ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን፥ መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 9 እትሟን ይዛ ተመልሳለች።
ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል።
ስለምታነቡን እናመሰግናለን።
/channel/Medinamagazine
በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL
https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj
ለአስተያየትዎ
medinadigitalmagazine@gmail.com
ኅዳር 2017 ዓ.ም
እጅግ የተመረጡ የፍልስፍና መጽሐፍት !!!!
✍ ኤዞፕ የእናንተው ተወዳጅ ቤተ መጻሕፍት
ጎብኙን !!!
ተደስታችኹ ትመለሳላችኹ
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
@Mesay21
@Mesay21
Wub Arege ሜሮን:
የቃላት ነገር- በሎሚ ተራ ተራ
አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ “ኤርትራዊው አስገዶም” በሚለው መጽሐፋቻው መግቢያ ላይ “ኢትዮጵያዊው ሥነ-ጽሑፍ” የሚል ርዕስ በሰጡት ጽሑፍ እንዲህ ይላሉ።
“ጸሐፊ ፈትለ ነገሩን አስፋፍቶ ለማቅረብ የቋንቋው ባለቤት ከመሆን በላይ የቃላት አመራረጥና አደራደር፤ የሰዋሰው ደንብና የአገላለጽ ስጦታ እንዲኖረው ያስፈልጋል” ይላሉ።
ስነ ግጥምና ቃላት ውላቸው የበረታ ነው። ምን የተባ ሃሳብና የመጠቀ ነጽሮት ቢኖር ለግጥም ቃላት ዋና እስትንፋስ ናቸው። በቸኩና በተሰለቹ ቃላት የተሰደሩ ግጥሞች ይቆመጭራሉ። ግጥም የሚሻውን ውበትና እንግዳ ስሜት ለመያዝ ይቸግራቸዋል።
አንድ ገጣሚ የግጥምን ምጣኔና የቋንቋን ውበት ካስመሰከረ ግጥሙን ለሃሳቡ ባይሆን እንኳን ለውበቱ ስንል ማንበባችን አይቀርም።
የቃላት ውበቱ እያሳሳቀ፣ በአደራደሩ እያስደመመ እስከ ጸባኦት ይዞን ሊጓዝ መብት አለው። ለዘወትራዊ መፍገምገም ያልዋሉ፣ በንዑድነታቸውና በእምቅነታቸው አንቱ የተባሉ ቃላትን እየከረከመ የሚጠቀም ገጣሚ እውነትም ከነፍስ ሀገር በሃለዮ ደርሷል እንላለን።
ከቃላት መረጣ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ደግሞ የቃላት አደራደር ይትበሃል ነው። ቃላትም ከተመረጡ በኋላ እንደ ልደታቸው፣ እንደ መንፈሳቸው፣ እንደ ልካቸው መደርደር አለባቸው። እንዲህ ብለን ድንጋጌ ባናወጣላቸውም በአቋቋማቸው ግን ቦታቸውን መመስከር አይገደንም። ታዲያ ይሄንነ የቃል ስደራ የተካነ ገጣሚ ሲገኝ ደግሞ ስባሄ የአባት ነው።
ሎሚ ተራ ተራ
ሎሚ ተራ ተራ የፋሲካ ጌታቸው የግጥም እስትግቡእ ናት። ለአንባቢ ከደረሰች ወር የሞላት ብላቴና ናት። ልጁም ብላቴና ነው። ሃያን ለመድፈን በአንድ የፈራ ነው። ታዲያ በዚህ እድሜው ልጅ እግር ግጥሞቹን ይዞ ሲቀርብ መንክር ብለናል።
በተለይ የቋንቋ ችሎታውና ግጥማዊ ውበቱ አንቱ የሚያስብል ነው። በወሎ ዘዬ የታሹ ቃላትን እየመረጠ ሰድሯቸዋል። መሰደር ሲባል እንዲሁ መደርደር አይደለም። እንደ ቀራጺ ጡብ መልክ እያስያዘ አስሸብርቆ አቅርቦልናል እንጂ።
በዋናነት በየስንኞቹና በየሃረጎቹ ላይ የሚያስቀምጣቸው ተመሳሳይ ድምጸት የሚሰጡ ሙዚቃዊ ቃላት የግጥሙን ሀቅም በደንብ አሳይተዋል። ቃላቶቹ በትንሽ ፊደል እየተለያዩ፣ የሚያስገመግም ድምጸት እየሰጡ ስንኝ ይገነባሉ። ልክ እንደ መንቶ ግጥም ሁለተኛውም ስንኝ ተመሳሳይ የድምጽ ርክክብ ያደርግና ዜማውን ምሉዕ ያደርገዋል።
የዚህ ጽሑፍ ዋና አላማው ለግጥሙ ትንታኔ መስጠት አይደለም። በሎሚ ተራ ተራ ላይ ያለውን የቃል አደራደር ይሁንታ መስጠት፤ እንደ ማሳያም ከግጥሞቹ ላይ ጥቂት ስንኞችን መዝዝን መመልከት እንጂ።
“ሞረሽ” በሚል ግጥም
ጠመዥ በበላ አፌ፣ ጠበጃ ሳወድስ
ጠብ እንጃ እሚል ጠፋ፣ ጠበኛዬን ሳልድስ
ጡት አስጥል ወዳጄ መንታ መንትያዬ
ዋሽንቱን አነሳ ቀን ጥሎኝ እያየ። … ገጽ 5
