binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

He is my king
His Name is Jesus Christ the Son of God.❤️

እሱ የኔ ንጉስ ነው።
ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ፀጋ ኃጢአተኛውን ማጽደቅ ብቻ ሳይሆን በጽድቅ የሚያኖር የመለኮት ብቃት ነው።

ፀጋው በእምነት አጽድቆናል
ፀጋው በእምነት ያፀናናል
ፀጋው በእምነት አድኖናል

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ተራ ሰው ነኝ አልጠቅምም አትበል ደም ከፍሎብሃል ገንዘቡ ነህ።

መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
— ቲቶ 2፥14


እግዚአብሔር የማይጠቅም ልጅ የለውም።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔርን የምንፈልግበት ጊዜው አሁን ነው😭😭😭

እግዚአብሔርን የምንፈልገው ጠፍቶብን ልናገኘው አይደለም ምክኒያቱም አንዴ በክርስቶስ ኢየሱስ እራሩ ፈልጎ አግኝቶናል።

እግዚአብሔርን የምንፈልገው እግዚአብሔር በህይወታችን ያለውን ዋጋ እየነገርነው ነው።

የሚፈለግ ነገር የጠፋ እና የሩቅ ነገር ነው እግዚአብሔር ግን ለእኛ አልጠፋብንም አልራቀንም እግዚአብሔር የቅርባችን እንደውም በውስጣይን ነው ነገር ግን እፈልግሃለሁ ስንለው በህይወታችን ያለውን ትልቅ ዋጋ እና ያለ እርሱ መኖር እንደማንችል ረሃባችንን ፍቅራችንን እየነገርነው ነው።

“እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤”
— ኢሳይያስ 55፥6

“እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።”
— መዝሙር 105፥4


መንፈስ ቅዱስ ሆይ እጅግ በጣም ታስፈልገናለህ❤️😭


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍርድ ማምለጣችሁ በፍፁም እንዳይቀልባችሁ....

👉ከመዳናችሁ ይበልጥ በሚገለጥባችሁ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ይበልጥ ከተገረማችሁ እጅግ በጣም ስህተት ላይ ናችሁ።

👉ከመዳናችሁ ይልቅ ለሚገለጥባችሁ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ አብልጣችሁ Value ከሰጣችሁ ትልቅ ስህተት ላይ ናችሁ...

👉ከዘላለማዊው ፍርድና ቁጣ በመዳናችሁ ካልተደሰታችሁና ካልተገረማችሁ፤ ካላመሰገናችሁ ምንም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በናንተ ላይ ቢገለጥ ልትደሰቱ አትችሉም።

በበደላችንና በኃጢአታችን ምክኒያት ሙታን በነበርን ጊዜ የአለም ቤዛ የሆነውን ኢየሱስን ወደ ህይወታችን ስናስገባ #ሁለት ታላላቅ ነገሮች በህይወታችን ሆነ...

1⃣ የነፍሳችንን እረኛ ወደ ህይወታችን በፈቃዳችን በማስገባታችን ነፍሳችንን ለሰይጣን ከተዘጋጀለት ከዘላለም ከገሃነም እሳት አስመለጥናት

👉ኢየሱስ ወደ ህይወታችን መድሃኒት ሆኖ ባይመጣ ኖሮ ማንም ከዚህ አስፈሪና ዘላለማዊ ሞት ሊያድነን አይችልም ነበር። ሲኦል ለዘላለም ከመኖር ባንፈጠር ይሻላል....

2⃣ ኢየሱስን ወደ ህይወታችን በማስገባታችን የሆነው ሌላኛው እጅግ ትልቁና ትልቁ ነገር በክርስቶስ ኢየሱስ ለዘላለም በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መሰወራችን ነው። ይሔ እጅግ በጣም እውነትና እውነት የሆነ ነገር ነው አዎ በክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ተሰውረናል በእግዚአብሔር ዘንድ በክርስቶስ ስፍራ አለን።

ከዘላለም ፍርድ ማምለጣችን አንዱ እጅግ የሚያስደንቅ ታምራትና የምናመሰግንበት ምክኒያት ቢሆንም እግዚአብሔር መልካምነቱን በዚህ አላቆመውም ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንድንናር በእርሱ ዘንድ በክርስቶስ በኩል ስፍራን ሰጠን ከእርሱም ጋር በሚያስገርም ብርሃኑና ክብሩ ውስጥ እያመለክነው ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንኖራለን

📌ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥9


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የከፉን ሆነ ክፉ የሚጠቀምባቸውን ድምፅ ሰምታችሁ ልባችሁ ለደነገጠና ተስፋ ለቆረጣችሁ ለእናንተ ዛሬ መልእክት አለኝ

የሰማችሁትን የክፉ ድምፅ የሚቆሪርጥና የሚሽር የእግዚአብሔር ኃያሉ ድምፅ በኢየሱስ ተገለጠበት🔥🔥🔥

የእግዚአብሔርን ድምፅ የሚቋቋም የጨለማ ድምፅ የለምና በኢየሱስ ስም የሚያሳርፈው የእግዚአብሔር ድምፅ በልባችሁ ገነት ላይ ይፍሰስ ጨለማ የሆነባችሁ ሁሉ ከኃያሉ ከእግዚአብሔር ድምፅ የተነሳ በብርሃን ተዋጠ በኢየሱስ ስም።

መዝሙር 29 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።

⁵ የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።


እነሆ፤ የውዴ ድምፅ በተራሮች ላይ እየዘለለ፣ በኰረብቶችም ላይ እየተወረወረ፣ ሲመጣ ይሰማኛል።
— መኃልየ. 2፥8 (አዲሱ መ.ት)


ድምፅ የሚሻረው በድምፅ ነው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Apostle Tamrat Tarekegn

History Maker🔥
Planet Shaker🔥
Atmosphere Changer🔥

አሁንም ትውልድ አለ የእግዚአብሔርን መንግስት በመንፈስ ቅዱስ የሚገልጥ የልጁን መልክ የሚያንፀባርቅ ሰማይን በምድር የሚያስተዋውቅ የክርስቶስ አምባሳደር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወንጌልን የሚገልጥ አሁንም ትውልድ አለ🔥🔥🔥🔥🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰው ስለኢየሱስ ሲያወራህ ይደክምሃል ይሰለችሃል።

መንፈስ ቅዱስ ግን ኢየሱስን ሲያወራህ ያስደንቅሃል ፍቅሩን ያስይዝሃል።

ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ሲያወራህ እንቅልፍህ ይመጣል መንፈስ ቅዱስ ግን ቃሉን ሲያወራህና ቃሉን ሲገልጥልህ አይኖችህን ይከፍተዋል።


ከመለኮት ጋር ያለንን ህብረት የወደድነው ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ ነው።

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
— ዮሐንስ 14፥26


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ያባቴ ብሩካን ዘላለማችንን የእረፍት ያደረገው ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ክርስትና ያለ ጥያቄ መኖር ሳይሆን በህልውናው መኖር ነው።

በህይወታችን ብዙ ያልገባንና ጥያቄ የሆነብን እልፍ ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላል ነገር ግን ኢየሱስ ከገባን በቂ ነው ህልውናው የጥያቂዎቻችን ሁሉ መልስ ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በጣም የሚያስፈልጋችሁ መዝሙር ነው።😍😭
#የልመናዬን ድምፅ 🎙
Pastor Yared Maru
መዝሙር ግብዣ
🎙
@Binarevivalist 🎙
🎙
@Binarevivalist 🎙
🎙@Binarevivalist 🎙

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢሳይያስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።

² የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።


ክርስቶስ የህይወታችሁ ራስ ነው እናንተ ደግሞ አካሉ ናችሁና የመንፈሱ ሙላት በህይወታችሁ በሙላት ይገለጥ🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ከእግዚአብሔር ጋር ቀጥሉ እንጂ ነገአችሁ የከፍታ፣ የብርሃን፣ የእግዚአብሔር ክብር በሙላት የሚገለጥበት ነው።

ለምን መሰላችሁ እነ ጴጥሮስ ሁሉን ጥለው ሲከተሉት ነገአቸውን ለኢየሱስ አስረክበውት ነው...ከኢየሱስ ጋር አየሄዳችሁ ከሆነ የውርደት ነገ ሳይሆን የክብር ነገ እየጠበቃችሁ ነው🔥❤️

አባቶቻችን ዛሬአቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው ነገአቸው የውርደት አልሆነም የክብር እንጂ እናንተም ዛሬአችሁ ለእግዚአብሔር ከሆነ ነገአችሁ የብዙ ክብር ነው🔥❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ፍቅር እንደዚህ ነው....

ፍቅር ብቁውን ወይንም ጻድቁን ሰው እወድሃለው የሚል የአንደበት ንግግር ሳይሆን ለኃጢአተኛው ሰው አንድያ የሚወደውን ልጁን እስከ ሞት አሳልፍ የሚሰጥ የእግዚአብሔር የልብ ቋንቋ ነው።

ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10


እግዚአብሔርን ጥላኝ ብትለው ሊጠላህ አይችልም ምክኒያቱም ከእግዚአብሔር ውስጥ ጥላቻን በፍጹም አታገኝም። ያለህ ነገር ሊያልቅብህ ይችላል እግዚአብሔር ግን የሚያልቅበት ፍቅር የለውም እራሱ ፍቅር ነው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መዝሙር 103 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤
³ ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣
⁴ ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣
⁵ ጐልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰይጣን ስለ እናንተ ተጨባጭና እውነት የሆነ ነገርን እኳን ቢያወራም ውሸታም ነው።

ከሰይጣን ማስረጃ የእግዚአብሔር እውቀት እውነት ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

Singer Bereket lemma
አንተን ባየ አይኔ

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ቲቶ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።

⁴ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥

⁵ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤

⁶-⁷ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመንፈስ ቅዱስ ተልእኮ የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስን ማድመቅ ነው።🔥❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወንጌል እግዚአብሔር ወደ ሰው ልጆች የፃፈው የፍቅር ደብዳቤ ነው❤😭

ወንጌልን ባገኛችሁት አጋጣሚ ለሰዎች ሁሉ ተናገሩ ፀጋው ይብዛላችኃል😭😭

ወንጌል😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንገዳችን🔥❤️

የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።
— ምሳሌ 4፥18 (አዲሱ መ.ት)

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእግዚአብሔር #ኃይል ያስፈልገናል።

እንደ
#ኃይሉ ሥራ እንደ ተሰጠኝም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ስጦታ መጠን #የወንጌል አገልጋይ ሆንሁለት።”
— ኤፌሶን 3፥7

#ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ #ኃይል_የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥12

እምነታችሁም
#በእግዚአብሔር_ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም #መንፈስንና_ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥4-5

“እርሱ ግን፣ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤
#ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው #በድካም ጊዜ ነውና” አለኝ። ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 12፥9 (አዲሱ መ.ት)


#ኃይልን_በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13

ጳውሎስ በምድር ላይ ለነበረው አገልግሎት ለእግዚአብሔር ኃይል በተደጋጋሚ እውቅና የሚሰጥና ያለ እግዚአብሔር ኃይል በራሱ ኃይል እንደሌለው አስረግጦ ተናግሯል።

ወዳጆቼ ሆይ ለእኛም በምድር ላይ ባለን አገልግሎትና የህይወት ጎዳናዎቻችን የሚያስፈልገን የእግዚአብሔር ኃይል ነው።

መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
#በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
— ዘካርያስ 4፥6

#በቀረውስ በጌታና #በኃይሉ ችሎት #የበረታችሁ ሁኑ።”
— ኤፌሶን 6፥10

የቃሉ ህይወትና መንፈስ ኃይሉን በህይወታችሁ ይግለጠው🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ራእይ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።

¹³ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።


¹⁷ መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የልብ አይኖቻችን በእግዚአብሔር ቃል ሲበሩ ለባዶነታችን ሙላትንና መትረፍረፍን እናገኛለን።

የነፍሳችን አቁማዳ ልትሞላና ልትረካ የምትችለው በቃሉ የልቦና አይኖቻችን ሲበሩ ነው።

እግዚአብሔርም
#ዓይንዋን_ከፈተላት፥ የውኃ ጕድጓድንም አየች፤ ሄዳም #አቁማዳውን_በውኃ ሞላች፥ ብላቴናውንም አጠጣች።
— ዘፍጥረት 21፥19

የነፍሳችንን አቁማዳ ሊሞላና ሊያረካት የሚችለው መኬና ቤት ዝና የሰዎች ክብርና አጀብታ ሳይሆን የልቦና አይኖቻችን በቃሉ ሲበሩና ከቃሉ ውስጥ ተአምራቱን ማየት ስንጀምር ብቻ ነው።

ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።
— መዝሙር 119፥18

የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
— መዝሙር 36፥9

የልቦና አይኖቻችሁ በኢየሱስ ስም ይከፈቱ🔥


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

👉ኢየሱስ ሊናገርህ ሲፈልግ አፉ መንፈስ ቅዱስ ነው።

👉ኢየሱስ ሊዳስስ ሲፈልግ እጁ መንፈስ ቅዱስ ነው።

👉ኢየሱስ ፍቅሩን ሊያስተምርህ ሲፈልግ አስተማሪው መንፈስ ቅዱስ ነው።

👉ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሳይደክምና ሳያረጅ በሙሉ ክብሩ በሙሉ ውበቱ በሙሉ ስልጣኑ በሙሉ ኃይሉ እየቀጠለ ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በአካላችሁ ላይ ስራ የሌለው ብልት እንደሌላችሁ ሁሉ በክርስቶስ አካል ላይም ስራ የሌለው ብልት (አማኝ) የለም።

በክርስቶስ አካል ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ብልቶች ሆናችሁ ተጠምቃችኋል።

የክርስቶስ አካል ብልቶች ከሆናችሁ እናንተ ብቻ የምትሰሩትና ራስ በሆነው በክርስቶስ አማካኝነት Function የምታደርጉት ስራ አላችሁ።


ምናልባት የሚገለጥባችሁ አሰራር ሊለያይ ይችላል እንጂ የሚሰራባችሁ መንፈስ ግን አንድ ነው።

👇👇👇👇👇👇
1ኛ ቆሮንቶስ 12 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ስጦታዎች ልዩ ልዩ ሲሆኑ፣ መንፈስ ግን አንድ ነው፤

⁵ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ሲሆን፣ ጌታ ግን አንድ ነው፤

⁶ አሠራርም ልዩ ልዩ ሲሆን፣ ሁሉን በሁሉ የሚሠራው ግን ያው አንዱ እግዚአብሔር ነው።

⁷ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው።

⁸ ለአንዱ በመንፈስ የጥበብን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የዕውቀትን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤

⁹ ለአንዱ በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ በዚያው በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታዎች ይሰጠዋል፤

¹⁰ ለአንዱ ታምራትን የማድረግ፣ ለሌላው ትንቢትን የመናገር፣ ለሌላው ደግሞ መናፍስትን የመለየት፣ ለአንዱ በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር፣ ለሌላው ደግሞ በልዩ ልዩ ልሳን የተነገረውን የመተርጐም ስጦታ ይሰጠዋል።

¹¹ እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰው እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ ይሰጠዋል።


¹² አካል ብዙ ብልቶች ቢኖሩትም አንድ አካል ነው፤ ነገር ግን ብልቶች ብዙ ቢሆኑም አካል አንድ ነው። ክርስቶስም እንደዚሁ ነው።

¹³ አይሁድ ወይም የግሪክ ሰዎች ብንሆን፣ ባሪያ ወይም ነጻ ሰዎች ብንሆን፣ እኛ ሁላችን አንድ አካል እንድንሆን በአንድ መንፈስ ተጠምቀናልና፤ ሁላችንም አንዱን መንፈስ እንድንጠጣ ተሰጥቶናል።


በአካሉ በክርስቶስ ላይ ስኬታማ ብልት መሆን የምንችለው በተደረግንበት ቦታ እና የተደረግነውን ነገር ስንኖርና ስንገልጥ ብቻ ነው። እጅ ከሆንን እንደ እጅ መንቀሳቀስ እግር ከሆንን እንደ እግር መንቀሳቀስ አይን ከሆንን እንደ አይን መንቀሳቀስ አፍ ከሆንን እንደ አፍ መንቀሳቀስ ጆሮ ከሆንን እንደ ጆሮ መንቀሳቀስ ስንችል አካሉ (ክርስቶስ) በሙላት ይገለጣል።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በህይወታችን ከሚያስፈልገን አንዱ የእግዚአብሔር እሳት ነው።

የእግዚአብሔር እሳት ሁለት ነገሮችን ይሰራል

አንደኛው ከእኛ ላይ ያልተገባውንና የሚያደክመንን፣ የሚያዝለንን፣ የሚጎትተንን ነገር ከህይወታችን ላይ በማራገፍ እንድንበላ አድርጎ የሚያበስለን የእግዚአብሔር እሳት ነው።

ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ
#የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
— ሮሜ 12፥11

ሁለተኛው ደግሞ ጠላታችንን ዲያቢሎስን እና ስራውን አመድ የሚያደርገው የእግዚአብሔር እሳት ነው።

በህይወታችን ሊጠፋ የሌለበት ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር እሳት ነው ጠላታችሁ ሊቋቋማችሁ የማይችለው የእግዚአብሔር እሳት ዘውትር በህይወታችሁ ሲነድ ነው🔥🔥

በኢየሱስ ስም የእግዚአብሔር እሳት በህይወታችሁ ይጨምር🔥🔥🔥

አምላክህ እግዚአብሔር
#የሚበላ_እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።
— ዘዳግም 4፥24


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በጌታ ወንድሞቼና እህቶቼ ሁላችሁን በጌታ ፍቅር እወዳችኋለሁ አከብራችኋለሁ እናንተ የጌታ ምርጦች ናችሁ❤️❤️🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

1ኛ ቆሮንቶስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?

¹⁷ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በዚህ ቀን ባረኳችሁ ✋✋

እግዚአብሔር እንጀራን ሳይሆን ምጣድን ይስጣችሁ መብላት ብቻ ሳይሆን ማብላት ይሁንላችሁ❤️❤️

Читать полностью…
Subscribe to a channel