📚 Ganda Beeyladootaa | Animal Farm | የእንስሳት ዕድር
Har’a galgala sa'aatii 2:00 irratti nuu eega!
Animal Farm በአፋን ኦሮሞ ተተርጉሞላችሁ መጥቷል። ዛሬ ምሽት 2:00 ላይ ይለጠፋል።
@goferebooks
#ቅምሻ
የሰው ልጅ በልቡ ያስባል ወይስ አያስብም?
ጤና ይስጥልኝ! ውድ አንባቢዎቼ በዛሬው ጽሑፌ የሰው ልጅ በልቡ ያስባል ወይስ አያስብም? በሚል ርዕስ ያገኘኋቸውን ነጥቦች አጋራችኋለሁ።
በድሮ ዘመን ሰዎች የሰው ልጅ በልቡ ያስባል የሚል እምነት ነበራቸው። የሰው ልጅ በልቡ ያስባል ብቻ ሳይሆን ሁሉም ስሜቶች የሚመነጩት ከልብ ነው ይሉ ነበር። ይህንን አስተሳሰብ የሚያጠናክሩ በርካታ አባባሎችም አሉ።
ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል “በፍቅር የተሞላ ልብ በመከራም ውስጥ ሆኖ መልካም ነገርን ያስባል”፤ “ጥሩ ልብ የሌሎችን መጥፎነት አያስብም”፤ “A thinking heart is the source of wisdom and the master of the brian” የሚሉ አባባሎች የሰው ልጅ በልቡ እንደሚያስብ የሚገልጹ እምነቶችን ያመለክታሉ። በየዘመኑ በተደረጉና በሚደረጉ ጥናቶች የሳይንስ ባለሙያዎች ይህንን አስተሳሰብ ለማጥናት እና ለመበየን በጣም ብዙ ጥረት እድርገዋል።
የሰው ልጅ በልቡ ያስባል ወይስ አያስብም? የሚለው ጥያቄ እስካሁን ድረስ አጠያያቂና አከራካሪ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። ሁላችንም እንደምናውቀው እያሰበና እያሰላሰለ ለቀሪዎቹ የሰውነት ክፍሎቻችን ትዕዛዝ የማስተላለፍ ተግባር የተሰጠው ለአዕምሯችን ነው። ይህ ማለት ግን ልባችን አያስብም ወይም ስሜት የሚመነጨው ከልባችን አይደለም ብሎ ለመደምደም አያስችልም።
ከስሜት ጋር በተያያዘ ልብን ከሆርሞኖች ጋር አያይዞ የሚያጠናው ካርዲአክ ኢንዶክሪኖሎጂ (Cardiac endocrinology) የተሰኘ ራሱን የቻለ ሳይንስ አለው። ሆርሞኖች ከልብ አጠገብ ስለሚያልፉ፤ እንዲያውም ነክተውት ስለሚያልፉ ስሜት ከልባችን ጋር ተያያዥነት አለው የሚል በሳይንስ የተደገፈ ሀሳብ ስላለ ልብ ያስባል የሚለው አስተሳሰብ በጥቂቱም ቢሆን እውነትነት አለው።
ይህ አስተሳሰብ ዛሬም ያልተቋጨ በመሆኑ ምርምሩም ክርክሩም ይቀጥላል። በጥሞና ስላነበባችሁልኝ ከልብ አመሰግናለሁ።
ተማሪ ህሊና የሺዋስ
ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
———
ታዳጊ ህሊና የሺዋስ “ስለ ልብ የተነገሩ ምርጥ አባባሎች” እና “ANATOMY AND PHYSIOLOGY OF THE HEART” የተሰኙ ሁለት መጽሓፍትን ያዘጋጀች ስትሆን ወንድሟ ቅዱስ የሺዋስ ደግሞ “THE FUNDAMENTAL OF AIRPLANE DESIGN” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ አብቅቷል። Kudos to them👏👏👏
የተማሪ ህሊና የሺዋስ የቴሌግራም ቻናሏን ተቀላቀሏት፣ አበረታቷት👇
/channel/Cardiology101
#goferebooks #gofere #books #book #ethiopia #ethiopian #ethiopians #ethio #eritrea #eritrean #africa #african #africans #kimsha #ጎፈሬ #ጎፈሬ_ቡክስ #ኢትዮጵያ
@goferebooks
የቻናል ጥቆማ ~ Rica Trip ቴሌግራም ቻናል❗️
🚕 ሪካ ትሪፕ (Rica Trip)፣ በከተማችን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ የራይድ ካምፓኒ ነው።
ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ተቀላቀሉ 👇👇👇
/channel/+ggQ9tT5Q6xllYjFk
/channel/+ggQ9tT5Q6xllYjFk
/channel/+ggQ9tT5Q6xllYjFk
የቻናል ጥቆማ ~ Rica Trip ቴሌግራም ቻናል❗️
🚕 ሪካ ትሪፕ (Rica Trip)፣ በከተማችን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ የራይድ ካምፓኒ ነው።
👇👇👇
/channel/rica_trip9899
/channel/rica_trip9899
/channel/rica_trip9899
ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን!
አሜሪካዊ ደራሲ፣ መምህር፣ ፈላስፋ እና ገጣሚ የነበረ የጥበብ ሰው!
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #RalphWaldoEmerson #RalphWaldoEmersonquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes
@investorscafethiopia
#ዕድል
#motivation #investorscafe #investors #investment #ethiopia #ethioinvestors
@investorscafethiopia
ቢል ኮዝቢ ~ አሜሪካዊ ኮሜዲያን፣ ተዋናይ እና ደራሲ!
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #BillCosby #BillCosbyquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes
@investorscafethiopia
ግብ እንዴት ልቅረጽ?
ለቢዝነሳችንም ሆነ ለግል ሕይወታችን የት እና እንዴት መድረስ እንደምንፈልግ ግልጽ የሆነ ግብ መያዝ ከመባከን ያድነናል። ይሁን እንጂ ሰዎችም ሆኑ ቢዝነሶች ብዙ ጊዜ ግባቸውን ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ይቸገራሉ፤ አንዳንዴ እንደውም ጭራሽ ምንም ግብ ሳይቀርጹ ይቀራሉ።
የትኛውም ዓይነት ግብ ሲቀረጽ፣ በሚከተለው መልኩ ቢሆን ለመቅረጽም፣ ለመከታተልም፣ እንዲሁም ለመተግበር ያመቻል። ይህ የግብ አቀራረጽ ዘዴ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል “SMART” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ 5 መስፈርቶች አሉት።
የትኛውም የምናስቀምጠው ግብ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ መሆን ይኖርበታል።
1. የማያሻማ (Specific)
የማያሻማ ግብ ማለት ግልጽ እና “ምን ማለት ይሆን?” የማያሰኝ መሆን አለበት።
ለምሳሌ፣ “በዚህ ዓመት ስኬታማ መሆን” የሚለው ፈጽሞ ለአንድ ቢዝነስ ግብ ሊሆን አይችልም። ስኬታማ ሲል ምን ማለት እንደሆነ፣ በዝርዝር እና ቁልጭ ባለ መንገድ መገለጽ መቻል አለበት።
2. የሚለካ (Measurable)
የሚለካ ግብ ማለት ተሳክቷል አልተሳካም የሚለው በቀላሉ መመዘን የሚችል ማለት ነው።
ለምሳሌ፣ “ትርፋማ መሆን” የሚለው ግብ የሚለካ አይደለም። “የአንድ ሺህ ብር ትርፍ ማግኘት” የሚል ብናደርገው፣ ምን ያህል ተሳክቷል የሚለው በቀላሉ መመዘን ስለሚችል የሚለካ ግብ ሆነ ማለት ይቻላል።
3. ሊደረስበት የሚችል (Achievable)
ግባችን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ለመሳካት የማይቻል መሆን የለበትም። ሊደረስበት የሚችል የሚለው የሚያመለክተው ካለንበት ወቅታዊ ይዞታ አንጻር የመሳካት ዕድል ያለው መሆኑን ነው።
ለምሳሌ፣ በወር የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ዝውውር ያለው ቢዝነስ፣ “በዓመቱ መጨረሻ የአንድ ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት” ቢል ካለበት ሁኔታ ጋር የማይጣጣም እና ሊደረስበት የማይችል ሆኖ ይገኛል። ይልቅ፣ ነገሮችን አገናዝቦ የበለጠ ሥራን በሚያበረታታ መልኩ ከፍ ያለ ግን ከእውነታው በጣም ያልራቀ ግብ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
4. ከእውነት ያልራቀ (Realistic)
ይህ “ሊደረስበት የሚችል” ከሚለው ጋር ተቀራራቢ የሆን መለኪያ ነው። “ሊደረስበት የሚችል” የሚለው የራስን አቅም ማገናዘብን የሚመለከት ሲሆን፣ “ከእውነት ያልራቀ” የሚለው ደግሞ የምንኖርበትን አገር እና አካባቢያዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባትን የተመለከተ ነው።
ለምሳሌ፣ አሁን ባለው የአገራችን ሁኔታ፣ የቱንም ያህል የገንዘብ እና የሰው ኃይል አቅም ቢኖረን በኦንላይን የገንዘብ ዝውውር የመላው ዓለም ሰዎች የሚገበያዩበት የግብይት ቢዝነስ ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመር አይቻልም። እንዲህ ያለ ግብ አንድ ሰው ቢቀርጽ፣ ከእውነት የራቀ ሆኖ ይገኛል።
5. በጊዜ የተገደበ (Time-bound)
የጊዜ ወሰን ያልተበጀለት ግብ፣ ግብ ሳይሆን ሕልም ነው። “የእኔ ቢዝነስ ወደፊት አንድ ቀን አንድ ሚሊየን ብር ትርፍ ይኖረዋል” ማለት ጥሩ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግብ አይደለም። ይህ የሚሆነው መቼ ነው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ መመለስ ይኖርበታል።
ለምሳሌ፣ “አንድ ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት” የሚለው ‘ሕልም’ “የሚቀጥለው ሰኔ መጨረሻ አንድ ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት” የሚለው ቢጨመርበት በጊዜ የተገደበ ግብ ይሆናል።
አምስቱን የትክክለና ግብ መገለጫዎች ስናስብ መርሳት የሌለብን ነገር፣ አንድ ግብ እውነትም ግብ እንዲባል ከአምስቱ አንዱን ወይም ሁለቱን ቢያሳካ በትክክል ግብ ሊባል አለመቻሉን ነው። ግባችን እውነትም ግብ እንዲባል አምስቱንም የትክክለኛ ግብ መለያዎች ማሟላት ይኖርበታል።
(Kefta)
#investorscafe #investors #investment #business #businesstips #businessideas #ethiopians #Ethiopia #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors
@investorscafethiopia
#ወቅታዊ
የኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይተዋወቁ!
በቅርቡ ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ያደረጋቸውን ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን በአጭሩ እናስተዋውቃችሁ።
ቴሌ ብር መላ
የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ በቀን እስከ 2,000 ብር፣ በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው።
ቴሌ ብር እንደኪሴ
በቴሌብር አማካኝነት ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ የቴሌብር ሂሳብዎ ከሚገዙት እቃ በታች ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ ይከፍልና ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ ከሂሳብዎ ላይ ተቀናሽ የሚያደርግ አገልግሎት ነው።
ቴሌብር ቁጠባ
ቴሌብር ላይ ካለው የገንዘብ መጠን ላይ መቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን በሁለት አማራጮች ማለትም በወለድና ያለወለድ የቀረበ ነው። የወለድ መጠኑም 7% ሲሆን የወለዱ መጠን በቀን ተሰልቶ በሂሳብዎ ገቢ ይደረጋል።
#investorscafe #investors #investment #ethiopia #ethioinvestors
@investorscafethiopia
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #AlbertEinstein #AlbertEinsteinquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes #ኢትዮጵያ
@investorscafethiopia
ስቲቭ ጆብስ ~ የአፕል ካምፓኒ መስራች
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #SteveJobs #SteveJobsquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes #ኢትዮጵያ
@investorscafethiopia
አል ደንከን ~ አነቃቂ ንግግር አቅራቢ
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #AlDuncan #AlDuncanquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes #ኢትዮጵያ
@investorscafethiopia
#425
የአፋን ኦሮሞ PDF ግብዣ
📚 Seenaa Gabaabaa Abuubakar Muussaa
✍🏾 Abbaa Urjiitiin
Qabiyye (Genre): Seenaa dhuunfaa (Biography)
Lakkoofsa fuulota: 18
Seenaa Abuubakar Muussaa fi
Gumaata Guddina Afaanii fi Aadaa Oromootiif laate
Dubbisuu fi share gochuudhaan dirqama Afaan keenyaa guddisuus haa baanu!
"BE CHAIN READER"
@goferebooks
#369
📚 ከርቸሌ
በስንዱ አበበ
ንዑስ ርዕስ: በውስጥ ዓይን
ይዘት: እውነተኛ የታሪክ ማስታወሻ
የገጽ ብዛት: 45
የኅትመት ዘመን: 1998 ዓ.ል.፣ አሳታሚ ስንዱ አበበ (በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ)
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በነበረው «ከርቸሌ» የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች፤ የቀድሞ ቦታው ለሌላ ጉዳይ ስለተፈለገ እየፈረሰ መሆኑን ሰማሁና ለረዥም ዓመታት በዕጄ የሚጉላላው የአንዲት ጓደኛዬ የከርቸሌ ቆይታ ሰነድ ትዝ አለኝ።
ከ1991-1993 ዓ.ም ማለቂያ ለሦስት ተከታታይ ዜያቶች አንድ ዓመት ቆይታ የወጣችው ጓደኛዬ ስለከርቸሌ ማውራት ባትወድም፤ በብዙ ጉትጎታ የቻለችውን በማስታወሻ፣ የጎደለ የመሰለኝን በጥያቄና መልስ ሞልቼ ይህን መረጃ አግኝቻለሁ።
ይህ መረጃ በሴቶች እስረኞች የመኖሪያ ክልል ያለውን ሁኔታ ብቻ የሚያሳይ፤ ከከርቸሌ ብዙ ገድሎች «አባይን በጭልፋ» ታክል የተቆነጠረ እውነተኛ ታሪክ ነው።
ከመጽሐፉ የተቀነጨበ
በከርቸሌ ግዙፍ ዓለም ውስጥ በድንገት ከተሠራ ስህተት የተረፈ እልፍ ፀፀትና ንዴት፤ በበቀልና በጥላቻ በተፈጸመ የክህደት ሰንሰለት እንደየወንጀሉ ዓይነት፤ ሰዎች ማንም ተመልካች በሌለበት እስር ቤት ውስጥ ብዙ በደሎች ይደርሱባቸዋል። በግቢው ውስጥ ያለነው ታራሚዎች በእኩል ዓይን አንታይም! ፖሊሶች፣ ሲያላግጡ «እኩል የምትሆኑት ፍርድ ቤት ብቻ ነው!» ይላሉ። እውነትም ነው!
#ሼር
"BE CHAIN READER"
@goferebooks
#ቅምሻ
ባዶ በርሜል!
___
“ባዶ በርሜል ስታንከባልለው ይጮኋል፡፡ በዛው ልክ በውሃ የተሞላን በርሜል ስታንከባልለው ድምፅ የለውም። ሲንከባለልም በእርጋታ ነው። የሰው ልጅም እንደዛ ነው። ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ ሰው ከመጮህ እና ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ የሚችለው ነገር የለም፡፡ በዕውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡ በጮኽን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡
ራሳችንን በዕውቀት እንገንባ!!!”
___
ከዶ/ር ምህረት ደበበ
(Zein Nure እዳጋራው)
@goferebooks
የቻናል ጥቆማ ~ Rica Trip ቴሌግራም ቻናል❗️
🚕 ሪካ ትሪፕ (Rica Trip)፣ በከተማችን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ የራይድ ካምፓኒ ነው።
👇👇👇
/channel/rica_trip9899
/channel/rica_trip9899
/channel/rica_trip9899
የቻናል ጥቆማ ~ Gofere Books ቴሌግራም ቻናል❗️
☕️ በዚህ ቻናል ቆየት ያሉ (ከገበያ የጠፉ) የአማርኛ መጻሕፍት፣ የAfaan Oromoo መጻሕፍት እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ዝናን ያረፉ የእንግሊዝኛ መጻሕፍትን የሚያገኙበት ነው።
🔹ወጎች 🔹ግጥም
🔹ልብ-ወለድ 🔹ራስ-አገዝ
🔹ስነ-ልቦና 🔹ቀልድ
🔹ታሪክ 🔹ሳይንስ
🔹ፍልስፍና 🔹ግለ-ታሪክ...ወዘተ
Join our readers community to shape your future life.
👇🏾👇🏾👇🏾
/channel/goferebooks
/channel/goferebooks
ናፖሊዮን ሂል!
አሜሪካዊ የራስ አገዝ መጽሐፍ ደራሲ ሲሆን የሰዎችን የግል መነሳሳትና የጋለ ስሜት የሚፈጥሩና አስተሳሰብን የሚያሠፉ መጽሓፍትን በመጻፍ ይታወቃል፡፡ በተለይም “Think and Grow Rich” በተሰኘው መጽሐፉ በዓለም ያሉትን የአንባቢውን ልብ የሠረቀበትና በብዙ ሚሊዮን ኮፒ ቸብችቦ ብዙ ገንዘብ ያስገኘለት ነበር።
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #NapoleonHill #NapoleonHillquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes
@investorscafethiopia
#ወቅታዊ
(ክፍል 1)
መካሪና ሰባኪ በዝቷል። ከመገናኛ እስከ ኢኒስታግራም፤ ከዩትዩብ እስከ ድልብ መጻሕፍት፣ ከመድረክ እስከ ታክሲ...!
የሁሉም መልዕክት አንድ ነው፤ ‘የብልጽግና ባቡር ቀርባለችና ተሳፈሩ’ የሚል። በየዓመቱ መቶ ሺዎች እየተመረቁ ሥራ ያጣሉ። ‘የሥራ ፍጠሩ’ ሰባኪዎች ይቀበሏቸዋል። በስንት ደጅ ጥናት የተገኘን ሥራ ‘ጥላችሁ ውጡ’ ይላሉ። ዛሬውኑ የራሳችሁ አለቃ ሁኑ እያሉ ያስጎመዣሉ።
ከእጅ ወደ አፍ ቀርቶ፣ እንደ ወፍ- ከአፍ ወደ አፍ በሆነ የዛሬ ኑሮ፣ ‘ከቆጠባችሁ ከነገ ወዲያ ሚሊዮነር ትሆናላችሁ’ ይላል።
አነቃቂ መጻሕፍት ሕይወት ይለውጣሉ! የመድረክ ዲስኩሮች ያበለጽጋሉ? አንዳንዶች ‘አዎና! እኛን ነው ማየት!’ ይላሉ። ሌሎች ደግሞ በአነቃቂ መጻሕፍት የሚለወጥ ሕይወት ካለ የደራሲውና የዲስኩረኛው ብቻ ነው ብለው ያፌዛሉ። በሁለቱም ጎራ የካበተ ልምድ ያላቸውን አሰልፈን ጉዳዩን ብናብላላውስ?
ዶ/ር ወሮታው፡ “የአንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት ለመለወጥ እየሠራሁ ነው”
በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ግንኙነት ሦስተኛ ዲግሪ አላቸው። የእርሳቸው ሥራ ግን የሰዎችን አእምሮ ከብልጽግና ጋር ማዋደድ ነው። ወጣቶችን ወደ ሃብት ማማ ማውጣት። የትኛውንም አእምሮ በመግራት ስኬትና ልዕልናን ማጎናጸፍ ይቻላል ብለው ያምናሉ።
እንደተመረቁ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ተቀጠሩ፣ ከዚያም ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ሆኑ።
ከዕለታት አንድ ቀን “ሕይወቴን የሚለውጥ አጋጣሚ ተፈጠረ” ይላሉ ዶ/ር ወሮታው። ቀንና ወሩን ሁሉ አይረሱትም። 1992 ዓ.ም. ነሐሴ ከዩኒቨርስቲው ለስልጠና ተላኩ። አሰልጣኞቹ ከጋና የመጡ ነበሩ። የሥልጠና ማዕከሉ ‘ኢንተርፕራይዝ ኢትዮጵያ’ ይባል ነበር። ሥልጠናውን ሲጨርሱ ከባድ የአስተሳሰብ ነውጥ ገጠማቸው። የአስተሳሰብ ነውጡ፣ የሕይወት ለውጥን አስከተለ።
“በዚያች ቅጽበት የራሴን ነጻነት አወጅኩ፤ ከዚያ በኋላ በጭራሽ አልተቀጠርኩም፤ በጭራሽ!” ይላሉ።
“ተቀጥሮ መሥራት አንገሽግሾዎት ስለነበር ነው ዶ/ር?"
“አይደለም፤ በዚያች ቅጽበት የምኖርለትን ሕልሜን ስላገኘሁ ነው።”
"የሚኖሩለት ሕልም ምንድን ነበር?"
“ማሰልጠን፤ ባለጸጎችን ለኢትዮጵያ ማፍራት።”
“የምር ይሳካል ብለው ያምናሉ?”
“ያለጥርጥር! አንድ ሚሊዮን ባለጸጎችን ለኢትዮጵያ እናፈራለን።”
“መቼ ነው ይህን ሁሉ ሰው ባለጸጋ የሚያደርጉት?”
“የዛሬ 20 ዓመት፤ በነሐሴ 2023 ዓ.ም።”
ዶ/ር ወሮታው ይህን የሚሉበት እርግጠኝነት የእምነታቸውን ጥንካሬ ያሳብቃል። እንዴት ያለ ሥልጠና ቢሆን ነው?
“...በዚያ ሥልጠና ወሮታው ላይ ሳቅኩበት፤ ወሮታውን ነጻ አወጣሁት። ለሕልሜ ታማኝ እንድሆን፣ ሃብቴ አስተሳሰቤ እንደሆነ፣ የማምንበትን እየሠራሁ እንድኖር ያደረገኝ አጋጣሚ ነበር።”
የእሳቸው ሕይወት በአንድ ሥልጠና ከተለወጠ የሌሎች ሕይወት ለምን አይለወጥም?
ናትናኤል ፋንታ፡ “የሞቲቬሽን ሥልጠና በብድር መደሰት ማለት ነው”
‘ናትናኤል ሜሞሪ’ በሚለው የንግድ ስሙ ድፍን በርካቶች ያውቀው ይሆናል። የሕይወቱን እኩሌታ በአእምሮ ሥልጠና ላይ አሳልፏል። ናትናኤል በተለይ በማስታወስ ጥበቡ በ90ዎቹ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እየቀረበ ብዙ ሰዎችን ሲያስደምም አንዳንዶች ዛሬም ድረስ ያስታውሱታል።
ናትናኤል ከማስታወስ ጥበብ በኋላ በቀጥታ ወደ ‘ሞቲቬሽን’ [ማነቃቃት] ተሸጋገረ። ብቻ በጥቅሉ ባለፉት በ21 ዓመታት በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአእምሮ ጋር በተያያዘ አሰልጥኗል።
የእሱን ልብ አንጠልጣይ ‘ሞቲቬሽን’ ቃል ለመስማት ብዙዎች 22 አካባቢ ደጅ ጠንተዋል።
እሱም ያንን ዘመን በመለስተኛ ፀፀት እያስታወሰ፣ “...ሙሉ ጉባኤ ቁጭ ብድግ አስደርግ ነበር” ይላል።
አሁን ግን ፍጹም በተቃራኒው ቆሟል። የአነቃቂ ንግግሮች አድናቂ አይደለም። እንዲያውም ‘ሞቲቬሽን’ አይሠራም ሲል አውጇል።
“ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ያረጋገጥኩት አንድ ነገር ቢኖር የሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ ትክክለኛው መንገድ ያ እንዳልነበረ ነው” ይላል።
ለምን? በ21 ዓመት ውስጥ ምን ተፈጠረ? ትክክለኛው መንገድ ያ ካልሆነ ታዲያ የቱ ነው?
በዓመታት ጥናት ደረስኩበት የሚለውን ይነግረናል።
የአነቃቂ መጻሕፍት አጭር የሕይወት ታሪክ
ራስ አገዝ መጻሕፍት፣ የይቻላል ዲስኩሮችና መሰሎቻቸው በጅምላው ‘ሰልፍ ዴቨሎፕመንት ኢንዱስትሪ’ ውስጥ ይከተታሉ። በአሜሪካ በአንድ ወቅት ከሙዚቃ ኢንዱስትሪው ቀጥሎ ሚሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ዘርፍ ነበር። በተለይ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ወዲህ።
የአነቃቂ መጻሕት አባት የሚባለው ቻርልስ ሃናል ነው። ኋላ የመጡት ገናናዎች የእርሱ ደቀ መዛሙርት ናቸው። በዘመኑ የጻፈው ነገር አእምሮን የሚያሸፍት ነበር። “…ኋላ ላይ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን መጽሐፎቹን ለቅማ አቃጥላበታለች” ይላል ናትናኤል።
ከእርሱ በኋላ አብረሃም ማስሎው መጣ። “አእምሮን በመግራት ማንም ሰው ምንም መሆን ይችላል” ብሎ ተነሳ። ቀስ በቀስ ሞቲቬሽን ከቤትና ከቢሮ ወጥቶ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሰተት ብሎ ገባ። የይቻላል መንፈስ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንቀጾች ጋር ስምም ሆኖ በሰባኪዎች አንደበት ተነገረ። ሚሊዮኖች በተስፋ ራሳቸውን ሳቱ። ያለስስት ጥሪታቸውን ለሰባኪያን ሸለሙ። ከአፋቸው ማር ጠብ የሚልልላቸው ሰባኪየን መቅደስ ጠበባቸው። በቲቪ መስኮት መጡ። ‘ቴሌቫንጀሊስቶች’ ተወለዱ። በስብከት ጉባኤ መዋጮ የግል ጄት ገዙ። ምዕመናን የታክሲ እያጡ፣ እየነጡ መጡ። ካፒታሊዝም ፋፋ። የገበያ ትንቅንቅ ተፈጠረ። ‘ሞቲቬሽን’ ሽያጭን የሚያስመነድግ ሁነኛ መሣሪያ እንደሆነ ተደረሰበት። ሰዎች የስቶክ ማርኬት የድርሻ ገበያ እንዲገዙ ማሳመን ፈተና ሆኖ ነበር። ለዚያም ነው በሞቲቬሽን አእምሯቸውን ማጦዝ፣ በተስፋ ካውያ ማጋል አስፈላጊ ሆኖ የተገኘው። እንዲህ እንዲያ እያለ በ80ዎቹ እና በ90ዎቹ የሞቲቬሽን ኢንዱስትሪ ጣሪያ ነካ። ደራሲያን ሚሊዮን ቅጂ መሸጥ ጀመሩ። በእኛም አገር ‘ኔትዎርክ ማርኬቲንግ’ በስፋት ዘልቆ ገባ።
የ’ጎልድ ኩዌስት’ ዘመን፣ የፒራሚድ ገበያን ለማሳለጥ ሁነኛ የ’ሴልስ’ ስትራቴጂ ኾኖ አገለገለ። ሐኪሞች ሆስፒታልን፣ መምህራን አስኳላን ጥለው ወጡ፤ ወደ ሀብት ይወስዳል የተባለው አውራ ጎዳና በሕዝብ ታመቀ፣ተጨነቀ። ብዙዎች “አይቤን ማን ወሰደው”ን እያነበቡ አይባቸውን ፍለጋ ባዘኑ። አንዳንዶች አገኙት። ብዙዎች አጡት።
ናትናኤል ያን ዘመን የነበረውን አስደማሚ መነቃቃት ሲያስታውስ፣ “አዳራሽ ውስጥ ‘I believe I can fly’ የሚል ሙዚቃ ተከፍቶ ሰዎች በተስፋ ብቻ ሲያለቅሱ አይቻለሁ’ ይላል። ይህን ነው እሱ “የብድር ደስታ” የሚለው። ምን ማለቱ እንደሆነ ቆየት ብሎ ያስረዳናል።
(ይቀጥላል...)
#investorscafe #investors #investment #ethiopia #ethioinvestors
@investorscafethiopia
በዛሬው የጥቆማ መርሃግብራችን በእኛ አገር እድናቆትን ካተረፉ ጠንካራ የቢዝነስ ሰዎች መካከል፣ የአምባሳደር ልብስ ስፌት ባለቤት ሆኑትን አቶ ሰዒድ መሐመድን ያሳለፉትን ውጣ ውረድ እና ያገኙትን ስኬቶች በራሳቸው አንደበት ያጋሩናል፡፡
በሚከተሉት የዩቲዩብ መስፈንጠሪያዎች (Links) ይከታተላሉ😊
ክፍል 1
https://youtu.be/Qv1bSVwp2Nk
ክፍል 2
https://youtu.be/oIKKP7F5ybQ
«Think Big»
#investorscafe #investors #Ethiopia #investment #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #AmbassadorRealEstate #AmbassadorHotel #AmbassadorMall #SeidMohammedBirhan
@investorscafethiopia
ላሪ በርድ ~ ከምንጊዜውም ምርጥ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች አንዱ የነበረ...!
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #LarryBird #LarryBirdquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes
@investorscafethiopia
ዩሪፒደስ ~ ከጥንት ግሪክ የጥበብ ሰዎቹ አንዱ የነበረ...!
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #Euripides #Euripidesquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes
@investorscafethiopia
ቲም ኩክ ~ የአፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ!!!
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #TimCook #TimCookquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes #ኢትዮጵያ
@investorscafethiopia
ካህሊል ጂብራን (1883-1931) ~ ሊባኖስ የተወለደው ጂብራን የዘመናችን ድንቅ ጸሐፊ፣ ሠዓሊ፣ ገጣሚ፣ ባለቅኔና ፈላስፉ ነበር።
«Think Big»
#investorscafe #investors #investment #KahlilGibran #KahlilGibranquotes #motivation #quote #ethiopians #ethiopia #ethiopian #ethio #ethioinvestors #Ethiopia #motivationalquotes #ኢትዮጵያ
@investorscafethiopia
#ቅምሻ
ቅንነት የክፉ ቀን ስንቅ😊
እንዲህ እንደዋዛ ቀን ሳይጥላት በፊት ሕንድ ውስጥ በምትገኝ ኪራላ በምትባል ከተማ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የሒሳብ መምህርት ነበረች። አንድ ቀን የቀድሞ ተማሪዋ ባቡር ልትሳፈር ተሰልፋ ዘወር ስትል ከዓመታት በፊት የሆነ ቦታ የምታውቀው ፊት ጋር ተገጣጠመች። ይሄንን ኑሮ ያጎሳቆለውን የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር የተፈራረቁበትን ፊት የት እንደምታውቀው ለማስታወስ ብዙ ጥረት ካደረገች በኋላ የቀድሞ ሂሳብ መምህሯ መሆኗን አስታወሰች።
ተማሪዋም ከሰልፉ መኸል ፈጠን ብላ በመውጣት "ይቅርታ አድርጊልኝና አንቺ ሒሳብ አስተማሪ አልነበርሽምን?" አለቻት። መምህርትም መለሰች "አዎ ከዓመታት በፊት የሂሳብ አስተማሪ ነበርኩ፤ ነገር ግን ጡረታ ስወጣ ደሞዜ ለኑሮ በቂ አልነበረም። ድህነት እና እርጅና ሲጫኑኝም ልጆቼ ጥለውኝ ሄዱ። አሁን ጭራሹን ደብዛቸው ጠፍቱዋል። የት እንደደረሱም አላውቅም እኔም ይሄው ከባቡር ጣብያ ደጃፍ ምጽዋት እየለመንኩ የዕለት ኑሮዬን እገፋለሁ” ብላ መለሰች።
ተማሪዋም ልጅ እያለች የአስተማሪዋን ቅንነት እና ለተማሪዎቹዋ የነበራትን ፍቅር ባሰበች ጊዜ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። በአንድ እጁዋ እንባዋን እየጠረገች፣ በአንድ እጅዋ መምህሩዋን ይዛ ወደ ቤቱዋ ተመለች። የመምህሩዋን ገላ አጥባ ልብሱዋን ቀይራ የዕለት ጉርስም ሰጠቻት። ከዛም በኋላ ድሮ አብረዋት የተማሩትን ተማሪዎች በማስተባበር የመኖሪያዋን እና ለኑሮ የሚያስፈልጋትን ሁሉ አመቻቹላት።
ቁምነገር!
የራሱዋ ልጆች ቢሸሹዋትም ያስተማረቻቸው ልጆች ደረሱላት። ቅንነት እና በየተሰማሩበት መልካምን ሰርቶ ማለፍ የክፉ ቀን ስንቅ ይሆናል!
(ትርጉም ዘላለም ጸጋዬ)
@goferebooks
#409
📚 The Einstein Theory of Relativity
By Hendrik Antoon Lorentz
Genres: Non-fiction, Science and technics, Science
Goodreads rate: 🌟(3.89/5)🌟
Number of pages: 27
Publication date: 1920
Publisher: Feedbooks
Source: http://www.gutenberg.org
Whether it is true or not that not more than twelve persons in all the world are able to understand Einstein's Theory, it is nevertheless a fact that there is a constant demand for information about this much-debated topic of relativity.
The books published on the subject are so technical that only a person trained in pure physics and higher mathematics is able to fully understand them. In order to make a popular explanation of this far-reaching theory available, the present book is published.
Brought to you by http://www.feedbooks.com
"BE CHAIN READER"
#Share
@goferebooks
#ጥቆማ
"የትሮይ ፈረስና ሌሎችም አጫጭር ታሪኮች" የተሰኘው የአሳምነው ባረጋ ተወዳጅ መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ሌሎች ተጨማሪ 4 ተረኮችን አካቶ ለገበያ ይቀርባል።
@goferebooks
#361
📚 The Way of the Bow
By Paulo Coelho
Genres: Fiction, Short stories
Goodreads rate: 🌟(3.66/5)🌟
Number of pages: 31
Publisher: Feedbooks
Published in: 2008
Source: Feedbooks
“The Way of the Bow” relates the story of Tetsuya, the best archer of the country, who conveys his teachings to a boy in his village. Throughout the story, several thoughts are reflected; our daily efforts and work, how to overcome difficulties, steadfastness, courage to take risky decisions, etc.
Paulo Coelho expressed in these few pages many of the values which inspire our daily work: innovation, flexibility, adaptation to changes, enthusiasm, team work.
“I wrote this text in which bow, arrow, target and archer form an integral part of the same system of growth and challenge.” — Paulo Coelho.
Brought to you by http://www.feedbooks.com
"BE CHAIN READER"
#Share
@goferebooks