binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ😭😭😭😭😭

እስቲ ስለ ኢየሱስ የሆነ ነገር ፃፍ የተነካችሁበትን🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ ክርርቶስ የኀጢአታችንን ዋጋ ሊከፍል ሞተ፣ እኛን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብ ከሞት ተነሳ።

እርሱ ስለ ኀጢአታችን እንዲሞት ዐልፎ ተሰጠ፤ እኛን ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብም ከሞት ተነሣ።
— ሮሜ 4፥25 (አዲሱ መ.ት)


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ቁስል እንዴት ይፈውሳል??

ቁስል ፍውስ ነው እንጂ የሚያስፈልገው እንዴት ሊፈውስ ይችላል??

ወዳጄ ቁስል በእኛ ቀመር መድሃኒትና ፈውስ ነው የሚያስፈልገው ነገር ግን በእግዚአብሔር ቀመር ቁስሉ እኛን ከኃጢአት ካንሰር የሚፈውስበት መድሃኒት ነው።

የተቦጨቀው ስጋው ነው እኛን ከእርግማን የፈወሰን

እንደ ጅረት የፈሰሰው ደም ነው እኛን ከኃጢአት በሽታ የፈወሰን

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24

የእግዚአብሔር የማዳን ኃይልና ጥበብ በኢየሱስ በመገረፉ ቁስል ውስጥ ነው።

ቁስሉ ፈውሶኞል🥺🥺😭😭😭


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የፀጋው ባለጠግነት ወይም የፀጋው ብዛት የተገለጠው በበደልና በኃጢአት ምክኒያት ሙታን የነበርኩትን (ከእግዚአብሔር ህይወት የተለየሁትን) ህይወት በመስጠት በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊው ስፍራ ከእርሱ ጋር ሲያስቀምጠኝ ነው።

የፀጋው ባለጠግነት ኃጢአተኛውን ከሲኦል ጥልቀት በማውጣት እርሱ ራሱ በሚኖርበት የህይወት ከፍታ ላይ ከእርሱ ጋረሰ ያስቀምጣል።


በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት #ከሁሉ #የሚበልጠውን #የጸጋውን #ባለ_ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ #ከእርሱ ጋር #አስነሣን #በክርስቶስ_ኢየሱስም #በሰማያዊ ስፍራ #ከእርሱ ጋር #አስቀመጠን።
— ኤፌሶን 2፥6-7


የፀጋው ባለጠግነት አይመረመርም❤️❤️❤️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ይህንን ድንቅ ትምህርት ሁሉም ሰው መስማት አለበት😭😭😭😭

በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን
#የጸጋውን_ባለ_ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።
— ኤፌሶን 2፥6-7


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር ብርሃን ነው የሁሉም ሰው ዕውቀት ነው።እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው የግል መገለጥ ነው።እግዚአብሔር ብርሃን እንደሆነ ማንም ሰው ያውቃል።እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው ለማለት ግን ከእግዚአብሔር ጋር personal intimacy ይጠይቃል።

ዳዊት ያለውን ተመልከቱ እግዚአብሔር ብርሃን ነው አይደለም ያለው ወይም እግዚአብሔር መድሃኒት ነው አይደለም ያለው።ዳዊት ያለው እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው አለ?ስለዚህ ማንም ሰው እግዚአብሔር ብርሃን እና መድኃኒት እንድሆነ ጠቅላላ ዕውቀት ሊኖረው ይችላል ነገር ግን "ብርሃኔ ነው" ወይም "መድኃኒቴ ነው"ለማለት ነፍሱ በመገለጥ ብርሃኑን ልታገኝ መድኃኒነቱን ልትቀምስ ይገባል።


📜“እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?”
  — መዝሙር 27፥1

ከዚህ ቀን ጀምሮ በጌታ በኢየሱስ ስም እግዚአብሔር ብርሃን ነው መድኃኒት ነው ከሚል ያለፈ ህይወት አድርጎ የሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ያግኛችሁ።

Emmanuel...እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ግሪክ፡ χάρις
በቋንቋ ፊደል ሲጻፍ: charis
አጠራር: khar'-ece

