bahir_dar_university | Unsorted

Telegram-канал bahir_dar_university - Bahir Dar University,Ethiopia

21374

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses! www.bdu.edu.et

Subscribe to a channel

Bahir Dar University,Ethiopia

Alumni Success Story: From a Dissertation on Waste to Building a Company that Creates Wealth

Dr. Medhanit Mamaye, a graduate of the Bahir Dar Institute of Technology(BiT-BDU), earned her B.Sc. in Chemical Engineering in 2001 E.C. She later pursued graduate studies at Addis Ababa University, where she obtained both her M.Sc. and Ph.D. in Chemical Engineering. Before becoming an entrepreneur, she served as a researcher and instructor at Hawssa University.

Building on her Ph.D. dissertation, "Pulp and Paper Production from Non-Wood Biomass: Sustainable Eco-Packaging," Dr. Medhanit founded Prim Pulp and Paper Manufacturing PLC, where she currently serves as its CEO. Her company produces pulp and paper products, with an initial focus on manufacturing paper bags as an environmentally friendly substitute to currently banned plastic bags.

Beyond replacing plastic products, Prim Pulp and Paper Manufacturing aims to create additional income opportunities for farmers by purchasing agricultural biomass by-products tha

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

BDU-IUC ፕሮጀክት ከግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የክረምት ችግኝ ተከላ አካሄደ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሀምሌ 09/2018 ዓ.ም.

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ BDU-IUC ፕሮጀክት ከግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ አካል የሆነውን የክረምት ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ ቀበሌ፣ ደወል ጎጥ ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የቦረቦር ልማትና ማዳን ስፍራ አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የBDU-IUC ፕሮጀክት ማናጀር  ተስፋዬ ሽፈራው(ዶ/ር)፣ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በንቃት ተሳትፈዋል። በዚህም ለአካባቢው ተስማሚና የቦረቦር መስፋፋትን በመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የተመረጡ የአገር በቀልና ሌሎች የዛፍ ችግኞች ተተክለዋል።

የመርሃ ግብሩ አስተባባሪና የBDU-IUC ፕሮጀክት የእፅዋት ቤተ መዘክር ኃላፊ አቶ ጌታሰው ሞገስ እንደገለጹት፣ የችግኝ ተከላው በበጋ ወቅት የተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎችን፣ በተለይም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሰሩ የጎርፍ መከላከያ እርከኖችን (Wooden with Stone Check Dams) ለማጠናከር እና መሬቱ በተፈጥሮ እንዲያገግም በማሰብ የተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

የተጎዱ መሬቶችን መልሶ ማገገም፣ የአፈር መራቆትንና የቦረቦር መስፋፋትን መቆጣጠር፣ ለምርምርና ለትምህርት የሚያገለግል ሰርቶ ማሳያ ማቋቋም፣ እንዲሁም ማህበረሰቡን በቀጥታ በማሳተፍ ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ማጠናከር ዋና ዓላማው መሆኑ ተገልጿል።
በመጨረሻም፣ BDU-IUC ፕሮጀክት በምርምር፣ በትምህርትና በማህበረሰብ አገልግሎት የሚገኘውን ዕውቀት በተግባር በማዋል፣ ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃና ልማት ሥራዎችን በቀጣይነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ሆኖ እንደሚሰራ ተገልጿል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

🌍 Call for Applications: Erasmus+ Student Exchange Opportunity at Middle East Technical University (METU), Turkey (Fall 2026)

External Relations and Partnership Directorate,
Vice President for Information and Strategic Communication, Bahir Dar University
 
Date of Publication: July 13, 2026
 
Bahir Dar University (BDU) is proud to announce a renewed call for student applications for our ongoing institutional partnership with Middle East Technical University (METU) in Ankara, Turkey. Funded under the European Union’s Erasmus+ KA171 International Credit Mobility (ICM) student program, this collaboration bridges BDU’s academic talent with one of Turkey's leading research institutions, fostering international exposure, shared academic resources, and cross-cultural development.
We are currently inviting applications from highly qualified BDU students to spend the Fall Semester of the 2026–2027 Academic Year studying at METU.
💰 Scholarship Benefits
Monthly Stipend: €800 per month to cover living expenses.
Travel Allowance: A fixed, one-time payment between €211 and €1,735 (calculated via the EU distance calculator based on the distance between Ethiopia and Ankara).
Tuition: Fully waived at the host institution.
📊 Available Quotas
Main Fully Funded Nominees: 2 slots (with full Erasmus+ scholarship).
Zero-Grant / Self-Funded Nominees: Eligible students who pass the selection criteria but wish to participate using personal funds (waived tuition, but no monthly stipend).
📋 Eligibility & Academic Requirements
METU is an English-medium, highly competitive research university. Applicants must meet the following strict criteria:
Þ    Undergraduate Students: Must have completed a minimum of one full year of study at BDU at the time of application.
Þ    MSc / PhD Students: Eligible if they plan to take courses OR have already independently secured a Research Supervisor at METU who has provided a signed acceptance letter. Note: Graduate students cannot graduate from METU; they return to BDU to defend their thesis.
Þ    English Language Proficiency: A minimum of B1 level according to the CEFR framework is strictly required.
Þ    Academic Load: Selected students are required to take a full workload of at least 30 ECTS credits at METU.
⏱️ Selection & Internal Application Deadlines
To comply with international transparency rules, this call will remain open for student submissions for a full 15 days.
BDU Student Internal Application Deadline: July 28, 2026 (5:00 PM)
Review & Interview Period: July 29 – August 2, 2026
Official BDU Institutional Nomination to METU: August 5, 2026
Final Online Application Portal Deadline for Students: August 10, 2026
📂 How to Apply (Internal BDU Process)
Interested and eligible students should submit their application along with all required digital uploads directly through the online application portal.
👉 Apply here: https://forms.gle/MyNHZpPsDJaDtZ5B8
 
⚠️ Important Financial Notice: Erasmus+ grants are distributed in two installments (70% upon physical arrival in Turkey, 30% at the end of the semester). Because processing takes 2 to 3 weeks after arrival, selected students must be financially prepared to cover their own initial accommodation and living costs for the first month. On-campus dormitories are available but subject to strict quotas and are not guaranteed.
 
📧 Shortlisted applicants will be contacted via email. There is no need to submit application documents in person unless requested. 

📩 Should you require further information, please reach out to the External Relations and Partnership Directorate via bduexternalrelations@gmail.com
 
📍 External Relations and Partnership Directorate,
Vice President for Information and Strategic Communication
Bahir Dar University

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University–AfRIE Partnership Gains International Recognition in Nature Methods
The strategic partnership between Bahir Dar University (BDU) and the Alliance for Research, Innovation and Education for Africa (AfRIE) has received international recognition through a feature in the July 2026 issue of Nature Methods, one of the world's leading scientific journals. The article, titled "They Build Science Capacity in Africa for Africa," highlights how the collaboration is strengthening genomics education, biomedical research, and scientific capacity in Ethiopia and across Africa.
Established through a shared vision of building scientific capacity in Africa, the BDU–AfRIE partnership has successfully launched Ethiopia's pioneering Master's Program in Public Health Genomics at Bahir Dar University. The program brings together internationally renowned scientists and local experts to equip healthcare professionals, researchers, and laboratory scientists with advanced knowledge and practical skills in genomics, bioinformatics, precision medicine, and collaborative research.
The Nature Methods feature also recognizes Bahir Dar University's growing role as an emerging research-intensive university through expanded international partnerships, interdisciplinary research, and investments in state-of-the-art facilities such as the Tana Diagnostic and Research Center, which is strengthening research and graduate training in biomedical and genomics sciences.
The article showcases the experiences of BDU faculty members and graduate students whose work demonstrates how international collaboration, mentorship, and knowledge exchange are preparing the next generation of African scientists to address pressing health challenges while contributing to global scientific discovery.
Bahir Dar University expresses its sincere appreciation to AfRIE and all national and international partners whose commitment continues to advance research excellence, innovation, and graduate education. Together, we are building scientific capacity in Africa—for Africa and the world.
#BahirDarUniversity #AfRIE #NatureMethods #ResearchExcellence #Genomics #Innovation #ScienceForAfrica #GlobalPartnerships

