bahir_dar_university | Unsorted

Telegram-канал bahir_dar_university - Bahir Dar University,Ethiopia

21305

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses! www.bdu.edu.et

Subscribe to a channel

Bahir Dar University,Ethiopia

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለህግ ባለሙያዎቹ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማእከል ከዩኒቨርሲቲው የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለህግ ባለሙያዎች ያዘጋጀው የሁለት ቀን ስልጠና  ተጀመረ።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ እንደገለጹት፤ ስልጠናው የባለሙያዎችን የስራ አፈጻጸም ክፍተት ለመሙላትና የተሻለ የዜጎች አገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። "ስልጠናው መሰረታዊ ከመሆኑም ባለፈ፣ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን አንጋፋ የህግ ባለሙያዎች በመጋበዝ የልምድ ልውውጥ እንዲደረግበት ታቅዷል" ያሉት አቶ ወርቁ፣ ሰልጣኞች በቀጣይነት ለሌሎች መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች እውቀታቸውን እንዲያካፍሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የህግ አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ ተመስገን ሲሳይ በበኩላቸው፣ ስልጠናው በተለይ በቅርቡ የተቀጠሩ አዳዲስ ሰራተኞች ተገቢውን እውቀት እንዲጨብጡና ነባር ሰራተኞችም አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
የስልጠናው ዋና ዋና ትኩረቶች የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግና፣የውል ህግ እና ግንባታ፡  በተለይም ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ያሉ በርካታ የግንባታ ስራዎችን ተከትሎ የሚነሱ የህግ ክርክሮችንና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ግንዛቤ በግንባታ ህግ ዙሪያ እንደሚሰጥ የህግ አገልግሎት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። አክለውም ይህ ስልጠና ዩኒቨርሲቲው በህግ አገልግሎት ዘርፍ ያለውን ተወዳዳሪነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከጀመራቸው ተከታታይ ስልጠናዎች መካከል የመጀመሪያው መሆኑንም ገልጸዋል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የሙዝ ችግኝ ልማት ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተገለጸ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአረንጓዴ ልማት ሥራዎቹ ጎን ለጎን በዋናው ግቢ፣ በዘንዘልማና በይባብ ግቢዎች የጀመረው የሙዝ ችግኝ ተከላ የሚጨበጥ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አስታወቀ።
በዩኒቨርሲቲው የእንግሊዝኛ ትምህርት ክፍል መምህርና የደንገልና ሙዝ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት ንብረት አስራደ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል የተጀመረው የደንገል ችግኝ ልማት ከተማውን ማዳረስ ከመቻሉም በላይ ማህበረሰቡ በራሱ አልምቶና ተንክብክቦ ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።
ከ2016 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የተከናወነው የሙዝ ችግኝ ተከላም አሁን ላይ የሚጨበጥ ውጤት እያሳየ እንደሚገኝና ፕሮጀክቱ በዩኒቨርሲቲው ግቢዎች ብቻ ሳይወሰን፣ በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚገኙ አትክልተኞችን በማሳተፍ የከተማዋን አየር ንብረትና አፈር የተላመደ የሙዝ ልማት እንዲስፋፋ እየተሰራ መሆኑን አስተባባሪው ገልጸዋል።

