bibleztewahido | Unsorted

Telegram-канал bibleztewahido - ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

8045

"ልጄ ሆይ በክርስትናህ መጎልመስ ከፈለክ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር ራስህን አዛምድ" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

" በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ።"
(የሉቃስ ወንጌል 19:38)

እንኳን አደረሰን

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

የ100 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

በ30 ሰከንድ ውስጥ ስለሚጠፍ ምርጥ ቻናል ነው ይቀላቀሉ 👇

/channel/addlist/gpX29GzfGs43MWE0

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥9

“እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥9

“ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥3

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

"ይህ ዓለም ፈጽሞ እንዲያልፍ ተድላ ደስታውም ለዘላለም ፀንቶ እንዳይኖር አውቀው በሰማይ ካለ እሳት ይድኑ ዘንድ ዕውነታቸውን ለሳት ሰጡ።በዚህ ዓለም ብዙ ዘመን ከመኖርም በጎነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት እንዲሻል ከብዙ ዘመኖችም አቤቱ አንዲት ሰዓት ይቅርታህን ማግኘት እንዲሽል አውቀዋልና ሰውነታቸውን ለሳት ሠጡ።የኛ ዘመን ምንድነው እንደ ጥላ የሚያልፍ በእሳት ዳር ያለ ሰም ቀልጦ እንዲጠፋ እንደዚያ አይደለምን?አቤቱ አንተ ግን ለዘላለሙ ትኖራለህ ዘመንህም የማይፈጸም ነው ስም አጠራርህም ለልጅ ልጅ ነው።"

2ኛ መቃብ 13:3-6

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
— ማቴዎስ 28፥19-20

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 5፥20

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

የኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት
ወልደ እግዚአብሔር፣ ወልደ ማርያም (የእግዚአብሔር አብ ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ) ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት አሉት፡፡ የመጀመሪያው (ቀዳማዊ) ልደት ዘመን ከመቆጠሩ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ ከሰው አእምሮ በላይ በሆነ ምሥጢር (አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ) የተወለደው ልደት ነው (መዝ 2፥7 መዝ 109፥3 ምሳ 8፥25)፡፡ ሁለተኛው (ደኀራዊ) ልደቱ ደግሞ  ዓለም ከተፈጠረ አዳም ከበደለ ከአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደው ልደት ነው (ገላ 4፥4 ኢሳ 7፥14 ኢሳ 9፥6 ዘፍ 3፥15 ፤18፥13 ፤ 12፥8 ፣ መዝ 106፥20)፡፡ ዘመን የማይቆጠረለት፣ በቅድምና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረ፣ ዓለምንም በአምላክነቱ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አካላዊ ቃል መለኮታዊ አካሉን፣ መለኮታዊ ባሕርይውን ሳይለቅ በተለየ አካሉ ንጽሕት፣ የባሕርያችን መመኪያ ከምትሆን  ከድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምላካዊ አካልና ባሕርይን ከሰው አካልና ባሕርይ ጋር ያለመጠፋፋት፣ ያለመቀላቀል ተዋሐደ እንጅ አካሉም ባሕርይውም አልተለወጠም፡፡
ሊቁ አባታችን ቅዱስ ፊሊክስ የጌታችንን ቀዳማዊና ደኀራዊ ልደቱን በተናገረበት አንቀጽ “ዓለም ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው በኋላ ዘመን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረ እርሱ ነው፤ እርሱ ሰውም ቢሆን አንድ አካል፣ አንድ ገፅ፣ አንድ ባሕርይ ነው” በማለት ሁለቱን ልደታት አስተምሯል፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ፊሊክስ 38፡10 በተጨማሪም ቅዱስ ናጣሊስ “ከእግዚአብሔር አብ በተወለደው በቀዳማዊ ልደቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው፤ ከድንግል በተወለደው በደኃራዊ ልደቱ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ እርሱ አንዱ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ የሚሆን የሚተካከል ፍጹም አምላክ ነው፤ እርሱ ብቻ ከድንግል በተወለደው ልደት በሥጋ ከሰው ጋር አንድ የሚሆን ፍጹም ሰው ነው፡፡” ብሏል፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ናጣሊስ 46፡3-4)

