም ፡
ዝናብ አይዘንብበት ድርቀት ነው ዘላለም፡፡
ማንም አይጎዳ ማንም አይጠቀም፡፡
ሞት ማለት፡- የሞት ሞት -
አእምሮ ፈራርሶ
ኅሊና በስብሶ፤
ሰውነት ረክሶ፤
አንደግም፤ እንደጥንብ፤
የጭልፊቶቹ ምግብ፤
የሞት ሞት ይኸ ነው፤
ትንሣኤ የሌለው፡፡
መስፍን ወልደ ማሪያም መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ የተወሰደ !!!
መልካም ንባብ!!
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገር አፈታሪክ
ከዕለታት አንድ ቀን ሴት አንበሳ ፡ ነብር እና ውድንቢ የሠሩትን ኃጢአት እየተናዘዙ ረጅም መንገድ በአንድነት ለመጓዝ ተስማሙ።
ሴቷ አንበሳ « የጫካው ንግሥት ስለሆንኩ በቅድሚያ እኔ እናዘዛለሁ» አለች። ቀጥላም « አንድ ቀን አንድ ትልቅ ድፋርሳ አጣጥሜ በልቼ እንደጨረስኩ የሜዳ አህያ ብቅ አለ። ወፍራምና የሚያስጐመጅ ስለነበር ዘልዬ አነቅሁትና ገደልኩት። ግን ሆዴ በጣም ሞልቶ ስለነበር ልበላው እንደማልችል ተረዳሁ። ካለምንም ዓላማ ይህን የጫካ አውሬ ገድያለሁ።»
ነብርም ተቻኩሉ « አንች የጫካው ንግሥት፣ ለምን ብለሽ ትጨነቂ ያለሽ ? ከሁላችንም የላቅሽበትን ሥራ ነው የፈጸምሽው። ስለዚህም ይቅር ብለንሻል » አላት። «ነብርስ ስለምንድነው የምትናዘዘው ? » ብላ ጠየቀች አንበሳ።
«ይኸውላችሁ፣ አንድ ቀን ሁለት ግልገሎቿን አስከትላ የምትሄድ በግ አየሁ። ስለራበኝ አንዷን ግልገል ወዲያውኑ ቁርጥምጥም አድርጌ ዋጥ ኳት።እናቲቱ እየሮጠች ወደኔ መጥታ አያ ነበር፣ ከፈለግህ እኔን ብላኝ፣ የተረፈችውን ግልገሌን እንኳን ማርልኝ ብላ እያለቀሰች ተማጸነችኝ። እኔም እሺ ፣ እምርልሻለሁ ካልኳት በኋላ እሷንና ግልገሏን ስለቀጥኋቸው» አለ። አንበሳም « እኔም እናት ስለሆንኩ ያደረግኸውን አልደግፍም፤ ግን ውብ፣ ፈጣንና ኃይለኛ ስለሆንክ ልጨክንብህ አልችልም። ስለዚህም ተምረሃል » አለችው።
«ውድንቢ እስካሁን አልተነፈስክም፣ አንተስ ምን የምትናዘዘው አለህ?» በማለት አንበሳ ጠየቀች። «ክብርት አንበሳ ፣ ለጊዜው የምናዘዝበት ነገር ትዝ አላለኝም » አለ
ውድንቢ።
«ሁላችንም ሟቾች ነን፣ ኅሊናህ ውስጥ አንድ ነገር መኖር አለበት » አለች።
ውድንቢ ጥቂት አሰበና « አንድ ቀን ከጧት አንስቶ በምድረ በዳ ስሄድ ወዬ በጣም ርቦኝ ስለነበር ጥቂት ሳር አይቼ በልቻለሁ» አለ። በዚህ ጊዜ አንበሳና ነብር በኅብረት « ይቅር የማይባል ጥፋት ስለፈጸምክ መኖር አይገባህም » ብለው ውድንቢን ቀረጣጥፈው በሉት።
ካነነብኩት
ጥርስ የገባች ሀገር ገጽ 10 ላይ የተወሰደ !!
ዘወትር፣ ፍቅር ዕውር ነው ብላችሁ ስታወሩ እሰማለሁ፡፡ አዎን፣ አፍቃሪ በተፈቃሪው ላይ አንዳችም እንከን አያይም ማለታችሁ ነው፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ … ይሄ ዓይነት አለማየት የማየት ከፍታ ጫፍ ነው፡፡
በምንም ነገር ላይ እንከን አታዩ ዘንድ ምነው ሁሌ በታወራችሁ፡፡
አይይ … የፍቅር ዓይኖችማ … ንጹህ፣ የጠሩና ሰርስረው የሚያዩ ብሌኖች ናቸው፡፡ ስለዚህም ምንም እንከን አያዩም፡፡
አዎን … ፍቅር ዓይናችሁን ሲያበራው … ያኔ … ለፍቅራችሁ ያልተገባ ምንም ነገር አታዩም፡፡ በእርግጥም፣ ፍቅር አልባ የተንሸዋረረ ዓይን ብቻ ነው በሌሎች ላይ ስህተት ፍለጋ የሚተጋ፡፡ የትኛውም የሚያያቸው እንከኖችም … የሌላም ሳይሆን የራሱ ናቸው፡፡
ፍቅር አንድ ያደርጋል፡፡ ጥላቻ ይበትናል፡፡ ይህ የመሠዊያው ጫፍ የምትሉት ግዙፍ የአለት ክምር እንኳ፣ በፍቅር እጅ ባይያያዝ ተበታትኖ በበረረ ! ይሄ በስባሽ ገላችሁ፣ መፍረስን የመከተው፣ እያንዳንዷን የአካል ሕዋስ በጥልቅ ፍቅር ብትወዱ ነው !!! ፍቅር፣ በሕይወት ማራኪ ዜማ የሚደንስ ሰላም ነው፡፡ ጥላቻ … ጨካኝ የሞት ጥላ ያጠላበት የተቅበዘበዘ ጦርነት ነው፡፡ የቱን ትመርጣላችሁ - ፍቅርና ዘላለማዊ ሰላምን ወይንስ ጥላቻን እና ማለቂያ የለሽ ጦርነትን ? መላዋ ምድር እናንተ ውስጥ ሕያው ነች፡፡ ሰማየ ሰማያቱ እና የሰማየ ሰማያቱ አለቆች እናንተ ውስጥ ሕያው ናቸው፡፡ ስለዚህም ራሳችሁን የምትወዱ ከሆነ፣ ምድርን እና መላ ፍጡራኖቿን ውደዱ፡፡ እናም ራሳችሁን የምትወዱ ከሆነ ሰማያቱን እና አገልጋዮቹን በመላ ውደዱ፡፡
ከ“መጽሐፈ ሚርዳድ”
የካህሊል አማልዕክትን
ማንበብ ላላነበባችኹት !!!