ዶ/ር ንብረት አክለውም ፕሮጀክቱ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑንና ለልማቱ ተነሳሽነት ላላቸው 175 የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የሙዝ ችግኝ በመስጠት በአንድ ዓመት ውስጥ የሚታይ የተግባር ለውጥ መመዝገቡ እንዲሁም በአማራ ክልል ያለውን ሰፊ የልማት አቅም በመጠቀም፣ በተለይም እንደ ፍኖተ ሰላም፣ ሜጫ እና ወረታ ባሉ ቆላማ አካባቢዎች የሙዝ ልማትን በማስፋፋት በምግብ ራስን ለመቻል ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ይህ ተነሳሽነት የአካባቢ ጥበቃን ከምግብ ዋስትና ጋር በማቀናጀት ለከተማ ግብርና ተምሳሌት የሚሆን ተግባር መሆኑ ተመላክቷል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበርን ለማጠናከር እንደሚሠራ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በቅርቡ አዲስ ስራ አስፈጻሚ በማቋቋም የዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ደመላሽ መንግሥቱ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ዶ/ር መንገሻ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የራሳቸው ማኅበር ስራ አስፈጻሚ በአዲስ መልክ መደራጀቱን በማድነቅ፤ ማኅበሩ ለሀገርና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚጠበቅበትን ጠቃሚ ሚና እንዲወጣ እንዲሁም ማኅበሩ ይበልጥ ሊጠናከር ስለሚገባባቸው ሁኔታዎች መክረዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዲያቆን ውቤ እንግዳው በበኩላቸው፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአገር አቀፉ ማኅበር ውስጥ የዋና ጸሐፊነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር መንገሻ አየነ ማኅበሩ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚያስተምሩና የሚመራመሩ መምህራንን፣ ተመራማሪዎችንና ፕሮፌሰሮችን በአባልነት ያቀፈ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች የላቀ ሙያዊ አበርክቶ ለማድረግ አቅዶ መሥራት እንዳለበት መክረዋል። አክለውም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበር (ኢዩመማ) ለሀገር ዕድገት፣ ለዩኒቨርሲቲዎች ራስ-ገዝ (Autonomy) እንቅስቃሴና ለመምህራን ሁለንተናዊ ሕይወት መሻሻል ትልቅ ፋይዳ ያለው ተቋም በመሆኑ በጥንካሬ ሊመራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማኅበሩ አገራዊ ተልዕኮውን እንዲወጣ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን ክብርና ድርሻ በማስጠበቅ ረገድ የአስተባባሪነት ሚናውን እንዲያጠናክር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግና አብሮ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል።
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደመላሽ መንግሥቱ በቆይታቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን የሥራ እንቅስቃሴና የግቢዎቹን ወቅታዊ ሁኔታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

https://euraxess.ec.europa.eu/worldwide/africa/events/horizon-europe-info-day-and-grant-writing-workshop-bahir-dar-university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 06/04/2018 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለ College of Business and Economics Dean ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ Dean for College of Business and Economics
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ታህሳስ 06 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

BDU Establishes Advanced Technology Partnership with Russia

BDU, ADDIS ABABA (Late Post) – Bahir Dar University (BDU) is seeking to substantially enhance its international collaborations following a high-level meeting at the recent Russian Culture Day in Addis Ababa. The focus is on critical and emerging technological sectors.

Dr. Mengesha Ayene, President of Bahir Dar University, delivered a keynote speech at the event, emphasizing the longstanding bilateral relationship between Ethiopia and Russia and advocating for its expansion into strategic, high-impact areas.

President Dr. Mengesha Ayene specifically identified four vital high-tech fields with significant potential for collaboration, which are integral to Ethiopia's national development plans and BDU's capacity-building initiatives: Data Science and Cyber Security, essential for the country's digital transformation and safeguarding critical infrastructure; Aerospace Engineering, a fundamental area for advancing technological innovation and research; and Nuclear Engineering, which promotes energy independence and supports advanced scientific exploration.

Dr. Mengesha Ayene stated, “Ongoing cooperation in these fields is imperative for enhancing BDU's capabilities and directly contributing to Ethiopia's developmental objectives.”

Following the cultural exhibition, a high-level Russian delegation engaged in constructive discussions with the BDU team. The deliberations focused on establishing concrete, impactful partnerships with significant influence, including collaborative research and innovation projects, student and staff exchange programs, and joint PhD initiatives aimed at developing high-level national expertise.

The meeting concluded with a mutual consensus to develop a Memorandum of Understanding (MoU) to formally establish and govern the partnership with prominent Russian universities, representing a significant milestone in BDU's strategic internationalization efforts. Dr. Mengesha Ayene expressed sincere appreciation for the Russian delegation's invitation and facilitation, underscoring the success of the fruitful discussions.

Bahir Dar University, one of Ethiopia's largest institutions, is actively dedicated to enhancing its capacity through global partnerships. The historical friendship between Russia (formerly the USSR) and Ethiopia extends over more than a century. Notably, the former USSR played a pivotal role in founding Bahir Dar University and establishing the current Bahir Dar Institute of Technology. The university's main library, Jan Moskov, bears the name in recognition of this historical connection.

Russian Foreign Ministry - МИД России
Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University, Ethiopia
Ministry of Education Ethiopia

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

A Day Remained!!!

Dear Bahir Dar University, PTI & BDTC Former Graduates,

We request you to participate in the Alumni Engagement Survey that will be closed tomorrow on Friday, 12th December 12:00 noon. Your input is essential in helping us strengthen alumni relations, improve programs, and build a lasting legacy of impact.

Please click the link below to complete the survey:

Survey Link:  https://srvy.pro/F685N4R

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የነፃ ትምህርት ዕድል (Scholarship) ማስታወቂያ
የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የትምህርት ኮሌጅ በኖርዌይ የልማትና ትብብር ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ባስጀመራቸው በስነ ትምህርት ማስትሬት ዲግሪ በሒሳብ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Mathematics) እና በስነ ትምህርት ማስትሬት ዲግሪ በሳይንስ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Science Subjects) ፕሮግራሞች ከየካቲት 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የነፃ ትምህርት ዕድል አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡
አመልካቾች ፡-
1.  የሁለተኛ ዲግሪ ለመማር በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test) ተፈትነው ማለፍ ይኖርባቸዋል፡፡ 
2.  በባዮሎጅ፣ በኬሚስትሪ፣ በፊዚክስ እና በሂሳብ ትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
3.  ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ማመልከት ይችላሉ፡፡
4.  የማስተማር ልምድ ያላቸው አመልካቾች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
5.  በፕሮግራሞቹ ተቀባይነት ለሚያገኙ አመልካቾች የነፃ ትምህርት ዕድሉ በዋናነት የሚሸፍነው ለዩኒቨርስቲው የሚከፈለውን የትምህርት ክፍያ (Tuition fee) እና የምርምር ገንዘብን ሲሆን መጠነኛ የሆነ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብም ይታሰብላቸዋል፡፡
6.  አመልካቾች ዩኒቨርስቲው ለ2018 2ኛ ሴሚስተር ለሚያወጣው የትምህርት ጥሪ ማስታወቂያ የማመልከቻ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማመልከቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፤ ትምህርት ኮሌጅ

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Scholarship Opportunity

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

CALLING ALL BAHIR DAR UNIVERSITY ALUMNI!

​You are invited to participate in the Alumni Engagement Survey. Your input is essential to help us strengthen our community and shape the future of BDU alumni relations.

​WHY PARTICIPATE?
​Your feedback directly helps us:
​✅ Strengthen Alumni Relations
​✅ Improve Programs & Events
​✅ Shape Future Initiatives
​✅ Build a Lasting Legacy of Impact


​⚠️ DEADLINE CLOSING SOON! ⚠️
​SURVEY CLOSES: DECEMBER 12TH AT 12:00 NOON

​► CLICK HERE TO TAKE THE SURVEY ◄
https://srvy.pro/F685N4R
​Thank you for contributing to the growth of your alumni community.

​With Appreciation,
Tamiru Delelegn
Alumni Affairs Coordinator, Bahir Dar University

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 25/03/2018 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት  ለ School of Earth Sciences ዲን ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡   ለ School of Earth Sciences  ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ማእረግ/ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ህዳር 25 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

CALL FOR PAPER

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ከታላቁ ዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ታላላቅ ተግባራት የሚጠበቁ ናቸው

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የልማትና በጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ከታላቁ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታላላቅና በጎ ተግባራት ሁሌም የሚጠበቁ ናቸው። በዚሁ መሠረት፣ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ባስተባበረው ዘመቻ በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች የደም ልገሳና የግቢ ጽዳት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በዘመቻው የዩኒቨርሲቲያችን ክበባትና ማኅበራት ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሆነዋል።

በዛሬው የቅዳሜ(ሕዳር 20/2018ዓ/ም) ውሎ 🩸 የደም ልገሳ ዘመቻ እና የጽዳት ሥራዎች "ደም ያስተሳስረናል" በሚል መሪ ቃል በሠላም እና በፔዳ ግቢዎች የደም ልገሳ መርሃ ግብር ሲካሄድ ውሏል። በተመሳሳይ በግልገል ዓባይ(CoBE) ግቢ ደግሞ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል። በሁሉም ግቢዎች የጽዳትና የወባ መራቢያ ቦታዎችን የማፋሰስ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሙያ ማኅበራት በተጨማሪ በበጎ አድራጎት ክበባት አማካኝነት በጎ ተጽዕኖ በመፍጠር የዩኒቨርሲቲያችንን መልካም አምባሳደርነት በተግባር እያረጋገጡ ይገኛሉ። የደም ልገሳ፣ የግቢ ጽዳት እና ለተቸገሩ የማልበስ በጎ ተግባራት በቀጣይነትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
የየግቢው ተማሪዎች ህብረት አመራሮች (በፔዳ፣ በፖሊ፣ በጥበበ ግዮን፣ በሠላም፣ በዘንዘልማ፣ በግሽዓባይ፣ በግልገል ዓባይ/CoBE ግቢዎች) ከዩኒቨርሲቲው የውስጥ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ተግባራቸውን ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደም ልገሳ ሳምንት
BDU BLOOD DONATION WEEK
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደም ልገሳ ሳምንት መካሄድ ጀመረ!!
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደም ልገሳ ሳምንት ከህዳር 20-29/2018 ዓ/ም ድረስ በሁሉም ግቢዎች ይካሄዳል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ደም በመለገስ የበጎ ተግባር አድራጎቱን እንዲገልጽ እንጠይቃለን፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመተባበር የሚከናወን ሲሆን የባህር ዳር ደም ባንክ ከየግቢዎች ተማሪ ህብረት አመራሮች ጋር ፣ የተማሪዎች ክበባት ጋር በመሆን ደም ልገሳ ሳምንቱን የሚመሩት ይሆናል፡፡ ደም በመለገስ ደም ለሚፈልጉ ወደገኖቻችን እንድረስ!

የደም ልገሳ የሚካሄድባቸው ቀናትና ግቢዎች
ዋና ግቢ፡ 20-21/03/2018ዓ/ም
ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፡ 21/03/2018ዓ/ም
ሰላም፡ 23-25/03/2018ዓ/ም
ፖሊ ፡ 27-28/03/2018ዓ/ም
ግሽ ዓባይ፡ 27/03/2018ዓ/ም
ጥበበ ግዮን፡ 20-21/03/2018ዓ/ም
ዘንዘልማ፡ 28/03/2018ዓ/ም

ደም ያስተሳስረናል!
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ!
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Huge congratulations to Dr. Amare Kasaw on this remarkable achievement!

Leading the Technical Working Group to deliver these six major outputs—including the BTIC Directive and Standards—is a massive contribution to the Ethiopian higher education innovation ecosystem.

​As your home institution, Bahir Dar University is incredibly proud of your leadership and the technical rigor you and your team have demonstrated.

We look forward to seeing the impact of these documents across all HEIs.
Well done!

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህራን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ እና ማሪታይም ኮሌጅ ጋር የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ እና ማሪታይምኮሌጅ በመገኘት የልምድ ልውውጥ እና የመስክ ምልከታ አደረጉ። በጉብኝቱ ወቅት የሁለቱ ተቋማት መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በሰው ኃይል ልማት፣ በቁሳቁስ አቅርቦት እና በአስተዳደራዊ መዋቅሮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
የልዑካን ቡድኑ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ደረጃቸውን የጠበቁ የቤተሙከራ መሣሪያዎችንና የምርምር ማዕከላትን የጎበኘ ሲሆን፣ በተለይም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርገው የዋሸራ ምርምር ማዕከል የሥራ እንቅስቃሴ የልዑካን ቡድኑን ትኩረት ስቧል።
የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ እና ማሪታይምኮሌጅ ዲን የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሀኑ አሳየ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ለመስራት እና እርስ በእርስ ለመተዋወቅና አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ፣የተለያዩ የቤተሙከራ መሳሪያዎች በጋራ መጠቀም እንዲሁም ለማህበረሰብ እድገት የሚያገለግሉ ቴክኖሎጂዎችን በጋራ መስራት ጥቅሙ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል ።
የሀረማያ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ስለሽ እንደገለጹት በጉብኝቱ ያዩት እና ትኩረታቸውን የሳበው ደረጃቸውን የጠበቁ የቤተሙከራ መሳሪያዎች እና አጠቃቀማቸው ትልቅ ተሞክሮ የቀሰሙበት እንደሆነ ገልጸው ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ለመሰራት መስማማታቸው የአቅም ውስንነትን ለመቅረፍ ፣ፕሮጀክት በመክፈት የመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ እንዲሆን ፣ለተማሪዎች ልውውጥ ፣ለማህበረሰብ እድገት ፣ለሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የማማከር አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ስምምነቱን ለማጠናከርም በሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች በኩል ኮሚቴ ተቋቁሞ የጋራ ስምምነት"MOU" እንደሚፈራረሙ ገለጸዋል፡፡

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 10/04/2018 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ (በድጋሜ የወጣ)
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት  ለ School of Earth Sciences ዲን ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም በወጣው ማስታወቂያ በቂ አመልካች ባለመገኘቱ በድጋሜ ማውጣት ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡   ለ School of Earth Sciences  ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ማእረግ/ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ታህሳስ 10 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና ፕላን ኢንተርናሽናል 16 ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን አሰልጥነው አስመረቁ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ15 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የስራ ፈጠራ ስልጠና በማጠናቀቅ ለወጣት ሰልጣኞች የእውቅና መርሀ ግብር አከናወነ።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በገላ፣ ልብስ ፣ ፈሳሽ ላቫ ፣ የእጅ መታጠቢያ፣ የዕቃ፣ የዱቄት ሳሙና እና በመዋቢያ ምርቶች ከሰቆጣ፣ ላሊበላ እና ባሕር ዳር  ለተመለመሉ 16 ሰልጣኞች ባለፉት 15 ቀናት ላሰለጠናቸው ስራ ፈጣሪ ወጣቶች እውቅና የሚሰጥበት መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን በአውደ ጥናቱና በእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር ለተሳተፉ አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ ካሰው እንደገለጹት ሰልጣኞች ከማምረት ባለፈ የገበያ ትስስር በመፍጠር ለሌሎች ወጣቶችም ሰፊ የስራ እድል መፍጠር አለባችው ብለዋል፡፡ 
በእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር ለታደሙ አካላት ስልጠናውን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት  በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኬሚካልና ምግብ ምህንድስና ፋኩሊቲ  መምህርና ተመራመሪ እንዲሁም ዲን የሆኑት ፕሮፌሰር ሰሎሞን ወርቅነህ ተቋሙ ከ50 በላይ ላቦራቶሪዎች ያሉት መሆኑን ገልፀው፣ እነዚህን በመጠቀም ዩኒቨርሲቲው በርካታ የስራ ፈጠራ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ መሆኑን አብራርተዋል። ፕሮፌሰሩ አያይዘውም፣ ተቋሙ ከማሰልጠን ባሻገር ሰልጣኞች ለስራቸው የሚሆን የዕውቅና ሰርተፍኬት የሚያገኙበት መንገድ እንደተመቻቸ ገልጸዋል።
ከሰልጣኞች መካከል ስራ ፈጣሪ ፊቨን አብዲ በበኩሏ የተገኘው እውቀትና ክህሎት ልዩ መሆኑን እና እነሱ የሚያመርቷቸው ምርቶች ከሌሎች የሚለዩት "ለእጅ፣ ለልብስ እና ለገላ መታጠቢያ የሚያስፈልገውን ኬሚካል መጠን ከጤና አንፃር ተለይቶ መወሰን የሚያስችል" ሳይንሳዊ እውቀት ያገኘችበት ስልጠና መሆኑን ገልጥጻለች።
በስልጠናውም አስራ አምስት ሴቶች እና አንድ ወንድ በድምሩ አስራ ስድስት ወጣቶች በደረቅና ፈሳሽ ሳሙና አመራረት ዙሪያ ስልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ ሲሆን በሰልጣኞች የተሰሩ ምርቶችም በተሳታፊዎች ተጎብኝተዋል፡፡
መርሀ ግብሩ ሲጠናቀቅ የላቀ አፈፃፀም እና ቁርጠኝነት አሳይተው ላጠናቀቁ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች፤ ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ተወካይ እና ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች ጋር በመሆን የእውቅና ሰርተፍኬት ለሰልጣኞች ተሰጥቷል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

The Poly Journal of Engineering and Technology (PJET) is a peer-reviewed, open-access, and multidisciplinary journal published biannually by the Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University.

