azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቆየት ያለ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በብዙዎቻችኹ ጥያቄ መሰረት የአማርኛውን ቨርዥን ትንሽ ኮፒዎች አግኝተናል !!!


ሞርደኻይ አቢር (1927-2014 ዓ.ም.)

በ1927 ዓ.ም. በእስራኤል፣ ኢየሩሳሌም የተወለደው የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ሞርደኻይ አቢር በሐምሌ 2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ከ1963-1967 ዓ.ም. በቀድሞው ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (የአሁኑ አዲስ አበባ) ዩኒቨርሲቲ የአርትስ ፋኩልቲ ተባባሪ ዲን ሆኖ ያገለገለው አቢር፣ በሂብርው ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛው ምሥራቅና እስላማዊ ጥናቶች ፕሮፌሰር ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የኢየሩሳሌም ማኅበረሰብ አቀፍ ጉዳዮች ማእከል አንጋፋ አባል ነበር። በመካከለኛው ምሥራቅ፣ ቀይ ባሕርና ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ፖለቲካ… ወዘተ. ዙሪያ በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን ያቀረበው አቢር፣ የቀጣዮቹ መጻሕፍት ደራሲ ነበር:

1. Saudi Arabia: Society, Government and the Gulf Crisis

2. Saudi Arabia in the Oil Era: Regime and Elites: Conflict and Collaboration

3. Ethiopia: The Era of the Princes: The Challenge of |slam and the Re-Unification of the Christian Empire

4. Ethiopia and the Red Sea: The Rise and Decline of the Solomonic Dynasty and Muslim - European Rivalry in the Region

5. Oil, Power & Politics: Conflict in Arabia the Red Sea and the Gulf

6. In the Direction of the Gulf: The Soviet Union and the Persian Gulf

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ቢትወደድ ዘውዴ ገብረ ሕይወት በ፲፱፻፬ ዓ.ም ነሐሴ ፭ ቀን በሽዋ ጠቅላይ ግዛት፣ በመናገሻ አውራጃ ሆለታ ከተማ ተወለዱ፡፡

በአምስት ዓመት ዕድሜያቸው ወደ አዲስ አበባ መጥተው በየደረጃው፣ በቤተ ክርስቲያን ይሰጥ የነበረውን የአማርኛና የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት፤ አከታትለውም በአሊያንስ ፍራንሴዝ እና በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤቶች በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች በዘመኑ የተመደበውን ትምህርት አጠናቀዋል።

የባለአገርነት እንቅስቃሴ የጀመሩት ከፋሽስት ኢጣልያ ወረራ አስቀድሞ ከጓደኞቻቸው ጋራ የኢትዮጵያ ወጣቶች የፍቅርና የአንድነት ማኅበር የተባለውን በመመሥረት ነበር፡፡ ይህም የአገር ፍቅር ማኅበሮ” ተብሎ እንደገና የተደራጀው ነው:: በዚያን ጊዜ የአርበኞች ትግልና ዕድል : በሚል ሥያሜ ተቋቁሞ ቀጥሎ የጀግኖች አርበኞች ማኅበር የተባለውም ከዚሁ የፍቅርና የአንድነት መንፈስ የተወለደ ነው፡፡

ቢትወደድ ሀውዴ ወደ ሥራ ዓለም የተሰማሩት በ፲፱፻፳፫ ዓ.ም በአዲስ አበባ ጉምሩክ በሂሳብ ሠራተኝነት ሲሆን፥ ከአንድ ዓመት በኋላ ለዘመናዊ አስተዳደር ምሳሌነት ወደ ተመረጠው ጨርጨር አውራጃ ተዛውረው ከስመ ጥሩው ገዥ ከአዛዥ ወርቅነህ እሽቴ ጋር የሥራና የሕዝብ መገናኛ ምክትል ሹም በመሆን ልዩ አገልግሎት ፈጽመዋል።

ቀጥሎም በጅጅጋ መምህር ሆነው ሲያገለግሉ በኢጣልያ ወረራ ምክንያት ትምህርት በመቋረጡ የገደቡርሲ ተጠባባቂ አስተዳዳሪና የጠረፍ ጥበቃ ሠራዊት የሻምበል ጦር አዛዥ ሆነው በግንባሩ በተከፈተው ጦርነት ቢሠለፉም ጠላት አይሎ ጦሩ ሲበተን በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ወደ እንግሊዝ ሶማሊላንድ ለመሰደድ ተገደዋል።

በስደት ዘመናት የወገኖቻቸው ኑሮ የተመቻቸ እንዲሆንና በተለይ ልጁ፥ ወጣቱና ጎልማሳው በዘመናዊ ትምህርት እንዲታነፅ ያከናወኑት ተግባር ብልኅነታቸውንና አርቆ አሳቢነታቸውን ያስረዳል። ከዚያም በ ፲ ፱፻፴፫ ዓ.ም ወደ ኬንያ ዘልቀው ከእንግሊዝ ጦር ጋራ በመሆን በሲዳሞ ግንባር ኢትዮጵያን ነፃ ማውጣት በተደረገው ጦርነት በ፫ኛ ሻምበል ጦር አዛዥነት ጠላትን ተፋልመው በድል አድራጊነት ተመልሰዋል።

ከነፃነት በኋላ በተለያዩ አገሮችና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርና ቋሚ መልእክተኛ በመሆን በአገር ውስጥም በከፍተኛ የአስተዳደርና የአመራር ደረጃዎች በተመሰከረለት ብቃት አገልግለዋል፡፡ ካከናወኗቸውም አያሌ ተግባራት መሐከል፥ አዲስ አበባ ዘመናዊ ርዕሰ ከተማ እንድትሆንና በአገር አስተዳደር ቀና ለውጥ ለማምጣት ያደረጉት ጥረት ጉልህ ሆኖ ይታወሳል፡

የባለአገርነት ተግባራቸውንም በመቀጠል፥ ከደርግ ሥርዓት እስርና እንግልት በኋላ፡ በአሜሪካን አገር በቆዩባቸው የዳግም ስደት ዘመናት ለአገርና ለወገን የቆሙ ኢትዮጵያውያን በኅብረት በአንድነትና በፍቅር ለአገራቸው በጎውን ሁሉ እንዲሠሩ ሲያደራጁ፥ ሲያስተባብሩና ሲመክሩ ቆይተዋል።