እነሆ እንደ መግቢያ!!
የካህሊል ሴቶች
‹‹Beloved prophet››
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*
… የካህሊል ጅብራን ነፍስ ሁሉንም በመፈለግና ሁሉንም በማጣት ቅዝምዝም መሀል ተሰንቅራ የጠፋች የቅጽበት ብልጭታ ትመስላለች፡፡ በማይረካ ጥማትና በማያባራ ሽሽት መካከል ተወጥራ ሲነካኳት ስቃይን የምትዘምር አንዲት ፍሬ የክራር ክር፡፡ ሕይወቱን የምታተርፍለትን አንዲት የጉበት ቀዶ ጥገና ማድረግን ችላ ብሎ ሞትን በጨበጣ የታገለ…
ካህሊል ጅብራን የአባቱን ሕልፈት ተከትሎ በ1895 እ.ኤአ ከእህቱና እናቱ ጋር በስደት አሜሪካ ገባ፡፡ በዚያ ወቅት ራሱን እንኳን በቅጡ መግለፅ የማይችል አይናፋር ልጅ ነበረ፡፡ ድንገት ግን የ21 ዓመት ልጅ እያለ በአስር ዓመታት የምትበልጠውን ሜሪ ሐስከልን ተዋወቀ፡፡ ሜሪ ካህሊልን ዘግቶ ከተቀመጠባት ጠባብ የጭለማ ክፍሉ ጎትታ አውጥታ ከዓለም ጋራ አስተዋወቀችው፡፡ ፓሪስ ድረስ ልካ ስነ-ስዕል አስተማረችው፡፡ እርሱም በምላሹ እንደጣዖት አመለካት፡፡ የነፍስ ጓደኛው አደረጋት፡፡ የሴቶች ሁሉ መስፈሪያ ትልቋ ሔዋን እንደሆነች በነፍሱ ዘመረላት፡፡ እስከመጨረሻው ብቸኛ አርታኢውም እሷው ነበረች፡፡
የሜሪና የካህሊል ጓደኝንት ብዙ ጊዜ ተፈትኖ እየታደሰ የቀጠለ ከምናውቃቸው ጉድኝቶች የተለየና ሊገልፁት የሚያስቸግር ይመስላል፡፡ ሜሪ ሐስከል ሲበዛ ደግ ሴት ነበረች፡፡ ከካህሊል በፊት ቢሆን ለራሷ የሚላስ ሳይኖራት እየቆጠበች የምታስተምራቸው የግሪክ ታዳጊዎች ነበሯት፡፡ ይኸው መልካምነቷ ከአፈር ላይ አንስታ በዓለም ላይ ከዊሊያም ሸክስፒርና ላኦ ትዙ ቀጥሎ በሦስተኝነት በሰፊው የተነበበውን ደራሲ እንድትፈጥር አስችሏታል፡፡
ለ27 ዓመታት ይህን ሁሉ ስታደርግ ከካህሊል የምትጠብቀው ብቸኛ ነገር ቢኖር ለሚያገኛቸው ሰዎች ሁሉ የምወዳት ፍቅረኛዬ ናት ብሎ እንዲያስተዋውቃት ብቻ… በግል ማስታዎሻ ደብተርዋ ላይ አስፍራው እንደተገኘችው በዓለም ለእርሷ ካህሊል ጅብራንን ከመውደድ የሚበልጥ ነገር አልነበረም፡፡
ያለ ሜሪ ሐስከል ካህሊል ከትንኝ ያነሰ፣ ከላባ የቀለለ ለቁምነገር የማይጠራ ሰው በሆነ ነበር፡፡ ትልቁ ካህሊል ሜሪን አለመተዋወቅ ቀርቶ ከእርሷ ጋር የነበረው ጓደኝነት በሆነ ምክኒያት ተቋርጦ ቢሆን ኖሮ በተወዳጁ ፋንታ ዕድገቱ የቀነጨረውን ነብይ የማየት ዕድላችን የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚነሆነኝ ይመስለኛል። ሜሪ ሐስከል ግን ባደረገችው ነገር ለአፍታም ሳትኩራራ አንዲት ሴት በእህትነት፣ በእናትነት፣ በፍቅረኝነት፣ በጓደኝነት፣ በሰውነት ልትሰጠው የምትችለውን ፍቅር ሁሉ ቅንጣት ታህል ሳትሸራርፍ እየለገሰች በሐምራዊ የንቃት ክንፎች እየበረረ እልፍ መሻገሮችን እንዲያስስ አስችላዋለች፡፡ በ1914 እ.ኤ.አ ክረምት በጻፈላት ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡፡
“The day will come when I shall be able to say, ‘I became an artist through Mary Haskell… You have the great gift of understanding, beloved Mary. You are a life-giver, Mary. You are like the Great Spirit, who befriends man not only to share his life, but to add to it. My knowing you is the greatest thing in my days and nights, a miracle quite outside the natural order of things.››
ሜሪ በኪናዊ ምጥቀቱ ከፍ ባለበትም ይሁን በሞራል በተሸመደመደባቸው ጊዜያት ሁሉ ያለማመንታት ከጎኑ ነበረች፡፡ ይህንን ደብዳቤዋን ተመልከቱ፡፡
‹‹I don’t even want you to be a poet or painter: I want you to be whatever you are led or impelled to become… Your work is not only books and pictures. They are but bits of it. Your work is You, not less than you, not parts of you… These days when you “cannot work” are accomplishing it, are of it, like the days when you “can work.” There is no division. It is all one. Your living is all of it; anything less is part of it. — Your silence will be read with your writings some day, your darkness will be part of the Light.››
ካህሊል ለትዳር የጠየቃት ብቸኛዋ ሴት ሜሪ ሐስከል ነበረች፡፡ ባይሳክም ቅሉ… ምናልባት ያለመሳካቱ ምክንያት ካህሊል ትዳርን አጥብቆ የማይፈልግ ሰው በመሆኑ ሊሆን ይችላል፡፡
‹‹አብሮነታችሁ የመሰናዘሪያ ቦታ አይንፈጋችሁ፡፡ በአንድነት ቁሙ። ነገርግን መተዛዘል እስቲሆን ድረስ አትደራረቡ፡፡ የቤተ መቅደስ አዕማድ ሲቆሙ ራቅ ራቅ ብለው ነው፡፡›› ይላልና፡፡
እስኪ ይሄኛውንም ካህሊል ለሜሪ የጻፈላትን ደብዳቤ ተመልከቱ
‹‹I wish I could tell you, beloved Mary, what your letters mean to me. They create a soul in my soul. I read them as messages from life. Somehow they always come when I need them most, and they always bring that element which makes us desire more days and more nights and more life. Whenever my heart is bare and quivering, I feel the terrible need of someone to tell me that there is a tomorrow for all bare and quivering hearts and you always do it, Mary.››
የማግኘት አድሉ ያለችሁ ‹‹Beloved prophet›› በሚል ርዕስ በ416 ገጾች ተቀንብቦ የቀረበውን የሁለቱ ጓደኛሞች ደብዳቤዎች የተጠናቀሩበት መጽሐፍ እንድታነቡ እጋብዛችኋለሁ፡፡
ካህሊል ግን አሁንም ከፍታው ቀጥሏል፡፡ ሜሪም አስከ ዘለዓለም አብራው ከፍ የምትል ይመስላል፡፡ መጻሕፍቱ ዛሬም በሁሉም የዓለም ማዕዘናት በስፋት ይነበባሉ፤ ይተረጎማሉ፡፡ እንደ ጥናቶች ጥቁምታ ከሆነ ካህሊል አሁን በሚነበብበት ፍጥነት ከቀጠለ ከሃያ ወይም ሠላሳ ዓመታት በኋላ በሰፊው በመነበብ ሸክስፒርንም ሆነ ላኦትዙን የሚያስከነዳበት እድል አለው፡፡
ተፅዕኗቸው ከሜሪ ጋር ለንጽጽር የሚቀርብ ባይሆንም እንኳን ሌሎች በርካታ ሴቶች በካህሊል ሕይወት ውስጥ ነበሩ፡፡ እርሱም ስለ ሴቶች እንዲህ ብሏል ‹‹የዓይኔን መስኮት እና የመንፈሴን በሮች የሚከፍቱት ሴቶች ናቸው፡፡ እናቴ፣ እህቴና ጓደኛዬ የምላቸው ሴቶች ድጋፍ ባያደርጉልኝ ኖሮ ዛሬ እኔም የዓለምን ጸጥታ እና እርጋታ በማንኮራፋት ድምጽ ከሚረብሹት ሰዎች መካከል ተጋድሜ ሳንጎላንጅ እገኝ ነበር፡፡››
ውድ የኤዞፕ መጽሐፍት ደንበኞቻችን
በተደጋጋሚ ስትጠይቁን የነበረውን #የባስሊቆስ #እንባ በ100 ብር በሽያጭ ላይ ነን ጎራ ብለው ይሸምቱ
🌼🌻🌼🌻*የኔ*ጌታ*<በቸርነትህ*አመታትን* 🌻🌼ታቀዳጃለህ>*መዝ*64:11
*ይህ* 🌼አዲሱ*አመት🌻*የሰላም*የደስታ*🌼የፍቅር*🌻ያንድነት*የስኬት*ዘመን*🌻🌼 ያድርግልዎት 🌻*ሰላም*🌼 ለሀገራችን*ይሁንልን*መልካም*🌼🌻 አዉዳመት*🌼🌻 መጪው አዲስ ዓመት የሀገራችን እና የሕዝቦቿ ሰቆቃ የሚያበቃበት እውነተኛ ሰላም የሚሰፍንበት ተድላና ፍሰሃ የተትረፈረፈበት ዓመት ይሁንልን።
መልካም አዲስ አመት. *🌼🌻
ኤዞፕ መጽሐፍት
/channel/azop78
እንደ ወሸባ ከአንድ ቤትና ከhንድ ቤተሰብ የማይወጣ ትርክትመሆኑን ያጤኩት መጽሐፉን ጨርሼ ካጠፍኩት በኋላ አባትቶ እስደንቆኛል:
አንዳንዴ ብቻ እንዲህ ይገጥማል:: እንደ ውሃ አሳስቆ የሚወስድ ትርክት ማረፊያውን ለጥ ያለ ሜዳ ላይ ሲያደርግ ያኔ ጥያቄ ያስከትላል::
"የዚህ ቤተሰብ አባል አልነበርኩም? ታዲያ የተዘጋ ደጃፋቸውን አልፌ እንዴት ወደ ቤታቸው ዘለቅሁ? እንደ መርፌ የወጋኝ ስጋነት
ከየት መጣ? _ ሲስቁ አላጀብኩም? ሲያለቅሱ አልተንሰቀሰኩም? ይሄ ሁሉ ከት መጣ?"
'ወድቆ የተገኘ ሐገር' ካዳንዶቹ ትርክቶች አንዱ ነው:: ወድቀን እንደተገኘን ሁሉ ጉዲፈቻ ለመቀበል ቀድሞ እጆቹን ይዘረጋል::
በሂደት 'ስጋነትን' በውስጣችን ያኖራል:: ከዚያ ወዲያማ ለቤተሰባዊ ጥቃት 'ቤተሰባዊ መብከንከን ገጥሞን ባላለፍን' ስንል ራሳችንን እናገኘዋለን::
እስቲ አንብቡና ፍረዱኝ:
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
ኤፒክቲተስ
የስቶይኪዝም ፍልስፍና መሰረት የሆነው የኤፒክቲተስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ከዋለ ቆየት ቢልም ብዙ የመነበብ እድል ካላገኙት መካከል ነው
እንዳይነበብ ያደረገው የመጽሐፉ ጥሩ አለመኾኑን ሳስብብይገርመኛል።
ከኤፒክቲተስ [የስቶይኪዝም] ፍልስፍና መሰረተ ትምህርቶች ምንጭ የሆነውና ጥልቅ ለሰው ልጅ ጠቃሚ ትምህርቶችን ማስተላለፍ የቻለው ኤፒክ 2000 ዓመታት የሰው ልጅን ህይወት እጅግ ጣፋጭ እንዲሆን የሚያስችሉ ጠቃሚ ትምህርቶችን ያስተማረና 2000 ዓመታትን መሻገር የቻሉ ጥልቅ አስተምህሮቶች ባለቤት ነው...!!
#ከሕይወት ጋር #ግብግብ ትተው #ሕብረትን ይፍጠሩ ...!!
የራሴ ህግ የሚሉትን ነገር እንዳይሞክሩት፡፡ ትልቅ፣ ትንሽ፣ የሰለጠነ፣ የተናቀ ሳይሉ ከሁሉም ነገር ጋር ግንኙነትዎን በተፈጥሯዊ ህግ መሰረት ያድርጉ፡፡ ምኞትዎን ከተፈጥሮ ጋር ሕብር ባለው ሁኔታ ማናበብ ዋነኛ ግብዎ ሊሆን ይገባል፡፡
ይህንን ልምምድ የሚያከናውኑትስ የት ነው..?
በእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ነዋ... ይለናል ኤፒክ። ሲሰሩ፣ ሲመገቡ፣ ገላዎን ሲታጠቡ ፣ ብቻ ምን አለፋው ማንኛውንም ነገር ሲያከናውኑ ከተፈጥሮ ምሪት ጋር በተናበበ መልኩ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ ጉዳዩ ምን አከናወኑ አይደለም፡፡ እንዴት አከናወኑ እንጂ… ይህንን መርህ በቅጡ ተገንዝበን መተግበር ከጀመርን በሕይወታችን ውስጥ የቱንም ያህል ችግሮች ሊፈጠሩ ቢችሉ (ምክንያቱም ችግሮ የተፈጥሮ ሂደት አካል ናቸውና) ውስጣዊ ሰላምን መጎናጸፍ ዘወትር የሚቻል ይሆናል፡፡ የሚሉና ሌሎች ጠቃሚ መሰረታዊ የህይወት አስተምህሮዎችን ሰብኳል ።.!!..
ለንባብ ባህል መጎልበት እንተጋለን..!!
ኤዞፕ መጽሐፍት ቴሌግራም ተከተሉኝ ብሏችኊል !!
/channel/azop78
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አንዳንድ የራፕ ሙዚቃ ተጫዋቾች እና የስልቱ ወዳጆች የአሜሪካውያን የራፕ ስልት የተወሰደው ከኢትዮጵያውያን ባህላዊ የሙዚቃ አጨዋወት እንደ ፉከራ፣ቀረርቶ ከመሳሰሉት ነው ብለው ቢያምኑም ይህን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት በጥናት የተደገፈ መረጃ አልተገኘም፡፡
ኮንፊሽየስ /Confusioin/551-479B.C/:-የጥንታዊቷ ቻይና ገፀ-በረከት ሆኖ በብዙ ስራዎቹ የሚታወቀው ይህ ፈላስፋ በሙዚቃ ፍልስፍናውም ሙዚቃን እና የስልጣን አስተዳደርን እርስ በርሳቸው የተያያዙ እንደሆኑ አንድ ሰው የተሻለ የሙዚቃ አረዳድ ካለው ለስልጣናዊ አስተዳደር የተሻለ ችሎታ አለው በማለት አስረድቷል። ኮንፊሽየስ ሙዚቃ እንደ የግንባታ ጥበብ፣እጅ ፅሁፍ ሒሳብ የመሰሉት ጋር እኩል የሆነ ትልቅ የጥበብ ዘርፍ መሆኑን ያስረዳ ሲሆን በቻይናዊያን ባህል የአርአያነት እሳቤ የሚደገፍ በመሆኑ ኮንፊሽየስ በራሱ ሙዚቃን የሚጫወት እንደ ነበር ይነገራል፡፡
በ1903G.C ዊልያም ክርስቶፎል ሀንዲ (W.C Handy) (የብሉዝ ሙዚቃ አባትና የዳንስ ኦርኬስትራ መሪ) ከትንሽየዋ መንደር ቶቷዊር ሚሲሲፒ ባቡር በመጠበቅ ላይ ሳለ ባቡሩ በጣም ስለዘገየ አግዳሚ ወንበር ላይ ጋደም ይላል፡፡ ከእንቅልፉ ሲነቃም አንድ ጥቁር አፍሪካዊ ከጎኑ “Going where the southern cross the dog የሚል ሙዚቃ በጊታሩ ሦስት ጊዜ እየደጋገመ ሲጫወት ተመለከተ፡፡ ሙዚቃውን መጫወት እንዳቆመም ሀንዲ ይህ ስንኝ ምን እንደሆነ ጠየቀው ሙዚቀኛው ግን አልመለሰለትም፡፡ ሀንዲ በዚህ ሙዚቃ እጅጉን በመገረም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ይህንን ሙዚቃ “Yellow Dog Blues” በሚል ይሰራዋል፡፡ በዚህም ብሉዝ የሚባለውን ስያሜ ለሙዚቃው ስልት በመስጠቱ የብሉዝ አባት እንዲባል አስችሎታል።
ዲጄ የሚለው ምህጻረ-ቃል ዲስክ ጆከር/Disc Jockey/ የሚል ትንታኔና የሸክላ ሙዚቃ አጫዋች የሚል የአማርኛ ፍቺ ያለው ሆኖ የቃል ስያሜውን ያገኘው በአሜሪካ ነበር፡፡
ከመጽሐፉ የተወሰደ
ተከዜ...ተከዘ?
የላስታው ጠብታ...የወርዒ ዘለላ
የሰሜኑ ፍላቂ...ሥርወ ላሊበላ፣
ከጎንደር ከወሎ...ማዶ ለማዶ
ተሽሎኩልከህ ተወርውረህ...እንደ ዘንዶ፣
ቁልቁል ስትዘል ስትል ዱብ...ሿ....
ሸለቆውን ስታጠልቅ ጠባቡን ስታሰፋ፣
ማራኪው ፏፏቴህ...ተምዘግዝጎ ወራጅ
አለት አስደንጋጩ ድንግል መሬት ቀዳጅ፣
የጎርፍህ ፍጥነቱ...ሽታው ድምፁ
የአለት ድድህ ፍላፃ...ገጹ፣
ድፍርስ...ደፋር...አስፈሪ
ጉምልል...ጉምልል ባይ ጨፋሪ፣
ጋራ ገደሉን ሩጠህ...ሩጠህ
ጠባቡን መንገድ በፍጥነት አልፈህ፣ ምነዋ ተከዘ...
ሜዳው ላይ ስትደርስ መልክህ ይቀየራል?
የፊት ጠባይህ ድንገት ይለወጣል?
ሆድህ የማዕበል ግፊት አርግዞ
ደለል ጠጠሩ ምናምንቴ ይዞ፣
ጀርባህ ጥቁር አልማዝ አዝሎ
ከርስህ በነዲድ ሞገድ ግሎ፣
ምነዋ ተከዘላይ ላይህ ስትታይ
ረጋ ስልምልም ትላለህ «እንደ ቀላይ»! ኮሽታህን አጥፍተህ አድፍጠህ
ጸጥ ብለህ ጆሮህን አቅንተህ፣
የምትጓዘው የምታደምጠው አለህ?
ወይስ ትደነግጣለህ ድንገት ስትወርድ ቆላ
ላይህ ላይ ሲያርፍ ግዙፉ የጫካው ጥላ፣ ወይንስ ሥራ ተግባርህ አንተንም አስገርሞሃል
በሐሳብ ወጥመድ አስገብቶ ራስህንም ያስተክዝሃል?
የሀገርህን አንጡራ ሀብቱ
ልም ወርቁ የደለል ክምችቱ፣
ከየሜዳው አፍሰህ…ዝህ
ከየጋራው ፍቀህ..ፈርፍረህ፣
ወስደህ ለባዳ ማስረከቡ
ከወገን ነጥቆ የሰው ሰውን መቀለቡ፣
አሳልፎ መስጠቱ… ማፍሰሱ
ከራስ መንጭቆ ሌላውን ማጉረሱ አሳፍሮህ ይሆን ጸጥ ያልከው?
ይሉኝታ ተጫጭኖህ አንገትህን የደፋኸው?
እንደ አዋሽ ውኃ ውጠህ ኮረንቲ አለመትፋትህ
አፈር አርግዘህ ወይን ሸንኮራ አለመውለድህ፣
እንደ ባሮ ታንኳ አዝለህ እሽሩሩ ማለቱ
እንደ ዋቢ ሙዝ…በቆሎ ማምረቱ፣
እየቻልክ...አለመቻልህ
ይሆን እንዴ ያናደደህ
ዳግም ላትናገር ያስገዘተህ?
ወይንስ የደበቅከው አለህ ምስጢረ አባዜ በል እንጂ ተንፍሰው መላ ምታ ተከዜ፣
ለእልፍ ዓመታት ለፍልፈህ ለፍልፈህ የሚሰማህ ብታጣ ተናግረህ ቢደክምህ!
እርም ዳግም ላልናገር ብለህ በምናኔ የወንዝ ባሕታዊ ሆነህ፣
ይሆን እንዴ ጸጥ ያልከው?
ደብረ አባይ ሥር ዋልድባ ገዳም ከግርጌው
ትካዜን ለብሰህ...ዝምታን የጎረስከው?
ምነዋ! አትፎክር አታቅራራ
እንደ አባይ ኦሞ አትመታ ዳንኪራ
እንደ ሶር ፏፏቴ ምነዋ አታጓራ? ሀገር ለቆ መሄዱ ሲታይህ መለየቱ
ይሆን እንዴ የሆድ ብሶት ናፍቆቱ፣
እንዲህ ዝም የሚያሰኝህ
የሚያስከፋህ የሚያስኮርፍህ?
መልስ እንጂ ተከዘ ዝምታውን አበዛኸውሳ
ይህ ሁሉ በልተህ ጠጥተህ አንዴም አታገሳ?
አይታይህም ሜዳው የሴቲቱ
የወልቃይት ድንግል መሬት የዋልካ ሌማቱ፣
አፉን ከፍቶ ደርቆ
በዋዕይ ካራ ተሰነጣጥቆ፣
የውኃ ያለህ! እያለ ሲማጸን
እንዳልሰማ መስለህ ስትለመን፣
የላጭ ልጅ ቅማል በላው እንዲሉ
ሆድህ ውኃ ተሸክሞ ጀርባህ መቃጠሉ
ምን ይሉታል እንዲህ ዓይነቱ ዝንተ ዓለም ያለፍፌ መንከራተቱ…መዋተቱ እና...ተከዘ መተከዝህን አቁምና አንገትህን ወደ ሀገርህ ሜዳ አቅና ቁም ነገር ሠርተህ በእምነትህ ጽና። ዝመት በረሃብ ላይ አፍህ እሸት ይጉረስ
ተከዘዝመት በድርቅ ላይ ጀርባህ አረንጓዴ ይልበስ
ከወገን ነጥቆ የሰው ሰውን መቀለቡ፣
አሳልፎ መስጠቱ… ማፍሰሱ
ከራስ መንጭቆ ሌላውን ማጉረሱ አሳፍሮህ ይሆን ጸጥ ያልከው?
ይሉኝታ ተጫጭኖህ አንገትህን የደፋኸው?
እንደ አዋሽ ውኃ ውጠህ ኮረንቲ አለመትፋትህ
አፈር አርግዘህ ወይን ሸንኮራ አለመውለድህ፣
እንደ ባሮ ታንኳ አዝለህ እሽሩሩ ማለቱ
እንደ ዋቢ ሙዝ…በቆሎ ማምረቱ፣
እየቻልክ...አለመቻልህ
ይሆን እንዴ ያናደደህ
ዳግም ላትናገር ያስገዘተህ?
ወይንስ የደበቅከው አለህ ምስጢረ አባዜ በል እንጂ ተንፍሰው መላ ምታ ተከዜ፣
ለእልፍ ዓመታት ለፍልፈህ ለፍልፈህ የሚሰማህ ብታጣ ተናግረህ ቢደክምህ!
እርም ዳግም ላልናገር ብለህ በምናኔ የወንዝ ባሕታዊ ሆነህ፣
ይሆን እንዴ ጸጥ ያልከው?
ደብረ አባይ ሥር ዋልድባ ገዳም ከግርጌው
ትካዜን ለብሰህ...ዝምታን የጎረስከው?
ምነዋ! አትፎክር አታቅራራ
እንደ አባይ ኦሞ አትመታ ዳንኪራ
እንደ ሶር ፏፏቴ ምነዋ አታጓራ? ሀገር ለቆ መሄዱ ሲታይህ መለየቱ
ይሆን እንዴ የሆድ ብሶት ናፍቆቱ፣
እንዲህ ዝም የሚያሰኝህ
የሚያስከፋህ የሚያስኮርፍህ?
መልስ እንጂ ተከዘ ዝምታውን አበዛኸውሳ
ይህ ሁሉ በልተህ ጠጥተህ አንዴም አታገሳ?
አይታይህም ሜዳው የሴቲቱ
የወልቃይት ድንግል መሬት የዋልካ ሌማቱ፣
አፉን ከፍቶ ደርቆ
በዋዕይ ካራ ተሰነጣጥቆ፣
የውኃ ያለህ! እያለ ሲማጸን
እንዳልሰማ መስለህ ስትለመን፣
የላጭ ልጅ ቅማል በላው እንዲሉ
ሆድህ ውኃ ተሸክሞ ጀርባህ መቃጠሉ
ምን ይሉታል እንዲህ ዓይነቱ
ዝንተ ዓለም ያለፍፌ መንከራተቱ…መዋተቱ
እና...ተከዘ መተከዝህን አቁምና
አንገትህን ወደ ሀገርህ ሜዳ አቅና
ቁም ነገር ሠርተህ በእምነትህ ጽና።
ዝመት በረሃብ ላይ አፍህ እሸት ይጉረስ
ተከዘ......ዝመት በድርቅ ላይ ጀርባህ አረንጓዴ ይልበስ
(1979 ጅጅጋ)
ካህሳይ ገብረ እግዚያብሄር እንደፃፉት።
ህብረ ብዕር አንደኛ መጽሐፍ ገጽ 163-166
ክቡራት ደንበኞቻችን ዛሬ ማለትም እሑድ መስከረም 27 መጽሐፍት መደብራችን ክፍት መኾኑን ልጠቁመወት እንወዳለን።
እሑድን የእረፍት ጊዜውን መጽሐፍትን በመሸመት ያሳልፉ።
ይህ፡ ታሪክ፡ ቀድሞ፡ በአጼ ቴድሮስ፣ ዘመን፤ ባማርኛ ተተረጐመ። አጼ ቴዎ ድሮሰም፡ ታሪኩን አይተው፡ ጸሓፊውን፡ በቶሎ አስጠሩት፥ እርሱ፣ መምህር፥ ፍላድ፡ የተባሉ፡ የወንጌል፡ መልክተኛ፡ ነበሩ። አርሳቸው ወደ ንጉሡ ሲገቡ፥ ንጉሥ: በዙ ፋናቸው፡ ተቀምጠው፡ ያህን፡ ታሪክ፡ ሲመለከቱ፡ ቆይ፡ ደህን፡ መጽሓፍ፡ የጻፍኸው፡ አንተ፡ ነህን ፧ ብለው ጠየቁ። ቄስ፡ ፍላድም፥ አዎን፥ አኔ፡ ነኝ: የጻፍሁት፥ ብለው፡ መለሱላቸው። የጻፍኸው፡ ስለ፡ ምንድር፡ ነው፡ ብለው፡አጼ፡ ቴወድሮስ፡ ቢጠይቁዋ ቸው፥ መምህር፡ ፍላድ፡ አንዲህ፡ ብለው፡ መለሱ። ያገር፡ ሕዝብ፡ በጎ፡ ነገር፡ አንዲማሩ፡ ብዪ፡ ወደ፡ አገረ፡ወደ፡ ኤውሮጳ፡ ሰድጄ፡ ለማሳተም፡ አስባለሁ:: : ከታተወም፡ በ ኋላ፥ ብዙ፡ መጻሕፍት፡ ወደዚህ፡ አስመጣለሁ።, ይህ፡ መጽሓፍ፡ እጅግ፡ ደስ፡ ይላል፡ ብመልስልህ፡ ትወደለህን፧ ብለው፡ አጼ፡ ቢጠይቁ፥ መምህር፡ ፍላድ፥ አወን፥ አንሳትመው፡ ቢመልሱልኝ፡ በወደድሁ፡ ነበር፥ አሉ፡፡
ንጉሡም፡ ጥቂት፡ ዝም፡ ብ ለሁ፡ ቆይተው፡ አንዷህ አሉ፥ „ይህን፡ መጽሓፍ፡ አጅግ ወድጀዋለሁና፥ ይህን፡ ለኔ፡ አስቀራለሁ፥ አንተ፡ ግን፡ ሌላ፡ ጻፍ።, እርሳቸውም፡ አንደገና፡ በብዙ፡ ድካም፡ ሁለተኛ፡ ጊዜ፡ ሌላ፡ መሓፍ፡ ጽፈው፡ ወደ፡ ኤውሮጳ፡ ልከው፡ አሳትመው፡ አያሉ፡ ሽህ፡ መጻሕፍት፡ ወደ፡ ኢትዮጵያ፡ አስመጡ፡፡ ከዚያ፡ ጊዜ፡ ጀምሮ፡ መንፈሳዊ፡ አውቀት፡ የፈለጉ፡ የኢትዮጵያ፡ ሰወች ያነን፡ ታሪክ፡ ደስ፡ አያላቸው፡ ያነቡታል። ያም: የዛሬ አርባ፡ ዓመት፡ የታተመ፡ የመጽሓፍ፡ ቅዱስ፡ ታሪክ፡ አልቋዋልና፥። አንደ፡ ገና፡ አርመን፡ አሳተምነው። ያ፡ የቀድመው፡ ታሪክ፡ በአያሌ፡ የአማርኛው፡ ሳይቀና፡ ቀርተ፡ የፈረንጆች፡ አገር፡ ይመስል፡ ነበረ፥ ዛሬ፡ ግን፡ እንደ፡ ሕዝብ፡ አነጋገር፡ አድርገን፡ እንደ፡ ቅማችን አቃንተን፡ አረምነው። በዚህ፡ ስራ፡ የረዱኝ፡ መምህር፡ ዮሐንስ ወልደ፡ ማርያም፡ አቶ፡ ገብረ፡ ክርስቶስ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ናቸው፡፡
ከዚህ፡ በኋላ፡ አለቃ፡ ተየ፡ የብሉይን፡ ታሪክ፡ አባ፡ ዘጊዮርጊስም፡ አዲስ፡ ኪደንን፡ ታሪክ፡ አረሙት፡፡
ደህም፡ መጽሓፍ፡ የሰማይን፡ መንገድ፡ የሚመራን፡ የአምላክንም ምሕረት: የ ሚገልጽልን፡ነውና፥ እንደ፡ መልካም፡ ወዳጀችን፡ አድርገን፡ ደስ፡ አያለን፡ አንቀበለው፡፡
አዲስ አበባ ሕዳር ፲፱፻፳።
ካህሊል ስለሜሪና ልጅነቱን ስላደመቀችልት ሀገሩ ሊባኖስ ዘምሮ አይጠግብም፡፡ በስደት በኖረባት አሜሪካ ያፈራውን አብዛኛውን ነገር ለሀገሩ ተናዞላታል፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹የእኔዋ ሊባኖስ በማለዳ ክንፎቻቸውን የሚያማቱ የእርግብ መንጋዎችን ትመስላለች፡፡››
ለእኔም ሀገሬ ሊባኖስን ትመስለኛለች፡፡ ራቅ ራቅ ብለው በበቀሉ ዋርካና ዝግባዎቿ፣ እንደሊባኖስ መሰሎቻቸው ሁሉ ‹ለሕይወት› ዝግ በሆኑ ሴቶቿ ሀገሬ ሊባኖስን ትመስላለች፡፡ ውድቅት ላይ በሹክሹክታ ብቻ በሚሰማ የምስጋና ዜማ አንቀላፍታ ንጋት በምህላ ድምጾች የምትነቃ… ሀገሬ!
ካህሊል ግን እንደ ገጸባህሪው አልሙስጠፋ ጻድቅ ብቻ አልነበረም፡፡ ግለ ታሪኩን ያጠኑ ሰዎች ግብዝ(Hypocrisy)፣ የለየለት ቀጣፊ፣ እንደነበርም መስክረዋል፡፡ ለሜሪ ሕስከል ደጋግሞ ከኢየሱስ ጋር እንደሚገናኝ፣ ራሱም ኢየሱስ እኔ ኢየሱስ ነኝ ብሏታልይባላል፡፡ ግን ቢያንስ ለዛሬ ይህን ስለመሳሰሉ ነገሮች ባናወራስ?
አንድ ስሙን ለማስታወስ የተቸገርኩት ሰው እንዲህ ብሏል፡፡ ‹‹ውብ ፊቶች የተፈጥሮ ድንገቴ ክስተቶች ሲሆኑ ውብ ነፍስ ግን የሕይወት ዘመን የጥበብ ስራ ነች!›› በዚህ ላይ እውነተኛ ጓደኝነት ሲታከልበትማ አስቡት… ካህሊል አዕላፋት የሚረዳቸው አጥተው ወደ ውስጥ እያነፈረቁ በተሸኙባት ዓለም ሜሪ ሐስከልን በማግኘቱ ለዕድለኝነቱ መግለጫ ቃላት አይገኝለትም።
ግን ግን ስንቶቻችን ነን ውብ ጓደኝነታችንን በምስር የለወጥን?
ታላቅ ሰው የመፍጠር እድላችንን እንደ አንዳች ንቀን መወነጃጀልን የመረጥን?
ምናልባት ሁላችንም!
መልካም ንባብ ይኹንልዎ !!!
የናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ ጥናታዊ መጽሐፍ
(ሒሳዊ ንባብ)
**********
ደራሲ፦ ናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ
የመጽሐፉ አርእስት፦ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ሕይወቱ፥ ቀደምት ሥራዎቹና በሥራዎቹ ላይ ያተኮረሩ ጥናታዊ ጽሑፎች
የመጽሐፉ ይዘት፦ ግለ ታሪክ፥ ታሪክ፥ ረጅም ልቦለድ እና አጭር ልቦለድ፥ የሥነ ጽሑፍ ጥናት
ዘመን፦2013 ዓ.ም
አሳታሚ፦ ወገግታ አሳታሚ እና ኤዞፕ መጽሐፍ መደብር
ዐማርኛ መነገር የጀመረው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ7ኛውና በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መካከል ሲሆን፣ ቋንቋው በጽሑፍ የሠፈረው ደግሞ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ዐምደ ጽዮን መሆኑ በእርግጠኝነት ይነገራል፡፡ ዐማርኛ የአፄ ልሳን በመሆን ማገልገል የጀመረው በ13ኛው ክፍለ ዘመን የአገው ሥርወ መንግሥት በአፄ ይኩኖ አምላክ ተነጥቆ የሰለሞን ሥርወ መንግሥት“በዳግማዊነት” ሲቋቋም እንደነበር ያስረዳሉ።
የአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ በኢትዮጵያ የአማርኛ እድገትና ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ አድርጓል። በዚህ መጽሐፉ ውስጥ በውበታቸው ወይም በአጻጻፍ ሥልታቸው ወይም በያዟቸው ሐሳቦች (ቁም ነገሮች) ሳቢያ ህልው ሆነው የሚቆዩ የ1901 ዓ.ም ዘመን እንመለከትባቸዋለን።
እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን፣ የአፈወርቅ በመጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው የቋንቋቸው ውብና በአጻጻፍ ሥልታቸው አንባቢዎችን ማራኪ ወይም ያቀፏቸው ቁም ነገሮች ወይም ሐሳቦች ሁለንተናዊና መሠረታዊ መሆናቸውን ለማሳየት በአማርኛ ቋንቋ ታሪካችንና ሥነ ጽሑፎቻችን ብሎም የመንግሥት የሥራ ቋንቋ አማርኛ መሆን እንዳለበት በማራኪ ትረካዎች አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ "ዳግማዊ አጤ ምኒልክ" በሚል ርዕስ በ1901 ዓ.ም ከታተመው መጽሐፍ ለማሳያነት የሚከተሉትን አንቀጾች እንጠቅሳለን።
«ዳሩ ግን ማን ነው በመልካም አማርኛ አጣፍጦ አሳምሮ ላንባቢው እንዲቀና፥ ለሰሚው እንዲገባ፥ ትንሽ ትልቁ፥ እሴት ወንዱ እንዲያነበው፤ እንዲያደንቀው፤ እንዲቀና አድርጐ የሚጥፈው ?
የተማሩት ሊቃውንቱም ቅዳሴ፣ ምስጢረ ሥላሴ፣ ድጓ፥ቅኔ፥ መዋሲት፥ ዝማሬ ይመስል በጥንት ባሮጌው ቋንቋ በግዕዝ ብቻ ነው መጣፍ የሚወዱ። ይሄን አሮጌ ቋንቋ ለቤተ ክርስቲያን ትተው የቀረውን የዓለሙን ነገር የዓለሙን ሥራ ግን ሁሉ በሚአውቀው ሁሉ በሚናገረ ቋንቋ በአማርኛ ቢፅፍ ደግ ነበረ።
ደግሞም ለንግድ፣ ለጥበብ ለመንግሥት የሚጠቅመውን አማርኛውን ማረም፥ ማሳመር፥ ማስተማር፥ ማልማት ይሻላል፤ ይገባልም። ዛሬ አለቃ ታየ የሚሉት ደቀመዝሙር ያጤ ምኒልክን ታሪከ ነገሥት ሊጥፋ ታዝዟል ይባላል። እስቲ ተሆነ እናያለን፡፡ አግዚአብሔር ይገዘው፡፡ ነገር ግን ሁሉ እንዲያነበውና እንዲገባው በግዕዝ ትቶ ባማርኛ ባደረገው ደግ ነበረ።
አማርኛው ግን ገጥ ያለ፣ ቅልጥፍ ያለ ላንደበት የተስማማ፣ ለጆሮ ያልገማ ላንባቢው የሚመች፣ ለሰሚው ማይሰለች እንዲሆን አድርጎ መጣፍ ነው።
ግዕዝ ብቻ ማሳመር አባቱን ንቆ ግዕዝ ብቻ ማክበር፣ አባቱን ገሎ ላማቹ ይነጭ፣ አማቱን ጋርዶ እናቱን ያስፈጭ የሚሉት ነገር ነው። አማርኛ ማልከስከስ አሮጌ ቋንቋ ማደስ የተገባም አይደል፡፡ አማረኛን ማረም፣ ማሳመር ማስተማር ነው፡፡ አማርኛን የሚአሳምር ጠፋ እንጂ ለመዶግዶግማ ፊደል ሳይቆጥር በመጋፊያ እየጣፈ፣ በገል3 እየጫረ ጽሕፈት የተማረ ሁሉስ ይዶገዱግ የለምን?
ያም ሆነ ያም አለቃ ታየን የመሰለ ብልህ የተማረ ሰው አማረኛውን አስተውሎ ይጥፍ ዘንድ ተስፋ አለን። ያጤ ምንልክን ታሪክ በግዕዝ የጣፈ እንደሆነ ግን ታልተፃፈ ቁጥር ነው። ሮማይስጡን ለቤተ ክርስቲያናቸውና በፈረንጅ አገርም የጥንቱን ቋንቋ ለሌላ ነገር ትተው ሁሉም አዲስ ቋንቋቸውን እያረሙ፣ ለልጆቻቸውም ያስተምራሉ። ኢትዮጵያ እንዲሁ ማድረግ ይገባታል (ከገጽ 83 - 84)።
* * * * *
«ኮንት አንቶኔሊ አንሥቶ ውጫሌ የተዋዋልንበት ወረቀት በፈረንሳዊ ቋንቋ የተጻፈው ይታይ አለ። እቴጌ ጣይቱ ግን እኛ የምናውቀው ባማረኛ የተጻፈውን ነው እንጂ የፈረንጅ ቋንቋ አናውቅም:: አንተ ግን የኛን ቋንቋ ታውቃለህና ባማረኛ የተጻፈውን እየው አሉት።
ከዚህ ወዲያ ኮንት አንቶኔሊ ነገሩ ሁሉ እንዳልሆነለት አይቶ በንዴት ያን የታተመውን ደብዳቤ ብጭቅጭቅ አድርጐ ቀዳዶ ጣለና እንግዴህ ፍቅራችን ፈረሰ ብሎ የጦርነቱን ነገር ገልጦ ተናግሮ ወጣ።
እቴጌ ጣይቱ ከት ከት ብለው ስቀው የዛሬ ሳምንትም አድርገው። በዚህ የሚደነግጥልህ የለም። ሂድ የፈከርህበትን አድርግ። እኛም የመጣውን እናነሣዋለን፡፡ እግሩን ለጠጠር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው ከዚህ ያለ አይምሰል። የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነው እንጂ ሞት አይባልም። አሁንም ሂድ አይምሽብህ፤ የፈከርህበትን በፈቀደህ ጊዜ አድርገው። እኛም ከዚህኸው እንቆይሃለን አሉት።
ያው ፈረንጅ በንዴት እጅና እግሩ እየተንቀጠቀጠ ፊት እንዲያውም እንዲአ ነበረና ጭው ብሎ ላዳን እንዶድ የጨረሱበት ሸማ መስሎ እጅ ሳይነሣ ተወርውሮ ወጣ (ገጽ 127)።
---------------------------------------
እስከዛሬ በእኔ ትሑት አስተያየት ታሪክና ሥነ ጽሑፍን በአንድ ላይ አዋሕዶ በጥናትና በምርምር የተዘጋጀ መጽሐፍ በናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ የተዘጋጀው "የአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ" ሥራ ይመስለኛል። መጽሐፉ ሁለቴ የታተመ ሲሆን፣ ወደፊት ሦስተኛው እትም የሚታተም ከሆነ መጥቍም ቢኖረው መልካም ነው። ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ ጥናታዊ በመሆኑ ተመራማሪዎች፥ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ጋዜጠኞች የሚፈልጉት ጥናት ለማግኘት በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። እርግጥ የመጽሐፉ ማውጫ ላይ በየክፍሉ የተዋቀረው ምዕራፍ እያንዳንዱ ዓብይ ጉዳይ የሚገልጽ ቢሆንም የቦታ ስምች፣ የሰው ስም፣ በፊደል ቅደም ተከተል በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል። በተረፈ ናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ በለመደው እጅ ሌላ ጥናታዊ መጽሐፍ እንደምታበረክት ተስፋ አለ።
በመጨረሻም መጽሐፍ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ልቦለድ (1900 ዓ.ም) እንጎቻ ወግ (አጭር ልቦለድ) ከ1900 ዓ.ም ጀምሮ የታተመው የፈጠራ ሥራዎች፣ የኢትዮጵያ ታሪክን በተለይ የዐፄ ምኒልክ ከልጅነት አስከ ንጉሠ ነገሥትነት ዘመነ መንግሥት ደረስ ያለውን ታሪክ ሸጋ በሆነ አማርኛ ያስቃኛል።
አንባቢያን ሆይ መጽሐፉን አንብቡት ። ታዲያ መጣፉኑ በምታነቡበት ወቅት የእርጋታ ጊዜ፥ የመንፈስ ጸጥታን፥ በአመዛዛኝ ኅሊና፥ በአስተዋይ ልቦና ይሁን። መልካም ንባብ !
ፀጋየ ገብረመድን ሮበሌ እንደፃፈው