ኢዮኤል 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤
²⁹ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤
ይሄ ሊሆንብን ግድድድ ነው🔥🔥🔥🔥🔥
ይህንን ተረድቻለሁ🔥😍
በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤
— ፊልጵስዩስ 1፥6
#ሰይጣን ወደ ህይወታችን ሲመጣ 3 ነገሮችን ኢላማ አድርጎ ነው የሚመጣው።
ይህንን ድንቅ ትምህርት ሰምታችሁ በተሰጣችሁ ስልጣን የዲያቢሎስን አሰራር ማፍረስ ጀምሩ🔥🔥🔥🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ጌታ ሆይ ምን ቢገባቸው ነው?"
😭😭😭
"ምን ቢያገኛቸው ነው?"
😭😭😭
"ምን ሆነው ነው?"
😭😭😭
"ኧረ ምንድነው የተረዱት?"
😭😭😭
"ምን ቢነካቸው ነው?"
😭😭😭😭
"ምንድነው የበራላቸው ጌታ ሆይ?"
😭😭😭😭
"ለአመታት እንዲጸልዩና እንዲጾሙ ያደረጋቸው ምንድነው?"
😭😭😭😭😭
"ከአንተ ውጪ ሌላ ነገር እንዳይፈልጉ ያደረጋቸው ምንድነው?"
😭😭😭
"ከአንተ ውጪ ሌላ ነገርን እንዳይወዱ ያደረጋቸው ምንድነው?"
😭😭😭
"አለምንና የአለምን ነገር ያቀለለባቸው ምንድነው?" 😭😭😭😭😭
"ሁሉን ትተው አንተን መፈለግ ስራቸው እንዲሆን ያደረገው ምንድነው?"
😭😭😭
"ከአንተ ጋር ሕብረት ለማድረግና አንተን ከማወቅ በስተቀር፣ የአንተን ክብርና ኃይል ከመሸከም ውጪ ሌላውን ነገር ትርጉም አልባ ያደረገባቸው ምንድነው?"
😭😭😭😭
"ብዙ አማራጭ እያላቸው፤ አንተን ምርጫቸው እንዲያደርጉ ያደረጋቸው ምንድነው?" 😭😭😭😭
"በተገለጠው ነገር ረክተው እንዳይቀመጡ፤ ነገር ግን ለበለጠው፣ ለከበረውና ለጠለቀው ነገር ሁለንተናቸውን እንዲሰጡ ያደረጋቸው ምንድነው?" 😭😭😭😭
"ስጋዊነትን፣ ስንፍናን፣ ድካምን፣ ትዕቢትን፣ ንቀትንና ቅናትን፣ ራስ-ወዳድነትን፣ ተድላን መውደድን፣ የገንዘብ ፍቅርን፣ ዝናንና ክብርን፣ በቀላሉ ተስፋ መቁረጥንና መታከትን፣ መወላወልን ከእነርሱ የወሰደው ምንድነው?"
😭😭😭😭😭😭
"ያላቸውን ሁሉ ለክብርህና ለኃይልህ እንዲለውጡ ያደረጋቸው ምንድነው?"
😭😭😭😭😭
"ከምክንያት በላይ አንተን ያለማቋረጥ እንዲፈልጉ ያደረጋቸው፣ መንፈስህን ከህይወታቸው፣ ከምንም ደግሞም ከማንም በላይ እንዲወዱና እንዲጠሙ ያደረጋቸው ምንድነው?"
😭😭😭😭😭
"ነፍሳቸውን በስጦታው ሳይሆን በሰጪው ፍቅር እንዲያዝ ያደረጋቸው ምንድነው?"
😭😭😭😭😭😭😭
"የትውልድን መዳንና መለወጥን ረሃብ አጥንታቸው ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ ያደረገው ምንድነው?"
😭😭😭😭
"አለምን በጀርባቸው ላይ እንደተሸከሙ ለመጸለይ መንበርከክን ያቀለላቸው፣ ምጥ እንደያዛት ሴት ተንበርክከው በእንባና በሲቃ እንዲያምጡ ያደረጋቸው ምንድነው?" 😭😭😭😭😭
"ኦ! ጌታ ሆይ የነካቸው ይንካን! የበራላቸው ይብራልን! የተገለጠላቸው ይገለጥልን! እነርሱን ያገኘው ያግኘን! ወደ ሕብረት፣ አንተን ወደ ማወቅ፣ ክብርህን ወደ መራብና መጠማት ደግሞም ወደ ማየት እናድግ ዘንድ የገባቸው ይግባን በኢየሱስ ስም!!" 😭
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ወንጌል🔥❤
ወንጌል ንግግርና ቃል ብቻ ሳይሆን በቃል ውስጥ የሚገለጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ (መረዳት) የሚታወቅ የእግዚአብሔር የማዳን ኃይል ነው።
1ኛ ተሰሎንቄ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።
⁶ ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤
ሰው ወንጌልን በመገለጥ ሲቀበል በመከራ ብቻ ሳይሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ብዙ ደስታንም ይቀበላል።
ወንጌል የሚሰጠንን ሰላምና ደስታ ማንም ምንም ሊሰጠን አይችልም።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ኧረረረረ ስሙትት😭😭😭
ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁን personal fellowship አቅም የሚሰጠው ነገር ነው ያወራሁት አሁን ስሙትና ከኢየሱስ ጋር ያላችሁን ህብረት ይበልጥ አጠንክሩት🌧🌧🔥🔥
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
እንደ እኔ የእግዚአብሔርን ምህረት ያጣጣመ የለም😍😍😍
ጌታ ሆይ ወላጆቼን ተጠቅመህ ልትሰራብኝ ወደዚህች ምድር ስላመጣኸኝ አመሰግንሃለሁ እወድሃለሁ🥰🥰🥰🥰
“ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ።”
— መዝሙር 22፥10
ለወንጌል ተወልጃለሁ❤❤🔥🔥
2ኛ ቆሮ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤
¹⁵ በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤
¹⁶ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?
በህይወት መዝገብ ፃፍከኝ😍😍😭😭
ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ❤️❤️
ይህንን ዝማሬ ስሙት ብቻ ሳይሆን ደጋግማችሁ ስሙትትትት😭😭😭
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ኢየሱስን በቃል ለመግለፅ ስለተቸገርኩኝ ትንሽ ውስጤ ያለውን ቃል ስለሚገልጥልኝ ነው ይህንን photo የለጠፍኩት❤️
“ኮሬብ አጠገብ ባለው ዐለት በዚያ እኔ በአንተ ፊት እቆማለሁ። ዐለቱን ምታው፤ ከእርሱም ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ ይወጣል።” ስለዚህ ሙሴ በእስራኤል አለቆች ፊት ይህንኑ አደረገ።”
— ዘጸአት 17፥6 (አዲሱ መ.ት)
““በትሪቱን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን በአንድነት ሰብሰቡ፤ እነርሱም እያዩ ዐለቱን ተናገሩት፤ ዐለቱም ውሃ ያወጣል። አንተም ለማኅበረ ሰቡ ከዐለቱ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እነርሱና ከብቶቻቸውም ይጠጣሉ።””
— ዘኍልቁ 20፥8 (አዲሱ መ.ት)
“ሁሉም ከአንድ መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዐለት ጠጥተዋልና፤ ያ ዐለት #ክርስቶስ ነበረ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥4 (አዲሱ መ.ት)
1ኛ ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።
² ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
የቅርብ ዘመዴ ቃልኪዳን ጥላሁን
እጅግ በጣም ድንቅ ዝማሬ ነው ተባረኩበት😍😍😍
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ፅድቅ ማለት #በእግዚአብሔር_ፊት ያለ ፍርሃትና ያለመሸማቀቅ የመቆም #ብቃት ማግኘት ማለት ነው።
ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት የቆምኩበት #ብቃቴ ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ጥገኛ ነኝ❤❤❤
መንፈስ ቅዱስ በጣም እወድሃለሁ ያላንተ ባዶ ነኝ😭😭
መንፈስ ቅዱስ በጣም እወድሃለሁ ያላንተ የማልጠቅም ነኝ😭😭
መንፈስ ቅዱስ እወድሃለሁ አንተ ከሌለኸኝ ማንም አይፈልገኝም😭😭😭
መንፈስ ቅዱስ አንተ የድካሜ መበርቻ የውድቀቴ መነሻ ኢየሱስን በልቤ አድምቀህ የምትስል ልዩ ወዳጅ ነህ አጥብቄ እወድሃለሁ ከምንም በላይ ታስፈልገኛለህ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ዳዊት ሲናገር እንደዚህ አለ...የታመንኩት እግዚአብሔር ስለሆነ ለምን ነፍሴን ወደ ተራሮች (ወደ ትላልቅ ሰዎች) ተመልከቺ ተቅበዝበዢ ትሏታላችሁ?? የታመንኩትና የተደገፍኩት የተመካሁበት እግዚአብሔር ነው ትላልቅ ሰዎች ዘመዶች እኔን ሊረዱኝ አይችሉም እረድኤቴ ዘመድ ወይም ትላልቅ ሰዎች ሳይሆኑ እግዚአብሔር ነው፣ በእግዚአብሔር ተደግፌአለሁ በእግዚአብሔር ታምኛለሁና እንደ ሸንበቆ የሚሰበረውን ሰው አምኜ መውደቅ አልፈልግም።
#በእግዚአብሔር_ታመንሁ፤ ነፍሴን፦ እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት #ትሉአታላችሁ?”
— መዝሙር 11፥1
ሰውን የሚታመን የተረገመ ነው በእግዚአብሔር የሚደገፍ ግን ብሩክ ነው።
እረድኤቴ ሰማንና ምድርን ከሰራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
መዝሙር 121
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?
² ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
አይኖቻችን ሰዎች ላይ ሳይሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ናቸው።
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
መዝሙር 42
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።
² ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
ውሃ ለአሳ የግድ እንደሚያስፈልጋት
አፈር ለሳር የግድ እንደሚያስፈልገው እእንዚሁ ለእኛም መንፈስ ቅዱስ የግድ ያስፈልገናል😭😭😭😭🔥🔥
ኤፌሶን 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴-¹⁵ ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤
¹⁶-¹⁷ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥
¹⁸-¹⁹ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።
Kingdom manifestation 🔥
Day 1🔥
Arbaminch Mountain prayer With Arbaminch Gods General🔥
Their said to them, "The kingdom of God is in your midst."
— Luke 17:21
#መንፈስ_ቅዱስ፦ ትልቁ አባታችን የገባልንን የተስፋ ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን ትልቁ ስጦታ፣ ለቤዛ ቀን የታተምንበት የርስታችን መያዣ ነው።
እነሆም፥ ከባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።
-----ሉቃስ 24፥49
ኤፌሶን
-----------
13፤-----በተስፋውም መንፈስ ቅዱስ ታትማችሁ፤
14፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥
አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
— ዮሐንስ 14፥26
መንፈስ ቅዱስ ከሌለ ህይወት የለም።
መንፈስ ቅዱስ ከሌለ ክርስትና የለም።
መንፈስ ቅዱስ ከሌለ ኢየሱስ ክርስቶስም የለም።
@Binarevivalist
@Binarebivalist
@Binarevivalisy
በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ
በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ
ሌሎቹ እንዳዮኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል
ከነ አሮን ክህነት #የኢየሱስ ይበልጣል
ሊቀ-ካህኔ እንደ መልከ ጸዴቅ
ሊቀ-ካህኔ ለዘላለም ሹም ነህ
ሊቀ-ካሆኔ ለኔም ህይወት መዳን
ሊቀ-ሊቀ ካህኔ ምክኒያቱ አንተ ነህ
ሊቀ-ካህኔ በማይጠፋው ክህነት
ሊቀ-ካህኔ በማይሽረው ሞት
ሊቀ-ካህኔ የምትማልድልኝ
ሊቀ-ካህኔ ቆመህ በአብ ፊት
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን ሰጥሃለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ
አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር
ዕብራውያን 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
መንፈሳዊ አለም ላይ ሩጫውን ቀደምኩኝ ሳይሆን ሩጫውን ጨረስኩኝ ነው የሚባለው።
ሩጫችሁን ከሌላው ሩዋጭ አንፃር determine ማድረግ የለባችሁም።
በእግዚአብሔር ዓለም መቅደምና መቀዳደም የለም የተሰጣችሁን የእምነት ሩጫ በመስመራችሁ ላይ በማጠብጠብ በተሰጣችሁ ሰዓት ጀምራችሁ ትጨርሳላችሁ።
ብላቴኖች ይደክማሉ እግዚአብሔር የሚተማመኑ ግን.....🔥🔥🔥
ኢሳይያስ 40
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤
³¹ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ክብር ነው : የእግዚአብሔር ጥበብ ነው:ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሃይል ነው :ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው: ኢየሱስ መሲሕ ነው:ኢየሱስ የእባቡን ራስ የቀጠቀጠው የሴቲቱ ዘር ነው: ኢየሱስ የእግዚአብሔር እውነት ነው : ኢየሱስ የአለም ብርሃን ነው: ኢየሱስ የክብር ተስፋችን ነው: ኢየሱስ የእግዚአብሔር የመጨረሻው መገለጥ ነው: ኢየሱስ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን የተማረ ነው :ኢየሱስ በአብ ፍቅር የሚኖር ነው: ኢየሱስ ከራሱ ፍቃድ የአባቱን ፍቃድ የሚያስቀድም ታዛዥ አምላክ ነው: ኢየሱስ መንገድ እውነት ህይወት እና በር ነው: ኢየሱስ እንደ መልከፀዴቅ ያለ ለዘላለም ሊቀካህናት ነው: ኢየሱስ በእውነተኛይቱ ድንኳን የገዛ ደሙን ይዞ የገባ ነው: ኢየሱስ ዳግም በክብር ይመጣል።
አላለቀም ግን እኔ መፃፍ ደከመኝ....😭❤️