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

በጌታችንና በአምላካችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተደረገልን ፍጹም ሥርየትና እርቅ ግልጥ ሆኖ የተጀመረው በነገረ ልደት ነው። የጌታችን ልደት በነገረ ድኅነት ትልቅ ስፍራ የያዘና እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ፍጹም ልዩ መሆኑን ያሳየ ነው። መስተጻርራን የነበሩ ሰማይና ምድር፣ ሰውና መላእክት በአንድነት ለምስጋና ታድመዋል። የእረኞች አንደበት ከመላእክት ጋር ለሰማያዊ ምስጋና ብቁ የሆነበት፤ ግዕዛን የሌላቸው እንስሳት ሰራኢ መጋቢያችን፣ በዘባነ ኪሩቤል በሰማያት የምትገለጥ አንተ ነህ ሲሉ እስትንፋሳቸውን የገበሩለት፤ የምድር ነገሥታት በሥልጣንህ ሽረት በመንግሥህ ህልፈት የሌለብህ የነገስታት ንጉሥ አንተ ነህ ሲሉ ወርቅን ለመንግሥቱ፣ ዕጣንን ለክህነቱ፣ ከርቤን ለህማሙ ዕጅ መንሻን ያበረከቱለት፤ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ያን ልዩ ክብር የዩበት፤ ይህ ልደት በእውነት ልዩ ነው።

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት
👇

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።”
— መዝሙር 14፥2

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

ኅዳር ጽዮን
"ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል፡፡

ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡

ነቢዩ ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጸልዮና ጹሞ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት ‹ታቦተ ጽዮንን› እንደተቀበለ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡

ታቦተ ጽዮን ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸችበት ምክንያት የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ንጽሕና ለማመልከት ነው፡፡ በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ የተለበጠች መሆኗ ደግሞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል የመሆኗ ምሳሌ ነው፡፡

ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር በዝማሬ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ‹‹ለንጉሥ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራ ቤት የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት፡፡

ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ራሱ ከተማ በደስታ አመጣት፡፡ ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ መዘምራን ነበሩ፤ በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር፡፡ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት በገና ይደረድር ነበር›› እንዲል፤ ነቢዩ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት የተቀኘው ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳናችን ምክንያት የሆነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያመስገን ነው፡፡ (፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፬)

ታቦተ ጽዮን እስራኤል የዮርዳኖስን ባሕር ለመሻገር በተቸገሩ ጊዜ ነቢዩ ኢያሱ እግዚአብሔር አምላክ በነገረው መሠረት ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት ወደ ዮርዳኖስ እንዲሄዱ ነገራቸው፤ እነርሱም እንደታዘዙት አደረጉ፤ ታቦቱን የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ፡፡ (ኢያ. ፫፥፩-፲፯)

እስራኤላውያን በመካከላቸው የቃል ኪዳኑ ታቦት በያዙ ቁጥር በጦርነታቸው ሁል ጊዜ ያሸንፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤል ስለበደሉት እንዲሁም የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በደላቸውና ክፋታቸው ስለበዛ ታቦተ ጽዮን ተማርካ ወደ ፍልስጥኤም ሄደች፡፡ በዚያ በአሕዛብ ምድርም ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገች ፍልስጥኤማውያንን ስለአስጨነቀቻቸው የፍልስጥኤማውያን አለቆች የቃልኪዳኑን ታቦት ልዩ ልዩ ገጸ በረከቶችን አስይዘው ወደመጣችበት በሠረገላ አድርገው በክብር ሸኝተዋታል፡፡ (፩ኛ.ሳሙ. ፭፥፩-፲፭)
ሀገራችን ኢትዮጵያም በንግሥተ ሳባ አማካኝነት ለታቦተ ጽዮን መቀመጫ እንድትሆን የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኗል፡፡ ይህም እንዲህ ነበር፤ ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብ ለማድነቅ ምድረ እስራኤል ድረስ መጓዟን ተከትሎ ከንጉሡ ቀዳማዊ ምኒልክን ፀነሰች፡፡

ቀዳማዊ ምኒልክ ከአደገ በኋላ አባቱን ሊጠይቅ ሂዶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ አብረውት አንድ ሺህ ሁለት መቶ እስራኤላውያን የበኩር ልጆች፣ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት በአዛርያስ የሚመሩ ሌዋውያን ካህናትም አብረውት ለጉዞ ተነሡ፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትንና ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶችን ይዘውም ነበር።

ነገር ግን ታቦተ ጽዮንን አዛርያስና ካህናቱ ተማክረው ቀዳማዊ ምኒልክ እንኳን ሳይሰማ በምሥጢር ይዘዋት ሊመጡ ተስማሙ፡፡ ዕቅዳቸውን ለማሳካት በታቦተ ጽዮን አምሳያ ሌላ ታቦት አዘጋጅተው ለመሄድ በሚነሡበት ዕለት ሌሊትም ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ሄዱ፡፡

ከቤተ መቅደስ ሲደርሱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበርና የቤተ መቅደሱ በር ተከፍቶ እና ውስጡም በብርሃን ተሞልቶ ታቦተ ጽዮንም ከመንበሯ በመነሣት ከፍ ብላ አገኟት። በዚህም የአምላክን ፈቃድ ተረድተውና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በፍጥነት ይዘዋት ወጡ፡፡ በአምሳያዋ የሠሩትንም ቅርፅ በመንበሩ ላይ አስቀምጠው ሄዱ።

የንጉሡ ወታደሮች በፍጥነት ቢጓዙም ቀዳማዊ ምኒልክ እና አዛርያስ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ሲጓዙ እጅግ ፍጣን ስለበር ሊደርሱባቸው አልቻሉም። መጽሐፈ ክብረ ነገሥት ይህንን ሲጠቅስ ‹‹ከመሬት አንድ ክንድ ያህል ከፍ ብለው ይሄዱ ነበር›› በማለት ይገልጸዋል። ባሕረ ኤርትራን ከተሻገሩና ግብፅ ከደረሱ በኋላ ዕረፍትን ባደረጉ ጊዜ አዛርያስ ለቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዘዋት እንደመጡ ነገረው፡፡

አያይዞም ‹‹አንተም ብትሻ ታቦቷንም ወደ ሀገሯ ልመልሳት ብትል አትችልም፤ አባትህ ሰሎሞንም ሊወስዳት ቢመጣ አይሆንለትም›› አለው። ከቦታ ቦታ ይዣት እንቀሳቀሳለው ቢልም ያለ ፈቃዷ ምንም እንደማያደርግና ሁሉ ነገር በአምላክ መልካም ፈቃድ እንደሚፈጸም ነገረው። ቀዳማዊው ምኒልክም ይህን ሲሰማ ተደሰተ፤ ሕዝቡና ሠራዊቱ በሙሉ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከግብፅ ምድር ወጥተው እስከ ኢትዮጵያ በታላቅ እልልታና ሆታ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ።

ኅዳር ፳፩ ቀን አክሱም በደረሱ ጊዜም እናቱ ንግሥተ ሳባ ተቀበለችው፤ ደስታና እልልታውን ተመልክታ ያገኙት ነገር እንዳለ ብትጠይቀው ታቦተ ጽዮንን እንዳመጧት ነገራት፡፡ የእርሷም ደስታ እጥፍ ድርብ ሆነ። ታቦቷንም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስቀመጡአት፡፡

ከዚያም ዘመን ጀምሮ በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራትን በማሰብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፤
ክብረ ነገሥት ተርጓሚ ሥርግው ገላው (1994 ዓ.ም)
መዝገበ ታሪክ ቊጥር 1 (መምህር ኅሩይ ኤርምያስ)

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

#በእንተ #ቁርባን
"ሥጋውን በምንቀበልበት ጊዜ በትናጋ መብላት እንጂ በጥርስ ማኘክ አይገባም" ይላል (ገድለ አቡነ መብዓ ጽዮን)። ካህናትም መጥነው ማቀበል ይገባቸዋል። ነገረ ቁርባን አምስቱን አዕማደ ምሥጢር ላልጠነቀቀ ምእመን እንዳይከብደው አስቀድሞ አምስቱን አዕማድ ማስተማር ይገባል። ትምህርተ ኅቡዓት ከቁርባን በፊት በመምህራን ይተርጎም መባሉ ስለቁርባን ባለመረዳት ብዙው ሰው እንዳይጎዳ በማሰብ ነው።

ከጥምቀት በፊት የሠራነው ኃጢአት በጥምቀት ይሠረያል። ከጥምቀት በኋላ የሠራነው ኃጢአት ደግሞ በክርስቶስ ሥጋና ደም ይሠረያል። ስለሆነም ማንኛውም ክርስቲያን ንሥሓ እየገባ ሥጋውን ደሙን መቀበል ይገባዋል። በክርስቶስ ሥጋና ደም የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን። ስንቆርብ አንድነታችን ይጠነክራል (1ኛ ቆሮ.10፥17፤ ዮሐ.6፥51-58)። ሥጋውን ደሙን በንጹሕ ልብ ቢቀበሉት ምሥጢር ያናግራል። የወይኑና የኅብስቱ መልኩና ጣዕሙ ሳይለወጥ ወደ ክርስቶስ ሥጋነትና ደምነት ይለወጣል። "ኢይትዌለጥ ኅብስት እምጣዕሙ ወእምልምላሜሁ ዘትካት። እንዘ ኅዱር ላዕሌሁ መለኮት" እንዲል (መጽሐፈ ባሕርይ)።

ከመቁረባችን በፊት ንሥሓ መግባት፣ ከበደል መንጻት፣ መልካም ሥራዎችን መሥራት ይገባል። ይህንን ሳናደርግ ብንቆርብ መቅሠፍትን በራሳችን ላይ እናመጣለን (1ኛ ቆሮ.11፥27-29፤ ሃይ.አበ.20፥27-28)። ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ ለፍጹማን በአምሳለ ሕፃን፣ በንጹሕ በግ አምሳል የሚገለጽበት ጊዜ አለ (አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን 30፥ ድርሳን 31፤ ፊልክስዩስ ተስእሎ 90)። የክርስቶስን ሥጋና ደም ከተቀበልን በኋላ ለወጣንያን ዕለቱን ለፍጹማን እስከ ዘለዓለም ምራቅን መትፋት አይገባም (ፊልክስዩስ 10)። ከመቁረባችን በፊት በውሃ አፍን መጉሞጥሞጥ አይገባም፣ ሳንጾምና ለአፋችን ምረት ሳይሰማንም መቁረብ አይገባንም (ሳዊሮስ ዘእስሙናይን)።

ከቁርባን በኋላ ዕለቱን ሰውነትን መታጠብ፣ ከልብስ መራቆት፣ መስገድ፣ ጥፍርን መቆረጥ፣ ጸጉርን መላጨት፣ ፍርድ ቤት ገብቶ መሟገት፣ ከአቅም በላይ መብላት፣ መበጣት አይገባም።

ምንጭ፦ የእግዚአብሔር ስጦታ (ከገጽ 350 እስከ 355)።

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት 👇

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

📍 ሕማማት 📍

📍በዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ተጽፎ በ ቢኒያም ብርሃኑ የተተረከውን ሕማማት የተሰኘውን መጽሐፍ በትረካ ለማግኘት
👇👇👇

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።”
— ዘፍጥረት 16፥13

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።”
— 1ኛ ሳሙኤል 2፥3-7

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

https://youtu.be/KhfBtmlTJXQ?si=Flj_GJyeSKpuJxtJ

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

ነብዩ የእግዚአብሔርን መልእክት ለእየሩሳሌም አምጸኞች እንዲህ ይላል:-
👇

ትንቢተ ሕዝቅኤል 9
1  እርሱም፦ እያንዳንዳቸው የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ከተማይቱን የሚቀሥፉ ይቅረቡ ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ።
2  እነሆም፥ እያንዳንዳቸው አጥፊውን መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መንገድ መጡ፤ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ የጸሐፊም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
3  የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፤ በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።
4  እግዚአብሔርም፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው።
5  እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ፦ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም፤ ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤
6  ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
7  እርሱም፦ ቤቱን አርክሱ፥ በተገደሉትም ሰዎች አደባባዮችን ሙሉ፤ ውጡ አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ገደሉ።
8  ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ።
9  እርሱም፦ የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኃጢአት እጅግ በዝቶአል ምድሪቱም ደም፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል እግዚአብሔርም አያይም ብለዋል።
10  እኔም ደግሞ በዓይኔ አልራራም አላዝንምም፥ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ አለኝ።
11  እነሆም፥ በፍታ የለበሰው የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው፦ ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ ብሎ በቃሉ መለሰ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።”
— ገላትያ 3፥27

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥13

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።”
— ሚክያስ 5፥2

“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
— ኢሳይያስ 9፥6

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።”
— መዝሙር 27፥13-14

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

እንኳን ለመላኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

"ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።"
ዳን9: 21

   የመላኩ ምልጃ እና ተራዳይነት አይለየን አሜን፡፡
መልካም በዓል !!!!

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“በነጋውም ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቈርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር፤ የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር።”
1ኛ ሳሙኤል 5፥4

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

Читать полностью…

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም። እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤ የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
— ማቴዎስ 8፥10-12

Читать полностью…
Subscribe to a channel