binarevivalist | Unsorted

Telegram-канал binarevivalist - Bina revivalist 🔥

5949

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2) ---------- 1፤ #በዓለ ኀምሳ #የተባለውም ቀን #በደረሰ ጊዜ፥ #ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው #አብረው ሳሉ፥ 2፤ #ድንገት #እንደሚነጥቅ ዓውሎ #ነፋስ ከሰማይ #ድምፅ መጣ፥ #ተቀምጠው #የነበሩበትንም ቤት #ሁሉ #ሞላው። 🔥🔥🔥🔥 @Binajesus

Subscribe to a channel

Bina revivalist 🔥

የልቤ የውስጤ😭😭😭😭
ከእነኔ ጋር በዚች ትንሽ ደቂቃ ጌታን እናምልክ😭😭😭😭

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የጨለማውን ስራ መፍረስና ማሸነፍ እንችል ዘንድ ሽንገላውንም መቋቋም እንችል ዘንድ መልበስ ያለብን የእግዚአብሔር እቃ ጦሮች🔥

*የእውነት ዝናር🔥🔥
*የጽድቅ ጥሩር🔥🔥
*የሰላም ወንጌል🔥🔥
*የእምነት ጋሻ🔥🔥
*የመዳን ራስ ቁር🔥🔥
*የመንፈስ ሰይፍ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል🔥🔥

በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።
— ኤፌሶን 6፥10


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

🎼አየሱሴ ግባ ከቤቴ 😭
መዝሙር ግብዣ🥰

🔥እየሱሴ ድንቁ ወዳጅ

🔥ልክፈትልክ ግባ ከቤቴ

መልካም ውሎ ይሁንላችሁ❤ 🙏

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ሰው ሆነህ በሰው ላይ ቂም መያዝ የሰይጣን ባህሪ ማርገዝ ነውና ልብህ ቂምን ሲያስብ ናቀው እንጂ አክብረህ አትያዘው።

ቂም አፍን የሚያመር ልብን የሚያነቅዝ ነፍስን የሚያዝል የዲያብሎስ መውጊያ ነው።ቂመኛ ሰዎች ደስታቸውን በተበድያለሁ የተቀሙ መራራ ህይወት የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

በእናንተ የውስጥ ሰውነት ውስጥ ከእግዚአብሔር ደስታና ሰላም ውጪ ማንንም በቂም ገመድ አስራችሁ ማኖር የለባችሁም።ወጫዊ ዓላማችሁ በውስጣዊ ዓለማችሁ በምታኖሩት አካል ይወሰናልና ውጫዊ ገጽታችሁ የተዋበ ይሆን ዘንድ ዛሬ በውስጣችሁ በቂም በቀል ገመድ ለአመታት ያሰራችኋቸውን ሰዎች በሙሉ በነፃ ፍቱና ልቀቋቸው ይህን ስታደርጉ የእግዚአብሔር አብሮነትን ታገኛላችሁ።

እግዚአብሔር በፍጹም ይቅር ባይነት ፀጋ ይደግፍችሁ።በኢየሱስ ስም አሜን።

✍የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist .

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእግዚአብሔር ፊት ከተንበረከክ በማንኛውም ችግር ፊት ትቆማለህ

በእግዚአብሔር ፊት ከተንበረከክ በማንኛውም ሰው ፊት መቆም ትችላለህ።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ህይወታችንን ለዘለአለም የለወጠ የእግዚአብሔር ጥበብ😭😭😭

በብሉይ ወይም በአሮጌው ኪዳን ዘመን ሰዎች ከእግዚአብሔር ለመታረቅና ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ በግ ይዘው ይሄዱ ነበር አሁን ግን በአዲሱ ኪዳን እግዚአብሔር እራሱ የራሱን በግ ይዞ መጥቶ በጉን መስዋእት በማድረግ ደሙን  በማፍሰስ እንታረቅ ብሏል ይህ በግ ኢየሱስ ከርስቶስ ነው።

በበጉ ደም በኩል ወደ አብ የመግባትና ከአብ ጋር ህብረት የማድረግ ብቃትን አግኝተናል።

የበጉ ደም ወደ አብ ክብር የምንገባበትን Access ሰጥቶናል።

የበጉ ደም ወደ አብ የምንገባበት ቀይ ምንጣፍ ሆኖልናል።

የበጉ ደም መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ለዘለአለም እንዲኖር ለመንፈስ ቅዱስ ምቹ መኖሪያ አድርጎናል።