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና ቦይንግ የአቪዬሽን ፈጠራ ማዕከል ለማቋቋም ታሪካዊ የረጅም ጊዜ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም) — ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና የዓለም አቀፉ የቦይንግ (NYSE:BA) ኩባንያ በፍጥነት እያደገ የሚገኘውን የአቪዬሽን ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር፣ በኤሮስፔስ ምህንድስና ትምህርት ፈጠራን ለማበረታታት እንዲሁም ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ ስምምነት በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) ውስጥ "የአቪዬሽን ፈጠራ ማዕከል" (Aviation Innovation Center) ለመገንባት የሚያስችል ሲሆን፣ ማዕከሉ በተግባር ላይ የተመሰረተ ትምህርት፣ ምርምር፣ ፈጠራ እንዲሁም ለጀማሪ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሥራዎች የድጋፍና የማብቃት (Incubation) አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል። የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ እጅጉ እና የቦይንግ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ሻውል ያከናወኑት ሲሆን፣ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶክተር ምትኩ ዳምጤ ስለ ተቋሙ አጠቃላይ ገለጻ አድርገዋል።
የቦይንግ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ እንደገለጹት፣ በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት የአፍሪካ አየር መንገዶች ከ1,200 በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን እና ከ74,000 የሚበልጡ አዲስ የአቪዬሽን ባለሙያዎችን ይፈልጋሉ። ኢትዮጵያ በዘርፉ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም መሆኗንና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ አንጋፋ የኢንጂነሪንግ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው፣ ትብብሩ ተሰጥኦ ላላቸው ወጣቶች የሙያ ዕድገት ከመፍጠሩም በላይ እየተስፋፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎት፣ የአየር ማረፊያ መሠረተ ልማት እና የኤሮስፔስ አካላት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዕድገትን ይደግፋል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ በበኩላቸው ትብብሩን "ታሪካዊ ምዕራፍ" በማለት የገለጹት ሲሆን፣ በኤሮስፔስ ትምህርት፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ማዕከል ለመገንባት በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ማዕከል የብቁ ሰው ኃይል ልማትንና የቴክኖሎጂ ንግድን በመደገፍ ለሀገራዊ ኢንዱስትሪ ሽግግር አስተዋፅኦ የሚያበረክት ሲሆን፣ ቦይንግ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ውስጥ በሂሳብና ሳይንስ (STEM) ትምህርት የጀመረውንና ባለፉት አምስት ዓመታት ከ14,700 በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገውን ተግባር ይበልጥ ያጠናክረዋል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ-ሆሳዕና ምርምር ማዕከል ከኢትዮጵያ ብዝኅ ሕይዎት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የመጀመሪያዉን አገር አቀፍ ኮንፈረንስ ሰኔ 29/2018 ዓ.ም አካሄደ፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ

“ዩኒቨርሲቲዎችን በምርምር ማዕከላትና መናፈሻዎች አታክልት አማካኝነት ወደ ዘላቂ የላቀ ብቃትና የብዝኅ ሕይዎት  ጥበቃ መለወጥ››  በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ምሁራን፣የሀገር በቀል መዳህኒት አዋቂዎች፣ተመራማሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት  በቤንማስ ሆቴል አመታዊ ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የ ዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ ተሳትፎ  ም/ፕሬዝዳንት እንየዉ አድጎ (ፕ/ር) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለባሕላዊ ሕክምና ምርምር እና ለወደፊቱ ደግሞ በመላዉ ኢትዮጵያ የብዝኅ ህይወት ጥበቃ ዙሪያ ታሪካዊ ምዕራፍ የሚያስጀምር ልዩ ቀን ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 በፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 ጥቅምት ወር ላይ የተፈራረምነዉን የመግባቢያ ሰነድ በመከተል ፤ዛሬ በዚህ መገኘታችሁ  ይህ ትብብር በመደርደሪያ ላይ ብቻ እንዳልሆነ ግን ሕያዉ ፤ንቁና በእድገት ላይ ያለ መሆኑን ያረጋገጠ ነዉም ብለዋል፡፡
ባሕላዊ ፈዋሾቻችን የዚህን ማዕከል  እዉነተኛ ልብና ነፍስ የሆናችሁ፡በሙሉ ልብ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንደ ቅዱሰ አደራ የተላለፈዉ እዉቀታችሁ የስራችን መሰረታዊ ዓለት መሆኑ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጽኑና የማይናወጥ ከኢትዮጵያ ብዝኅ ሕይዎት ኢንሲቲትዉት ጋር ለረጅም ጊዜ እጅ ለእጅ ተያይዘን ፤በጋራ ምርምር፤ በጋራ ሀብታችን፤ በጋራና ቀጣይነት ትርጉም ያለዉ ትብብር እንደሚሰሩም በአጽዕኖት ገልጸዋል፡፡
በኮንፈረንሱ ላይ ቁልፍ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብዝኅ ህይዎት ኢንስትቲዩት ም/ዳይሬክተር የሆኑት  አቢዮት  ብርሃኑ (ዶ/ር) ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመስራታቸዉ ምርምራችን ሚጨበጥና ሚዳሰስ የምርምር ዉጤት እንደሚያገኙ ገልፀው የዩኒቨርሲቲው የስነ-ሆሳዕና  ምርምር ማዕከል ከሀገር በቀል መዳሕኒቶች እጽዋት  በትብብር ለመስራት አጠቃላይ ትብብር ማዕቀፍ ተፈራርመን ወደስራ ከገባን ቆይተናል ብልዋል፡፡
በአባይ ወንዝ ላይ የዕጽዋት አጸድ በማቋቋም ትልቅ እድገት እንደሚያመጣና ለባሕር ዳር ወይም ለአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ለአገር የሚጠቅም ምርምር እንደሚካሄድም እምነታቸውን ገልጸዋል። ለተማዋና አካባቢዋም የእጽዋት እድገት ምቹም ከመሆኑም የተነሳ ይህን አጋጣሚ ወደምርምር መለዎጥ አስፈላጊ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
እጽዋትን ማንበር/መጠበቅ/፤የባህል መዳህኒት አዋቂዎችን እዉቀት መጠበቅና በሳይንሳዊ መንገድ ዕዉቀታቸዉን ማሳደግ ተገቢ መሆኑን እና የዕጽዋት አጸደ ማቋቋም ያስፈለገዉ ዋናዉ አላማ የስነ-ሆሳዕና የምርምር ማዕከል የሀገር በቀል መዳህኒቶችን በሳንሳዊ ምርምር መጠበቅ ፤ማሳደግ፤የሚል መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስነ-ሆሳና የምርምር ማዕከል ዳይሬክተር  ደስታዉ ዳምጤ(ዶ/ር) እንዳሉት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የእጽዋት እዉቀት እየቀነሰ መምጣቱን እንዲሁም ሀገር በቀል ሕክምናዎች በተለያዩ ምክኒያቶች እየተዳከሙ መምጣታቸዉን ከነዚህም ዉስጥ የባህል መዳህኒት አዋቂዎች እድሚያቸዉ መግፋቱንና ለተተኪ ማዉረስ አለመቻላቸዉ፤ወጣቱም ለሀገር በቀል እዉቀቶች ያለዉ ደካማ አስተሳሰብ እንዳብነት እንደሚጠቀሱም ገልጸዋል፡፡የስነ-ሆሳዕና ምርምር ማዕከል እነዚህን የባህል አዋቂዎችን እዉቀታቸዉን  በዘመናዊ መንገድ እንዲሰንዱና እንዲታገዙ ማድረግ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ በኮንፈረንሱ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት  የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማሕበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክተር  ነጻነት ፈንታሁን (ፕ/ር)  እንዳሉት፡-የኮንፈረንሱ ዉይይት የሀገር በቀል ዕዉቀትን ለመጠበቅ፤በሳይንሳዊ መንገድ ለማረጋገጥ፤ለልማትና ለቀጣይ ትዉልድ ለማስተላለፍ እጅግ አስፈላጊ መሰረት የጣለ እንደሆነ ገልጸው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደምርምር ተኮር ዩኒቨርሲቲ በምርምር፤በማኅበረሰብ አሳታፊነት፤በቴክኖሎጅ ሽግግር እና ለፈጠራ ስራዎች ከፈተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ አውስተዋል፡፡  የስነ-ሆሳዕና ምርምር ማዕከል የሀገር በቀል ዕዉቀትን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማገናኘት፤በማረጋገጥ፤በመመዝገብና ለማኅበረሰቡ ጥቅም በማዋል የላቀ ሚና እንደሚጫዎት እና የአንድ ሀገር ዘላቂ እድገት የሚረጋገጠዉ የሀገር በቀል ጥበብን ከዘመናዊ  ሳይንስ ጋር በማጣመር መስራት ሲቻል መሆኑን ፕ/ሩ ገልጸዋል፡፡
 