ይላል። በመጀመሪያው ስንኝ ላይ “ጠመዥ” ብሎ በሁለተኛው ሀረግ ላይ “ጠበጃ” የሚል ቃል ይጠቀማል። ለ “ጠበጃ” በድምጸት የሚጠጋ ቃል ሁለተኛው ስንኝ ላይ “ጠብ እንጃ” ብሎ ያመጣዋል። በዚያው ሁለተኛ ሀረግ ላይ “ጠበኛዬን” ብሎ ይጀምርና ቤት መምቻውንና ቤት መድፊያውን “ድስ” በሚሉ ሁለት ፊደላት ያደርገዋል። ይሄን ስንመለከት አጠቃላይ ስንኞቹ የዜማ ዣት የተሸከሙ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
በተመሳሳይ “አባ ኮልሼ” በሚለው ግጥም ይሄንኑ አካሄዱን ያስቀጥለዋል።
እጠጣው ያልኩት ወንዝ፣ ወዝ ወዜን ከጠጣኝ
ምንጩን ድርቅ ያናጨው እኔን ምን በወጣኝ
ንስሃም ውሃ ነው ካህን አያሳጣኝ። … ገጽ 18
እዚህ ላይ ወንዝ፣ ወዝወዜን፣ ከጠጣኝ፣ ምንጩን፣ ያናጨው፣ በወጣኝ የሚሉ ቃላት መልክና ልክ ይዘው ሲደረደሩ ከአፍ የማይጠፋ ዜማን ያረግዳሉ።
ስለ አባቱ ውዳሴ በተቀኘው “ሰው ተራ” በሚል ግጥሙ እንዲህ የሚሉ ስንኞች ይገኛሉ።
ከአባትነት ክህነት
የነፍስ ቡራኬ የልጅ ስልጣን ስጠኝ
ስልጡን ሰይጣን ሰልጧል እንዳያዳልጠኝ።… ገጽ 31
እንዲሁም “ኑሪልኝ” በሚለውና ስለ እናቱ መወድስ በቋጠራቸው ስንኞች
ሴትን ደርባባ እናት እግዜር ፈጥሮን ስልጣን
ለእግዜር እግዜር ይስጠው ያስምርለት ስልጣን
ባይሆን ማመስገኛ ቃላትን ባላጣን። …ገጽ 54
ግሸን ደርበ ከርቤ በሚለውና ለዚያች መስቀለኛ ቅዱስ ስፍራ በሚያዥጎደጉደው የቅኔ አዝመራ እንዲህ የምትል መንቶ ስንኝ ለእማኝነት መምዘዝ ይቻላል።
ቀና ቢሉ ዋርላ፣ ደፋ ቢሉ ደሴ፣ ዘንበል ቢሉ የጁ
የምድር ማማ ነሽ ደጅሽ የእግዜር ደጁ። …ገጽ 66
በተመሳሳይ በልጅ ልብናው ለታዘባት የሀገሪቱ መዲና ትዝብት አዲስ አበባ በሚል ርዕስ ባስነበበን ረዘም ያለ ግጥም ውስጥ መሰል መንቶ ስንኞች ተደጋግመው ይገኛሉ።
ሁሉ ሚኖርብሽ መኳንንትና አጤው
በላቡ ሚታጠብ መጤውና ላጤው ።…ገጽ 69
የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል
ጉድ ጉዱን ሲወልድ ገድ በገድ ያረጃል። …ገጽ 70
እዛ እሸት እያለ እዚህ ሰው ይታሻል
ወገሸሁ እንግዲህ ካንቺ ማን ያመሻል። … ገጽ 71
አሜን በይ አንቺዬ በሚለው ግጥሙ
ይልቅስ አሜን በይ፣ አሜን በይ አንቺዬ
ለሙሃባው ስወድቅ አይበጆዬን ጥዬ
ገዢን ግዢ ያደረግው ባርያ ቤቱ ይብራ
ሸረኛን ያዝልን ተንደፋርሶ ይጥራ።…ገጽ 77
እያለ ግሩም በሆነ ቋንቋው ዱዓ ያደርጋል።
ደህና ሁኝ በሚለው ግጥሙ ላይ ደሞ
ዘማች ሙቶ መጣ፣ ሟች ያልነው ገደለው
ለቀን ቀን ይውጣለት፣ ቀን ቀንን በደለው። … ገጽ 80
እያለ ይማጸናል። ብዙ ግጥሞቹን ሲጽፍ ሀገራችን በጦር ስትናጥ በልጅ እድሜው ታዝቧል። ሰው በሚባለው ፍጡር ተስፋ የቆረጠ በሚመስል አኳኋን ለቀን ራሱ ቀን ይውጣለት እንጂ እርስ በእርስ ተበዳደለ እያለ ከሰው አሻግሮ ፍርጃና ተስፋውን ቀን ላይ ያንጠለጥላል።
ይሄ መብሰክሰክ የወለደው የሚመስል ሌላም መንቶ ስንኝ እስኪ እንተራረም በሚለው ግጥሙ ላይ ይገኛል።
ሁሉም ሰው እንደሰው እኩል ነው ህግ ፊት
ሁሉም ህግ እንደ ህግ ምንድን ነው ከሰው ፊት? … ገጽ 82
ሲል ይጠይቃል። በጉልብታሞች የሚጠመዘዝን የዓለም ህግ ከሰው ፊት አቅርቦ ሊፋረደው ይከጅላል። ጸዓዳ አለምን የሚመኘው ንጹህ የልጅ ነፍሱ ያንዘረዝረዋል።
“ሰለውላዋ ሦለል” በሚለው ግጥሙ ላይ እንዲህ ይላል
ሦለል ስትል ሦለል
የመስክ ሳዱላ ዜማዋን ቀጥለው
እሷን አገኘሁኝ፣ አንጀቴን ባንጀቴ፣ ልቤን ቢሰልለው። …ገጽ 90
እያለ ያቺን የወሎ ሳዱላ ከእነ ሶለል ዜማዋ በዓይነ ህሊናችን ይስላታል። በእዚያው ግጥሙ ላይ ያቺን የሻደይ ሰለውላዋ ከልጅነት ህለሙ ጋር አጋምዶ ምኞቱን እንዲህ ሹክ ይለናል።
ሻደይ ባመት አይሁን፣ ይሁን በወር በወር
እርጅናማ እዳ ነው ልጅነት ይጠወር። …ገጽ 90
ይለናል። በዚህ ለጋ እድሜው ለሻደይ ክምንምን ሲል እርጅናን ይፈራዋል። ሰማኒያ ጎስሞት ከቤት እየዋለ በልጆቹ ከሚጠወር ሽማግሌ ይልቅ የፍንደቃው ዘመን ይጠወርለት ዘንድ ይማጸናል። የታላላቆቹን ዓለምማ አይት ታዝቦት እንደሆነ ማን ያውቃል?
“አልጋ ባልጋ” በሚለው ግጥሙ ላይ እነዚህን መንቶ ስንኞች በቃለ ተክህኖ እንዲህ ይተኩሳቸዋል።
እሰይ ሲሏት ሸርመም፣ ከንፈሯን አዝልጋ
መሳም ምሳ አድርጋው፣ ሳይፈልግ ፈልጋ። … ገጽ 97
“የህልም ቀጠሮ” በሚለው ግጥም ላይ የመጀመሪያዎቹ መንቶ ስንኞች እንዲህ ይናደፋሉ።
ብኩን ሆነ ቀልቤ ሰንበት ክራሞቴ
ሞትም ቀልቦ ጠፍቶት፣ ካልሞተልኝ ሞቴ። …ገጽ 100
እያለ ከፍጥረታችን ጋር የተጣባውን ሞታችንን ራሱ ይሞትለት ዘንድ ይማጸናል። በሁሉም ልጅ ነውና ነፍስያው ትፈቅዳለች።
ይህ መጽሐፍ
ድንቅ መጽሐፍ ኑው።
የሊቃውንትን ታሪክ ይዟል።
እባክህ የሁለተኛው ዙር ውድ ህትመት ሳያገኘው ቶሎውኑ የግል ያድርጉት።
አሁ በጥሩ ዋጋ እየተሸጠ ነው
ሰሞኑን ኑዛዜ የተሰኘ የልዮ ቶልስቶይ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፊ የ ቶልስቶይ የእድሜ የዘመኑን አጋማሽ የተገነዘበውን ስህተቶች እየነቀሰ፣ የፃፈው መጽሐፍ ነው።
ኑዛዜ ፣ እውነተኛ የህይዎት ኑዛዜ ነው።
ስለ ዓለምና የቶልስቶይ የዉጣትነት ዘመን፣
ስለ ሰው ልጅ ጠባይ ሥለ ህይወቱ ብዙ ምስቅልቅሎች ጽፏል ቶልስቶይ።
ብታነቡት መልካም ነው።
ቶልስቶይ ገጽ 86 ላይ ይህንን ይላል
[ እስኪ ዛሬም በዘመናችን ስላሉ በርካታ ሰዎች የሕይወት ዘይቤ እናስብ። ከእነዚህ ሰዎች በርካቶች ከኅሊናቸው ድንዳኔ የተነሣ፣ አኗኗራቸውን የሚገራውን የተበላሸ አስተሳሰብ ኣወንታዊ የሕይወት ፍልስፍና አድርገው ይቈጥራሉ። እነዚህ ሰዎች አስጨናቂውን የሕይወት ጥያቄ የሚያስወግዱት ማር በመላስ ነው። እኔ ከእነዚህ ሰዎች ጋራ ኅብረት ማድረግ አልችልም። እነዚህ ሰዎች እንደሚያደርጉት ኅሊናዬን የሚያደነዝዝ አሳሳች አመለካከት በጭቅላቴ ውስጥ ፈጥሬ ራሴን ማታለል አልችልም። እንደ እነዚህ ሰዎች የተንጠለጠልኹበትን ገመድ ከሚገዘግዙ ዐይጦችና ከታች ሊውጠኝ ጥርሱን አግጥጦ ከሚጠብቀኝ ዘንዶ ዐይኖቼን መንቀል አልችልም።]
መልካም ንባብ።
መሳይ
በጣም ቆየት ያሉ መጽሐፍ ቅዱሶች !!!
#1879 ዓ.ም የቁም ጽሑፍ
#1899ዓ.ም ኦኒስሞስ ንነሲብ ኦሮሚኛ ሳባ ጽሑፍ የቁም ጽሑፍ
#1936ዓ.ም የቁም ጽሑፍ
#1947ዓ.ም ሞዓ አንበሳ ዘምነገደ ይሁዳ
#1954ዓ.ም ሞአ አንበሳ ሰማኒያ አሀዱ
#1980ዓ.ም አባ ተክለ ሃይማኖት ርሥነ ሊቀ ጳጳስ ዘ ኢትዮጵያ ዘመን የታተመ ሰማኒያ አሀዱ
#2000 ዓ.ም አቡነ ጳውሎስ
#2014 ዓ.ም ግዕዝ ሰማንያ አሀዱ የታተሙ መጽሐፍ ቅዱሶች !!!
ከኤዞፕ books 0911723656 ይደውሉ
👇👇👇
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56
መጽሐፍ ለማዘዝ ሊንክ
@Mesay21
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ቅጽ 1 ቁጥር 10
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- /channel/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
The Complete Short Stories of MARK TWAIN
NOW COLLECTED FOR THE FIRST TIME. Edited with an introduction by Charles Neider
Only 1 copy
ይች መጽሐፍ የውድቀታችን ምንጭ ምን እንደሆነ የእርገታችን መሰላልም የትና እንዴት እንደሚገኝ ለማሳየት ወደ ፈረንጅ የሚነዳውን የመጥፊያ/ የማምለጫ በር ትዘጋለች። በተዘጋው የመጥፊያ በር ፈንታ ሀበሻ የማያውቀውንና ማወቅም የማይፈልገውን ሌላ አበልጻጊ በር ትከፍታለች፡፡ ያ ጠፍቶ የመገኛ የብልጽግና ቤትም ይገባበት ዘንድ የበሩ ቁልፉ ፍቃደኝነት ይባላል፡፡ ያ አበልጻጊ ቤትም አይነ ጎሊና ነው፡፡ ዓይነ ኀሊና ውስጥም ራስl self ኢትዮጵያዊነት/ ማንነት አለ:: ፍቅር መገለጫው ነው፡፡ ጥበብ ምንገዱ ነው፡፡ ስለዚህ በውበት የተሞላ ነው። ይህን ማወቅም የብልጽግና መጀመሪያ ነው:: ... ፈላጊ ራሱ ጠፍቷልና ይመለስ ዘንድ ፍቅርን ታበራለች - ይች መጽሐፍ።»
9 «ዲሞክራሲ ከሀገሩ ከምዕራቡ ዓለም ውጭ ስርቶ አያውቅም፡፡ ግን ደግሞ ሁሉም ሰው የሀገራችን ችግር የዲሞክራሲ መጥፋት ነው ይላል፡፡ ከሰላሳ ዓመት በፊት የሀገራችን ውድቀት ዲሞክራሲያዊውን ሶሻሊዝም አለመከተላችን ነበር ተባለ፡፡ ከ17 ዓመታት በኋላ ሶሻሊዝም ሲወድቅና ካፒታሊዝም መመሪያችን ነው ሲባል ደግሞ እንደገና የሀገራችን ውድቀት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ያለችግር እንዲፈስ የሚያደርገው ዲሞክራሲ ስለሌለ ነው ተባለ፡፡ ሁሉም በእንቅልፍ ልቡ የሚያወራ ይመስላል::›