የበጉ ደም ከኢየሱስ ጋር የጠለቀ የነፍስ ትስስር እንዲኖረን አድርጎናል።

“በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።”
  — ዮሐንስ 1፥29


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የዘር ክብር ያለው በሞቱ ውስጥ ነው።

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።”
— ዮሐንስ 12፥24

አንተ ሞኝ፥ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥36

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔር ፍቅር ብቻ ነው😭😭

ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።


²⁴ የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን።

²⁵ እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤

²⁶ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በኢየሱስ ትንሳኤ የተገኙ በረከቶች

በኢየሱስ መስቀል አሮጌው ሰውና ለእግዚአብሔር የማይታዘዘው አመጸኛው የሕይወት ስርዓት ያለፈ እና ፍጻሜ ያገኘ ሲሆን፣
በክርስቶስ ትንሳኤ ፦የእግዚአብሔርን ሕይወት የተካፈለው አዲሱ ፍጥረት ከሕይወት ስርዓቱ ጋር ወደ ሕልውና የመጣበት ነው።

ኢየሱስ ለማርታ ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ ብሏል ዮሐ 11:25
ስለዚህ ትንሣኤ አመት ጠብቀን የምናከብረው ቀን ሳይሆን ማንነት ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

እንዲሁም በ 2 ቆሮንቶስ 5፡17
ስለዚህ ማንም
#በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

1) የክርስቶስ
#ትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መጀመሪያ (ጅማሬ) ነው። 2ቆሮ 5፡17.

2) የክርስቶስ
#ትንሳኤ ከክርስቶስ ጋር ህይወት አግኝተን የአካል ክፍሎቹ የሆንበት ነው።ሮሜ 7፡1-4, አፌ 2፡4-, ኤፌ 5፡30 KJV.

3) የክርስቶስ
#ትንሳኤ ፅድቃችን የተረጋገጠበት እና በእግዚአብሔር ፊት ሃጢአት አልባ የሆንበት ነው። ሮሜ 4:24-25,2ቆሮ 5፡21

4) የክርስቶስ
#ትንሳኤ የእምነታችን እውነተኛነት የተረጋገጠበት ነው። 1ቆሮ 15:

5) የክርስቶስ ትንሳኤ ፦
ክርስቶስን ሲያስነሳ እኛንም አብሮ በማስነሳት የእግዚአብሔር የብርታቱ ሀይል የተገለጠበት ነው።ኤፌ 1:14

6) የክርስቶስ
#ትንሳኤ በመንፈስ እና በስጋ የተባረክንበት ነው። ገላ 3፡13 , ኤፌ 1፡4

7) የክርስቶስ
#ትንሳኤ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት ብቁ የሆንበት ነው። 1 ጴጥሮስ 1፡3-5፤

8) የክርስቶስ
#ትንሳኤ በጠላት ሀይል ሁሉ ላይ ባለስልጣን ለመሆን ስልጣን የተቀበልንበት ነው። ማቴ 28፡18-20,ሉቃ 10፡1

9) የክርስቶስ
#ትንሳኤ አባት እኛን የተቀበለበት እና አለቅህም ከቶም አልተውህም ያለበት ነው። ዕብ 13፡5

10) የክርስቶስ
#ትንሳኤ አባ አባት ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ የተቀበልንበት ነው። ሮሜ 8፡14-17
ገላ 4፡5-

11) የክርስቶስ
#ትንሳኤ አማኝ ሁሉ አዲስ ፍጥረት እና ሰማያዊ ዜጋ የሆንበት ነው። 2ቆሮ 5:17,ራዕ 5፡10-, ፊሊ 3፡20

ኤፌሶን 1 (Ephesians)
20-21፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤

1 ጴጥሮስ 1 (1 Peter)
3-5፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በሞቱ የኃጢአት እዳችን ሲከፈል በትንሳኤው ደግሞ የእግዚአብሔር ፅድቅ ሆነናል።

የትንሳኤው ልጆች ነን።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።”
— ሐዋርያት 2፥24