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የ4.00 ውጤት (perfect 4:00) ላስመዘገቡ 111 ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ

(ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚያደርገው ጥረት፣ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ሙሉ የ4.00 CGPA ውጤት ያስመዘገቡ 111 ተማሪዎችን የክብር ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል። በዚህ ደመቅ ባለ መርሃ ግብር ላይ ከተሸለሙት ተማሪዎች መካከል 11ዱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ለተሸላሚዎቹ ባስተላለፉት ልዩ መልዕክት፣ ውጤቱ የአካዳሚክ ስኬት ብቻ ሳይሆን ራስን የማክበር መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። ተማሪዎቹ ይህንን ውጤታማ ልምድ አዳብረው እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ፕሬዝዳንቱ፣ ብቃትና ስኬት ለግለሰብ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ትልቅ ሀብት መሆኑን አስምረውበታል። አክለውም "ኢትዮጵያ የነገ የኖቤል ሎሬቶች ከእናንተ መካከል ትጠብቃለች" በማለት፣ ተማሪዎቹ በየተሰማሩበት የሙያ መስክ አገርን የሚያስጠሩ ባለሙያዎች እንዲሆኑ የሞራል ጥሪ አቅርበዋል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር እሰይ ከበደ በበኩላቸው በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው እንደገለጹት፣ የዕውቅና መርሃ ግብሩ ዋነኛ ዓላማ ተማሪዎች ያላቸውን ዕውቀት ይዘው እንዲቀጥሉና ለበለጠ ትጋት እንዲነሳሱ ለማድረግ ነው። ይህ ታሪካዊ ውጤት በአመራሩና በተማሪዎች መካከል በተደረገ የተቀናጀ የቅርብ ክትትል የተመዘገበ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ ጠቁመዋል። ምክትል ፕሬዚደንቱ አክለውም የተማሪዎቹ ስኬት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ጥራት እና አካዳሚያዊ ልሕቀት ለሚሰጠው ትኩረት ማዕከል መሆኑን ገልጸው፣ ውጤቱ በተለያዩ ፈተናዎች፣ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች መካከል ሆኖ የተገኘ፣ በዲሲፕሊን የታጀበ ጥናት፣ የጠንካራ ቁርጠኝነትና የማያቋርጥ ጥረት ውጤት መሆኑን አስገንዝበዋል። "ይህንን ስኬት በድንገት ያገኛችሁት ሳይሆን በመስዋዕትነት፣ በጽናትና በዓላማችሁ ላይ በማተኮር ያመጣችሁት ነው" ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ውጤቱ ተማሪዎች ቁርጠኛ ከሆኑ የላቀ የትምህርት ስኬት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ገልጸው እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። የቤተሰቦቻቸው ድጋፍ፣ ማበረታቻና ምክር በትምህርት ጉዟቸው ወቅት ተነሳሽነትን፣ ዲሲፕሊንን እና በራስ መተማመንን እንድታዳብሩ ትልቅ እገዛ ማድረጉንም አድናቆታቸውን ችረዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ የተማሪዎች ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት ተማሪ ብርሃነመስቀል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በሳይንሳዊ ምርምር እንዲሳተፉ የሚያግዙ አዳዲስ ፕሮጀክቶች መጀመራቸውን ገልጾ፤ ዕውቀትና መሪነት አብረው የሚሄዱ በመሆናቸው አገርና ሕዝብን የማስከበር ኃላፊነት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስቧል። ከተሸላሚዎች መካከል አስተያየቷን የሰጠችው የሁለተኛ ዓመት የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ በለጡ ደረስ፣ የተሰጣት ዕውቅና ውጤቷን ለማስቀጠል ትልቅ ጉልበት እንደሚሆናት ገልጻለች። ተማሪዋ አክላም የላቀ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በጋራ ተሰባስበው ዕውቀትና ልምድ የሚለዋወጡበት ምቹ ሁኔታ ቢፈጠር ያላቸውን አቅም ይበልጥ እንደሚያሳድገው ጠቁማለች።

"ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ" በሚለው መሪ ቃሉ የሚታወቀው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ በአሁኑ ወቅት በዘጠኝ ግቢዎችና በ18 የአካዳሚክ ክፍሎች ከ26,000 በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው በአፍሪካ ቀዳሚ የምርምር ተቋም ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ እንዲህ ያሉ የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

6ኛው ዓለም አቀፍ የጤና ምርምር ኮንፈረንስ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተካሄደ
ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ፤ [ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም]
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 6ኛውን ዓለም አቀፍ የጤና ምርምር ኮንፈረንስ በዩኒቨርሲቲው  ጥበብ ህንፃ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት አስጀመረ።
ኮንፈረንሱ በዘርፉ ያሉትን ወቅታዊ የጤና ችግሮች በመለየት፣ በሳይንሳዊ ጥናት የተደገፉ መፍትሄዎችን በማፍለቅ እና የባለሙያዎችን የዓመታት ተሞክሮ በመለዋወጥ ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል። በስነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ከተለያየዩ ዓለም አቀፍና የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመክፈቻው መርሃ ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር በቃሉ ዉበሸት፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የጤናው ዘርፍ በውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆኖም አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
በተለይም የእናቶችና የህፃናትን ሞት በመቀነስ ረገድ የተመዘገበው ስኬት ተቋሙ ለኅብረተሰቡ ያለው የላቀ አስተዋጽኦ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። "የህክምና ሳይንስን ከምርምር ጋር አቀናጅተን በመስራታችን፣ የማህበረሰብ አገልግሎታችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ችለናል፤ ይህ ኮንፈረንስም ይህንኑ ተሞክሮ ለማስቀጠል ትልቅ አጋጣሚ ነው" ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው በአገራችን ከሚገኙ የጥናትና ምርምር ማዕከላት መካከል ግንባር ቀደም መሆኑን አስታውሰዋል። ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለክልሉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለሀገር አቀፍ የህክምና አገልግሎት ያለውን ፋይዳ በመጠቆም፣ ኮንፈረንሱ እንዲሁ የውይይት መድረክ ብቻ ሳይሆን ሳይንሳዊ ግኝቶች የሚቀመጡበት መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል።
"ይህ መድረክ የኅብረተሰባችንን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ የሚረዱ፣ በምርምር የተረጋገጡ ሳይንሳዊ መፍትሄዎችን በማፍለቅ ፖሊሲ አውጪዎችና የጤና ባለሙያዎች የሚመሩበትን አቅጣጫ ይጠቁማል" ሲሉም አክለዋል።

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ፣ በበኩላቸው የኢንስቲትዩቱንና የዩኒቨርሲቲውን የትብብር ስራ አድንቀዋል። በጤናው ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን ተቋማዊ ትብብር ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ኮንፈረንሱ በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት እና የህዝብ ጤና ችግሮችን ለመፍታት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የውይይት መድረክ፡-በጤናው ዘርፍ የተሰሩ አዳዲስ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ምርምሮች፣ከምርምር የተገኙ ውጤቶች ወደ ተግባር የሚለወጡበት  እንዲሁም በተመራማሪዎችና በተግባር አራማጆች መካከል የልምድ ልውውጥ የተካሄደበት ሲሆን ይህ መድረክ በአካዳሚክ ማህበረሰቡ እና በጤና ባለሙያዎች መካከል የዕውቀት ሽግግር በማድረግ፣ በማስረጃ የተደገፈ የጤና አሰራርን (Evidence-based practice) በስፋት ለማስረጽ ትልቅ ፋይዳ አለው ተብሏል።
ኮንፈረንሱ ነገም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ የጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች የነገውን የጤና ስርዓት ለመቅረጽ የሚያስችሉ ሀሳቦችን እንደሚያንሸራሽሩ ይጠበቃል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማህበር (ECDD) አካል ጉዳተኞችን በዘላቂነት ለመደገፍ የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም)
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአገር በቀሉ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማህበር (Ethiopian Center for Disability and Development/ECDD) ጋር ለአካል ጉዳተኞች የገንዘብ፣ የሙያ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ፣ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጎጃም ወንዲፍራው፣ የECDD ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ለጋሱ ልዑልሰገድ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በመቀበልና ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታን በመፍጠር ረጅም ልምድ ያለው ተቋም እንደሆነ ግልጸው ECDD እኛን አምኖ ይህን ትልቅ ኃላፊነት በመስጠቱ እናመሰግናለን ብለዋል ዶ/ር መንገሻ፡፡ አክለውም ስምምነቱ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን በክልሉ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ሁሉ ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን የመረጥነው በአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ግንዛቤ ያላቸው ምሁራን ስላሉት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም በመሆኑና ለምናከናውናቸው የሥልጠናና የጥናት ሥራዎች የዩኒቨርሲቲውን ምሁራን ለመጠቀም እንደሆነ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማህበር ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ለጋሱ ልዑልሰገድ ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ለዚህ ታላቅ ተቋም የራሳችንን ጠብታ አስተዋፅዖ ማበርከታቸው ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸውና ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