As PJET advances toward international visibility and academic excellence, we invite accomplished scholars to help steer our mission of publishing pioneering research in engineering, technology, and applied sciences. Serving on the PJET editorial team presents a unique opportunity to shape scholarly discourse, expand global networks, and make meaningful contributions to the advancement of engineering and technology research.

Hence, you could apply either as 1. Editor-in-Chief or 2. Associate Editors position as outlined in the attached call.

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 06/04/2018 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለ Science College የ Research and Community Services V/Dean ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ V/Dean for RCS, Science College
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ታህሳስ 06 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Commits to Excellence: Launches Major Faculty Training to Improve Assessment Skills and Educational Quality

Bahir Dar University in Ethiopia – December 12, 2025 – has officially started a four-day, impactful training program for its faculty, highlighting its proactive effort to improve academic standards. Organized by the Training Directorate and the Examination Center, this initiative aims to boost the professional skills of BDU's teaching staff, ultimately enhancing student assessment and the overall quality of education.

The training concentrates on two key areas: Basic Test Construction (covering the principles of designing valid True/False, Multiple Choice, Matching, and Essay questions) and Performance-Based Assessment (PBA). The latter includes intensive practical work on creating accurate Rubrics for the evaluation of hands-on and skill-based learning.

Building on last year's success, BDU plans to train 300 faculty members across its colleges and institutes during the 2025/2026 academic year. This effort is crucial for ensuring that student assessments accurately measure knowledge, critical thinking, and skills, thereby maintaining a high standard of education for all BDU students.

~~~~~~

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ያለመ የመምህራን ስልጠና አስጀመረ

ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም(ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) –የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ምርምር ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኝነቱን በተግባር ለማረጋገጥ፣ ለመምህራኑ ሙያዊ ብቃት ማጎልበቻ የተዘጋጀ የአራት ቀናት ልዩ ስልጠና ተጀምሯል። ስልጠናው በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክቶሬት እና የፈተና ማዕከል ተብብር የተዘጋጀ ነው።

ስልጠናው ከታህሳስ 03/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የትምህርት ጥራት መሻሻል ወሳኝ መሠረት በሆኑት በሁለት ዋና ዘርፎች ያተኮረ ሲሆን፣ መሠረታዊ የፈተና አዘገጃጀት (Basic Test Construction) አንዱ የስልጠናው ትኩረት ነው። በዚህም የተለያዩ የንድፈ ሐሳብ ትምህርቶችና የፈተና አይነቶች (እውነት/ሐሰት፣ ምርጫ፣ አዛምድ እና አብራራ) አዘገጃጀት መርሆዎች ላይ ጥልቅ ትንተና በማድረግ፣ የፈተና ጥራትን የማሳደግ ዘዴዎችን የሚያካትቱ መሆኑ በስልጠናው መጀመሪያ ተብራርቷል።

ሁለተኛውና የስልጠና ትኩረት ተግባር ተኮር ምዘና (Performance-Based Assessment) ሲሆን ተግባር ተኮር ትምህርቶችን በትክክል ለመመዘን የሚያገለግለውን ሩብሪክ (Rubric) ዝግጅት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ ተግባራዊ ልምምዶችና የልምድ ልውውጦች በማድረግ እንደሆነ ግንዛቤ ተሰጥቷል።

የስልጠና ዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ እንዳብራሩት፣ ይህ ስልጠና የመምህራን የፈተና ዝግጅት አቅም በማሳደግ የተማሪዎችን እውቀት፣ ክህሎት፣ የማሰብ ችሎታና አመለካከት በትክክል የሚመዝን የፈተና ሂደት ተግባራዊ እንዲሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ትክክለኛ የፈተና አዘገጃጀትና ሂደት መከተል ለአጠቃላይ የትምህርት ጥራት መሻሻል እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ ዩኒቨርሲቲው ይህንን ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራበት ይገኛል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ጥሩወርቅ ታምሩም በበኩላቸው፣ ስልጠናው በተማሪ ምዘና መሳሪያ ዝግጅት ላይ በማተኮር የተሻለ የትምህርት ምዘና ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም ለ180 መምህራን ስልጠና በመስጠት ውጤታማነት በማስመዝገቡ፣ በ2018 ዓ.ም ደግሞ ለ300 መምህራን ስልጠናውን ለመስጠት አቅዷል። በአሁኑ ጊዜ በመጀመርያው ዙር 180 መምህራን ከአካዳሚክ ክፍሎች ተውጣጥተው ስልጠናውን እየተከታተሉ ነው። በመሆኑም የግብርናና አካባቢ ሳይንስ፣ የሂውማኒቲ ፋኩልቲ፣ የስፖርት አካዳሚ፣ የሳይንስ ኮሌጅ፣ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) እና የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) መምህራን የስልጠናው ተካፋዮች ናቸው።