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እመነኝ ኢየሱስን የተከተልከው ለዳቦ እና ለእንጀራ ለቁሳቁስ ከሆነ የሆነ ፌርማታ ላይ እስታክ አድርገህ ትቆማለህ ትንሸራተታለህ።

ነገርግን ኢየሱስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደህነ በርቶልህ ህይወትን ፈልገህ ከተከተልከው ማንም አያስቆምህም ሞት እንኳን ከኢየሱስ አይለይህም።

ኧረረ ኢየሱስ እራሱ የመለኮት ሙላት ነው እርሱን ከያዝነው የሚጎድለን አንዳች ነገር አይኖርም።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስ የፈራውና የተጨነቀው መገረፉን፣ መሰቃየቱን፣ በመስቀል ላይ መሰቀሉን፣ መሞቱን ሳይሆን በእርሱና በአብ መካከል ያለው ህብረት በመቋረጡ በአብ መተውን ነው ምክኒያቱም አብ ከኃጢአት ጋር ምንም ህብረት የለውም።

አብ መስቀል ላይ የተሰቀለውን ሲመለከት ኢየሱስን ሳይሆን ኋጢአትን ነው ለዛም ነው እግዚአብሔር አብ ኢየሱስን በመስቀል ላይ እንደዛ በሰዎች እርግማንና ኃጢአት ሲሰቃይ አይቶ ለቅጣት የተወው።

“በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥
#ለምን_ተውኸኝ? ማለት ነው።”
  — ማርቆስ 15፥34


ኢየሱስ ኃጢአትችንን ወስዶ በምድረበዳ የተንከራተተልን ፍየል ነው።

ዘሌዋውያን 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዝዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል።

²² ፍየሉም ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሀ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል።


እኛን ከኃጢአት በሽታ ሊያድነን በኃጢአት ምክኒያት ወደ ህይወታችን የገባውን እርግማን ወስዶ በእግዚአብሔር የተተው እኛን ወደ ብርሃን ህይወት ሊያመጣ ነው።

ኢየሱስ ምንም በእግዚአብሔር ቢተውም ከብዙ ድካም ቡኋላ ዘሩን አይቷል። የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ተከናውኗል።


እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
  — ኢሳይያስ 53፥10



@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ትንሳኤ አመታዊ በአል ሳይሆን ኃጢአትን፣ ሞትን፣ እርግማንን፣ ሲኦልን፣ አሮጌውን ሰው ያሸነፈ እያሸነፈም የሚገለጥ መለኮታዊ የህይወት ስርአት ነው።

ትንሳኤ እራሱ ኢየሱስ ነው።

ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤
— ዮሐንስ 11፥25


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

እግዚአብሔርን ጠብቄው😍🥰

የተባረኩበት መዝሙር ነው ተባረኩበት😍😍😍

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ቆይ ግን ወዳጆቼ ሆይ ልጠይቃችሁ😭😭😭

የት ሃገር ነው ቁስል መድሃኒት የሆነው????

የት ሃገር ነው ቁስል ፍውስ የሆነው???

ቁስል እኮ ለራሱ መድሃኒት ያስፈልገዋል።

ቁስል እኮ ለራሱ ፈውስ ያስፈልገዋል።

የኢየሱስ የመገረፉ ቁስል ግን እራሱ ቁስሉ መድሃኒትና ፈውስ ነው😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

እግዚአብሔር መድሃኒትንና ፈውስን የሰወረው በኢየሱስ የመገረፍ ቁስል ውስጥ ነው😭😭😭😭😭😭😭

ሰው ያንን የመገረፍ ቁስል ሲመለአት ከሃጢአት በሽታ ፈፅሞ ይፈወሳል😭😭😭😭😭😭

አያችሁ እግዚአብሔር የዓለምን ጥበብ እንደሞኝነት የቆጠረው ለዚህ ነው።

የኢየሱስ የመገረፉ ቁስል ከሃጢአት እንደሚፈውስ ለዓለም እንደሞኝነት ነው።

እግዚአብሔር ግን የሃጢአት መድሃኒትን ያስቀመጠው በዛ በተጎሳቆለው በዛ በቆሰለው ለማየት እንኳን በሚዘገንነው በኢየሱስ ቁስል ውስጥ ነው።

እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥
#በእርሱም #ቍስል እኛ #ተፈወስን
  — ኢሳይያስ 53፥5

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤
#በመገረፉ_ቁስል_ተፈወሳችሁ
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእግዚአብሔር ኃይል ዘውትር የምንሞላው ተሞልተን ተሞልተን እራሳችንን ችለን ለመቆም ሳይሆን የበለጠ የእሱ ጥገኛ ለመሆን ነው።

ሁሌም የመንፈስ ቅዱስ ጥገኛ ነኝ❤️

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አንተን እናፍቅሃለው አንተን አንተን አንተን ጌታ😭😭😭😭😭
አንተን አወድሃለው አንተን አንተን አንተን ውዴ😭😭😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በህይወቴ ሁሉ በቃ ይህንን ተረድቻለሁ።😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥

³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል
#ተረድቼአለሁ።😭😭😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በአባታችን በእግዚአብሔር ፊት ሙሉ በሙሉ በልጅነት መንፈስ መቅረብ ችለናል በፊቱ የመቆም ድፍረትና ብቃትን አጊንተናል

በዚህ ፈቃድ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ አማካይነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቀረበው መሥዋዕት ተቀድሰናል።
— ዕብራውያን 10፥10 (አዲሱ መ.ት)


ዕብራውያን 10 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በኢየሱስ ደም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ድፍረት አግኝተናል፤

²⁰ ይኸውም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል በከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የእግዚአብሔር ጥገኛ ነኝ😭😭😭

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።”
— ሮሜ 8፥11

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በሞቱ የኃጢአቴን ዋጋ እንደከፈለ በትንሳኤው ደግሞ በአብ ፊት ፃድቅ እንዳረገኝ በእምነት እቆጥራለሁ።

የኢየሱስ ትንሳኤ የእኔ ትንሳኤ እንደሆነ በእምነት እቆጥራለሁ።

ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።
— ሮሜ 4፥24-25

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤
— ቆላስይስ 2፥14

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ዝም ብለህ ቁጠር ወዳጄ...

ኢየሱስ ኃጢአት የሆነው አንተ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድትሆን ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ስለአንተ ኃጢአት እንደሆነ አንተ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንደሆንክ
#በእምነት_ቁጠር

የፋሲካ ምስጢር ይሄ ነው❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ፋሲካችን ከርስቶስ የእግዚአብሔር በግ ታርዶልናል❤

ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?

² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።

³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።

⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።

⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።

¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።

¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።

¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

አብ የፈዘዘው ኢየሱስ ላይ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ያደመቀው ኢየሱስን ነው።

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

የሁለቱ ኪዳን በጎች❤️

የብሉይ ኪዳኑ በግ ኃጢአትን ይሸፍናል እንጂ አያስወግድም።

የአዲስ ኪዳኑ በግ ግን ኃጢአትን ያስወገደ ብቻ ሳይሆን ኃጢአትን የደመሰሰ የገደለ በግ ነው።

የብሉይ ኪዳኑ በግ ከሰው ነው
የአዲስ ኪዳኑ በግ ደግሞ ከእግዚአብሔር ነው።

የብሉይ ኪዳኑ በግ የአንድን ወይ የሁለትን ሰው ኃጢአት ብቻ ነው መክደን የሚችለው።

የኢዲስ ኪዳኑ በግ ግን የአለምን ሁሉ ኃጢአት ነው ያስወገደው።

የብሉይ ኪዳኑ በግ የሰው አቅም የሚታይበት በግ ነው

የአዲሱ ኪዳን በግ ግን የእግዚአብሔር አቅም የታየበት በግ ነው።

የብሉይ ኪዳኑ በግ ደም Expiredቱ ለአንድ አመት ነው።

የአዲስ ኪዱኑ በግ ግን ሁሌም ትኩስ ነው ሁሌም fresh ነው።


ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
#የእግዚአብሔር_በግ


³⁶ ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ
#የእግዚአብሔር_በግ አለ።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist

Читать полностью…

Bina revivalist 🔥

ኢየሱስን የገደሉት የሮማውያን ወታደሮች ሳይሆኑ ለዘመናት ከአብ የለየኝ ኃጢአት ነው😭😭😭😭😭

Читать полностью…
Subscribe to a channel