"ልጄ ሆይ በክርስትናህ መጎልመስ ከፈለክ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር ራስህን አዛምድ" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥5
"በመስቀል ላይ ሳለ ጌታችን ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ሁሉ ተፈጸመ አለ" (ማር. ፲፭፥፴፯)
Читать полностью…“የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና፤ በዙሪያው ፍርሃት ነበረ በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ ነፍሴን ለመንጠቅ ተማከሩ።”
— መዝሙር 31፥13
“ኢየሱስን የያዙትም ጻፎችና ሽማግሎች ወደ ተከማቹበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት። ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፥ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ። የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጐውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙም፤ ብዙም የሐሰት ምስክሮች ምንም ቢቀርቡ አላገኙም። በኋላም ሁለት ቀርበው፦ ይህ ሰው፦ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ልሠራው እችላለሁ ብሎአል አሉ። ሊቀ ካህናቱም ተነሥቶ፦ እነዚህ ለሚመሰክሩብህ አንድ ስንኳ አትመልስምን? አለው። ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ ሊቀ ካህናቱም፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው። ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው። በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እርሱም፦ ሞት ይገባዋል ብለው መለሱ። በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጐሰሙትም፥ ሌሎችም በጥፊ መትተው፦ ክርስቶስ ሆይ፥ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን አሉ።”
— ማቴዎስ 26፥57-68
" በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ።"
(የሉቃስ ወንጌል 19:38)
እንኳን አደረሰን
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
የ100 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃♀️🏃♂️
Читать полностью…በ30 ሰከንድ ውስጥ ስለሚጠፍ ምርጥ ቻናል ነው ይቀላቀሉ 👇
/channel/addlist/gpX29GzfGs43MWE0
“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥9
“እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥9
“ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥3
“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4
"ይህ ዓለም ፈጽሞ እንዲያልፍ ተድላ ደስታውም ለዘላለም ፀንቶ እንዳይኖር አውቀው በሰማይ ካለ እሳት ይድኑ ዘንድ ዕውነታቸውን ለሳት ሰጡ።በዚህ ዓለም ብዙ ዘመን ከመኖርም በጎነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት እንዲሻል ከብዙ ዘመኖችም አቤቱ አንዲት ሰዓት ይቅርታህን ማግኘት እንዲሽል አውቀዋልና ሰውነታቸውን ለሳት ሠጡ።የኛ ዘመን ምንድነው እንደ ጥላ የሚያልፍ በእሳት ዳር ያለ ሰም ቀልጦ እንዲጠፋ እንደዚያ አይደለምን?አቤቱ አንተ ግን ለዘላለሙ ትኖራለህ ዘመንህም የማይፈጸም ነው ስም አጠራርህም ለልጅ ልጅ ነው።"
2ኛ መቃብ 13:3-6
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
— ማቴዎስ 28፥19-20
“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 5፥20
የኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት
ወልደ እግዚአብሔር፣ ወልደ ማርያም (የእግዚአብሔር አብ ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ) ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት አሉት፡፡ የመጀመሪያው (ቀዳማዊ) ልደት ዘመን ከመቆጠሩ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ ከሰው አእምሮ በላይ በሆነ ምሥጢር (አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ) የተወለደው ልደት ነው (መዝ 2፥7 መዝ 109፥3 ምሳ 8፥25)፡፡ ሁለተኛው (ደኀራዊ) ልደቱ ደግሞ ዓለም ከተፈጠረ አዳም ከበደለ ከአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደው ልደት ነው (ገላ 4፥4 ኢሳ 7፥14 ኢሳ 9፥6 ዘፍ 3፥15 ፤18፥13 ፤ 12፥8 ፣ መዝ 106፥20)፡፡ ዘመን የማይቆጠረለት፣ በቅድምና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረ፣ ዓለምንም በአምላክነቱ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አካላዊ ቃል መለኮታዊ አካሉን፣ መለኮታዊ ባሕርይውን ሳይለቅ በተለየ አካሉ ንጽሕት፣ የባሕርያችን መመኪያ ከምትሆን ከድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምላካዊ አካልና ባሕርይን ከሰው አካልና ባሕርይ ጋር ያለመጠፋፋት፣ ያለመቀላቀል ተዋሐደ እንጅ አካሉም ባሕርይውም አልተለወጠም፡፡
ሊቁ አባታችን ቅዱስ ፊሊክስ የጌታችንን ቀዳማዊና ደኀራዊ ልደቱን በተናገረበት አንቀጽ “ዓለም ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው በኋላ ዘመን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረ እርሱ ነው፤ እርሱ ሰውም ቢሆን አንድ አካል፣ አንድ ገፅ፣ አንድ ባሕርይ ነው” በማለት ሁለቱን ልደታት አስተምሯል፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ፊሊክስ 38፡10 በተጨማሪም ቅዱስ ናጣሊስ “ከእግዚአብሔር አብ በተወለደው በቀዳማዊ ልደቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው፤ ከድንግል በተወለደው በደኃራዊ ልደቱ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ እርሱ አንዱ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ የሚሆን የሚተካከል ፍጹም አምላክ ነው፤ እርሱ ብቻ ከድንግል በተወለደው ልደት በሥጋ ከሰው ጋር አንድ የሚሆን ፍጹም ሰው ነው፡፡” ብሏል፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ናጣሊስ 46፡3-4)
በጌታችንና በአምላካችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተደረገልን ፍጹም ሥርየትና እርቅ ግልጥ ሆኖ የተጀመረው በነገረ ልደት ነው። የጌታችን ልደት በነገረ ድኅነት ትልቅ ስፍራ የያዘና እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ፍጹም ልዩ መሆኑን ያሳየ ነው። መስተጻርራን የነበሩ ሰማይና ምድር፣ ሰውና መላእክት በአንድነት ለምስጋና ታድመዋል። የእረኞች አንደበት ከመላእክት ጋር ለሰማያዊ ምስጋና ብቁ የሆነበት፤ ግዕዛን የሌላቸው እንስሳት ሰራኢ መጋቢያችን፣ በዘባነ ኪሩቤል በሰማያት የምትገለጥ አንተ ነህ ሲሉ እስትንፋሳቸውን የገበሩለት፤ የምድር ነገሥታት በሥልጣንህ ሽረት በመንግሥህ ህልፈት የሌለብህ የነገስታት ንጉሥ አንተ ነህ ሲሉ ወርቅን ለመንግሥቱ፣ ዕጣንን ለክህነቱ፣ ከርቤን ለህማሙ ዕጅ መንሻን ያበረከቱለት፤ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ያን ልዩ ክብር የዩበት፤ ይህ ልደት በእውነት ልዩ ነው።
Читать полностью…"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።"
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥20-21
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ አደረሳችሁ አደረሰን፣መልካም በዓል!!!
❝እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንሁ፤ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ።❞
መዝሙር ፻፱ ፥ ፳፭
.....የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ። የሚያዩኝ ሁሉ ይላገዱብኛል፤ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይላሉ፦
በእግዚአብሔር ተማመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ቢወድደውስ ያድነው።
መዝሙር ፳፪÷፸
... የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፤- ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ አሉት።
ማቴዎስ ፳፯÷፴፱
“ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱት፥ የካህናት አለቆችም ሁሉ ሽማግሌዎችም ጻፎችም ተሰበሰቡ። ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለው፥ ከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር። የካህናት አለቆችም ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙምም፤
ብዙዎች በሐሰት ይመሰክሩበት ነበርና፥ ምስክርነታቸው ግን አልተሰማማም። ሰዎችም ተነሥተው፦ እኔ ይህን በእጅ የተሠራውን ቤተ መቅደስ አፈርሰዋለሁ በሦስት ቀንም ሌላውን በእጅ ያልተሠራውን እሠራለሁ ሲል ሰማነው ብለው በሐሰት መሰከሩበት። ምስክርነታቸውም እንዲሁ እንኳ አልተሰማማም። ሊቀ ካህናቱም በመካከላቸው ተነሥቶ፦ አንዳች አትመልስምን? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩብህ ምንድር ነው? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው። እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና፦ የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው። ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ። ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፦ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል? ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ፦ ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት። አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና፦ ትንቢት ተናገር ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።
— ማርቆስ 14፥53-65
"ሰውም። ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቍስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም። በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል።"
ትንቢተ ዘካርያስ 13:6
#በእንተ #ቁርባን
"ሥጋውን በምንቀበልበት ጊዜ በትናጋ መብላት እንጂ በጥርስ ማኘክ አይገባም" ይላል (ገድለ አቡነ መብዓ ጽዮን)። ካህናትም መጥነው ማቀበል ይገባቸዋል። ነገረ ቁርባን አምስቱን አዕማደ ምሥጢር ላልጠነቀቀ ምእመን እንዳይከብደው አስቀድሞ አምስቱን አዕማድ ማስተማር ይገባል። ትምህርተ ኅቡዓት ከቁርባን በፊት በመምህራን ይተርጎም መባሉ ስለቁርባን ባለመረዳት ብዙው ሰው እንዳይጎዳ በማሰብ ነው።
ከጥምቀት በፊት የሠራነው ኃጢአት በጥምቀት ይሠረያል። ከጥምቀት በኋላ የሠራነው ኃጢአት ደግሞ በክርስቶስ ሥጋና ደም ይሠረያል። ስለሆነም ማንኛውም ክርስቲያን ንሥሓ እየገባ ሥጋውን ደሙን መቀበል ይገባዋል። በክርስቶስ ሥጋና ደም የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን። ስንቆርብ አንድነታችን ይጠነክራል (1ኛ ቆሮ.10፥17፤ ዮሐ.6፥51-58)። ሥጋውን ደሙን በንጹሕ ልብ ቢቀበሉት ምሥጢር ያናግራል። የወይኑና የኅብስቱ መልኩና ጣዕሙ ሳይለወጥ ወደ ክርስቶስ ሥጋነትና ደምነት ይለወጣል። "ኢይትዌለጥ ኅብስት እምጣዕሙ ወእምልምላሜሁ ዘትካት። እንዘ ኅዱር ላዕሌሁ መለኮት" እንዲል (መጽሐፈ ባሕርይ)።
ከመቁረባችን በፊት ንሥሓ መግባት፣ ከበደል መንጻት፣ መልካም ሥራዎችን መሥራት ይገባል። ይህንን ሳናደርግ ብንቆርብ መቅሠፍትን በራሳችን ላይ እናመጣለን (1ኛ ቆሮ.11፥27-29፤ ሃይ.አበ.20፥27-28)። ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ ለፍጹማን በአምሳለ ሕፃን፣ በንጹሕ በግ አምሳል የሚገለጽበት ጊዜ አለ (አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን 30፥ ድርሳን 31፤ ፊልክስዩስ ተስእሎ 90)። የክርስቶስን ሥጋና ደም ከተቀበልን በኋላ ለወጣንያን ዕለቱን ለፍጹማን እስከ ዘለዓለም ምራቅን መትፋት አይገባም (ፊልክስዩስ 10)። ከመቁረባችን በፊት በውሃ አፍን መጉሞጥሞጥ አይገባም፣ ሳንጾምና ለአፋችን ምረት ሳይሰማንም መቁረብ አይገባንም (ሳዊሮስ ዘእስሙናይን)።
ከቁርባን በኋላ ዕለቱን ሰውነትን መታጠብ፣ ከልብስ መራቆት፣ መስገድ፣ ጥፍርን መቆረጥ፣ ጸጉርን መላጨት፣ ፍርድ ቤት ገብቶ መሟገት፣ ከአቅም በላይ መብላት፣ መበጣት አይገባም።
ምንጭ፦ የእግዚአብሔር ስጦታ (ከገጽ 350 እስከ 355)።
መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️🔥
የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት 👇
📍 ሕማማት 📍
📍በዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ተጽፎ በ ቢኒያም ብርሃኑ የተተረከውን ሕማማት የተሰኘውን መጽሐፍ በትረካ ለማግኘት 👇👇👇
“እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።”
— ዘፍጥረት 16፥13
“አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።”
— 1ኛ ሳሙኤል 2፥3-7
https://youtu.be/KhfBtmlTJXQ?si=Flj_GJyeSKpuJxtJ
Читать полностью…ነብዩ የእግዚአብሔርን መልእክት ለእየሩሳሌም አምጸኞች እንዲህ ይላል:-
👇
ትንቢተ ሕዝቅኤል 9
1 እርሱም፦ እያንዳንዳቸው የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ከተማይቱን የሚቀሥፉ ይቅረቡ ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ።
2 እነሆም፥ እያንዳንዳቸው አጥፊውን መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መንገድ መጡ፤ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ የጸሐፊም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፤ በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።
4 እግዚአብሔርም፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው።
5 እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ፦ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም፤ ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤
6 ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
7 እርሱም፦ ቤቱን አርክሱ፥ በተገደሉትም ሰዎች አደባባዮችን ሙሉ፤ ውጡ አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ገደሉ።
8 ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ።
9 እርሱም፦ የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኃጢአት እጅግ በዝቶአል ምድሪቱም ደም፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል እግዚአብሔርም አያይም ብለዋል።
10 እኔም ደግሞ በዓይኔ አልራራም አላዝንምም፥ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ አለኝ።
11 እነሆም፥ በፍታ የለበሰው የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው፦ ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ ብሎ በቃሉ መለሰ።
“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።”
— ገላትያ 3፥27
“ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥13
“አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።”
— ሚክያስ 5፥2
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
— ኢሳይያስ 9፥6
“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11
“የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።”
— መዝሙር 27፥13-14