ስምምነትቱ በተለይ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሰሩ ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አካቷል፦ አካል ጉዳተኞች አስፈላጊውን መረጃና ድጋፍ የሚያገኙበት ማዕከል በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ማቋቋም፣አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የጤና አገልግሎት እና የኑሮ ማሻሻያ (Livelihood) ሥራዎች ላይ በትኩረት መሥራት፣ አካል ጉዳተኞች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙ ማስቻል እና በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ምሁራን ያላቸውን ዕውቀት በመጠቀም ለአካል ጉዳተኞችና ለባለሙያዎች ሥልጠና መስጠትን የሚያካትት እንደሆነ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ንጹህ ሀሳብ (Positive / Clean thinking) መያዝ
@necktop3
@necktop3
👍ነገሮችን በግልጽና በጥንቃቄ ማየት ያስችላል
👍ሰላምና ደስታ ያመጣል
👍ውስጣዊ ሰላምና ደስታ ይጨምራል
👍ከሰዎች ጋር በፍቅርና በክብር ያስኖራል
👍ስኬትን ይደግፋል
👍ጤናን ይጠብቃል
👍ጭንቀትን ይቀንሳል
👍ራስን መቆጣጠር ያስችላል
👍ሰው ስሜቱን እንዲቆጣጠር ይረዳል
ንጹህ ሀሳብ ለመልካም ሕይወት፣ ለስኬት እና ለሰላም መሠረት ነው!

@necktop3
@necktop3
contact @seen311
        SHARE

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሴት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ።
ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ፦ ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከ ፀሐይ መታሰቢያ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ ሴት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች  የህይወት ክህሎት የስልጠና መርሀግብርከመጋቢት 29-30/2018 ዓ.ም አካሂዷል።

በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሙሉጎጃም ወንድይፍራው (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ውስጥ አካታች የትምህርት ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ግንባር ቀደም ተቋም መሆኑና ዩኒቨርሲቲው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርታቸው ስኬታማ እንዲሆኑና በተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ጫናዎች ምክንያት ወደ ኋላ እንዳይቀሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዳይሬክተሯ አክለውም፦ከዚህ ቀደም ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን፤ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ጋር በመተባበር በግቢው ውስጥ ያሉ መሰረተ ልማቶች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እንዲሆኑ መደረጉንና አሁን እየተሰጠ ያለው ስልጠና ደግሞ ተማሪዎቹ በራስ መተማመናቸው እንዲጎለብትና ካደጉበት ማህበረሰብም ሆነ ከራሳቸው የሚመጡ ተጽዕኖዎችን አሸንፈው እንዲወጡ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት የብሩህ ዜጋ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር ካሳ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ምንም እንኳ አሁን ላይ ትኩረቱን አይነ ስውራን ተማሪዎች ላይ ቢያደርግም፣ ይዘቱ ግን ማንኛውም ሰው ተፈጥሯዊ ማንነቱን ተጠቅሞ በህይወቱ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች በውስጣዊ ጥበብ እንዲፈታ የሚያስችል ነው ብለዋል።
"ተማሪዎቹ ያሉባቸውን ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች በፀጋ እንዲቀበሉ፣ ጠንካራ የሰብእና እንዲኖራቸው እና ለማንኛውም ውጫዊ ፈተና የማይበገሩ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራን ነው" ሲሉ አቶ እስክንድር ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም በተማሪዎች ዘንድ የሚታዩ የክህሎት ክፍተቶችን በመለየት መሰል ስልጠናዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል። ይህ ስልጠና ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ከምረቃ በኋላም በህይወታቸው ስኬታማ ዜጋ እንዲሆኑ መሰረት የሚጥል መሆኑ ታምኖበታል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Study in Japan Opportunity: MEXT Scholarship Briefing (2027 Intake)

Bahir Dar University, in collaboration with the Embassy of Japan in Ethiopia, invites all students to attend an online briefing session on the prestigious Japanese Government (MEXT) Scholarship 2027.

This scholarship, offered by the Government of Japan through MEXT, supports outstanding international students to pursue undergraduate and graduate studies at leading universities in Japan.

Date: 28 April 2026
Time: 3:30 PM – 4:30 PM
Venue: Online

The session will provide:
Clear guidance on the application process
Practical tips for applying
Insights into studying and living in Japan

Students from all faculties and colleges are highly encouraged to attend!

👉 Register here: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdXkv2gxHtdXVNWbk6rKVLMt9Fmt4HFnaKWxbvckB0dH_sIMQ/viewform?usp=publish-editor

Don’t miss this valuable opportunity to take your academic journey global!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Call for Poly-BDU Alumni Association Meeting!

ለመላው የቀድሞ ፖሊ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን በሙሉ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30ጀምሮ መካኒሳ በሚገኘው በብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ አዳራሽ አጠቃላይ ዓመታዊ ስብሰባ ስለሚደረግ ማንኛውም የቀድሞ ምሩቅ በስብሰባው ላይ እንዲገኝ ጥሪያችንን እያቀረብን ስብሰባውን ከነ ሙሉ ወጪው Sponser ያደረገን ብሔራዊ አልኮል ለምሳ ግብዣው ዝግጅት እንዲረዳው የሚገኙትን የሰው ቁጥር ከወዲሁ ስለጠየቀን ስብሰባው ላይ የምትገኙ  "እኔ እገኛለሁ" የሚል መልዕክት በመላክ አረጋግጡልን::

Calll +251911636363

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#ማስታወቂያ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ/ጥበበ ግዮን ስፒሻላይዝድ ሆስፒታል  መደበኛ አገልግሎቱን በላቀ ደረጃ እየሰጠ ይገኛል።

ለሰራተኞች የሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎትም የሚቀጥል ሆኖ  ኮሌጁ ሲሰጠው የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳቋረጠ ተደርጎ በተያለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወረው ደብዳቤ ከኮሌጁ እውቅና ውጭ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቤተሰባዊ ትስስር መርሃ-ግብር መመዝገቢያ ቅጽ 
ውድ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች:-

ዩኒቨርሲቲያችን በ 2011 ዓ.ም ጀምሮት የነበረውና በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ ስያሜ ተስፋፍቶ በመተግበር ላይ የሚገኘውን “የባሕር ዳር እንደ-ቤቴ” ቤተሰባዊ ትስስር መርሃ-ግብር ተማሪዎቻችን ከከተማችን ማህበረሰብ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት እንዲመሰርቱ እና የዩኒቨርሲቲው አምባሳደር እንዲሆኑ የሚያስችል ተግባራዊ ጽንሰ-ሀሳብ ነው።
በመርሃ-ግብሩ ውስጥ ራቅ ካሉ የአገራችን ክፍሎች የሚመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ ወቅት ቤተሰባዊ ትስስር በመፍጠር በትምህርታቸው እንዲበረቱ፣ ስነ-ልቦናዊ ጫናዎችንና አቻ ግፊቶችን እንዲቋቋሙ እና ባህልና እሴቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል ይፈጥርላቸዋል።
እርስዎም የቃል ኪዳን ወላጅ በመሆን በተማሪዎች ሕይወት ውስጥ አይረሴ አስተዋጾ በማበርከት ትርጉምና ደስታን ያግኙ!

የመርሃ-ግብሩ ተሳታፊ ለመሆን መልካም ፈቃድዎ ከሆነ እባክዎን ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቅጹን ይሙሉ::

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfZQMNXEa-xLpr5ENqYvzUJ7UQs1LOKntpLcITHiKKNONPGTA/viewform

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 13/11/2018 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ (በድጋሜ የወጣ)

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለCollege of Business and Economics Postgrad. Research and Comm. Engagement V/Dean የኃላፊነት ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም በወጣው ማስታወቂያ በቂ አመልካቾች ባለመገኘታቸው በድጋሚ ማውጣት አስፈልጓል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ Postgrad. Research and Comm. Engagement V/Dean for College of Business and Economics
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ማዕረግ/ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ሀምሌ 13/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 05 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 2 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

From Lake Tana to the Global Fleet! ⚓️
Did you know that the Ethiopian Maritime Training Institute (EMTI), a purpose-built academy located on the shores of Lake Tana at Bahir Dar University, is helping shape one of Africa’s most promising sources of marine engineering talent for the global shipping industry?

We invite you to read the full article, "From Lake Tana to the Global Fleet: Inside Ethiopia’s Marine Engineering Cadet Program," by Anastasia Parali, Crewing Account Manager EMA Marine GmbH.

Article : https://allaboutshipping.co.uk/2026/07/09/from-lake-tana-to-the-global-fleet-inside-ethiopias-marine-engineering-cadet-program/?

Bahir Dar University extends its sincere appreciation to the author, Anastasia Parali, Crewing Account Manager EMA Marine GmbH, for sharing this inspiring story that highlights Ethiopia’s growing contribution to the global maritime sector, and to the former President of Bahir Dar University, Prof. Baylie Damtie, for bringing the article to our attention.
Kudos to both of you!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ የማህበረሰብ ተሳትፎና የቴክኖሎጂ ሽግግር አስተዳደርን ወደ ዲጅታል ሰርዓት በማሳደግ ለዩኒቨርሲቲው ዲኖች ፣ምክትል ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣   የኮርፖሬት ዳይሬክተሮች እና የምርምር ዳይሬክተሮች ሥልጠና አካሄደ
 
ሥልጠናው የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክና የአስተዳደር ኃላፊዎች ሥርዓቱን  በብቃትና በውጤታማነት እንዲጠቀሙበት ትውውቅና ተግባራዊ ክህሎት ለማጎልበት ታልሞ የተዘጋጀ ነው። የመረጃ ስርዓቱ ማንኛውንም የምርምር ውጤት በተመለከተ ቅሬታዎች ቢኖሩት የቅሬታ ማቅረቢያ ሞጁል የተካተተበት መሆኑን የሥልጠናው አዘጋጆችና የሥርዓቱ  አበልፃጊዎች ገልጸዋል።
ባለሙያዎቹ ሥርዓቱን በአንድ ዓመት ተኩል ውስጥ ዲዛይን በማድረግ፣ በማበልፀግ እና በመተግበር ለአገልግሎት ያበቁት ሲሆን ዲኖች ፣ምክትል ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣   የኮርፖሬት እና የምርምር ዳይሬክተሮች በሥልጠናው የተሳተፉ ሲሆን እነዚህ ኃላፊዎች በምርምር፣ በማህበረሰብ ተሳትፎና በቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ግምገማ፣ ውሳኔና ፈቃድ የመስጠት ሂደቶች ውስጥ ዋና ተዋናይ ናቸው ተብሏል። በሥልጠናው ወቅት ተሳታፊዎች የሥርዓቱን ዋና ዋና ባህሪያትና የሥራ ፍሰቶች በተግባር ተለማምደዋል። 

የልማት ቡድኑም ሥርዓቱ የምርምር፣ የማህበረሰብ ተሳትፎና የቴክኖሎጂ ሽግግር ፕሮጀክቶችን ከፕሮፖዛል ማቅረብ፣ በየደረጃ ያለዉን ያሰራር ፍሰት፣ በየደረጃው የሚካሄድ ግምገማ፣ አውቶማቲክ ማሳወቂያዎች (ለምሳሌ  እያንዳንዱን ሂደት ለሚመለከተዉ አካል በኢሜል ይልካል)፣ የእድገት ሪፖርት ማቅረብ፣ የእድገት ግምገማ፣ የውሳኔ አሰጣጥ፣ የመጨረሻ ሰነድ ማስገባት እና የመጨረሻ ማጽደቅ ድረስ ያሉትን ሁሉንም ሂደቶች በዲጂታል መልኩ እንደሚያስተዳድር አስረድተዋል።

በሥልጠናው ወቅት ከፍተኛ ትኩረት ካገኙ የሥርዓቱ ባህሪያት መካከል በዩኒቨርሲቲው ደረጃ የሚቀርቡ ተመሳሳይ ወይም ተደጋጋሚ የፕሮፖዛልና የምርምር ማመልከቻዎችን በራስ-ሰር የመለየት ችሎታው ይገኝበታል። ይህ አቅም ተደጋጋሚ ሥራዎችን በመቀነስ፣ የምርምር ታማኝነትን በማጠናከር፣ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ጥራት በማሳደግ ረገድ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

ሥርዓቱ በተጨማሪም የማጽደቅ ሂደቶችን በራስ-ሰር በማስተዳደር፣ የተሟላ ዲጂታል መዝገብ በመያዝ፣ በቅጽበት ሪፖርቶችን በማመንጨት እና ተጠቃሚዎች የሥራዎቻቸውን ሂደት በማንኛውም ደረጃ እንዲከታተሉ በማስቻል የተቋሙን አፈጻጸም ያሻሽላል።

ተሳታፊዎች  ሥርዓቱን  ለተጠቃሚዎች ምቹ መሆኑን፣ የተሟላ አገልግሎት መስጠቱን እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ የማህበረሰብ ተሳትፎና የቴክኖሎጂ ሽግግር አስተዳደርን በእጅጉ እንደሚያዘምን ገልጸዋል።
የልማት ቡድኑ በበኩሉ ሥርዓቱ በስኬት መጠናቀቁ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለዲጂታል ሽግግር፣ ለፈጠራ እና ለተቋማዊ ልህቀት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን በተጨማሪም ሥርዓቱ የምርምር አስተዳደርን በማጠናከር፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን በማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማበረታታት እና የተመራማሪዎች ቅሬታዎችን በቀልጣፋና በግልጽ አሰራር ለማስተዳደር የዩኒቨርሲቲው ዋና ዲጂታል መድረክ እንደሚሆን መተማመናቸውን ገልጸዋል።
 
 



Bahir Dar University Provides Training for Leadership Team on its Digital Research, Community Engagement, and Technology Transfer Management System
Bahir Dar University has conducted a training program for its college deans, vice deans, department heads, corporate and research directors following the digitalization of its research, community engagement, and technology transfer management system.
The training aimed to familiarize academic and administrative leaders with the new system and equip them with the practical skills required to use it effectively and efficiently. The organizers and system developers noted that the platform incorporates a grievance-handling module designed to address complaints and appeals related to research outcomes.
The system was designed, developed, and deployed within a year and half by a team of experts. The training brought together participants, who play key roles in the evaluation, decision-making, and approval processes related to research, community engagement, and technology transfer activities in the university. During the session, participants engaged in hands-on exercises to explore the system's core features and workflows.
According to the system development team, the platform digitally manages the entire lifespan of research, community engagement, and technology transfer projects. It covers every stage, from proposal submission and multi-level review processes to step-by-step evaluations, automated notifications to relevant stakeholders, progress report submission and evaluation, decision-making, final document submission, and ultimate approval.
One of the system's most notable features is its ability to automatically detect duplicate or highly similar proposals and research applications submitted within the university. Participants observed that this capability will significantly reduce redundancy, strengthen research integrity, and enhance the overall quality of research and innovation.
Furthermore, the system is expected to improve institutional performance by automating approval workflows, maintaining comprehensive digital archives, generating real-time reports, and enabling users to track the status of their projects at every stage.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

🌳 የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ 🌿
"ዛፎችን እንትከል! እንከባከብ! እናሳድግ!"
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ / ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም. የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተገኝተው ያስጀምራሉ።
በመሆኑም የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞች እና ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የአረንጓዴ አሻራችሁን እንድታሳርፉ በክብር ተጋብዛችኋል።
🌱 ዛፍ መትከል ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ የምናበረክተው ሕይወት ነው። አካባቢያችንን እንጠብቅ፣ አረንጓዴነታችንን እናጠናክር፣ ለቀጣዩ ትውልድ ጤናማና ውብ አካባቢ እንፍጠር።
📍 ቦታ፦ ጥበበ ግዮን ግቢ
📅 ቀን፦ ሐምሌ 4፣ 2018 ዓ.ም.
🕒 ሰዓት፦ ጠዋት 3:00

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ-ሆሳዕና ምርምር ማዕከል ከኢትዮጵያ ብዝኅ ሕይዎት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የመጀመሪያዉን አገር አቀፍ ኮንፈረንስ ሰኔ 29/2018 ዓ.ም አካሄደ፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ

“ዩኒቨርሲቲዎችን በምርምር ማዕከላትና መናፈሻዎች አታክልት አማካኝነት ወደ ዘላቂ የላቀ ብቃትና የብዝኅ ሕይዎት  ጥበቃ መለወጥ››  በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ምሁራን፣የሀገር በቀል መዳህኒት አዋቂዎች፣ተመራማሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት  በቤንማስ ሆቴል አመታዊ ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የ ዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ ተሳትፎ  ም/ፕሬዝዳንት እንየዉ አድጎ (ፕ/ር) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለባሕላዊ ሕክምና ምርምር እና ለወደፊቱ ደግሞ በመላዉ ኢትዮጵያ የብዝኅ ህይወት ጥበቃ ዙሪያ ታሪካዊ ምዕራፍ የሚያስጀምር ልዩ ቀን ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 በፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 ጥቅምት ወር ላይ የተፈራረምነዉን የመግባቢያ ሰነድ በመከተል ፤ዛሬ በዚህ መገኘታችሁ  ይህ ትብብር በመደርደሪያ ላይ ብቻ እንዳልሆነ ግን ሕያዉ ፤ንቁና በእድገት ላይ ያለ መሆኑን ያረጋገጠ ነዉም ብለዋል፡፡
ባሕላዊ ፈዋሾቻችን የዚህን ማዕከል  እዉነተኛ ልብና ነፍስ የሆናችሁ፡በሙሉ ልብ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንደ ቅዱሰ አደራ የተላለፈዉ እዉቀታችሁ የስራችን መሰረታዊ ዓለት መሆኑ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጽኑና የማይናወጥ ከኢትዮጵያ ብዝኅ ሕይዎት ኢንሲቲትዉት ጋር ለረጅም ጊዜ እጅ ለእጅ ተያይዘን ፤በጋራ ምርምር፤ በጋራ ሀብታችን፤ በጋራና ቀጣይነት ትርጉም ያለዉ ትብብር እንደሚሰሩም በአጽዕኖት ገልጸዋል፡፡
በኮንፈረንሱ ላይ ቁልፍ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብዝኅ ህይዎት ኢንስትቲዩት ም/ዳይሬክተር የሆኑት  አቢዮት  ብርሃኑ (ዶ/ር) ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመስራታቸዉ ምርምራችን ሚጨበጥና ሚዳሰስ የምርምር ዉጤት እንደሚያገኙ ገልፀው የዩኒቨርሲቲው የስነ-ሆሳዕና  ምርምር ማዕከል ከሀገር በቀል መዳሕኒቶች እጽዋት  በትብብር ለመስራት አጠቃላይ ትብብር ማዕቀፍ ተፈራርመን ወደስራ ከገባን ቆይተናል ብልዋል፡፡
በአባይ ወንዝ ላይ የዕጽዋት አጸድ በማቋቋም ትልቅ እድገት እንደሚያመጣና ለባሕር ዳር ወይም ለአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ለአገር የሚጠቅም ምርምር እንደሚካሄድም እምነታቸውን ገልጸዋል። ለተማዋና አካባቢዋም የእጽዋት እድገት ምቹም ከመሆኑም የተነሳ ይህን አጋጣሚ ወደምርምር መለዎጥ አስፈላጊ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
እጽዋትን ማንበር/መጠበቅ/፤የባህል መዳህኒት አዋቂዎችን እዉቀት መጠበቅና በሳይንሳዊ መንገድ ዕዉቀታቸዉን ማሳደግ ተገቢ መሆኑን እና የዕጽዋት አጸደ ማቋቋም ያስፈለገዉ ዋናዉ አላማ የስነ-ሆሳዕና የምርምር ማዕከል የሀገር በቀል መዳህኒቶችን በሳንሳዊ ምርምር መጠበቅ ፤ማሳደግ፤የሚል መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስነ-ሆሳና የምርምር ማዕከል ዳይሬክተር  ደስታዉ ዳምጤ(ዶ/ር) እንዳሉት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የእጽዋት እዉቀት እየቀነሰ መምጣቱን እንዲሁም ሀገር በቀል ሕክምናዎች በተለያዩ ምክኒያቶች እየተዳከሙ መምጣታቸዉን ከነዚህም ዉስጥ የባህል መዳህኒት አዋቂዎች እድሚያቸዉ መግፋቱንና ለተተኪ ማዉረስ አለመቻላቸዉ፤ወጣቱም ለሀገር በቀል እዉቀቶች ያለዉ ደካማ አስተሳሰብ እንዳብነት እንደሚጠቀሱም ገልጸዋል፡፡የስነ-ሆሳዕና ምርምር ማዕከል እነዚህን የባህል አዋቂዎችን እዉቀታቸዉን  በዘመናዊ መንገድ እንዲሰንዱና እንዲታገዙ ማድረግ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ በኮንፈረንሱ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት  የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማሕበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክተር  ነጻነት ፈንታሁን (ፕ/ር)  እንዳሉት፡-የኮንፈረንሱ ዉይይት የሀገር በቀል ዕዉቀትን ለመጠበቅ፤በሳይንሳዊ መንገድ ለማረጋገጥ፤ለልማትና ለቀጣይ ትዉልድ ለማስተላለፍ እጅግ አስፈላጊ መሰረት የጣለ እንደሆነ ገልጸው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደምርምር ተኮር ዩኒቨርሲቲ በምርምር፤በማኅበረሰብ አሳታፊነት፤በቴክኖሎጅ ሽግግር እና ለፈጠራ ስራዎች ከፈተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ አውስተዋል፡፡  የስነ-ሆሳዕና ምርምር ማዕከል የሀገር በቀል ዕዉቀትን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማገናኘት፤በማረጋገጥ፤በመመዝገብና ለማኅበረሰቡ ጥቅም በማዋል የላቀ ሚና እንደሚጫዎት እና የአንድ ሀገር ዘላቂ እድገት የሚረጋገጠዉ የሀገር በቀል ጥበብን ከዘመናዊ  ሳይንስ ጋር በማጣመር መስራት ሲቻል መሆኑን ፕ/ሩ ገልጸዋል፡፡
 

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ስልጠናና ምዘና በይፋ አስጀመረ።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር፣ በአማራ ክልል የከተማ መሬት፣ ፕላን ዘርፍ እና የከተማ ፋይናንስ ባለሙያዎች ላይ ያነጣጠረ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ስልጠናና ምዘና ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት አካሂዷል።

ይህ ስልጠና ከ19/08/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 02/10/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 150 ሰልጣኞች በ5 ዋና ዋና የሙያ ዘርፎች ላይ ስልጠናውን ይወስዳሉ።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ጉዳዮች ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ነጻነት ፈንታሁን፣ ስልጠናው የንድፈ ሀሳብ እውቀት ብቻ ሳይሆን፣ ሰልጣኞች የተማሩትን እውቀትና ልምድ በመጠቀም የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን የማዘመንና የመመዝገብ ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የፌዴራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተወካይ ወ/ሮ ሰሎሜ ጥላሁን፣ ከተሞቻችን ዘመኑ ከሚጠይቀው አንጻር የመሬት አያያዝና ምዝገባን በማዘመን ለነዋሪዎች ግልጽና ምቹ አሰራርን መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

የአማራ ክልል የመሬት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብሬ ከበደ፣ በሀገር ሀብትና ጊዜ ታቅዶ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ሰልጣኞች በዲሲፕሊንና በትጋት በመሳተፍ የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ዲን ዶ/ር ሰይድ ሁሴን፣ ኢንስቲትዩቱ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ሆኖ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ለሚሰሩበት ተቋም አርአያ የሚሆኑ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል።  ስልጠናው በዋናነት የሚያጠነጥነው የመሬት ይዞታ መለኪያና ካርታ ስራ ፣የመሬት ይዞታ ምዝገባ ስርዓት፣ የከተማ ፕላንና የመሬት አስተዳደር፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ዋጋ ግምት፣ የከተማ ፋይናንስ (ወይም የከተማ የገንዘብ አስተዳደር) መሆናቸውን ገልጸዋል። አክለውም ዩኒቨርሲቲያችን ለሀገራችን የከተማ ልማትና የመሬት አስተዳደር ዘርፍ የላቀ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በማፍራት የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Hosts 3rd BRICS Think Tank Council Ethiopia Conference

Bahir Dar University, in collaboration with the Institute of Foreign Affairs, successfully hosted the 3rd BRICS Think Tank Council (BTTC) Ethiopia Conference from 22–23 April 2026, under the theme “The Prospect of BRICS and Ethiopia’s Priorities.” The high-level forum brought together diplomats, university presidents, scholars, researchers, and policy experts for two days of rich dialogue and strategic reflection.

In his welcoming remarks, Dr. Zewdu Emiru, Vice President for Information and Strategic Communication at Bahir Dar University, emphasized that the conference aimed to provide vital platform for exchanging ideas, sharing experiences, and generating actionable recommendations on key global and national priorities, thereby strengthening economic, political, and diplomatic cooperation among BRICS member countries and partner nations. He underscored the importance of translating insights and recommendations from policymakers, scholars, and researchers into strategies that advance shared development goals.

H.E. Mr. Mohammedrafi Abaraya, Deputy Director of the Institute of Foreign Affairs, in his opening remarks, highlighted the growing global significance of BRICS, noting that the bloc represents approximately half of the world’s population and over a quarter of global trade. He further emphasized Ethiopia’s emerging leadership role in Africa, particularly in areas such as technology and innovation, green development, agricultural transformation, and climate action.

In his address, H.E. Ambassador Minelik Alemu, Special Policy Advisor to the Minister of Foreign Affairs, described the conference as a vital platform for Ethiopia to expand its economic, research, and diplomatic engagement, while fostering meaningful knowledge exchange with new global partners.

Over the two days, participants engaged in substantive discussions across a range of critical global and national priorities. Parallel breakout sessions enabled deeper engagement, culminating in forward-looking recommendations that will be submitted to the 18th BRICS Academic Forum (2026) and subsequently to the XVIII BRICS Summit.

In his closing remarks, Dr. Mengesha Ayene, Bahir Dar University, reflected on the depth and quality of the discussions, noting that the conference successfully created a platform for critical reflection, knowledge exchange, and strategic alignment between Ethiopia and BRICS partners. He highlighted the importance of addressing global challenges, ranging from climate change and digital transformation to inclusive economic governance, through collaborative, research-driven, and policy-informed approaches.

Dr. Mengesha reaffirmed Bahir Dar University’s strong commitment to supporting such high-level intellectual engagements, positioning the University as a hub for policy dialogue, research collaboration, and international partnership. He further emphasized the University’s readiness to contribute to evidence-based policymaking and regional and global knowledge systems.

Following the conference, participants visited Bahir Dar University’s Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology (EiTEX), where they were introduced to the University’s achievements in textile innovation, research, and industry linkage. The visit, complemented by a brief city tour of Bahir Dar, was met with highly positive reflections from participants, who praised the University’s academic excellence, innovation ecosystem, and the city’s unique cultural and natural appeal.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

U.S. Alumni Engagement Highlights Impact, Innovation, and Community Transformation

The visit of H.E. Ervin Massinga, U.S. Ambassador to Ethiopia, to Bahir Dar University featured an engaging and insightful dialogue with U.S. program alumni hosted at Bahir Dar Institute of Technology (BiT). The session brought together a dynamic group of beneficiaries of U.S.-funded programs, entrepreneurs, scholars, and faculty members who have participated in various academic and professional exchanges.

The discussion provided a powerful platform for alumni to share how their experiences in U.S.-supported programs have translated into meaningful contributions at the local level. Participants highlighted their active roles in transferring knowledge and skills to students and communities, supporting youth entrepreneurship, start-up development, and innovation ecosystems, and driving business development initiatives and community-based solutions.

A key highlight of the session was the role of the U.S. Alumni Bahir Dar Chapter, hosted at BiT, which serves as a growing network for collaboration, mentorship, and sustained engagement among alumni.

The discussion also underscored the importance of strengthening platforms such as the American Corner, recognized as a vital resource for youth learning, access to information, and cross-cultural exchange. Participants emphasized the need to further expand such initiatives to maximize their impact.

Both the Ambassador and the participants reflected on the importance of sustained partnerships, alumni engagement, and investment in human capital as key drivers of development. The session concluded with a shared vision to further strengthen alumni networks and enhance collaboration between U.S. programs and Bahir Dar University in fostering innovation, leadership, and community transformation.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 14/08/2018 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለ ግሽአባይ ግቢ የጀማሪ መርሃግብር ም/ዲን  በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ ግሽአባይ ግቢ የጀማሪ መርሃግብር ም/ዲን 
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ማዕረግ/ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ሚያዚያ14 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 Academic V/Dean 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መንገሻ አየነ የተላለፈ የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ለዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብ፣ ለአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ለአገር አቀፍና ለዓለም አቀፍ አጋሮቻችን በሙሉ፤

ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን።

የትንሣኤ በዓል ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበትና ተስፋ የታደሰበት ታላቅ የድል በዓል ነው። ይህ በዓል ለእኛ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እንደ ተቋም የጀመርናቸው ታላላቅ የለውጥ ጉዞዎች ፍሬ አፍርተው የምናይበት አዲስ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት "ርዕይ ጥበብ ቁጥር ፪" የተሰኘውን የ5 ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት በማድረግ ወደ ሙሉ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲነት የምናደርገውን ታሪካዊ የሽግግር ጉዞ በቆራጥነት እያከናወነ ይገኛል። ይህ የራስገዝነት ርዕያችን የምርምር ዩኒቨርሲቲነታችንን በጽኑ መሠረት ላይ በማቆም በተግባር የተገለጠ ማኅበረሰባዊ ለውጥ ማምጣትን ያለመ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ሥርዓተ-ትምህርታችን ሁሉ ተጨባጭ ማሳያችን እንዲሆን በማድረግ የላቀ የዕውቀትና የጥበብ ማዕከል ለመሆን በትጋት እየሠራን እንገኛለን።

ይህ የ5 ዓመት የሽግግር ጉዞ ስኬታማ ይሆን ዘንድ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እንዲሁም የአካባቢያችን ማኅበረሰብና አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ አጋሮቻችን የምታደርጉት ድጋፍና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።

የትንሣኤው ብርሃን በሥራችን ሁሉ እንዲበራና ተቋማችንን ወደ ላቀ ከፍታ እንዲያሸጋግረው እመኛለሁ።
በድጋሚ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ።

ዶ/ር መንገሻ አየነ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 28/08/2018 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአካዳሚክ ዩኒቶች ውጭ በተለያዩ ክፍሎች በኃላፊነት የሚያገለግሉ የመካከለኛ እና ዝቅተኛ አመራር ምርጫ፣ ሹመት/ ምደባን ለመደንገግ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ/ም በወጣው መመሪያ’ መሰረት ለስብእና ግንባታ ምክትል ዲን የኃላፊነት ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ ለስብእና ግንባታ ምክትል ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ማእረግ/ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፤ በካውንስሊንግ፣ በክሊኒካል ሳይኮሎጂ፣ ወይም በሳይካትሪ እና ተዛማጅ ዘርፎች ሁለተኛ ዲግሪ እና በላይ
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት የስራ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፤
4ኛ. የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/የምትችል፤
አመልካቾች፡- ከሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ-ገዝነት ለመሸጋገር እያደረገ ያለውን  ጉዞ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  (መጋቢት 28/ 2018 ዓ.ም) — በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከሆኑ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ አጠቃላይ የአሠራር ዘይቤውን በመቀየር ወደ “ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት” ለመሸጋገር የሚያስችለውን የልየታ ሂደት በይፋ ማብሰሩን ገለጸ። ይህ ሽግግር ዩኒቨርሲቲው ሙሉ በሙሉ ወደ “ራስ-ገዝነት” (Autonomy) ለመሸጋገር ለያዘው ብሔራዊ ግብ እንደ ትልቅ መነሻ ተወስዷል።የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር ) በጉዳዩ ላይ እንደገለጹት፣ ተቋሙ ካለበት መደበኛ የመማር-ማስተማር ሂደት ወጥቶ በምርምርና ፈጠራ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን መወሰኑ ለሀገራዊ ዕድገት ያለውን ድርሻ ያሳድገዋል ብለዋል። አክለውም ዋናው ግባችን በምርምር ግንባር ቀደም መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርና የፋይናንስና የአካዳሚክ ነፃነቱን ያረጋገጠ ሙሉ በሙሉ ራስ-ገዝ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት እሰይ ከበደ (ፕ/ር)ያቀረቡት ዝርዝር የልየታ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ዩኒቨርሲቲው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጡትን ጥብቅ መመዘኛዎች ለማሟላት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በተጨማሪም ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በ“ምርምር-ተኮር” ምድብ ውስጥ እንዲካተት የሚያስችሉ የመምህራን ብቃት፦ ቢያንስ 50 በመቶ የሚሆኑት መምህራን የዶክትሬት (PhD) ዲግሪ ያላቸው መሆን፣የተማሪዎች ስብጥር፦ የድህረ-ምረቃ (ማስተርስና ዶክትሬት) ተማሪዎች ቁጥር አጠቃላይ ከተማሪው ብዛት 30 በመቶ መድረስ፣የበጀት ድልድል፦ ከዓመታዊ በጀቱ ቢያንስ 5 በመቶ ለምርምርና ምርምር ነክ ተግባራት ብቻ መመደብና ዓለም አቀፋዊነት፦ የውጭ የምርምር ፈንድ ማሰባሰብና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ስትራቴጂካዊ ትብብር መፍጠር ዋና ዋና ነጥቦች መሆነቸውን አስገንዝብዋል፡፡  ዩኒቨርሲቲው ከብዛት ይልቅ ለጥራት ትኩረት ለመስጠት ፕሮግራሞቹን በድጋሚ እየፈተሸ መሆኑ ጠቅሰው  በዚህም መሠረት፦ተደጋጋሚና ተመሳሳይ የሆኑ የትምህርት ዘርፎችን በመቀነስ በላቀ ጥራት ላይ ማተኮር፣ዘርፈ-ብዙ (Multidisciplinary) ምርምሮችን በማጠናከር ለሀገራዊ ችግሮች ተግባራዊ መፍትሔ ማመንጨትና በዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር መጽሔቶች ላይ የሚታተሙ የጥናት ውጤቶችን ቁጥርና ጥራት ማሳደግ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በሪፖርቱ ማጠቃለያ ላይ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት ጋር ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ለተነሱ ስጋቶችና ጥያቄዎች በ መንገሻ አየነ (ዶ/ር) መሪነት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። በውይይቱም ዩኒቨርሲቲው የጀመረው  የለውጥ ጉዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችለው እንደሆነ ሀሳብ ተወስዷል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Holds the 3rd Stakeholders’ Consultation Forum on the “LINK” Project, Aiming to Transform the Agricultural Sector

[Bahir Dar University – April 04, 2026]

Bahir Dar University, in collaboration with the The Austrian Partnership Programme in Higher Education and Research for Development (APPEAR) and HAUP University in Austria, successfully held the LINK-351 Project’s two-year performance review and stakeholder consultation workshop.

The University’s Vice President for Information and Strategic Communication, Dr. Zewdu Emiru, attended the forum and delivered a welcome address, reaffirming the university’s commitment to implementing community-based projects as a problem-solving institution.

Dr. Zewdu said the project would modernize the postgraduate Agroforestry curriculum, equipping graduates with the skills needed to better serve farmers as they enter the workforce.

The Dean of the College of Agriculture and Environmental Sciences, Prof. Melkamu Alemayehu, noted that the project effectively integrates the university’s three core missions: teaching, research, and community service. He added that a “Living Lab” involving 10 farmers is currently underway, that the project is enrolling and training Master’s students, and that a student is pursuing PhD studies in Austria, contributing to the development of high-potential scholars.

Project Coordinator Dr. Zerihun Yohannes presented the two-year performance report, stating that the project has successfully completed two-thirds of its planned three-year duration. He explained that the workshop aimed to evaluate progress made so far and to gather input from stakeholders to inform further problem-solving research.

During the forum, group discussions were facilitated by Dr. Habtamu Asaye, Mr. Mekonnen Getachew, and DRMFSS Director Dr. Emiru. Stakeholders, including farmers, researchers, and representatives from executive bodies, actively participated in the discussions.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

PhD Opportunity
Bahir Dar University (BDU) invites applications for one PhD position under the project “Understanding scaling of soil moisture retention practices for climate-resilient food production in semi-arid Ethiopia and Kenya - SMARTSCALE”.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በዲጂታል የታገዘ የሒሳብ ትምህርት (Interactive Digital Mathematics Education) አገራዊ ወርክሾፕ ተካሄደ
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም | ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ኮሌጅ የሒሳብ ትምህርት ክፍል "National Workshop on Interactive Digital Mathematics Education" በሚል ያዘጋጀው አገራዊ የወርክሾፕና የሶፍትዌር ምርቃት መርሃግብር ተካሂዷል።

ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕ/ር እሰይ ከበደ፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኢትዮጵያ የትምህርት ስትራቴጂክ ዕቅድ አንዱና ዋነኛው መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ መድረኩ ላይ ለተገኙ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሳይንስ ኮሌጅ ዲን ፕ/ር ብርሃኑ አሳዬ በበኩላቸው፣ ለተጋባዥ እንግዶቹና ለተመራማሪዎቹ ምስጋና በማቅረብ የመድረኩን አስፈላጊነት አስገንዝበዋል።

ስለ ወርክሾፑ ዓላማና ስለ ሶፍትዌሩ ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡት የዩኒቨርሲቲያችን መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አብዱ መሐመድ፣ "Interactive Digital Mathematics" መጽሐፍ/ሶፍትዌር መዘጋጀቱ በሒሳብ ትምህርት ዘርፍ ያለውን የመምህራን እጥረትና የተማሪዎችን የግብረ-መልስ (Feedback) ችግር እንደሚቀርፍ ገልጸዋል።
አክለውም"ይህ ሶፍትዌር እያንዳንዱ ተማሪ ስህተቱንና ጥንካሬውን በራሱ እንዲለይ እንደሚረዳና ይህም ልክ ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ መምህር እንደተመደበለት እንደሚቆጠር እንዲሁም ሶፍትዌሩ የተዘጋጀው በአገራዊ የትምህርት ሥርዓተ መሠረት በመሆኑ፣ ጥቅሙ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንደሚተርፍ ገልጸዋል።

ከኬንያ ዩኒቨርሲቲ የመጡት መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ሚካኤል ኦቤሮ  INNODEMS and their Collaboration with Ethiopian Universities" በሚል ርዕስ ልምዳቸውን አጋርተዋል።
ዶ/ር ሚካኤል ተማሪዎች ሒሳብን እንዲወዱ ለማድረግ የማስተማር ዘዴን መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል። ሒሳብን በጨዋታ (Games)፣ በእንቆቅልሾች (Puzzles) እና በካርዶች (Cards) ማስተማር ተማሪዎችን የበለጠ እንደሚያነቃቃ ገልጸው፤ የራሳቸውን ተሞክሮ ሲያካፍሉም፦ "እኔ ራሴ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ በሒሳብ ጎበዝ አልነበርኩም፤ ነገር ግን በጨዋታ መልክ መለማመድ  መቻላቸው ፍላጎቱ እንደ ጨመረላቸውና ዛሬ ደግሞ የሒሳብ ምሁር ለመሆን እንዳበቃቸው ልምዳቸውን አካፍለዋል።

በመርሃግብሩ በዶ/ር አብዱ መሪነት የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በውይይቱ የተሳተፉት ከትምህርት ሚኒስቴርና ከክልል ትምህርት ቢሮ የመጡ እንግዶች የሶፍትዌሩን ቀጣይነት ለማረጋገጥና ለማስፋፋት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከክልል ትምህርት ቢሮ የመጡ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከኬንያ የመጡ መምህርና ተመራማሪ፣ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ተገኝተዋል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel