binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር እናንተን ከመቀየሩ በፊት የአሳብ ዓለማችሁን ነው የሚቀይረው።

እግዚአብሔር እናንተን ትልቅ ከማድረጉ በፊት ከአእምሮአችሁ ውስጥ የትንሽነትን አሳብ አውጥቶ የትልቅነትን አሳብ እንድታስቡ ያደርጋችኋል።

ትንሽነትን እያሰባችሁ ትልቅ ልትሆኑ እንደማትችሉ ሁሉ ትልቅነትን እያሰባችሁ ትንሽ ልትሆኑ አትችሉም።

ትልልቅ ነገሮችን የማስበው አባቴ ትልቅ ስለሆነ ነው🔥

ትልልቅ ነገሮችን አስቡ ደግሞም ትልቅነትን በህይወታችሁ አውጁ ትልቅነት ማንነታችሁ ነው🔥

አሁን ላይ ትልቅነትን እንድታስቡ ነገሮች ላይፈቅዱላችሁ ይችላል ነገር ግን አባታችሁ ትልቅ ነው ትልቅነት ዘራችሁ ነው የሚታየውንና የምትሰሙትን ሳይሆን ቃሉ ስለናንተ ያለውን እውነት አውጁ🔥🔥

አባቴ ትልቅ ነው፣ ትልቅነት ዘሬ ነው፣ ትንንሽ አሳቦችን አላስብም፣ ትልቅነት እድልፈንታዬ ነው፣ ትልቅ ነኝ አሳቤም ትልቅ ነው ምክኒያቱም አባቴ ትልቅ ነው🔥🔥🔥


ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
— መዝሙር 121፥2


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
  — ዮሐንስ 1፥5

ብርሃን በጨለማው ላይ በርቷል ጨለማም አላሸነፈውም አሁንም እየበራ ነው ወደፊትም በኃይል እየበራ ይቀጥላል ይህንን ብርሃን ጨለማ አያሸንፈውም።

#ይበራል የሚለው (Continues) ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚበራ ነው። ይህ ብርሃን በበጣይነት የሚበራው በእኛ በብርሃን ልጆች ነው ምክኒያቱም የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ብሎ ይናገራል።

#አላሸነፈውም የሚለው ደግሞ ያለፈ ወይንም (Past) የሆነ ነው። ጨለማ በብርሃን የተሸነፈው የዛሬ 2000 ዓመት በፊት ነው። ጨለማ Already በብርሃን ተሸንፏል።

ማቴዎስ 5
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ህይወት መብላት መጠጣት መራመድ መተንፈስ መኪና መንዳት ወዘተ ሳይሆን አካል ነው እርሱም #ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ የሌለበት ሁሉ ሞት ነው ምክኒያቱም ሕይወት ኢየሱስ ስለሆነ።

#ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን #ሕይወት እናወራላችኋለን፤
  — 1ኛ ዮሐንስ 1፥2


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔርን መፈለግና የእግዚአብሔርን መፈለግ ይለያያል።

በኢየሱስ ስም የእግዚአብሔርን ሳይሆን እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ይብዛላችሁ🔥🔥
🔥


እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
— 1 ዜና 16፥11

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ የዳነ ሰው የመንፈሳዊ ህይወት እድገቱ የሚለካው በሚናገረው የትንቢት ጥልቀት ወይ ደግሞ በሚገርም የስብከቱ ፀጋ ወይ ደግሞ በተለያየ የፀጋ ስጦታዎች መገለጡ ሳይሆን በህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባለው ህብረቱ በመንፈሱ በተካፈለው የእግዚአብሔርን ዘር በህይወቱ በፍሬ መገለጡ ነው።

መንፈሳችን ውስጥ የተካፈልነው የእግዚአብሔር ዘር አለ ይህ የእግዚአብሔር ዘር በህይወታችን እንዲገለጥ ከመንፈስ ቅዱስና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ህብረት በማድረግ የውስጡ ሰውነታችንን በኃይል በማጠንከር በመንፈሳችን የተካፈልነውን ዘር ወደ ፍሬ መግለጥ እንችላለን።

የመንፈሳዊ ህይወት እድገት የሚለካው በህይወታችን ፍረሆኖ በተገለጠው በእግዚአብሔር ዘር ነው።


በመንፈሳችን የተካፈልነውን የእግዚአብሔርን ዘር ወደ ፍሬ ስንቀይረው የዛኔ በመንፈሳዊ ህይወታችን እያደግን ነው ማለት ነው።

የእግዚአብሔርን ዘር የተካፍልነው በፍሬ እንድንገልጠው ነው።

የተካፈልነው የመለኮት ዘር በህይወታችን ሲገለጥ👇👇

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
— ገላትያ 5፥22


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#መስቀል ምንድነው..???

መስቀል እንጨቱ ሳይሆን ሰዎችን ከእግዚአብሔር የለየው ኃጢአት በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ሆኖ የተቀጣበት የእግዚአብሔር ጽድቅ ደግሞ ለሰው ልጆች በሙላት የተቆጠረበት ኃጢአትና ጽድቅ፣ ሞትና ሕይወት፣ እርግማንና በረከት፣ ጨለማና ብርሃን፣ በሽታና ጤንነት፣ ድህነትና ብልጥግና ቦታ የተቀያየሩበትና የመለኮት የማዳን ቀመር ነው።

መስቀል በየአመቱ እየተጠበቀ የሚከበር በኣል ሳይሆን የሰዎችን ኃጢአትና የኃጢአትን ውጤት እግዚአብሔር አብ በልጁ በኢየሱስ ላይ በማድረግና ልጁን በመቅጣት ለሰዎች ሁሉ የልጁን የኢየሱስን ጽድቅ የሰጠበት ቦታ ነው።

የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።
— ገላትያ 5፥24


መስቀል እኛ እና ኢየሱስ የተተካካንበት ቦታ ነው። ኢየሱስ እኛን ተክቶ በእንጨት ላይ የተረገመ ኃጢአተኛ ሆኖ ሲሰቀል እኛ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ የእግዚአብሔር ጽድቅ የተደረግንበት ነው።

መስቀል እኛ ለዓለም የተሰቀልንበት (ኃጢአታዊ ማንነታችን የተቸነከረበት) ዓለምም ለእኛ የተሰቀለበት (የዓለም የህይወት ስርአት በእኛ ህይወት ላይገለጥ የተወገደበት ቦታ እንጂ እንጨቱ አይደለም።

ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።
— ገላትያ 6፥14


መስቀል ኃጢአት የተገደለበት ቦታ ነው ኃጢአትን ደግሞ እንጨት ሊገድለው አይችልም ኃጢአትን ሊገድለው የሚችለው ጽድቅ ነው። ስለዚህ መስቀል እንጨቱ ሳይሆን ኃጢአት ተገድሎ የእግዚአብሔር ጽድቅ ህያው የሆነበት (የእግዚአብሔር ጽድቅ የነገሰበትና የገዛበት ቦታ ነው።)

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ይንበረከካሉ፥ ልጆቻቸውንም ይወልዳሉ፥ ከምጣቸውም ያርፋሉ።
— ኢዮብ 39፥3


ውስጣችሁ ያለውን መለኮታዊ ፅንስ የምትወልዱበትን ኃይልና አቅም (ፀጋ) ትቀበሉ ዘንድ በፀጋው ዙፋን ስር ተንበርከኩ።

ስትንበረከኩ ውስጣችሁ ያለውን መለኮታዊ ራዕይ አምጣችሁ የምትወልዱበትን መለኮታዊ ኃይል ከፀጋው ዙፋን ትቀበላላችሁ።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

👆እነዚህን 2 ትምህርቶች ስሟቸው አይን ከፋች ትምህርቶች ናቸው🔥🔥🔥

ደሞ ለወዳጆቻችሁ ሼር አድርጉ ወዳጆቼ❤️🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Part 1
🚨በአምሮ መንፈስ መታደስ💡🔥

እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ ትምህርት ነው ስሙትና ተቀጣጠሉበት🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#በዓለቱ ላይ ተተከሉ ስር ስደዱ በፍሬአችሁም ተገለጡ 🔥🔥

#ዓለቱ እርሱ በፍፁም እንዳንናወጥ የተተከልንበትና ስር የሰደድንበት የህይወት ምንጫችን ክርስቶስ ነው።

በህይወታችን ወደ ውጭ በፍሬ በሙላት ልንገለጥ የምንችለው ወደ ዓለቱ አጥልቀን በተተከልንበት ስር በሰደድንበት ልክ ነው።

ወዳጄ ልምላሜና ፍሬ እንዲህ በቀልዱ የሚገኝ ነገር ሳይሆን የህይወት ውሃ ምንጭ ወደ ሆነው ወደ ዓለቱ ስር ስንሰድና ስንተከል ነው።

ከልምላሜና በፍሬ ከመንዠርገግ በፊት በዓለቱ ውስጥ ስርን በመዘርጋት ስር መስደድ ይቀድማል።

በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።
— ኢሳይያስ 27፥6

ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፥ ወደ ላይም ያፈራል።
— 2ኛ ነገሥት 19፥30

ወዳጄ ኢየሱስ የጠራንና የሾመን ፍሬ እንድናፈራ ነው። በፍሬአችን ለመገለጥ ደግሞ በዓለቱ ውስጥ ስር መስደድ ይኖርብናል።

“...ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።”
— ዮሐንስ 15፥16

ሙሴ በምድረበዳ ከዓለቱ ለእስራኤላውያን ውሃ እንዳፈለቀ እኛም በዓለቱ ውስጥ በመተከልና ስራችንን በመስደድ የህይወትን ውሃ በመጠጣት በፍሬአችን ዓለምን መሸፈን ይኖርብናል ለዚህም ነገር ኢየሱስ ሾሞናል።


በፍሬ ስንገለጥ አብ በህይወታችን ይከብራል።

ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።
— ዮሐንስ 15፥8


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመንፈስ ቅዱስ ዋና ስራ ሙሽሪትን ከምድራዊ ህይወት በማላቀቅ በክብር ለሚገለጠው ሙሽራ ማስዋብና ማዘጋጀት ነው።

#መንፈስ_ቅዱስ_የህይወቴ_ውበት🔥❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሮሜ 8
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁵ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።

⁶ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዛሬ በስሙ ጠላቶቻችሁን ድል የምትነሱበት ቀን ነው🔥🔥🔥

መዝሙር 118
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁰ አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤

¹¹ መክበቡንስ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤

¹² ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንዲነድድ ነደዱ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰይጣን ውሸታም ነው።

Satan is a liar.

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈሳዊ ረሃባችሁ እጥፍ ሆኖ ሲመለስላችሁ ይታየኛል😭😭😭😭

መንፈሳዋ ረሃባችሁ ሲጨምር ይታየኛል😭😭😭😭😭😭

ረሃሃሃሃብብብብ😭😭😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የስላሴን ዓለም ወክሎ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሊኖር የፈሰሰው መኖሪያ ስላጣ ሳይሆን ከእኛ ጋር ዘላለማዊ የፍቅር ህብረት ሊመሰርት ነው።

ወዳጆቼ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ የሚኖረው የሰማይን ህይወት በምድር ላይ እውን ሊያደርግልን ነው።

#የአሳባችሁን_ዓለም ለመንፈስ ቅዱስ አስገዙለት እርሱ የራሱን የህይወት ስርአትና ዓለም በህይወታችሁ ይግለጠው🔥🔥🔥🔥

ሮሜ 8
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁵ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ
#መንፈስ_ፈቃድ የሚኖሩ ግን #የመንፈስን ነገር #ያስባሉ።

⁶ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ
#መንፈስ_ማሰብ ግን #ሕይወትና #ሰላም ነው።

#የአሳባችሁን_ዓለም ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ አድርጉት እንደ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ አስቡ🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እምነት ከመስማት ነው መስማትም ደግሞ ከእግዚአብሔር ቃል ነው።🔥

እምነት የሚባል ነገር ካለ መናገር አለ🔥

ያመናችሁትን ተናገሩት አውጁት🔥🔥

ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤
— 2ኛ ቆሮ 4፥13

የምናገረው ስሜቴን አይደለም
የምናገረው ምኞቴንም አይደለም
የምናገረው የሚታየውንና የሚሰማውን አይደለም
የምናገረው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለ እኔ የተፃፈውን ነው።

አምናለሁ ስለዚህም እናገራለሁ🔥🔥


“አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ፤....”
— መዝሙር 116፥10


ጻድቅ የሚኖረው በእንጀራ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ቃል በሚወጣው እምነት ነው ያመነውን እምነት ደግሞ ይናገረዋል ያውጀዋል በእምነት ቃል የተናገረውና ያወጀው ደግሞ በህይወቱ ፍሬ ሆኖ ይገለጣል🔥🔥

“ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።”
— ሮሜ 1፥17


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የሕይወትና የሞት ሽታዎች ነን።

ይህ በእኛ ላይ የሚሸተው ሽታ ደግሞ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

አንዱ ክርስቶስ ኢየሱስ ሕይወትም ሞትም ሆኖ በሕይወታችን ላይ በኃይል ይሸታል።

ጌታ ኢየሱስን በማመን ለሚቀበሉት ሁሉ የሕይወት ሽታ እንሆንላቸዋለን።

የጌታ የኢየሱስን ስራ እና አዳኝነት አምነው መቀበል ለማይፈልጉ የኢየሱስን አዳኝነትና ጌትነት አምነው መቀበል ለማይፈልጉ ሁሉ እኛ ለእነርሱ የሞት ሽታዎች ነን።

በምድር ላይ አመፅ ኃጢአትና ጨለማ እንዲበዛና ሰዎች ሁሉ ክርስቶስን ተረድተው በክርስቶስ እንዳያምኑ ተግቶ ለሚሰራው ለዲያብሎስ ለእርሱ እኛ የሞት ሽታዎች ነን።

የእግዚአብሔርን ሕይወት ለሚፈልጉ፤ ነፃነትን ለሚናፍቁ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለሚፈልጉ በፀጋ የሆነውን መዳን መቀበል ለሚፈልጉ እኛ ለእነርሱ የሕይወት ሽታዎች ነን።

2ኛ ቆሮ 2
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁵ በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤

¹⁶ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?


ሰዎች ሁሉ እንዲያሸቷችሁና ክርስቶስን እንዲያውቁ መአዛችሁ የሆነው ክርስቶስ በሕይወታችሁ በኃይል ይሽተትላችሁ🔥❤️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ረሃባችሁን እና ናፍቆታችሁን ጨምሩ መንፈስ ቅዱስ በኃይል ይጠቀምባቸዋል ሰማይ በምድር የሚገለጥበት መሳሪያ ትሁናላችሁ🔥🔥🔥😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እኔ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነኝ።

☝️በራሳችሁ ላይ በኃይል አውጁት🗣🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ጠላቶቻችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ ድብደባ ታዞባቸዋል እርሱም በከበሮ በማስንቆና በምስጋና ነው።🔥🔥🔥

እግዚአብሔር የሚያወርድባቸው የቅጣት በትር ሁሉ፣ በከበሮና በበገና ድምፅ የታጀበ ነው፤ በጦርነትም ክንዱን አሳይቶ መታቸው።
  — ኢሳይያስ 30፥32 (አዲሱ መ.ት)


ምስጋናችሁን ጨምሩ🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሮሜ 8
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
²⁹ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤

³⁰ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Part 2
🚨በአምሮ መንፈስ መታደስ🔥💡

ሁሉም ሰው መስማት ያለበት እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ አይን የሚከፍት ትምህርት ነው ሁላችሁም አሁን ስሙት🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#የእኛ በግ ከኃጢአት ሊያድነንና ከእግዚአብሔር ጋር ዘላለማዊ ህብረትን ሊሰጠን ስላልቻለ የዓለምን ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ #የእግዚአብሔር_በግ ተገለጠ እርሱም #ኢየሱስ ነው።

ኃጢአትን ማሸነፍ ከፈለጋችሁ
#የራሳችሁን_በግ ተውና #የእግዚአብሔርን_በግ ያዙ እርሱም #ኢየሱስ ነው።

በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት
#የሚያስወግድ #የእግዚአብሔር_በግ።
— ዮሐንስ 1፥29

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

👉ኢየሱስን መውደድ ትፈልጋለህ?
👉ኢየሱስን መምሰል ትፈልጋለህ?

1ኛ መንፈስ ቅዱስን የቅርብ ጓደኛ አድርገው።

2ኛ መንፈስ ቅዱስ ሲያወራ በደንብ ስማው
የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ያለው ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው ቃሉን አሰላስል የነፍስህ አደባባይ በቃሉ ትሞላ።

3ኛ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ ታዘዝ ፈቃድህን ለፍቃዱ ሰዋለት።

ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ #መንፈስ #ማሰብ ግን #ሕይወትና_ሰላም ነው።
— ሮሜ 8፥6

ስለ መንፈስ ቅዱስ ስታስቡ የነፍሳችሁን አሳብ መንፈስ ቅዱስ ሲቆጣጠርና ሲገዛ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስትውሉ የመንፈስ ቅዱስ የህይወት ስርአት በህይወታችሁ ያለማቋረጥ እንደ ወንዝ ይፈሳል። ኢየሱስ በሙላት በህይወታችሁ ይገለጣል ማለት ነው።


እመነኝ #ኢየሱስን በህይወትህ ህያው ሆኖ ሲንቀሳቀስና ሲሰራ ታየዋለህ

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ክርስትና ከሆነ ኃይማኖት ወደ ጴንጤነት የምንቀየርበት ሳይሆን ዘር የምንቀይርበት ነው።

ኢየሱስን በማመን ጴንጤነትን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ዘር ነው የተካፈልኩት።

ኢየሱስን በማመን ጴንጤ አይደለም የሆንኩት ጨለማውን የሚያሸንፍ ብርሃን ነው የሆንኩት።

Christianity is not a religion, it is a sharing of God's seed.


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መስቀል የአሮጌው ሰው(የአሮጌው አዳም) መጨረሻ ሲሆን

ትንሳኤ ደግሞ የአዲሱ ፍጥረት (የአዲሱ ሰው) መጀመሪያ ነው።

አሮጌው ሰው የተገደለው የተወገደው የተቀበረው ተጠርቆ የተሰቀለው በመስቀል ላይ ነው።

አሮጌው ሰው ስንል የአሮጌው የህይወት ስርአት እያልን ነው። የአሮጌው ሰው ህይወት ደግሞ ኃጢአትና የኃጢአት ውጤት ነው።

ስለዚህ በመስቀል ላይ ተጠርቆ የተሰቀለው ፣ የተወገደው ኃጢአትና የኃጢአት ውጤት ነው።

አዲስ ፍጥረት ነኝ ስል የትንሳኤ ልጅ ነኝ እያልኩኝ ነው።

አዲስ ፍጥረት ነኝ ስል የእግዚአብሔርን ዘር ተካፍያለሁ እያልኩኝ ነው።

አዲስ ፍጥረት ነኝ ስል የኃጢአት ተፈጥሮ የለብኝም እያልኩኝ ነው።

አዲስ ፍጥረት ነኝ ስል ኃጢአት አይገዛኝም እያልኩኝ ነው።

አዲስ ፍጥረት ነኝ ስል ኃጢአትና የኃጢአት ውጤቶች ሁሉ በእኔ ላይ ምንም ስልጣንና Ground የላቸውም እያልኩኝ ነው።

ምክኒያቱም የእግዚአብሔርን ዘር የተካፈልኩኝ አዲስ ፍጥረት ስለሆንኩኝ ነው።

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
— 2ኛ ቆሮ 5፥17


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዮሐንስ 6
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁴⁷ እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።
⁴⁸ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።

ይህንን የህይወት እንጀራ የበላች ነፍስ ታድላላላ😍😍😍😍

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አብ እኔን ገቢ ለማድረግ አንድያውን ኢየሱስን ወጪ ማድረግ ነበረበት ደግሞም አደረገው።

ወዶኝ ነው❤🙏

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመዝሙር ግብዣዬ😍
አገለግልሃለሁ😭😭😭

ጌታ አገልግለኝ ሲለኝ በዚህ ዝማሬ እንዲህ አልኩ😭😭😭😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…
Subscribe to a channel