English- Grace

Translation: acceptable, benefit, favour, gift, grace(- ious), joy, liberality, pleasure


አማርኛው -ጸጋ

ትርጉም፡- ተቀባይነት ያለው፣ ጥቅም፣ ሞገስ፣ ስጦታ፣ ደስታ፣ ነፃነት፣ ደስታ


ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት)
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁶ ከእርሱ ሙላት ሁላችንም
#በጸጋ ላይ #ጸጋ_ተቀብለናል፤
¹⁷ ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤
#ጸጋና እውነት ግን #በኢየሱስ_ክርስቶስ #በኩል #መጣ።❤❤❤

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የሚታየው ጊዜያዊ ነው። ፦ የምድር ኑሮ ቆይታችን በጊዜ የተገደበ ነው።

የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው። ፦ በስጋ ሞት ቡኃላ ያው ህይወት ዘላለማዊ ወይንም ጊዜ የሌለበት አለም ነው።

የተወደዳችሁ የምድር ቆይታችሁ በጊዜ የተገደበ ነው ጊዜአችሁን ስትጨርሱ በጌዜ ውስጥ ወደ ማትኖሩበት ዓለም ለዘለዓለም ወደምትኖሩበት ዓለም ትሻገራላችሁ በምድር ቆይታችሁ ኢየሱስ የህይወታችሁ ብቸኛ አዳኝና ተስፋ ከሆነ ኢየሱስ እንዳለው እኔ ትንሳኤና ህይወት ነኝ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳን ህያው ይሆናል እንዳለው የሚጠብቃችሁ ዓለም የእግዚአብሔር ዘላለማዊው መንግስት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለአለም በብርሃን ትኖራላችሁ። ነገር ግን የህይወት እንጀራ የሆነው ኢየሱስ በህይወታችሁ ከሌለ ፍፃሜአችሁ ለዘለአለም ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ በጨለማ እና በእሳት ውስጥ መኖር ነው የሚሆንባችሁ እና አሁን ከሚታየው ጊዜአዊው አለም ላይ አይናይሁን በማንሳት ለዘለአለም በእግዚአብሔር መንግስት ከእግዚአብሔር ጋር የምትኖሩበትን የህይወት ዋስትና ክርስቶስን ወደ ህይወታችሁ አስገቡ ኢየሱስ የሃጢአታችሁን ዋጋ ፈፅሞ ከፍሎታል።


ሼር በማድረግ ትውልድን ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንጥራ

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዘራችን ከላይ ስለሆነ ህይወታችንም ወደላይና ወደፊት ብቻ ነው😁

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መቼም የማታፍሩበትና የማትጸጸቱበት የህይወታችሁ ድንቅ ውሳኔ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ህይወቻችሁ እንዲገባ የወሰናችሁት ውሳኔ ነው።

በኢየሱስ የሚያምን አያፍርም።

መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
— ሮሜ 10፥11

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዮሐንስ 6
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
²⁷ ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።
²⁸ እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት።
²⁹ ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ
#በላከው #እንድታምኑ ነው አላቸው።

…
³³ የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው።
³⁴ ስለዚህ፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን አሉት።
³⁵ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦
#የሕይወት_እንጀራ #እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ #አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ #አይጠማም።

…
³⁷ አብ
#የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ #ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤
³⁸ ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።
³⁚
#ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው።
⁴⁰ ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
⁴¹ እንግዲህ አይሁድ፦ ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ ስላለ ስለ እርሱ አንጐራጐሩና፦
⁴² አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ፦ ከሰማይ ወርጃለሁ እንዴት ይላል? አሉ።
⁴³ ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፦ እርስ በርሳችሁ አታንጐራጕሩ።
⁴⁴ የላከኝ አብ
#ከሳበው በቀር ወደ እኔ #ሊመጣ #የሚችል_የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን #አስነሣዋለሁ።

…
⁴⁷ እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን
#የዘላለም_ሕይወት አለው።
⁴⁸
#የሕይወት_እንጀራ #እኔ ነኝ።

