binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

“በዚህ ሁሉ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።”
— ሮሜ 8፥37 (አዲሱ መ.ት)

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#ማንም_እንዳይመካ_ከስራ_አይደለም

ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

⁶-⁷ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።

⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤

⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።” ዘዳ 32:10

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።
መዝሙር 97፥11

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስን ቦታ በሌላ ነገር ስትተካ የስነልባና ትምህርት ቤት ማዕከል ነው የምትሆነው

በመንፈስ ቅዱስ የማትመራ ቤተክርስቲያን በሰማይ ዘንድ እውቅና የላትም።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በ ቢሾፍቱ ሊመጣ ያለ የ ክብር🌦🌦🌦🌦🌦🌦
እሄን መልእክት share argut
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🕧🕐🕜

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

#ከእርሱ ጋር #ተጣበቁ🔥🔥❤❤

አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር
#ተጣበቁ
— ዘዳግም 13፥4

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

1ኛ ዮሐንስ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ አብ ልጁን የዓለም አዳኝ ይሆን ዘንድ እንደላከው ዐይተናል፤ እንመሰክራለንም።

¹⁵ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምኖ በሚመሰክር ሁሉ፣ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የዘለአለም ሆይወት የተቆራኘው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ላይ ብቻ ነው።

የዘለአለምን ህይወት ከእግዚአብሔር ልጅ በስተቀር የትም አታገኟትም።

የዘለአለም ህይወት የሚኖርህ ኃይማኖት ወይም ስነምግባር ወይም ሌላ ሌላ ነገር ሲኖርህ ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶሰሰ በህይወትህ ሲኖርህ ነው።

1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

¹³ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በታሪክ ከሞተ ሰው ፍቅር የያዘውን አካል ሰምቼም አይቼም አላውቅም።

እግዚአብሔር ግን በበደላችንና በኃጢአታችን ምክኒያት ሙት የነበርነውን በክርስቶስ ኢየሱስ በዘላለማዊ ፍቅሩ አንዲሁ ወደደን
😭🙏😭

ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና።
-----ኤፌሶን 2፥5


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ትናንትና.....

በትናንትና ታሪካችሁ እትያዙ
የትናንት ስህተታችሁ አያድክማችሁ
የትናንት ህይወታችሁ ምንም ሊሆን ይችላል ነገር ግን በፍፁም ለትናንትና ማንኑታችሁ የነገውን የከበረ ማንነታችሁን አታደብዝዙት።

ትናንትናን ልቀቁት እርሱት ነገአችሁ እጅግ በጣም የተዋበና የከበረ ስለሆነ ዛሬአችሁን በመዋጀት ወደተዘጋጀላችሁ የከበረ ነገ በእምነት ተዘርጉ🔥🔥🔥🔥

“ወንድሞች ሆይ፤ እኔ ገና እንደያዝሁት አድርጌ ራሴን አልቈጥርም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ከኋላዬ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 3፥13 (አዲሱ መ.ት)


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የኢየሱስ ፍቅር እንደገና በመንፈስ ቅዱስ ልባችን ላይ ይፍሰስ🔥🔥🔥🔥

ነፍሳችን በፍቅሩ እሳት ትጋይ ትንደድ ትነደፍ🔥🔥🔥🔥🔥🔥


ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሶአልና።
— ሮሜ 5፥5 (አዲሱ መ.ት)

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ ነው🔥
እንሆ ንጉሳችን😍😍🔥🔥🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር ላንቺ መልካም ብቻ ነው🥰
እግዚአብሔር ላንተ መልካም ብቻ ነው🥰

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ጠላቴ እልል አይልብኝምና ስለዚህ እንደ ወደድኸኝ አወቅሁ።”
— መዝሙር 41፥11

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእንደገና አምላክ ነህ😍😍
ፓስተር ተከስተ ጌትነት❤️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የምስራች #በክርስቶስ_ኢየሱስ
The past
The present
The Future ኃጢአቶች ሁሉ ተወግደዋል።


የአንድ ጊዜ መስዋዕት የዘላለሙን ኃጢአት አስወግዶታል።

እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት #አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
  — ሮሜ 8፥1


ኢየሱስ ለጥያቄዎቻችን ሁሉ መልስ ነው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የመረዳት ሁሉ ባለጠግነት የእግዚአብሔርን ምስጢር ክርስቶስን ማወቅ ነው።

እግዚአብሔር አንድ ምስጢር አለው እርሱም ኢየሱስ ነው።

የመረዳታችን አቅም ባደገ ቁጥር more እየተገለጠልንና እየበራልን የሚሄደው የእግዚአብሔር ጥበብና ምስጢር የሆነው ኢየሱስ ነው።

ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም #ክርስቶስን #እንዲያውቁ እጋደላለሁ፤
  — ቆላስይስ 2፥2


ብዙዎች እግዚአብሔር ምስጢርን ገለጠልን ብለው ነገር ግን የተገለጠላቸው ምስጢር ኢየሱስ ካልሆነ ውሸት ነው ምክኒያቱም እግዚአብሔር ከኢየሱስ በቀር ሌላ ምስጢር የለውም።

ኢየሱስ ተገልጦ የማያልቅ የእግዚአብሔር ምስጢርና ጥበብ ነው የዘላለም ህይወት ማለት በራሱ ኢየሱስን ለማወቅ የተሰጠን ጊዜ ነው...

“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች
#የዘላለም_ሕይወት ናት።”
  — ዮሐንስ 17፥3

ዘላለምን በህይወት የምንኖረው እንኳን ኢየሱስን እንድናውቅ ነው።


ጎበዝ የመንፈስ ቅዱስ ተማሪ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ የእግዚአብሔርን ምስጢርና ጥበብ የሆነውን ኢየሱስን ይመለከተዋል።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በምድር ላይ ከምንም ነገር ልትነጥሉኝና ልትለዩኝ ትችላላችሁ ከወንጌል ግን ፈፅሞ አትችሉም።

ለምን ካላችሁኝ....

ወንጌል ህይወቴ ነው
ወንጌል ህልሜ ነው
ወንጌል ራዕዬ ነው
ወንጌል ቅዠቴ ነው
ወንጌል አላማዬ ነው
ወንጌል ስራዬ ነው
ወንጌል መታወቂያዬ ነው
ወንጌል ታሪኬ ነው

በቃ ወንጌል ወንጌል ወንጌል የምተነፍሰው አይሬ ነው😭😭😭

ቢናን ከወንጌል ከመለየት ይችን ምሽት ማቆም ይቀላል።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ይጠየቅ ዓሳ ስለ ውሃ
ይናገር ዛፍም ስለ አፈር
ጠይቁኝ እኔን ስለ እግዚአብሔር!!

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እንከን የማይገኝበትን እርሱን ተመልከቱ😍😍

የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤
  — ዕብራውያን 12፥2 (አዲሱ መ.ት)

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እናንተን በክፉ የሚነካ የአይኑን ብሌን እንደሚነካ ነው።

በከፍተኛ መለኮታዊ ጥበቃ ውስጥ ናችሁ🔥

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስን የምከተለው የልቤ እግር ላይ የታሰረው ፍቅሩ ስለሚጎትተኝ ነው።❤️❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

.               ምችለው
መስፍን ጉቱ - New Album
ድንቅ ዝማሬ ነው ከፍ በሉበት❤️🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እራሳችሁን በፀጋው ዙፋን ፊት ስታዋርዱ በፊታችሁ የማይዋረድ ኃይል አይኖርም።

እራሳችሁን በፀጋው ዙፋን ፊት ዘውትር ካስገዛችሁ የማይገዛላችሁ ኃይል አይኖርም።

እራሳችሁን በፀጋው ዙፋን ፊት ስታንበረክኩ የማይንበረከክላችሁ ኃይል የለም።

የገዢነት ህይወት ያለው በፀጋው ዙፋን ፊት በመገዛት ነው።

የምትገዙት በፀጋው ዙፋን ፊት ስትገዙ ነው።

የምታንበረክኩት በፀጋው ዙፋን ፊት ስትንበረከኩ ነው።

በፀጋው ዙፋን ፊት በመገዛት ለገዢነት ህይወት ተፈጥሬአለሁ።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፣ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።”
— ያዕቆብ 4፥10 (አዲሱ መ.ት)

“ስለዚህ እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤”
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥6 (አዲሱ መ.ት)

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ለወንጌል ተፈጥሬአለሁ🔥🔥
ለወንጌል ተወልጃለሁ🔥🔥

I was created for the gospel🔥🔥
I was born for the gospel🔥🔥

ገላትያ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ ነገር ግን፣ ከእናቴ ማሕፀን ጀምሮ የለየኝና በጸጋው የጠራኝ እግዚአብሔር፣
¹⁶ በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ እንድሰብክ ልጁን በእኔ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፣ ከማንም ሥጋ ለባሽ ጋር አልተማከርሁም፤

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አላውቅም ይሄ የእግዚአብሔር ቃል ለማን እንደሆነ በማለዳ መንፈሴ ላይ ስለፈሰሰ ነው❤❤❤

ኢሳይያስ 43
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
² በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።
³ እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤


በምታልፉበት መንገድ ሁሉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው❤️❤️❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእግዚአብሔር የመጨረሻ ፍቅሩ ተገልጧል
የእግዚአብሔር የመጨረሻ ጥበቡ ተገልጧል
የእግዚአብሔር የመጨረሻ ኃይሉ ተገልጧል

ኢየሱስን የማያውቅ አብን ፈፅሞ አያውቅም የእግዚአብሔር የመጨረሻ መገለጥ ኢየሱስ ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ፍቅር እንደዚህ ነው....

ፍቅር ብቁውን ወይንም ጻድቁን ሰው እወድሃለው የሚል የአንደበት ንግግር ሳይሆን ለኃጢአተኛው ሰው አንድያ የሚወደውን ልጁን እስከ ሞት አሳልፍ የሚሰጥ የእግዚአብሔር የልብ ቋንቋ ነው።

ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
  — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10


እግዚአብሔርን ጥላኝ ብትለው ሊጠላህ አይችልም ምክኒያቱም ከእግዚአብሔር ውስጥ ጥላቻን በፍጹም አታገኝም። ያለህ ነገር ሊያልቅብህ ይችላል እግዚአብሔር ግን የሚያልቅበት ፍቅር የለውም እራሱ ፍቅር ነው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰይጣን ያለኝን አይደለሁም 🙅
ሰነፎች ያሉኝን አይደለሁም🙅
ሁኔታው ያለኝን አይደለሁም🙅‍♂
አይሩ ያለኝን አይደለሁም🙅‍♂

እኔ እግዚአብሔር ያለኝን ያንኑ ነኝ ።
እግዚአብሔር ደግሞ እንዲህ ብሎኛል
            👇👇👇👇👇
📍በዘላለም ፍቅር ወድጄሃለሁ....
📍በክርስቶስ ያገኘሁ ውድ ልጄ ነህ...

📍በክርስቶ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ዓለም ሳይፈጠር በፊት ባርኬሃለሁ....

📍በኢየሱስ ክርስቶስ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት በምህረቴ ዳግም ወልጄሃለሁ....

📍የአለም ብርሃን ነህ ....
📍የምድር ጨው ነህ ...

📍የፍጥረት ናፍቆት ነህ ምክኒያቱም ልጄ ኢየሱስ ባንተ ውስጥ ስላለ...

📍የክብሬ ፀዳል በአንተ ላይ ያበራል
ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ትገልጠዋለህ ነው ያለኝ🔥🔥🔥


ያሉኝን ሳይሆን ያለኝን ነኝ✔️

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…
Subscribe to a channel