የጎሳ ዛር ያረፈበት ነጂ የሚገዛው ሀገር ዜጎች ቁጡዎች፣ ተጠራጣሪዎች፣ ጥገኞች ግዴለሾች፣ ጨለምተኞች ... በገዛ ሀገራቸው የውስጥ ስደተኝነት የሚሰማቸው፣ ከሕይወትና ከዓለም የተገለሉ ... በፍርሃት ባርነት የተያዙ ... በተጻራሪ ርዕዮችና በተቃራኒ አቅጣጫዎች የሚሳሳቡ ብኩኖች የመሆን እድላቸው ከፍተኛ ነው:)
«አገልጋይ መሪ ታማኝ፣ የወደፊቱን የሚያይ፤ የተስፋ መቁረጥ እርቃንን የይቻላል እምነት የሚያጎናጽፍ የበጎ ነገር ምሳሌ ነው፡፡ አገለልጋይ መሪ ግርማው ትልቅ ነውና ሰዎች በችሎቱ ፊት በመቆም እንኳን ኃይል ያገኛሉ፡፡ እግሮቹ በድንቁርና ጨለማ የተያዙትን ሕዝባችን ከሕይወት ለዋጭ ርዕይ በሚገኝ ብርሃን ፈትቶ ዳግም ትክክለኛውን ምንገድ ያሳያል አገልጋይ መሪ:: የአገልጋይ መሪ ተልዕኮ አይሆንም አይለወጥም የተባለን፤ ከብረት የጠነከረ ችግርን በይቻላል እሳቦት ግለት በማለዘብ ቀና ማድረግ ነውO”
«ሀገራችን አስፈሪ ድህነት ውስጥ የተጠመደችው ሕዝባችን በተፈጥሮ ደደብ ስለሆነ አይደለም፡፡ እንዲያማ ቢሆን የታላቅ ሥልጣኔ ወራሾች፣ በቅኝ ግዛት ውርደት ውስጥ ያላለፈች ሀገር ባለቤቶች አንሆንም ነበር፡፡የዛሬ ተስፋ አስቆራጭ የሥራ አጥ ሰራዊት ሀገሪቱን ማጥለቅለቅ፣ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መንሰራፋት ... የአመራር እጦት ውጤት ነው::)
«ኢትዮጵያ አምላኩ መሪ ማድረግ ያለበት ሰው በድክመቱ፣ በክፋቱ፣ በአፍራሽ ባህሪው ተውጦ የሚገኝ ገንቢና እግዚአብሔራዊ ተፈጥሮ እንዳለው ማስገንዘብ ነው:: ወርቅ ከአፈር ነጥሮ እንደሚወጣ ሁሉ የሰው ልጅም ከላዩ ላይ ያለው አፍራሽ ጥቀርሻው ሲነሳ እግዚአብሔራዊ ተፈጥሮው ወለል ብሎ እንደሚታይ ... ኅብረተሰቡም ከዚህ እንደሚያተርፉ ማሳየትና ይህም ተግባራዊ እንዲሆን ማገዝ ነው የኢትዮጵያ አምላኩ መሪ ኃላፊነት::
«ሰዎች ግላዊ ፍላጎታቸውን ክኅብረተሰብ ጥቅሞችና ፍላጎቶች የሚያስታርቅ ውስጣዊ መንፈሳዊ ህግ ከሌላቸው የፈለጉትን ለማግኘት ከመዝረፍ ከማጭበርበር ከመግደል የሚመልሳቸው ነገር አይኖርም፡፡ መንፈሳዊነት በሌለበት ኅብረተሰብ ውስጥ ኅብረተሰባዊ ቅራኔዎች መራራ፣ ቶች ግዙፍ ናቸው፡፡ ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶች የምናያቸው ጨቋ ንፈሳዊ ህጎች ውጭ ከመሆናችን ጋር ቀጥታ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች ከመንፈሳዊ የተገናኙ ናቸው፡፡ ገዦችም ጉልበትን የሚያመልኩት እግዚአብሔርን ስለማያመልኩ ነው:
ከመጽሐፏ የተወሰደ
ኢትዮጵያ አምላኩ መሪ
ዛሬ ቅዳሜም አይደል !!
የምንወዳት ቅዳሜ
ትዝታችን !!
✍ ድሮድሮ ጋዜጣ ልንገዛ እንሰለፍባት ነበር።
ቅዳሜ ሲመጣ ፒያስ ሙሀሙድ ጋ የማይወጣ አልነበረም።
ማኪያቶ አዞ ፣ ፍርድ ህንፃ ላይ ቁጭ ብሎ፣ ቁልቁል ፒያሳን እያየ ጋዜጣ ያላ ነበበ አልነበረም።
አወ ቅዳሜ ትዝታችን !!!
የምንወዳት ቀን !!!
እና ምን ለማለት ነው ይህችን ልዩ የትዝታ ቀናችንን ያስታወሰኝ !!!
ቅዳሜና እንተ፣ ቅዳሜና የመጻሕፍት ማስተዋወቅህ እኮ አሁንም ይገርመኛል ሲለኝ ነበር።
ልክ ነው። ቅዳሜና መጽሐፍት ቤቶች፣ ቅዳሜና የኢትዮጵያ ጋዜጦች ልዩ ቁርኝት ነበራቸው።
ይህ ሁሉ ምን ለማለት ነው ?
ቅዳሜ ይምጣ እንጅ ልዩ ልዩ መጽሐፍት ማስተዋወቃችን በልዩ ሁኔታ ይቀጥላል ለማለት ነው።
ኤዞፕ የእናንተው ቤተ መጽሐፍት !!!!
0911723656 !!!
በልጅ እድሜው ተወራውሮት ባለፈው የቃል ጨዋታ ሌላ የግጥም ቤት መስራት ያምረዋል።
“እንካ ስላንትያ” ሲል በሰየመው ግጥሙ እንዚህ ስንኞች ይገኛሉ።
እንካ ስላንትያ
በምኔ ምንትያ
የመላ መንትያ
ወርቅ በይፋ እንጂ፣ አይውልም በጉያ
መንታ ጉድ ቢወለድ፣ በጉያ ገበያ
አፍ ከምክሜ አልዘልቀው፣ የጉድን አበያ። … ገጽ 112
ሲል እናገኘዋለን።
“መስተ-ጻርር” በሚለው ግጥም መዝጊያ ላይ እነዚህ መንቶ ስንኞች በቃል ድርደር የተዋቡ ናቸው።
አባይ ሲሾርበው፣ ለአበያ መታመን
መዳን እያደኑ፣ ላይድኑ መመነን። … ገጽ 119
እንደ መጨረሻ አብነት አንድ ልጥቀስ። የመጽሐፉ ርዕስ ለመሆን ከተመረጠውና ሎሚ ተራ ተራ የሚል ርዕስ ከሰተጠው ግጥም ውስጥ መንቶ ስንኝ ልምዘዝ።
ሎሚዬ ዛሬማ፣ ንዋይ ጉያ ገብተሽ፣ በገበያ ሸላይ
ቆርጦ በሽሬታ፣ ሽልሽ በሾተላይ። … ገጽ 122
ይላል።
ስንጠቀልለው
----------
የፋሲካው ግጥሞች በቃል ውበታቸውና በአቀራረጻቸው ግሩም የሚባሉ ናቸው። ለአንድ ገጣሚ ተቀዳሚ መሳሪያ የሆነውን የቃል ባለቤትነትን ታድሏል። ቃላትን ከማዎቅ ባሻገርም ድንቅ የሆነ ውበት እንዲጎናጸፉ በድምጸት መልካቸው መደርደሩን አበልጽጎታል። እና እነዚህን ቀዳማይ መሳሪያዎችን ታሳቢ አድርገን በዚህ ብላቴና ላይ ተስፋ ብንጥል ቃል ገደፋችሁ እንባላለን?
ፋሲካው በ ሎሚ ተራ ተራ ላይ ጥሩ ነገር አሳይቶናል። በንባብና በነጽሮት ብሎም በማሰላሰል ሲበለጽግ በአማርኛ ስነ-ግጥም ላይ አሻራውን አስቀምጦ እንደሚያልፍ ተስፋ አለን። ሎሚ ተራ ተራን ታነብቡ ዘንድ እንጋብዛለን።
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- /channel/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
ሰብአ ሰገል
✍️አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ በመጽሐፋቸው ላይ ሰብአ ሰገል 3 ነገሥታትና 2 ልዑላን ናቸው በማለት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ናቸው ይሉንና እኒህ ነገሥታት ኢትዮጵያዊ ናቸው፤ ቀለማቸው ግን ነጭ ሊኖር ይችላል። ያኢትዮጵያዊነታቸውን አይፍቅም።
ኢትዮጵያዊ ከአንድ እናትና አባት 4 አይነት ቀለም ያላቸው የተለያዩ አበባ የመሰሉ ልጆችን ይወልዳሉና ይላሉ በጥናታቸው ላይ።
✍️አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ የነገሥታቱን ስምና የትውልድ ቦታ እንዲህ በማለት ያብራሩታል።
📌1- ናሁ አዳም(ከወንድሙ ጋር) ተነሳ ከኢትዮጵያ
📌2- ራይናስ(ከወንድሙ ጋር) ከምሥር
📌3- አሕራም ከየመን
ኮከቡን ያዩት በነገሡ በ13ኛው ዕለት ሲሆን የጉዞው መሪ ከ3ቱ ኢትዮጵያውያን ውስጥ እስከ መካከለኛው ምሥራቅ ይገዛ የነበረው ናሁ አዳም ነው ይላሉ።
~ በአጠቃላይ በሰብአ ሰገል ማንነት ላይ ሁሉም ተመራማሪዎች ቢያንስ ከ3 ወይንም ከ12 አንዱ ኢትዮጵያዊ ነው በማለት ይስማማሉ።
✍️ከላይ የጠቀስናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ የትንቢተ ኢሳያስና የመዝሙረ ዳዊት አገላለጾችና አንድምታዎች በተጨማሪም ኢትዮጵያ በሥነ-ጠፈር ምርምር የተራቀቀች መሆኗ ሰብአ ሰገል ኢትዮጵያዊ ናቸው ወደሚለው ጥናት ይወስደናል።
በዚያም ሆነ በዚህ ሰብአ ሰገል ውስጥ አንዱ ወይንም ከዚያ በላይ የሆኑት ኢትዮጵያዊ ናቸው የሚለው ሃሳብ ሁሉንም ተመራማሪዎች ያስታርቃል።
👇
☑️ሰብአ ሰገል የተመለከቱት ኮከብ
ምን አይነት ነው? መቼስ ታየ? ☑️
✍️ከጠዋቱ ፀሐይ እንደወጣች ልክ ሦስት[፫] ጫማ በዘመናችን አነጋገር ከጠዋቱ 3 ሰዓት እንደሆነ ጂራቱ 13 ክንድ የሚያህል 7 ሕብረ ቀለማት ያለው በጣም የሚያምር ጂራታም ኮከብ ከምሥራቅ በኩል ወጥቶ በኢትዮጵያና በዓለም ላይ አበራ፤ ይህንን ኮከብ የሚያዩት ለማየት ከአምላካችን #ሥላሴ የተፈቀደላቸው ብቻ ናቸው። ይላሉ አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ።
✍️በተመሳሳይ የታኅሣሡ ስንክሳር “ልውጥ ኮከብ” ይለዋል፤ ይህም የሚቀያየር የሚሰወር ኮከብ ለማለት ሲሆን አንድም ሕብረ ቀለሙን ለመግለጽም ነው። ሰብአ ሰገል በመሃል ከተማ በሚገቡበት ጊዜ ኮከቡ ይሰወራቸው ነበር ይላል። ኮከቡ አንዴ ሕጻን የታቀፈች ድንግል ብላቴናን አንዴ ደግሞ ራስ፥ እጅና እግር ያለውን ሰው ይመስል ነበረ። ይህ ኮከብ የታየው ክርስቶስ ከመወለዱ ከ2 ዓመታት በፊት ነበረ፤ ይሄም ቀድሞ በቅድስት ሥላሴ ፈቃድ የተከናወነ ጎዞ መሆኑን ያመለክተናል። ምክንያቱም ከ2 ዓመት በኋላ በቤተልሔም ስለሚደርሱ ነው።
✍️ስለ ኮከቡ ምንነት በቤተክርስቲያን አስተምሕሮ መሰረት ሁሉም አንድ ወጥ ሃሳብ አላቸው፤ ‘ኮከቡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው’ የሚል። ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ኮከብ በቀን አይታይምና ኮከብ ዝቅ ብሎ እነርሱ ባሉበት ደረጃ አይጓዝም የሚል ነው። ኮከብ የተባለው በምስጢራዊ አነጋገር ነው ይላሉ መተርጉማነ መጻሕፍት።
👇
☑️የሰብአ ሰገል ጉዞ[ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም]☑️
✍️ሰብአ ሰገል ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም የሄዱት ስዊዝ ካናል ከመከፈቱ በፊት መንገድ ነበረ በዚያ ነው። ከቦታው ለመድረስም 2 ዓመት ፈጅቶባቸዋል። በትርክቶች መሰረት ሲነሱ 12 ነገሥታት ሲሆኑ ኢየሩሳሌም ግን የደረሱት 3ቱ ናቸው ይባላል፤ ምክንያቱም ስንቅ ስላለቀባቸውና ጦር ስለ ተነሳባቸው ነው ይላሉ። ይህ ግን በኢትዮጵያ መዛግብት ዘንድ ተቀባይነት የለውም።
✍️ሰብአ ሰገል ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ከተማዋ ተሸበረች እነ ሄሮድስ ደነበሩ፤ ለወረራ የመጡ መስሏቸው ነበረና ኢትዮጵያውያን ሮማውያንን ከጥንት ጀምሮ አይቀጡ ቅጣት ይቀጧቸው ነበረና። እነርሱም ለንጉሡ ልንሰግድለትና ሥጦታ ልንሰጥ መጣን ሲሉ ሄሮድስ ተደሰተ ለርሱ መስሎት ነበረና፤ ለርሱ አለመሆኑን ሲረዳ ግን ተበሳጨ ከእኔ ውጭ የይሁዳ ንጉሥ አለ እንዴ በሚል ተናደደ። እነርሱንም ንጉሡን ስታገኙት ንገሩኝ እኔም መጥቼ እንድሰግድለት አላቸው።
✍️ሰብአ ሰገል ከበረቱ በደረሱ ጊዜ ኮከቧ ቆመች[ ከላይ መልከጼዴቅ ያለውን ይመልከቱ] ወደ ውስጥም ገብተው ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስና ለእናቱ ለድንግል ማርያም ሰግደው ዮጵ ወርቅ፥ ዕጣን፥ ከርቤ፥ ቅባት፥ አክሊል፥ ዘውድ፥ በትረ መንግሥት፥ በትረ መስቀልና ሽቶ ሥጦታ አበረከቱ።
☑️ሰብአ ሰገል ከዚህ ሁሉ በኋላ አስቀድሞ የአምላክን ሰው መሆን ለድንግል ማርያም ባበሰራት በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ትእዛዝ በነፋስ ኃይል በብርሃን ሰረገላ በስውር ዓለምን ዙረው ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የአምላክን ሰው መሆን የምስራች ለኢትዮጵያ ሕዝቦች በሙሉ አበሰሩ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በመሆን ሰበኩ።
✍️ከዚህ በኋላ ዋልድባ[አርምኃ ደጋ] በመግባት ከአበው ጋር በመቀላቀል አምላክን ሲያገለግሉ ኖሩ።
😲ሰብአ ሰገል በሕይወት ይኖራል እንጂ አልሞቱም፥ ቅዱስ ገብርኤል ጌታን ዳግም እስከምታዩት ድረስ አትሞቱም ብሏቸዋልና አሁን እንደነ ነብዩ ሄኖክ፥ ቅዱስ ኤልያስ፥ ቅዱስ ያሬድ፥ ቅዱስ ነአኩቶለአብ፥ አቡነ አረጋዊ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሳን ተሰውረው ይገኛሉ።
🖐️ፔጃችንን like እና follow በማድረግ ይከታተሉን!ቤተሰብ ይሁኑ
ለውሏችኹ የሚሆን ሸጋ ነገር እነሆ
ተዘናፋ
(በታዲዮስ አዲሱ)
አጀብ!
ሳንታጀብ
ይህ በግርግር ዘመን ላይ ቆሞ የሚደነቅ ዘመነኛ ድምጽ ነው። የብቻ መንገዱን እየተመናተለ የሚገፋ ሰው ህቅታ። በሚያየው አጉል ዳንኪራ የሚሳቀቅ ብክን ነፍስ ሲቃ ነው። ሰው የመሆንን ውል ላጣን፣ እንደ ሸርጣን እየተጓተትን ለምንደማ መናኛዎች የተወረወረ የመገረም ቃል ነው።
ኖሮ ከሚታዘብ፣ ትርምስምሱን በአርምሞ ከሚመለከት ነፍስያ የሚቀዳ መባከን ነው። ቡድናዊነት እንደ ብራቅ ከሚጮህበት፣ አጀቡ፣ ወጀቡ ከሚያናፈበት ቀዬ የተገኘ ዘመነኛ የሚያስተጋባው ቃል ነው። አጀብ! ያውም ለብቻ ቆሞ።
አንድ ቀን ሳይሞላ!?
ወደ ነበረ ሆድ፣ ወደ ዛሬ ጥላ
ከነፍን
ታለፍን
እኔና ዘመኔ
ሀሳብና ህይወት፣ ሆነውብን ቅኔ፤
እነሆ ዘመን እንደ ጥላ እያለፈ ነው። ቀን ቀንን እየተካ እየተሸበለለ እልም ይላል። የሰው ልጅ እግሮች ወደ ሞት ይሰግራሉ።
ይሄ ሁሉ የሚጥመለመል ትውልድ አንድ ቀን እንኳን ኖሮ አያልፍም። አንድ ቀን ማለት ባህርይው ብዙ ነውና። በተለይ ለገጣሚማ አንድ ቀን ውሉ ብዙ ነው።
እነሆ የፀሐይ መግባትና መውጣት በቀን የተተለመ አይደለምን። ፀሐይስ ምንድን ነው ቢሉ ብርሃን አይደለምን? በብርሃን ለመመላለስ የታደለ ትውልድማ ምንኛ የበቃ፣ የነቃ ነው?
ትናንት ላይ ለመድረስ ስንባክን፣ ነበርን ለመሻገር ስንዳክር ይሄው አንዲት እለት እንኳን አልሞላንም። መክነፋችን ፣ መትመማችን፣ ከነበር ላለመሻገር መሆኑ አያስቆዝምም ወይ?
እንደ ዋዛ ያለፍነው እልፍ ነው። ከነገ ለመድረስ ስንንጠራራ ከትናንት ጥላ አንዲት ጋት አልተሻገርንም። ዘመን እንደ ጥላ እያለፈ፣ ጊዜ እንደ አቡጀዲ እየተተረተረ እንዴት ሰው ነገን ማየት ያቅተዋል? እንዴት ሰው ብርሃን መመልከት ይከብደዋል?
አጀብ!
የግርንቢጥ
ሰርክ በተቃርኖ
ማን ልቡን ይሰጣል፣ በዋጋ ተምኖ?
አጀብ! ይገርማል እናንትዬ። የሰርክ መባከናችን አያሳዝንም፣ አያስገርምም ወይ? ነገራቸን ሁሉ የግርንቢጥ መሆኑ ምንኛ ያንግበግባል? ልብ ቦታዋ የት ነው? ቅንነት፣ ንጽህና አይደለምን? እሱን የንጹህ ነፍስ አድባርስ እንዴት በዘመን ዋጋ ይተምንታል? ዘመንስ ዋጋው ምን ያህል ነው? የትውልድ ቁዘማ ለልብ ይደርሳልን?
እነሆ መቃቃራችን ለከት የለውም። ጨለማው ያስፈራል። ጭካኔው ያስደነብራል። ልብ አልባ ሰው መሆን ይገማሸራል። ሰውነት ያለ ልብ ምንድን ነው? ልብ የአስተውሎት ሁሉ አድባር አይደለምን? ታዲያ ሰው መሆንን፣ አስተውሎትን የተነጠቀ ዘመን ምን ይባላል? ልብን በዲናር መዝኖ ለሚንከላወስ ድንጉጥ ዘመን ማርከሻው ምንድን ነው? በጨለማ የተሰነገ ልቡን አቅፎ ለየብቻው ለሚርበተበት ትውልድ ዘመንስ ዋጋው ምን ያህል ነው?
እንገዛ ነበር
እኛም ባገር ዋጋ፣ ልብን ከሥጋ እኩል
ቃል ያጠፋውን ስም፣ ላይስቅለን ነገር ከምንኮለኩል።
(አቡዬን)
(አያምንምና ቀድሞም ያልካለ፣ ገጽ 16)
ይህ ዘመነኛ ገጣሚ የነፍሱ ውል ያስጨንቀዋል። ሰው የመሆን መማሰን መንፈሱን ሰቅዞ ይዞታል። ዘመኑን ለመሸሽ የሚንደረደር ይመስላል። ከሰው ልጆች አጉል እብደት ለመነጠል ይከጅለዋል።
ይሄን የጅምላ ስካር ይጸየፋል። ልብ እንደ ግዘፍ አካል በልባችን የምንገዛው ንብረታችን ነበር ይለናል። ከልብ መታመናችን ባመንነው ልክ ነው። እነደ በረሀ አበባ ተስፋቸን በንጽህና ላይ ነበር። እንደ ሰማይ ወፎች ልባችንን ላመንነው ሰጥተን የምንቀዝፍ ቀዘባዎች ነበርን ይለናል። ልባችንን አስይዘን ልብን አፍሰን እንኖር ነበር እያለን ነው።
ወደዚህ ዘመን ይወረወራል። የመሆን ሁሉ ውል የሆነውን ቃል ያጠፋውን "ሰው" የሚል ስም ወዲያ ጥለን ብንኮለኩለው ወዴት መድረሻ አለንና እያለን አይደለም ወይ።
ቃል ተሽሮ ሰው መሆነ የታል። ቃል ተሽሮ ከልብ ሀገር መድረስ የት አለ?
----------
ብቻ "አያምንምና ቀድሞም ያልካደ" የኮራ፣ የተጀነነ የግጥም እስትግቡእ ነው። ለነፍስ የሚደርሱ፣ ዲበ አካላዊ ጥያቄዎችን ሳይቀር በኩራት የሚሞግቱ፣ ነፍስያን የሚያፋትጉ፣ ውበትን፣ ፍቅርን፣ መናፈቅን፣ ቁዘማን ሁሉ የሚፈት ብዙ ግጥሞች አሉት። ግጥማዊ ቁመናውም ያማረ ነው።
በሙሉ ግጥሞች ላይ ሰፋ ያለ ዳሰሳ እሰራለሁ የሚል ተስፋ አለኝ። ያው ግጥም አንድ ዙር ተነብቦ ልቡን አይሰጥምና መደጋገም ስላለበት ቆየት እላለሁ እንጂ።
አንድ ስራ ከወጣ በኋላ የሳምንት ሆሆታ ይደረግና "ጨዋታው ፈረሰ ዐባይ ደፈረሰ" እንደሚሉ ህጻናት በትነው መሄዳችን ቢያሳዝነኝ፤ በመሐል ለማስታወስ መምጣቴ እንጂ የታዲዮስ ስራዎች ከዚህ በላይ ሊባልላቸው ይገባል። ግና ምን ያደርጋል በዚህ ዘመንና፣ ከእኛው መሐል ተገኘ። የእኛን ነገር ደሞ የምታውቁት ነው።
ብቻ መጽሐፏ ትነበብ!
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
................
ሰሞኑን ረፍት ለማድረግ አሰቤ ትንሽ ቀናትን በቤት ውስጥ አሳለፍኩ። ትንሽ ከወከባውና ከእሩጫው ገለል ለማለት ነበር።
ቤት ቁጭ ስትል ምንያህል መቅበዝበዝ እንዳለው ብረዳም ፣ ዝም ብሎ ቁጭ ማለት አልፈቀድኩም። ሁለት ውብ መጽሐፍት እጀ ላይ ነበሩ።
፩. ሊዮ ቶልስቶይ ኑዛዜና
፪ the alchemy of happiness የፋርስ ፈላስፋ ገዛሊ መጽሐፍ በአሮን ገዙ የተተረጎመው የደስታ ቅመም የተሰኘው ነበሩ።
በእውነቱ ሁለቱንም መጽሐፍት ወጣቶች ቢያነቧቸው ይመከራል። በገዛሊ መጽሐፍ ውስጥ ለድፍን 6 ወራት ያሳለፍኳቸውን ከባድ ጊዜወች የፈውስ ቅመም ነው የሆነልኝ።
ስለ አልልም ጥናት ብዙ ሊቃውንት ጽፈዋል። ይገዛል የደስታ ቅመም the alchemy of happiness ግን ይለያል፣ ሌላኛው አለም አልኬሚ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተርጓሚውን አቅም በደንብ አይቻለው። ለመተርጎም አስቸጋሪ የሆኑትን ፍልስፍናወች ወደ አማርኛ መልሶ ያዋቀረበት ችሎታ እጅግ ማራኪ ነው።
ደግሜ እላችኋለው በብዙ የምታተርፉበት መጽሐፍ ታትሟል።
የኣንድን ቁስ ኣካል በተለይም እንደ እርሳስ (lead) ያሉ ተራ ብረት ነክ ቁሶችን ወደ ወርቅ ለመቀየር የሚደረግ ሙከራ፣ ወይም ደግሞ የከበሩ ማዕድናትን የተለያየ ዘዴን በመጠቀም ለመፍጠር የሚደረግ ሙከራና ተግባር ከመካከለኛው ክፍለዘመን ጀምሮ “ኣልኬሚ" በመባል ይጥጠራ እንደነበር ይነገራል:: ይኽ ቃል ለመጀመርያ ጊዜ በኣጠራር ደረጃ በኣስራ ሁለተኛው ክፍለዘመን ኣካባቢ በኣውሮፓ ላይ ብቅ ያለ ቢኾንም፣ምናልባትም የዓረብኛ ወይም የጥንታዊ ግብጽ ሥርወ ቃላዊ መሠረት ሊኖረው እንደሚችል ይገመታል::
የኣልኬሚስት ወይም የቀማሚ ዋና ትኩረትም “ዕብነ ፈላስፋን" (The philoso- pher's stone) ለማግኘት ሲኾን ፣ ይኽ ቁስ ብረት ነክ ቁሶችን ወደ ወርቅ ከመቀየር ባልለፈ የሕይወት ውንንም (Elixir of life) ለመቀመምና ለመፍጠር እንደሚያስችል ቀማምያኑ ያምናሉ:: ከዚህም በላይ “ዕብነ ፈላስፋ" በመባል የሚጠራውን ቁስ እጁ ውስጥ ያስገባ ሰው የፍጽምና ደረጃ፣ (perfection) ግልጸትና (enlightment) ሠማያዊ ቡራኬ (heavenly bliss) ላይ እንደሚደርስም ይነገራል::
ፓራሴልሰስ (Paracelsus) በመባል የሚታወቀውና በኣስራ ስድስተኛው ክፍለዘመን ኣካባቢ እንደኖረ የሚነገርለት ስዊዘርላንዳዊ ቀማሚ፣ ይኽ ምሥጢራዊ ቁስ እስካሁን ያልተገኘ እንደኾነና ከተገኘ ግን ማንኛውም ነገሮች ከእርሱ ሊፈጥጠሩ እንደሚችሉ ያስባል:: ይኽ ቁስ ምናልባትም "ራዲየም" (radium) ሊኾን ይችላል ብለው የገመቱም ኣልጠፉም:: ምክንያቱም ይኽ ጨረር የመጠነ ቁስን ቅርጽ (atomic structure) በመለወጥ ከቀድሞ ተፈጥሮው ሊቀይረው ይችላል ተብሎ ይታሰባልና ነው::
በቅርቡ ያለ ኣልኬሚያዊ ወይም የነገረ ቅመማ እሳቤን ስንመለከት ደግሞ በዋናነት ተራ ብረቶችን ወደ ወርቅ የመቀየሩ ዓላማ እንዳለ ኾኖ፡ የሰው ኣካል፣ ጤናና ከተፈጥሮ ጋር ያለው ስምምነት (harmony) የበለጠ ትኩረት ሊያገኝ ችሏል:: ይኽም የሰው ማንነት ራሱ በቀመራዊ የቅመማ ልምምድ ውስጥ በማለፍ ወደ ከፍታ ሊቅቀየር የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ በመታመኑ ነው::
በኺደት እንደምናየው ገዛሊ ደግሞ በተቃራኒው ይኼንን ውድ የኾነ ቁስ በመፈለግ ኣትባዝኑ ይሉናል፤ የዚህ ቅመማ ንጥረ ነገር የሚገኘው በነቢያት ኣስተምህሮ ውስጥ እንደኾነና ከዚህ ውጭ የሚፈልገው ሰው ግን የከስሰረ ሰው ነው ይሉናል
ገዛሊ ሲጽፉ "ጌታ ስለዚህ ቅመማ ኣሠራር ለእያንዳንዱ ሰው ለማስተማር ኣንድ መቶ ሃያ ኣራት ሺ የሚኾኑ ነቢያትን ወደ ምድር ላከ:: ትምህርታቸው የነበረውም የልብ ማቅለጫ የኾነውን ተዓቅቦን(abstinence) በመያዝ ከተራ መዳበነት (bas- er quality) እንዴት መንጻት ወይም መጥራት እንደሚቻል ለማስተማር ነው:: ይኽም ቅመም በግልጽ ኣነጋገር ዓለማዊነትን ትቶ ወደ ፈጣሪ መምመለስ ነው ተብሎ ሊወስሰድ ይችላል" ይላሉ::
የደስታ ቅመም ተብሎ የተሰየመው ይኽ የትርጉም ሥራ የተመለሰው The Al- chemy of Happiness ተብሎ ከሚታወቀው የክላውድ ፊልድ (Claud Field) የትርጉም ሥራ ላይ ነው:: ክላውድ ፊልድ እ . ኤ . ኣ በ1910 ዓ.ም ኪሚያ ১৭৭৮১ (The Alchemy of Happiness). ከፋርስ የተተረጐመውን የኡርዱ ኪታብ በመጠቀምና፥ ሙሓመድ ሙስጠፋ ኣን ናዋሊ ወደ ቱርክ ልሳን የተረጐመውን የእንግሊዝኛ ንባቦች (paraphrase) በመጥጠቀም የዚህን መጽሓፍ ኣጠር ያለ የትርጉም ኪታብ (abridged translation) ለማሳተም ችለው ነበር::
✍ የ መ ካ ከ ለ ኛ ው ዘ መ ን
የኢትዮጵያ ታሪክ
ከዓፄ ይኲኖ እምላክ – ዓፄ ሱስንዮስ
📚📚📚የሰለሞናዋው ሥርዉ መንግሥት አነሳሥና ውድቀት በቀይ ባሕር ክልል የሙስሊሙና የዕውሮጳ ፋክክር ከ12 70 እስከ 16 32
ደራሲ - ሞርደኻይ አቢር
ተርጓሚ - ማውሮ አዛሪዮስ
በኢኮኖሚክስ BA
በውጭ ቋንቋዎች ጥናት BA
በበሳል አማርኛ በጥሩ የአተረጓጎም ዘይቤ የተተረጎመ።
ተርጓሚው በብዕር ሥሙ ከ5 በላይ ጋዜጦችን አርትኦት በማድረግ የረጅም ዘመናት ልምድ ያለውና ከ10. በላይ መጥሐፍት ያሉት ተርጓሚ ነው
በ250 biir ብቻ
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ቅጽ 1 ቁጥር 10
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- /channel/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ የከፍተኛ ትምህርት መቋቋምና መስፋፋት ጉዞ በኢትዮጵያ
የተሰኘው መጽሐፍ ትንሽ ኮፒዎች እጃችን ላይ !!!!
በዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ ተዘጋጅቶ በአሜሪካን ሀገር ታትሟል።
A landmark new biography that presents the man behind the many myths.
Napoleon arouses more passionate and violently conflicting feelings than any other figure in history. Was he a god-like genius, a Romantic avatar, a megalomaniac monster, a compulsive warmonger or just a nasty little dictator?
In his magnificent new study the first in English to go back to original European sources - Adam Zamoyski shows that he was none of these. Napoleon was a brilliant tactician but a poor strategist, responsible for the worst disaster in military history.
A man of boundless ambition, he was also deeply insecure. He could be selfish and violent, but also kind and generous. Callous yet sensitive, ruthless but not cruel, the reviled emperor was as creative as he was destructive.
Based on primary sources in many European languages and beautifully illustrated with portraits made from life, this biography dives deep to examine how Napoleone Buonaparte, the boy from Corsica, became 'Napoleon': how he achieved what he did, and brought about his own undoing.
'FRESH, NUANCED, BEAUTIFULLY WRITTEN, GRIPPING'
Simon Sebag Montefiore
'OUTSTANDING' New York Review of Books
'MAGNIFICENT'
Economist
እሱ ባለው በለጠ።
የገሀነም ደጆች የተሰኝ መጽሐፍ እንዳስነበበን ይታወቃል።
ነገር ግን በ1997 ዓ.ም ሌላ ኢትዮጵያ አምላኩ መሪ የተሰኝፕ መጽሐፍ እንደነበረውስ ያውቃሉ።
ብዙ ለስርጭት የበቃ መጽሐፍ አደለም።
5 ቅጅወች አግኝተናል።