በዚህም ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ መምህራን በዩኒቨርሲቲው የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Only Three Days Remained!!!
Dear Bahir Dar University Former Graduates,

We invite you to participate in the Alumni Engagement Survey that will be closed on Friday, 12th December 12:00 noon. Your input is essential in helping us strengthen alumni relations, improve programs, and build a lasting legacy of impact.
Please click the link below to complete the survey:
Survey Link:  https://srvy.pro/F685N4R
/channel/c/1630371649/3669

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

We are excited to announce the Designer Showcase as part of the upcoming 2nd National Conference on Sustainable Fashion held on january 31, 2026. This prestigious event brings together innovators, educators, entrepreneurs, and industry leaders to explore the future of fashion rooted in sustainability, culture, and creativity.

✨ Why Participate?

• Visibility: Present your designs to a national audience of academics, professionals, and fashion enthusiasts.
• Networking: Connect with fellow designers, industry leaders, and potential collaborators.
• Impact: Contribute to shaping Ethiopia’s sustainable fashion movement and inspire the next generation.
• Recognition: Gain acknowledgment for your creativity, innovation, and commitment to sustainability.

👗 Who Can Apply?

We welcome applications from:
• Emerging and established designers
• Fashion entrepreneurs and creative collectives
• University students and graduates in fashion and design
• Innovators working with sustainable materials, cultural heritage, or circular fashion practices

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Call for Papers for the historic May International Education Conference

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በጥበብ አዳራሽ በደማቅ ስነስርዓት ይከበራል።
✅መምህራንና አስ/ሠራተኞች
✅ተማሪዎች በሙሉ ተጋብዛችኋል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Dear Bahir Dar University Alumni,
We invite you to participate in the Alumni Engagement Survey, open from December 3rd through December 12th at 12:00 noon. Your input is essential in helping us strengthen alumni relations, improve programs, and build a lasting legacy of impact.
Please click the link below to complete the survey:
Survey Link:  https://srvy.pro/F685N4R
Completing the survey will ensure your perspectives are included in shaping future alumni initiatives. In January, your university will receive a comprehensive Alumni Engagement Report highlighting key findings and recommendations based on your feedback.
Thank you for taking a few minutes to share your voice and contribute to the growth of your alumni community.
With appreciation,
Tamiru Delelegn
Alumni Affairs Coordinator
Bahir Dar University
tamiru.delelegn@gmail.com

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

🚀 Call for Innovative Business Ideas!

Bahir Dar University Business Incubation and Startup Hub (BDU-BISH) is excited to launch a Business Idea Competition for our Incubation Program!

What BDU-BISH Offers:
✅Entrepreneurship Training
✅ Access to develop Prototypes
✅ Mentorship and Coaching
✅Working space

Eligibility:
✅ BDU Student/Staff
✅Have an Innovative business idea
✅ Not supported by any other incubation program
✅Willing to work in the new BISH working space

DEADLINE: December 20, 2025

Register Now: https://forms.gle/r7YaPrcnBLrqYnQ58
Don't miss the chance to turn your idea into reality!

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የደም ልገሳ የሚካሄድባቸው ቀናትና ግቢዎች
ዋና ግቢ፡ 20-21/03/2018ዓ/ም
ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፡ 21/03/2018ዓ/ም
ሰላም፡ 23-25/03/2018ዓ/ም
ፖሊ ፡ 27-28/03/2018ዓ/ም
ግሽ ዓባይ፡ 27/03/2018ዓ/ም
ጥበበ ግዮን፡ 20-21/03/2018ዓ/ም
ዘንዘልማ፡ 28/03/2018ዓ/ም

ደም ያስተሳስረናል፤ ደም ይለግሱ!
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ!
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

“ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት አድርጓል።”
