azop78 | Unsorted

Telegram-канал azop78 - ኤዞፕ መጽሐፍት

8609

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !! ስልክ:- 09 11 72 36 56 @Mesay21 @Mesay21

Subscribe to a channel

ኤዞፕ መጽሐፍት

ከእነዚህ ትርጉም የኢትዮጵያ ታሪኮች ውስጥ የቱን አንብብ ውል ????

ካነበቡም የቱን ታሪክ ወደዋል ?

እኛ ጋ በምርጫዎ ይገኛሉ!!!
ለዋጋቸው እጅጉን አያስቡ !!!
በተመጣጣኝ ዋጋ እንሸጥልዎታለን !!!!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

Timely, forceful and essential. A groundbreaking and deeply re- searched exploration of of the war still ravaging Tigray. A vital contribu- tion to the understanding of a devastating but largely hidden conflict, which could well prove to be a defining moment, not just for Ethiopia and the Horn of Africa, but for the whole continent.-Andrew Harding. HBC Africa correspondent, and author of The Mayor of Mogadishu

"With historical depth, trenchant analysis of current events and con- cern for the human suffering involved, this is essential for understand- ing the tragic war in northern Ethiopia?-Christopher Clapham, Centre of African Studies, University of Cambridge, and author of The Horn of Africa

"The Ethiopian-Eritrean war against Tigray is the world's most lethal conflict, characterised by extreme brutality and the use of mass starva- tion as a weapon. It has unfolded behind a wall of silence and disinfor mation. This important book sets a high standard, paying scrupulous attention to the evidence and analysing the conflict and atrocities in their political context. Alex de Waal, Executive Director, World Peace Foundation

A moving account that chronicles the genesis, nature and key features of the Tigray war, as well as the Tigrayans' resistance. This lucid analy sis of developments will be of significant interest to scholars of contem- porary Ethiopia.-Mulugets Gebrehiwat Berhe, Senior Fellow and former Program Director: World Peace Foundation, Tufts University, and author of Laying the Past to Rest: The EPRDF and the Challenges of Ethiopien State-Building

"Not only a good political history of modern Ethiopia, but an attempt at answering the question; is war the only way to arbitrate between a uni tary and a federalist version of a nation?-Gérard Prunier, author of The Country That Does Not Exist: A History of Somaliland and co-editor of Understanding Contemporary Ethiopia

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

Terrorism in Ethiopia and the Horn of Africa
Author
Nowhere today is untouched by the threat of terrorism but the Horn of Africa is one
of the worst affected regions: Somalia, a collapsed state and centre for piracy, offers
Al Qaeda a safe haven and training facilities; Eritrea uses terrorism in foreign policy:
Ethiopia, Kenya, Somalia and Uganda have all been targets again and again.
This book is about the threat posed by terrorism in the Horn of Africa, focusing on
Ethiopia, detailing hundreds of terrorist atrocities. It unravels the false distinction
between "international" and "domestic" terrorism, analyzing suicide missions, the
impact on human security, and looking at responses of the international community
and IGAD.
The author argues that focus on violence shouldn't blind policy-makers to the
economic and social problems underlying terrorist activity; that credible long-term
response must be based on systematic research, realistic development and inclusive
politics as well as human security. He provides intriguing recommendations for the
way forward.
The author, a serving intelligence and security officer in Ethiopia, and himself a
former freedom fighter, uses an exceptionally wide range of sources, interviewing
victims, terrorists, security experts and academics and drawing on his own experi-
ence, to detail the impact of terrorism in Ethiopia.
This is a serious and readable attempt to understand and explain terrorism and
respond to it. One of the first real efforts to produce a detailed analysis of terrorism
in Ethiopia and the Horn of Africa, it defines the tension between terrorist activity
and government response, and shows the effects on human security in
ccurity in one of the most
"" "
volatile regions of the world,
Patrick Gilkes, author of The Dying Lion, Conflict in Somalia and Ethiopia, The War
between Ethiopia and Eritrea (with Martin Plaut), etc.
azop book
December 6, 2023 9:37 AM

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሻለቃ መሐመድ ያሲንን በቀድሞው በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ፣ ሐረር ቀ/ኃ/ሥላሴ ጦር አካዳሚ በሦስት አመታት የስልጠና ጊዜና ከዚያም በኋላ እኔ በዚያው አካዳሚ በአሰልጣኝነት ተመድቤ፣ ሻለቃ መሐመድ ደግም በ3ኛ ክ/ጦር መሐንዲስ መምሪያ ተመድቦ በጠቅላላው ለስምንት አመታት በነበረን መቀራረብና መግባባት ማንነቱን ጥሩ አድርጌ አውቀው ነበር።

የሻለቃ መሐመድ አራተኛና የመጨረሻ ልጁ ዶ/ር ያሲን መሐመድ ስለአባቱ የሕይወት ታሪክ “የቀይ ባሕር ዕዳ፣ ከሻለቃ መሐመድ ያሲን ማስታወሻዎች”፣ በሚል ርዕስ የአባቱን የግል ማስታወሻዎች፣ የደብዳቤ ልውውጦች፣ በየጊዜው ከበላይ ኃላፊዎቹ የተፃፉለትን የምስጋናና የአድናቆት ፅሁፎችና በርካታ አንፀባራቂ ፎቶዎች አጅቦ አሳምሮ አቅርቦታል። ሻለቃ መሐመድን ከምንም በላይ በትክክል የሚገልፁትን ባሕርያት፣ መልካም ስነ-ምግባር፣ የተረጋጋ ሥነ ልቦና፣ ደከመኝ ታከተኝን የማያውቅ ታታሪ ሠራተኛ፣ የአመራር ተስጥኦ፣ ፍትሐዊነትና የአገርና የወገን ፍቅር ደራሲው እዚህ ቀረው በማይባል ሁኔታ አስቀምጦታል፡፡