…
⁵⁰ ሰው ከእርሱ
#በልቶ_እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው።
⁵¹ ከሰማይ የወረደ
#ሕያው_እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ #ሥጋዬ ነው።

…
⁵³ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥
#የሰውን ልጅ #ሥጋ ካልበላችሁ #ደሙንም ካልጠጣችሁ #በራሳችሁ ሕይወት #የላችሁም።
⁾⁴
#ሥጋዬን_የሚበላ #ደሜንም_የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
⁵⁵ ሥጋዬ
#እውነተኛ መብል ደሜም #እውነተኛ መጠጥ ነውና።
⁵⁶ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ
#በእኔ_ይኖራል እኔም #በእርሱ እኖራለሁ።
⁵⁷ ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ
#የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።

…
⁶⁰ ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ፦ ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ።
⁶¹ ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያሰናክላችኋልን?

…
⁶³ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።

…
⁶⁵ ደግሞ፦ ስለዚህ አልኋችሁ፥
#ከአብ #የተሰጠው ካልሆነ ወደ #እኔ_ሊመጣ የሚችል #የለም አለ።
⁶⁶ ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች
#ወደ _ኋላ #ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር #አልሄዱም።
⁶⁷ ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ፦ እናንተ ደግሞ
#ልትሄዱ_ትወዳላችሁን? አለ።
⁶⁸ ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥
#ወደ ማን #እንሄዳለን? አንተ #የዘላለም_ሕይወት ቃል አለህ፤
⁶⁹ እኛስ አንተ
#ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር #ልጅ እንደ ሆንህ #አምነናል #አውቀናልም ብሎ መለሰለት።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ራእይ 1
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁴-⁵ ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥

⁶ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።

⁷ እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ለዘመናት የተነሱ ነብያት የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነበሩ እንጂ የእግዚአብሔር መልእክት አልነበሩም።

ኢየሱስ ክርስቶስ የዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔር የመጨረሻ መልእክተኛ እና የእግዚአብሔር የመጨረሻ መልእክት ነው።

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን አሳብና ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ጨርሷል።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

♥️♥️♥️ እየሱስ ♥️♥️♥️

☑️የተወለደው...........................ለኔ (ኢሳ 9፥6)
☑️የኖረው.................................ለኔ
☑️ሁሉን የታገሰው......................ለኔ (ኢሳ 53)
☑️ገዢ ለሻጭ እንደሚገምት በግ ዝም ያለው.....ለኔ
☑️ሲሳለቁበት አፉን ያልከፈተው...........ለኔ
☑️ጥርሱን ነክሶ የተሰቃየው.................ለኔ
☑️ሐጢአትና እርግማን የሆነው.............ለኔ (ገላ 3፥13)
☑️የሞተው………………………......…………ለኔ
☑️ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው.......ለኔ (1ቆሮ 15፥17)
☑️ወደ ሰማይ ያረገው................ለኔ (ዮሐ 14፥2)
☑️በአብ ፊት የሚታየው..............ለኔ
☑️ተመልሶ የሚመጣው.............ለኔ

የኔ የሚለው ሕይወት እስከማይኖረው ድረስ እንዲህ የሚሆንልኝ ስለወደደኝ ብቻ ነው።
እኔ እሱን ስለወደድኩት ሳይሆን እርሱ ስለወደደኝ አዳነኝ።

ኢየሱስ የተወለደው በምክኒያት ነው።
ይሀንን አስቡ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

✍የምንኖረው በወደቀው አለም ውስጥ ነው አማኝ ሁሉ የመንፈስ መዳን ሆኖለታል የነፍሱ መዳን ግን እለት እለት ከጌታ ጋር ባለው ህብረት ይፈፀማል ስጋው ደግሞ በትንሳኤ ቀን በማይበሰብሰው ሰማያዊ ስጋ ይቀየራል ይህ ስጋችን አሁን ኃጢአተኛ ስለሆነ ሁሌ ኃጢአትን ነው የሚመኘው ስለዚህ በዚህ ሂደት ውስጥ ብዙ ድካም ሊኖር ይችላል ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር በቀረብንና ራሳችንን ለፀጋው ባስገዛን ቁጥር ክርስትና እኛ የምንኖረው ሳይሆን ክርስቶስ በእኛ የሚኖረው ይሆናል።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በዚህ መዝሙር ስሙን እየጠራችሁ ባርኩት🔥🔥😭😭😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤
— ዕብራውያን 4፥12

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ወንጌልን ሰብኬ አልጠግብም ፣ወንጌልን ሰብኬ አልረካም፣ ገና ኢየሱስን ለመናገር አንደበቴን ውስጤ መላወስ ይጀምራል አንደበቴ በፀጋው ቃል ይከፈታል ገና ስሙን መጥራት ስጀምር ፍቅሩ በልቤ እንደ ጅረት ይፈሳል ብሰብከው ብሰብከው አልረካም አልጠግብም🔥🔥🔥🔥🔥😭😭😭😭

አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ።
  — ፊልጵስዩስ 3፥12


አንደበቴን በፀጋህ ቃል ሞልተሃልና አመሰግንሃለሁ😭😭😭😭❤️❤️❤️❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ጻፍከኝ በህይወት መዝገብ ጻፍከኝ
ጻፍከኝ በህይወት መዝገብ ጻፍከኝ🥹🥹🥹🥹

ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።
— ሉቃስ 10፥20

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

መንፈስ ቅዱስ የደስታችን ምንጭ ነው😁😂

መዝሙር 46
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁴ የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ
#ደስ ያሰኛሉ፤ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።

⁵ እግዚአብሔር
#በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ #ይረዳታል።❤❤❤

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የክርስቶስ ጸጋ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባል እንጂ ወደ ኃጢአት አያቀርብም።

ወደ እግዚአብሔር ስትቀርቡ ደሞ ከኃጢአት ትርቃላችሁ።

ጸጋ ከኃጢአት የሚያርቅ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ የመለኮት ብቃት ነው።

ቲቶ 2
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤

¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤


በህይወታችሁ የክርስቶስ ጸጋ ይትረፍረፍላችሁ❤️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ልባችሁን የሚያነቃ ድምፅ ይምጣላችሁ!

“እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል...።” መኃልየ. 5፥2

👉ውስጠኛው ማንነታችሁ ከተኛ ነገራችሁ እንደ ተነገራችሁ የተስፋ ቃል መንቀሳቀስ አይችልም።
👉ልቡ የነቃ ሰው ተቀምጦም ተኝቶም እየሰራም፣ እየተንቀሳቀሰም ቢሆን ሰማያዊ የሆነ ድምፅና ራዕይን ይቀበላል።
👉የሰው መንፈሳዊ ሕይወት ለውጥ የሚጀምረው በመንቃት ውስጥ ነው።

“በዚያ ጊዜ ዔሊ ሳሙኤልን፣ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ስለዚህም ሳሙኤል ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።”— 1ኛ ሳሙኤል 3፥9


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አይዟችሁ አትፍሩት ዘሩ እና ጅማሬው ከታች ስለሆነ ህይወቱም ወደታች ነው😁😁

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመዝሙር ግብዣዬ😂😁
ዘራችን ከላይ ሰለሆነ ህይወታችንም ወደላይና ወደፊት ብቻ ነው😁

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ ክርስቶስ የሌለበት ህይወት ሲኦል ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ በሄድክበት መንገድ እሄዳለሁ
ቢመችም ባይመችም በወንጌል ፀናለሁ
  እግሮቼ እንደዋላ ከፍታውን ረግጠው
  ምፅአትህን ልጠብቅ ነው የምናፍቀው(×2)
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
እንዳልዝል እንዳልወድቅ እርዳኝ ጌታ
ዛሬም በመንፈስ አበርታኝ አትራቀኝ ላፍታ
   አትራቀኝ ላፍታ ጌታ አትራቀኝ ላፍታ😭😭
   አትራቀኝ ላፍታ ኢየሱስ አትራቀኝ ላፍታ😭

ከፊት ለፊት ሮጬ ዛሬን እንደታየው
መንፈስህ እረድቶኝ እንደበረታሁኝ
   የንስር ክንፍ ስጠኝ ከፍታውን ልውጣ
   በአገልግሎት ልትጋ አንተ እስክትመጣ(×2)

እንዳልዝል እንዳልወድቅ እርዳኝ ጌታ
ዛሬም በመንፈስ አበርታኝ አትራቀኝ ላፍታ
   አትራቀኝ ላፍታ ጌታ አትራቀኝ ላፍታ😭😭
   አትራቀኝ ላፍታ ኢየሱስ አትራቀኝ ላፍታ😭

በመከራም ቢሆን በስቃይ በጣር
ማለፍ የሚያስችለው ፀጋና ክብር
   በዚህ በሸክላ ውስጥ ባለው መዝገብህ
   ይገለጥ ጌታ ሆይ ሃይልህ ማዳንህ(×2)

እንዳልዝል እንዳልወድቅ እርዳኝ ጌታ
ዛሬም በመንፈስ አበርታኝ አትራቀኝ ላፍታ
   አትራቀኝ ላፍታ ጌታ አትራቀኝ ላፍታ😭😭
   አትራቀኝ ላፍታ ኢየሱስ አትራቀኝ ላፍታ😭

ከጎኔ ሁን የኔ ጌታ ከጎኔ ሁን የኔ ጌታ
አቁመኝ አፅናኝ በቤት እርቄ እንዳልሄድ ከፊትህ❤️❤️❤️😭😭😭😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ለዘመናት የተነሱ ነብያት የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነበሩ እንጂ የእግዚአብሔር መልእክት አልነበሩም።

ኢየሱስ ክርስቶስ የዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔር የመጨረሻ መልእክተኛ እና የመጨረሻ መልእክት ነው።

ይህ መልእክተኛ በዘመን መጨረሻ ሲገለጥ እንደ ሌሎቹ ነብያትና መልእክተኞች መልእክትን ይዞ ሳይሆን እራሱ የእግዚአብሔር የመጨረሻ መልእክት ሆኖ ነው የተገለጠው።

እግዚአብሔር ከዚህ መልእክተኛና መልእክት የሚበልጥና የተሻለ ሌላ የለውም የተሻለውንና የሚበልጠውን መልእክትና መልእክተኛ ወደ ሰው ልጆች ገልጦ ጨርሷል።

የእግዚአብሔር ፍቅር ኢየሱስን ያክላል።
የእግዚአብሔር ጥበብ ኢየሱስን ያክላል።
የእግዚአብሔር ሃይል ኢየሱስን ያክላል።

ታዲያ እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን ፍቅር የማዳን ጥበብና የማዳን ሃይል በልጁ በኢየሱስ ላይ ገልጦ ጨርሷል።

የእግዚአብሔር የመጨረሻው ኃይል በመስቀል ላይ እንደተሸነፈ ሰው ሆኖ እርቃኑን የተሰቀለው ኢየሱስ ነው።


ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥24


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኤፌሶን 1
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
³ በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።

⁴
#ዓለም_ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ #በክርስቶስ_መረጠን።

⁵ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በዚህ ዓለም የምትወለድበት ስፍራ ባይገኝልህም ለምን እንደተወለድክ ገብቶኛል መድህኔ😭😭😭❤❤

ልትሞትልኝ በግርግም ተወለድክ የኔ ፈዋሽ😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰዎች ቢንቁአችሁ፣ ሰዎች ቦታ ባይሰጡአችሁ፣ በእነሱ ዘንድ ዋጋ አታችሁ ርካሽ ብትሆኑ ይህ ሁሉ የእናንተን ዋጋ ፈፅሞ ሊናገር አይችልም የእናንተ ዋጋ የክርስቶስ የፍቅሩ ጥልቀት ልክ ነው።

ሰዎች ስለናንተ ባላቸው አመለካከት ላይ ሳንሆን እግዚአብሔር ስለናንተ ባለው አመለካከት ላይ ፀንታችሁ ቁሙ።

እግዚአብሔር ለእናንተ መልካምና መልካም ብቻ ነው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel