binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

ነፍሳችሁን ያያስጨነቁ ጠላቶቻችሁ በኢየሱስ እንደገለባ ተበተኑ🔥🔥🔥

“እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።”
— መዝሙር 68፥1

ህናው ጌታ ምስክር ጠላቶቻችሁ እንደገለባ ተበተኑ🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ነፍሳችሁን ያጠመደ ማንኛውም የክፉ እውቀት በኢየሱስ ስም ዛሬ ምሽት ከነፍሳችሁ ላይ ወደቀ ወደቀ ወደቀ ነፍሳችሁ ከጨለማ ወጥመድ አመለጠች በኢየሱስ ስም🔥🔥🔥🔥

ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
— መዝሙር 124፥7

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በጓዳዬ ያለህ አለማዜ ንብረቴ
ለሰው የማሳይህ ትምክህቴ ኩራቴ🥺😭😭

    እውነተኛ ወዳጅ ቀን የማይለውጥህ
    አነሰብኝ ለኔስ እድሜዬን ብሰጥህ😭😭

መደምደሚያዬ ነህ የመጨረሻዬ
ኢየሱሴ ለኔ ×2
😭😭😭😭

1ኛ ዮሐንስ 5
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

¹³ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ የሚገኙት ፍቅር በሚባል መንገድ ላይ ነው።

ፍቅርን ስትከታተሉ ወደ መንፈሳዊ ስጦታውች ይወስዳችኃል።

ፍቅር ወደ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚያመራና የሚያደርስ መንገድ ነው።

መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙላት እንዲገለጥባችሁ ከፈለጋችሁ ፍቅርን ተከታተሉ ያደርሳቹሃል።

#ፍቅርን_ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ።
— 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥1


#ፍቅርን ተከታተሉ...

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ እኮ የህይወት ውሃ ነው😭😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የአብ ትኩረት ልጁ ኢየሱስ ላይ ነው የኢየሱስ ትኩረት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ላይ ነው የመንፈስ ቅዱስ ትኩረት ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው።

ሰው ኢየሱስን ካላየ እና ካልሰማ ፈፅሞ መዳን አይችልም።


ትኩረት ሁሉ ወደ ኢየሱስ🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዘማሪ አውታሩ ከበደ
አምላኬ ነው የደገፈኝ😭😭😭
ተባረኩበት😭😭😭


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ከእግዚአብሔር ማንነት በጣም የሚገርመኝና የምወደው አንዱ መልካምነቱ ነው። እስቲ ከእግዚአብሔር ማንነት የሚገርማችሁንና የምትወዱለትን ባህሪ ፃፉ😍😍😍

እግዚአብሔር ሁሌም መልካም ነው❤😊

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰው ሲራብ ስታዩ ~ወንጌል ስሩ !😭😭

ሰው ሲሞት ስታዩ ~ ወንጌል ስሩ !😭😭

ሰው ሲረክስ ስታዩ ~ወንጌል ስሩ !😭😭

ሰው ሲሰክር ስታዩ ~ወንጌል ስሩ !😭😭

መጨረሻ እንደቀረበ ስታስቡ ~ወንጌል ስሩ !😭😭😭

ነጻነታችሁን ስታጣጥሙ ~ወንጌል ስሩ !😭😭

ከቁጣ እንዳመለጣችሁ ስታዩ ~ወንጌል ስሩ !😭😭😭

ከስዖል ቃልክዳናችሁ እንደፈረሰ ስታስቡ ~ወንጌል ስሩ !😭😭

ከገሃነም መሃላችሁ እንዳልጸና ስታውቁ ~ወንጌል ስሩ !😭😭

እግዚአብሔር በልጁ እንደተቀበላችሁ ስታውቁ ~ወንጌል ስሩ !😭

ወደ እናንተ ማንም ቢመጣ ሳትምሩ ወንጌል ንገሩት !😭

“ቃሉን ስበክ።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2

አገልጋይ ዕንባቆም

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አራቱ የመንፈስ ቅዱስ ስራዎች በአማኞች ህይወት ውስጥ....❤️❤️❤️

ኢየሱስ በአብ ዘንድ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በነበረው ክብር ከከበረ በኋላ አብ መንፈስ ቅዱስን በኢየሱስ ለምናምነው ለእኛ በኢየሱስ ስም አፍስሶልናል።

በዚህ ዓለም ስንኖር ክርስቶስ በአብ ፊት እንዳለ ሁሉ እኛም ሰማይን ወክለን በምድር አለን ክርስቶስን የወከልነው ውስጣችን የእግዚአብሔር መንግስት ወይንም መንፈስ ቅዱስ ስላለ ነው።

ታድያ ውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሆኖ አራት መሰረታዊ ስራዎችን ያከናውናል።

1. ስለኃጢአት መውቀስ
2. ስለ ጽድቅ ማረጋገጥ
3. ስለ ፍርድ
4. ኢየሱስን ለማክበር

አንደኛው መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ውስጥ ሆኖ ኃጢአተኞችን ይወቅሳል።

ኋጢአተኛ ማለት የሚሰርቅ የሚቅም የሚያጨስ የሚዋሽ ሳይሆን በኢየሱስ የማያምን ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ የማያምኑትን ወደ ኢየሱስ እንዲመጡና መዳናቸውን እንዲቀበሉ በእኛ በአማኞች ውስጥ ሆኖ ይወቅሳቸዋል። አስተውሉ አይከሳቸውም መክሰስ የዳቢሎስ ነው መውቀስና መክሰስ ይለያያል።

“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።”
— ኢሳይያስ 1፥18

ሁለተኛው አማኞች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ስላገኙት ፅድቅ ያለምንም ጥርጥር እርግጠኛ እንዲሆኑ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንደሆኑ እንዲረዱ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ህይወት ዘውትር ይሰራል።

ሶስተኛው የሰዎችን ህይወት የሚያበላሸውን ዲያቢሎስ ሲኦል ስለተፈረደበት አማኞች ዘውትር የዲያቢሎስን ስራ በማፍረስ ሰዎችን ሁሉ ከዲያቢሎስ ስራ እየፈታን በዲያቢሎስ ላይ ፍርድ እያስተላለፍን እንድንኖር መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ዘውትር ስራውን ይሰራል።

አራተኛውና ዋነኛው መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ህይወት ውስጥ ሆኖ የሚሰራው ስራ ኢየሱስን ማክበር ነው።

ኢየሱስ እራሱ ሲናገር እርሱ ያከብረኛል እያለ ይናገራል የኢየሱስን ህይወት በሙላት በህይወታችን እያበዛ ዞዌ የሆነውን የእግዚአብሔርን ህይወት በእኛ እያትረፈረፈ ዘውትር ኢየሱስን በህይወታችን እያከበረ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ይኖራል።

ዮሐንስ 16
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁷ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።

⁸ እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤

⁹-¹⁰ ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤

¹¹ ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።


¹² የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።

¹³ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

¹⁴ እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰማይ የበለጠ በምድር ላይ የተገለጠ የሚሆነው ኢየሱስ በስጋ በምድር ላይ መኖሩ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በሙላት መፍሰሱ ነው። ለዛም ነው ኢየሱስ እኔ ብሔድ ይሻላቹሃል ያለው።

ኢየሱስ በስጋ ተገልጦ በምድር ሲመላለስ አማኑኤል ወይም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነበር የተባለው። ይህም የሆነው በሰውነት ተገልጦ ነበር። በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ነበር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የተበባለው።

ኢየሱስ በአብ ዘንድ ቀድሞ በነበረው ክብር ከከበረ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ህይወት ውስጥ ለዘለአለም ሊኖር በኢየሱስ ስም ከወረደ በኋላ ግን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ወይም አማኑኤል ሳይሆን የሆነው እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ነው የሆነው። መፅሐፍም ሲናገር ስጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ/መኖሪያ ነው እናንተ የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ ናችሁ ብሎ ይናገራል።

ኢየሱስ በስጋ መገለጡ እግዚአብሔርን አማኑኤል ሲያደርገው መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ህይወት ለዘለአለም ሊኖር መውረዱ ደግሞ እግዚአብሔርን በእኛ ውስጥ ነው ያደረገው።

ኢየሱስ በስጋ በተገለጠበት ዘመን በስጋ የተገለጠውን አማኑኤል ለመንካት ለመዳሰስ ለማውራትና ህብረት ለማድረግ የግድ ኢየሱስ በሚያገለግልበት ቦታ መኖርና መገኘት ግድ ነው ምክኒያቱም ኢየሱስ ወይም አማኑኤል የተገለጠው በስጋ ሰውነት ስለሆነ።

መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ ግን ኢየሱስን እንዳይገደብና በሁሉም ቦታ በተመሳሳይ ሰአት እንዲገኝ አድርጎታል።

አሁን ኢየሱስን ለመንካት ለመዳሰስ ለማውራትና ህብረት ለማድረግ የግድ ኢየሱስ ሲያገለግልበት የነበረው ቦታ መገኘት አይጠበቅብንም ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ለዘለአለም በውስጣችን ሊኖር ስለፈሰሰና መቅደሱ ስላደረግ ውስጣችን በመንፈስ ቅዱስ ታትሟል ዝም ብለን ስሙን በመንፈስ ስንጠራው ከእርሱ ጋር የጠለቀውን ህብረት እንድናደርግ ተፈቅዶልናል የልጅነትንም ስልጣን ተሰጥቶናል።

አሁን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሳይቀንስና ሳይከፋፈል በእያንዳዳችን ውስጥ አለ።

ኢየሱስን እኔ በሄድ ይሻላቹሃል ያስባለውም ይሄ ይመስለኛል።

ኢየሱስ ሄዶ ለጴጥሮስ መንፈሱን ባያፈስለት ኖሮ ጴጥሮስና ሌሎቹም ሐዋርያት ፈሪ እንደሆኑ ይቀጥሉ ነበር ሰው ሰው ይሸቱ ነበር።

አዎ ኢየሱስ ሄዶ መንፈስ ቅዱስን ባይልክልን ኖሮ ምን እንሆን ነበር??

መንፈስ ቅዱስ እጅግ አብዝቼ እወድሃለሁ አነሰተ ኢየሱስን በህይወቴ ከታሪክ ወደ እውነት ከነበር ወደ አሁን የምኖረው ህይወቴ አድርገህልኛል❤🙏

ኢየሱስ የምማረው ታሪክ ሳይሆን የምኖረው ህይወት ነው።

ይህንን ደግሞ ያደረገልኝ ለቤዛ ቀን የታተምኩበት የርስቴ መያዣ ከአብ ዘንድ በኢየሱስ ስም የተሰጠኝ ለዘለአለም በውስጤ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ነው።


ዮሐንስ 16
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁵ አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

⁶ ነገር ግን ይህን ስለ ተናገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።

⁷ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ።
— ራእይ 22፥17

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መልህቄ😭😭😭
በደንብ ስሙት😭😭😭😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ያለንበት ሁኔታ ወንጌልን እንዳንናገር ቢከለክለንም ይህንን የመዳን ወንጌል በሰው ሁሉ ፊት ከመናገር ዝም አንልም። ምክኒያቱም መድሃኒቱን ይዘን ሰው በበሽታ ሲሰቃይ ማየት ትልቅ ወንጀል ስለሆነ።

