እንኳን አገር አጥበው ቀሽረው ሊያወርሱን ...
(አሌክስ አብርሃም)
በፈረንጆቹ 2011 ጃፓን ውስጥ Fukushima የተባለ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ያውም በሬክተር ስኬል 9.0 የተመዘገበ። በሰዓታት ውስጥ 20 ሺ ህዝብ በዘግናኝ ሁኔታ አለቀ ፣6ሺ ሰው ከከፍተኛ እስከቀላል የአካል ጉዳት ደረሰበት ፣ 2500 ሰው የደረሰበት ጠፋ ፣ ግማሽ ሚሊየን ህዝብ ቤት ንብረቱን ጥሎ ተፈናቀለ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚሉት የኛ አበወች ከነገሩ በላይ ዓለምን ያስደነገጠ ሌላ ዜና ተሰማ ። ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ጣጣ!
ይሄ ጦሰኛ አደጋ የተከሰተባት ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ የኒውክሌር ማብለያ ተቋም አለ። Fukushima Daiichi nuclear power plant ይባላል። በዓለማችት ካሉ 25 የኒውክሌር ሀይል ማምረቻወች አንዱ ነው። በአደጋው ከዚህ ግዙፍ ተቋም የራዲዮ አክቲቭ ጨረር አፈትልኮ ወጣ። ራዲዮ አክቲቭ በቀጥታ ካገኘ ማንኛውንም ህይወት ያለው ፍጡር የሚገድል እንዲሁም ውሃ ይንካ ድንጋይ ሁሉንም ቁስ በመበከል ወደገዳይ ቁስነት የሚቀይር መራዢ ጨረር ነው። በአካባቢው ላይ ለአመታት በመቆየትም ይታወቃል። ከዚህም የከፋ ነው ኬሚስትሪው። ተጠቅቶ ከአደጋ መትረፍ ቢቻል እንኳን መትረፍ አይበለው። ዓለማችንን የሚያስጨንቃት የኒውክሌር መሳሪያ የሚፈራበት አንዱ ምክንያት ይሄው ነው።
አደጋው ጋፕ ሲል ከአካባቢውን ከገዳዮ ብክለት ለማፅዳት መላው ጃፓናዊ ተረባረበ። ይሄን ሁሉ መከራ ያወራኋችሁ ቀጥሎ ለምነግራችሁ የሚያስቀና ጉዳይ ነው። በእርግጥ ብክለቱን ማፅዳት፣ ጉዳቱንም መቀነስ ይቻላል ፣ ግን መጥረጊያህን አንስተህ በሞራል ዘው የምትልበት ዘመቻ አይደለም! የረቀቀ ሳይንስ ነው። በክር ላይ የመራመድ ያህል ጥንቃቄ ልምድና ዕውቀት እንዲሁም ዕድል የሚጠይቅ ነገር! በደመነፍስ ቦታው ላይ መገኘት ወዲያው ከመሞት የእድሜ ልክ ካንሰር ፣ለሌሎችም ዘግናኝ ጉዳቶች ሊዳርግ ይችላል። መቸስ ችግር ጀግኖችን ይፈጥራል። መላው ዓለም
"Fukushima 50"ብሎ የሰየማቸው ጡረታ የወጡ ሽማግሌወች ይህን ራዲዮ አክቲቭ ጉዳት ለመከላከል በፈቃደኝነት ከፊት ተሰለፉ።
እነዚህ ሰወች የጡረታ ክፍያቸው ያነሰባቸው ፣ ከዚህ ኑሮ ሞት ይሻላል ያሉ ጧሪ አልባ ሽማግሌወች እንዳይመስሏችሁ ፣ ከፍተኛ የኒውክሌር ኢንጅነሮች፣ ተመራማሪወች የነበሩ ጡረታ ወጥተው የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩ ጃፖናዊያን አባቶች እንጅ። ብቸኛ ዓላማቸው የድርሻችንን ኑረናል ይህን የኒውክሌር ተቋም የመሰረትነውም እኛ ነን ሀላፊነቱን መውሰድ ያለብን እኛ ነን፣ ልጆቻችንና ለቀጣዮ ትውልድ ይሄን ገዳይ ቆሻሻ አናወርስም! የድርሻውን ንፁህ አገር ይረከብ ዘንድ ሞትም ቢሆን ዋጋ እንክፈል የሚል ነበር። አንዷ የ72 ዓመት ጡረተኛ እንዲህ አለች "My generation built these nuclear plants. So we have to take responsibility for them. We can't dump this on the next generation,"እናም ወጣቶቹንና ብዙ ሊሰሩ የሚችሉትን ኢንጅነሮች ተክተው በዛ ቀውጢ ወቅት ወደተበከለው ተቋም ባጭር ታጥቀው ገቡ።
በእርግጥም ይህን ከባድ ሀላፊነት በመወጣት አደገኛውን ስራ በመፈፀም ከኋላ ለሚመጡ ወጣት ኢንጅነሮች እና ብክለቱን ለማፅዳት ለተሰለፉ ሁሉ መንገድ ጠረጉ። ጣቢያው ውስጥ ለቀናት በመቆየትና ሪአክተሩን በማቀዝቀዝ ጃፓን ይገጥማት ከነበረ የሚሊየኖች ሞት ታደጓት! ትውልድን ከቆሻሻና የሀዘን ታሪክ ውርስ ታደጉ!! የሚደንቀው ነገር አንድኛቸውም በአደጋው አልሞቱም!! አገር ለትውልድ እንዲህ ታጥቦ ተቀሽሮ በውርስ ይሰጣል ። እኛስ? እንኳን አገር አጥበው ቀሽረው ሊያወርሱን የኛን ዕድሜ የሚቀሙ፣ የቀጣዮ ትውልድ ዕጣፋንታ ላይ የጥላቻ ቆሻሻ ደፍተው የሚፎክሩ አባቶች ልጆች ሆንን ! አየህ ወጣትን እየማገዱ ኑሯቸውን ለሚያመቻቹ የጠነዙ ፖለቲከኞቻችን ይሄ ጅልነት ነው። ጃፓን እንደምን ሰለጠነች ይሉናል አገራችን እንደምን ሰየጠነች ብለን ስንጠይቅ!
@wegoch
@wegoch
@paappii
Watch "አዲስ መዝሙር ለሀይማኖቴ እንቢ ለክብሬ እሰዋለሁኝ ለናት ሀገሬ" on YouTube
https://youtu.be/uf8HiQgC10Q ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ይዳረስ ዘንድ ሸር ይደረግ
#ይነበብ
❖በMotivational Speech (አነቃቂ ንግግር) እና Capacity building (አቅም ግንባታ) ሰበብ በቤተ ክርስቲያን ላይ የታወጀ ጥቃት!
☞Entertainment (መዝናናት) በሚል ሰበብ አዕምሮው የደነዘዘ፤ መንፈሳዊና ሰብአዊ እሴትን የማያከብር፤ ባሕላዊና ማኀበራዊ ድንበርን ከእሥር የሚቆጥር፤ ግለኛ፤ እኔን ይድላኝ የሚልና ከፈሪሐ እግዚአብሔር የተፋታ ትውልድ ቁጥሩ እጅጉን በርክቷል።
☞አሁን አሁን ደግሞ (በውጪው ዓለም የቆየ ጉዳይ መሆኑ ሳይዘነጋ) በመነቃቃት/Motivation ሰበብ በቅዠት የሚኖር ትውልድ ሲፈጠር ዝም ብለን መመልከቱን የመረጥን ይመስላል፡፡
☞በገንዘብ ሀብታም መሆንን እና ዝናን እንደ ስኬት መለኪያ የሚያሳዩ አነቃቂ ነን ባዮች፥ ይበልጡኑ የሚያደነዝዝ ተግባር ላይ ተጠምደዋል።
*አነቃቂ ንግግሮች ልክ እንደ ቀልድ (comedy) እና ድራማ script ተዘጋጅቶላቸው በጥንቃቄ የሚከወኑ በመሆናቸው በአብዛኛው የሰውን ቀልብ ይስባሉ፡፡
*ለሚሰማቸው ሰውም (በተለይ ወጣት ከሆነ) ሱስ መሆናቸው አይቀርም።
*በፍጻሜው ግን ተናጋሪው (አነቃቂ ነኝ የሚለው) ከደንበኞቹ በቀጥታም ሆነ በመጻሕፍት ሽያጭ ኪሱን ሲሞላ፥ አዳማጩ (በአብዛኛው) ሜዳ ላይ ነው የሚቀረው።
*እንዲያውም በዚሁ ሰበብ በአሜሪካና በአውሮጳ ለከፍተኛ የድብርት (depression) ሕመም የተጋለጡም ብዙ እንደሆኑ ይሰማል፡፡
*ስለዚህም ነው ነገሩ ማነቃቃት ሳይሆን፥ ማደንዘዝ ነው የሚባለው።
አሁን ባለን መረጃ በኢትዮጵያ ወደ ስልጠና ለመግባት (የአቅም ግንባታ የሚል የዳቦ ስም ተሰጥቶት) ታዳጊዎችና ወጣቶች እስከ 39,000 ብር ይከፍላሉ፡፡
በነገራችሁ ላይ በጉዳዩ ላይ ራሳቸው የሰሯቸው ዘጋቢ ፊልሞች (Documentaries) እንኳን ታዳጊዎችን፥ የገንዘብ ፍላጎት ያለውን ማንኛውንም ሰው የማማለል አቅም አላቸው፡፡
☞ትልቁ ሥጋት ግን ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት ከጀርባቸው ቤተ ክርስቲያንን የትኩረት ማዕከል ማድረጋቸው ነው፡፡ (ነገሩ Secular/ዓለማዊ ቢመስልም ፥ ከውጤቱ እንደተረዳነው የፕሮቴስታንታዊ ተልዕኮ አንዱ መንገድ ነው)
ወይም በቀጥታው አነጋገር ከቤተ ክርስቲያን (በተለይ ከሰንበት ት/ቤቶች) መልምለው ባሰለጠኗቸውና ጠቀም ያለ ገንዘብ በሚከፍሏቸው ወጣቶች ተጠቅመው "ተሐድሷዊ" ጥፋትን በቤተክርስቲያን ላይ ዳግም አውጀዋል።
ነገሩን በጥንቃቄ ስለያዙት ብዙዎቻችን ልብ አላልናቸውም፤ አንዳንዱም እያወቀ ቸል ማለቱን መርጧል፡፡ ነገር ግን የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች ላይ ያላቸውን ትኩረት እንረዳው ዘንድ ከአንድ አጥቢያ (ሰ/ት/ቤት) ታዳጊዎች ክፍል ብቻ ከ20 በላይ ልጆችን ወስደዋል፡፡
"ሳይቃጠል በቅጠል" ካላልነው ቤተ ክርስቲያንን እና የነገውን ትውልድ ለሌላ አውሬ አሳልፈን መስጠታችን ነው!
"Motivational speakers are scam (fraud) artists. Because they give speeches & sell books in exchange of money."
& If possible, no need to listen them or buy their products.
☞በጉዳዩ ዙሪያ ለታዳጊዎችና ወጣቶች የተሰጠውን ማብራሪያ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ፦
https://youtu.be/K3y5-AnXNcI
@beteesdros
ተበልቶ + ተጠጥቶ = "ኃጢአት"
ተጹሞ + ተጸልዮ = "ጽድቅ" ይሠራል፡፡
ሕግን ሳይሆን ፍቅርን ብቻ እያሰብን እንድንጾማት ይኽች የጽጌ ጾም እንኳንም የፈቃድ ጾም ሆነች!!!
ምንም እንኳን ነፍስ ያለ ሥጋ፣ ሥጋም ያለ ምግብ መቆም ባይችሉም ሐዋርያው እንዳለው (1ኛ ቆሮ 6:13) "መብል ለሆድ ነው፣ ሆድም ለመብል ነውና ፤ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋልና" አምላክን የወለደች የክብርት እመቤታችንንና የልጇን ስደት በጾም በጸሎት የምታሳልፉ ኦርቶዶክሳውያን ሁላችሁ እንኳን ለጾመ ጽጌ አደረሳችሁ! አደረሰን!!!
@beteesdros
goytsh44/video/7128089682683923718?_r=1&u_code=dh5lbj8lkideh7&preview_pb=0&language=en&_d=e1aghc7lc7d314&share_item_id=7128089682683923718&source=h5_m&timestamp=1659676088&user_id=6930676657112761350&sec_user_id=MS4wLjABAAAAHoDkmCluGpZ-5gx4gngJsFVrplIXYNwMoKvZps9hNVn0WenNASqdRWjKG5xu8mpt&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7119480320873744134&share_link_id=e46222f3-633b-4e7a-b4ad-de7f6ad76845&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@goytsh44/video/7128089682683923718?_r=1&u_code=dh5lbj8lkideh7&preview_pb=0&language=en&_d=e1aghc7lc7d314&share_item_id=7128089682683923718&source=h5_m&timestamp=1659676088&user_id=6930676657112761350&sec_user_id=MS4wLjABAAAAHoDkmCluGpZ-5gx4gngJsFVrplIXYNwMoKvZps9hNVn0WenNASqdRWjKG5xu8mpt&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7119480320873744134&share_link_id=e46222f3-633b-4e7a-b4ad-de7f6ad76845&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main
Читать полностью…እንዴት አመሻቹህ የቅዳሜ እና እሁድ የመስቀል አደባባዩ ጉባኤ የተሳካ ይሆን ዘንድ ነገ ጠዋት 2.30 ጀምሮ ዳስ በመስራት ከዛም በማስተባበር እና በጥበቃ ስራ እንድንረዳ ስለተጠየቀ ሀላፊነታችንን በአግባቡ እንድንወጣ አደራ እላለሁ የማስተባበሩ ሀላፊነት የወንድማችን አንተነህ ይሆናል ሁላችንም ለመታዘዝ ተዘጋጅተን እንምጣ ሰላም እደሩ
Читать полностью…ማን ነው እኔ አለሁ የሚል? ማነው የኦርቶዶክስ ጠበቃ ነኝ የሚል? ማን ነው መስቀሉን ተሽክሞ ከመድኃኔ ዓለም ጋር ቀራንዮ የሚገኝ? ማን ነው የሰማዕታት ወዳጅ? ሰማዕታት እጅና እግራቸው ታሥሮ አፋቸው ታፍኖ በሰይፍ ተቆርጠው ነው የክብር አክሊል ያገኙትና ሃይማኖታችንን ለዛሬ ያቆዩልን?! ዛሬስ እኛ ዝግጁ ነን??
በብዙ ነገር ሰማዕታት መሆን እንችላለን፦ ጊዜ ሰጥተን መሬት ላይ መሥራት፣ ዕውቀታችንን ባግባቡ መጠቀም፣ ጉልበታችንን ተግባር ላይ ማዋል፣ በገንዘባችን ወቅታዊ አገልግሎቶችን መደገፍና በመጨረሻም ከፊት ሆነን ሰማዕትነት መቀበል ናቸው። ከነዚህ ውስጥ በዚህ ወቅት አንዱን የማያደርግ ክርስቲያን ክርስቲያን አይደለም።
#እንጨክን
የሰላም አለቃ መድኃኔ ዓለም ሆይ ሰላሙን ስጠን፣ ጽኑዓንም አድርገን።
.ይቤላ መልካሟ ርግብ ነይ ነይ አሏት
.ይደሉ ስባሔ ለስሉስ ቅዱስ ልዩ ለሆነ ሶስትነት ምስጋና ይገባል ፍፁም አስር የሆነ ምስጋና ይገባል አስር በእኛ ፍፁም እንደሆነ ሁሉ በእብራውያን 7 ፍፁም ነውና
.በመብራት መቅረዝ አመሳሰልንሽ /የመብራቱ መቅረዝ አንች ነሽ መብራቱ ያለመቅረዙ እንደአልቆመ ወልድም ያለአንች ሠው አልሆነም
👉ዳዊትም አለ አቤቱ አቤቱ ነይ አለ
ጨለማን ያሸነፈ ሀይልሽ ፍፁም ነው
ደግምሞ ዳዊት አለ እናቴ ቃልሽ ሁሉን አረጋጊ ነው
ደግሞም አለ ለልኡል አዶናይ ማደሪያ የሆንሽ ነይ
የፊትሽ ክበብ እንደሰማይ ጨረቃ ነው
አይኖችሽም ብሩህ ናቸው ከፀሐይ ኮከብ/መሞቅ መድመቅ ብርሃን ይልቅ ማለት ነው
#ማየ ዮርዳኖስ
ማየ ዮርዳኖስ ሥሙር /2/ በዮሐንስ
ኀበ ወረደ /3/ መንፈስ ቅዱስ /2/
#ትርጉም፡- በዮሐንስ የተወደደ የዮርዳኖስ ውሃ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወረደበት፡፡
#የጥምቀት #መዝሙሮችን #ለማግኘት #ቻናላችንን #ይቀላቀሉ
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ @beteesdros ★
wuludeesdiros" rel="nofollow">https://youtube.com/@wuludeesdiros
ይህ የሰንበት ትምህርት ቤታችን የዩቲዩብ ቻናል ነው ሰብስክራይብ በማድረግ ተደራሽነታችንን እናስፋ
በሩቅ መወደድ
ለመወደድ ትክክለኛው መንገድ ከጉዳዮች ሁሉ መራቅ ለምሳሌ ዘመድና ፎቶን በሩቁ ይባላል የራቀ ሰው እርሱ የለበትም እርሱ መች እንዲህ ይላል
ተብሎ ይወደዳል ደግሞ መች እከሌ እና እከሌ እንዲህ ብለው እነእከሌ አንዲህ አይነት ነገር ውስጥ አይገቡም አንዲህ በሩቅ መወደድ በጣም ቀላል መንገድ ነው ግን በጣም ደግሞ አጥፊ አካሄድ ነው
ይህ ለዘመናችን ሰባክያን ነው አንተ ማን ሁነህ ነው ምናምን እንዳትሉኝ ምንም ልሳኔ መልካም ሆኖ መድረክ ወጥቸ ባላስተምር እውቀት ባይኖረኝ የቤተክርስቲያን መገፋት የክርስቲያኖች መጨፍጨፍ የሚያንገበግበኝ የቤተክርስቲያን ልጅ ነኝ
አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተጋረጠባት መከራ እየደረሰባት ካለው ፈተናና ስደት አንፃር ብዙ ሰባክያን ችግሩን እያወቁ ዝም ማለት በሩቁ የመወደድ እንጅ መከራውን ለመቀበል አይደለም ለመግለጥ እንኳን አለመፈለግን ሳይ
በመንግስትም
በርእዮተ አለምም
በአፍም
በሰይፍም
በሌሎች የሃይማኖት ተቋማትም እየደረሰ ያለውን ፈተና እንዴት ምቋቋምና ማሽነፍ እንደምንችል ለምእመኑ ማስተማር ሲገባ ለእርድ ማስባት ነገ ቤተክርስቲያኒቱን ተተኪ አልባ እንድትሆን ምእመናንን ማደንዘዝ ተገቢ አይደለም
ኦርቶዶክሳውያን በሃገራቸው ተሳዳጅ ሆነዋል የቤተክርስቲያን መከራ ማብቂያ እንዲኖረው በአጀንዳ መስራት ካልቻልን እውነቱን ካልተናገርን ካላስተማርን ወደማያባራ መከራ እንገባለን ........አላለቀም
በዲ/ታየ
@beteesdros
+ ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል +
ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት . . .
ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ
ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው . . . በሲጋራና በመጠጥ ሽታ የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤
‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት
‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት . . . ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን . . . ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት . . . ለረጅም ዓመታት . . . አክሊለ ጽጌ ብዬ . . . ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ
‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ . . . በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ. . . አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ . . . ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ. . . ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል
‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም . . . ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ. . . መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣ . . . የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ . . . ማልቀስ እጀምራለሁ . . . ፍቅሯን አስባለሁ . . . የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው. . . ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል . . . በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ››
አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣
‹‹ማን . . . እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ . . . እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ››አልኩ አምላኬን፣
በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት
ዲ/ን አብርሃም ይኄይስ እንደጻፈው
@beteesdros
➕➕➕➕
"እመቤቴ ሆይ በአንቺ ጸሎት በልጅሽ ቸርነት ከታመንሁ ሰማይ ወፍጮ ምድር መጅ ቢሆኑ ሁለቱም ሊያጠፉኝ ቢፈልጉ አንዳች ሊያደርጉኝ አይችሉም" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
➕➕➕➕
አንድን አባት ሰዎች መጡና "ዘወትር ጸሎት በማድረግህ በሕይወትህ ላይ የጨመረልህን ነገር ንገረን?" አሉት:: እርሱ ግን "ጸሎት በማድረጌ ከጨመርሁት ይልቅ የቀነስሁት ይበዛልና እርሱን ልንገራችሁ:: ጸሎት በማድረጌ ከሕይወቴ ውስጥ ጭንቀት ፍርሃት ተስፋ መቁረጥና ቁጡነትን ቀንሻለሁ አላቸው::
➕➕➕➕
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታላቅ የምሥራች ለጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ
በሥነ ምግባር የታነጸ ሀገር ተረካብ ትውልድ ማፍራትን ዓላማ ያደረገው ሐራ ዘኢትዮጵያ እፀደ ሕፃናትና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከኬጅ እስከ 8ኛ ) ዝግጅቱን እጠናቆ በቀድሞው ሰላም እካዳሚ ት/ቤት ምዝገባ ጀመረ
የምዝገባ ቦታ-1ኛ-ከቀድሞው ሰላም እካዳሚ ት/ቤት ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ጀርባ
2ኛ-እዘዞ ክቀድሞው ኢዛና ፔንስዮን
3ኛ-ቀበሌ 14 ይዛኑ ፔንስዮን ፊት ለፊት ከቀድሞው እቡነ ሳሙኤል ት/ቤት
የምዝገባ ጊዜ-ከሐምሌ 18 እስክ ነሐሴ 15/2014ዓ ም
ክፍያን በተመለከተ
መመዝገቢያ 300 የትምህርት 800 የሰርቢስ እንደየቦታው እርቀት
https://chng.it/NgpMnSGpKr
በ7ቱ የኦርቶዶክሳዊያን ጥያቄዎች የምታምኑ ሁሉ ይህን ፔትሽን ፈርሙ፤ ለወዳጆቻችሁ ሼር እያደረጋችሁና እያስረዳችሁ አገርአቀፍና ዓለም አቀፍ አድርጉት። ኢ ሜይል ለሌላቸው እገዛ በማድረግ ክፈቱላቸው።\
ሞትሰ
ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ
ሞታ ለማርያም/2/ የአፅብ ለኩሉ
ትርጉም
ሞትስ ለሟች ይገባ ነበረ የማርያም ሞት ግን ለሁሉ (ሁሉን) ያስደንቃል
👉ለአንች ክብር ከሩቅ ቦታ መጥተው ነይ አሉ ይሰግዱላት /ይሰግዱ ዘንድ ወጣቶች ደናግል ነይ አሏት
ጥበብ ቃልሽን አንደበቴ ተናገረ /አውጥቶ ተናገር
ፍፁም ምስጋናሽ ምግብ ሆነኚ
አለምን ዞርኳት ነገር ግን እንደአንች ያለ ሰው አጣሁ በእግዚአብሔር በታች ነይ አሏት
መልካም እይታሽ ለእውር ሰው መሪ መንገድ ጠራጊ /መንገድ ነው
እኔ ደካማ ሰው በምስጋና ከክብርሽ መድረስ አልችልም/በመዝሙር ክብርሽን አልጨርሰውም
.ይቤላ መልካሟ ርግብ ነይ ነይ አሏት
.ይደሉ ስባሔ ለስሉስ ቅዱስ ልዩ ለሆነ ሶስትነት ምስጋና ይገባል ፍፁም አስር የሆነ ምስጋና ይገባል አስር በእኛ ፍፁም እንደሆነ ሁሉ በእብራውያን 7 ፍፁም ነውና
.በመብራት መቅረዝ አመሳሰልንሽ /የመብራቱ መቅረዝ አንች ነሽ መብራቱ ያለመቅረዙ እንደአልቆመ ወልድም ያለአንች ሠው አልሆነም
👉ዳዊትም አለ አቤቱ አቤቱ ነይ አለ
ጨለማን ያሸነፈ ሀይልሽ ፍፁም ነው
ደግምሞ ዳዊት አለ እናቴ ቃልሽ ሁሉን አረጋጊ ነው
ደግሞም አለ ለልኡል አዶናይ ማደሪያ የሆንሽ ነይ
የፊትሽ ክበብ እንደሰማይ ጨረቃ ነው
አይኖችሽም ብሩህ ናቸው ከፀሐይ ኮከብ/መሞቅ መድመቅ ብርሃን ይልቅ ማለት ነው
#ይቤሎ ኢየሱስ
ይቤሎ ኢየሱስ ለዮሐንስ አጥምቀኒ በማይ ከመ ይትቀደስ ማይ በማዕተበ ሰማይ/2/
አጥመቆ ዮሐንስ ለኢየሱስ በፈለገ ዮርዳኖስ
#ትርጉም፡- ኢየሱስ ዮሐንስን አለው “በሰማይ መባረክ ውሀ ይቀደሰ ዘንድ በውሀ አጥምቀኝ” አለው፡፡ ዮሐንስም ኢየሱስን አጠመቀው፡፡
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ @beteesdros★