binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

ተስፋችን ምኞት ሳይሆን ተጨባጭ ነው።
ኢየሱስ ሊወስደን ይመጣል
።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

👉መፃሕፍት ያመለከቱት
👉ነብያት የተነበዩት
👉መላእክት ያበሰሩት
👉ሐዋርያት የሰበኩት
👉አባቶች የተሰውለት

ከሰማይ ለሰው ልጆች የተላከው የምስራች ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ኢየሱስ የህይወት እንጀራ ነው።
ኢየሱስ የህይወት ውሃ ነው።
ኢየሱስ የኃጢአት መድሃኒት ነው።
በኢየሱስ የሚያምን የዘለአለም ህይወት አለው አያፍርም።

ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን #ከኃጢአታቸው_ያድናቸዋልና ስሙን #ኢየሱስ ትለዋለህ።
  — ማቴዎስ 1፥21

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈስ ቅዱስ የወረደው በሐዋርያት የ10 ቀን ፆም ፀሎት ሳይሆን ኢየሱስ ስለከበረ ነው።

ኢየሱስ በትንሳኤው ያልከፈተው ሰማይ የለም🔥❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ማርያምና ዮሴፍ መሲሁ ሲወለድ ስሙን እንኳን የማውጣት መብት አልነበራቸውም ምክኒያቱም ህፃኑ የማርያምና የዮሴፍ ፕሮግራም ሳይሆን የእግዚአብሔር የዘመናት ፕሮግራም ነው።

ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤
#ስሙንም #ኢየሱስ_ብለህ_ትጠራዋለህ፤ #ሕዝቡን_ከኀጢአታቸው_ያድናቸዋልና።
— ማቴዎስ 1፥21 (አዲሱ መ.ት)

ኢየሱስ በግሪኩ ሲሆን በእብራይስጡ ደግሞ ኢየሱ ነው። ትርጉሙም እግዚአብሔር ያድናል ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በበጎች በረት ህፃን ሲወለድ በቤተ መንግስት ዲያቢሎስ ደነገጠ....

የመሲሁ የኢየሱስ መወለድ ለእኛ የምስራች ቢሆንም ለዲያብሎስ ግን ትልቅ ድንጋጤ ነው።

ማቴዎስ 2
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹-² ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Âł
#ንጉሡ #ሄሮድስም ሰምቶ #ደነገጠ፥ #ኢየሩሳሌምም_ሁሉ #ከእርሱ_ጋር፤

ይህንን ቃል እንደ ቀላል እንዳታዩት የአንድ ህፃን ልጅ መወለድ በቤተ መንግስት ያለን ትልቅ ሀገር ገዢንና ህዝብን እንዴት ሊያስደነግጥ ቻለ??? ያ ብቻ አይደለም የዚህ ህፃን ልጅ መወለድ የብዞዎችን ህፃናት በሰይፍ ስለት ያስጨፈጨፈ እና ብዙ የእስራኤልን እናቶች ሃዘን ውስጥ የከተተ ነው።

መሲሁ ሲወለድ ብርሃንን አይቶ የተደሰተ ሰው ቢኖርም የደነገጠና የተቆጣም የጨለማው ዓለም አለ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#እርሱን_ስሙት....

የሚያሳርፍና የሚያረጋጋ እንዲሁም ሰላምን የሚሰጠው ድምፅ ወይም ንግግር የኢየሱስ ድምፅ ብቻ ነው።

እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤
#እርሱን_ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
— ማቴዎስ 17፥5

#የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።
— ምሳሌ 1፥33


የኢየሱስ ድምፅ ያሳርፋል ያረጋጋል።



@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ የመጣው ኃጢአተኞችን ሊያድን ነው ኃማኖት ግን ስራው ኃጢአተኞችን ከኢየሱስ ማራቅ ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈስ ቅዱስን የተቀበልነው ስለኢየሱስ መረጃ እንዲኖረን ሳይሆን የኢየሱስን ህይወት እየኖርን መግለጥ እንችል ዘንድ ነው። በኢየሱስ ስም በህይወታችሁ ላይ እርሱን ና ሀይሉን መግለጥ ይሁንላች።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወደፊት ሳይሆን ዛሬ በክርስቶስ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል ነኝ።

ምስጢሩ #በክርስቶስ ነው።❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“...አንተ ግን አንተ ነህ፥...”
— ዕብራውያን 1፥12

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ህግ ኃጢአትን እንድናውቅ ሲያስተምር ፀጋ ደግሞ እግዚአብሔርን እንድናውቅ ያስተምረናል።

“የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥56

ኤፌሶን 1
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁸ ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።

⁹ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤


የዳነው በፀጋ ነው
የቆምነው በፀጋ ነው
የምንኖረው በፀጋ ነው
የምንበረታው በፀጋ ነው
ህይወታችን በፀጋ ነው

አማኝ ከፀጋው ውጪ የሆነ ህይወት ሊኖር አይችልም፣ በፀጋው ጀምረናል በፀጋው እየቀጠልን ነው በፀጋው እንጨርሳለን።


ኤፌሶን 2
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁸
#ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤

⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወንጌላችን ገና ድል ያደርጋል 🔥🔥
ድንቅ መዝሙር

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢሳይያስ 26
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
³ በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።

⁴ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወንጌል ዘመናቸውን ጠቀለለው😭😭😭😭
አባት ሆይ ስለነዚህ አባት ድንቅ የወንጌል አርበኛ አመሰግንሃለሁ😭😭😭😭

አቤት የሚጠብቃቸው ክብርና አክሊል😭😭😭 ለእኛ ትልቅቅ ምሳሌ እና የወንጌል አርበኛ ናቸው😭😭😭😭

ቄስ ዶክተር በሊና ሳርካ ለወንጌል የከፈላችሁት ትልቅ ተጋድሎና ዋጋ እግዚአብሔርን ለማገልገል ሁሌ ብርታት ይሆነናል በእግዚአብሔር መንግስት እስከሰንገናኝ ትናፍቁናላችሁ😭😭😭😭

መሞትስ ካልቀር እንደእርሶ ነው😭😭😭😭😭


“የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”
  — መዝሙር 116፥15

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የሚቆሶቆስና የሚቀጣጠል እሳት እንጂ የሚመጣ እሳት የለም።

መንፈስ ቅዱስ በማንኛውም ሁኔታ ከእኛ ጋር በእኛ ውስጥ ነው። ዘውትር ልንቆሶቁሰው ልናቀጣጥለው ያስፈልጋል እንጂ እንደገና ናና ልንለው አይገባም ከእኛ ጋር በእኛ ውስጥ ለዘላለም ሊኖር ተሰጥቶናል።


ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት)
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁶ እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤

¹⁷ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ አብሮአችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ።


ቆስቁስት አቀጣጥሉት አትጠብቁት።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

♥#የኢየሱስ_ክርስቶስ_ክቡር_ደም♥
===============================

♥"የቀረበው መስዋዕት ዘላለማዊ ከሆነ የተቀበልናቸው በረከቶች ሁሉ ዘላለማዊ ናቸው" ዕብ 10:1-18♥

✍️በብሉይ ኪዳን ለ1500 አመታት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የእንስሳት ደም መስዋዕት ሆኖ ቢፈስም የአንድን ሰው ሀጥያት አንዴ ለዘለዓለም ማስወገድ ግን አልተቻላቸውም። የእግዚአብሔር አብንም የጽድቅ ጥያቄ ሊመልሱለትም ሆነ ደስ ሊያሰኙት አልተቻላቸውም።

ዕብራውያን 10 (Hebrews)
4፤ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና።......
6፤ በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ሰለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም።

✍️በአዲስ ኪዳን ግን በማያዳግም ሁኔታ አንዴ ለዘላለም መስዋዕት ሆኖ የቀረበው ክቡር ደም አለ እሱም የእግዚአብሔር በግ የሆነው የኢየሱስ ደም ነው ።
✍️የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እግዚአብሔርን ያስደሰተና በብሉይ ኪዳን መስዋዕቶች ያልተመለሰለትን የጽድቅ ጥያቄ የመለሰ አንዴ ለዘላለም የቀረበ ዘላለማዊ መስዋዕት ነው። ዕብ 10:1-

♥ ከዚህም የተነሳ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በማመናችን ምክንያት የተደረጉ እና የተቆጠሩልን በረከቶች ፦

📌 በደሙ አዲስ እና ዘላለማዊ ኪዳን ተገባልን ሉቃ 22:20, ዕብ 13:20
📌በደሙ የእድሜ ዘመን የሀጢአት ስርየት አግኝተናል ..ሮሜ 3፡25, ሮሜ 4:6-7
📌 በደሙ ከእግዚአብሔር ቁጣ ድነናል....ሮሜ 5፡8
📌 በደሙ ፀድቀናል....ሮሜ 5፡9
📌 በደሙ ቤዛነታችንን አግኝተናል.. .ኤፌ 1፡7, ቆላ 1፡14
📌በደሙ ሰላም አግኝተናል.. ....ቆላ 1፡19-20
📌 በደሙ ወደ አባት እና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አግኝተናል.... ኤፌ 2፡13 ,ዕብ 10፡19-20

📌 በደሙ ተቀድሰናል ዕብ10:10
📌 በደሙ የዘላለም ፍጹማን ሆነናል
ዕብ 10:14
📌በደሙ ከጥፋተኝነት , ከሚከስ አእምሮ ነፃ ወጥተናል..ዕብ 9፡13-14,
📌 በደሙ ከሀጥያት ሁሉ ታጥበናል
ዮሐ 1:7
📌በደሙ ታጥበናል....ራዕ 1፡4-5
📌በደሙ ካህናት እና ነገስታት ተደርገናል
ራዕ 1:4-5,5:10
📌በደሙ = ከነገድ(ከዘር) ሁሉ
= ከቋንቋ ሁሉ
= ከወገን ሁሉ
= ከሕዝብ ሁሉ ተዋጅተናል
ራዕ 5:10

👉 የቀረበው መስዋዕት ዘላለማዊ ስለሆነ የተቆጠሩልን በረከቶቻችን ሁሉ ዘላለማዊ ናቸው።

✍️ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5 :8

📌 2 ቆሮንቶስ 13
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ጠላቴ እልል አይልብኝምና ስለዚህ እንደ ወደድኸኝ አወቅሁ።
— መዝሙር 41፥11

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

❤️ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ❤️

በእኔ ዘንድ ያለ😭😭😭
ይህንን ድንቅ መዝሙር ጋበዝኳችሁ😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?
— ሮሜ 8፥33

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

👉ትኩረትህ አብረሃም ላይ ከሆን አብረሃም የሳተበትን ስተት ትስታለህ።
👉ትኩረትህ ይስሃቅ ላይ ከሆነ ይስሃቅ የሳተበትን ስህተት ትስታለህ።
👉ትኩረትህ ሙሴ ላይ ከሆነ ሙሴ የሳተበትን ስህተት ትስታለህ።
👉ትኩረትህ ኢያሱ ላይና ሌሎች ሁሉም የእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ከሆነ እነርሱ የሳቱበትን ስህተት ትስታለህ።

👉በየዘመናቱ የተነሱ ሁሉም የእግዚአብሔር ሰዎች የራሳቸው ድካም አለባቸው ነገርግን ከኃጢአት በስተቀር ነገር ሁሉ የተፈተነው ነገር ግን እያንዳንዱን ፈተና በብቃት ያለፈ አንድ ታላቅ ሊቀ ካህን አለ እርሱም የእምነታችን ራስና ፈፃሚ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

📌ኢየሱስን እያያችሁ ልትደክሙ አትችሉም።
📌ኢየሱስን እያያችሁ በውድቀታችሁ ልትቀሩ አትችሉም።
📌ኢየሱስን እያያችሁ ተስፋ ልትቆርጡ አትችሉም።

✍ወዳጆቼ ሆይ እናንተ ለሰማይ ርስት የተጠራችሁና የተመረጣችሁ ደግሞም የሰማይ ተጓዦች ናችሁ በጉዞዋችሁ ደክማችሁ ከመንገድ እንዳትቀሩ ሊቀ ካህናችሁን የእምነታችሁን ጀማሪና ፈፃሚ እርሱን ኢየሱስን ብቻ ተመልክታችሁ በፅናት ጉዞአችሁን ቀጥሉ።

እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
— ዕብራውያን 12፥1-2

ግባችን ከክርስቶስ ጋር ለዘላለም አብሮ መኖር ነው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰላም ሰላም✋ ሃያላን አርብ ማለትም በ21/4/2015 መንፈስ ቅዱስ በሚል ርዕስ ተከታታይ ትምህርት እንጀምራለን🔥
ስለዚ ተዘጋጁ🔥 ለሌሎችም ልጆች share አርጉ🙏✋✋
👉መንፈስ ቅዱስ በሚለዉ ትምህርት የምናነሳቸዉ ነጥቦች
- የመንፈስ ቅዱስ ማንነት በዚህ ርዕሰ ዉስጥ ስለፀባዩ፣ ስለ ስራዉ.............እንመለከታለን
-ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ለምሳሌ
ሰለልሳን፣ስለ ትንቢት፣................ሰለ 9ኙም የፀጋ ስጦታዎች እናያለን
-ስለ መንፈስ አለም ለምሳሌ
ስለ መላዕክት አለም
ስለ አጋንንት አለም.............በሰፊዉ እናያለን
- የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ አላማዉ አንድ ነዉ አለማትን በክርስቶስ መጠቅለል በመጨረሻም ስለ ወንጌል ስርጭት ወንጌልን እንዴት እንስበክ
የሚሉና የተለያዩ ወንጌል በተመለከተ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን በመመለስ መንፈስ ቅዱስ የሚለዉን ተከታታይ ትምህርት እንጨርሳለን✋
👉ሌሎችም እንዲጠቀሙ ሼር አድርጉ እወዳችኋለሁ ሀሳብ ካላችሁ inbox አድርጉልኝ ተባርካችኋል✋✋✋✋
/channel/soliderhenok
/channel/soliderhenok
/channel/soliderhenok

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር በእያንዳዱ የታሪኮችና ዘመናት ውስጥ ያተኮረው (ያፈጠጠው) በልጁ በኢየሱስ ላይ ነው።

ትኩረታችሁ እግዚአብሔር በኢየሱስ ላይ ብቻ ይሁን።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

1ኛ ቆሮንቶስ 1
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁷ እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤

⁸ እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።

⁹ ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

. ደስ ደስ እያለኝ ነው
አቤኔዘር ፍቅሩ
- New Clip

@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል #ሕይወትንና_አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥10-11

በጌታ በኢየሱስ በማመን ብቻ የማይጠፋ ህይወትን ተቀብለናል።


ህይወት ማለት በዚህ ምድር ላይ በምድር ላይ እየኖርነው ያለነው ህይወት አይደለም ምክኒያቱ የዚህ ምድር ህይወት የሚጠፋና ማብቂያ ያለው ህይወት ነው።

የዘለአለም ህይወት ግን የእግዚአብሔር ህንወት ነው። ታድያ እኛ ኢየሱስን በማመን የተቀበልነው ህይወት የማይጠፋ ህይወት ነው።

ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር
#አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል #ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥23


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#በክርስቶስ የእግዚአብሄር ጽድቅ ተደርገናል።

በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ ለአማኞች ከተፈጸሙላቸት ድንቅ የእግዚአብሔር ስራዎች መካከል አንዱ በክርስቶስ በማመናቸው ብቻ የእግዚአብሔር ጽድቅ መደረጋቸው ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ መታዘዝና የቤዛነት ስራ ያመኑ ቅዱሳን ሁሉ ጽድቃቸው ከክርስቶስ ጽድቅ ጋር የሚተካከል እንሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስተምራል። ቅዱሳን ሁሉ በዚህ እውነት ላይ ተመስርተውና ተደላድለው ሊመላለሱ ይገባቸዋል።

2
#ቆሮንቶስ 5፡21
#እኛ_በእርሱ_ሆነን_የእግዚአብሔር_ጽድቅ_እንሆን_ዘንድ_ኃጢአት_ያላወቀውን_እርሱን_ስለ_እኛ_ኃጢአት #አደረገው።

አዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ
#ተደርጋችኋል እና #አደረጋቸው የሚሉ ቃላቶች ትልቅ ትርጉም የያዙ ናቸው። የጸጋ አለም ውስጥ እግዚአብሔር አድራጊ ነው እኛ ደግሞ ተደራጊ ነን፣ እግዚአብሔር ሰጪ ነው እኛ ተቀባይ ነን።

ከዚህም የተነሳ ኃጥያተኛ ሰው በመልካም ስራውና ሐይማኖታዊ ስርአትን በመፈጸም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን ማግኘት ስለማይችል እግዚአብሔር ግን ሀጥያተኛው ሰው በክርስቶስ የቤዛነት ስራ በማመኑ ብቻ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደተደረገ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ።

2
#ቆሮንቶስ 5፡21
#እኛ_በእርሱ_ሆነን_የእግዚአብሔር_ጽድቅ_እንሆን_ዘንድ_ኃጢአት_ያላወቀውን_እርሱን_ስለ_እኛ_ኃጢአት #አደረገው።

በዚህ ጥቅስ የምንመለከተው ኢየሱስ ሃጢያት የተደረገው የሃጥያት ተፈጥሮ ኖሮትና ሃጥያት ስለሰራ ሳይሆን እግዚአብሔር ኢየሱስን በእኛ ቦታ ሃጥያት ስላደረገው ነው። ኢየሱስ በራሱ ሃጥያት መሆን ስለማይችል እግዚአብሔር ሃጥያት እንዳደረገው እንዲሁ ፦
እኛም በራሳችን መልካም ስራ የእግዚአብሔር ጽድቅ መሆን ስለማንችል እግዚአብሔር ግን በክርስቶስ ቦታ የራሱ ጽድቅ አደረገን።

✍️ኤፌሶን 1
6፤ በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የፈለከውን ስም ጥራ ማንም ምንም አይልህም።
ኢየሱስን ግን ስትጥራው የሰዎች ፊት መርዘም ይጀምራል።

የትኛውም አካል ስም ልዩነትን ተፅእናን ማምጣት አይችልም።

በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ፍጥረት ሁሉ የሚሰማውና የሚታዘዝለት ግን አንድ ስም አለ እሱም ኢየሱስ ይባላል።

ኢየሱስ የሚለው ስም ለሹክሹክታ እንኳን የሚከብድ ስም ነው።


ኢየሱስ🔥❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ የህይወት እንጀራ ነው።
ኢየሱስ የህይወት ውሃ ነው።

ህይወት ይህንን ሰማያዊ መብልና መጠጥ ካላገኘች ሟች ናት።

ያለ ኢየሱስ ህይወት ፈፅሞ የለም።

ዮሐንስ 6
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁴⁷ እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።
⁴⁸ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።

ኢየሱስ❤️❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመዳናችን ማረጋገጫው የመንፈስ ቅዱስ ማህተም ነው።

ኤፌሶን 1
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹¹ እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።

¹² ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።

¹³ እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤

¹⁴ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።


ንብረትነታችን የእግዚአብሔር ነው ምክኒያቱም በኢየሱስ በማመን በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

"The age of miracles has not past. The miracle worker is still ALIVE. His name is Jesus Christ!" - Prophet T.B. Joshua

"የተአምራት ዘመን አላለፈም ተአምረኛው አሁንም ሕያው ነው ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!"
- ነብይ ቲ.ቢ. ኢያሱ

Читать полностью…
Subscribe to a channel