በማይመች ሁኔታ ውስጥ ይህንን የህይወት ቃል ለሰዎች ሁሉ እንድናገር ፀጋውን ያበዛልኝን ጌታዬን ኢየሱስን አመሰግነዋለሁ።😭😭🙏🙏

ድካሜን ሳስብ ብርታቱን በህይወቴ አሳይቶኛልና መንፈስ ቅዱስን እባርከዋለሁ😭😭😭🙏🙏

ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም።
  — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እኔ ሸንበቆ፣ ጉንዳን፣ ትል፣ የማልጠቅምና የማልረባ ሳልሆን በእግዚአብሔር የተወደድኩኝ ከእግዚአብሔር የተወለድኩኝ በእውነት ቃል ታስቤ የተወለድኩኝ ዋጋዬ የክርስቶስ ደም የሆነ እጅግ በጣም ውድ ነኝ።

እግዚአብሔር የተወደደ እንጂ ሸንበቆ ልጅ የለውም። 😊❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

❤️ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ❤️

በእኔ ዘንድ ያለ😭😭😭
ይህንን ድንቅ መዝሙር ጋበዝኳችሁ ካልሰማችሁት ደጋግማችሁ ስሙት😭😭😭😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥9

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በህየውት በማልፍባቸው መንገዶች የሚመጡበኝ ወጀቦችና ፈተናውች ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው ውስጤ በመንፈስ ቅዱስ ከፈሰሰው ከእግዚአብሔር ፍቅር ፈፅሞ ሊለየኝ አይችልም።

ሮሜ 8
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?

…
³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።

ወጀብ፣ ማዕበል፣ ከፍታ፣ ዝቅታ፣ ማጣት፣ ማግኘት የማያደበዝዘውና የማያቀዘቅዘው መለኮታዊ አጋፔ ፍቅር ውስጤ በመንፈስ ቅዱስ ፈሷል። ❤️❤️❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓለምና ለዘላለም በእግዚአብሔር ምሕረት ታመንሁ።
— መዝሙር 52፥8

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የማይቀየርና የፀና ኪዳን አለን😭👇

ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። 2ሳሙ 7፥15

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ቅጥር ሆኖልኝ ነው እኔስ ያለፍኩት
አላልፈውም ነበር ባይኖረኝ አባት🥺🥺🙏

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ከመረጠን ማንም ሊኮንነንና ሊከሰን አይችልም።

ምክኒያቱም አንደኛ በክርስቶስ ነን።

ሁለተኛ ደግሞ የመረጠን እግዚአብሔር እንጂ አኛ ልመረጥነውም። መመረጣችን የእኛ የሆነ ምንም ነገር ስለሌለ እና መራጩ እግዚአብሔር ሲመርጠን ከራሱ ማንነት ተነስቶ ስለሆነ ማንም ሊኮንነን እና ሊከሰን አይችልም።

እግዚአብሔር ሲመርጥ ከእግዚአብሔር ምርጫ በተቃራኒ ሊቆም የሚችል ኃይል የለም።

ሮሜ 8
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን
#ኵነኔ_የለባቸውም።

…
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥
#የሚኰንንስ #ማን_ነው?

እግዚአብሔር ከመረጠን ማን ይከሰናል?? ማንም።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የተቀበልነው ነገር ሁሉ አላቂ ሲሆን ሰጪው ግን ዘላቂ ነው።

አላቂው ላይ ሳይሆን ዘላቂው ላይ ትኩረታችንን እናድርግ🔥❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በህግ አመለካከት ውስጥ ሆነህ የእግዚአብሔር ፀጋ ሊሰራብህ አይችልም።

በህግ አቁማዳ የፀጋ ወይነጠጅ አይቀመጥምና ከህግ አቁማዳ የፀጋ ወይነጠጅ አይቀዳም።

ፀጋ የሚቀመጠው በእምነት አቁማዳ ነው።

ሉቃስ 5
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
³⁷ ባረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳል፥ እርሱም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል።

³⁸ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ማኖር ይገባል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።

³⁹ አሮጌ የወይን ጠጅ ሲጠጣ አዲሱን የሚሻ ማንም የለም፤ አሮጌው ይጣፍጣል ይላልና።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

. ቅድስና
እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ-ቁ-1[1997]
እጅግ በጣም መንፈስ ያለበት መዝሙር ነው ተባረኩበት🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“ቤተክርስቲያን አለም ፊቷን ያዞረችባቸው ሰዎች ህብረት ሳትሆን ፊታቸውን በአለም ላይ ያዞሩ ሰዎች ህብረት ናት”

"ንቀነው እንጂ ንቆን የተለየነው የአለም ክብርም ይሁን ተድላ የለም"

"ሳናገኘው ቀርተን ሳይሆን ሳንገኝለት ቀርተን ያፈረስነው የአለም ኪዳን እልፍ ነው"

በኢየሱስ ቆፍጠን ያልን አለምን የካድን ህዝቦች ነን
።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር አንዳንዴ ነፍሳችሁን ጭካኔ እና ድፍረትን ሊያስተምራት ሲፈልግ በሞት ጥላ ውስጥ እንድታልፍ ያደርጋታል።

የዛኔ ነፍሳችሁ የእግዚአብሔርን ረዳትነትና ጥበቃ በደንብ መረዳት ትጀምራለች ነፍሳችሁ ምንም እስከማትፈራ ድረስ ጨካኝና ጠንካራ ደፋር ትሆናለች።

የምታልፉባቸው ከባድ የህይወት ጎዳናዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አለመኖሩን ሳይሆን የሚናገሩ እግዚአብሔር ለትልቅ ፕሮግራም እያሰለጠናችሁ እንዳለ ነው የሚናገረው

ሌላው ደግሞ መርሳት የሌለባችሁ ነገር በምታልፍበት በህይወት ውጣ ውረድ ሁሉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አብሯችሁ ነው።

መዝሙር 23
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁴ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።

⁵ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።

⁶ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መዝሙር 91
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
² እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።
³ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።
⁴ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
⁵ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
⁶ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
⁷ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
⁸ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።
⁹ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
¹⁰ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
¹² እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ደስታችሁ እና ውስጣዊው ሰላማችሁ ፍፁም or ሙሉ እንዲሆን ማድረግ ያለባችሁ አንድ ነገር ብቻ ነው እርሱም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ጋር ያላችሁን የጥልቀውን ህብረት ማሰብ ነው።

1ኛ ዮሐንስ 1
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
³ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።

⁴ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።

ሐዋርያው ዮሐንስ ለአማኞች ደስታቸው ፍፁም እንዲሆን የፃፈላቸው በአገልግሎታቸው ስለሆነው ድንቅና ታምራት ሳይሆን ህብረታው (አንድነታቸው) ከአባትና ከልጁም ከኢየሱስ ጋር እንደሆነ እንዲያውቁ ነው።

የአማኝ ደስታው በፀሎቱ የሚመለስለት ጥያቄው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ጋር ያለው ህብረት ነው።

የአማኝ ደስታው ከእጁ በሚቀበለው ነገር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ጋር ባለው ጥልቅ ህብረት ነው።

ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።
— 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥17


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእግዚአብሔር ፍፁም ሙላት ያለው የክርስቶስን ፍቅር በማወቅ ውስጥ ነው።

ማወቅ ማለት የ theory እውቀት ሳይሆን የ Experience እውቀት ማለት ነው።

የ theory እውቀት ሳይሆን የ Experience እውቀት ነው ህይወታችንና ማንነታችን ሊሆን የሚችለው።


ኤፌሶን 3
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁶-¹⁷ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥

¹⁸-¹⁹ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።


በክርስቶስ ፍቅር መሞላት ይሁንልን የዛኔ የእግዚአብሔር ዞዌ ህይወት በህይወታችን ሙሉ ይሆናል

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…
Subscribe to a channel