የሻለቃ መሐመድ ያሲን የግል ማስታወሻዎች የደራሲው ጥልቅ ምርምርና ክትትል እንዲሁም እልህ አስጨራሽ ጥረት ታክሎበት ደራሲው አባቱ በጨቅላ ሕፃንነቱ በአጭር ከተቀጨ ከአራት አሰርት አመታት በኋላ እንዲህ አይነት የተሟላ ታሪክ ማቅረብ መቻሉ የሚደነቅ ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ ለቀሪው ትውልድ በማስታወሻነት ለሻለቃ መሐመድ ያሲን እንደ ሕያው ሐውልት ሊቆጠር ይችላል።

ሻለቃ አርጋው ካብታሙ
ከሰጠው አስተያየት የተወሰደ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

business masterminds

ROADS to SUCCESS

PUT INTO PRACTICE THE BEST BUSINESS IDEAS OF EIGHT LEADING GURUS

WARREN BUFFETT

STEPHEN COVEY

PETER DRUCKER

BILL GATES

ANDREW GROVE

CHARLES HANDY

TOM PETERS

JACK WELCH
BSTSELLING BUSINESS AUTHOR & MANAGEMENT COMMENTATOR

Robert HELLER

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

some of the more important aspects of Ethiopia's complex social life. Moreover there were often many variations of practice from one district or village to another, for the communities under review were composed, it should not be forgotten, of individual men, women and children, who lived their varied lives as they could, or thought fit- in blissful ignorance of the foreign traveller's accounts, and other historical sources, upon which scholars base their accounts and develop their interpretations - of traditional Ethiopian behaviour.

The present volume, conceived as a first installment towards a full Social History of Ethiopia, is primarily descriptive. It is intended to present a survey based on available sources, and thereby to lay a groundwork for other writers to develop more ambitious, comprehensive and interpretative, studies of old-time Ethiopian life. It is hoped at a later stage to publish companion volumes on the south of the country, as well as on the period from Téwodros to more recent times.

I should like to thank friends and colleagues who made this publication possible. I am grateful to Dr. Taddese Beyene, the devoted Director of the Institute of Ethiopian Studies, for his kind help and encouragement, as well as to Margaret Last for typing part of the first draft, to Amanda Woodlands for generously devoting her time to putting most of the text on computer, to my children Alula and Helen for initially helping me wrestle with that machine, to the computer wizard Bruno Neeser for producing IBM-compatible diskettes, and to Tatek Samare for expertly preparing the final work for printing and assisting in computer-indexing. Special thanks are also due to Demeke Berhane and to the ever-enthusiastic Dr. Carla Zanotti for helping me identify manuscript illustrations at the Institute; to Dr. Vincenzo Francaviglia, Denis Gérard, Santha Faiia and Membere Wolde Ghiorgis for kindly photographing these and other works; to the dedicated Degife Gabre Tsadik and his staff for constant library assistance, and to Belai Giday for approaching local informants on my behalf. I am, as always, indebted to my wife Rita for innumerable comments, criticisms and suggestions.

RICHARD PANKHURST

Institute of Ethiopian Studies, Addis Ababa University.

azop book
December 2, 2023 2:16 PM

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

INTRODUCTION

In introducing the present essay on the Social History of Ethiopia, it should be emphasised that the country, which today covers an area as large as France and Spain combined, has always been one of immense geographical and other contrasts. High mountains, which in the Sämén range tower more than 4,600 metres above sea level, give way to flat lowlands which in the 'Afär depression sink below sea level. Temperature, which, geographically, is no less varied, ranges from the icy cold of the mountains, with frost, and in places even snow, through the temperate highlands - the site of most of the country's historic settlements to the torrid lowlands, with the Red Sea and Gulf of Aden ports reckoned as among some of the hottest places in the world. Differences in rainfall have been no less dramatic, the torrential downpours of the highlands contrasting with minimal precipitation in the parched almost waterless lowlands. It follows that vegetation was equally varied, with tropical jungles, particularly in the west, deserts and semi-desert scrublands, mainly in the east and south, and fertile - but largely deforested-regions in many areas of medium elevation.

The population of the country, not surprisingly, came to terms with such greatly varying environments in different ways, with the result that the world's principal types of economic activity were all represented with agriculturalists, many of them practicing plough agriculture, in the extensive highlands, pastoralists in the even more widespread lowlands, and hunters and gatherers in the vicinity of the many rivers, lakes and forests. (This three-fold division is, however, far from rigid, for there was often much overlapping, particularly in the highlands where the supposed "agriculturalists" devoted much of their time to the upkeep of cattle which many farmers and peasants regarded as their principal source of wealth).

Ethiopia like so many countries on the African continent is in no less measure a land made up of varied ethnic and linguistic threads. It comprises members of no less than four broad language groups: Semitic, mainly in the north, but with pockets in the south (Guragé and Adaré), Cushitic, mainly in the south, but with pockets in the north (Beja, Agaw, Saho, and 'Afar), Omotic (Wallamo, Kafa, Gemerra, etc.) in the south-west, and Nilo-Saharan in the far west, near the Sudan border. The situation was, however, historically far from static, for there were over the centuries major movements of population, notably in the ancient and medieval period when Tegrés moved from north to south; in the sixteenth, seventeenth and early eighteenth centuries when Oromos migrated from south to north; in the nineteenth century when there was once more a movement, mainly of Amharas, from north to south; as well as throughout the centuries to and from sundry national or provincial capitals. For this and other reasons bilingualism, and indeed multilingualism, may well have existed throughout this period.

The religious pattern - in which the world's three main monotheistic faiths are all represented was no less varied. For centuries Christians of the Orthodox faith predominated in the all-important northern and central highlands, Muslims were no less dominant in most of the lowlands, particularly to the east, as well as at the great commercial centre of Harär, but were also of paramount importance as merchants

throughout the region as a whole. Followers of traditional local faiths preponderated in the south-west (the source of much of the country's exports of gold, ivory, civet and

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ዛሬ መጽሐፍትን ልናስተዋውቃችኹ አይደለም፣ ይልቁንም ብታነቧቸው ነብሳችኹን ሀሴት እንድታደርጉበት የምንጠቁማችኹ መጽሐፍት ልንጠቁማችኹ ነው። ያዕቆብ ብርሃኑ ይባላል። ገና ወጣት ደራሲ ነው፡፡ ነገር ግን ከእድሜው በላይ የበሰለ ትንታግ ብዕረኛ ሲኾን ዘመናችን እያቀለሙ ካሉ ወደፊት እንደሚጎሉ ከምንጠብቃቸው ወጣት ደራሲያን መካከል ግንባር ቀደሙ አሰላሳይ ፀሐፊ ነው፡፡ የሚያነሳቸው ሃሳቦች ያስደምማሉ። በፍልስፍና፣ በስነ ልቦና፣ በታሪክና በስነተረቶች የላቁ መረዳቶችን የሚያነሱና እጅግ በበሳል ቋንቋ የታሹ ተረኮች በማቅረብ ረጃጅም ሃሳቦችን አሳጥሮ በተከሸኑ የቋንቋ ብስለት ሲገልፃቸው ያስደምማል፡፡ ያስቀናል።
የቃላት ወጌሻነቱ አንብቡኝ አንብቡኝ ያሰኛል። በእያንዳንዱ ምዕራፍ አንድ ሙሉ መጽሐፍ የማንበብ ያክል እንዲሰማኽ እያደረገ መተረክን ይችልበታል።
በሉ ነገር ቢያበዙት በአኽያ አይጫንም ፣ ግዙና አንብቧቸው።
ኤዞፕ መጻሕፍት መደብርም የዚህን ወጣት ደራሲ የሚከተሉትን ምርጥ ምርጥ አራት መጻሕፍት አሳትሞ ለገበያ አቅርቧል፡፡
* ከባዶ ላይ መዝገን ልዩ ልዩ ሀሳቦች፣ ፍልስፍናዎች - 2014 ዓ.ም
* በፍም እሳት ማቃመስ (initiating by fire) ልዩ ልዩ ሀሳቦች፣ ፍልስፍናዎች - 2016 ዓ.ም
* የመሻገር ሲቃ - ልብወለድ፣ 2015 ዓ.ም
* የካህሊል አማልክት - ትርጉም፣ የካህሊል ጅብራንና የሜሪ ሐስከል የፍቅር ደብዳቤዎች፣ 2014 ዓ.ም

ያንብቧቸው!
ያስነብቧቸው!
በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮች ያገኟቸዋል፡፡
ይደውሉልን 09 11 72 36 56 ኤዞፕ መጻሕፍት
መልካም ምንባብ!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

‹‹ካንተ አንድ ነገር ፈልገን ነበር›› ‹‹ምንድነው?››

‹‹እንከፍልሃለን ፡ ፡ ሥምህን የሚመጥን ገንዘብ እንሰጥሃለን››

‹ምንደንው የምትፈልጉት?››

‹‹ፊልም እንድትሸጥልን››

‹ፊልም?››

‹‹እዎን ፡፤ በቀይ ሽብር ዘመን የቀረጽካቸው ፊልሞች አሉህ አሉ ያልተሰራጩ ፤ ቅጂዎቹ አንተ ዘንድ ብቻ የሚገኙ ፤ እና ብዙ የተንገላታህበት ፤ ከሞት የተረፍክበት…ብዙ ብዙ ነገር የሆንክበት››

‹‹እውነት ነው ››

‹‹ሸጥልን››

‹‹ምኑን?››

‹‹ፊልሙን››

‹‹እኔ ደም አልሸጥም››

‹‹ደም?››

‹‹አዎን ደም››

‹‹የምን ደም ነው የምታወራው? እኛ ምንልህ የቀይ ሽብርን ፊልም ነው››

‹‹እኔ ደም አልሸጥም አልኳችሁኮ ፡ ደሙ የኢትየጵያውያን ደም ነው ፤ የኢትዮጵያውያንን ደም በገንዘብ የመለወጥ ሞራል የለኝም››

ከመጽሐፉ የተወሰደ

azop book
December 1,2023 2:20 PM

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የዚህ መጽሀፍ ዋነኛው መነሻ የእኔን የግል የህይወት ታሪክ መተረክ ሳይሆን በትውልድ ቅብብሎሽ የእያንዳንዳችን ማንነት እንዴት እንደሚቀረጽ ማሳየት እና የዚህም ድምር ውጤት አንድን ሃገር በመገንባትም ሆነ በማፍረስ ያለውን ጉልህ ድርሻ ማመላከት ነው፡፡

ወላጆቻችን ከአያት ከቅድም አያት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ለነፃነት ቀናኢነት እና አልበገርም ባይነት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኖረውት ጥብቅ የሆነ የሃገር መውደድ ስሜትን አውርሰውናል። በስጋ ከሚወለዷቸው ባልተናነሰ የሚያፈቅሯቸው እህቶች እና ወንድሞች በማፍራት፣ መወለድ ቋንቋ ነው የሚለውን ሃገራዊ ብሂል በተግባር ኖረው ሰፊ ማህበራዊ ትስስርን አስተላልፈውልናል።

በማንኛውም ህብረተሰብ ውስጥ ወጣቱ ትውልድ ቀዳሚ የለውጥ አራማጅ እንደሚሆነው ሁሉ እኔም እንደዚያ የ1960ዎቹ ትውልድ በ966ቱ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ተሳትፌአለሁ። ይህ ተሳትፎዬ በወቅቱ ውድ ዋጋ ቢያስከፍለኝም፣ የዚህ አካል በመሆኔ ከፍተኛ ደስታ እና እርካታ ይሰማኛል።

ባለፉት ዓመታት በርካታ ልሂቃን ሐገራችንን ካለችበት ችግር ለማውጣት መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ደጋግመው ተናግረዋል። የማንኛውም መዋቅራዊ ለውጥ አስኳሉ እና ቀዳሚው ደግሞ የአዕምሮአዊ ውቅር ለውጥ ነው። የዓለማችን ቀደምት ሳይንቲስት አልበርት አይንሽታይን እንዳለው፣ ችግሮቻችንን የፈጠረው አስተሳሰባችንን ሳንቀይር መፍትሄ ማግኘት አንችልም˙ እና።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ገጣሚ አንዱዓለም ተሰፈዬ

ለካ ሰው ይኖራል
ፍላጎቱን አቶ
ህልሙን ተቀምቶ

ለካስ ሰው ይኖራል
አፍቅሮ ሲክዳም
የሚረዳው ሲያጣም

ለካ ሰው ይኖራል
በወዳጅ ተገፍቶ
ኑሮም ተከፍቶ


ለካስ ሰው ይኖራል
እምነቱ መንምኖ
ማንነቱ መክኖ

ለካስ ሰው ይኖል
ቃል ኪዳኑን ምሶ
በቃል ያሰረውን ሰንሰለት በጣጥሶ

ደጋግሞ ይኖራል ሁሉን አየቻለ
የሰው ልጅ ብርቱ ነው ትግስት የታድለ
ካለመኖር መኖር ይሻላል እያለ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

The Forum for Social Studies (FSS) is an independent, non-profit institution engaged in policy-oriented research on the develop- ment challenges facing Ethiopia. It provides an open forum for the discussion of public policy and promotes public awareness. FSS believes that encouraging broad participation in policy debates is an important contribution to the democratic process. To achieve its goals, FSS organizes public conferences, and pub- lishes and distributes its research findings to policy makers and other government officials, civil society institutions, profession- als, the business community, donor agencies and the public at large.

azop book

November 25, 2023 4:07 PM

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የሰው እድገት ሞተር ትምህርት ነው፡፡ የአንድ ገጠሬ ሴት ልጅ ዶከተር ለመሆን የምትበቃው በትምህርት ነው፡፡ እንዲሁም የአንድ ማዕድን ቆፋሪ የማዕድኑ ስራ አስኪያጅ የሚሆነው፣ የገበሬ ልጅም ለአንድ አገር ፕሬዚዳንትነት የሚበቃው ከውጪ በሚሰጠን ሳይሆን ከራሳችን ውስጥ በምናወጣው ነው፣ አንዱን ካንዱ የሚለየው፡፡

ኔልሰን ማንዴላ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሙዚቃ እና ጥይት ግን ትዕምርቶች (metaphors) ናቸው፡፡ ጥይት እና ሙዚቃ፣ ፀጥታ እና ሁካታ፣ silence vs violence...


ሙዚቃ ፀጥታውን ይወክላል፡፡ ሙዚቃ ውስጥ የረቀቀ ሕብር አለ፡፡ ሙዚቃ እንዲያውም እየተዋበች፣ እየረቀቀች ስትሄድ ዝምታ ትሆናለች፡፡ ባለሙያዎቹን ብትጠይቁ ዝምታ (ወይም እነርሱ በሙያዊ ቋንቋቸው እረፍት የሚሏት) ለሙዚቃ ምን ያህል መሰረታዊ እንደሆነች ይነግሯችኋል፡፡


በአንጻሩ ጥይት ስሪቱ የነውጥ፣ የሁካታ፣ የረብሻ፣ የብጥብጥ ነው፡፡ ጥይት ውስጥ ስርዓት ብሎ ነገር የለም፡፡ ይህ የንጉሥ ገጸባህሪይ የተጠማው ግን ጥይቱንም ሙዚቃውንም - ምልዓቱን - ሆነ፡፡ ንጉሡ ከላይ በጥቂቱ ተቀንጭቦ ባነብነው ጥቅስ ላይ ‹ሙዚቃን ያለ ጥይት መስጠት ኑፋቄ ነው፡፡ በስጋና በመንፈስ ግማሽ መሆን...  ጥይት ነው ምልዑ የሚያደርግህ፡፡›  ይላል፡፡


ምልዓቱ ደግሞ ሙዚቃውን ጥሎ ጥይቱን አንጠልጥሎ ብቻ የሚሳካ አይደለም፡፡ ምልዓቱን የሚሻ ማንኛውም ሰው ጥይቱን ከሙዚቃው እኩል ሊያባብል ግድ ይሆንበታል፡፡ ከፍ ብዬ በአጽዕኖት እንዳነሳሁት ጥይት እና ሙዚቃ የመላው ምድራዊ ኑረታችን ምንታዌነት (dualistic nature) ወካይ ምልክቶች ናቸው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፣ ፍቅር ከጥላቻ፣ ጽድቅ እና ኩነኔ... ሌላም፣ ሌላም...


ደግሞም የተደነቀው ሳይኮአናሊሲስት ፈላስፋ ካርል ዩንግ ‹‹I would rather be whole than good.›› እንዲል እንዲያ መልካም ከመሆን ይልቅ ምልዓቱን መሆን ይበልጣል፡፡ መልካም መሆን ሙዚቃውን አንጠልጥሎ ጥይቱን ግን ጥሎ እንደመንጎድ እንዲያ በመንፈስ ግማሽ መሆን ነው...  ምልዓቱን በመዋረስ ሂደት ሰው ቅንጣት መለኮታዊነቱን ያስታውሳል፡፡ ምልዓቱን መዋረስ ግን የሆነ ዓይነት የነፍስ ሀቀኝነት (genuinity) ይፈልጋል፡፡ በውሸት በጭካኔ በሚጋለብ ዓለም ስለእውነት መኖር ከባድ ዋጋ ማስከፈሉ የማይቀር ነው፡፡



ከመጽሐፉ እነኾ ቅምሻ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

The African Prester John and the Birth of Ethiopian-European Relations, 1402-1555

From the 14th century onward, political and religious motives led Ethiopian trave- lers to Mediterranean Europe. For two centuries, their ancient Christian heritage and the myth of a fabled eastern king named Prester John allowed Ethiopians to engage the continent's secular and religious elites as peers. Meanwhile in Ethiopia, the nobility came to welcome European visitors and at times even co-opted them by arranging mixed marriages and bestowing land rights. The protagonists of this encounter sought and discovered each other in royal palaces, monasteries, and markets throughout the Mediterranean basin, the Red Sea, and the Indian Ocean littoral, from Lisbon to Jerusalem and from Venice to Goa. Matteo Salvadore's narrative takes readers on a voyage of reciprocal discovery that climaxed with the Portuguese intervention on the side of the Christian monarchy in the Ethiopian- Adali War. Thereafter, the arrival of the Jesuits in the Horn of Africa turned the mutually beneficial Ethiopian-European encounter into a bitter confrontation over the souls of Ethiopian Christians.



Matteo Salvadore is Assistant Professor of History at American University of Sharjah, United Arab Emirates.


Azope book
November 22, 2023 1:37 PM

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ሀገር በሕገመንግስት ብቻ አትገነባም፡፡ በህገ መንግስት የተገነቡቱ ፈርሰዋል፡፡ ዩጎዝላቪያ፣ ሶቤትሕብረት... በአንጻሩ የማንነታቸውን መሰረት በሚት (ትርክትና ሥነ ተረት) ላይ ያፀኑት እስራኤላዊያን ግን ሁለት ሺህ ዘመናት ያለ ሀገር በባርነት፣ በስደት መሻገር ተችሏቸዋል፡፡ የኮሎምቢያ ጥንታዊ ሕዝቦች ኮጊዎች ምንም ተቋማዊ አስተዳደርና ሥነ-መንግስት ሳይኖራቸው ለንጽህና በመታመን ብቻ ግማሽ ምዕተ ዓመት ቅኝ ገዥዎችንና ኢምፔሪያሊስቶችን ተቋቁመው ማንነታቸው ጠብቀው ቀጥለዋል፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች የሀገረ መንግሥት ግንባታቸውን በጸረ ቅኝግዛት ትርክት ላይ ገንብተውት አሁን ከቅኝግዛት በኋላ ሌላ የጋራ ትርክት መፍጠር ተስኗቸው በመንግሥት ግልበጣና በእርስበርስ ጦርነት አዙሪት ሲዳክሩ ይታያል፡፡

ኢትዮጵያዊን ብሄረሰቦች፣ ጎሳዎችና ነገዶች በሺህ ዘመናት ፈተናዎች መካከል ጸንተው መቀጠል እንደምን ተቻለቸው? ቢሉ መልሱ በቀላሉ ስለትርክታቸው ይሆናል፡፡ ስለሕገመንግሥቱማ እንኳንስ ያኔ ዛሬም በኃይል ቢጫንባቸው እንጂ የሚያውቁት አይመስለኝም፡፡ ሀገር ግን ስለ አንድ ሰው ጥልቅ ምናብ ትጠነሰሳለች፡፡ ስለእዕላፍት ላብና ደም ትገነባለች፡፡ ስለጥቂቶች ድንቁርናና ስንፍና ልትፈርስም ትችላለች፡፡

ከበፍም እሳት መቃመስ መጽሐፍ የተወሰደ !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

በጣም ጥሩ መጽሐፍቶችን አስገብተናል !!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የገጽ ብዛት 540
B5 ሳይዝ
በታላቅ ቅናሽ
በ200 ብር ብቻ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

https://vm.tiktok.com/ZM6RHAJvd/

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ይህ መጽሐፍ ከተለመዱት የታሪክ መጽሐፍት መካከል ልዩ ከሚያደርጉት ጉዳዮች ውስጥ ይህንን በኔ ግምት ዋነኛው የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ የታሪክ ጉዞ ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር አጣምሮ ለአንባቢያን ግልፅ በሆነ ሁኔታ በማቅረቡ ነው፡፡

ደራሲያኑ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ሙያዊ አስተዋፅኦ ከማድረጋቸው ባሻገር ብዙ የምርምር ሥራዎችን አበርክተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ጋርም የጠበቀ ቁርኝነት ስለአላቸው የሀገሪቷን የፖለቲካ ውጣ ውረዶችን ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ከብዙ ዝግጅት በኋላ በጥናት ላይ የተመሰረተ ጠቃሚ ሰነድ ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡

ይህ ጽሁፍ ወጣቱ ትውልድ የአገሩን ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ እንዲረዳው የቀረበለት ስለሆነ፣ የወደፊት የኢትዮጵያን የልማት አቅጣጫ ለመተለም ስለሚያስችለው እንዲያነበው ና እንዲያወያይ በ እመክራለሁ፡፡ ከዚህ በዘለለ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ በራሳቸው የፖለቲ ካ መነጽር እያዩ በሳይንሳዊ ማስረጃ ያልተደገፈ ‹‹ታሪክን›› በማቀንቀን ትውልድን የሚያሳስቱ ‹‹ደራሲያን›› ከዚህ ጽሁፍ ግንዛቤ ሊያገኙ ይገባል እላለሁ፡፡

ዓለማየሁ ተፈራ ኤሜሬተስ ፕሮፌሰር
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

slaves), but also, we may assume, exerted some cultural influence in the north where they accounted for no small proportion of the slave population which, we may arise was by no means instantly assimilated to the locally dominant faith or faiths. The Fälaša, or Judaic Ethiopians, who constituted the smallest of the country's four religious groups, were located mainly in the north-west. Though their faith was in many ways distinct - both from other Ethiopians and from the Jews of other lands their social life had much in common with Ethiopian Orthodox Christians, with whom they shared the Ge'ez Old Testament, whose scribes often wrote out their sacred writings and whose Church schools they sometimes attended. They also had some cultural affinities with the nearby Qemant who represented an intermediary faith between Judaism and an ancient Ethiopian religion often referred to as a form of Animism.

Such immense variations of physical and human geography coupled with those of language, culture and religion, inevitably resulted in the existence within the confines of the present-day Ethiopian region of many differing customs and ways of life. There ensued much cross-fertilisation of cultures and traditions, which still requires detailed study. Any comprehensive examination of so rich, and geographically varied, a history obviously requires many detailed monographs for it would seem impossible, within the compass of one small volume such as this, to do justice to the rich variety of Ethiopia's historic social and cultural experience, either on a country- wide basis or over the time span of more than a few centuries. Further factual studies, when completed, will doubtless lead to works of greater synthesis and interpretation.

The present volume, which is planned as the first of a series dealing with various aspects of the country's varied social history, is devoted by and large to the northern and central highlands, and covers the period from early medieval times to the reign of Emperor Tewodros II which is considered a turning-point in the country's history- and serves at the same time as a point of departure for the dramatic changes that were to characterise the late nineteenth and twentieth centuries. The region under review was important in that it constituted the core of the traditional Ethiopian State, and was over the centuries to exercise no small influence on other parts of the country. The area was at the same time distinctive - and formed a cohesive entity-in that it had a unique highland, and predominantly Christian, culture. The region is moreover of special interest on account of its indigenous chronicles and hagiographies, and the many descriptions by foreign travellers, which made it, at least until the middle or second half of the nineteenth century, by far best documented part of Ethiopia. It is thus an area that can be studied over a considerable span of time. Since the northern and, central highlands in the period under review are so

palpably better documented it would be impossible to devote anything like equal coverage to other parts of the country without adopting the arbitrary, and from the scholarly point of view surely misguided policy of suppressing available data on a region for which it is available, in the interests of geographical balance.

Even with the above strictly limited geographical confines generalisation is often hazardous. It has been possible within the time and space available to consider only.

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

“ባለፉት አስርት ዓመታት የህይወት ሂደቴ ውስጥ የተማርኩት፣ የተገነዘብኩት፣የሄድኩበትናለዛሬው በነፃነቴ ልክ የሚሰፈረው፣ በነፃ ፍቃዴና ፍላጎቴ፣ በእስትንፋሴ ሙሉ የማጣጥመው የህይወት ምእራፌ ካደረሱኝ ምስጢሮች መካከል የመጀመሪያዋን ምእራፍ በዚህ መንገድ ከትቤ እንደኔ የህይወት ሂደታችሁ ግራ ላጋባችሁ፣ላንገዳገዳችሁና፣ገና አዲስ የህይወት ምእራፎቻችሁ ሙሽሮች ለሆናችሁ ሁሉ አንድ ብየ አቀረብኩላችሁ። "

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የአድዓው ጥቁር አፈር !!!
ተስፋየ ገብረ አብ
ህይወትን ምስጢር ደርሶናል !!!


በሽያጭ ላይ ነን !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

ፕሮፌሰር ደስታ መብራቱ፣ በኬሚካል፣ ኢንዱስትሪ እና አካባቢ ምህንድስና ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በስራው ዓለም፣ ከሰላሳ አራት ዓመት በላይ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ሰርተዋል። ከዚህ ውስጥ ለአስራ ሶስት አመታት በተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም (UNEP) ውስጥ የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር መሆንን ጨምሮ በልዩ ልዩ ሃላፊነት ሰርተዋል። ፕሮፌሰር ደስታ በተለይ በዘላቂነት ሳይንስ እና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ላይ ያተኮሩ በርካታ የምርምር ስራዎች አሳትመዋል። ከታህሳስ 2009 ጀምሮ፣ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ስታለንቦሽ ዩኒቨርሲቲ (Stellenbosch University) ፕሮፌሰር ሲሆኑ በአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም ያስተምራሉ፡፡

ቀደም ሲል በሃገር ውስጥ የሙያ ህይወታቸው ከሰሩባቸው መሥሪያ ቤቶች በተጨማሪ፣ የኢትዮጵያ የኬሚስትሪ ባለሙያዎች ማህበር እና የኢትዮጵያ የኬሚካል መሐንዲሶች ማህበር ፕሬዚዳንት እንዲሁም የለም ኢትዮጵያ የአካባቢ እና ልማት ማህበር መስራች ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል። ፕሮፌሰር ደስታ መብራቱ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ (African Academy of Sciences) እና በተለያዩ ሃገሮች የሚገኙ ቀደምት የሳይንስ ጥናት ተቋሞች አባል ናቸው።

azop book
December 1, 2023 2:14 PM

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የጳውሎስ ኞኞ መጽሐፍት ከቅጽ አንድ እስከ ቅጽ ስድስት ድረስ እጃችን ላይ ይገኛሉ!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"..... ሠራዊቱ 'አንበሳው' ነበር የሚላቸው ... ሠርተው የሚያሠሩ፣ሁልጊዜ ከውጊያ መሀል የሚገኙ ሞትን የናቁ፣ለሀገርና ለባንደራ መብትን ታላቅ ክብር አደርገው የሚያምኑ፣በአርአያነታቸው የወታደሮቻቸውን ወኔ እየቀሰቀሱ 'ፈፅሞ አይቻልም'  የተባሉ ግዳጆችን በድል ያጠናቀቁ፤ የእኛው አርበኛ ናቸው። . . . የሀገርን አንድነት ለመጠበቅ፣ የነበረው ፍፁም የማይበገር፣ የማይለወጥ፣ የማይሸጥ፣ የማይመነዘር ስሜት ለመረዳት የኚህን ያልተዘመረላቸውን የአንበሳው የኮለኔል
#ካሣ_ገብረማሪያም_ታሪክ እናንብ።”

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ለመፅሐፉ የተሠጠ አስተያየት

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

“በዚህ የሞከርኩት መጽሐፍ አበው ለማድረግ ሾችን (አባቶቻችን) | ያቆዩልንን የባሕረ ሐሳብ ትምህርት በትውልዳችን ቋንቋ ማቅረብ ሲሆን ዓላማዬ ፡ ለማንም የአራት መደብ የቍጥር ትምህርት ለተማረ ሰው (ከልሂቅ እስከ ደቂቅ) ባሕረ ሐሳብ የማውጣት ችሎታን ነው” (ገጽ 14)። ማስተማር

ዓመቱ፡፡ ሰ ኣዳም

“የዛሬው ትውልድ ታሪክ ሲጠቅስ ብዙ ጊዜ ከአፄ ቴዎድሮስ ወደኋላ ሲሄድ ስለማልሰማ ከመጻሕፍቱ ጋራ በመስማማት ከሳቸው በፊት ያሉትን ዘመናት ለማስተዋወቅ ብዙ ገጾች ወስጃለሁ። ኣፄ ቴዎድሮስና ተ ከ ታ ዮ ቻ ቸ ው ነ ገ ሥ ታ ት ኢትዮጵያን ከወደቀችበት እናንሣ ሲሉ አገራችን ያሸበረቀችበትና የወደቀችበት ዘመን ነበረ ማለታቸው ነው” (ገጽ 229)።

“በምዕራፍ ፭ የተመዘገበው በዓውደ ሰማዕ(ታ)ት መጀመሪያ ጀምሮ በዓመተ ምሕረት (ዓ.ም.) እና በዓመተ እግዚእ (A.D.) መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳየው (ሠንጠረዥ) … በኛ ዘመንቈጠራዎች የተመዘገበን የታሪክ ድርጊት ወደ እነሱ የዘመን ቈጠራ (ወደ ዓመተ እግዚእ A.D.)፣ በነሱ (በዓመተ እግዚእ) የዘመን ቈጠራ የተመዘገበን የታሪክ ድርጊት ወደኛ (ወደ ዓመተ ቈጠራ ምሕረት) ለማዞር ነው” የሚረዳ ነው

(ገጽ 17)።

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

መጽሐፉ ስለ መሪነት ያለንን አጠቃላይ ግንዛቤ ከማዳበሩ ባሻገር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰጡ ተዛማጅ ኮርሶችም ጥሩ ሬፈረንስ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡

ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

"ምንድነው እሱ?"

“የአዳም ፊርማ'

‹‹የአዳም ፊርማ?›› ‹‹አዎ የአዳም ፊርማ፡፡››

"አዳም መቼ ፈርሞ ያውቃልና?

"አትሳሳት! በህይወቴ ይህን ሁሉ ሁነት ሆኜ ያሳለፍሁት አንድ ሰው ስለ ፈረመ ነው፡፡ እሱም ሰው አዳም ነው። አዳም ባይፈርም ህይወት በሞት ባልጠቆረ ነበር፡፡ አዳም ባይፈርም ከገነት ጓሮ ሲዖል ባልተገነባች ነበር፡፡ አዳም ባይፈርም የህይወት ዛፍ ፍሬ ዘላለማዊ ደዌ ይዞ ባልመጣ ነበር።

እመነኝ! አዳም ስለ ፈረመ ነው ህልሜን ከእግሬ በታች ወርውሬ አስራ አንድ ዓመት ታስሬ የወጣሁት። የእሱ ፊርማ ነው ሀረጌን በድንገተኛ ሞት ነጥቋት የቆየኝ፡፡ የእሱ ፊርማ ነው ትውልዱን የኃጢአት ዓለም እስረኛ ያደረገው፡፡ በእሱ ፊርማ ነው ቁጥር የሌላቸው ደጅ የሚያንኳኩ ልቦች ግቡ ብሎ ማረፊያ የሚሰጣቸው አስተናጋጅ ያጡት፡፡ በአጠቃላይ ‹‹የአዳም ፊርማ የህይወቴን ታሪክ ሙሉ ክታብ ሸክፎ የሚይዝ ውድ ቃል ሆኖ አግኝቸዋለሁ እና ርዕሴ ይሆን ዘንድ መረጥሁት፡፡"

'ታዲያ ጽሁፉን መቼ ልትጀምር ነው?"

'ተፈጸመ ታሪክ ለመጀመር ብእር ከሚጨብጡ ከሚቀይጡ ጸሃፍት መካከል አይደለሁም፡፡"


ከመጽሐፉ የተወሰደ !!!!

Читать полностью…

ኤዞፕ መጽሐፍት

የባለቅኔው የፑሽኪን ስም ለብዙ ኢትዮጵያውያን እንግዳ አይደለም፡፡ ቢያንስ የዘር ሐረጉን ከኢትዮጵያ እንደመዘዘ ብዙዎች ዕውቀት አላቸው። አልፎ አልፎም አንዳንድ የሀገራችን ደራስያን ከሩሲያኛና ከእንግሊዝኛ ቋን ቋዎች ወደ ቋንቋችን የመለሷቸውን የተንጠባጠቡ ግጥሞቹንና ቅኔዎቹን ለማን በብ ዕድሉ አልታጣም፡፡

ታደለ ገድሌ ጸጋዬ ግን በሩቅ የምናውቀውን ፑሽኪንን እጅግ አቅርቦልን ቤተኛ እንድንሆን የባለቅኔውን ሙሉ ሥራዎች በቋንቋችን ተርጉሞ አቅርቦልና ል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት የባለቅኔው የፑሽኪን ሥራዎች ምሉዕ ናቸው፡፡ ሥራዎቹ ብቻም ሳይሆኑ የፑሽኪን የሕይወት ውጣ ውረድ ከጅማሬው እስከ ፍጻሜው በግልጽነት ቀርቧል፡፡ ክብረቱና ውድቀቱ ፣ ጀግንነቱና ሽንፈቱ እንዲሁም ፍቅሩና ጥላቻው በየግጥሞቹ መካከል በመቅረቡ ስሜትን እያማለለ፣ እያስፈገገና እያሳዘነ አንባብያንን ያጓጉላል፡፡ እያንዳንዱን ግጥም ለመጻፍ ምክንያት የሆኑት ሰበቦችም እንዲሁ በግልጽነት ቀርበዋል፡፡ አንባቢው ይህንን መጽሐፍ ለማንበብ ሲጀምር ታላቅ ባሕር ውስጥ ገብቶ እንደሚዋኝ ሲያስብ ይገባል፡፡ የደራሲው የሐሳብ ምጥቀትና የተርጓሚው የትርጉም ብቃት አንባቢው ንባቡን ሳይጨርስ እንደማያፈናፍኑት ተረድቻለሁ - በተዕይ ተርጓሚው እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋው የተካነበትን የሩሲያኛ ቋንቋና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታውን በግዕዝ ቅኔ ዕውቀቱ ላይ ደምሮ ፑሽኪን የሩቅ ዘመዳችን ብቻ ሳይሆን የቅርብ ወዳጃችን እንዲሆን ግዘፍ ነሥቶ በሥራዎቹ ሕያው እስትንፋስ ዘርቶባቸዋል። ወዳጄ ታደለ ገድሌ ጸጋዬ እኛ ወደ ፑሽኪን የተራራ ቅኔ እንድንሄድ ሳይሆን የባለ ቅኔው የቅኔ ተራራ ወደ እኛ እንዲመ ላበረከትከው የላቀ አስተዋጽኦ _ ከወንበሬ ከፍ ብዬ እብ ቤልሃለሁ:: እውነትም ተርጓሚ ይሏል እንዲህ ነው፡፡

ወዳጅህ ዳግላስ ጴጥሮስ፡፡
Azop books 12.03.16

Читать полностью…
Subscribe to a channel