ዶ/ር መንገሻ አየነ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፣ (ህዳር 18/2018 ዓ/ም)፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ገለጹ፡፡ ዶ/ር መንገሻ አየነ በህዳር 16/2018 ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በአደረጉት ቆይታ “ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት አድርጓል። ይህ ዝግጅት በምርምር፣ በመማር ማስተማር፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና በማህበረሰብ አገልግሎት ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ለመዝለቅ የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተሻለ አካዳሚያዊ፣ የፋይናንስና አስተዳደር ነፃነት ኖሯቸው ለትምህርት ጥራት እንዲሰሩ ራስ ገዝ መሆናቸው መልካም ጅማሮ መሆኑ እንደተመከረበት አስታውሰው ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አሥሩ ራስ ገዝ እንዲሆኑ የማድረግ ጥረት የቀጠለ እንደሆነና ከእነዚህ መካከል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ ሆኖ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ በመግለጫቸው የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የሀገሪቱ አቅምና ገበያውን መሰረት ያደረገ የሰው ኃይል ለማፍራት የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝነት ወሳኝ መሆኑን አንስተው ለዚህም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጸዋል። በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅርና መሰል ተግባራትን በማካተት ውስጣዊ ግምገማ በማድረግ ውጤቱን ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ገልፀው፣ የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት የዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት አሰራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ !

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Enhances Entrepreneurial Vision with Stakeholder Workshop

BDU, Bahir Dar, Ethiopia (November 21, 2025) — In a dedicated effort to promote innovation and economic growth, Bahir Dar University (BDU) successfully hosted a consultative workshop titled "Workshop on Building Entrepreneurial Ecosystem in Bahir Dar University" on November 20, 2025. The event played a key role in the university’s celebration of Global Entrepreneurship Week (GEW).

The impactful workshop brought together diverse stakeholders, including university management, faculty, students, and community representatives, to develop collaborative strategies for strengthening the entrepreneurial landscape within the university and the broader community.

Professor Enyew Adgo, Vice President for Research and Community Engagement at Bahir Dar University, delivered the welcoming address, emphasizing the important role of entrepreneurship. "Honoring and commemorating entrepreneurs plays a significant role in boosting a country's economy and bringing about societal prosperity," stated Professor Adgo. He also reaffirmed BDU's proactive approach of integrating entrepreneurship courses into all academic programs to build the capacity of future innovators.

Dr. Sisay Geremew, Director of the Bahir Dar University Startup, provided context on the university's participation in Global Entrepreneurship Week, which has been celebrated internationally by over 200 countries since 2008. This year marks the third time BDU has participated in the global event; the university organized six different platforms throughout the month as part of the celebration.

Dr. Sisay noted that these platforms are essential for participants to exchange experiences, address challenges, and explore favorable opportunities.

The workshop included an engaging panel discussion and presentation of research papers by academic scholars. A key aspect of the session was the lively interaction, with participants offering diverse feedback and asking questions that were thoroughly addressed.

In his closing remarks, Professor Nigus Gabye, Corporate Director for Community Engagement and Industry Linkage, emphasized BDU’s identity as a veteran research university dedicated to integrating impactful research with teaching and learning.

Professor Nigus acknowledged that the consultative forum was highly productive, providing valuable "homework" for the university to undertake as it advances in implementing the discussed strategies. He expressed sincere gratitude to all stakeholders for their committed participation in the successful event.

Bahir Dar University is one of Ethiopia's most respected research institutions, dedicated to excellence in teaching, research, and community engagement.

Читать полностью…
Subscribe to a channel