የሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፍት
#ተአምኖ ቅዱሳን ብድር ሮዳስ ታደሰ የተተረጎመ
#ኋኅተ ብርሃን
#እንዚራ ስብሐት
ግዕዝና አማርኛ
መጽሐፍቶ !!!!
እውነት ሆይ! ‹ምንድን ነኝ› ትያለሽ?
ዳኝነትን ይዞ ሐሰትን ለማጥፋት፣ ያም አለ ያም አለ አልተገኘም እውነት አሉ አስተዋዮቹ አበው፡፡
የአበው አስተውሎት ጥልቀት የሚገባንም በእውነት ህልውነት (መኖር) ላይ ስምምነት ኖሮን የእውነት ትርጓሜን በመረዳት ስለምንነቷና መገለጫዎቿ መነጋገር፣ ከዕውቀትና ከመልካምነት ጋር እንዴት በተዋሕዶ እንደምትከብር ስንገነዘብ ነው፡፡ ‹እውነት ምንድን ናት?› እንዳለው ጲላጦስ፡፡ ምን ጲላጦስ ብቻ በፍልስፍናው ዓለምም ጥልቅና ምጡቅ የኾነች አስጨናቂ ጥያቄ ኾና ስንቱን ምሁር አነሁልላለች እንጂ በጥቅሉ ግን ሊቃውንቱ እንደሚከተለው ተርጉመዋታል፡፡
‹እውነት› ማለት ይላል እጓለ ‹ሕሊና የሚሰጠው ፍርድ ከገዛ ራሱ ሕግጋት ጋር የሚስማማ ሲኾን ነው፡ የሕሊና ሕግጋት ደግሞ በልቦና የተጻፉ ናቸው። እነዚኽ ሕግጋት ከውጭው ዓለም እውን ነገር ጋር ተስማምተው ሲገኙ እውነትን ያስገኛሉ። ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ ‹የአንድ እውን (ህልው) ነገር ከሕሊና ዳኝነት ጋር በትክክል፣ በበቂትና በምሉዕነት ተስማምቶ መግኘት ነው› ወይም ‹እውነት ማለት የህልው ነገር በሐሣብነት በአእምሮ በትክክል መወከል ነው› ይሉናል ። ስለዚኽ በእውነት ውስጥ ኹለት ነገሮች ተያይዘው ይገኛሉ ማለት ነው፡ (፩) የሚታወቀው የህልው ነገር መኖር (Existence) እና (፪) የእሱም በትክክልና በምሉዕነት በሕሊና ውስጥ በሐሳብነት መወከል ወይም የሕሊና ትክክለኛና ብቁ ዳኝነት፡፡ ይኽም ማለት የሚታወቀው ነገርና ማወቂያው አእምሮ ያላቸው የምሉዕነትና አግባባዊ ግንኙነት እውነትን ይፈጥራል፡፡ ስለዚኽ ህልው ነገር (Reality)፣ ሐሳብ (Idea) እና እውነት (Truth) አንድም ሦስትም በመኾን በአንድነት ተያይዘው ይገለጻሉ ማለት ነው፡፡ ህልው ነገር ካለ ሊታወቅ የሚችለው ከሕሊና ጋር በሚያደረገው መስተጋብር _ ነው (በመታሰብ)፡፡ የህልው ነገር በትክክልም በሐሳብነት ሲወከልም ለሚያስበው እውነት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ያለው ህልው ነገር በሐሳብነት የማይታወቅ ከኾነ ወይም የሚታሰበው ነገር በእውንነት ህልው ያልኾነ ከኾነ እውነት ልትኖር አትችልም፡፡
ቅኔ ፍልስፍና ዘጦቢያ
ገጽ 129
በአፌ ውስጥ በስብሶ የሚያስቸግረኝ አንድ ጥርስ አለኝ በቀን ሰላማዊ ሆኖ ይውላል ። ምሽቱ ሲገፋ፣ የጥርስ ሃኪሞቹ እንቅልፍ ሲጥላቸው እና መድሃኒት ቤቶቹ ሲዘጉ ግን ይጠዘጥዘኝ ይጀምራል።
አንድ እለት ትዕግስት ተሟጠጠና ወደ አንድ የጥርስ ሃኪም ሄጄ ያንን ስቃይ ያበዛብኝንና የምሽቴን ፀጥታ ወደ ማቃሰት እና ማጓራት በመለወጥ እንቅልፍ የነሳኝን ጥርስ እንዲነቅልልኝ ነገርኩት ።
የጥርስ ሃኪሙ ራሱን ከግራ ቀኝ እየወዘወዘ " ጥርሱን ማዳን ስንችል መንቀሉ ቂልነት ነው " አለኝ ። ከዚያም ጎንና ጎኖቹን በስቶ ቀዳዳዎቹን በማፅዳት ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሊመልሰው እና ከብስባሴው ሐራ ሊያወጣው ያለውን መንገድ ሁሉ ተጠቀመ ። መብሳቱን ከጨረሰ በኋላ በንፁህ ወርቅ ሞላውና " የበሰበሰው ጥርስህ አሁን ከጤነኞቹ የበለጠ ጠንካራና ብርቱ ነው " አለኝ በኩራት።
እኔም አመንኩት። ከፈልኩትና ስፍራውን ለቅቄ ሄድኩ ።
ነገር ግን ገና ሳምንቱ ሳይገባደድ የተቀሰፈው ጥርስ ወደ ህመሙ ተመለሰና የነፍሴን ጥዑም ዜማ ወደ ለቅሶና ስቃይ ለወጠብኝ ። እናም ወደ ሌላ የጥርስ ሃኪም አመራሁና " ምንም ጥያቄ ሳይጠይቀኝ ይህንን ጥርስ አውጥተህ ጣልልኝ ። የደረሰበትና ያልደረሰበት ግልግልን እኩል አያውቃትም! " አልኩት ።
ትዕዛዜን በማክበር ጥርሴን ነቀለልኝ ። ከዚያም ጥርሴን እያየ " ይህ ጥርስ እንዲነቀል በማድረግህ መልካም አድርገሃል " አለ ።
በአፍ ማህበረሰብ ውስጥ እስከ መንጋጋ አጥንት ድረስ የበሰበሱ ብዙ በሽተኛ ጥርሶች አሉ። ይሁንና ማህበረሰቡ እነዚህን የተበላሹ ጥርሶች ለማስነቀልና ከስቃዩ ለመገላገል ምንም ጥረት አያደርግም ። ራሱንም በወርቅ ፍቅፋቂ ይሞላል። አብዛኞቹ የበሰበሱትን የማህበረሰብ ጥርሶች በሚያብለጨልጭ ወርቅ እንደሚያክሙ የጥርስ ሃኪሞች ናቸው ።
እንደዚህ ተጠጋግነው በመደለል የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ስቃይ ህመምና ሞት ዕጣ-ፈንታቸው ናቸው ።
ሀገር አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ እና ቆሻሻ ፣ ያመረቀዙና የሚሸቱ ጥርሶች አሉ። ሃኪሞቹ ከመንቀል ይልቅ በወርቅ ፍቅፋቂ አክመዋቸዋል። ህመሙ ግን እንዳለ ነው።
የበሰበሰ ጥርስ ያለው ሃገር የታመመ ጨጓራ እንደሚኖረው እርግጥ ነው። በዚህ ያለመፈጨት ችግር ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሀገራት አሉ።
ሀገር ዳቦውን በበሰበሰ ጥርሱ እንደሚያኝክ እና አንዳንዱም ጉርሻ ከተመረዘ ምራቅ ጋር በመዋሃድ በሽታውን በሃገሩ ጨጓራ ውስጥ እንደሚያሰራጭ ስትነግሯቸው " አዎ ግን የተሻሉ የጥርስ ሙሌቶች እና ማደንዘዣዎች እየፈለግን ነው " ይሏችኋል።
📖 " የጥበብ መንገድ " የውስጥ ገፅ የተቀነጨበ
ደራሲ ✍ ካህሊል ጂብራን
ትርጉም✍ሀብታሙ ተስፉዬ
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
🙏🙏🙏🙏
የኛ ሰንደቅ
ጨርቁ
ጨለም ብሎ ይወርዳል፤
ነፈሰ ብሎ ይርዳል።
ምሰሶው ማን ...........
በጥቁር ሰማይ ስር፡ በአውሎ ነፋስ መሃል፤
አርማ ተሸክሞ፡ ዘላለም ይቆማል፡ ዘላለም ይፀናል፡፡
ስለዚህ..............
ውረድ! ሲሉት ከሚወርድ፡ ነፈሰ ብሎ ከሚርድ፡
የቀለማት ድርድር፤
ም
ሰ
ሶ
ው
ነው ያገር ሰንደቅ፡ ሌቱን ጸንቶ አሳልፎ፡
መዓቱን ቆሞ ሚሻገር።
ያልተፈቀረች ሴት ገጽ 19
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
/channel/azop78
/channel/azop78
/channel/azop78
ይህን መጽሐፍ ሳነበው የተሰማኝ እንዲህ ነው
እኛ ሰዎች የፈጠርናቸው ነገሮች ያለ እኛ ትርጉም አልባ አይደሉምን? እንዲሁ ተፈጥሮም በዓላማ ክፈጠራትና ካስገኛት ከፈጣሪዋ ውጪ ምንድን ናት? በጥቂት አሳቢዎች ፍልስፍና መነሻነት የምዕራቡ ዓለም ስልጣኔ አምላክ የለሽ ሆኗል፡፡ ምዕራባዊው ማኅተፈ-ዕሳቤ ሕይወትና ዓለሙን ሁሉ ከፈጣሪው ዓላማ ነጥሎ ትርጉም ሊሠጣቸው ይሞክራል፡፡ ሕይወት ግን ከተፈጥሮ ዓላማዋ በራቀችበት መጠን ይበልጥ ትርጉም እያጣች ሔዳለች፡፡ ከዚህ የተነሣ ሰዎች ደስታን ፍለጋ የሚያደርጉት ጥረት በተቃራኒው ለበዛ መከራ ዳርጎታል፡፡ ይህም ደግሞ ወንዝ ዳር የለመለመችውን ተክል ወስዶ አሸዋ ላይ እንደመትከል ነው፡፡
ሥዝሙ ሥልጣኔ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለሕይወት የሚያደርገው አስተዋጽኦ ሁሉ ያለ ተፈጥሮ ዕሴቷ አለት ላይ ለተተከለችው ተክል ውኃ እንደማጠጣት፣ ጊዜያዊ እፎይታን እንጂ ዘላቂ ሰላምና እርካታን ሲያስገኝላት አይታይም፡፡ ይህ ምዕራባዊ ቁሳዊ ዕሳቤ ዛሬ መደበኛው ቢሮክራሲ የሚመራበት ፖሊሲ ነው፡፡
የመንግሥት ፖሊሲና የትምሕርት ተቋሞቻችንም ይህንኑ ይግቱናል፡፡ ጥቂቶች ሀገራት በራሳቸው መንገድ ወንዝ ሆነው ሲፈሱ፣ የራሳቸው ቀለም ያለው ልህቀት ባለቤት በመሆን ለዓለም አበርክቶ ኖሯቸዋል፡፡ ብርቱ አእምሮ ያጡ እንደኛ ያሉ ሀገራት የምዕራቡን ዓለም መንገድ ኩረጃ ላይ በማትኮር ከጅራትነት የማያሳልፍ ጉዞ ውስጥ ገብተዋል ፡፡
አንባቢያን እጅ እንዲደርስ ጸሎቴ የነበረው ይህ የመምህሬ ጋሽ ፈንታሁን መጽሐፍ እሳቤዎችን እንድንፈትንና ግለሰባዊ ንቃት ኖሮን ማኅበረሰባዊ ልዕልናን እንድናደርግ የሚያስችለን ነው፡፡ እንደ ግል አንዴ ብቻ የምንኖራትን የምድር ሕይወት እንደ ንስር ከፍ ባለ ዕይታ ከሐሳቦች ሁሉ መርጦ በላቀው መንገድ የመምራት አዕምሮን ያስታጥቃል፡፡ እንደ ማኅበረሰብ ወንዝ ሆነን በራሳችን ማኅቀፈ-ዕሳቤ መፍሰስ እንድንችል የሚረዳን መጽሐፍ ነው፡፡
አንድ ክፍለ ዘመን የደፈነው ምዕራባዊው የትምሕርት ጉዟችን ችግሮቻችንን ይበልጥ እያወሳሰባቸው የመጣበትን መንስኤ ማሳየት ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ የዕውቀት ሥሪቱን ጉድለቶች ማከምም የሚያስችለን መጽሐፍ ነው፡፡
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
ኤፒክቲተስ
የስቶይኪዝም ፍልስፍና መሰረት የሆነው የኤፒክቲተስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ከዋለ ቆየት ቢልም ብዙ የመነበብ እድል ካላገኙት መካከል ነው
እንዳይነበብ ያደረገው የመጽሐፉ ጥሩ አለመኾኑን ሳስብብይገርመኛል።
ከኤፒክቲተስ [የስቶይኪዝም] ፍልስፍና መሰረተ ትምህርቶች ምንጭ የሆነውና ጥልቅ ለሰው ልጅ ጠቃሚ ትምህርቶችን ማስተላለፍ የቻለው ኤፒክ 2000 ዓመታት የሰው ልጅን ህይወት እጅግ ጣፋጭ እንዲሆን የሚያስችሉ ጠቃሚ ትምህርቶችን ያስተማረና 2000 ዓመታትን መሻገር የቻሉ ጥልቅ አስተምህሮቶች ባለቤት ነው...!!
#ከሕይወት ጋር #ግብግብ ትተው #ሕብረትን ይፍጠሩ ...!!
የራሴ ህግ የሚሉትን ነገር እንዳይሞክሩት፡፡ ትልቅ፣ ትንሽ፣ የሰለጠነ፣ የተናቀ ሳይሉ ከሁሉም ነገር ጋር ግንኙነትዎን በተፈጥሯዊ ህግ መሰረት ያድርጉ፡፡ ምኞትዎን ከተፈጥሮ ጋር ሕብር ባለው ሁኔታ ማናበብ ዋነኛ ግብዎ ሊሆን ይገባል፡፡
ይህንን ልምምድ የሚያከናውኑትስ የት ነው..?
በእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ነዋ... ይለናል ኤፒክ። ሲሰሩ፣ ሲመገቡ፣ ገላዎን ሲታጠቡ ፣ ብቻ ምን አለፋው ማንኛውንም ነገር ሲያከናውኑ ከተፈጥሮ ምሪት ጋር በተናበበ መልኩ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ ጉዳዩ ምን አከናወኑ አይደለም፡፡ እንዴት አከናወኑ እንጂ… ይህንን መርህ በቅጡ ተገንዝበን መተግበር ከጀመርን በሕይወታችን ውስጥ የቱንም ያህል ችግሮች ሊፈጠሩ ቢችሉ (ምክንያቱም ችግሮ የተፈጥሮ ሂደት አካል ናቸውና) ውስጣዊ ሰላምን መጎናጸፍ ዘወትር የሚቻል ይሆናል፡፡ የሚሉና ሌሎች ጠቃሚ መሰረታዊ የህይወት አስተምህሮዎችን ሰብኳል ።.!!..
ለንባብ ባህል መጎልበት እንተጋለን..!!
ኤዞፕ መጽሐፍት ቴሌግራም ተከተሉኝ ብሏችኊል !!
/channel/azop78
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አንዳንድ የራፕ ሙዚቃ ተጫዋቾች እና የስልቱ ወዳጆች የአሜሪካውያን የራፕ ስልት የተወሰደው ከኢትዮጵያውያን ባህላዊ የሙዚቃ አጨዋወት እንደ ፉከራ፣ቀረርቶ ከመሳሰሉት ነው ብለው ቢያምኑም ይህን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት በጥናት የተደገፈ መረጃ አልተገኘም፡፡
ኮንፊሽየስ /Confusioin/551-479B.C/:-የጥንታዊቷ ቻይና ገፀ-በረከት ሆኖ በብዙ ስራዎቹ የሚታወቀው ይህ ፈላስፋ በሙዚቃ ፍልስፍናውም ሙዚቃን እና የስልጣን አስተዳደርን እርስ በርሳቸው የተያያዙ እንደሆኑ አንድ ሰው የተሻለ የሙዚቃ አረዳድ ካለው ለስልጣናዊ አስተዳደር የተሻለ ችሎታ አለው በማለት አስረድቷል። ኮንፊሽየስ ሙዚቃ እንደ የግንባታ ጥበብ፣እጅ ፅሁፍ ሒሳብ የመሰሉት ጋር እኩል የሆነ ትልቅ የጥበብ ዘርፍ መሆኑን ያስረዳ ሲሆን በቻይናዊያን ባህል የአርአያነት እሳቤ የሚደገፍ በመሆኑ ኮንፊሽየስ በራሱ ሙዚቃን የሚጫወት እንደ ነበር ይነገራል፡፡
በ1903G.C ዊልያም ክርስቶፎል ሀንዲ (W.C Handy) (የብሉዝ ሙዚቃ አባትና የዳንስ ኦርኬስትራ መሪ) ከትንሽየዋ መንደር ቶቷዊር ሚሲሲፒ ባቡር በመጠበቅ ላይ ሳለ ባቡሩ በጣም ስለዘገየ አግዳሚ ወንበር ላይ ጋደም ይላል፡፡ ከእንቅልፉ ሲነቃም አንድ ጥቁር አፍሪካዊ ከጎኑ “Going where the southern cross the dog የሚል ሙዚቃ በጊታሩ ሦስት ጊዜ እየደጋገመ ሲጫወት ተመለከተ፡፡ ሙዚቃውን መጫወት እንዳቆመም ሀንዲ ይህ ስንኝ ምን እንደሆነ ጠየቀው ሙዚቀኛው ግን አልመለሰለትም፡፡ ሀንዲ በዚህ ሙዚቃ እጅጉን በመገረም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ይህንን ሙዚቃ “Yellow Dog Blues” በሚል ይሰራዋል፡፡ በዚህም ብሉዝ የሚባለውን ስያሜ ለሙዚቃው ስልት በመስጠቱ የብሉዝ አባት እንዲባል አስችሎታል።
ዲጄ የሚለው ምህጻረ-ቃል ዲስክ ጆከር/Disc Jockey/ የሚል ትንታኔና የሸክላ ሙዚቃ አጫዋች የሚል የአማርኛ ፍቺ ያለው ሆኖ የቃል ስያሜውን ያገኘው በአሜሪካ ነበር፡፡
ከመጽሐፉ የተወሰደ
ተከዜ...ተከዘ?
የላስታው ጠብታ...የወርዒ ዘለላ
የሰሜኑ ፍላቂ...ሥርወ ላሊበላ፣
ከጎንደር ከወሎ...ማዶ ለማዶ
ተሽሎኩልከህ ተወርውረህ...እንደ ዘንዶ፣
ቁልቁል ስትዘል ስትል ዱብ...ሿ....
ሸለቆውን ስታጠልቅ ጠባቡን ስታሰፋ፣
ማራኪው ፏፏቴህ...ተምዘግዝጎ ወራጅ
አለት አስደንጋጩ ድንግል መሬት ቀዳጅ፣
የጎርፍህ ፍጥነቱ...ሽታው ድምፁ
የአለት ድድህ ፍላፃ...ገጹ፣
ድፍርስ...ደፋር...አስፈሪ
ጉምልል...ጉምልል ባይ ጨፋሪ፣
ጋራ ገደሉን ሩጠህ...ሩጠህ
ጠባቡን መንገድ በፍጥነት አልፈህ፣ ምነዋ ተከዘ...
ሜዳው ላይ ስትደርስ መልክህ ይቀየራል?
የፊት ጠባይህ ድንገት ይለወጣል?
ሆድህ የማዕበል ግፊት አርግዞ
ደለል ጠጠሩ ምናምንቴ ይዞ፣
ጀርባህ ጥቁር አልማዝ አዝሎ
ከርስህ በነዲድ ሞገድ ግሎ፣
ምነዋ ተከዘላይ ላይህ ስትታይ
ረጋ ስልምልም ትላለህ «እንደ ቀላይ»! ኮሽታህን አጥፍተህ አድፍጠህ
ጸጥ ብለህ ጆሮህን አቅንተህ፣
የምትጓዘው የምታደምጠው አለህ?
ወይስ ትደነግጣለህ ድንገት ስትወርድ ቆላ
ላይህ ላይ ሲያርፍ ግዙፉ የጫካው ጥላ፣ ወይንስ ሥራ ተግባርህ አንተንም አስገርሞሃል
በሐሳብ ወጥመድ አስገብቶ ራስህንም ያስተክዝሃል?
የሀገርህን አንጡራ ሀብቱ
ልም ወርቁ የደለል ክምችቱ፣
ከየሜዳው አፍሰህ…ዝህ
ከየጋራው ፍቀህ..ፈርፍረህ፣
ወስደህ ለባዳ ማስረከቡ
ከወገን ነጥቆ የሰው ሰውን መቀለቡ፣
አሳልፎ መስጠቱ… ማፍሰሱ
ከራስ መንጭቆ ሌላውን ማጉረሱ አሳፍሮህ ይሆን ጸጥ ያልከው?
ይሉኝታ ተጫጭኖህ አንገትህን የደፋኸው?
እንደ አዋሽ ውኃ ውጠህ ኮረንቲ አለመትፋትህ
አፈር አርግዘህ ወይን ሸንኮራ አለመውለድህ፣
እንደ ባሮ ታንኳ አዝለህ እሽሩሩ ማለቱ
እንደ ዋቢ ሙዝ…በቆሎ ማምረቱ፣
እየቻልክ...አለመቻልህ
ይሆን እንዴ ያናደደህ
ዳግም ላትናገር ያስገዘተህ?
ወይንስ የደበቅከው አለህ ምስጢረ አባዜ በል እንጂ ተንፍሰው መላ ምታ ተከዜ፣
ለእልፍ ዓመታት ለፍልፈህ ለፍልፈህ የሚሰማህ ብታጣ ተናግረህ ቢደክምህ!
እርም ዳግም ላልናገር ብለህ በምናኔ የወንዝ ባሕታዊ ሆነህ፣
ይሆን እንዴ ጸጥ ያልከው?
ደብረ አባይ ሥር ዋልድባ ገዳም ከግርጌው
ትካዜን ለብሰህ...ዝምታን የጎረስከው?
ምነዋ! አትፎክር አታቅራራ
እንደ አባይ ኦሞ አትመታ ዳንኪራ
እንደ ሶር ፏፏቴ ምነዋ አታጓራ? ሀገር ለቆ መሄዱ ሲታይህ መለየቱ
ይሆን እንዴ የሆድ ብሶት ናፍቆቱ፣
እንዲህ ዝም የሚያሰኝህ
የሚያስከፋህ የሚያስኮርፍህ?
መልስ እንጂ ተከዘ ዝምታውን አበዛኸውሳ
ይህ ሁሉ በልተህ ጠጥተህ አንዴም አታገሳ?
አይታይህም ሜዳው የሴቲቱ
የወልቃይት ድንግል መሬት የዋልካ ሌማቱ፣
አፉን ከፍቶ ደርቆ
በዋዕይ ካራ ተሰነጣጥቆ፣
የውኃ ያለህ! እያለ ሲማጸን
እንዳልሰማ መስለህ ስትለመን፣
የላጭ ልጅ ቅማል በላው እንዲሉ
ሆድህ ውኃ ተሸክሞ ጀርባህ መቃጠሉ
ምን ይሉታል እንዲህ ዓይነቱ ዝንተ ዓለም ያለፍፌ መንከራተቱ…መዋተቱ እና...ተከዘ መተከዝህን አቁምና አንገትህን ወደ ሀገርህ ሜዳ አቅና ቁም ነገር ሠርተህ በእምነትህ ጽና። ዝመት በረሃብ ላይ አፍህ እሸት ይጉረስ
ተከዘዝመት በድርቅ ላይ ጀርባህ አረንጓዴ ይልበስ
ከወገን ነጥቆ የሰው ሰውን መቀለቡ፣
አሳልፎ መስጠቱ… ማፍሰሱ
ከራስ መንጭቆ ሌላውን ማጉረሱ አሳፍሮህ ይሆን ጸጥ ያልከው?
ይሉኝታ ተጫጭኖህ አንገትህን የደፋኸው?
እንደ አዋሽ ውኃ ውጠህ ኮረንቲ አለመትፋትህ
አፈር አርግዘህ ወይን ሸንኮራ አለመውለድህ፣
እንደ ባሮ ታንኳ አዝለህ እሽሩሩ ማለቱ
እንደ ዋቢ ሙዝ…በቆሎ ማምረቱ፣
እየቻልክ...አለመቻልህ
ይሆን እንዴ ያናደደህ
ዳግም ላትናገር ያስገዘተህ?
ወይንስ የደበቅከው አለህ ምስጢረ አባዜ በል እንጂ ተንፍሰው መላ ምታ ተከዜ፣
ለእልፍ ዓመታት ለፍልፈህ ለፍልፈህ የሚሰማህ ብታጣ ተናግረህ ቢደክምህ!
እርም ዳግም ላልናገር ብለህ በምናኔ የወንዝ ባሕታዊ ሆነህ፣
ይሆን እንዴ ጸጥ ያልከው?
ደብረ አባይ ሥር ዋልድባ ገዳም ከግርጌው
ትካዜን ለብሰህ...ዝምታን የጎረስከው?
ምነዋ! አትፎክር አታቅራራ
እንደ አባይ ኦሞ አትመታ ዳንኪራ
እንደ ሶር ፏፏቴ ምነዋ አታጓራ? ሀገር ለቆ መሄዱ ሲታይህ መለየቱ
ይሆን እንዴ የሆድ ብሶት ናፍቆቱ፣
እንዲህ ዝም የሚያሰኝህ
የሚያስከፋህ የሚያስኮርፍህ?
መልስ እንጂ ተከዘ ዝምታውን አበዛኸውሳ
ይህ ሁሉ በልተህ ጠጥተህ አንዴም አታገሳ?
አይታይህም ሜዳው የሴቲቱ
የወልቃይት ድንግል መሬት የዋልካ ሌማቱ፣
አፉን ከፍቶ ደርቆ
በዋዕይ ካራ ተሰነጣጥቆ፣
የውኃ ያለህ! እያለ ሲማጸን
እንዳልሰማ መስለህ ስትለመን፣
የላጭ ልጅ ቅማል በላው እንዲሉ
ሆድህ ውኃ ተሸክሞ ጀርባህ መቃጠሉ
ምን ይሉታል እንዲህ ዓይነቱ
ዝንተ ዓለም ያለፍፌ መንከራተቱ…መዋተቱ
እና...ተከዘ መተከዝህን አቁምና
አንገትህን ወደ ሀገርህ ሜዳ አቅና
ቁም ነገር ሠርተህ በእምነትህ ጽና።
ዝመት በረሃብ ላይ አፍህ እሸት ይጉረስ
ተከዘ......ዝመት በድርቅ ላይ ጀርባህ አረንጓዴ ይልበስ
(1979 ጅጅጋ)
ካህሳይ ገብረ እግዚያብሄር እንደፃፉት።
ህብረ ብዕር አንደኛ መጽሐፍ ገጽ 163-166
ክቡራት ደንበኞቻችን ዛሬ ማለትም እሑድ መስከረም 27 መጽሐፍት መደብራችን ክፍት መኾኑን ልጠቁመወት እንወዳለን።
እሑድን የእረፍት ጊዜውን መጽሐፍትን በመሸመት ያሳልፉ።
ይህ፡ ታሪክ፡ ቀድሞ፡ በአጼ ቴድሮስ፣ ዘመን፤ ባማርኛ ተተረጐመ። አጼ ቴዎ ድሮሰም፡ ታሪኩን አይተው፡ ጸሓፊውን፡ በቶሎ አስጠሩት፥ እርሱ፣ መምህር፥ ፍላድ፡ የተባሉ፡ የወንጌል፡ መልክተኛ፡ ነበሩ። አርሳቸው ወደ ንጉሡ ሲገቡ፥ ንጉሥ: በዙ ፋናቸው፡ ተቀምጠው፡ ያህን፡ ታሪክ፡ ሲመለከቱ፡ ቆይ፡ ደህን፡ መጽሓፍ፡ የጻፍኸው፡ አንተ፡ ነህን ፧ ብለው ጠየቁ። ቄስ፡ ፍላድም፥ አዎን፥ አኔ፡ ነኝ: የጻፍሁት፥ ብለው፡ መለሱላቸው። የጻፍኸው፡ ስለ፡ ምንድር፡ ነው፡ ብለው፡አጼ፡ ቴወድሮስ፡ ቢጠይቁዋ ቸው፥ መምህር፡ ፍላድ፡ አንዲህ፡ ብለው፡ መለሱ። ያገር፡ ሕዝብ፡ በጎ፡ ነገር፡ አንዲማሩ፡ ብዪ፡ ወደ፡ አገረ፡ወደ፡ ኤውሮጳ፡ ሰድጄ፡ ለማሳተም፡ አስባለሁ:: : ከታተወም፡ በ ኋላ፥ ብዙ፡ መጻሕፍት፡ ወደዚህ፡ አስመጣለሁ።, ይህ፡ መጽሓፍ፡ እጅግ፡ ደስ፡ ይላል፡ ብመልስልህ፡ ትወደለህን፧ ብለው፡ አጼ፡ ቢጠይቁ፥ መምህር፡ ፍላድ፥ አወን፥ አንሳትመው፡ ቢመልሱልኝ፡ በወደድሁ፡ ነበር፥ አሉ፡፡
ንጉሡም፡ ጥቂት፡ ዝም፡ ብ ለሁ፡ ቆይተው፡ አንዷህ አሉ፥ „ይህን፡ መጽሓፍ፡ አጅግ ወድጀዋለሁና፥ ይህን፡ ለኔ፡ አስቀራለሁ፥ አንተ፡ ግን፡ ሌላ፡ ጻፍ።, እርሳቸውም፡ አንደገና፡ በብዙ፡ ድካም፡ ሁለተኛ፡ ጊዜ፡ ሌላ፡ መሓፍ፡ ጽፈው፡ ወደ፡ ኤውሮጳ፡ ልከው፡ አሳትመው፡ አያሉ፡ ሽህ፡ መጻሕፍት፡ ወደ፡ ኢትዮጵያ፡ አስመጡ፡፡ ከዚያ፡ ጊዜ፡ ጀምሮ፡ መንፈሳዊ፡ አውቀት፡ የፈለጉ፡ የኢትዮጵያ፡ ሰወች ያነን፡ ታሪክ፡ ደስ፡ አያላቸው፡ ያነቡታል። ያም: የዛሬ አርባ፡ ዓመት፡ የታተመ፡ የመጽሓፍ፡ ቅዱስ፡ ታሪክ፡ አልቋዋልና፥። አንደ፡ ገና፡ አርመን፡ አሳተምነው። ያ፡ የቀድመው፡ ታሪክ፡ በአያሌ፡ የአማርኛው፡ ሳይቀና፡ ቀርተ፡ የፈረንጆች፡ አገር፡ ይመስል፡ ነበረ፥ ዛሬ፡ ግን፡ እንደ፡ ሕዝብ፡ አነጋገር፡ አድርገን፡ እንደ፡ ቅማችን አቃንተን፡ አረምነው። በዚህ፡ ስራ፡ የረዱኝ፡ መምህር፡ ዮሐንስ ወልደ፡ ማርያም፡ አቶ፡ ገብረ፡ ክርስቶስ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ናቸው፡፡
ከዚህ፡ በኋላ፡ አለቃ፡ ተየ፡ የብሉይን፡ ታሪክ፡ አባ፡ ዘጊዮርጊስም፡ አዲስ፡ ኪደንን፡ ታሪክ፡ አረሙት፡፡
ደህም፡ መጽሓፍ፡ የሰማይን፡ መንገድ፡ የሚመራን፡ የአምላክንም ምሕረት: የ ሚገልጽልን፡ነውና፥ እንደ፡ መልካም፡ ወዳጀችን፡ አድርገን፡ ደስ፡ አያለን፡ አንቀበለው፡፡
አዲስ አበባ ሕዳር ፲፱፻፳።
አምስት ቅጅዎች እጃችን ላይ ይገኛሉ። ቀድመው ይሸምቱ !!!n
1 "የምጽዋ በር የአባቶቼ የነገሥታት ኢትዮጵያን ነው፡፡ እንበለ ዘር ቤተ መንግሥት አይቀናምና በእርስዎ ወኪልነትና እርዳታ የምጽዋን በር እንድይዝ ያድርጉልኝ ብዬ እለምናለሁ፡፡
አፄ ዮሐንስ 4ኛ ለንግሥት ቪክቶርያ ከጻፉት ዳብዳቤ።
2. የዘይላን በር ነገር በሚቻልዎ ነገር ሁሉ ተባጥረው በእኔ አጅ ቢሆን እንኳን በሐረርጌና፣ በአፉ ያ በከንባታ፣በጅማ፤ በከፋ ያለን ንግድ ሁሉ በዘይላ አደርገው ነበር፡፡ ስለዚህ ጠንቅቀው ቢያስለቅቁኝ እወዳለሁ፡፡ ይህም ማለቴ ለእርስዎ እንዳይቸግርዎ ባውቀው የኢትዮጵያ ልጆች በንጉሥ ኡምቤርቶ ብር ት የዘይላ በር እጃችን ተመልሶ ገባ እንዲሉ ስምዎ በነገሥታት ታሪካችን ይተከላል፡፡
ዳግማዊ አፄ ምኒልከ ለንጉሥ ኡምቤርቶ እ.ኤ.አ በ376 ዓ.ም ከጻፉት ደብዳቤ ታደለ ገድሌ ጸጋየ እንደ ዘገበው
3. ለብዙ ዓመታት የሁለቱን ወንድማማች ሕዝቦች ለያይቶ የኖረውን የመከራ ምዕራፍ በሩውን እንዘጋለን
በቀዳማዊ አጼ ኃሥላሴ ንግግር ዘውዴ ረታ(አምባሳደር) የኤርትረ ጉዳይ እ.አ.አ 1941-1963፤ 1990 ዓ.ም አዲስ አበባ
4. በዚህ በቀይ ባህር ወደብ እና ጠረፍ ላይ ሆነን ካሌን ጥንታዊ የባህር ኃይላችንና የንግድ መርከቦን በቀይ ባህር የነበረን ገናናነት አዱሊስን እና መጠራን፤ ዳህላከን፣ እና ናኩራን በአጠቃላይ የታሪክ ኩራታችንን አሉላን ጭምር እንመለከታለን ቀይ ባህርና የባህር በሮቻችን የታሪካችን ልዩ አሻራዎች ናቸው፡፡
ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አዲስ ዘመን ጥር 22 ቀን 1969 ዓ.ም
5 እነዚህ ስህተቶች ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረግ/ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲዊ ህጋ መንግስት ሳይቋቋም የሽግግር ወቅት የኤርትራ ሪፈረንደም እንዲካሄድ ማመቻቸት ነበር፡፡ ኤርትራ ነፃነቱ ን ስታውጅ ኢትዮጵያ የአሰብን ጉዳይ ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮችም የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት፣ ጥቅምና መብቶች የሚያስካብር አግባብነት ያለው ስምምነት እንዲፈረም ያለማድረግ ነው፡፡
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዘዳንት)
6. “ይህ አሰብን እንይዛለን እንወርራለን የሚል አካሄድ ከዚያው ከዘውዳዊ ትምክህታዊ አስተሳሰ በ የሚመነጭ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ይህ አስተሳሰብ የተጠናወታችው ስዎች ከዘመነ ግሎባላይዜሽን ር አብረው ሊሄዱ ያልቻሉ ከድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ያልተላቀቁ ናቸው፡፡ አሰብን ካልያዝን እያየ ይፎክራሉ ፤ተግባራዊ በማድርግ በአሰብ ላይ ወረራ እስካልተፈጸመ ድረስ እርምጃ ልንወስድባች አንችልም"
አቶ መለስ ዜናዊ ከእስማሪኖ ድረ ገጽ ባለቤት ከአቶ ተሰፋ ልደት መሃረነ ጋር አቶ መለስ ዜናዊ ያደረጉት ቃል ምልጃ ስ 2010 ዓ.ም.
ጠመንጃ አንግቦ ጫካ ከገባ በኋላ ወደ ከተማ ያልተመለሰ የእኔ
ቢጤ ጨዋ፣ የኤርትራ በረሃዎች ለኤርትራ ነፃ አውጭዎች ብቻ
የተፈቀዱና የተለቀቁ ይመስሉታል፡፡ ሌላውን እውነታ የሚያሳይ
ትርክት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ተካቶ ቀርቧል፡፡ የዚህ መጽሐፍ
ዋና ገፀ-ባሕርይ በልብወለድ ወይም በምንባብ የተፈጠረ ሰው
አይደለም። ተወልዶ ያደገው ግሼ-ዐባይ መንደር ነው። ፍኖተ-
ሰላምንና ደብረ-ማርቆስን በትምህርት ቤት በኩል አልፎ፣
የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲን ከሦስተኛ ዓመት ላይ
አቋርጦ፣ በሶማሌ እስር ቤት ማቋል። በሳህል በረሃ ከኢሳያስ
አፈወርቂ (ከአሁኑ የኤርትራ ፕሬዚዳንት) ጎን ተሰልፎ ተዋግቷል፡፡
ከኤርትራ በረሃ ወጥቶ አሲምባ ገብቶ በአዲስ መንፈስ የኢትዮጵያን ሕዝብ መብት አስከብራለሁ' ብሎ ጠመንጃ አንግቦ ታግሏል፡፡ የፍልሚያውን የመጀመሪያ ምዕራፍና የሕይወት ታሪኩን በበሳል ብዕር ሰንዶ፣ በአገርኛ ቃላት አስውቦ፣ በአካባቢው ይትባህል አጅቦ ለንባብ አብቅቶልናል፡፡ የመሀል አገሩ ሰው ከኤርትራ ነፃ አውጭ ድርጅት ጎን ቆሞ መፋለሙ ለእኔ አዲስ ዜና ቢመስልም፣ ድርጊቱ በተጨባጭ ተፈጽሟል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ፣ የዓቢዩ ብርሌን “በሀገር ፍቅር ጉዞ"
ታሪካዊ መጽሐፍ ነው በጥሞና አንብቡት፡፡
የቅዱስ ቁርኣን ማብራሪያ መጽሐፍት በእንግሊዝኛና በአረብኛ ቋንቋ ብርታት ቅጽ እጃችን ላይ ይገኛል !!!
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
ጥቂት ማብራሪያ ስለ ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ጉዞ ፪ መጽሐፍ
1. ከትንሿ ቤተ ክርስቲያን የቀጠለ መጽሐፍ አይደለም፤ ቢያንስ በጥር የሚጋቡ ዕጮኛሞች እንዳያመልጡኝ በሚል ቀደመ እንጂ ቁጥር ፩ ማንን ላግባ ለሚሉ የተዘጋጀና በዚህ ዓመት የሚወጣ ነው። ለባለትዳሮች የተዘጋጀ ቁጥር 3ም አለው።
2. ለዕጮኛሞች የተዘጋጀ ቢኾንም ከተነሡት ከ6ቱ ርእሰ ጉዳዮች ውስጥ 5ቱ ከዚህ በፊት ላገቡም ጭምር በደንብ የሚጠቅም ነው።
3. ትንሿን ቤተ ክርስቲያን ያነበበ ሰውም እነዚህን መጻሕፍት ማንበብ አለበት። ለምን ሲባል፥ አንደኛ የትዳር ጉዞ በሚል እየወጡ ያሉት በሌላ እይታ የተጻፉ ናቸው። ኹለተኛውና ዋናው ደግሞ ማሠልጠኛ ማኗሎች ናቸው። ማኗሎች ቢኾኑም በተቻለ መጠን የሚነበቡም ናቸው።
4. የትዳር ጉዞ ተከታታይ መጻሕፍት ማሠልጠኛ ማኗሎች እንደ መኾናቸው አጋዥ መምህር ይፈልጋሉ። ለምሳሌ መምህረ ንስሓ! በተጨማሪም ጥንዶች ይኹነኝ ብለው የሚወያዩባቸው፣ የሚተዋወቁባቸውና በዚሁ መሠረት የሚገናዘቡባቸው ናቸው።
ደራሲው ገብረ እግዚአብሔር ኪዲ እንደከተበው።
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
09 20 74 57 40
@Mesay21
በቅዱስ ያሬድ ላይ ትኩረት ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ጥቂት ቀናቶች ነው የቀሩት።
“ስምከ ሕያው ቅዱስ ያሬድ” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 11/ 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ፡፡
በብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ፣ የየምና የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፍቃድና ቡራኬ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ህንጻ አሠሪ ኮሚቴ እና በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት የሚካሄድ ይሆናል።
የቻለ ሁሉ የማይቀርበት ልዩ ጉባኤ!
ኑ! አንድ ሁነን ቅዱስ ያሬድን ዘክረን ከበረከቱ እንካፈል!
በዕለቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት፣ መምህራነ ወንጌል፣መዘምራንና ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ።
መግቢያ ዋጋ 100 ብር!
ትኬቱ በኤዞፕ መጽሐፍት መደብር ይገኛል።
ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000560510091
አቢሲኒያ ባንክ
145735858
አባይ ባንክ
146-101-9959527-013(9959527)
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
የፃድቃን ሠማዕታትን ታሪክና ተጋድሎን የያዘ !!!
በጣልያንኛና በእንግሊዝኛ የቀረበ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ !!!
//t.me/azop78
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት ጥንታዊ ጥበቦች መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ ጥበብ
አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት መገኛችን ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
Our laws must be divorced from society. While they must aim at safeguard- ing the freedom. the happiness and the prosperity of the individual citizen, they must not lose sight of the interests of society as a whole.
KWAME NKRUMAH
Who are the components of 'the whole'? If you destroy all the individuals by taking away their rights, for whom do you keep the 'interests of society as a whole'? The idea that society is an end in itself must have caused the French King to ask: 'The State? Who is the State? I am the State!'
J. B. DANQUAH
ሞት ማለት፡-
ሞት አለመስጋት ነው የግዴለሽ ዓለም፤
ድንጋይ ተሸክሞ በውሀ ላይ መቆም፤
ጤንነት የለበት፤ አያጠቃው ሕመም
ትዝታ የለበት፤ አይታይበት ሕልም፤
ቡቃያው አያሽት፣ ፍሬው አይለመልም ፡
ዝናብ አይዘንብበት ድርቀት ነው ዘላለም፡፡
ማንም አይጎዳ ማንም አይጠቀም፡፡
ሞት ማለት፡- የሞት ሞት -
አእምሮ ፈራርሶ
ኅሊና በስብሶ፤
ሰውነት ረክሶ፤
አንደግም፤ እንደጥንብ፤
የጭልፊቶቹ ምግብ፤
የሞት ሞት ይኸ ነው፤
ትንሣኤ የሌለው፡፡
መስፍን ወልደ ማሪያም መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ የተወሰደ !!!
መልካም ንባብ!!
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገር አፈታሪክ
ከዕለታት አንድ ቀን ሴት አንበሳ ፡ ነብር እና ውድንቢ የሠሩትን ኃጢአት እየተናዘዙ ረጅም መንገድ በአንድነት ለመጓዝ ተስማሙ።
ሴቷ አንበሳ « የጫካው ንግሥት ስለሆንኩ በቅድሚያ እኔ እናዘዛለሁ» አለች። ቀጥላም « አንድ ቀን አንድ ትልቅ ድፋርሳ አጣጥሜ በልቼ እንደጨረስኩ የሜዳ አህያ ብቅ አለ። ወፍራምና የሚያስጐመጅ ስለነበር ዘልዬ አነቅሁትና ገደልኩት። ግን ሆዴ በጣም ሞልቶ ስለነበር ልበላው እንደማልችል ተረዳሁ። ካለምንም ዓላማ ይህን የጫካ አውሬ ገድያለሁ።»
ነብርም ተቻኩሉ « አንች የጫካው ንግሥት፣ ለምን ብለሽ ትጨነቂ ያለሽ ? ከሁላችንም የላቅሽበትን ሥራ ነው የፈጸምሽው። ስለዚህም ይቅር ብለንሻል » አላት። «ነብርስ ስለምንድነው የምትናዘዘው ? » ብላ ጠየቀች አንበሳ።
«ይኸውላችሁ፣ አንድ ቀን ሁለት ግልገሎቿን አስከትላ የምትሄድ በግ አየሁ። ስለራበኝ አንዷን ግልገል ወዲያውኑ ቁርጥምጥም አድርጌ ዋጥ ኳት።እናቲቱ እየሮጠች ወደኔ መጥታ አያ ነበር፣ ከፈለግህ እኔን ብላኝ፣ የተረፈችውን ግልገሌን እንኳን ማርልኝ ብላ እያለቀሰች ተማጸነችኝ። እኔም እሺ ፣ እምርልሻለሁ ካልኳት በኋላ እሷንና ግልገሏን ስለቀጥኋቸው» አለ። አንበሳም « እኔም እናት ስለሆንኩ ያደረግኸውን አልደግፍም፤ ግን ውብ፣ ፈጣንና ኃይለኛ ስለሆንክ ልጨክንብህ አልችልም። ስለዚህም ተምረሃል » አለችው።
«ውድንቢ እስካሁን አልተነፈስክም፣ አንተስ ምን የምትናዘዘው አለህ?» በማለት አንበሳ ጠየቀች። «ክብርት አንበሳ ፣ ለጊዜው የምናዘዝበት ነገር ትዝ አላለኝም » አለ
ውድንቢ።
«ሁላችንም ሟቾች ነን፣ ኅሊናህ ውስጥ አንድ ነገር መኖር አለበት » አለች።
ውድንቢ ጥቂት አሰበና « አንድ ቀን ከጧት አንስቶ በምድረ በዳ ስሄድ ወዬ በጣም ርቦኝ ስለነበር ጥቂት ሳር አይቼ በልቻለሁ» አለ። በዚህ ጊዜ አንበሳና ነብር በኅብረት « ይቅር የማይባል ጥፋት ስለፈጸምክ መኖር አይገባህም » ብለው ውድንቢን ቀረጣጥፈው በሉት።
ካነነብኩት
ጥርስ የገባች ሀገር ገጽ 10 ላይ የተወሰደ !!