በሽምግልና ዘመናቸውም ይኸው የባለአገርነት መንፈስ ይበልጥ እንዲጎለብት ኢትዮጵያዊነት የተሰኘውን ማኅበር መሥርተው መርተዋል። እንዲሁም የኦርቶዶክስ ምዕመናን ማኅበርን በሰብሳቢነት፡ የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ድርጅትን መልሶ በማቋቋምና በመምራት ረገድ የሳተ ምሳሌነትን የተላበሱ አገልግሎቶችን አቅርበዋል።

በተወለዱ በዘጠና ዓመታቸው የካቲት ፮ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም በሞት የተለዩት ቢትወደድ ዘውዲ ለትውልድ ቅርስ የሚሆነውን ይህን የአገልግሎት ታሪካቸውን ትውስታ ትተው አልፈዋል።

                      የካቲት ፲፱፻ገራዔም

azop book
November 21, 2023 1:08 PM

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከጋሽ ማሞ ውድ ነህ ድንቅ ስራዎች መካከል የቱን አንብበዋል ???

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መጽሐፉ አጭር፣ ጠንካራ ሀሳብ የያዘ፣ ሀይለኛ እና ቀጥተኛ ነው። መጽሐፉ የያዘው ሀሳብ ብዙውን ጊዜ በገንዘብ ማበረታቻዎች የሚገኘው ውጫዊ ተነሳሽነት ከውስጥ ከሚመነጨው ፍላጎት ከውስጣዊ ተነሳሽነት የበለጠ ውጤታማ ነው የሚለውን ሀሳብ የሚጻረር ነው።


መጽሐፍ ለመጠየቅ @Mesay21 ይጠቀሙ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የሮበርት ኪዮሳኪ መጽሐፍቶች ትንሽ ኮፒዎች አሉን !!!

ዋጋ ለመጠየቅ @Mesay21 ይጠቀሙ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

from autobiography

People of my generation have lived through the most interesting times in the modern history of Ethiopia, and. I dare say, of the world times when leaders like Hitler Stalin. Mussolini. Churchill, Roosevelt and Haile- Selassie were dramatic actors on the international scene. This pre- cious experience can never be duplicated by our juniors. I consider myself very fortunate, indeed, that I have lived through these most fas cinating times when the world was tottering precariously on the brink of a cataclysmic disastor Politically, socially and economically also, at home Ethiopia was just beginning to emerge from darkness to light in 1941.

Ethiopians of my generation were being indoctrinated right from child- hood to respect authority in such a way that the tradition of doing so was verging on some form of divine worship. It mattered little or noth- ing whether the authority being rigorously imposed from above was spiritual, temporal or parental in nature. The dictum that God proposes and man disposes also held true in relationships among members of society depending upon the status of the individual concerned. In a family, the authority of parents especially of the father was unques- tionable and, in society as a whole, that of elders was not open to debate by those who were their juniors. The same thing can be said about those who are exercising authority over others by virtue of an. apparently, divine right to do so.

The Ethiopian political malaise was that the government was being manipulated by the landed gentry. As soon as the educated classes had joined the government, they were encouraged to own land and to build themselves villas by offering them plenty of money on loans from the treasury which would be later cancelled. Of course, in this system- atic method of corrupting the intelligentsia, military officers were en- joying special privileges not even granted to high-ranking civilian offi- cials. It was not. therefore, only Ras Mesfin Sileshi who was reputedly owning most of the land in the country. In the late 1960s, in particular with every Ethiopian official entitled to own 40 hectares of land at the expense of the peasantry many more little Ras Mesfins, who were conspicuously residing in the Bolo quarters of Addis Ababa. were be- ginning to emerge in Ethiopia as its future potential feudal lords.

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ኮፒ ብቻ እጃችን ላይ ይገኛል

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዘጋጅ ፀሀይ መላኩ

አሳታሚ ማህበረ ቅዱሳን !!!

የደራሲዋ ቀደምት ሥራዎች

1ኛ ቋሳ
2ኛ አንጉዝ
3ኛ. ቢስ ራሔል
4ኛ. እመምኔት
5ኛ. የስሜት ትኩሳት ቁጥር 1 2002 ዓ.ም

6ኛ, የስሜት ትኩሳት ቁጥር 2 2002

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ኮፒ እጃችን ላይ ይገኛል !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ ከውድ ወዳጃችን ዘርዓ ጽዮንና ለደራሲው ያዕቆብ ብርሃኑ ጋር ስለ አዲሷ የያዕቆብ ብርሃኑ መጽሐፍ በደንብ አወጋን ተጨዋወትንም።

ስለ መጽሐፏ ብስለትም እንዲኹ !!!!


አንብቧትማ
የምትደሰቱባት መጽሐፍ ነች!!!

በፍም እሳት መቃመስ ያዕቆብ ብርሃኑ !!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

The African Prester John and the Birth of Ethiopian-European Relations, 1402-1555

From the 14th century onward, political and religious motives led Ethiopian trave- lers to Mediterranean Europe. For two centuries, their ancient Christian heritage and the myth of a fabled eastern king named Prester John allowed Ethiopians to the continent's secular and religious elites as peers. Meanwhile in Ethiopia, the nobility came to welcome European visitors and at times even co-opted them by arranging mixed marriages and bestowing land rights. The protagonists of this encounter sought and discovered each other in royal palaces, monasteries, and markets throughout the Mediterranean basin, the Red Sea, and the Indian Ocean littoral, from Lisbon to Jerusalem and from Venice to Goa. Matteo Salvadore's narrative takes readers on a voyage of reciprocal discovery that climaxed with the Portuguese intervention on the side of the Christian monarchy in the Ethiopian- Adali War. Thereafter, the arrival of the Jesuits in the Horn of Africa turned the mutually beneficial Ethiopian-European encounter into a bitter confrontation over the souls of Ethiopian Christians.

Matteo Salvadore is Assistant Professor of History at American University of Sharjah, United Arab Emirates.

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ስለ ምስልን ፍለጋ መጽሐፍ የተሰጡ አስተያየቶች


በትናንት ትዝታዬ እና በነገ ምናቤ መሀል ሆኔ የተኖሩ ቀናቶችን ከንሀዱ ዓለም ከተቀዱ የልብወለድ ገፀ ባህሪዎች ጋር አዋህጄ ይኽን መፅሐፍ ለእናንተ ለአንባቢያን አበርክቻስሁ።

ሐና ኃይሎ የግላዊ እና ሞየዊ አደንት አሰልጣኝ | ፀሀፊ | የለበሪ ማይንድስ መስራች አና ስራ አስኪያጅ

ደስ እየለኝ እንብቤዋለሁ። ይህን ክፊል ግለታሪክ የተካተተበትን መጽሐፍ ጠቃሚና ጽኑ ዓላማ ያላቸው ታታሪዎች ሁሉ በየነበት ተጨማሪ ቁምነገሮችን ያገኛሉ። በኀ እሰተሳሰብ ጠቃሚ ዕወቁት፣ ብልኅነት ጥበብ የድል አድራጊነት መሠረት... መሆናቸውንም ይበልጥ ይንነዘባሉ...


ኃይለመስከኮት መዋዕል (መምህርና ደራሲ)

በአንዲት ስጋ ወጣት የተከተበውንና የስሰሰት አንደምንጭ ውሀ ከብዕሯ የፈስቀውን ሙሉ ወጥ ሥራ እንብቤ፣ ትጋቷና በድፍረ± ጭምር +ደምኸ፡ በአጭር እድሜዋ ይህን ያህል የሕይወት ውጣ ውረደ በጽናት ተቋቁማ ዛሬ ሰስደረሰችበት ከፍታ በማሰብ ተገረምኩ። ጸሐፊዋ ከተለመደው የሥነ-ጽሑፍ ዘውግ ወጣ ብላ፣ የራሷን የአጻጻፍ ስልት ይዛ ብቅ አንዳለችም ተገነዘብክበት።


ውደ. አላት ገዳሙ (ደራሲ እና የሥነ-ጽሑፍ አርታዒ )

የሰው ልጅ ሁለንተናዋና ምሉዕ ስኬት የሚገኘው በዚህች ምድር ውሱን ጉዞው በአግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረበትን ዓላማ ፈልጎ ሲያገኝ ነው...ጸሐፊዋ “ምስሌን ፍለጋ'' በተሰነው ውብ ሥራዋ ይህንን ጉዞዋን በመሳጭና ተነባቢ ትረካዋ ታስቀናለች።

ማሙሻ ፈንታ (ዶ/ር)

"ምስሴን ፍለጋ " በሚል ርዕስ ፡ በወ/ት ሃና ነይስ የተፃፈው መፅሀፍ በትንሽ አደዋ በርካታ ሰሞዶች የቀሰመችበትን ቁምነገሮችን እና ትልቅ መልእክት የዘለ ነው።


አምባሳደር ሙሉ ስሎሞን (ባለቅኔ ገጣሚና የቀድሞ የኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ማህበር ፕሬዘዳንት)

ይህ መጽሐፍ ለምን እንደተፈጠርነ፣ በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ምን መሥራት አንዳለብን አንዲሁም ስትውልድ አንዴት አሻራ እሰቀምጠን መሄድ እንዳለብን የሚያስታውስ መጽሐፍ ነው።ወጣቶችም የውስጣቸውን ጨከቶ እንዲያዳምጠና የውስጥ ጨክታቸውን እንዲኖሩ ይረዳቸዋል።

ምሕረቱ ሻንቆ ግዱ ( የተዘነጋው ሀብት መጽሐፍ ደራሲ)

ራዕይ፣ ዓላማ፣ ፍቅር፣ ይቅርታ፣ ትዳር፣ ወጣትነት እና ፈተና… በምስሌን ፍለጋ ያልተነስ ርእሶች የልተጻሰሱ ጉዳዮች የሉም። ትንሹ መጽሐፍ ትልቅ መልአክትን የሚነካ የሚዳስስ እና የሚታይ ምስልን ይዟል። ከገቡ የማይወጡበት የታሪክ ውበት እና ልብ ወለዳዊ ብቃት ታይቷል...

ፌቨን ጋሻው (የንጉስ ሴት ልጅ)

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

Since 1961 when I began teaching Ancient and Medieval Ethiopian History at the old University College of Addis Ababa, I have been interested in writing a book on the same subject. As the sources were scattered in different places, I realized that the task was not an easy one. Fortunately the Haile Sellassic I University provided me with all facilities so that I was able to visit various places and collect material. For the same purpose, I was released from my teaching assignments for one semester in 1963 and spent the time on re- search in Northern Ethiopia. The financial and moral support of my University encouraged me to take the matter more seriously and in 1965 I produced the first draft. Hereafter, I continued to work on this manuscript, improving the text and adding more material until 1967.

Another occasion was offered to me to concentrate on this work. In the 1967-68 aca- demic year, I was granted sabbatical leave and the British Council agreed to pay my air fare to London. There I had a chance to consult many printed works and manuscripts in the British Museum. Meanwhile through the energetic efforts of Dr. Abebe Ambatchew, then Secretary General of Ethiopian National Commission for UNESCO, I received a fel- lowship of six months from UNESCO and this helped me to work under better conditions. I am deeply obliged to the above Institutions and to Dr. Abebe Ambatchew.

At the same time I recall with great pleasure the hospitality and encouragement I received from Dr. Eguale Gebre Yohannes, then Councellor at the Imperial Ethiopian Embassy in Bonn and now Head of Cultural Affairs in the Ministry of Foreign Affairs. He did all he could to assist in the success of my work. He deserves many many thanks for his generosity, constructive criticism and wise advice.

Many other friends and colleagues also helped me in one way or another. Particular mention is due to Dr. Abraham Demoz, Ex-Dean of Arts at Haile Sellassic I University, and Dr. Merid Welde Aregay, Assistant Professor of History in the same institution. The former sought to establish a fellowship during the period of my sabbatical leave and the latter lent me his best advice which I found very useful.

Editing and typing the work involved many people. W/ro Belaynesh Mikael of the Haile Sellassie I University Press helped me in editing part of the manuscript. Mrs. M. White, from Britain edited the second half and typed it. My wife Selamawit and W/ro Mulu Alem Mengistu volunteered to type the draft. I thank all of them very much indeed.

Sergew Hable Sellassie

Department of History

Haile Sellassie I University

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

እሳት ግን ለሰው ልጅ ሁለመናው ነው፡፡ መንፈሱን፣ ምናቡን፣ ጥበቡን፣ ሁለንተናውን የሚዳስስ፣ የሚያሻግር ሁነት... የሰው ልጅ አሳትን ካላመደ በኋላ በቁጥር የማይለኩ ዘመናት አለፉ፡፡ ዋሻውን ድንኳን፣ ደመነፍሱን ወንጌል ተካው፡፡ አንዳንዶች በምድጃው ብቻ ተወሰኑ፡፡ ዘላኖች ተባሉ፡፡ ሌሎች ከምድጃው ጎን መሰዊያም ነበራቸው፡፡ እኛን ይመስላሉ፡፡ እንደገና ሌሎች መሰዊያውን በማቅለጫው ቀየሩ፡፡ የኤሮፓ ሰዎች ይባላሉ፡፡

እሳቱ ግን ሰዎች ሳያገኙት በፊትም ነበረ!
ይኖራልም!
ያለ እና የነበር ነውና!
የሚገሩትን ሊያሻግር!
የሚሰግሩትን ሊያሳርር!

መልካም ንባብ!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

These six stories-here presented in memorable new translations-represent Chekhov's narrative ge- nius at the full range and power of its maturity. As masterfully constructed as his earlier stories, but with far greater richness and dimension, they deal with human beings suffering the pain of existence, their lives illumined by the author's rigorous objectivity. The novella Ward Six, with its hauntingly symbolic depiction of the world of an insane asylum; The Duel, with its theme of moral degradation, its hint of regen- eration; and A Dull Story, with its relentless depiction of a culture that corrupts and alienates...these and others present a vivid portrait of what Rufus W Mathewson calls a "blighted" society, seen through the eyes of a writer whose understanding of "human foolishness" is without equal. In his incisive After- word Mr. Mathewson discards the accepted stereo- types, reappraising Chekhov's personality and work. He points out that Chekhov demands much of his read- ers, but gives much in return: "The reader is chal- lenged to collaborate in the experience of the story, to interpret it in the way an actor interprets the text of a play, or a musician a score. A good 'performance' by the reader will yield a very great reward."

azop book

A New Translation by Ann Dunnigan Afterword by Rufus W. Mathewson

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከዚህ በፊት እንዲህ ዓይነት መውደድ አውቅ ነበርን? በፍጹም! በቃ ከዚህ ሰው ጋር መወዳጀት እሳተ ገሞራን እንደ መጎራበት፣ ኃይለኛ ወጀብን እንደመግራት ያለ አደገኛ ጀብድ አለበት፡፡ ግን ደግሞ ጨረቃን ዘና ብሎ የመጎብኘት ያህልም አስደሳች…

ይህ ሰው እንደሌሎቹ ጀልጋጋ ተረት እየተረከ እወድሻለሁን ቢያላዝንብኝ ኖሮ ምናልባት ለማየትስ ስንኳ ያስጠላኝ ይሆናል፡፡ I like it a little bit stupid, rush, unpredictable and strange... ሞዛዛ ነገር አይስበኝም፡፡ ቆፍጣና ወንድ ደስ ይለኛል፡፡ ኃይለኝነቱ የተገራ እስከሆነ ድረስ በጥባጭ ቢሆንስ ስንኳ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ዓለምን በዙሪያው ያለውን ነገር ኹሉ የናቀ በመጠኑ ኩሩ ለእያንዳንዱ ብርቅርቅ የሕይወት ውልብታ የማይሽቆጠቆጥ ወንድ ከሆነ ዋው እሱ የልቤ ሰው ነው... ‹የእኔይቱ የሜቲኮ›...
እንዲያም ሆኖ እኔ ባልሆን ኖሮ ማንኛዋም ሴት የዚህን ሰው የበዛ ቁምነገረኝነትና ቀጥተኝነቱን ለማስተናገድ የማትቸገር ይመስለኛል፡፡
ለነገሩስ ሁሊቷም ሴት በአዕምሮዋ የምትስለው የሆነ የምናብ ወንድ አላት አይደል? የሆነ ወንድ... ምናልባት ደረቱ ላይ ጸጉር ያለው... እንደ አዳኝ ወይ እንደ ጃዊሳ ቤቱ ጋራ ስር ሰርቶ ለብቻው የሚኖር... ምናልባት አስራ ስድስቱን ብቻውን የሚያባርር የሚነዳ... ወይ ዓልማው የማታውቀውን ጀብደኛ ሕይወት የሚያሳያት... ምናልባት ጥንቁቅና ንጹህ... አዎ ማንኛዋም ሴት የሆነ የምናብ ወንድ አላት፡፡ መቼውኑም ባታገኘውም ቅሉ... የእኔስ? የእኔማ ግልጽ ነው፡፡ ሁለት ነገር ብቻ... የሚያማምሩ ጣቶችና የሚያነሆልለኝ ድምጽ...


ከመጽሐፉ የተወሰደ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች መጽሐፍ፣ ሰዎች በፍቅር ግንኙታቸው ውስጥ ፍቅርን የሚቀበሉባቸውና ፍቅራቸውን የሚገልጹባቸውን መንገዶችን ይገልጻል።  የአጋርሽን የፍቅር ቋንቋ ማወቅ እና ያንቺንም ማሳወቅ፣ ሁለታችሁም እንደተወደዳችሁ እና ለጥረታችሁም የተደነቃችሁ ሆኖ እንዲሰማችሁ የሚረዳችሁ መንገድ ነው።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ምንጊዜም ቀይባህር ሲነሳ የማይረሳ መጽሐፍ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

A GROUNDBREAKING MANIFESTO ON THE MEANING OF LIFE

Make sure you're not missing the point of your life-read this book! The Purpose-Driven Life will guide you to greatness through living the Great Commandment and the Great Commission."

- Billy Graham and Franklin Graham

"Destined to be a classic on the Christian life, I predict The Purpose-Driven Life will become the My Utmost for His Highest of the 21st century Timeless, profound, compelling, and transforming, this book is a priceless gift for everyone who wants to know their purpose and fulfill their destiny As The Purpose-Driven Church has had the most profound impact on the church worldwide than any other book in this generation, Rick Warren's new, groundbreaking manifesto will set millions of people free to live the lives God intended. This is the book we've all been waiting for!"

- Bruce Wilkinson, Author, The Prayer of Jabez

"if you only read one book on what life is all about-make it this one! This book is life-changing. Rick Warren is absolutely brilliant at explaining our real purpose on earth and stating profound truths in simple ways. Give this book to everyone you care about. Believe me, you'll never be the same after reading this! What a gift!"

-Lee Strobel, Author, The Case for Christ

"Disoriented about your direction in life? Are decisions tough to make and steps hard to take? If so, Rick Warren has written a masterpiece of wise counsel for you. Whether you are a seeker, a new believer, or a seasoned saint, let God use these pages to place your feet firmly on the right path?"

- Max Lucado, Author, Traveling Light

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

business masterminds

JAKE THE FAST TRACK TO SUCCESS with Robert Heller's inspiring guide to business management that analyzes the achievements, innovations, and ideas of the world's leading business and management gurus, showing you how to make their strategies work in practice

WARREN BUFFETT

Globally acclaimed financial investor and pioneer of managing for shareholder value

STEPHEN COVEY

Author of The Seven Habits of Highly Effective People and celebrated teacher of practical management skills

PETER DRUCKER

The first to define the art of effective management and a ground-breaking pioneer of management theories

BILL GATES

Multibillionaire co-founder of Microsoft and master of seizing opport and staying ahead ame

ANDREW GROVE

Silicon Valley innovator who piloted the rise of Intel and defined the model for high- tech management

CHARLES HANDY

Renowned social philosopher and prophet of emerging business trends, such as portfolio careers

TOM PETERS

Author of In Search of Excellence and leading advocate of management by "perpetual revolution"

JACK WELCH

CEO of General Electric for 30 years and an advocate of motivating the workforce and discarding bureaucracy

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ገጣሚው እንዳለው  ‹ጥበብ ያለው ውበት ይገባዋል፡፡ ውበት ያለው ኅሊና አለው፡፡ ጭካኔ የውበት አረዳዱ የተዛነፈ ሰው መገለጫ ነው፡፡› -ንጽህናን ብትመርጥም ቅሉ - ... የእውነተኛዋ ውበት ማደሪያ ሙዳይዋ ነፍስ ነች፡፡ ውበት እንደ ወንጌልም ነች፡፡ አሳስተው ለሚረዳት ግና እንደ ወንጀልም፣ እንደ ኩነኔም ትሆናለች፡፡ ሆኖም - ከዳሌና ተረከዝ - የሚያልፍ የነፍስ ውበትን ለመረዳት በመንፈስ እንደገና ተወልዶ - የንጽህና ልጅ - መሆን ያስፈልጋል፡፡
... እኔ ግን መሄድ መድኃኒቴ ነውና እሄዳለሁ፡፡ መራመድ ቃልኪዳኔ ነው፡፡ በሰው ልጅ ሁኔታ፣ በከበበኝ ድንግርግር ላይ ሁሉ ተስፋ እንዳልቆርጥ የሚያደርገኝ መተማመን እሱ ነው፡፡ መራመድ ነጻ ያወጣኛል፡፡
ሄጄ ሄጄ የምቆመው ወንዝ ወይ ታላቅ ተራራ ፊት ከሆነ ደግሞ ነፍሴን የሆነ ዓይነት መደነቅ ይቆጣጠራታል፡፡ በተራራው ወገብ በምሽቱ ደብዛዛ ብርሃን ከአድማሱ ጀርባ (behind the horizon) እየተራመዱ ወደ ጨለማው ሲሰርጉ እንደሕልም የማያቸው የማላውቃቸው ሰዎች ቅድመ አያቶቼ ይመስሉኛል፡፡ በእንቅስቃሴያቸው ውስጥ የመላውን የሰው ልጅ እስትፋስ አደምጣለሁ፡፡ ያሉበት ሆነው በነፍስ እንገናኛቸዋለሁ፡፡
ከተራራው ጀርባ ጨለማ ነው፡፡ ያ ጨለማ ግን ስሪቱ የኦናነት (negation)፣ የመሰወር፣ የመጋረድ ሳይሆን የማስተሳስር የማጣመር መሆኑን አያለሁ፡፡ እንዲያ ሲሆን የመላው ሁለንታ ኃይል ሞገሱን የገለጠልኝ ይመስለኛል፡፡ ከአድማሱ ጀርባ ሲጋረድ ያየሁት በሰዎች ፈንታ አንዲት ብኩን መንገደኛ ወፍ፣ ወይ የሆነች የደመና ቁራጭ ብትሆንስ ስንኳ ልዩነት የለውም! በመላው ስነተፈጥሮ መተማመኔን ለማጽናት በቂ ናት፡፡ ያቺ አፍታ አሁን እና ቅድም፣ ቅጽበት እና ዘለዓለም፣ ጊዜ እና ቦታን የምታሟሟ፣ ሁሉንም ጊዜያት፣ ወቅቶችና ቦታችዎች በአንድ ጊዜ መኖር የምታስችል ምትሃተኛ ትሆንልኛለች፡፡


ያዕቆብ ብርሃኑ
በፍጹም እሳት መቃመስ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አንድ ቅጅ ብቻ እጃችን ላይ ይገኛል እጅግ ጥሩ ህትመት የሆነና ሙሉ ተአምሯን የያዘ መጽሐፍ ነው !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሁለት ኮፒወች ብቻ እጃችን ላይ

አዘጋጅ ብርሃኑ አድማስ
እና መርጌታ ኃየሎም በርሄ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ አሉ።
ፈጥነው ድርድር ያድርጉን !!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በተናጥል አንድ አንድ ኮፒዎች ብቻ አለን!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ውላል።


መምህር ሰሎሞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወንበር የተማሩ፣ በባችለር ኦፍ አርት ባይብል ኤንድ ቲኦሎጂ ዲግሪ ፣ በድህረ ምረቃም በቢቢሊካል ኤንድ ቲኦሎጂካል ስተዲስ በሲስተማቲክ ቲኦሎጂ ማስተርስ የተማሩ አገልጋይ ካህን ናቸው፡

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የተቀነጨበ...

*
እኔ የማወራለት ዳንስ ሁለንታን በአካላዊ እንቅስቃሴ ቅጥ ለመወዳጀት የመሞከር፣ ራስን በውዝዋዜ ቅጣቅጥ ለመግለጽ መቋመጥ እንጂ ሌላ ምንም አይደለም፡፡ ነፋሳትስ ስንኳ ከዛፎች፣ ከአዝዕርት፣ ከእያንዳንዱ ስነሕይወታዊ አካል ጋር በሚያደርጉት ተራክቦ ንዝረትን ይጋራሉ፡፡ በእርግጥም የልብ ምቷን ካገኘኸው ተፈጥሮ ራሷ እርግብግቢት መሆኗ ይገለጥልሃል፡፡ ነፍስም እንደዛው ነች፡፡ በእያንዳንዱ የውበት ቅኝት፣ ንብርብር፣ መጥበርበር ትነካለች፤ ትርበተበታለች፤ ታድጋለች፤ ትጎለምሳለች፡፡ ሆኖም የትኛውም ፍንደቃ በአጠቃላይ የሕይወት ልምምድ ሥሩ ሕመም ነው፡፡ ሀዘን! ጥልቅ ሀዘንና ልክ የለሽ ደስታ የሚተላለፉባት ያቺ ነጥብ ደግሞ ‹ሲቃ› ትባለች፡፡ ሰው እጂጉን ሲያዝንም አለቅጥ ሲደስትም እኩል የሚያለቅሰው ለዚህ ይመስለኛል፡፡

ሆኖም እነዚህ ወትሯዊ (eternal) ተቃርኖዎች ሊታረቁ የሚችሉ ናቸው፡፡ ጀርመናዊው ደራሲ ሔርማን ሔሰም አለ፡፡ ‹‹ሕይወት በልዩነት፣ በተቃርኖ ውስጥ ብቻ ማበብ ትችላለች፡፡›› ልዩነቶቹን የሚገራ እሱ ግን በተቃርኖዎቹ ላይ ይሰለጥናል፡፡ ሕይወት በእንቅስቃሴና ስልታዊ ተቃርኖ ውስጥ ስትቃኝ ይበልጥ መበልጸግ ትችላለች፡፡ እንቅስቃሴ ቅኝት ሲበጅለት ውዝዋዜ፣ ሽብሻቦ፣ ዳንስ ይባላል፡፡ ዳንሱ ሽሽት ሊሆን ይችላል፡፡ ማሳደድ፣ ማማለል፣ ማግባባት ሊሆን ይችላል... ሕይወት ሁሉንም ነች፡፡ አንዱንም ብቻ ልትሆን አትችልም፡፡
ለነገር መጠቅለያ የሚሆን ተረክ እነሆ...

*

ታላቁ የሱፊ መምህር ጁናይድ ፍጽምናውን ከመቀዳጀቱ በፊት በመንገዱ ላይ ነበረ፡፡ በአንድ የጠፍ ጨረቃ ዕለት አመሻሽ ከመስጂድ በመመለስ ላይ እንዳለ በኩራዝ ብርሃን እየታገዘ የሚራመድ ታዳጊ ልጅ አገኘ፡፡ ጁናይድ ታዳጊውን እንደዘበት ጠየቀው...
‹‹ልጅ የምትገለገልበት የፋኖስ ብርሃን የለኮስከው አንተ ነህን?››
‹‹አዎ››‹‹እንግዲያውስ የፋኖሱ ብርሃን ከየት እንደተቀዳ ታውቃለሃ፡፡ የብርሃኑ ምንጭ ከየት እንደሆነ ልትነግረኝ ትችላለህን?››
ታዳጊው ምንም ሳይጨነቅ የፋኖሱን ብርሃን ካጠፋ በኋላ መለሰለት...
‹‹እነሆ አሁን የፋኖሱን ብርሃን ሲከስም ተመልክተሃል፡፡ እናም የፋኖሱ ብርሃን ወደ የት እንደሸሸ ከነገርከኝ በእርግጥም እኔም ብርሃኑ ከየት እንደመጣ ልነግርህ ይቻለኛል፡፡ ነገርግን ብርሃኑ ወደ የት እንዳፈገፈገ ልትነግረኝ አትችልም አየህ፡፡ ምክንያቱም ብርሃኑ የተቀዳውም፣ የሚፈሰው፣ የሚሸሸውም ‹ወደዚያው› ነው፡፡ ወደ ምንጩ...››

*

ታላቁ መምህር ዘወትር ዕውቀትን ለሚገልጡለት ሁሉ እንደሚያደርገው መሬት ላይ ወድቆ ታላቅ መገለጥ ያስታጠቀውን ታዳጊ እግር ሳመ፡፡
‹ወደዚያው› ሲሰሙት ተራ ቃል ቢመስልስ ስንኳ ሕልውና የነጥብ ያህል ያነሰች ቅጥ (elemental, eternal, archetypal being) ሆና የተቋጠረችባት አጽቅ እሷ ናት፡፡ ሕይወትም እንደ ብርሃኑ ሁሉ በክብ የማርገድ፣ የማመርገድ ሂደት ነች፡፡ ከዚያው ወጥቶ ወደዚያው የመመለስ መቅበጥበጥ... በታላቁ ገጣሚ ገብረክርቶስ ደስታ አንደበት እንደተፈከረችው ‹ሕይወት ወደ ግራ ሲያነቧት ሞት› ትሆናለች፡፡ ዳንስም ከዚህ ጥቅል ሕልውና ነጥለው ለብቻው ሊያፈክሩት የሚሽቱ ያኮሰምንታል፡፡

ይልቁንስ ዳንስ መንገድ ነው፡፡ ወደ ዘለዓለም የሚያደርስ መንገድ፡፡ የመብቃት፣ የመሻገር፣ የመንጻት፣ የመፈወስ፣ የመባረክ ፍኖት... አሁን ሁለት ሲደመር ሁለት ስለምን ዜሮ ወይ ሕልቆመሳፍት (ኢንፋይናት) ይሆናል እንዳልኩህ ገባህ? ሕልውናን የሚገልጸው ልኬታ ምንም ወይም ሕልቆመሳፍርትነት ብቻ ነዋ! ‹ሁለት› ገባጋበው የሰው ልጅ አዕምሮ የፈጠረው ወካይ ምልክት እንጂ ሌላ ምንም

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ኤፒክቲተስ

የስቶይኪዝም ፍልስፍና መሰረት የሆነው የኤፒክቲተስ አዲስ መጽሐፍ በአንድ ወር ውስጥ ሁለት ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ..!!
ከኤፒክቲተስ [የስቶይኪዝም] ፍልስፍና መሰረተ ትምህርቶች ምንጭ የሆነውና ጥልቅ ለሰው ልጅ ጠቃሚ ትምህርቶችን ማስተላለፍ የቻለው ኤፒክ 2000 ዓመታት የሰው ልጅን ህይወት እጅግ ጣፋጭ እንዲሆን የሚያስችሉ ጠቃሚ ትምህርቶችን ያስተማረና 2000 ዓመታትን መሻገር የቻሉ  ጥልቅ አስተምህሮቶች ባለቤት ነው...!!

#ከሕይወት ጋር #ግብግብ ትተው #ሕብረትን  ይፍጠሩ ...!!
       የራሴ ህግ የሚሉትን ነገር እንዳይሞክሩት፡፡ ትልቅ፣ ትንሽ፣ የሰለጠነ፣ የተናቀ ሳይሉ ከሁሉም ነገር ጋር ግንኙነትዎን በተፈጥሯዊ ህግ መሰረት ያድርጉ፡፡ ምኞትዎን ከተፈጥሮ ጋር ሕብር ባለው ሁኔታ ማናበብ ዋነኛ ግብዎ ሊሆን ይገባል፡፡
ይህንን ልምምድ  የሚያከናውኑትስ  የት ነው..?
በእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ነዋ... ይለናል ኤፒክ። ሲሰሩ፣ ሲመገቡ፣ ገላዎን ሲታጠቡ ፣ ብቻ ምን አለፋው ማንኛውንም ነገር ሲያከናውኑ ከተፈጥሮ ምሪት ጋር በተናበበ መልኩ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ ጉዳዩ ምን አከናወኑ አይደለም፡፡ እንዴት አከናወኑ እንጂ… ይህንን መርህ በቅጡ ተገንዝበን መተግበር ከጀመርን በሕይወታችን ውስጥ የቱንም ያህል ችግሮች ሊፈጠሩ ቢችሉ (ምክንያቱም ችግሮ የተፈጥሮ ሂደት አካል ናቸውና) ውስጣዊ ሰላምን መጎናጸፍ ዘወትር የሚቻል ይሆናል፡፡ የሚሉና ሌሎች ጠቃሚ መሰረታዊ የህይወት አስተምህሮዎችን ሰብኳል ።.!!..

ለንባብ ባህል መጎልበት እንተጋለን..!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በፍም እሳት ማቃመስ
(እንደ ማስተዋወቂያ እነሆ...)
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*

የሰውን ልጅ ከተራ አውሬነት ጎራ ነጥሎ ወደ መለኮታዊነት ያሸጋገረው እሳትን መፈልሰፉ ነበር፡፡ እሳትን ከማላመዱ በፊት የሰው ልጅ ከ20 በማይበልጡ ትንንሽ ቡድናት የሚንቀሳቀስ፣ የአዳኝ አራዊት ሰለባነትን ሽሽት የእውርድንብር የሚቃትት ድንጉጥ ፍጥረት ሆኖ አሳለፈ፡፡ እሳትን ማላመዱ ግን በአንድ ጊዜ ድርድርብ መሳሪያዎችን እንደመታጠቅ ሆነለት፡፡ አብስሎ መብላት ተቻለው፤ ጤናው ተሻሻለ፡፡ ምግቡም በረከተ፡፡ በአንድ ጊዜ ‹food chain›ኑ አናት ላይ ለመቀመጥ በቃ፡፡ እሳቱ ራሱን ከቅዝቃዜና ከአራዊት ጥቃት ለመከላከል እንደ ሁነኛ መሳሪያ አገለገለው፡፡

በእርግጥም የሰው ልጅ እሳቱን እስኪፈለስፍ ድረስ ለመጥፋት የተቃረበ፣ በስራ ፈትነት የሚንጀባረር ለአደጋ የተጋለጠ እንሰሳ ነበር፡፡ (Man was a meandering and jabbering around beast until he discover fire...) እሳትን ካላመደ በኋላ የሰው ልጅ ለስልጣኔው -ም-ት-ክ-የ-ለ-ሽ- መሠረቶች የሆኑትን የእሳት ግኝቶች -
ምድጃን (hearth) -
መሰዊያን (Altar) እና
ማቅለጫን (forge) ፈለሰፈ፡፡

ምድጃው ሁለተናዊ ደኅንነት እና መረጋጋትን አቀዳጀው፡፡ ምድጃው እንደ ‹ሴል› (cell) ሆኖ የሰው ልጅ በዙሪያው እንዲሰባሰብ ምክንያት ሆነ፡፡ ቤተሰብ እንዲመሰረት አገዘው፡፡ ከቤተሰብ አስር ሃያ እያለ ወደ ትንንሽ ማኅበረብነት አደገ፡፡ መረጋጋት ቻለ፡፡ ቀስበቀስ መንደሮችን መገንባት ጀመረ፡፡ በምድጃው ዙሪያ ብዙ ዓይነት ተረቶችን አደራ፡፡ የሰው ልጅ ተረቶች፣ ታሪኮች፣ ሚቶች በሙሉ የመነጩት ከምድጃው ነበር፡፡ ተረቶቹ አፈታሪኮቹ ምናቡን ለመሳል ጠቀሙት፡፡

መሰዊያው መንፈሳዊ በጎነትን አጎናጸፈው፡፡ የዓለም ኃይማኖቶች በሙሉ የመነጩት ከመሰዊያው ነበር፡፡
ማቅለጫው ቅኝቱ የፈጠራ ሆነ፡፡ ከጦር አንካሴና ማጭድ ጀምሮ እስከ ሮኬት ሳይንስ ዛሬም ድረስ እየተራቀቀ ለቀጠለው ቴክኖሎጂያዊ መራቀቁ መነሻው እሱ ማቅለጫው ነበር፡፡

ነገርግን በግሪክና መሰል ጥንታዊ ተረታዊ ትርክቶች እንደሚባለው የሰው ልጅ እሳትን ከአማልክት አልሰረቀም፡፡ የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ጫረውም... እሳትን ከክዋክብት ገጽ ለመጫር ደግሞ ከገል እና ኩበት ይልቅ ምናብ ያስፈልጋል፡፡

ምናብ ምንጊዜም አሸናፊ ያደርጋል፡፡ ጥቂትስ ስንኳ የተሳሉ ምናቦችን ከመካከሉ መፍጠር የሆነለት ሕዝብ ምንጊዜም የትርክት የበላይነትን ይቀዳጃል፡፡ ስለምናብ ሳወራ ስለድርሰት ብቻ እየተናገርሁ የሚመስለው ካለ መቸስ ምን እላለሁ፡፡ ነገርግን ቴሌስኮፕ፣ ማይክሮስኮፕ፣ የማተሚያ ማሽን፣ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክን ጨምሮ በጠቅላላው የኤሮፓ ሥልጣኔ ግኝቶች የምናብ ውጤቶች መሆናቸው እሙን ነው፡፡

የእሳትንም ያህል ፍጹም ቅን፣ ገር እና በስነተፈጥሮው ቀጥተኛ ነገር መኖሩን አላውቅም፡፡ እሳት ከብሉያት፣ ነብያት፣ ወንጌላዊያን፣ ከአፈታሪኮች እና ባለቅንያት ዘመን ጀምሮ ብዙ የተባለለት መለኮት አከል ረቂቅ ክንውን ነበር፡፡ እሳት ሲፈጅ፣ ሲበላ እንጂ ሲያርፍ ማደሪያው የት፣ ሲግለበለብ መከሰቻው ከወዴት እንደሆንስ ስንኳ የሚያውቅም የለም፡፡ እሳት ስሪቱ የነበልባል፣ የፍላጻ ብቻ አይደለም፡፡ የቃል፣ የቀለም፣ የመንፈስ ልዩ ልዩ ዓይነት አለው፡፡ እሳት ንጹህ ነው፤ ቅን ነው፤ ገር ነው፡፡ ግን ደግሞ አውዳሚ፣ ጨራሽ፣ ፈጅ፣ ቀሳፊ፣ ቁጡም ነው፡፡ የዚህ ረቂቅ የነበልባል ቅኝት ጥሪ እና ምሪት ሰብዓዊነትን ማበልጸግ መሆኑ ጥንት ከአፈታሪክ፣ ከነፕሮሚተስ ዘመን ጀምሮ ይታወቃል፡፡

አሳት ሥሪቱ የእንከንየለሽነት፣ የምኅረትየለሽነት መሆኑም እሙን ነው፡፡ እሳት በመንፈሳዊውም (spirited) ይሁን በገቢራዊ (empirical) ባህሪው የሚያሻግር (fire of transmuting) እና የሚያሳርር (fire of destruction) መንታ ጉልበት ያለው ረቂቅ ሁነት ነው፡፡ እሳት የነካውን ሁሉ የሚያነጻ (purifying) ወይም የሚያገረጣ (terrifying) አቅም አለው፡፡ ቁም ነገሩ ለየትኛው አሰልጥነሽዋል/ አሰልጥነኸዋል የሚለው ብቻ ነው፡፡
ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ያም በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈ - ምልክት ሆነለት - ... ነብዩ ኢሳያስ ለነብይነት የተመረጠበትን አኳኋን በሚናገርበት በትንቢተ ኢሳያስ ምዕ 6፡8 ላይ እንደምን በፍም እሳት መቃመስን ተቃምሶ መንጻትን እንደተቀዳጀ ሲገልጽ...
‹‹ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፡፡ በእጁም ከመሰዊያው በጉጠት የወሰደው ፍም ነበረ፡፡ አፌን ዳበሰበትና ‹እነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል፡፡ በደልህም ከአንተ ተወገደ፡፡ ኃጥያትምህም ከአንተ ተሰረየልህ› አለኝ፡፡›› ይላል፡፡
የሰው ልጅም የእሳት አቀባበል እንዲህ ይመስለኛል፡፡ ልክ የባላገር እናት የአራስ ቤት ጨቅላ ልጇን ወደ ሕይወት ለመጥራት በቅቤ እንደምታቃምስ እንዲያ የሰው ልጅ የነቢይ በሆነ በእሳት መቃመስን ተቃመሰ፡፡ ከእሳት ጋር መገናኘቱ ሁለንተናውን የሚያሻግር ክስተት ሆነለት፡፡ መቼ? የት? የሰው ልጅ ከእሳት ጋር ተዋወቀ ሳይንስ ባዝኖ ባዝኖ መልስ ቁርጥ ያለ መልስ ያጣላቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በደፈናው እስከ 2 ሚሊዮን ዓመታት ይገመታል ብሎ ማለፍ ይሻል ይመስለኛል፡፡ ነገርግንስ የሰው ልጅ እሳቱን ማላመዱ፣ በትንታግ መፈተኑ፣ ነበልባሉን መግራቱ ራሱ የሰው ልጅ ብዙ ዓይነት ሞራላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሥነልቦናዊና አካላዊ ሽግግር እንዲያከናውን ረዳው፡፡
እሳትን ከፈለሰፉት የመጀመሪያዎቹ አውሬ መሰል የሰው ልጆች እስከ እሳትን ወደ ኤሌክትሪክ የቀሩት ድረስ ከ50 - 60 ሺህ ትውልዶች እንደተፈራረቁ ይገመታል፡፡ የእኛ ግን እርግማን ይመስላል፡፡ ሌላው ዓለም እሳቱን ከአመድነት ወደ ስማርት ምድጃነት ከፍታ ሲያሻግር እኛ ዛሬም ጉልቻዋን የሙጥኝ ብለናታል፡፡ ከጥንታዊነት (primitive sentiment) ያልተሻሻለ ቢሆንስ ስንኳ... ለዘመናት ጉልቻውን ታክከን ተረቱን ማንዘገጋችን አልቀረም፡፡ መሰዊያዎችንም (የአምልኮ ቦታዎች) በዓይነት እና በጥራት እየገነባን ስናደገድግ ምዕታት አልፈዋል፡፡ ለሰብዓዊ ልማት ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበረውን ዋነኛውን የእሳት ግኝት ማቅለጫውን (forge) ግን ሆነ ብለን ረሳን፡፡ ማቅለጫውን ሙሉ ለሙሉ ብንረሳ ከብዙ መቶ ሺህ ዓመታት በፊት የመጀመሪያው የሰው ልጅ በተጠቀመበት ጦር ጀት የታጠቀውን ጣሊያንን ለመግጠም ተገደድን፡፡

የኢትዮጵያን የሥልጣኔ ታሪክ በተለይ ከአክሱም ውድቀት በኋላ የነበረውን ሂደት በጥልቀት የሚመረምር ሰው የጎደለን ነገር ማቅለጫው እንደነበር ግልጽ ይሆንለታል፡፡ ማቅለጫው ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሌላም ሌላም ብዙ ነገር ነው፡፡ በዚህ መጽሐፌ ከተካተቱ አስራ አንድ መጣጥፎች ውስጥ ስድሳ ገጾችን በሚሸፍነው የመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ ሥልጣኔ የጎደለው የመሰለኝን የማቅለጫውን ነገር በጥድፊያም ቢሆን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ፡፡ ሌሎች በዚህ መጽሐፍ ስር የተካተቱ ሌሎች አስሩም መጣጥፎቼ በልህቀት ለሚያነባቸው የእሳት ንክኪ እንዳላቸው አምናለሁ፡፡

Читать полностью…
Subscribe to a channel